قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
907
مشترکین
-224 ساعت
-127 روز
+4630 روز
آرشیو پست ها
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«ከጀርባዬ አንድ ግዙፍ ተራራ!!»
---------------------------
.......✍አባትነት
ግዙፍ ተራራ ነው ስሙ የደመቀ፡
ለልጁ ነፍስ ሰጭ ወኔው የታመቀ፡
በህይወት እስካለ ይደምቃል ልጅነት፡
ጋሻ መከታ ነው ማዕረግ ነው ወንድነት፡
የጥበብ መነሻ ይህ ነው አባትነት፡
ልጄ የሚል ጥሪ አባት ሲያስተጋባ፡
አበጥሮ ሲለይ ምርቱን ከገለባ፡
ልጁን እንዳይደፍረው ዱርየና ሌባ፡
አለኝ ማለት ብቻ ማዕረግ ነው አባ።
«አባት ሳለ አጊጥ ጀንበር ሳለ ሩጥ»
........ ከኔ የበዙ ደስታዎች ጀርባ አንድ የሆዱን በሆዱ አምቆ የያዘ የኔን ሳቅ ብቻ በጉጉት የሚጠብቅ አንድ ግዙፍ ሰው አለ።
ከኔ የወጣትነት ውበትና መሽቀርቀር ጀርባ አንድ የተበሳቆለ፣
የተንከራተተ፣
ያደፈ ልብስ የለበሰ አንድ እምቅ ወኔ ያለው ሰው አለ።
......ከኔ የለሰለሱ እጆች ጀርባ አንድ የሻከሩ መዳፎች ያሉት ሰው አለ።
.......ከኔ በሁለት እግር መቆም እና በራስ መተማመን ጀርባ አንድ ጠንካራ ሰው አለ ።
........ከኔ የመኖር ትርጉም እና ሰው የመሆን ማንነት ጀርባ አንድ ብልህ ሰው አለ ።
.......ከኔ ዛሬና የተስፋ ነገዎቼ ጀርባ አንድ ለኔ ሲል ትናንቱን ያጣ ሰው አለ ።
......ከኔ ህይዎት መቃናት ጀርባ አንድ የጎበጠ ሰው አለ ።
......➢ከኔ ምርጥ አባወራ የመሆን ምኞት እና ለሰው የመኖር ጥበብ ጀርባ አንድ ለቤተሰቡ እንደ ሻማ እየበራ እራሱን በማቃጠል ለቤቱ ብርሀን ሁኖ የቆመ ሰው አለ።
...ያ አንድ ሁኖ ብዙ የሆነ ጀግና ያ እናትም አባትም በመሆን ፍቅርን ሳይሰስት እየለገሰ ሁሌም እና በምንም ሁኔታ ከጎኔ ሳይለይ የመከታ ክንዱን የሚዘረጋልኝ ድንቅ ሰው #ውድ_አባቴ ነው ።
«ሌላውን ተውት ካርድ እንደልብ በማይገኝበት በገጠር ህይወት እየገፋ ለኔ በቀጥታ ስልክ የደወለልኝ ማንም ሳይሆን አባቴ ነው ።»
.....ከእማዬ የዘጠኝ ወር ሸክም በኋላ እስከ አሁኗ ጊዜዬ ድረስ አርግዞ አምጦ ወልዶ አዝሎ ልጄ አንቀልባህኮ ዛሬም ከወገቤ አልተፈታም መቼ ይሆን ከሀሳብ የማርፈው እያለ እንባው በአይኑ ሲያቀር አሁን እየፃፍኩ ከሆሄወቹ ጋር ምስሉ የሚታየኝ ይመስለኛል።
«የኔ አባት ለማንም ክፉ እንዳልመኝ፣
የማንም ማግኘት እንዳስደስተኝ፣
ምቀኝነትና ክፋት ከውስጤ እንድጠፋ እና የተሰማኝን ነገር ሳልደብቅ በነፃነትና በድፍረት እንድናገር ሳትማር ያስተማርከኝ የኔ ንጉስ አንተ ነህ ዲግር ተሸክመህ ለኔ ድግሪ የምትጨነቅ የገጠር ግዙፍ #ካንፓሴ አባ.....!!!
ሁሉም አልፎ በልጅህ ኮርተህ እንደኖርክልኝ እንድኖርልህ አላህ ረጂም ሀያት ይስጥህ አባ ኢንሻ አሏህ ሁሉ ይሳካል አንድ ቀን ሰርፕራይዝ አለህ እሽ የኔ አባት እወድሀለሁ።
.....ኑረዲን አል-አረብ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
Repost from ተቀርተው ያለቁ ደርሶች
ሪዝቅ ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ ማን ነው?
|| - ዶር ደጘሽ ብኑ ሸቢብ አልዐጅሚ
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/MohamedAljawi
Repost from Abu_Oubeida~channel
✨ የመርከዝ መናሩ ሱና ታላቅ የደስታ እና የምረቃ ጥሪ! ✨
📖 "ቁርኣንን የተማረና ያስተማረ ከሁሉ በላጭ ሰው ነው!
ተማሪዎችን ከቃዒዳ ጀምሮ ቁርኣንን በነዞር የሚያስተምረው መርከዝ መናሩ ሱና፤ ለረጅም ጊዜያት በፅናትና በትጋት ሲማሩ የቆዩ፣ ቃዒዳ ኑራኒያን በአግባቡ ያጠናቀቁ እና ቁርኣንን በነዞር ያኸተሙ ውድ ተማሪዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ (#1) በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል።
በዚህ ታላቅ የኸይር እና የደስታ መድረክ ላይ እርሶም የክብር ተጋባዣችን ነዎት!
🎙 በዕለቱ በዳዕዋ እና በሙሀደራ የሚያደምቁን ውድ ኡስታዞቻችን፦
❶❶ ሸይኽ አወል ቢን አሕመድ (ከተመቻቸው)
❶ ኡስታዝ ኸዲር ቢን አሕመድ
➋ ኡስታዝ አሚር ቢን ሙሀመድ
➌ ኡስታዝ አብዱል መሊክ
➍ ኡስታዝ አቡ አዩብ
➎ ኡስታዝ አቡ ኢምራን
➏ ኡስታዝ አቡ ረያን
➐ ኡስታዝ አቡ ሉቅማን
➑ ኡስታዝ አቡ ሂባ
➒ ኡስታዝ አቡ ሀፍሷ
➓ ወንድም አቡ ማሒ
11,ወንድም አቡ ሹራ (እንዲሁም ሌሎች በርካታ ድንቅ ወንድሞቻችን የዕለቱ ድምቀቶች ይሆናሉ!)
🌟 የዕለቱ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች፦
●በተማሪዎች የሚቀርቡ ልብ የሚነኩ የቁርኣን ቂርኣቶችና ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች
●በኡስታዞች የሚሰጡ ጠቃሚና አነቃቂ የዳዕዋ መልእክቶች
●የተማሪዎች የምረቃና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት
📍 ቦታ፦ ከሚሴ በኢማሙ ሻፊዒይ መስጅድ
📅 ቀን፦ 01/ ነገ/ እሑድ
⏰ ሰዓት፦ ጠዋት 2፡30 ጀምሮ
🧕 ማስታወሻ፦ ለእናቶችና ለ እህቶች በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል።ኧረ ምን ምን ይቀርባል ካሉን! ቤተሰብዎንና ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው ይምጡ እና እዚያው ያዩታል ። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
~ ሃኪም እና ታማኝነት ~
~
አንድ ሃኪም / ሃኪም ቤት ሊታከም ለመጣ ሰው ታማኝ መሆን አለበት።
* የታካሚውን ሚስጥር ሊያወጣ አይፈቀድም። የታካሚውን ምስል ያለ ፈቃዱ ለሚዲያ ሊያቀርብ አይገባም።
* ከአቅሙ በላይ የሆነ ነገር ከገጠመው ወደተሻለ ቦታ መጠቆም እንጂ የሰውን ልጅ መለማመጃ ሊያደርግ አይፈቀድም። ከባድ ወንጀል ነው።
* ገንዘቡን ያላግባብ ሊያስወጣው አይፈቀድም። የሰው ገንዘብ ሐራም የሚሆነው በስርቆትና በዝርፊያ ብቻ አይደለም። ምርመራና መድሃኒት በማዘዝ፣ አስተኝቶ በማከም፣ በቀዶ ህክምና፣ በየትኛውም መንገድ ባልተገባ መልኩ የታካሚውን ገንዘብ ያስወጣ ሰው የሰው ገንዘብ እየዘረፈ ነው። ይህን ያደረገ ሰው እያንዳንዱ ሰው ገንዘቡን እንዴት እንዳመጣው እና በምን እንዳወጣው በሚጠየቅበት አስፈሪው የቂያማ ቀን ወዮለት። ዛሬ ያላግባብ ለተወሰደ ገንዘብ ሁሉ ነገ ጥብቅ ሂሳብ አለ። ብር በብር አይመለስም። ከመልካም ስራህ ነው ተላልፎ የሚሰጠው። እሱ ካልበቃ የተበዳይ ወንጀል ነው ባንተ ላይ የሚጣለው። ለማይረባ አላፊ ዱንያ ዘላለማዊ ህይወትን ከማጨለም መጠንቀቅ ይገባል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 30/2014)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from قناة الشيخ عبدالله النجمي
يجتمع في أهل البدع الجهل والهوى والتعصّب لباطلهم.
الشيخ عبدالله النجمي حفظه الله تعالى
☔️ለክረምት የሚነበቡ ምርጥ ኢስላሚክ ታሪክ ትፈልጋላችሁ⁉️
👇🏽ከስር ነክተው በምርጥ ታሪኮች ይደሰቱ👇🏽
😊ወላሒ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው😊
Repost from N/a
ኢስላማዊ ታሪኮች
ዲናዊ ምክሮች
የተለያዩ ዳዓዋዎችን
ቁርዓን እና ሀዲስ የምታገኙበት
🧩 ምርጥና ተወዳጅ ቻናል ✨
# ተቀላቀሉ ✅👇
https://t.me/+KXmTq2tJLzxjYzQ0
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢኽወቲ ወአኸዋቲ ፊ'ላህ!
~
አመለካከታችንም፣ ግንዛቤያችንም ስለሚለያይ የምፅፈው ሁሉ ለሁሉ ሰው ይስማማል ተብሎ አይታሰብም። የማንም የግል ፀሐፊ አይደለሁምና የማምንበትን እንጂ ሰው እንዳይከፋ እያልኩ እንደማልፅፍ ማሳወቅ አይጠበቅብኝም። ከዚህ በተቃራኒ፣ ሰው እንደመሆኔ ራሴን ማጥራራት ባልፈልግም፣ ማንንም ለማብሸቅና ለእልህ ከመፃፍም እጠነቀቃለሁ ብዬ አስባለሁ። መነገር አለበት ብዬ የማምንበትን ሃሳብ ሰዎችን እንደሚያስከፋ እያወቅኩም ለመናገር እሞክራለሁ። ይሄ አካሄዴ ለአንዳንዶቻችሁ እልህ፣ ለሌሎች የሒክማ ማጠር፣ ለሌሎች ደግሞ ከፋፋይነት ሊሆን ይችላል። የውስጤን አላህ ያውቃል። በኔ ቤት ለወገኔ ይበጃል የምለውን ማካፈሌ ነው።
የሆነ ሆኖ ሃሳቤ በቀጥታ በፅሁፌ የማሰፍረው ነው። የምደብቀውም የለኝም፣ የምደብቅበትም ምክንያት የለኝም። ይህን የምለው "በዚህ ንግግሩኮ ይህንን ነው የፈለገበት" አይነት ትንታኔ ስለሚገጥመኝ ነው። ተወገዘም፣ ተወደሰም የምፈልገው የፃፍኩትን ነው፣ አለቀ። ሌላ ትርጉም የምትሰጡ ሁሉ! ሆነ ብላችሁ አጣማችሁ ሳይሆን መስሏችሁ ብትሳሳቱብኝ ከየትኛውም ቡድን ብትሆኑ ዐፍው ብያለሁ። ሆነ ብሎ ንግግሬን አጣሞ በመተርጎም ለሚከሰኝ ደግሞ ሂሳባችን ከአላህ ዘንድ ነው።
እኔንም እናንተንም ልባችንን አላህ ለሐቅ ክፍት ያድርግልን። በሐቅ ላይም ይሰብስበን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
➥ይሔ ሠውየ የሚለንን እንስማ እስኪ
➥ እና ለምን ካፊር አትሉንም ይሉናል።
➥ካፊር አንላችሁም ምክንያቱም ተእዊል እየተጠቀማችሁ ነው ይላል
♦️♦️ያ ማለት በተእዊል ኡዝር እየሠጠ ስለሆነ ነው።
➥ከዛ ኢብን ዑሠይሚን መረጃ ያጣቅሳል
➥ኢብን ዑሠይሚን ኡዝር ቢል ጀህል አይሠጡም የሚሉትን ይተቻል.....የኪታቡን ስም ተናገሩ ቀውሉል ሙፊድን አንብቡ በሏቸው ይለናል
➥ሽርክ የሠራን ሠው ሙሽሪክ እንዳትለው ተንደርድረህ ይለናል.....አዳምጡት
...ንጉስ የሚሔድ ሠው ሙሽሪክ ነው ግን ፋጡማ ሙሽሪክ ናት ለማለት ሁጃ ቆሞባታል የሚለውን ማየት ያስፈልጋል...
➥ምሳሌ ቀብርን መጠየቅ ሽርክ ነው ግን የሆነ ሽርክ የሚሠራን ሠው ከሠማህ ሙሽሪክ ማለት አይፈቀድም እንደዚህ ነው አይቻልም........ታስተምረዋለህ ይላል...ጨርሱት
በደንብ ይደመጥ...
ይችን ሸር አድርጓትማ በሌላም ይቀጥላል👇👇
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin
https://t.me/al_irshad_studio_selefiyin
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መድ'ኸሊይ እንዳትሆን!
~
ሸይኽ ረቢዕ አልመድ'ኸሊይ - ረሒመሁላህ - እንደማንኛውም ዓሊም ናቸው። ይሄ ደረጃቸውን ዝቅ ማድረግ አይደለም። ከሳቸው የሚበልጡ ታላላቅ ዑለማኦችን በጭፍን መከተል አይፈቀድም ስንል ደረጃቸውን ዝቅ ማድረግ እንደማይሆነው ማለት ነው። ረቢዕ ልክ እንደሌሎቹ ዓሊሞች በየትኛውም ርእስ ላይ ቢሆን ፍፁም አይደሉም። በትንሽ በትልቁ በሸይኽ ረቢዕ ንግግር የሚያስፈራራ ቢኖር ራሱን ነው የሚሸውደው። ሱናን እከተላለሁ የሚል አካል በየትኛውም ዓሊም ላይ ያለው ምልከታ ለከት ሊኖረው ይገባል። አንድን ዓሊም መለኪያም፣ መስፈሪያም፣ መቁረጫም ማድረግ አይገባም። ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ አራጂሒይ - ሐፊዞሁላህ - የሌሎች ዓሊሞችን ንግግር ገሸሽ በማድረግ የሸይኽ ረቢዕን ንግግር በተለዬ የሚይዙ ስለሆኑ ሰዎች ሲጠየቁ እንዲህ ነበር ያሉት፦
يعني جعلوه رسولا، جعلوا ربيع رسولا، جعلوه رسولا، وهذا باطل، هذا باطل، ربيع ... يخطيء و يصيب و لا هو المييزان، الميزان: كلام الله و كلام الرسول، فمن قال: الميزان ربيع، هذا باطل.
"መልእክተኛ አደረጉት ማለት ነው?! ረቢዕን መልእክተኛ አደረጉት?! ይሄ ውድቅ ነው። ይሄ ውድቅ ነው። ረቢዕ ... ይስታል፣ ያገኛል። ሚዛን አይደለም። ሚዛኑ የአላህ ንግግር እና የመልእክተኛው ንግግር ነው። ሚዛኑ ረቢዕ ነው የሚል ይሄ ውድቅ ንግግር ነው።" [ከድምፅ ቅጅ የተወሰደ ነው።]
ስለዚህ የአልባኒይ፣ የኢብኑ ባዝ፣ የኢብኑ ዑሠይሚን፣ ወዘተ ንግግር በጭፍን እንደማይወሰደው የረቢዕ ንግግርም በጭፍን አይወሰድም። ረቢዕ በሌሎች መሻይኾች ላይ የሚናገሩትም በማስረጃ የተደገፈ ሲሆን ይወሰዳል፣ ካልሆነ ይጣላል። እንጂ ተናጋሪው ረቢዕ በመሆናቸው ብቻ ይወሰዳል ማለት አይደለም። አልባኒያ፣ ባዚያ፣ ዑሠይሚኒያ፣ ፈውዛኒያ፣ ... የሚባል መዝሀብ እንደሌለው መድ'ኸሊያ የሚባል መዝሀብም የለም። ስለዚህ አኢማዎችን በጭፍን የሚከተል ሐነፊይ፣ ማሊኪይ፣ ሻፊዒይ፣ ሐንበሊይ፣ ... መሆን እንደሌለብህ ሁሉ ረቢዕን በጭፍን የሚከተል መድ'ኸሊይ ልትሆንም አይገባም። እዚህ ላይ በቃል ደረጃ ችግር የለም። በተግባር ግን በተለያዩ መሻይኾች ላይ ድንበር ማለፍ ስላለ ጥንቃቄ እንዲኖረን ማስታወስ ነው የፈለግኩት። (ለጥጠው ሌላ ትርጉም ከሰጡ በኋላ በራሳቸው ምናብ ላይ ነብር ሆነው ለረድ የሚነሱ እንደሚኖሩ እጠብቃለሁ።)
በተረፈ የኢኽ'ዋን ጀሌዎች እዚህ እንዳትመጡ። የዚህ ፅሑፍ ጭብጥ በቅርብም በሩቅም ከናንተ ጋር የሚገናኝ አይደለም። የኢኽ'ዋን ቡድን ዘንድ የአንጃቸውን ጥመት ከተናገርክ፣ የነ ሐሰን አልበና፣ ሰይድ ቁጥብ፣ ቀርዷዊይ፣ ... ጥፉ አካሄዶች ካስጠነቀቅክ፣ ... በኢኽ'ዋን ቫይረስ በተጠቁ አካላት ዘንድ አንተ መድ'ኸሊይ ወይም ጃ'ሚይ ነህ። ልክ የሙታን አምልኮን፣ በአላህ ሲፋት ላይ ማራቆትን ስታወግዝ "ወሃ'ቢይ" እንደምትባለው ማለት ነው። ለነዚህ ሸይኽ ዒምራን ዐሊይ ሪድዋን አልፋሪሲይ - ረሒመሁላህ - እንዳሉት እንላለን፦
قُـلْ لِلَّذِي اتَّـخَـذَ الـتَّـجَـهُّـمَ مَـرْكَـبًـا
وَ رَآهُ دِيـنًـا و ارْتَــضَـاهُ مَـذْهَــــبًـا
وَ لِـمَـذهَبِ الأَبـــرَارِ صَارَ مُـكَـذِّبـًـا
إنْ كَانَ تَـابِـعُ أَحـمَــــدٍ مُـتَـوَهِّــبًـا *** فَـأَنـا الـمُــــقِـرُّ بِـأَ نَّـنِـي وَهَّـــابِي
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 17/2016)
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
«የሀገራችን ኢኽዋኖች ተከታታይ ፅሁፍ»
√ #ክፍል 04
|• «የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን አሉ?»
በክፍል አንድ ባሰማሁት የድምፅ ፋይል ሸይኽ ሙሐመድ ሓሚዲን «"ኢኽዋን ከአህለሱና ውጭ ነው የሚለው" ትክክል አይደለም።» ማለታቸው ይታወሳል። እናም ከዚህ ቀደም የሸይኽ ኢብኑ ባዝን እና የሸይኽ አልባኒን ንግግር እንዳቀረብኩትና ድምፃቸውንም እንዳሰማሁት ሁሉ ዛሬም በአላህ ፍቃድ ሌሎች የሱና ዑለማኦች ስለ ኢኽዋን ምን እንዳሉ እንመልከታለን። ከዚያም ሸይኹ የተናገሩት እውነት ወይስ ሀሰት የሚለውን በጋራ እናያለን ኢንሻአላህ።
3. ታላቁ ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ አልፈውዛን (ሐፊዘሁላሁ ተዓላ) ይጠየቃሉ፦
السائل: "نشأت كثير من الأحزاب والفرق التي مناهجها تختلف عن منهج أهل السنة والجماعة، وهناك الإخوان المسلمون والتبليغ، فنود من فضيلة الشيخ معرفة هل هم من الاثنين والسبعين الفرقة الضالة؟ علما أن الأذكان والمناهج التي يقومون بها لم تقم إلا على مشاكل وانقلبات."
ጠያቂ፦ "አካሄዳቸው ከአህለ ሱንና ወልጀማዓ መንገድ የሚለይ ብዙ አንጃዎችና የተለያዩ ቡድኖች ተፈጥረዋል። ከእነዚህም መካከል “ኢኽዋን አል-ሙስሊሙን” እና “ተብሊግ” ይገኛሉ። ከዚህ በመነሳት -እነሱ የቆሙበት መንሃጅ ችግሮችንና አደጋዎንች የሚያስከትል መሆኑን ከማወቃችን ባሻገር- የተከረበሩት ሸይኽ ሆይ፣ እነዚህ ቡድኖች ከሰባ ሁለቱ የጥመት ቡድኖች ውስጥ ይገባሉን? የሚለውን ጥያቄ ምላሽ ከእርስዎ ማወቅ እንፈልጋለን።"
جواب الشيخ: "يا إخواني، هذا بيَّنه الرسول ﷺ، لما ذكر أن أمته ستفترق على ثلاث وسبعين فرقة، قال: «كلها في النار إلا واحدة». قيل: من هي قال: «من كان على ما أنا عليه وأصحابي». فمن خالف منهج أهل السنة، الذي هو سنة الرسول ﷺ وأصحابه، فهو من الفرق المخالفة، ومتوعد بالنار، بأي اسم سُمِّي. سُمِّي من الإخوان، أو من التبليغ، أو من أي تسمية سُمِّي بها، من خالف منهج أهل السنة والجماعة فهو متوعد بالنار، وهو من الفرق المخالفة."
ሸይኹም እንዲህ መለሱ፦ “ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ነገር የአላህ መልእክተኛ ﷺ በግልጽ አብራርተውታል። እርሳቸውም የእርሳቸው ኡማ በሰባ ሦስት ቡድኖች እንደሚከፈል ሲገልጹ፣ ‘ሁሉም በእሳት ናቸው፣ አንዱ ብቻ እንጂ’ ብለዋል።
‘ያ አንዱ ቡድን ማነው?’ ተብለው ሲጠየቁ፣
‘እኔና ባልደረቦቼ ያለንበትን መንገድ የተከተለ ነው’ ብለዋል።
ስለዚህ፣ የአህሉ ሱንና መንገድን -ይህም የነቢዩ ﷺ እና የሶሐቦቻቸው ሱንና የሆነውን መንገድ- የሚቃረን ሰው፣ ከተቃራኒ ቡድኖች ውስጥ ነው፤ እንዲሁም በእሳት የተዛተበትም ነው። ይህም ሰው ራሱን በምንም አይነት ስም ቢጠራ ልዩነት የለውም። ‘ኢኽዋን’ ተብሎ ቢጠራ፣ ወይም ‘ተብሊግ’ ተብሎ ቢጠራ፣ ወይም በሌላ ስም ቢጠራ፣ የአህሉ ሱንና ወልጀማዓን መንገድ የሚቃረን ማንኛውም ሰው በእሳት የተዛተበት ነው፤ እናም ከተቃራኒ ቡድኖች ውስጥ ነው። አዎ።"
『• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። https://youtu.be/fkJzPTVmHuY?si=nrnjIHb6RlePTRuu
4. ታላቁ ሸይኽ ሷሊሕ አል'ሉሐይዳን (ረሒመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ ይላሉ፦
" الإخوان وجماعة التبليغ ليسوا من أهل المناهج الصحيحة فإن جميع الجماعات والتسميات ليس لها أصل في سلف هذه الأمة. ..." [فتاوى العلماء في الجماعات وأثرها على بلاد الحرمين: تسجيلات منهاج السنة السمعية بالرياض ]
«ኢኽዋንና ጀማዓቱ ተብሊግ ከትክክለኛ መንሃጅ ባለቤቶች አይደሉም፤ እነዚህ ቡድኖችና የተለያዩ የቡድን ስያሜዎችም የመጀመሪያዎቹ ሰለፎች ዘንድ መሠረት የላቸውም። ...»
『• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። https://ar.alnahj.net/audio/737?utm_source=chatgpt.com
5. ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዓብዱል ሙሕሲን አልዓባድ (ሐፊዘሁላሁ ተዓላ) ይጠየቃሉ፦
السائل: بسم الله الرحمن الرحيم، فضيلة الشيخ هناك جماعات محدثة. مثل جماعة الإخوان وجماعة التبليغ وغيرها هل هذه الجماعات من أهل السنة وما نصيحتكم حول هذا الموضوع؟
ጠያቂ፦ "በአላህ ስም እጀምራለሁ። የተከበሩ ሸይኽ ሆይ! እንደ ኢኽዋን እና ተብሊግ ያሉ አዳዲስ መጤ የሆኑ ጃማዓዎች አሉ። እነዚህ ጃማዓዎች ከአህሉስ-ሱና ወል-ጀማዓ ውስጥ ናቸውን? በዚህ ጉዳይ ላይ የምትሰጡን ምክር ምንድነው?"
جواب الشيخ: "... هذه الفرق المختلفة الجديدة أولاً هي مُحدثة ميلادها في القرن الرابع عشر، قبل القرن الرابع عشر ما كانت موجودة, هي في عالم الأموات و وُلدت في القرن الرابع عشر. أما المنهج القويم والصراط المستقيم فميلاده أو أصله من بعثة الرسول الكريم صلى الله عليه وسلم, ما كان عليه رسول الله صلى الله عليه وسلم وأصحابه من حين بعثته عليه الصلاة والسلام, فمن اقتدى بهذا الحق والهدى فهذا هو الذي سَلِمَ ونجى، ومن حاد عنه فإنه منحرف. ..."፧
ሸይኹ፦ "እነዚህ የተለያዩ አዳዲስ አንጃዎች፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም መጤ ናቸው። መነሻቸውም በ14ኛው ሂጅራ ክፍለ ዘመን ነው። ከ14ኛው ክፍለ ዘመን በፊት አልነበሩም። ሁሉም በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተፈበረኩ ናቸው።
ያማ ትክክለኛውና ቀጥተኛው መንገድወ መነሻው የነቢዩ ﷺ መልእክት ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ማለትም፣ ነቢዩ ﷺ ከተላኩበት ጊዜ ጀምሮ እርሳቸውና ሰሓቦቻቸው የነበሩበት መንገድ ነው።
ስለዚህ ይህንን እውነትና መመሪያ የተከተለ ሰው ከጥመት የጠራና የዳነ ነው፤ ከዚህ መንገድ የወጣ ግን እርሱ ጠማማ ነው።..."
ንግግራቸው ይቀጥላል በሌላ ጊዜ ሙሉውን የማሰፍረው ይሆናል ኢንሻአላህ።『• ይህንን ሊንክ በመጫን ንግግራቸውን ማድመጥ ይቻላል። https://ia601607.us.archive.org/0/items/AlhizbiyaWaIkhwaniya114/alhizbiya%20wa%20ikhwaniya%20%2894%29.mp3?utm_source=chatgpt.com
ውድ አንባቢያን "ኢኽዋን" ከሱና ውጭ መሆኑን በግልፅ የተናገሩ ዑለማኦች ቁጥር በጣም ብዙ ቢሆንም ሐቅን ለፈለገ ሰው የነዚህ ታላላቅ ዑለማኦች ንግግር ከበቂ በላይ ነው ብየ አስባለሁ። ከመሆኑም ጋር ግን ከዚህ ቀደም አቀርባለሁ ብየ ቃል ስለገባሁና ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንም በክፍል ሦስት ባሰማሁት ሪከርድ ላይ "ምንጊዜም ማስረጃ ነው እኛን ሊገዛን የሚገባው" ስላሉ ኢኽዋን ከሱና ውጭ የሆነባቸውን ነጥቦች ከማስረጃ ጋር በቀጣይ ክፍሎች የማቀርብ ይሆናል ኢንሻአላህ።
√ #ክፍል 03
t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3688
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from N/a
.
ጥያቄ
▬▭▬▭
ቁርዓን ውስጥ ስንት ምህራፎች አሉ ?
Repost from መርከዝ ሰልማን አል'ፋሪሲ የቂርአት ግሩፕ
أُمَّاهُ...
፡ እናቴ ሆይ...
لَوْ كَانَ عُمْرُكِ بِيَدِي لَزِدْتُهُ
፡ እድሜሽ በእኔ እጅ ቢሆን ኖሮ እጨምርልሽ ነበር።
وَلَكِنَّهُ بِيَدِ رَبِّي
፡ ነገር ግን (እድሜሽ) በጌታዬ እጅ ነው።
يا الله اِحمِ أُمِّي يا الله
፡ አላህ ሆይ! እናቴን ጠብቅልኝ አላህ ሆይ።
أُمَّاهُ...
፡ እናቴ ሆይ...
خُذِي مِنْ صِحَّتِي وَلاَ تَمْرَضِي
፡ ከጤናዬ ወስደሽ አትታመሚ።
خُذِي مِنْ رَاحَتِي وَلاَ تَتْعَبِي
፡ ከእረፍቴ ወስደሽ አትደክሚ።
خُذِي مِنْ بَسْمَتِي وَلاَ تَبْكِي
፡ ከሳቄ/ከፈገግታዬ ወስደሽ አታልቅሺ።
خُذِي مِنْ فَرْحَتِي وَلاَ تَحْزَنِي
፡ ከደስታዬ ወስደሽ አትዘኚ
ብናገኝም
ብናጣም
ጤና ብንሆንም
ብንታመምም
ከማመስገን ወደኋላ አንልም።
ما فعله الجليل
فهو جميل
الحمد لله
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
تلاوة صباحيَّة محبَّرة لسورة الكهف.
🎙الشيخ: بندر بليلة.
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
በውር ድንብሩ የሚጓዘው የለተሞው መንጋ መርከዝ ኢብኑ መስዑድ ያሉ ሰዎችን ሙብተዲዕ ባለማለታችን "ሙመይዕ" ቢሉንም እንደው እኛ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎችን "ሙብተዲዕ" ብንል እንኳን ከለተሞዎች አንድ የማያደርጉን ልዩነቶች አሉን።
Repost from 🔹قَناةُ أبي جُلَيبيب الأثري
በለተሞ መንጋ የምርቃና ስብከት ለተጠለፋችሁ ሁሉ!
~
1ኛ፦ እነዚህ ሰዎች የመንሀጅ ግንዛቤያቸው የተንሻፈፈ፣ የግል አመላቸውንና ሰለፊያን የሚያምታቱ ስለሆነ የሰለፊያን ግንዛቤ ከነዚህ ሰዎች አትውሰዱ። ይልቁንም ጊዜው የሚመች ነውና ከነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ፣ ... ኪታቦችና የድምፅ ቅጂዎች ተጠቀሙ። ከነሱም በላይ የቀደምት ዑለማዎችን አካሄድ በሚገባ ፈትሹ። እነዚህ ሰዎች ሰለፊያ ነው ብለው የሚያቀርቡላችሁ ከክፉ አመላቸውና ሸውራራ ግንዛቤያቸው ጋር የተቀላቀለ ቡድንተኛ አካሄድ ነው። የሱና ዑለማኦችን የሚያጣቅሱት ለሽፋን ያህል ነው።
2ኛ፦ ደዕዋችሁ የአካባቢያችሁን ተጨባጭ ያገናዘበ ይሁን። አዲስ ብሄርተኛ ይመስል መንሀጅ በተገነዘባችሁ ማግስት በትንሽ በትልቁ ሌሎች ጋር አትላተሙ። እነዚህ የሚያጋጯችሁ አካላት ከምትገቡበት አጣብቂኝ እንድትወጡ የሚያግዝ ይሄ ነው የሚባል ሃሳብ እንኳ ማቅረብ አይችሉም። እነሱ እንደሆኑ ለራሳቸው ጥቅም ሲሆን ካሜራ ውስጥ እንዳይገቡ እየተሹለከለኩ፣ ማስክ እያጠለቁ የሚጣዱ ናቸው። እነሱን ተከትላችሁ ደዕዋችሁ ቢሰናከል ብዙ ርቀት ወደ ኋላ ይመልሷችኋል።
3ኛ፦ ለፍረጃና ለተብዲዕ አትቸኩሉ። በቂ የመንሀጅ ግንዛቤ ያልያዘ ሰው ፈፅሞ ለተክ -ፊርና ለተብዲዕ ብቁ አይደለም። ነገሩ በሚገባ ተገልጦልናል ብላችሁ በምታምኑበት ጉዳይ ራሱ በመናገራችሁ የሚገኘውን ትርፍና ኪሳራ አስሉ። የደመ ነፍስ አካሄድ ማንንም አይጠቅምም።
4ኛ፦ የለተሞ ጭፍራዎች ጋር መጓዝ መስጂዶቻችሁን ያሳጣችኋል። ከማህበረሰብ ጋር ያጋጫችኋል። በሂደት ደዕዋችሁን ወይ ሙሉ ለሙሉ ያጠፋዋል። ወይ ደግሞ በእጅጉ ያቀጭጨዋል። ብዙ ካበላሻችሁ በኋላ ግራ ቀኝ አይታችሁ የተሻለ መስለሐ ያለበትን ውሳኔ ብትወስኑ ራሱ እነዚህ እባቦች ከማንም በላይ የሚናደፉት እናንተን ነው። የቻግኒው ሸይኽ ከማል አፍሪ ጉዳይ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል። ቀድመው በነዚህ አካላት የተሳሳተ አቅጣጫ ይዘው ነበር። አሁንም ምን ያህል እንደነቁ አላውቅም። የተሻለ መስለሐ አይተው መስጂድ ገብተው ሲያስተምሩ እድሜያቸውንም፣ ውለታቸውንም በማይመጥን መልኩ እያብጠለጠሏቸው ነው። "ያሳደጉት ውሻ፣ ያሳጣል መድረሻ!"
5ኛ፦ የአካባቢያችሁን መስለሐ ራሳችሁ ወስኑ። በሩቅ ያለ ሰው ያላችሁበትን ተጨባጭ ላያውቅ ይችላል። በተለይ እነዚህ ከህሊናቸው የተጣሉ አካላትን ፈፅሞ አታማክሩ። እንኳን ለናንተ ለራሳቸውም የሚሆኑ አይደሉም። አስፈላጊ ሲሆንና ከተቻላችሁ ዑለማኦችን አማክሩ። እነዚህ የሚጮሁትን የማይኖሩ ደናቁራን እንዳያሳስቷችሁ። ለተሞ በራሱ ምስክርነት ከ10 አመት በላይ ኢኽዋንን ሲያደንቅና አብሮ ሲጓዝ የኖረ ሰው ነው። አሁንም ከተወሰኑት ጋር ያፋጠጠው የጥቅም ግጭት ነው። እንጂ የጥቅም ቃል ሲገባለት እንኳን ከነዚህ ጋር ይቅርና ቀድሞ ተብዲዕ ካደረጋቸው ሰዎች ጋር ራሱ ሊታረቅ እልል ሲል ነበር። አሁንም የተሻለ ካየ ለሌላ ይፈርማል። ባህሩም ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሲል ለዲን ተቆርቁሮ አይደለም። የራሱ አንዱ ጋሻጃግሬ ከሚያወግዛቸው አካላት ጋር የመስጂድ ኮሚቴ አባል ነው። ኮሚቴው በመጅሊስ መዋቅር ስር እንደሆነ አስተውሉ። የባህርዳሩም ጭፍራ ዲን አይደለም ከመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ጋር ያፋጠጠው። "ለኛ የተላከ ኪታብ ወስደውብን ..." እያለ ነው የህፃን ለቅሶ የሚያለቅሰው። ራሳቸው በቡኻሪ መስጂድ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ፕሮግራም አስተዋውቀው ሲያበቁ እነዚህ ከህዝቡ ብር ሲሰበስቡ ጊዜ ጨርቃቸውን ጣሉ። በቀናት ልዩነት ውስጥ ተነስተው አስጠነቀቁ። ስሜታቸውን የማይቆጣጠሩ፣ ይሉኝታ የማያውቁ ጉዶች ናቸው። እንጂ ዛሬ ለተብዲዕ የሚመዙትን ጉዳይ እየጠቀሱ ተብዲዕ ግን አናደርግም ሲሉ እንደነበር የድምፅ መረጃ አለ።
6ኛ፦ በደዕዋ ላይ ተመዩዝ አስፈላጊ ነው። ተመዩዝ ማለት ግን በራስ ላይ በር ዘግቶ መጮህ አይደለም። ከሆነላችሁ ያለ ንክኪ አስተምሩ። መድረክ ካገኛችሁ አቋማችሁ የተጠበቀ እስከሆነ ድረስ በሱፊዮች መስጂድ እንኳ ቢሆን አስተምሩ። ታላላቅ መሻይኾች በሱፊያ መስጂዶች ያስተማሩበት ተጨባጭ አለ። ለምሳሌ ሸይኽ ረቢዕ ሱዳን ውስጥ በሱፊያ መስጂድ አስተምረዋል። "በአቋም ቢገናኙ ነው ከነ እንትና መስጂድ የሚያስተምሩት" የሚለው የነዚህ ሰዎች ጩኸት ዝቅ ቢል ድንቁርናቸውን ከፍ ቢል አታላይነታቸውን ነው የሚያሳየው። ለአመታት ሂዝቢዮች ላይ ቁጭ ብለው ሲማሩ ነው የኖሩት። ባህሩ፣ ሁሴን ሲልጢ እና ጠሀ ኸዲር ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። ራሳቸው የሳዑዲ ጃሚ0ዎች በሒዝቢዮች የተጥለቀለቁ እንደሆኑ ይገልፃሉ። ራሳቸው በንዲህ አይነት ተቋማት ቁጭ ብለው እየተማሩ እኛ ጋር መጥተው እንትናን ከእንትና ጋር አየነው እያሉ አድብተው ይጠብቃሉ።
በሰሜን ወሎ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ ዞኖች የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። ለተሞ በሚያብጠለጥላቸው የየመን መራኪዝ የሚማሩ የለተሞ መንጋዎች አሉ። የመን መዕበር ድረስ ሄደው ሙሐመድ አልኢማም ዘንድ የሚማሩ ሁሉ አሉ። እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐረብኛ ትምህርት በሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ሙመይዐ ከሚሏቸው እና ኢኽዋኒዮች ዘንድ ቁጭ ብለው የሚማሩ አሉ። ከዚህም የባሰ ሱፊዮች ዘንድ ሳይቀር ሉጋ የሚማሩ አሉ። ራሳቸው በሚሰሩት ጉዳይ ሌሎችን ተብዲዕ የሚያደርጉ የማፊያ ስብስብ ናቸው።
ጩኸታቸው የእውነት መስሏችሁ እነሱን የተከተላችሁ በጊዜ ብትነቁ ይሻላችኋል። ጥሪዬ በተለይ መሬት የረገጠ ደዕዋ ላላችሁ ነው። ደዕዋችሁን ሳታጡት በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
⚠️ ስሙ ጉድ :- የሙስጤን ውጤት "የዘራው ፍሬ ምን እንደሚል ።
🌟 አፍ ሲሰፋ :ሲንቦረቀቅ ጭቅላት ይጠባል።
ይሄ እ'storage ,"የለለው ባዶ ጭቅላትህ'" አጎል እንጂ ምንንም ነገር መሸከም አይችልም።
የዛሬው ጫን ያለ ነው
▫️ አዚሮች ሁሉ ካፊር ናቸው 😔
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
