cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
26 384
مشترکین
+1724 ساعت
+1057 روز
+58730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 📙 የሸይኽ ሙባረክ አል ወልቂጢይ የቂርዓት ፕሮግራሞች የሚለቀቁት የድምፅ ፋይሎች በአንዳንድ ምክንያት ሳንለቅ በመቆታችን ይቅርታ እይጠየቅን ከዚህ በኋላ ካቆምንበት ቀጥሎ ያሉትን ተራ በተራ የምንለቅ ይሆናል ኢንሻ አላህ። https://t.me/shikmubarek https://t.me/shikmubarek
نمایش همه...
"የሸይኽ ሙባረክ አል-ወልቂጢይ" ትምህርቶች ቻናል [THE OFFICIAL CHANNEL OF SHAYKH MOBARAK WOLKITE]

* የቻናሉ አላማም የኢትዮጵያ ሙስሊሙን ማህበረሰብ በተለይም ወልቂጤ እና ዙሪያዎቿ ያሉ ሙስሊሞችን ጥርት ያለውን እስልምና ማስተማር ሲሆን ሻዕባን 05 በ 1445 አ’ሒ ተከፍቷል።

https://t.me/bahruteka mesael al jahiliya online ders የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ ሳአት ፣ እሮብና ሐሙስ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ማኢዳ 05.mp310.19 MB
መሳኢሉል ጃሂሊያ 32.mp37.41 MB
👉 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ካወደመና ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድንና መማክርቶቹን እንዲሁም ጠባቂዮቹን ካስረሸነ በኋላ ዲርዒያን ሙሉበሙሉ ለማፅዳት ባደረገው ዑለሞችን የማደን ሂደት ሸይኽ ሱለይማን ኢብኑ ዐብዲላህ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብን በቁጥጥር ስር አደረጋቸው ። ሸይኽ ሱለይማን ማለት ተይሲሩል ዐዚዚል ሐሚድ ሸርሕ ኪታቡ ተውሒድን እየፃፉ የነበሩ ታላቅ ዓሊም ሲሆኑ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጅ ናቸው ። የጀመሩት ኪታብ የአጎታቸው ልጅ ዐ/ራሕማን ኢብኑ ሐሰን ፈትሑል መጂድ በሚል ጨርሰውታል ። ኢብራሂም ባሻ ስልጣናችን ተነካ ባሉ የቱርክ ኤምፓየር መሪዮች የፈለገውን ሰርቶ ስልጣናቸውን ከስጋት እንዲከላከልላቸው በአባትየው አማካይነት ስልጣን የተሰጠው አረመኔ ነውና የቁርኣንና ሐዲስ ዓሊም ክብር ምኑም አይደለም ። ሸይኽ ሱለይማንን የፊጥኝ አስሮ ወደ መቃብር ቦታ ወሰዳቸው ። እዛ ከመረሸንና ከረሀብ የተረፈውን ህዝብ ሰብስቦ የግብፅ የሙዚቃ ባንድ እያስጨፈረ በከባድ መሳሪያ እንዲመቱ አደረገ ። የሸይኽ ሱለይማን ስጋ ተቆራርጦ ተበታተነ ።‼ ጀናዛቸው ታጥቦ ተከፍኖ ሊቀበር ይቅርና አካላቸው እንኳን መሰብሰብ አዳጋች ሆነ ። በዚህ አላበቃም ኢብራሂም ባሻ ወደ ሱለይማን አባት ሄዶ በግብፅ አነጋገር ያ አጉዝ ( አጁዝ ) ( አንተ ሽማግሌ ሆይ) ቀተልና ኢብነክ ( ልጅህን ገደልኩት ) አለው ። የሸይኽ ሱለይማን አባት ግን ታሪክ የማይረሳው መልስ ሰጡት ። መልሱ የኢብራሂም ባሻን አእምሮ እንደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ሰርስሮ ገባ ። አባትየው እንዲህ ነበር ያሉት : – ኢን ለም ተቅቱልሁ ማተ ( ባትገድለውም ኖሮ ሟች ነበር ። !!!!! ከዚህ በኋላ ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያ ላይ አሻንጉሊቶቹን አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ ። ግብፅ ላይ ሹማምንቶች ፣ የጦር አበጋዞችና ዑለሞች ተሰብስበው እየጠበቁት መሆኑን ተነገረው ። እሱም በትካዜ የኋልዮሽ ተመልሶ እያየ ዑለሞችማ የዲርዒያ በረሀ ላይ ቀሩ አለ ። የሸይኽ ሱለይማን አባትም ዓሊም መሆናቸውን ያውቅ ነበርና ንግግሩ ከአእምሮ አልወጣ ብሎት ። በቱርክ ኤምፓየርና በመምለካ ተዋጊዮች መካከል የነበረው ጦርነት ለስልጣንና ለተውሒድ የተደረገ ጦርነት ነበር ። የአላህ ስራ አስገራሚ ነውና አላህ ያን ግዙፍ የኢስላሙን ዐለም ሲመራ የነበረው የቱርክ ኤምፓየር ስርወ መንግስ ከአምስት አመት በኋላ ዲርዒያ ላይ ዳግም ላይመለስ ገርስሶ ከእነዚያ የተውሒድ መሪዮች ጋር ተቀብሮ የነበረው የተውሒድ ችግኝ እንቡጥ በደማቸው በዐብዱላሂ ልጅ ቱርኪ አማካይነት ዳግም እንዲያብብ በማድረግ የተውሒዷን ሀገር እስከ ዛሬ እንድትቀጥል አድርጓል ። የቱርክ ኤምፓየር ግን በዛው ማብቂያው ሆኗል ። ለአላህ የሆነ ይቀራል የሚባለው ለዚህ ነው ። ክፍል አንድን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5079 ክፍል ሁለትን ለማግኘት 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/bahruteka/5081 https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ ክፍል አንድ ነጅድ ማለት በሳውዲ ዐረቢያ የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን የሚያካልል ግዛት ስም ነው ። የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ ነጅድ ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሓኢል ፣ ዲርዒያ ፣ ዑየይናና ፣ ሑረይሚላእ እንዲሁም አሕሳእ የመሳሰሉ ከተሞች ያሉበት አካባቢ ነጅድ በመባል ይታወቃል ። የነጅድ አንበሶች በማለት የፈለግሁበት የሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ የልጅ ልጆችና የሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ የልጅ ልጆችን ነው ። የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱል ወሀብ የልጅ ልጆች የነጅድ ዑለሞች ሲባል ቅድሚያ ዪዛሉ ። ሳውዲ ( መምለከቱል ዐረቢያ ሱዑዲያ) የሚባለው ሀገር የተመሰረተው በሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድና በሸይ ሙሐመድ ኢብኑ ዐ/ወሃብ ነው ። ሸይኽ ሙሐመድ ዐ/ወሃብ ዳዕዋቸውን ሲጀምሩ ሑረይሚላእ ከሚባለው ከተማ ወደ ዑየይና ከዛ ወደ ዲርዒያ እየተሰደዱ መጥተው ዲርዒያ ላይ የሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ባለቤት በወቅቱ የጎሳ መሪ ለነበረው ባልዋ ይህን ሰው ተቀበለው አላህ ወዳንተ የላከው ስጦታ ነው ብላው ሸይኽ ሙሐመድን ተቀብሎ አክብሮ በነፃነት ዳዕዋ እንዲያደርጉ አደረገ ። በየቦታው ተደብቆ የነበረው የተውሒድ ዳዕዋ የተጠማ በሙሉ የተውሒድ ዳዕዋ ነፃነት ሲሰማ ወደ ዲርዒያ ጎረፈ ። ሸይኽ ሙሐመድ ከየቦታው የሚመጣውን የተውሒድ ተማሪ በማስተማርና ዳዕዋ በማድረግ ዲርዒያን ከፅልመት አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ቀየሯት ። የተውሒድ ባንዲራ ዲርዒያ ላይ ከፍ ብሎ መውለብለብ ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ በእውኑ አይደለም በህልሙም ይሆናል ብሎ ያልጠቀው ክስተት ማየት ጀመረ ። ማህበረሰቡ ተቀየረ ። ቀብር አምልኮ እየመነመነ ሄደ ። በጎሳ ህግ ሲተዳደር የነበረው ገበሬ በቁርኣንና ሐዲስ መመራት ጀመረ ። ሙሐመድ ኢብኑ ስዑድ…

https://t.me/bahruteka mesael al jahiliya online ders የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ቀጥታ ስርጭት ቦታ ፣ አል ኢስላሕ መድረሳ ሳአት ፣ እሮብና ሐሙስ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የኒቃብ ጥላቻ በሽታ ሲሆን የታሪክ መዛግብቶች እንደ ሚያስነብቡት የአላህ መልእክተኛ ከመላካቸው በፊት አዩሁዶችና ነሳራዎች ( ክርስቲያኖች ) ዘንድ ኒቃብ የንፁህነትና የክብር ራስን የመጠበቂያ ምልክት እንደነበር ነው ። በዛን ዘመን አንድ ክብሯን የምትጠብቅና ከፀያፍ ተግባር ለመራቅ የፈለገች ሴት ሙሉ ልብስ ከነኒቃቡ ጋር ትለብስ እንደነብርና የዚህ አይነት ልብስ የምትለብስ ወጣት በማህበረሰቡ የተከበረች እንደነበረች መዛግብቶቹ ያስረዳሉ ። አላህ ነብዩ ሙሐመድን ሲልክ ሴትን ልጅ የክብር ማማ ላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው ሕያው ቃሉ ስለ ሒጃብ በሚቀጥለው ቃሉ አስቀምጧል ። « وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ » النور (31) " ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ፡፡ በእነዚህ አንቀፆች ሴት ልጅ የውበቷ መገለጫዎች ለማን ግልፅ ማድረግ እንዳለባትና ከማን መሰተር እንዳለባት አስቀምጧል ። በመሆኑም ኒቃብ ኢስላም ሴት ልጅ ክብሯን መጠበቅ ስትፈልግ እንድትለብሰው ሳይሆን ለብሳው ክብሯን መጠበቅ እንዳለባት አዟል ። ኒቃብ በኢስላም ክብንና ንፅህናን የሚጠብቁበት ብቻ ሳይሆን ወደ አላህ የሚቃረቡበት የአምልኮ ክፍል ነው ። ምክንያቱም አምልኮ ( ዒባዳ) ማለት የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ መፈፀም ስለሆ ነው ። በመሆኑም ኒቃብ በሁለቱም ሀገር እጅግ በርካታ ቱሩፋቶች ያሉት መሰተሪያ ሲሆን ከእነዚህ ቱሩፋቶቹ ውስጥ ጥቂት በቅርቢቱ ዓለም ካሉት ውስጥ እንመልከት : – አንደኛና ሁለተኛው – ተለይተው እንዲታወቁና ጎንታዮች ባለጌዎች እንዳይጎነትሏቸው እንዳያስቸግሩዋቸውም ይረዳል ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ያላል : – « يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا » الأحزاب ( 59 ) " አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም ፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው ፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡" ሶስተኛው – ክብራቸውን ይጠብቁበታል ። አራተኛው – አላህን የመፍራታቸው ምልክት ነው ። አምስተኛው – ልባቸው በተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የታመሙ ሰዎች በእነርሱ ምክንያት እንዳይሳሳቱ ያደርጋል ። ስድስተኛ – ዝሙት እንዳይስፋፋ ያደርጋል ። እነዚህ ከብዙ ጥቂት ቱሩፋቶቹ ናቸው ። በመሆኑም ኢስላም ሴትን ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጣት ስለሆነ አንድ ሴት ጌጥ የሆነው ወርቋን ደብቃ ከምትጠብቀው በላይ ራስዋን ደብቃ ለሚገባው አካል ብቻ እንድታስረክብ ያዛታል ። ይህን ስትፈፅም የክብሩ ማማ ላይ ትወጣለች ። በጣም የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ኒቃብ የኋላ ቀርነት ምልክት አድርጎ ያየዋል ። ከዚህም በላይ አንዳንዶች ልጃቸው ዝሙት ሰርታ በዝሙት አርግዛ ሲያዩ የማይደነግጡትና የማይበሳጩት አይነት ብስጭት ኒቃብ ለብሳ ሲያዩ ይበሳጫሉ ።‼ ይህ በርግጥ ትልቅ በሽታ ነው ። ከዚህም በላይ ደግሞ ልጃችሁ ከፍራለች ቢባሉ በብስጭት የማይታመሙትን ያክል ታመው ሆስፒታል ይገባሉ ። ይህ ምናባዊ ሀሳብ ሳይሆን በገሀዱ ዐለም ያለ እውነታ ነው ። በቅርቡ ሶስት ኒቃብ የለበሱ እህቶቻችን ቤተሰቦች ላይ ከታየው አሳፋሪ ተግባር ውስጥ የአንደኛዋ እህት እናትና አባት በብስጭት ታመው አባትየው ሆስፒታል ይገኛሉ ። ‼ በእነዚህ እህቶች ላይ ከተማም ገጠርም ያለ ዘመድ አዝማድ በሙሉ ኒቃቡን ለማስወለቅ የሚችለውን ያደረገ ሲሆን የሁለቱ እስካሁን አልተሳካም ። በተለይ ቤተሰቦቿ በዚህ ምክንያት የታመሙት ፀንታ ነው ያለችው ። ከሁለቱ እህቶቿ አንደኛዋ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ መብትሽ ነው እኔ ጋር ነይ ብሎ ከዘመዶቿ አንዱ ወደ ማታውቀው ከተማ እንድሄድ ካደረገ በኋላ መንገድ ላይ ጠብቆ ከመኪና ስትወርድ የምታወልቂ ከሆነ ልውሰድሽ ካልሆነ አዚሁ ጥዬሽ ነው ምሄደው ብሎ የቀን ጨለማ ውስጥ እንድትገባ አድርጎ አስሆልቋቷል ። ‼ አላህ ይድረስልን እንጂ ኒቃብ ለበሽታ ሰበብ የሚሆንባቸው ሙስሊሞች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ። ለእህቶቻችን ፅናቱን ለቤተሰቦቻቸው አላህ ሂዳያ እንዲሰጣቸው ዱዓእ እናድርግ እላለሁ ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

አመተ ምህረትም አመተ ልደትም ሳይሆን አመተ እርገት ነው      የሀገራችን ኢትዮጲያ ብዙ ክፍል ማህበረሰብ ኢትዮጲያ ውጪውን አለም ያልተከተለችበት ብዙ አይነት መገለጫዎች አሏት ብለው ያምናሉ። ከነዛ መካከል የራሷ የሆነ አመታት አቆጣጠር እንዳላት ያምናሉ። ይህም አቆጣጠር በሰላሳ የሚቆጠሩ የፀሀይ ቀናቶች ያሏቸው 12 ወራቶች አሉት። የወራቶቹ ስምም የተለየ እና የራሷ ነው። ሌሎች በፀሀይ መውጣት እና መግባት የሚቆጥሩ ሀገራቶች ወራቶቻቸው አንዳን ግዜ 31 ቀን እንደሚኖረው ይነገራል። የኢትዮጲያ ቆጣሪዎች ደግሞ አንዳንዴ የሚመጣውን ትርፉ አንድ ቀን ሰብሰብ አድርገው ጳጉሜ የሚባል አንዳንዶች 13ኛው ወር የሚሉት ቀሪ 5 – 6 ቀናቶች ያተራርፋሉ። ከዛ ቡሀላ ነው እንዳዲስ የቀናቶች እና የወራቶች ቆጠራ የሚጀመረው። በጣም የሚገርመው እስካሁን ያለፉት ትርፍ የጳጉሜ ቀናቶች ሲሰሉ ሰላሳ አመት ሁነው ይገኛሉ። እነሱ እንደሚሉት አመታቱን መቁጠር የጀመሩት ኢስላም ባይቀበለውም (እነሱ እንደሚሉት) ዒሳ (እየሱስ) ከተሰቀለ ግዜ ጀምሮ ነው ይላሉ። ይህ የእየሱስ መሰቀል የምህረት ፍፁም ታላቅ ክስተት ነው ብለው ያምናሉ። ለዛም ነው አቆጣጠሩን አመተ ምህረት ብለው ይጠሩታል። ግን ደግሞ ኢስላም በክስተቱም በአቆጣጠሩም ላይ የተለየ አመለካከት አለው። ክስተቱን በተመለከተ ዒሳ በፍፁም በጭራስ አልተሰቀሉም የሚል እምነት አለው። የተሰቀለው ግን ከሀዋሪያት መሀከል የሆነ ጀነትን ትገባለህ እኔን እንድትመስል ትደረጋለህ በሚል ትእዛዝ ከዒሳ በስተኩል የታዘዘ አንድ ግለሰብ ነው። ሌሎች እንደሚሉት ደግሞ አይ ሰውዬው ዒሳን ለመግደል ከሚሯሯጡት መሀከል አንዱ ነው አላህ እሳቸውን እንዲያርጉ ካደረገ ቡሀላ የሳቸውን ምስል ለሱ አለበሰውና እሱን ሰቀሉት ይላሉ። ይህም ይሁን ያ ዒሳ ዐለይሒ ሰላም አልተሰቀሉም። በዚህም ክስተት ምክንያት የተማረ ማንም ሰው የለም። ስለዚህ ኢስላም አቆጣጠሩን በተመልከተ ግልፅ የሆነ ተቃውሞ አለው። አንደኛ ኢስላም የራሱ የሆነ በዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የተጀመራ ከዛም ቡሀላ ሙስሊም ሊቃውንቶች ሁሉ የተስማሞበት የሒጅራ አቆጣጠር ስላለው ነው። በመቀጠልም ደግሞ ክስተቱ የምህረት ነው ብሎ ስለማያምን። ከዚህም በመነሳት ብዙ የኢስላም እምነት ተከታዩች ይህን የአቆጣጠር ስያሜ በመቃወም ወደ አመተ ልደት ቀይረው ይጠቀማሉ። አመተ ምህረት የሚለው ከእምነታቸው ጋር ስለማይሔድ። በመሰረቱ በራሳቸው በኢስላም የሒጅራ እና የጨረቃ አቆጣጠርን መጠቀሙ ያዋጣቸዋል። ከተለያዩ የአምልኮው ስነስርአት ጋር የሚሔድላቸው ይህ ነው። የሀገሩን አቆጣጠር ከሀገሩ ብዙ ነዋሪዎች ጋር ለመግባባት ብቻ ቢጠቀሙት ችግር የለውም። ብቻ ግን አመተ ምህረት የሚለውን እንደማይስማሙበት ለመግለፅ አመተ ልደት ይላሉ። እኔ ግን ይህ ትክክል እንዳልሆነ አምናለው። የሀገራን አቆጣጠር ከሀገሩ ብዙ ነዋሪዎች ጋር ለመግባባት ብቻ ብንጠቀምበት ችግር የለውም። ግን ደግሞ አመተ ምህረት የሚለውን ለመቃወም የምንጠቀመው አመተ ልደት ትክክል አይደለም። ምክንያቱም አቆጣጠሩ የጀመረበት ግዜ እና ስያሜያችን አይገጣጠሙም። ለምን ከተባለ አቆጣጠሩ የጀመረው እንደከሀዲያን ዒሳ ከተሰቀሉበት እንደ ኢስላም ደግሞ ዒሳ ካረጉበት እንጂ ከልዳታቸው ማለትም ከተወለዱበት አይደለም። ከልደታቸው ብለን ስንሰይም ገና ከ2016 ላይ 33 አመት መጨመር ግድ ይለናል። ምክንያቱ መቁጠር የተጀመረው ከተወለዱ ከ 33 አመታት ቡሀላ ነው። ስለዚህ ለዚህ መፍትሄ የሚሆን አንድ ሀሳብ አለኝ። ለመቃረንም በደንብ የጎላ ኢስላም ያፀደቀውን መቃረን በቀጥታ የሚገልፅ እንዲሁም ቆጠራውም ጋር የማይጋጭ የሆነ ስያሜ አለኝ እሱም አመተ እርገት የሚል ነው። ይህ ስያሜ እነሱ የሚያምኑበትን ስቅለት በቀጥታ የሚቃረን ሲሆን አቆጣጠሩም የጀመረበት ጊዜን ይገጥማል። ስለዚህ ይህን የሀገራችን አቆጣጠር ስንጠቀም አመተ እርገት ወይም በአጭሩ ደግሞ (አ እ) የሚለውን ብንጠቀም የተሻለ ነው። ✍ ወንድማችሁ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ https://t.me/abuzekeryamuhamed
نمایش همه...
ሙሐመድ አል-ወልቂጢይ ((አቡ ዘከሪያ))

https://t.me/abuzekeryamuhamed

✍ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱ ላሂ ወበረካቱ። ውድ እና የተከበራቹ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ይህ ቻናል ረመዳን 29 1442 አ.ሂ የተከፈተ ቻናል ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰቦችን በተለይም ደግሞ ወልቂጤ ላይ እና ዙሪያዎቿ የሚገኙትን ታሳቢ በማድረግ የተከፈተ ጥርት ያሉ የሰለፊያ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

🔷 የነጅድ አንበሶች ለተውሒድ የከፈሉት ዋጋ የቱርክ ኤምፓየር ሱዑዲያ የምትባለውን ሀገር ማጥፋትና መካና መዲናን ማስመለስ ጊዜ የማይሰጠው ዋናው ስራ አደረገው ። ግዙፍ ጦር አዘጋጅቶ ወደ ዐረቢያ ግዛት ላከ ። ጦሩ ወደ መዲና ለመድረስ በሚያደርገው ግስጋሴ ያገኘውን ሁሉ ከምድር በታች እያደረገ ጉዞ ቀጠለ ። መዲና ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዶ ህፃን አዋቂ ፣ ሽማግሌ አሮጊት ሳይል እየረሸነ መዲናን ተቆጣጠረ ። መዲና የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶችን ወደ ኢስታንቡል ጫነ ። እነዚህ ታሪካዊ ቅርሶች አሁንም በቱርክ ዋና ከተማ ሙዘየም ላይ ይገኛሉ ። አላማው የመምለካን መሪዮች የሱዑዲ ዋና ከተማ የነበረችው ዲርዒያን ወሮ መሪዮቹን ማርኮ መቀጣጫ ማድረግና የተውሒድዋን ሀገር ማፈራረስ ነበርና መገስገስ ጀመረ ። ጉዞውን ወደ መካ ያደረገው ይህ ጦር ማውደሙንና መረሸኑን በመቀጠል መካ ደረሰ ። መካ ላይም የተለመደውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በማድረግ በቁጥጥሩ ስር አደረጋት ። ሒጃዝን ( መካና ነዲናን) በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ጉዞውን ወደ ነጅድ አደረገ ። የዚህን ትልቅ ሀላፊነት መወጣት ለሚስር ( ግብፅ ) መሪዮች አስረከበ ። በወቅቱ የነበረው ሙሐመድ ዐሊ ባሻ ጦሩን እየመራ ወደ ዲርዒያ አቀና ። ከመጀመሪያ የባሰ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተለያዩ ከተሞች እያደረሰ ቢሄድም ዲርዒያን መቆጣጠር አልቻለም ። መሪነቱን ለልጁ ኢብራሂም ባሻ አስረክበ ። ኢብራሂም ባሻ በአዲስ መልኩ ጦሩን አደራጅቶ ሳር ቅጠሉን እያነደደ የህፃንና አዋቂን የአረጋዊያንን ጀናዛ ለአሞራ እየተወ ወደ ዲርዒያ ገሰገሰ ። ዲርዒያን ለሰባት ወር አካባቢ ከበባት ። ምንም ነገር እናዳይገባና እንዳይወጣ ከለከለ ። ረሀቡና ጥሙ ህፃናትና አረጋዊያንን ማርገፍ ሲጀምር የሳውዲ ( የሱዑዲ ) መሪ የነበረውን ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ሱዑድ ከበባው እንዲያበቃና ዋስትና ከሰጠው እጁን እንደሚሰጥ መልእክት ላከ ። ኢብራሂም ባሻ ጥያቄውን የተቀበለው መሆኑና ምንም ጉዳት እንደማያደርስ መልስ ሰጠ ። ዐብዱላሂ ኢብኑ ሙሐመድ ከነመማክርቱና ጠባቂዮቹ እጅ ሰጠ ። አሳፋሪው ኢብራሂም ባሻ ግን ቃሉን አፍርሶ ዲርዒያን አነደዳት ። ‼ በህዝቡ ላይ የተለመደውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ አካሄ ። ሙርከኛቹን ወደ ግብፅ ላካቸው ። ከግብፅ ወደ ቱርክ ተላኩ ። ቱርክ ላይ ዐብዱላሂ ኢብኑ መሐመድ ተገሎ አንገቱ ተቆርጦ ወደ የቱርክ ኤምፓየር መሪ ተላከ ። የተቀሩትም ተረሸኑ ። ኢብራሂም ባሻ ዲርዒያን ለማፅዳት ዑለሞቹን ማደን ጀመረ ። አላህ ካለ ይቀጥላል ። https://t.me/bahruteka
نمایش همه...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

አል አጅዊባ 40.mp38.52 MB
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.