fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

Berbir Mereja / በርብር መረጃ

رفتن به کانال در Telegram

Welcome back to our channel, where we bring you the latest updates and news from around the world.

نمایش بیشتر
5 133
مشترکین
-824 ساعت
-207 روز
-230 روز
آرشیو پست ها
ኬንያ ኢትዮጵያን በመብለጥ የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ሆነች የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ለአምስት ዓመታት ይዛው የ
ኬንያ ኢትዮጵያን በመብለጥ የምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ ኢኮኖሚ ሆነች የዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ በግዙፍ ኢኮኖሚ ለአምስት ዓመታት ይዛው የቆየችውን የአንደኝነት ደረጃ ለኬንያ አስረክባለች። የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ዋጋ 126 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ የኬንያ ግን ወደ 135 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተገልጿል። በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከነበረችበት 7ኛ ደረጃ ወደ 8ኛ ዝቅ ስትል፣ ኬንያ ባንጻሩ ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች። ኢትዮጵያ የቀዳሚነት ደረጃዋን እንድትለቅ ያደረጋት ዋናው ምክንያት የምርት ማነስ ሳይኾን፣ የብር ምንዛሬ ዋጋ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከዶላር አንጻር ማሽቆልቆሉ መሆኑ ተመላክቷል። ሆኖም ከዓመታዊ የኢኮኖሚ እድገት አንጻር ሲታይ፣ ኢትዮጵያ አሁንም በኬንያ ላይ ከፍተኛ ብልጫ እንዳላት የጥናቱ መረጃዎች ያሳያሉ። @berbirmereja @berbirmereja

'መኪኖቻችሁን ከከተማዋ ጎዳናዎች ይዛችሁ ውጡ!' የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። 'ለአንድ ዓመት ተኩል መክረናል፣ አስጠንቅቀናል፤ ከእንግዲ
'መኪኖቻችሁን ከከተማዋ ጎዳናዎች ይዛችሁ ውጡ!' የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። 'ለአንድ ዓመት ተኩል መክረናል፣ አስጠንቅቀናል፤ ከእንግዲህ ግን እርምጃ እንወስዳለን' ብሏል። ከመጠን በላይ በካይ ጭስ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች  ሁለት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል፦ የበካይ ጋዝ መቀነሻ ቴክኖሎጂ መግጠም፣ አለበለዚያ የከተማዋን ጎዳናዎች ለቀው መውጣት! ኃላፊዎቹ 'እስካሁን በጭስ ምክንያት ያቆምነው መኪና የለም፤ ከእንግዲህ ግን ይህ አይቀጥልም ሲሉ የመጨረሻውን ቀይ መስመር አስቀምጠዋል። በከተማዋ ለሚታየው የአየር ብክለት 32 በመቶው የተሽከርካሪዎች ጭስ ነው ተብሏል። ያረጁ መኪኖችና ታክሲዎች መንገዱን ለቀው ከወጡ የከተማዋ የትራንስፖርት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? @berbirmereja @berbirmereja

+1
በአየር ላይ መብረር የሚችል የቴስላ ኩባንያ አዲስ መኪና‼️ የቴስላ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢሎን ማስክ በቴክሳስ በሚገኘ የስፔስ ኤክስ የሙከራ ማዕከል "በአየር ላይ መብረር ይችላል" ያሉትን አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ይፋ አደረጉ። በሮኬት አይነት አስወንጫፊዎች የታገዘው 'ቴስላ ሮድስተር' የተሰኘው ይህ የሁለት ሰው የስፖርት መኪና በኤሌክትሪክ መኪና ኩባንያው ቴስላ እና በስፔስ ኤክስ የሮኬት ቴክኖሎጂ ትብብር የተሰራ መሆኑን ኤሎን መስክ ገልጸዋል። ይህ ድንቅ መኪና በሰዓት ከ0 እስከ 97 ኪ/ሜ ያለውን ፍጥነት ከ1 ሰከንድ ባነሰ ጊዜ (በ0.8 ሰከንድ) ውስጥ መጓዝ ይችላል። የላቀ የአየር ግፊት እና የታመቀ አየር ማስወጫ ቴክኖሎጂን በመጠቀም፦ - ቁልቁል ተደፍቶ/የላይኛውን አካሉን ወደታች ዘቅዝቆ የመጓዝ፣ - ከከፍታ ላይ ዘሎ አየር ላይ የመቆየት፣ - ከመሬት ላይ ተነስቶ አየር ላይ የመንሳፈፍ፣ - አየር ላይ የመሽከርከር፣ የመገለባበጥ እንዲሁም አቅጣጫውን መቀየር የሚያስችል ችሎታዎች አሉት ተብሏል። በሙከራው ወቅት ሊከሰት የሚችል የአደጋ ስጋት ለመቀነስ እና የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ሙከራው ሙሉ በሙሉ ሰው አልባ ነው የተከናወነው። ኢሎን ማስክ እንደገለጹት ተሽከርካሪው በ2028 ወደ ምርት ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የዘርፉ ባለሙያዎች የሮኬትና መኪናን ቴክኖሎጂ አዋህዶ ረጅም ርቀት የማንሳፈፍ / የመብረር አቅሙን በተግባር ማረጋገጥ ከፍተኛ የቴክኒክ ፈተና እንደሚኖረው ጠቁመዋል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ ምሽግ በመቆፈር ላይ መሆኑ እና ከሕወሓት ኃይሎች ጋር ቅንጅት መፍጠሩ ተሰማ» ​የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን አዲ አሠር ቆይቶ ከነበረበት ቦታ
🚨 «የኤርትራ ሠራዊት በድንበር አካባቢ ምሽግ በመቆፈር ላይ መሆኑ እና ከሕወሓት ኃይሎች ጋር ቅንጅት መፍጠሩ ተሰማ» ​የኤርትራ ሠራዊት በትግራይ ሰሜን ምዕራብ ዞን አዲ አሠር ቆይቶ ከነበረበት ቦታ በመልቀቅ በድንበር አቅራቢያ በሚገኙ አዲ ጸጸር እና ዲችናማ አካባቢዎች ዳግም መሰማራቱ ተገለጸ። ​የሠራዊቱ አቀማመጥ እና ምሽግ ቁፋሮ፦ የኤርትራ ወታደሮች በብዛት ወደ ኢሮብ ወረዳ በመግባት የመከላከያ ምሽጎችን በመቆፈር ላይ እንደሚገኙ የዋዜማ መረጃዎች አመልክተዋል። ​ከሕወሓት ጋር የተደረገ ቅንጅት፦ የሕወሓት አርሚ 70 የተወሰኑ ተዋጊዎች ከኤርትራ ሠራዊት ጋር በመቀላቀል ላይ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ የሁለቱ ወታደራዊ አዛዦች በዲችናማ አካባቢ በቅርቡ በመሰብሰብ ወታደራዊ ዕቅዶችን ማቀዳቸውን እና የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ መስማማታቸው ተሰምቷል። @berbirmereja @berbirmereja

ሰበር - በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተቋቋመ‼️ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የፌዴራል መንግሥት ለቀጣዮቹ 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ባለአደራ አ
+4
ሰበር - በትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ተቋቋመ‼️ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የፌዴራል መንግሥት ለቀጣዮቹ 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ባለአደራ አስተዳደር በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማቋቋሙን አስታወቀ። 👉የባለአደራ አስተዳደሩ ዋና ዋና ተግባራት የሰላምና መረጋጋት ችግርን በፍጥነት መፍታትና የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ መጠገን የፈረሱ የመንግሥት መዋቅሮችንና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን መልሶ መዘርጋት የተፈናቀሉትን መመለስ እና ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈትቶ ማቋቋም 👉በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ነፃና ግልጽ ምርጫ በማካሄድ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እንዲቋቋም ማመቻቸት ነው። የአስተዳደሩ ዋና አስፈጻሚዎች ሹመት፦ 📌አቶ አሰፋ አብርሃ ሐጎስ — የአስተዳደር እና የሕዝብ አገልግሎት ዋና አስፈጻሚ 📌ዶክተር ቴዎድሮስ አረጋይ — የኢኮኖሚ እና መልሶ ግንባታ ዋና አስፈጻሚ 📌ብ/ጄ ገብረ እግዚአብሔር በየነ — የጸጥታና ሰላም ዋና አስፈጻሚ 📌አቶ ረዳኢ ኃለፎም — የፖለቲካ እና ሕዝብ አደረጃጀት ዋና አስፈጻሚ 📌ዶክተር ሽሻይ አማረ — የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተመድበዋል። @berbirmereja @berbirmereja

ተሿሚዎች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገቡ‼️ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተሾሙ አዳዲስ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ለመውሰድ ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸው ተሰማ። ይህ ያልተለመደ እርምጃ የመጀመሪያው ዙር ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ባለስልጣናት በተከታታይ ተመሳሳይ ወታደራዊ ስልጠና እንደሚወስዱ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በፓርላማ እና በተለያዩ መድረኮች ላይ፣ የመንግስት ሹመኞች "ቦርጭ ማውጣት እና ከመጠን በላይ መወፈር እንደሌለባቸው" በማንሳት፣ ጂም በመግባት እና ስፖርት በመስራት ንቁና ቀልጣፋ መሆን እንዳለባቸው በሳቅ የታጀበ ማሳሰቢያ ሲሰጡ ተሰምተው ነበር። Via:- ዘሐበሻ @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድሮን የታገዙ ብርቱ ውጊያዎች መካሄዳቸው ተገለጸ» ​የኢትዮጵያ ፌዴራል ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ተዋጊዎች ከሕወሓት ኃይሎች ጋር በመሆን በትግራይ
🚨 «በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድሮን የታገዙ ብርቱ ውጊያዎች መካሄዳቸው ተገለጸ» ​የኢትዮጵያ ፌዴራል ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ተዋጊዎች ከሕወሓት ኃይሎች ጋር በመሆን በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድሮን ጭምር የታገዘ ውጊያ ማድረጋቸው ተሰማ። ​የውጊያው አካባቢዎች፦ የፌዴራል ሠራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል በጋራ በመሆን በትግራይ ማዕከላዊ ዞን ተምቤን ልዩ ስሙ ሸውዓተ አሕጉም እንዲሁም አበርገለ በተባሉ አካባቢዎች ከባድ ውጊያ እያካሄዱ መሆኑ ተመላክቷል። ​የድሮን ድጋፍ፦ በግጭቱ ወቅት በድሮን የተደገፉ የውጊያ እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ተገልጿል። @berbirmereja @berbirmereja

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት “ድንበር ተሻጋሪ ወረራዎችን ማስወገድ ይገባቸዋል” አሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር “በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ስለበረታው
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት “ድንበር ተሻጋሪ ወረራዎችን ማስወገድ ይገባቸዋል” አሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር “በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ስለበረታው ውጥረት” በዛሬው ዕለት በስልክ የተነጋገሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፤ “በሁሉም ወገኖች በኩል ውጥረት ማርገብን እደግፋለሁ” አሉ። በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት፤ “ድንበር ተሻጋሪ ወረራዎችን ማስወገድ ይገባቸዋል” ሲሉም አሳስበዋል። ማርኮ ሩቢዮ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ያደረጉትን ውይይት በማስመልከት አጠር ያለ ማብራሪያ የተሰጠው፤ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ጽህፈት ቤት በኩል ነው። ጽህፈት ቤቱ ማብራሪያውን ከማውጣቱ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሩቢዮ በስልክ መነጋገራቸውን ይፋ አድርገው ነበር። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስለ ውይይቱ ባወጣው መግለጫ፤ የዛሬው የስልክ ንግግር ያተኮረው በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል እየጨመረ ስለመጣው ውጥረት እንደሆነ ገልጿል። ሁለቱ ሀገራት ላለባቸው “ውስጣዊ እና ውጫዊ ውጥረቶች ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ የሚገኘው” በ2010 ዓ.ም. በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በተፈረመው “የሰላም ማዕቀፍ” አማካኝነት እንደሆነ ማርኮ ሩቢዮ ማሳሰባቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት ለማድረግ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ ተገለጸ» ​ኢትዮጵያ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የምታደርገውን ድጋፍ ካቋረጠችና የሱዳንን ደህንነት ከሚያሰጉ እንቅስቃሴዎች ከተቆ
🚨 «ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት ለማድረግ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ ተገለጸ» ​ኢትዮጵያ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የምታደርገውን ድጋፍ ካቋረጠችና የሱዳንን ደህንነት ከሚያሰጉ እንቅስቃሴዎች ከተቆጠበች ከጎረቤቷ ጋር ውይይት ለማድረግ በሩ ክፍት መሆኑን ሱዳን ገለጸች። ​የውይይት ቅድመ ሁኔታ፦ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሙህዪዲን ሳሌም ከፈረንሳይ የሱዳን እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ዦን ማሪዬ-ሳፋ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ኢትዮጵያ ለፈጥኖ ደራሽ ኃይል የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም እና የደህንነት ስጋት ከሆኑ እንቅስቃሴዎች እንድትቆጠብ አሳስበዋል። ​የዲፕሎማሲ ውይይት ትኩረት፦ በካርቱም የተደረገው ይኸው ውይይት በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጣናዊ ጉዳዮች እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «የኤርትራ ሠራዊት አቅምና ከጎረቤት ሀገር ጋር ያለው ወታደራዊ አለመመጣጠን መገለጹ ተመላክቷል» ​የኤርትራ ሠራዊት ከ350,000 በላይ አባላት ያሉት ትልቅ ኃይልን ያሰለፈ ቢሆንም፣ የሚሠሩት 7
🚨 «የኤርትራ ሠራዊት አቅምና ከጎረቤት ሀገር ጋር ያለው ወታደራዊ አለመመጣጠን መገለጹ ተመላክቷል» ​የኤርትራ ሠራዊት ከ350,000 በላይ አባላት ያሉት ትልቅ ኃይልን ያሰለፈ ቢሆንም፣ የሚሠሩት 7 አውሮፕላኖች ብቻ እንዳሉት እና አንድም አገልግሎት ላይ ያለ ተዋጊ ጀት (Fighter Jet) እንደሌለው ተገለጸ። ​የወታደራዊ መሣሪያዎች ዕድሜ፦ አብዛኛው የሠራዊቱ መሣሪያ ከ1990ዎቹ የድንበር ጦርነት (1990-1992 ዓ.ም.) ጀምሮ የቆየ መሆኑ ተመላክቷል። ​የመከላከያ በጀት ውስንነት፦ የሀገሪቱ 219 ሚሊዮን ዶላር የመከላከያ በጀት ኤርትራ ከሌሏት ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎች እና ድሮኖች አንፃር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲወዳደር እጅግ የተገደበ መሆኑ ተገልጿል። ​የቴክኖሎጂ ልዩነት፦ ጎረቤት ሀገራት ኤርትራ በሌሏቸው ድሮኖች እና የጦር መሣሪያዎች እራሳቸውን እያጠናከሩ እና እያመረቱ መምጣታቸው በሁለቱ አካባቢዎች ያለውን የወታደራዊ አቅም ልዩነት እንዳሰፋው ተመላክቷል። @berbirmereja @berbirmereja

የሚሳይልና የፀረ-አውሮፕላን ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ፀሃየ (ወዲ ፀሃየ) በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነገረ። በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም፣ የህወሓት ታጣቂ ኃይል የሚሳይልና የ
+1
የሚሳይልና የፀረ-አውሮፕላን ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ፀሃየ (ወዲ ፀሃየ) በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተነገረ። በዛሬው ዕለት፣ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ.ም፣ የህወሓት ታጣቂ ኃይል የሚሳይልና የፀረ-አውሮፕላን ክፍል አዛዥ ተብሎ የተጠቀሰው ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ፀሃየ፣ በቅጽል ስሙ ወዲ ፀሃየ፣ በተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ለማምለጥ ሲሞክር በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት (ENDF) እና በትግራይ የሰላም ኃይል (TPF) በቁጥጥር ሥር መዋሉን ምንጮች ገልጸዋል። @berbirmereja @berbirmereja

ጄነራል ፊሊጶስ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተሰማ ‼️ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለረጅም ዓመታት በቀኝ እጃቸውነት ሲያገለግሏቸው የቆዩትንና የሀገሪቱን ጦር ኃይል ጠቅላይ ሹም የነበሩትን ጄነራ
ጄነራል ፊሊጶስ ከኃላፊነት መነሳታቸው ተሰማ ‼️ የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ለረጅም ዓመታት በቀኝ እጃቸውነት ሲያገለግሏቸው የቆዩትንና የሀገሪቱን ጦር ኃይል ጠቅላይ ሹም የነበሩትን ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስን ከነበሩበት ኃላፊነት ገለል ማድረጋቸው ታወቀ። 📌ጀኔራል ፃድቃን በአንድ ወቅት "ጀኔራል ፊሊጶስ የኤርትራን መገንጠል እንደማይደግፍ ነግሮኛል" ማለታቸው አይዘነገም። በጄነራል ፊሊጶስ ምትክም ሜጀር ጄነራል አስመሮም ገብረእግዚአብሔር የኤርትራን ጦር ኃይል በበላይነት እንዲመሩ ተሾመዋል። ዕድሜያቸው 71 ዓመት የሆኑት ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ከኤርትራ የትጥቅ ትግል ጀምሮ በወታደራዊው ዘርፍ የቆዩ ሲሆን፣ በ1990ዎቹ በተካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ወቅትም የምዕራብ ግንባር አዛዥ ሆነው አገልግለዋል። ከማርች 2014 ዓ.ም ጀምሮ የኤርትራ መከላከያ ኃይል ጠቅላይ ሹም ሆነው ለ12 ዓመታት ያህል በኃላፊነት ላይ ቆይተዋል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጄነራል ፊሊጶስን ከኃላፊነታቸው ያነሷቸው ከተወሰነ የታማኝነት ጥርጣሬ ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ ለጊዜው ገለል እንዲሉ በማድረግ በምትካቸው ቀደም ሲል የሎጂስቲክስ ዘርፉን ሲመሩ የነበሩትን ሜጀር ጄነራል አስመሮም ገብረእግዚአብሔርን መሾማቸው ተገልጧል። ይህ በኤርትራ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ላይ የተደረገው ለውጥ፤ ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ወቅት የተከናወነ መሆኑ ትኩረት ስቧል። @berbirmereja @berbirmereja

❗️ሸራሮ ምን እየተካሄደ ነው!!? በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የአየር ድብደባዎች እየተደረጉ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 2 እና 3 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ
❗️ሸራሮ ምን እየተካሄደ ነው!!? በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ከባድ የአየር ድብደባዎች እየተደረጉ ነው። የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፉት 2 እና 3 ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ከባድ ድሮን እና የአየር ድብደባዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል። የኤርትራ ጦር እና የትግራይ ተዋጊዎች ከዋና ዋና ከተሞች ሲወጡ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደህንነታቸው ወደተጠበቁ ቦታዎች እንዳይሸሹ እና ጥቃቶችን እንዳይሰነዝሩ ለመከላከል ቀጣይነት ያለው የአየር ዘመቻዎችን እያደረገ ይገኛል። ከአዲግራት እስከ ዛላምበሳ፣ ከአድዋ እስከ ራማ፣ እና ሺራሮ አካባቢዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል። ይህንን ተከትሎ በኤርትራ አዋሳኝ ሽራሮ አካባቢ የእሳት አደጋ የተነሳ ሲሆን ባለፉት ሁለት ወይም ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ ኤርትራ ድንበር እየተዛመተ መሆኑን ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዳታገኝ ግብፅ የመቃወምም ሆነ የመከልከል የሞራልም ሆነ የሕግ መብት የላትም - ቲቦር ናዥ» ​የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ና
🚨 «ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዳታገኝ ግብፅ የመቃወምም ሆነ የመከልከል የሞራልም ሆነ የሕግ መብት የላትም - ቲቦር ናዥ» ​የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ፍጹም ተገቢና ሕጋዊ መሆኑን ገለጹ። ​የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ፦ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጥያቄ ፍጹም ተገቢና ሕጋዊ መሆኑ ተመላክቷል። ​ስለግብፅ አቋም የተሰጠ አስተያየት፦ ዲፕሎማቱ ግብፅ ለአባይ ወንዝ ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ ሳይኖራትና በባሕሩ ላይ የመከልከል ሕጋዊ መብት ሳይኖራት፣ ኢትዮጵያ ወደብ እንዳታገኝ የምታደርገው ጽንፈኛ ተጽዕኖና ፉክክር ፍጹም ግብዝነት መሆኑን አጋልጠዋል። @berbirmereja @berbirmereja

በአዲስ አበባ የተቋቋመውና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተው «የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ክልሉን በጊዜያዊነት ለመረከብና ለማስተዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የፌደራል
በአዲስ አበባ የተቋቋመውና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተው «የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ክልሉን በጊዜያዊነት ለመረከብና ለማስተዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የፌደራል መንግሥት ሳይቀበለው መቅረቱ ታውቋል። ምክር ቤቱ ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው ህወሓት መቀሌን ለቆ ከወጣ በኋላ የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት በሚል ፤ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪል ማኅበራትንና ታጣቂዎችን በማካተት የተመሠረተ ነው። ይህ ስብስብ «የድህረ-ህወሓት ስትራቴጂ ሰነድ» በማዘጋጀት ህጋዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ክልሉን በጊዜያዊነት የማስተዳደር ሐሳብ ለመንግሥት ቢያቀርብም፣ የፌደራል መንግሥቱ ግን ሰነዱን ከመረመረ በኋላ ውድቅ ማድረጉን የምክር ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል። የፌደራል መንግሥቱ ዕቅዱን ያልተቀበለው በምክር ቤቱ አባል ድርጅቶች መካከል ባሉ የውስጥ ልዩነቶች ምክንያት እምነት በማጣቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከውሳነው በኋላ ከቀናት በፊት መቀሌ ለሚዲያ ቃላቸውን የሰጡት የጠ/ሚ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ክልሉን በቀጥታ የፌደራሉ መንግሥት እንደሚያስተዳድረው መግለፃቸው ይታወሳል። @berbirmereja @berbirmereja

ትግራይ ክልል‼️ 📌ከትግራይ ክልል ገጠር ወረዳዎችም ሆነ ከተማ የህውሃት ኃይሎች ለቀው ኤርትራ መግባታቸው በስፋት እየተነገረ ነው።በርካታ የጦር መሳሪያዎች ባልተጠበቁ ቦታወች ጭምር መገኘቱ ተሰምቷል
+4
ትግራይ ክልል‼️ 📌ከትግራይ ክልል ገጠር ወረዳዎችም ሆነ ከተማ የህውሃት ኃይሎች ለቀው ኤርትራ መግባታቸው በስፋት እየተነገረ ነው።በርካታ የጦር መሳሪያዎች ባልተጠበቁ ቦታወች ጭምር መገኘቱ ተሰምቷል። 📌መቀሌና አካባቢው የዲዲአር ምዝገባ በስፋት እየተካሄደ ነው። 📌ለቀጣይ 6 ወራት በኮማንድ ፖስት ይመራል ለተባለው ትግራይ ክልል ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ ካቆሙበት እንዲቀጥሉ ይደረጋል ተብሎ እየተገነረ ነው። 📌ከትግራይ ክልል እርዳታ በስፋት እየተሰራጨ መሆኑ ተሰምቷል። 📌መቀሌና ሽሬ ከእስር ያመለጡ ግለሰቦችን አድኖ የማስገባት ስራጨመጀመሩ ተነግሯል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «የአክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላምበሳ ከህወሓት ነፃ መውጣታቸው ተገልጾ፤ የባድመ አቅጣጫ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ» ​የአክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላምበሳ ከተሞች ከህወሓት ኃይሎች ነፃ መውጣታቸው የታወቀ
🚨 «የአክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላምበሳ ከህወሓት ነፃ መውጣታቸው ተገልጾ፤ የባድመ አቅጣጫ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ» ​የአክሱም፣ ሽራሮ እና ዛላምበሳ ከተሞች ከህወሓት ኃይሎች ነፃ መውጣታቸው የታወቀ ሲሆን፣ ቀጣዩ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ባድመ አቅጣጫ መሆኑ ተነግሯል። ​🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​የሕወሓት ኃይሎች አቀማመጥና ክፍፍል፦ የሕወሓት ኃይሎች በአሁኑ ወቅት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አካባቢ መከማቸታቸው የተሰማ ሲሆን፣ አመራሮች ወደ ኤርትራ ድንበር መሻገር እንዳለባቸውና እንደሌለባቸው በሚለው ሐሳብ ዙሪያ ከፍተኛ ክፍፍልና ውጥረት እንደነገሰባቸው ታውቋል። ​ከመንግሥት የተላለፈ መልእክት፦ መንግሥት በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ለተሰበሰቡ ታጣቂዎችና ካድሬዎች፣ ወደ ኤርትራ ምድር ለመሰደድ እንዳሞክሩና ተስፋ በመያዝ ለሠራዊቱ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ ማስተላለፉ ተገልጿል። ​በእንስሳት ላይ የደረሰ ንብረት ውድመት፦ በትግራይ በፍያ ቀሺ እና ፋፂ አካባቢዎች የሚገኙ የትግራይ አርሶ አደሮች እንስሳት (አህዮች) በኤርትራ ሰራዊት በኃይል ተነጥቀው ወደ ኤርትራ መወሰዳቸው ተሰምቶ፣ በጎ አድራጊ አካላት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ ቀርቧል። @berbirmereja @berbirmereja

“እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያሉ የሃይማኖት ተቋማትን የሚከፋፍል አካሄድን መንግሥት አይታገስም” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 45ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መን
+1
“እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያሉ የሃይማኖት ተቋማትን የሚከፋፍል አካሄድን መንግሥት አይታገስም” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 45ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ቤተ ክርስቲያኗ በታሪክ፣ በቅርስ እና በሀገረ መንግሥት ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽዖ ምትክ የሌለው መሆኑን ገልጸዋል። መንግሥት የሃይማኖት ተቋማትን አቅም የሚያዳክሙና የሚከፋፍሉ አዝማሚያዎችን ፈጽሞ እንደማይታገስ አስጠንቅቀዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም፤ ቤተ ክርስቲያኗ ዕምቅ አቅሟን ተጠቅማ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት፣ ሰላምን ለማጽናት እንዲሁም ሕዝቦችን ለማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚናዋን እንድትወጣ አደራ ሰጥተዋል። ለሀገር ግንባታ ከሚደረጉ ማናቸውም መንፈሳዊና ልማታዊ ጥረቶች ጎን መንግሥት ሁልጊዜም አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። EOTC - @berbirmereja @berbirmereja

ፖለቲካዉ እንዳሻዉ ይገለባበጣል! የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት!! የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን
+1
ፖለቲካዉ እንዳሻዉ ይገለባበጣል! የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት!! የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር)ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል። የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ አል ሳዑድ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ ብለዋል። አልጋ ወራሹ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ስኬትን፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀጣይነት ያለው እድገት እና ብልጽግናንም ተመኝተዋል። @berbirmereja @berbirmereja

🚨 «በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጥረት እየጨመረ ባለበት ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ» ​በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ኤር
🚨 «በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጥረት እየጨመረ ባለበት ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ» ​በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ኤርትራ መካከል ያለው የጸጥታ ውጥረት እየጨመረ በሄደበት ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ። ​🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​የውይይቱ ትኩረት፦ መሪዎቹ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ወቅታዊ በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ተመላክቷል። ​ቀደም ያሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች፦ ይህ የስልክ ውይይት የተካሄደው፣ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መካከል ከተደረገው ተመሳሳይ ከፍተኛ የስልክ ውይይት ተከትሎ መምጣቱ ይታወሳል። @berbirmereja @berbirmereja