KUE Community / አዲስ ነገር መረጃ /
رفتن به کانال در Telegram
4 593
مشترکین
-124 ساعت
+197 روز
+15030 روز
آرشیو پست ها
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ለሁት ቀናት የተሰጠው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ
**************
(ኮትዩ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም) ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የሕይወት ክህሎት ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቀት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ዲን ዶ/ር ኃይሉ መገርሳ እንደተናገሩት፣ ስልጠናው የተዘጋጀው አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከቤተሰብ ተለይተው ለመጀመሪያ ጊዜ የዩኒቨርሲቲን ህይወት ሲቀላቀሉ የሚገጥሟቸውን አካደሚካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች በምን አይነት ክሂሎት ሊወጡ እንደሚችሉ ለማስገንዘብ በመሆኑ በታቀደለት መልኩ ለተማሪዎቹ ጠቃሚ መረጃዎችን በመስጠት በስኬት ተጠናቋል፡፡
እንደ ዶ/ር ኃይሉ ገለፃ፣ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አገልግሎትን ለማግኘት የተቋሙን መዋቅራዊ አደረጃጀት በትክክል መረዳት፣ የት ምን እንዳለ በማወቅ አስፈላጊውን አገልግሎት ከተገቢው ቦታ ማግኘት፣ ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች የሚያስፈልጉትን የመማር ማስተማር፣ የምግብ፣ የመኝታ፣ የህክምና እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ሁሉ ተማሪዎችም በበኩላቸው አብሮ የመኖር፣ የመቻቻል፣ የመተጋገዝና የመረዳዳት መልካም ግንኙነት መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናውን በማዘጋጀትና በማስተባበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ምክትል ዲን ለወ/ሮ ምኞት ጌታቸው እና ለተቀሩት አሰልጣኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተማሪዎቹ በሁለት ቀናት ቆይታቸውም የህይወት ክሂሎት፣ የስነተዋልዶ ጤና፣ የአካዳሚክ እና የሬጅስትራር አገልግሎት፣ የዩኒቨርሲቲውን ህግና ደንብ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የዲሲፕሊን መመሪያ እንዲሁም በትምህርታቸው ውጤታማ ሊሆኑባቸው የሚችሉባቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ባለሙያዎች ገለጻ የተደርጎላቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education
ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች በሙሉ!
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ (የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ) ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ማለትም በሰርተፊኬት፣ በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's)፣ በሁለተኛ ዲግሪ (Master's) እና በዶክተሬት ዲግሪ (PhD) የተመረቃችሁ የቀድሞ ተማሪዎቻችን የዩኒቨርሲቲውን የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር(Alumni Association) የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን እንድትመዘገቡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
የምዝገባ ሊንክ፦ https://forms.cloud.microsoft/r/bmmpzyWkhz
ይህ መልዕክት ለሌሎችም የቀድሞ ተማሪዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩን!
“Once Kotebe, always Kotebe” አንለያይም!
አልሙናይ ግንኙነት ፅ/ቤት
forms.cloud.microsoft (https://forms.cloud.microsoft/r/bmmpzyWkhz)
Please fill out this form
ዩኒቨርሲቲው በአማራጭ የመምህርነት ሙያ መርሐግብር የሰለጠኑ መምህራንን አስመረቀ
****************
(ኮትዩ ጥቅምት17 ቀን 2019 ዓ.ም) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በአማራጭ የመምህርነት ሙያ ሥልጠና የሰለጠኑ 693 ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በዕጩ መምህራኑ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትና ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ ወ/ሮ አሰግድ መሬሳ፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ይህ የአማራጭ የመምህርነት ሙያ የስልጠና መርሐግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛውን ቁጥር በመቀበል፣ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግና ስልጠናውን ስኬታማ በሆነ መልኩ በማጠናቀቅ የመጀመሪው ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተመራቂዎችም መምህርነት ትውልድ የሚቀረፅበት ሙያ በመሆኑ በታማኝነት፣ በሥነ-ምግባር እና በቁርጠኝነት ሀገራችሁን እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አለባቸው ኬሚሶ በበኩላቸው፣ በዚህ ለየት ባለ አዲስ ሥርዓተ ትምህርት በ24 የትምህርት ዘርፎች ሰልጥነው፣ የሚፈለገውን የዩኒቨርሲቲያችንን የመመረቂያ መስፈርት በብቃት አሟልተው በዛሬው ዕለት የተመረቁት የ2019 ዓ.ም የአማራጭ የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ዕጩ ምሩቃን 693 ሲሆኑ፣ ከተጠቀሰው ቁጥርም 578 ያህሉ ወንዶች፣ 115 ያህሉ ደግሞ ሴት ተመራቂዎች በመሆናቸው በእጅጉ ያኮራናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት በማዕረግ ለተመረቁ ወንድ እና ሴት ዕጩ ምሩቃን ሰርተፍኬት እና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ ለአንዲት ሴት የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂም በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በኩል የተዘጋጀ ልዩ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሴኔት አባላት፣ መምህራን እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገኝተዋል፡፡
በማለት በነገው ዕለት ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education
ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook
የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሴኔት አባላት የ2019 ዓ.ም የአማራጭ የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ላይ የነበሩ የ693 ተማሪዎችን ምረቃ አጸደቁ
****************
(ኮትዩ ጥቅምት16 ቀን 2019 ዓ.ም) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሴኔት አባላት ከሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የቀረበላቸውን የ2019 ዓ.ም የአማራጭ የመምህርነት ሙያ ሥልጠና ተመራቂዎችን ውጤት በመመርመር እና በመቀበል የተማሪዎቹን ምረቃ አጽድቀዋል፡፡ የምረቃ ሥነ-ስርዓታቸው በነገው ዕለት ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
#Kotebe_University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education
ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/@kueducation
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook
Kotebe University of Education and the Ethiopian World Taekwondo Federation Sign MoU to Establish a Taekwondo Center of Excellence
****************
(K.U.E, October 23, 2026) A Memorandum of Understanding (MoU) has been signed between Kotebe University of Education (KUE) and the Ethiopian World Taekwondo Federation (EWTF) to collaborate on joint research, capacity-building training, and the establishment of a Taekwondo Center of Excellence.
The main objective of the MoU is to establish a Taekwondo Center of Excellence at Kotebe University of Education. The Center will serve as a regional hub for Addis Ababa, the capital city, and neighbouring cities. Furthermore, the partnership aims to advance the sport to a higher professional level through scientific training, research, and the development of elite athletes.
The MoU was signed by Dr. Tewodros Mulugeta, RCE Vice President of KUE, representing Kotebe Education University, and Ato Dawit Asfaw, President of the Ethiopian World Taekwondo Federation, representing the Federation.
Representing Kotebe University of Education, Dr. Melkamu Afeta, Director of University–Industry Linkage and Technology Transfer; Dr. Tilahun Bereded, Dean of Sports, Health and Wellbeing Education; and Dr. Wegene Walthengus, a university senior Sport Science academic staff, attended the signing ceremony. Representing the Ethiopian World Taekwondo Federation, Master Abdulkeder Mohammed, Head of the Technical Committee; Master Motuma Getachew, Secretary-General; and Mrs. Senaite Beza, Technical Expert, were also present at the signing ceremony.
-Public and International Relations Executive Office
#Kotebe_University_of Education-committed_to_excellence_in_Education
For more information, follow our official pages:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
#የአመራር_ብቃት_ (#Leadership_Competencies_)
የአመራር ብቃት (#Leadership_Competencies_)፦ ስኬታማ መሪ ለመሆን ማወቅ ያለብዎት ወሳኝ ክህሎቶች
📌 ዕውቀት ለስኬት
📌ክህሎት ለእድገት
📌 አመራር ለውጤት
🎯#መሪ_መሆን_ማለት_ምንድን_ነው?
✔ እውነተኛ አመራር ማለት የሰዎችን ሥራ መቆጣጠር ወይም ትዕዛዝ መስጠት ብቻ አይደለም። አመራር ማለት ራስን በትክክል መምራት፣ ሰዎችን ማነሳሳት፣ በችግር ጊዜ ትክክለኛ ውሳኔ መስጠት፣ ጠንካራ ቡድን መገንባት እና የጋራ ራዕይን ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር ነው።
✔ ታላቅ መሪ ማለት ሁሉንም ነገር በራሱ የሚያደርግ ሰው ሳይሆን፣ ሌሎች ሰዎች በብቃት እንዲሠሩ፣ እንዲያድጉ እና ውጤት እንዲያመጡ የሚያስችል ሰው ነው። በዛሬው ዓለም ውስጥ የአመራር ብቃት በቢዝነስ፣ በባንክ፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሥራ ፈጠራ እና በግል ሕይወት ስኬት ውስጥ ወሳኝ ሚና አለው።
✔ በምስሉ ላይ የተቀረቡትን ሐሳቦች በመነሳት፣ ስኬታማ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ሦስት ዋና ዋና የብቃት ዘርፎችን እና የቡድን ግንባታን በዝርዝር ስንመልከት።
1 #ራስን_ማሳደግ_(#Developing_Yourself_)
✔ ራስን መምራት የሌሎችን ሰዎች በብቃት ለመምራት መሠረት ነው። አንድ ሰው ሌሎችን እንዲመራ ከመጠበቁ በፊት ራሱን፣ ስሜቱን፣ ጊዜውን፣ አመለካከቱን እና የባለሙያነት እድገቱን መቆጣጠር መማር አለበት።
#የመማር_ቅልጥፍና_ (#Learning_Agility_)፦ ከአዳዲስ ሁኔታዎች፣ ከስህተቶች፣ ከልምዶች እና ከሌሎች ሰዎች በፍጥነት በመማር የተማሩትን ወደ ተግባር መቀየር።
#የዘርፉ ሙያዊ እውቀት (Industry Expertise)፦ መሪው በሚሠራበት ዘርፍ ያሉ ደንቦችን፣ ሂደቶችን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ የደንበኞችን ፍላጎት እና የገበያ ለውጦችን መረዳት።
#ራስን_መቆጣጠር_ (#Managing_Yourself_)፦ የጊዜ፣ የስሜት፣ የጉልበት፣ የቅድሚያ ሥራዎች እና የግል ሃላፊነት አስተዳደር።
#ድፍረት (#Courage_)፦ ፍርሃት ቢኖርም በእውቀትና በመርህ መመራት እንዲሁም የማይወደዱ ውሳኔዎችንና አስቸጋሪ ውይይቶችን በድፍረት ማካሄድ።
የተቋም ዜግነት ባህሪ (#Organizational_Citizenship_Behavior_)፦ ከመደበኛ የሥራ ግዴታ በላይ ለቡድኑና ለተቋሙ ስኬት በፈቃደኝነት አስተዋጽኦ ማድረግ።
2 #ሌሎችን_መምራት_ (#Leading_Others_):-
✔ የመሪ ትልቁ ሀብት ሰዎች ናቸው። የሰዎችን አቅም የሚያሳድግ መሪ የድርጅቱን የወደፊት አቅም ይገነባል።
የግንኙነት ክህሎት (Interpersonal Skills)፦ በትኩረት ማዳመጥ፣ ሐሳብን በግልጽ ቋንቋ ማቅረብ፣ ተገቢ ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ገንቢ ግብረመልስ መስጠት።
#ስሜታዊ_አስተዋይነት_ (#Emotional_Intelligence_)፦ የራስንና የሌሎችን ስሜት መለየት፣ መረዳት እና በተገቢው መንገድ መቆጣጠር።
#ማሰልጠንና_እምነት_መገንባት
(#Coaching_&_Trust_)
ግልጽ የሥራ ዒላማዎችን ማስቀመጥ፣ ሠራተኞችን ማብቃት እና ቃልን በተግባር በማረጋገጥ እምነትን መጠበቅ።
#ሁሉን_አሳታፊ_አመራር_ (#Inclusiveness_)፦ ለሁሉም ሰው አክብሮት መስጠት፣ የተለያዩ ሐሳቦችን መቀበል እና ተገቢ የተሳትፎ ዕድል መፍጠር።
#የሰው_ኃይል_አስተዳደር (#People_Management_)፦ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ማስቀመጥ፣ ዒላማ ማውጣት እና አፈጻጸምን መገምገም።
3 #ማሰብና_ውሳኔ_መስጠት (#Thinking_&_Deciding_)
✔ መሪነት የሚፈተነው ሁሉም ነገር በቀላሉ ሲሄድ ሳይሆን፣ ችግሮች ሲፈጠሩ በሚሰጠው ውሳኔ ነው።
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ዩኒቨርሲቲው የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎችን ተቀበለ
** ** ****
(ኮ.ት.ዩ፣ ጥቅምት 5 ቀን 2019ዓ.ም) - ተማሪዎቹ ወደ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡበት ወቅት ከበር ጀምሮ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ በአቀባበል ሥነስርዓቱም ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት፣ ምክትል ፕሬዘዳንቶች፣ የተማሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ዲኖች፣ የተማሪዎች ህብረትና ከየክፍሉ የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ በአቀባበል ሥነስርዓቱ ላይ ለተማሪዎቹና ለቤተሰቦቻቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ፣ ተማሪዎች ዛሬ የሚጀምሩት አዲስ የህይወት ምዕራፍ ከፍተኛ ጥንቃቄና ኃላፊነት የሚጠይቅ፣ ከቀድሞው በላቀ ሁኔታም የሚከናወን የመማር ማስተማር ሒደት እንደሆነ በመጥቀስ፣ በግቢ ወስጥ በሚኖራቸው ቆይታቸውም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ሆነ እርስ በርስ ባላቸው ማህበራዊ መስተጋብር በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በወንድማማችነት ስሜት በመቻቻል፣ በመከባበርና በመረዳዳት ቆይታቸውን ጤናማ፣ አስደሳችና ስኬታማ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡
የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ኬሚሶ፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት፣ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን በተሟላ ሁኔታ ተቀብሎ ለማስተማር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን ገልፀው፣ ከምዝገባ እስከ ምረቃ ባሉ ክንውኖች ተማሪዎች የራሳቸውን ኃላፊነት የሚወጡበትና ከቤተሰብ ውጪ አዲስ የህይወት ዘይቤ የሚለማመዱበት፣ በዩኒቨርሲቲ ህግና መመሪያ የሚተዳደሩበት አዲስ የአካዳሚክ ማእከል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎቹ ምዝገባ ያካሄዱ ሲሆን፣ ወላጆች ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ቅፅር ግቢ ውስጥ የተገነቡ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ታውቋል፡፡