fa
Feedback
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

رفتن به کانال در Telegram

📈 تحلیل کانال تلگرام የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

کانال የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU (@eotcgssu21) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 14 403 مشترک است و جایگاه 6 084 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 336 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 14 403 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 26 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 541 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 19 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 34.65% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً N/A% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 988 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 0 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 33 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

توضیحی برای کانال ارائه نشده است.

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 27 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

14 403
مشترکین
+1924 ساعت
+1197 روز
+54130 روز
آرشیو پست ها
የጅማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለተከታይ አምስት ወራት ያሰለጠናቸውን 41 የደረጃ 2 ተተኪ መምህራንን አስመረቀ! 26/4/2016 (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሲያሰለጥናቸው የቆዩ የደረጃ ሁለት ተተኪ መምህራን ሰልጣኞችን ታኅሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ክቡር መልአከ ሰላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በጅማ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል አዳራሽ አስመርቋል። በጅማ ከተማ ከሚገኙ 15ቱም ሰንበት ት/ቤቶች የተወጣጡና በሥልጠናዎቹ ወራት የተሰጡ መመዘኛዎችን በብቃት ተወጥተው ለምረቃ የበቁ 41 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል። ከሰልጣኞቹ መካከል 10 ዲያቆናት፣ 20 መምህራን ወንድሞች እና 11 እህቶች ለምረቃው በቅተው በትላንትናው ዕለት ከክቡር ሥራ አስኪያጁ ሰርተፊኬት የተቀበሉ ሲሆን የጅማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነትም ለሁለተኛ ዙር ካስተማራቸው አጠቃላይ 79 ሰልጣኞች መካከል ተመዝነው ለምረቃ የበቁት 41 ብቻ መሆናቸውን የጅማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ ዲ/ን ሀብታሙ ኃይለማርያም በምረቃው ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። ክቡር መልአከ ሰላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ "የዛሬ ተመራቂዎች ቤተ ክርስቲያን ከእናንተ ብዙ ነገር ትጠብቃለች ፤ በተለይም የተጀመረውን የሰንበት ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት ከግብ ለማድረስ ትልቁን ድርሻ የምትወስዱ ናችሁ፤ ልክ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በነፃ ያስተማረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር ልታገለግሏት ይገባል" ብለዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ ክቡር ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ የጅማ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ክቡር ላዕከ ወንጌል መ/ር ባዬ ከድር፣ የሀገረ ስብከቱ የመምያ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ሰባኪያነ ወንጌል መምህራን፣ የማኅበራት ተወካዮችና የሁሉም ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል። መረጃውን ከጅማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት አግኝተናል። (የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

"አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና" ማቴ 2፡5 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድ
"አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና" ማቴ 2፡5 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል..." ኢሳ 7፡14 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.
"ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል..." ኢሳ 7፡14 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

https://youtu.be/TGyfaIQdin0?si=jOJl8BWKWrqbgDr4 ትምህርት በሚዲያ 11ኛ ክፍል ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የድንግልና ሕይወት ክፍል ሦስት

"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ሉቃ 1፡14 እንኳን ለብጹዕ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድ
"በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ሉቃ 1፡14 እንኳን ለብጹዕ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ! የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የሥርዓተ ትምህርቱን ትግበራ ለማሳለጥ በሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር እያከናወነ መሆኑን የቦሌ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ገለፀ። ታኅሣሥ 23/2016 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥር ካሉት አንድነቶች አንዱ የሆነውና ብዛት ያላቸው አድባራት ካሉባቸው ወረዳዎች የቦሌ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ነው። በወረዳው የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች 61 ሲሆኑ ከ40 በላይ የሚሆኑት ሥርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ላይ ይገኛሉ። የወረዳው የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሥሩ የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች በትኩረት ትግበራው ላይ በማተኮር ይሰሩ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ከነዚህም የመስክ ጉብኝት ከማድረግ አንስቶ የመምህራን ሥልጠና በማዘጋጀት ማሰልጠን እንዲሁም በደብራት መሀልም የጥያቄና መልስ ውድድር መድረኮችን ማዘጋጀት ይጠቀሳሉ። ይህ የጥያቄና መልስ ውድድር ዓላማ በወረዳው ውስጥ ባሉ ሥርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ላይ ከሚገኙ ደብራት በ38 ደብር በአንደኛና በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የሚደረግና ሥርዓተ ትምህርቱን ለመተግበር የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ለመፈተሽ ታልሞ የተዘጋጀ ነው። ውድድሩ በየሳምንቱ የሚከወን ሲሆን በመጨረሻ ጥሩ ውጤት ለሚያመጡ ሽልማት እንደተዘጋጀና ሽልማቱም 1 ለወጣ 10000 ብር እና 100 ውዳሴ ማርያም 2 ለወጣ 7000 ብር እና 70 ውዳሴ ማርያም 3 ለወጣ 4000 ብር እና 40 ውዳሴ ማርያም እንደሆነ የክፍለ ከተማው ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ክፍል ተጠሪ ሊቀ መዘምራን ዳዊት ዘነበ ገልፀውልናል። የዝግጅት ክፍላችንም ይህን መሰል እንቅስቃሴዎች በሌሎቹም ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነትና በሀገረ ስብከቶች ሊለመድና ሊስፋፋ እንዲገባ መልዕክቱን ያስተላልፋል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

የሥርዓተ ትምህርቱን ትግበራ ለማሳለጥ በሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር እያከናወነ መሆኑን የቦሌ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ገለፀ። ታኅሣሥ 23/2016 ዓ.ም የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሥር ካሉት አንድነቶች አንዱ የሆነውና ብዛት ያላቸው አድባራት ካሉባቸው ወረዳዎች የቦሌ ክፍለ ከተማ ተጠቃሽ ነው። በወረዳው የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች 61 ሲሆኑ  ከ40 በላይ የሚሆኑት ሥርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ላይ ይገኛሉ። የወረዳው የሰ/ት/ቤቶች አንድነት በሥሩ የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች በትኩረት ትግበራው ላይ በማተኮር ይሰሩ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። ከነዚህም የመስክ ጉብኝት ከማድረግ አንስቶ የመምህራን ሥልጠና በማዘጋጀት ማሰልጠን እንዲሁም በደብራት መሀልም የጥያቄና መልስ ውድድር መድረኮችን ማዘጋጀት ይጠቀሳሉ። ይህ የጥያቄና መልስ ውድድር ዓላማ በወረዳው ውስጥ ባሉ ሥርዓተ ትምህርቱን በመተግበር ላይ ከሚገኙ ደብራት በ38 ደብር በአንደኛና በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የሚደረግና ሥርዓተ ትምህርቱን ለመተግበር የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ለመፈተሽ ታልሞ የተዘጋጀ ነው። ውድድሩ በየሳምንቱ የሚከወን ሲሆን በመጨረሻ ጥሩ ውጤት ለሚያመጡ ሽልማት እንደተዘጋጀና ሽልማቱም 1 ለወጣ 10000 ብር እና 100 ውዳሴ ማርያም 2 ለወጣ 7000 ብር እና 70 ውዳሴ ማርያም 3 ለወጣ 4000 ብር እና 40 ውዳሴ ማርያም እንደሆነ የክፍለ ከተማው ሥርዓተ ትምህርት ትግበራ ክፍል ተጠሪ  ሊቀ መዘምራን ዳዊት ዘነበ ገልፀውልናል። የዝግጅት ክፍላችንም ይህን መሰል እንቅስቃሴዎች በሌሎቹም ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነትና በሀገረ ስብከቶች ሊለመድና ሊስፋፋ እንዲገባ መልዕክቱን ያስተላልፋል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

"ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።" ሉቃ 1፡35 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.
"ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።" ሉቃ 1፡35 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰ/ት/ቤት ከቅድመ መደበኛ እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ሙሉ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ
+5
የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ደብር ሰ/ት/ቤት ከቅድመ መደበኛ እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ሙሉ የሥርዓተ ትምህርት ትግበራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ በተገኙበት በትላንትናው ዕለት ተከናውኗል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕፃናት ዓውደ ርዕይ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፍሬሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ተካሄደ። 21-04-2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) የብርሃናተ ዓ
+7
የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕፃናት ዓውደ ርዕይ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ፍሬሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ተካሄደ። 21-04-2016 ዓ.ም (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የሕፃናት የመዝሙር ፣ የስዕል ፣ የኪነ ጥበብ እና የጨዋታ ዓውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት አከናወነ። ቁጥራቸው በዛ ያለ ሕፃናትና ወላጆች ዓውደ ርዕዩን ተካፍለዋል። መርሐ ግብሩ የተለያዩ ሕፃናትን እያስተማሩ እያዝናኑ የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን እና ኪነ ጥበባዊ ሥራዎችን የያዘ ሲሆን በውጭ ተጽዕኖ ሥር እየተከበረ የመጣውን የልደት በዓል ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማክበርን ለሕፃናት ማስተማርና ማሳየትን ዓላማ አድርጎ እንደተዘጋጀ የመርሐ ግብሩ ዋና አስተባባሪና በሕፃናት ክፍሉ የልዩ ተሰጥዖ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ተመስገን ፍቃዱ ገልጸዋል። አክለውም እንዲህ ዓይነቱ መርሐ ግብር በሁሉም አጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች ሊተገበርና ሕፃናት ላይ መሥራት እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልልፈዋል። (የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ✍️YouTube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu ✍️ FaceBook 👇 https://www.facebook.com/EOTC.GSSU ✍️Telegram 👇 https://t.me/SSUGlobal ✍️Website👇 https://eotc-gssu.org/a/ ✍️Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@sundayschoolunion

"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው። የሚያሳጣኝ የለም። በለምለም መስክ ያሳድረኛል። በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።" መዝ 22፡1-2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው። የሚያሳጣኝ የለም። በለምለም መስክ ያሳድረኛል። በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።" መዝ 22፡1-2 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! መልካም ዕለተ ሰንበት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu

"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።" መዝ 43፡3 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት!
"ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።" መዝ 43፡3 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናልን ሰብስክራይብ ያድርጉ። ሰናይ ሌሊት! ✍️Youtube 👇 https://www.youtube.com/@eotc-gssu