cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Hanif (Abu Reslan)

የዚህ channal አላማው የሰለፎችን መንገድ መጠቆም(ማመላከት) አላማችንም ግዴታችንም ነው። በቻናሉ ላይ ኢንሻ አሏህ ጥርት ያሉ የሱና መሻይኾች ኡስታዞችና የዱአቶችን ፡ቂርዐቶች፡ ሙሃደራዎች ይለቀቅበታል በቻናሉ በሚለቀቁት ማንኛውም ነገሮች ስህተት ካያችሁ አስተያየት ካላችሁ ከታችባለው ሊንክ አሰተያየት ይስጡን፡፡ @nsiiha

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
255
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

قال أبو حازم – رحمه الله:-  "لاَ تكون عَالمًا حتَّى تكُونَ فيِكَ ثلاث خِصالٍ: لاَ تَبغِي عَلىَ مَنْ فوقكَ ، وَلاَ تحقرْ مَنْ دُونَكَ ، وَلاَ تأخذْ عَلىَ عِلْمِكَ دُنْيَا"  شعب الإيمان،  للبيهقي : 2/288አቡ ሓዚም የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል፦ "ሶስት ነገሮች ባንተ ላይ እስኪኖር ዐሊም አትሆንም። እነርሱም፦ "ከበላይህ አትፈልግ, የበታችህን አታሳንስ, በእውቀትህ የዱንያ ጥቅም አትውሰድ።" https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🌹 ለኡስታዝ ዐብዱል-ቃድር ቢን ሐሰን እና ለሙኒራ ቢንት ሻኪር:- ባረከላሁ ለኩማ ወባሪክ አለይኩማ ወጀማዓ በይነኩማ ፊል ኸይር ! ኡስታዛችን አቡ አብዱራህማን መልካሙን ሁሉ እመኝልሃለው መልካም ትዳር ይሁንላቹህ ። ✍ አቡ ያሲር ዩሱፍ ሙዘይን! https://t.me/YusufAsselafy
نمایش همه...
🎤 Ibn Muzayan ~ ኢብን ሙዘይን! ሁለንተናዊ ከፍታ የሚገኘው በቁርዓንና ሐዲስ ብቻ ነው።

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ ደዕዋ ሰለፊያ ማሰራጫ ይሆናል ኢንሻ አላህ!! አላህ መልካም የሻለትን~ ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል ።

https://t.me/YusufAsselafy

#አትንኩት ያን ጀግና!      የውሻ ጩኽት፣ ግመል አያስቆምም፣ ነጋዴው ይጓዛል፣ ይጮኻል ውሻውም፣ አትንኩት ያን ጀግና፣ ጦራችሁ አይርዘም፣ እንደው ለራሳችሁ፣ አስቡሉት በጣም፣ እሱ አይሰማችሁም፣ አፋችሁ አይድከም!! ~~~~ - - - - - - - - - - - - - - - አትንኩት ያን ጀግና፣ የለተሞውን ፈርጥ፣ ለባጢል የማይሰንፍ፣ የማይርመጠመጥ! ቅኔ ቆሌ አታብዙ፣ አተብትቡ ፈሊጥ! ~~~~ - - - - - - - - - - - - - - - የተውሒድ የሱና፣ ሥር ተከል መምህር፣ ሺርክና ቢድዓን፣ ይነቅለዋል ከሥር! የሱናው አርበኛ፣ የሚጠቅም ሀገር፣ በሄደበት ሁሉ፣ ዒልምየን መናገር፣ ወትሮም ልማዱ ነው፣ በሂፍዝ መዘርዘር፣ አላህ ጀግና አፍርቷል፣ ለተሞ ሰማይ ሥር፣ አላህ ከአይን ያውጣው፣ ከመጥፎ ከችግር፣ ከክፉው በሽታ፣ አቋም ከመቀየር! ~~ - - - - - - - - - - - - - - - ህዝቡ ሚወደውን፣ የዳዕዋ ርዕስ፣ እየመራረጡ፣ በዛቺው መልፈስፈስ፣ ሸይኻችን አያውቁም፣ መሽሞንሞን መላላስ፣ በወኔ ጀግንነት፣ ዲንን ለሰው ማድረስ፣ የተካኑ ናቸው፣ አጉል ልምድ በማፍረስ! ~~ - - - - - - - - - - - - - - - የወቃሽ ወቀሳ፣ ይዩሉንታ አይዘውም፣ እውነት አይቶ ማለፍ፣ ከባጢል ጋር መቆም፣ እውነት ሲመጣለት፣ ኩራት ይዞት መጥመም፣ ለጥፋት መወገን፣ ነካክቶት አያውቅም! ( ተ መ ል ሻ ለ ሁ! ሸይኽ አብዱል ሓሚድ) ~~ - - - - - - - - - - - - - - - ተው እናንተ ሰዎች፣ ምነው ሥራ አጣችሁ፣ መንሸራተት ህመም፣ ቫይረስ ቢለክፋችሁ፣ ለባጢል መርመጥመጥ፣ ቢጠናወታችሁ፣ ከሱና ላይ መቆም፣ ፅናት ቢያቅታችሁ፣ ታዲያ ምን ነካችሁ፣ በዛሳ ሴራችሁ፣ ዚክር እስኪመስል፣ እያላዘናችሁ በቆላ በደጋ፣ ለተሞ እያላችሁ፣ ለአፋችሁ በዛና፣ አነስ ለአይናችሁ! ~~ - - - - - - - - - - - - - - - በተውሒድ በመንሀጅ፣ በሱና እንዲያብቡ፣ ለትልቅ አላማ ሲጠሩ፣ በአግባቡ፣ ለዘላለም ህይወት፣ ጀነት እንዲገቡ፣ ትንሽ እያሰቡ፣ በአጭር በጠባቡ፣ -እነ ሀቁል አውከድ፣ የተሞሉ ተውሒድ፣ -እነ ለተምያ፣ ታትመው ሲቀርቡ፣ በእልህ ምቀኝነት፣ ውይ ተንገበገቡ፣ እስከ-ዚህ ድረስ ነው፣ የትንሽ ሰው ግቡ፣ ለትልቅ ሲመኙት፣ ያስባል በቅርቡ! ~~ - - - - - - - - - - - - - - - አላህ ይጠብቀዎት፣ ታላቁ ሸይኻችን፣ ሁል ጊዜ እሰማለሁ፣ ሲያሙ ሥመ'ዎትን፣ የባጢልን ባለቤቶች፣ አይወዱም እርሰዎን፣ እድሜዎትን ያቆይ፣ ይምራቸው እነሱን! ✍ አብዱረህማን ዑመር የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/Abdurhman_oumer/4497
نمایش همه...
" አብዱረህማን ዑመር"

አትንኩት ያን ጀግና፣ የለተሞውን ፈርጥ፣ ለባጢል የማይሰንፍ፣ የማይርመጠመጥ! ቅኔ ቆሌ አታብዙ፣ አተብትቡ ፈሊጥ! ------------------ ለተሞ ሰማይ ሥር አላህ የለገሰንን ታላቅ ሸይኽ አስመልክቶ የቀረበ ግጥም! ሙሉውን ለማግኘት 👇

https://t.me/Abdurhman_oumer/4497

ዳር አስ – ሱናህ የእውቀት ማእከል የሰለፍዮች መድረሳ አለም ባንክ ላይ : – 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 ይህ ብስራት ለሰለፍዮች ትልቅ ድል የሚያበስር ሲሆን ለሙመዪዓና ኢኽዋን ትልቅ ራስ ምታት ነው ። አላህ እንዲህ አይነት የሰለፍዮች ተቋሞችን ያብዛልን ። በዚህ ትልቅ ስራ ላይ የተሳተፉ ወንድሞችን ስራቸውን በመልካም ስራ መዝገባቸው ላይ ይመዝግብላቸው ። እኛንም እነርሱንም አላህ በሱና ላይ ያፅናን ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

🟢የሚዲያ ተጠቃሚዎች ሆይ: በተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች (ሚዲያዎች) ላይ የምትንቀሳቀሱና ዲናዊ ትምህርቶችን የምታሰራጩ ሁሉ የሚከተሉትን ነጥቦች ተጠንቀቁ⤵️ 1⃣ ያለ እውቀት መዳፈር አላህ በጥብቅ የከለከለው ጉዳይ ነው: قال الله سبحانه 《وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا》  الإسراء:(36) "እውቀት በሌለህ በሆነ ነገር አትከተል ።መስሚያ ፣ መመልከቻም ፣ ልብም በእነዚህ ሁሉ (ተግባር) ባለቤታቸው እኮ ተጠያቂ ነው።" ከዚህ ውስጥ ያላዳመጡትን ድምፅ ፣ ያላነበቡትን ፅሁፍ፣ ያልተረዱቱና ያለመኑበትን መልእክት ማስተላለፍ ይገባል። ጉዳዩ የስግብግቦች የጅምላ ንግድ ሳይሆን ትልቁን የነቢያትን ውረስ የማስተላለፍ ሀላፊነት ነው። 2⃣ ተከታዮችን አለማገናዘብ መልእክቱ በቀጥታ የሚደርሳቸውን ተከታታዮች ከግምት ያለስገባ ስርጭት አደጋው ብዙ ነው። ከመምራቱ ይልቅ ማጥመሙ ሊያዘነብል ይችላልና። ከጥቅሙም ጉዳቱ። በተቻለ መጠን በአስተላለፊው ደረጃ ሳሆን ተከታታዮችን ያገናዘበ ጉዳይ ነው መተላለፍ ያለበት። ዲኑ የምር ጉዳይ ነውና ዛዛታና የሀሰት ወሬ ይፃረረዋል። ከሚከተተሉን ውስጥ ብዙ የተከበሩ ሰዎች እንዳሉም እናተውል። አላህ እንዳዘዘው: ﴿…وَقُولُوا لِلنَّاسِ حُسْنًا…﴾[البقرة: ٨٣] 3⃣ ቀደም ቀደም ማለት አዲስ አጀንዳ ከማሰራጨት በፊት በጉዳዩ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸው ሰዎች ሊናገሩ ወይም ሊፅፉ እየቻሉ የደፋሮች ቀዳም ቀደም ማለት በርካታ መዘዞች አንዳሉት በመረጃም በታሪክም የታወቀ ነው። በተለይም ኡማውን የሚመለከቱ አዳዲስ ክስተቶችን አስመልክቶ ሰለፊይ ዑለማዎች የሚሉቱን በትዕግስት መጠበቅና መጠየቅ በራሱ አዋቂነትና ሰለፊይነት ነው። ተቃራኒውም በተቃራኒ። አላሁ ተዓላ እንዳለው: 《…وَإِذَا جَاۤءَهُمۡ أَمۡرࣱ مِّنَ ٱلۡأَمۡنِ أَوِ ٱلۡخَوۡفِ أَذَاعُوا۟ بِهِۦۖ وَلَوۡ رَدُّوهُ إِلَى ٱلرَّسُولِ وَإِلَىٰۤ أُو۟لِی ٱلۡأَمۡرِ مِنۡهُمۡ لَعَلِمَهُ ٱلَّذِینَ یَسۡتَنۢبِطُونَهُۥ مِنۡهُمۡۗ…》[النساء :٨٣] 4⃣ አመፅን ማሰራጨት ለምሳሌ: ሱረህ (ፎቶና ቪዲዮ) ፣ የዘፈን ድምፅ፣ የአጥማሚዎችን ጣቢያ (ቻናል) ፣ ከአመፅ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ቲክቶክ) የመጡ ነገሮች ፣ ውሸት እና የመሳሰሉትን ማስተላለፍ አለማው ጥሩ ቢመስልም በራሱ አመፅና ፈሳድን መባባስ (ማስተዋወቅ) ነው። 👌መርዝና ማር ከተቀላቀሉ መርዙ ገዳይ ነው ተብሎ አይፈራምን?! አላህ ፀያፍ ነገሮች እንዲሰራጩ የሚፈልጉትን አሳማሚ ቅጣት እንደሚቀጣ አስጠንቅቋል። ﴿إِنَّ ٱلَّذِینَ یُحِبُّونَ أَن تَشِیعَ ٱلۡفَـٰحِشَةُ فِی ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِیمࣱ فِی ٱلدُّنۡیَا وَٱلۡـَٔاخِرَةِۚ وَٱللَّهُ یَعۡلَمُ وَأَنتُمۡ لَا تَعۡلَمُونَ﴾ [النور: ١٩] 5⃣ ስህተትን አለመቀበል ያሰራጩት ጉዳይ ጥፋት ሆኖ  ሲነገራቸው ከማስተካከልና ወደ ሀቁ ከመመለስ ይልቅ የሚብስባቸው ቀልበደረቆችና ኩራተኞች ናቸው። ሚዲያ ላይ ከወጡ መካሪ ብቻ ሳይሆን ምክር ተቀባይ ለመሆንም መዘጋጀት ያስፈልጋል። ሀቅን አይቶ የማይረታ ድርቀቱ የከፋ ሰለመሆኑ አላህ ነግሮናል። ﴿ثُمَّ قَسَتۡ قُلُوبُكُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَ ٰ⁠لِكَ فَهِیَ كَٱلۡحِجَارَةِ أَوۡ أَشَدُّ قَسۡوَةࣰۚ وَإِنَّ مِنَ ٱلۡحِجَارَةِ لَمَا یَتَفَجَّرُ مِنۡهُ ٱلۡأَنۡهَـٰرُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَشَّقَّقُ فَیَخۡرُجُ مِنۡهُ ٱلۡمَاۤءُۚ وَإِنَّ مِنۡهَا لَمَا یَهۡبِطُ مِنۡ خَشۡیَةِ ٱللَّهِۗ وَمَا ٱللَّهُ بِغَـٰفِلٍ عَمَّا تَعۡمَلُونَ﴾ [البقرة :٧٤] 🤲አላህ ይጠብቀን 6⃣7⃣8⃣9⃣🔟 ✍አቡ ሀመዊየህ (ሸምሱ ጉልታ) http://t.me/Abuhemewiya
نمایش همه...
🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍

የጠራ እውቀት ከተቃና አቐም ጋር የተረዘቀ ታድሏል !!

ርዕስ፦➴➴➴➴➴ ❌ #የሸዋል ዒድ ተብሎ ሰለሚከበረው ብይኑ። ▬▬▬▬▬▬ ➤ ነቢዩን መቃረንና መከተል በ 6 (ስድሥት )ነገራቶች ይካተታል 🗓 ሸዋል ⓼/10/1443 የተደረገ ሙሓዶራ 🇸🇦 በሳዑዲ ዓረቢያ በጂዳ ከተማ የተደረገ አንገብጋቢና ወሳኝ የሆነ ሙሓዶራ። ▬ በተለይ በደቡብ እና በሐረር ክልል ይህ የሸዋል ዒድ ተብሎ ከዒድ አል-ፊጥር በበለጠ ሁኔታ ይከበራል። አላህን ልትፈሩ ይገባል ይላሉ ሸይኹ... 🎤 #በሸይኽ ዐብዱልሐሚድ አል-ለተሚ (ሀፊዘሁሏህ) https://t.me/abdulham/1904
نمایش همه...
➲_የሸዋል_ዒድ_ተብሎ_ሰለሚከበረው_ሁክም.mp33.87 MB
Photo unavailableShow in Telegram
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته አስደሳች ዜና 🎤🎤 ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም 🎤🎤 ከረመዷን ቡኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሸዋል 17 ማለትም እሁድ ሚያዚያ 29/08/2015 ከወትሮው ለየት ያለና ያማረ እንዲሁም ትላላቅ እና ብርቅዬ የሰለፍያ መሻይኾች፣ ኡስታዞች እና ዱዓቶች የሚገኙበት ታላቅ የሙሓዶራ ፕሮግራም በአል-ኢስላህ መድረሳ ስለተዘጋጀ ይህ ታላቅ እድል እንዳያመልጠዎት በአክብሮት ጋብዘንዎታል። 🕌 አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ፉሪ፣ኑሪ ሜዳ አል-ኢስላሕ መድረሳ 📅 እለተ፡- እሁድ 29/08/2015 🧭 ሰዓት፡- ከጠዋቱ 2 : 30 ጀምሮ 🌷ለሴቶችም በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!! ጥብቅ ማሳሰቢያ : – 👉 ይህንን በአይነቱ ልዩ የሆነ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎት ፕሮግራሞትን ከወዲሁ በማመቻቸት ከቤተሰብዎ፣ ከጓደኛዎ፣ ከስራ ባልደረባዎ ጋር ለመታደም ቁጥር አንድ ፕሮግራምዎ አድርገው ይያዙ ። 👉 ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው !!!አዘጋጅ፡- አል-ኢስላሕ መድረሳ https://t.me/medresetulislah
نمایش همه...
ትንሹ ዒድ ባህላዊ በዓል ወይስ እንደ አምልኮ ዘርፍ የተያዘ ቢድዐ?! ————— ከዒደል ፊጥር ማግስት ጀምሮ የሚፆመውን 6ቀን የሸዋል ፆምን ተከትሎ ዒደል ፊጥር በወጣ በሳምንቱ የተወሰኑ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከበር የሸዋል ፍቺ ወይም ትንሹ ዒድ በመባል የሚታወቅ በዓል አለ። ይህ በዓል እንደ ሸሪዓ ምንም አይነት ማስረጃ የሌለው በዋናነት ወደ ደቡብ ያሉ የተወሰኑ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረተ ቢስ የሆነ በዓል ነው። በተለይ አላህ ምንም አይነት ማስረጃን ያላወረደበት ይህ በዓል ስልጤና ጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ በልዩ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው። ዲናችን ሙሉ ነው። ከሁለቱ ዒድና ከሳምንታዊ ጁምዓ ውጪ ምንም ይሁን ምን አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ነው። በዲናችን ላይ አዲስ ፈጠራ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በየ ሳምንት ጁምዓ ኹጥባቸው ላይ እንዲህ ይሉ ነበር:- «…የነገሮች ሁሉ ሸር ማለት (በዲን ላይ) አዲስ ፈጠራ ነው፣ አዲስ ፈጠራ (ቢድዐ) ሁሉ ጥመት ነው» ሙስሊምና ነሳኢይ የዘገቡት ሲሆን፣ ነሳኢይ «ጥመት ሁሉ የእሳት ነው» የሚል ዘገባ ጨምሯል፣ ሰነዱም ሶሂህ ነው። ይህ በዓል ከላይ የጠቀስኩላችሁ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበር መሰረቱ ገጠር የነበረ ቢሆንም ከጊዜ ወዲህ ግን በየ ከተማውም በተለየ መልኩ ሌሎች ብሔረሰቦችም ተሳትፈውበት መከበር ጀምሯል። ለበዓሉም ልክ እንደሌሎች በሸሪዓ እንደተጠቀሱ በዓሎች (እንዲያውም በበለጠ መልኩ) የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ይስተዋላል። ታዲያ ማስረጃ የሌለው በዓል እስከሆነ ድረስ ምንም ይሁን ምን፣ መውሊድን ጨምሮ መላው የአለማችን ህዝብ ቢያከብረው እንኳን ቢድዐ ከመሆን አይወገድም!!። ቢድዐ ደግሞ ጥመት ነው፣ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው። በትንሹ ዒድ ላይ አንዳንድ ስለ ዲናቸው ግንዛቤ አላቸው የሚባሉ፣ ሸሪዓው ከሚያግራራው ውጭ እያግራሩ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ለማግኘት የሚዳክሩ ሰዎች የሚያነሱት ብዥታ አለ። እሱም "ምን ችግር አለው? ቢከበር ባህል ነው እንጂ ሃይማኖታዊ ይዘት የለውም" ይላሉ። መልስ:- 1ኛ, ባህላዊ በዓል ቢሆንስ በዚህ መልኩ በየ አመቱ እየጠበቁ በድምቀጥ ማክበሩን ማን ፈቀደው? የሙስሊሞች ሸይኽ በመባል የሚታወቁት ታላቁ ሊቅ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ረሂመሁላህ) የሸዋልን ስምንተኛውን ቀን እንደ በዓል አድርገው የሚይዙና (የደጋጎች ዒድ) ብለው የሰየሙ ሰዎችን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ:- (وأما ثامن شوال : فليس عيداً لا للأبرار ولا للفجار , ولا يجوز لأحد أن يعتقده عيداً, ولا يحدث فيه شيئاً من شعائر الأعياد ) ا. هـ. الاختيارات الفقهية ص/199 “የሸዋል ስምንተኛው ቀንማ ለደጋጎችም ሆነ ለጠማሞች ዒድ አይደለም!። ለአንድም ሰው እለቱን ልዩ የመደሰቻ ዒድ ቀን አድርጎና አምኖ መያዝ አይፈቀድለትም!። በእለቱም ምንም አይነት ለዒድ ከሚንፀባረቁ ነገሮች ማንፀባረቅ አይፈቀድለትም!።” [አል-ኢኽትያራት አል-ፊቅሂየህ 199] ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢምሙ ዐብዲልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁላህ) በውስጣቸው ሸሪዓን የሚፃረር ነገር ባይኖርባቸው እንኳን እንደ ባህል (ልማድ) ተደርገው የሚከበሩ በዓላትን በተመለከተ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:- “ከሁለቱ ዒዶች ውጪ ማንኛውንም ዒድ አድርጎ መያዝ አይፈቀድም!። የእርዱ ቀን ዒድ (ዒደል አድሃ) እና ዒደል ፊጥር፣ እነዚህ ናቸው የሙስሊሞች ዒድ ማለት። እንዲሁም በየ ሳምንቱ የሚመጣው የሚሰገድበት እለተ ጁም ነው። በተረፈ በየ አመቱ የሚሽከረከር የሚሰባሰቡበት የሆነን ዒድ መያዝ መሰረት የሌለው ተግባር ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በኋላ ሶሃቦችም ይሁኑ ታቢዒዮች 3ቱ ክፍለ ዘመናት ውስጥ የነበሩ ትውልዶችም እንዲህ ያሉ በዓላትን አላከበሩም!። በኛ ላይ ግዴታው እነሱ የተጓዙበትን መከተልና በመንገዳቸው መጓዝ ብቻ ነው… ሰዎች መልካም ነው ብለው የሚያስቡት የሚደጋገም ባህል ካላቸው ሀቁን ካወቁና ከተረዱ በኋላ ያንን ባህል መተው ግዴታ ይሆንባቸዋል…” [የሸይኹ ዌብሳይት ላይ በድምፅም በፅሁፍም አለ።] 2ኛ, እንደ አምልኮ ዘርፍ ነው የሚይዙት። 2.1, ለዒደል ፊጥ ከሚያደርጉት ዝግጅት የበለጥ ለዚህ ቀን ነው የሚዘጋጁት። 2.2, በዋናናት አባቶችና እናቶች የሸዋልን 6ቀን አከታትለው የሚፆሙት የዚህን ቀን ፍቺ ለማክበር ነው። 2.3, በተጋነነ መልኩ ለዒደል ፊጥር ሀይላቸውን ቆጠብ አድርገው ለዚህ ቀን ግን ሀይላቸውን አሟጠው ይጨርሱና ከፊታችን ለሚመጣው ዒደል አድሃ እንኳን በቂ ዝግጅት አያደርጉም። ለዚህም ነው ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንቶች "አንድ ቢድዐ በተተካ ቁጥር ሌላ አንድ ሱንና ይሰርዛል" የሚሉት። 2.4, ዝግጅቱን በዋናነት የሚያከብሩ ሰዎች ሲጠየቁ የሸዋል 6ቀን ፆም ፍቺ (ዒድ) ነው ብለው ነው የሚናገሩት እንጂ ባህል ነው የሚል አመለካከት የላቸውም። ይህ (ባህል ነው) የሚለው አመለካከት ጠንካራ አቋም ያላቸው የሱና ሰዎች "ትንሹ ዒድ ቢድዐ ነው" ብለው ሲያስጠነቅቁ እነ ሸህ ገራገር ህዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት ለማግኘት ሲጠየቁ የፈበረኩት አመለካከት ነው። ይህን አመለካከት ሲፈበርኩ ግን ይህን ሁሉ እውነታ ያውቁታል። እያወቁ ሀቁን ይደብቁታል፣ ያምታቱታል። ይህ ደግሞ አላህ እንዲህ በማለት አይሁዶችን የወቀሰበት አደገኛ ተግባር ነው:- وَلَا تَلْبِسُوا الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُوا الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ «እውነቱንም በውሸት አትቀላቅሉ፡፡ እናንተም የምታውቁ ስትሆኑ እውነትን አትደብቁ፡፡» አል-በቀረህ 42 3ኛ, እንዲህ ያሉ በዓላት ላይ ሌላው ከባድ አደጋ!! የተለያዩ የኢስላምና የሙስሊሙ ጠላቶች እንዲህ ያሉ አዳዲስ በዓላትን ቀንና መስለው በተለየ መልኩ በየ ሚዲያዎቻቸው እያስተዋወቁ ሙስሊሙ በሀይማኖቱ ከተደነገጉ ብርቅዬ በዓላት እንዲዘናጋና ከሀይማኖቱ ተቃራኒ መንገድ እንዲጓዝ ይሰራሉ። ወላሁ አዕለም!! ✍🏻 ኢብን ሽፋ: (t.me/ibnshifa) የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም 👇👇 ቻናላችን #join በማድረግ ይቀላቀሉ https://telegram.me/IbnShifa https://telegram.me/IbnShifa
نمایش همه...
[ኢብን ሽፋ Ibn Shifa]

👌 ማስታወቂያ ለዚህ ቻናል ተከታታዮች በሙሉ!       በኡስታዝ አቡ ኡበይዳ አብራር አወል ተቀርተው ያለቁ ኪታቦችን በመስማት የአቂዳ እና ሌሎችንም እውቀቶችን ለማስረፅ የምትፈልጉ እህት እና ወንድሞች አንድ ፕሮግራም አመቻችተናል። ↪️ እሱም ከትናንሽ ኪታቦች ጀምረን በየቀኑ ሁለት ሁለት ደርሶች እንለቅላቹሀለን። ታዲያ ከናንተ የሚጠበቀው በተመቻችሁ ሰአት እያወረዳችሁ መስማት ብቻ ነው። 👍 ከነገ ጀምሮ የሚለቀቅላችሁ የ"ሀኢያ" እና የ"ነዋቂዱል ኢስላም" ኪታብ ቂርአት ነው። እነዚህን ኪታቦችን በመስማት መሀፈዝ ይኖርባቹዋል። ➡️ ታዲያ ይህንን እድል ለጓደኞቻችሁ ሼር በማድረግ ጋብዟቸው። https://t.me/AbraribnAwal
نمایش همه...
አብራር አወል ( Abu ubeyda)

ይህ ቻናል የአቡ ዑበይድ አብራር አወል ትምህርቶች የምለቀቁበት official ቻናል ነው። ሙሓደራዎች ደርሶች ሩዱዶች ሌላም መልዕክቶች ይተላለፉበታል

ማን ነው የተለወጠው? እያልክ፡- "እነሱፍያ - ማቱሪድያ "እነአህባሽ - አሽአርያ "እነተብሊግ - ቲጃንያ "ዛሬማ ተለውጠዋል "ተውሂዱን ይዘዋል "ሱናውን ጨብጠዋል" - ነጋ-ጠባ የማልክልኝ - ያለመታከት የጀነጀንከኝ፤ ከቶ መቼ ቀረ መባሉ፡- "እናንተ የአሏህ ልጆች - ቶሎ ድረሱ" "ሀጃዬን ሙሉሉኝ - አሁን አድርሱ?" ከቶ መቼ ቀርቶ ነው፡- የአሏህን ስልጣን - ለፍጡር ማውረሱ በስቲጋሳ ቆሻሻ - ኢባዳን ማርከሱ? "ሽርክ ቀርቷል" -"ተለውጠዋል" ያልከኝ፣ በስል ምላስህ - ጧት-ማታ የጀነጀንከኝ - ተጃጅለህ ልታጃጅለኝ ከቶ መቼ ቀርቶ ነው፡- "ወልዮች - ኑ ድረሱልኝ "ልጅም - ሀብትም ስጡኝ" "ጅላሌዋ - ኑ ገስግሱልኝ "ሙሉ ጤየናዬን መልሱልኝ" - ቀን ከሌት ማለቱ - ሙታንን መጥራቱ፡፡ ከቶ መቼ ቀረና ነው፡- አፈር-ትቢያ የሆኑ - ሙታንን መማፀኑ ለሙታን መሳሉ - በየቀብሩ መባዘኑ የቀብር አፈር - እንደ "ጁስ" መጠጣቱ ለሙታን መስገዱ - ሙታንን መፍራቱ? "ዛሬማ ተለውጠዋል" "ተውሂዱን ይዘዋል" "ሱናውን ጨብጠዋል" በማለት፡- - ነጋ-ጠባ የጀነጀንከኝ - ደጋግመህ የማልክልኝ - ተጃጅለህ ልታጃጅለኝ ከቶ መቼ ቀረና ነው፡- "አሏህ ከአርሽ በላይ አይደለም" ማለቱ ከስድስቱ አቅጣጫ እሱን ማጥራቱ? ለአሏህ ብሎ መወዳጀትን ለአሏህ ብሎ መቆራረጥን - በሙመይእ - የተኩላ ጥርስ ለመበጣጠስ - በኢኽዋን - የቀበሮ መንጋጋ ለማፈራረስ "ተለውጠዋል" አልከኝ - አንተው ተለውጠህ? "ሱና ይዘዋል" አልከኝ - ሱናህን አሟምተህ? ሼህ አልባኒ ምን ነበር ያሉት? ሊቀይሩ ገብተው ወጡ ተቀይረው ረጅም ፂማቸውን - ሙልጭ አድርገው ላጭተው አጭር ሱሪያቸውን - ጫማ ጠራጊ አርገው፡፡ ተውሂዴን - በምላስህ ግለት አቅልጠህ ሱናዬን - በሰበካህ ጨረር አሟምተህ በተለውጠዋል ሽፋን - እኔን ልትለውጠኝ የኢኽዋንን - ቁሞ-ቀራዊ መንሀጅ ልትጭነኝ የሙመይእን - እስስታዊ ካባ ልታከናንበኝ "ተውሂድ ይዘዋል - ለተውጠዋል" አልከኝ? እነሱ ሳይሆኑ - አንተ ተለውጠህ! እነሱ ሳይሆኑ - አንተው ሟምተህ-ቀልጠህ! ባተሌው ወንድሜ! ምስራቅና ምእራብን - ለማገናኘት እሳትና ቤንዚንን - ለማወዳጀት ጨለማና ብርሀንን - ለማቀናጀት፤ ሚዳቆን ልታድን - ከጣና ባህር ከዳሽን ተራራ - አሳን ልታሰግር ባተሌው ወንድሜ! ሌት ከቀን እየዳከርክ ጧት-ማታ እየባዘንክ "ተለውጠዋል" አልከኝ - አንተው ተለውጠህ! እነሱ ሳይሆኑ - አንተው ሟምተህ-ቀልጠህ! #በዶ/ር ጀማል ሙሐመድ የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.