قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
رفتن به کانال در Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
897
مشترکین
-124 ساعت
-157 روز
+2930 روز
آرشیو پست ها
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
قال ابن القيم -عن يوم الجمعة-: «وهو في الأيام كشهر رمضان في الشهور، وساعة الإجابة فيه كليلة القدر في رمضان.
ولهذا من صحَّ له يومُ جمعته وسلِمَ؛ سلِمَتْ له سائرُ جمعته.
ومن صحَّ له رمضانُ وسَلِم؛ صحَّت له سائرُ سَنته.
ومن صحَّت له حجَّته وسلِمَتْ؛ صحَّ له سائر عُمره.
فيومُ الجمعة ميزان الأسبوع،
ورمضانُ ميزان العام،
والحجُّ ميزان العمر».
«زاد المعاد» ٤٩٢/١
አላህ ሆይ!
እሰው ፊት ከመቆም፣የሰው እጅ ከማየት፣ጤናን ከማጣት አንተው ጠብቀን።
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
✍ [ سنن يوم الجمعة ]
قال فضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين - رحمه الله تعالى - :
➊ قراءة سورة الكهف .
➋ الإغتسال .
➌ السواك .
➍ الطيب .
➎ التبكير إليها، أن يبكر حين تطلع الشمس .
➏ أن يلبس الإنسان أحسن ثيابه التي عنده سواء كان جديداً أم غسيلاً .
➐ يتحرى الدعاء لأن في الجمعة ساعة لا يوافقها عبد مسلم يسأل الله شيئاً وهو قائم يصلي إلا أعطاه إياه .
➑ أن يكثر من الصلاة على النبي ﷺ .
( لقاء الباب المفتوح، 105).
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abulabas1444
t.me/Abulabas1444
Repost from Woldia University Muslim Students
የሙሐደራ ማስታወቂያ
ተጋባዥ እንግዶች፦
1. ኡስታዝ ኢብኑ መነወር
ርዕስ፦ { العذر بالجهل }
2. ዶ/ር ሰዒድ ሙሳ
ርዕስ፦ { التسرع في التبديع }
3. ዶ/ር ሑሰይን ዓሊ
ርዕስ፦ { خطر التعصب }
ፕሮግራሙ በአቡ ሂበቲላህ እና በአቡ ሐኒፋ የሚመራ ይሆናል።
የፊታችን ጁሙዓ ከምሽቱ 3:00pm በኢትዮ
አድራሻ፦ ዳሩ ተውሒድ
https://s.imoim.net/A6NRGx?from=copy_link
Repost from ብርሃን ፍለጋ{نور الهدى}
❌ ድንግል ያልሆነች ሴት አታግባ”❌
ግን ለምን ⁉️
በአሁኑ ወቅት በየሚዲያውና በየሶሻል ሚዲያው ሰልጥነናል በሚሉ፣ ነገር ግን የዕውቀትና የሃይማኖት ጠብታ በሌላቸው “ጃሂሎች” የሚነገሩ ቃላትንና የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን እንታዘባለን። ከእነዚህም መካከል ትልቁ ማስተዋያ አልባነታቸውን የሚያሳየው “ድንግል ያልሆነች ሴት አታግባ” እያሉ በሴቶች ክብር ላይ የሚቀልዱትና የማይገባቸውን ስም የሚለጥፉት አጉል ሰለጠንኩ ባዮች ናቸው።
እነዚህ አካላት ሊያውቁት የሚገባው ትልቅ እውነት አለ፦ ሴት ልጅ ማለት ከምንም በላይ በእስልምና ውስጥ ታላቅ ክብርና ቦታ የተሰጣት ውድ ፍጡር ናት!
💢 በቅድሚያ የነቢያችን (ﷺ) ህይወት እና የእስልምና ሚዛን ምን ይመስል ነበር የሚለውን እናያለን
እነዚህ አጉል ሰለጠንኩ ባዮች የንፅህና ሚዛናቸውን ከራሳቸው ጠባብ አስተሳሰብ ሲቀዱ፣ እስልምና ግን ንፅህናንና ክብርን የሚያየው ከልብ፣ ከአኽላቅ (መልካም ስነ-ምግባር) እና ከእምነት ጥንካሬ ነው።
ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች የዓለማቱ እዝነት የሆኑትን የነብያችንን (ﷺ) የትዳር ህይወት አያውቁትም?
የነቢያችን (ﷺ) የመጀመሪያ፣ ተወዳጅና የልባቸው ማረፊያ የነበሩት እናታችን ኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ድንግል አልነበሩም። ነገር ግን በታሪክ “ጧሂራህ” (ንፅህቷ) በሚል ስም የምትታወቅ፣ ነቢያችንን በገንዘቧ፣ በጉልበቷና በሃሳቧ የደገፈች ታላቅ ሴት ናት።
ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ውጭ የነቢያችን (ﷺ) ሚስቶች በሙሉ (የሙዕሚኖች እናቶች) ቀደም ሲል ትዳር የነበራቸው፣ የፈቱ ወይም ባሎቻቸው የሞቱባቸው ነበሩ።
⁉️ ታዲያ እነዚህ አጉል ሰለጠንኩ ባዮች ከነብዩ (ﷺ) በላይ ሊያስተምሩን ነውን? ድንግልናን ብቻ የሴት ልጅ ብቸኛ የክብር መለኪያ አድርጎ ማስቀመጥ የጃሂሊያ (የድንቁርና) ዘመን አስተሳሰብ እንጂ የስልጣኔ ምልክት አይደለም።
💢 ሌላው ደግሞ ሴት ልጅ በእስልምና ያላት የክብር ከፍታ ምን ይመሳላል⁉️
እስልምና ለሴት ልጅ የሰጣት ክብር ፍፁም ወደር የለውም። ሴት ልጅ በየደረጃው የጀነት መክፈቻ ቁልፍ ናት፦
● ልጅ ስትሆን፦ በጥሩ ሁኔታ ላሳደጋትና ላስተማራት አባት ለጀነት መግቢያ ሰበብ ናት።
● ሚስት ስትሆን፦ የባሏን ዲን (እምነት) ግማሽ የምታሟላ፣ የቤቱ ንግስት ናት።
● እናት ስትሆን ደግሞ፦ “ጀነት ከእናቶች እግር በታች ናት” ተብሎ የተነገረላት፣ የሰው ልጅ ሁሉ ሊያከብራትና ሊንከባከባት የሚገባ ታላቅ መድረክ ናት።
ሴት ልጅ በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች (በትዳር መፍረስ፣ በሞት ወይም በተለያዩ ፈተናዎች) ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች።
ይህ ማለት ግን ክብሯ ቀነሰ፣ ትዳር አይገባትም ማለት በፍጹም አይደለም!
👁🗨 ይልቁኑ በእስልምና መስፈርት ትልቁ ሚዛን ዲን (እምነት) እና መልካም ስነ-ምግባር ነው። ነቢያችን (ﷺ) በትዳር ጊዜ እንድንመርጥ ያዘዙን ባለዲኗን ሴት እንጂ ሌላ አይደለም።
ወንድሞቼ ሆይ! በሚዲያ ላይ በሚለቀቁ የድንቁርና መርዞች አትታለሉ። አንዲት ሴት መልካም ስነ-ምግባር ካላት፣ አላህን የምትፈራ ከሆነች፣ ለትዳሯ ታማኝና አፍቃሪ ከሆነች እሷ የአይን ማረፊያና የዱንያ ትልቁ ጸጋ ናት።
እህቶቻችን፣ እናቶቻችንና ሚስቶቻችን ሊከበሩ፣ ሊጠበቁና ሊወደዱ ይገባቸዋል። በምላሳችን የምንወረውረው ቃል ልባቸውን እንዳይሰብረው እንጠንቀቅ።
እውነተኛ ስልጣኔ የአላህን ዲን ማወቅ፣ የነብዩን (ﷺ) ሱና መከተልና ለሴቶች የሚገባውን ክብር መስጠት ብቻ ነው።
"ከናንተ መካከል ምርጡ ማለት ለሚስቱ (ለቤተሰቡ) መልካምና ገር የሆነው ነው!" — ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ)አላህ እውነተኛውን እውቀት ይስጠን፤ እህቶቻችንንም በኢስላም ጥላ ስር ክብራቸውን ጠብቆ ያኑርልን። አሚን። 👉✍𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓱𝓲 𝓲𝓫𝓷𝓾 𝓲𝓭𝓻𝓲𝓼 ሼር እያደረጋችሁ ተቀላቀሉ፣ትጠቀሙበታላችሁ https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega
Repost from የሰለፊዮች መገናኛ በሐይቅ ملتقى السلفيين في حيق
⚠️ አትናገረው ወይም አተግብረው!
ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ اللَّهَ تَجَاوَزَ لِأُمَّتِي عَمَّا وَسْوَسَتْ أَوْ حَدَّثَتْ بِهِ أَنْفُسَهَا، مَا لَمْ تَعْمَلْ بِهِ أَوْ تَكَلَّمْ﴾
“አላህ ለኡመቴ (ለሕዝቦቼ) በልባቸው ውስጥ የሚመላለሰውንና ነፍሳቸው የምታወራውን (መጥፎ ሃሳብ) ይቅር ብሏቸዋል። እስካልተገበሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6664
🟧🟧🟧🟧🟧🟧🟧
Repost from قناة أبي ماهر الأثري الحبشي𝐀bu Mahir )
أبرز صفات السلف الصالح ومنهجهم
السلف الصالح هم أهل القرون المفضلة الذين شهد لهم النبي ﷺ بالخيرية، وهم الصحابة والتابعون وأتباعهم بإحسان، الذين ساروا على كتاب الله وسنة رسوله ﷺ بفهمٍ صحيحٍ وعملٍ صادق.
ومن أعظم صفاتهم:
١- التمسك بالكتاب والسنة فكانوا يجعلون القرآن والسنة أصلَ كلِّ اعتقادٍ وعبادةٍ ومعاملة، لا يقدمون قول أحدٍ على كلام الله ورسوله ﷺ.
٢- فهم الدين بفهم الصحابة رضي الله عنهم فلم يكونوا يخترعون طرقًا جديدة في الدين، بل كانوا يحرصون على اتباع الطريق الذي سار عليه النبي ﷺ وأصحابه.
٣- تحقيق التوحيد والإخلاص كانوا يخلصون العبادة لله وحده، ويحذرون من الشرك والرياء وكل ما يفسد عبودية القلب لله تعالى.
٤- اتباع السنة والحذر من البدع كانوا يعظمون سنة النبي ﷺ، ويحذرون من كل أمرٍ محدثٍ في الدين يخالف هديه ﷺ.
٥- العلم والعمل لم يكن علمهم مجرد معلومات، بل كان علمًا يقود إلى العمل والخشية والتواضع، قال الله تعالى: ﴿إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ﴾ [فاطر: 28]
٦- الوسطية والاعتدال فهم بعيدون عن الغلو والتشدد، كما أنهم بعيدون عن التمييع والتفريط، يسيرون على الصراط المستقيم بلا إفراط ولا تفريط.
٧- تعظيم العلماء واحترام أهل العلم كانوا يعرفون لأهل العلم مكانتهم، ويرجعون إلى العلماء في النوازل والمسائل، مع بقاء الاتباع للدليل.
٨- التواضع وحسن الخلق فمع علمهم وفضلهم كانوا أشد الناس تواضعًا، ورحمةً بالخلق، وحسنًا في التعامل.
٩- الصبر والثبات على الحق كانوا يصبرون على الطاعة، وعن المعصية، وعلى ما يصيبهم في طريق الدعوة إلى الله.
١٠- سلامة القلوب كانوا يحرصون على طهارة قلوبهم من الحسد والكبر والبغضاء، ويحبون الخير للمسلمين.
١١- الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر بالحكمة كانوا يدعون إلى الله بعلمٍ ورحمةٍ وحكمة، لا بالجهل ولا بالظلم.
١٢- الخوف من الله ومحاسبة النفس كانوا يخافون من التقصير، ويجتهدون في إصلاح أنفسهم قبل الانشغال بعيوب الآخرين.
فهذه هي معالم طريق السلف الصالح: علمٌ صحيح، وعقيدةٌ سليمة، وعبادةٌ خالصة، واتباعٌ للسنة، وأخلاقٌ كريمة، واعتدالٌ في المنهج.
https://t.me/A2mnt
አይ ሞት!!
ቀን በቀን ሳናዉቀዉ ዕድሜያችን እየገፋ ወደ ሞት እየሄድን ነው፤ አንድ ቀን መድረሳችንም የማይቀር እውነት ነው። ዋናው የሚያሳስበን መቼ ነው የምንደርሰው ሳይሆን፣ «ከሞት በኋላ ምንድነው የሚጠብቀን?» የሚለው ጥያቄ ነው።
الْمَوْتُ بَابٌ وَكُلُّ النَّاسِ دَاخِلُهُ
فَلَيْتَ شِعْرِي بَعْدَ الْبَابِ مَا الدَّارُ؟
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abulabas1444
t.me/Abulabas1444
Repost from Dr. Seid Musa
✏️ [ ምስጋናን ችላ ማለት ]
ሳሊህ አድ'ዲማሽቂይ - አላህ ይዘንላቸውና - ልጃቸውን እንዲህ ሲሉ መከሩ፦ “ልጄ ሆይ! እምነትህ፣ ሰውነትህ፣ ሀብትህ እና ቤተሰብህ ደህና የሆኑበት ቀንና ሌሊት ካለፈ፣ ለጌታህ አላህ - ሱብሐነሁ ወተዓላ - ብዙ ምስጋናን አቅርብ። በዚያ ቀን ስንት እና ስንት ሰዎች እምነታቸውን አጥተዋል፣ ንብረታቸውን ተነጥቀዋል፣ ክብራቸው ተጎድሏል፣ ጀርባቸው ተሰብሮ፣ አንተ ግን በጥሩ ጤንነት ላይ ነህ። (ስለዚህ አላህን ተገቢ የሆነን ምስጋና አመስግነው)።”
[ የደማስቆ ታሪክ ቅጽ : 23 ገጽ : 325 ]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/AbulbukhariSeid
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
👉⭕️ለላጤወች አድርሱልኝ
🛡ለምን አታገባም⁉️🛡
አልሀምዱሊላሂ ሊመሊከል ቁዱስ
ሶመ ሶላቱሁ መዲነቲል አሩስ
ጌታችን በእዝነቱ ሀላልን ፈቀደ
አግብቶ መኖርን መውለድም ላቀደ
ያ ማእሸረ ሸባብ አሉና ጀግናችን
ለቻለ ሰው ብለው ጠርተው በስማችን
ያግባ እና ይጠንክር ከሀራም ይጠበቅ
ያልቻለ ሰው ይፁም በተቅዋ እንዲመጥቅ
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
በሌላም ዘገባ ኢማሙ ሷኢሚን
መክረዋል ወጣቱን ሙሀመዱል አሚን
ያገባ ሰውማ በሀላሉ መንገድ
ሸርጥ ሳያበዛ ሳይሄድ ወደ ፈሳድ
ከመለ ኒስፉሁ ተማሏ ኢማኑ
ፉል ይሆንለታል በአላህ የማመኑ
በግማሹ ደግሞ ከዚህ በተረፈ
አላህን ይፍራበት አመፅ በቀረፈ
አወ ኒካህ ማለት ሰበብ ነው ለሪዝቅህ
አግባና ፈልገው አላህ ይጠብቅህ
የነብያት ሱና ፈለግ ነው ጎዳና
ፀጋ ነው መከበር ደስታ የሰኪና
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
ሷሊህ ለወፈቀው ፀባይዋ ገራገር
በተውሂድ ተውባ አምራ ሳትበገር
ሰፈሯ ያደገች ወንዝ ሳትሻገር
ሽርክያት እርቃ ሳታልፍ ከድንበር
በሱና ያጌጠች ጃዳ ሰለፍያ
ፈና ፈኑን ያየች የቀራች ባልፍያ
የቢድአን ኮተት አንቅራ የተፋች
ቤቷ ቢሆንጂ በየ አደባባዩ ሽቶ ያልተቀባች
ኹራፋት ባጢልን በሩቅ ያወገዘች
ይዘወጅ በግዜ በወጣትነቱ
መጠኑ ሳይገፋ ደርሶ ለአንቱነቱ
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
አንተ ወንድሜ ሆይ መንሀጅ ያገናኘን
ጀሊል በራህመቱ ፀጋው ላይ ያናኘን
ጥያቄ አለኝ ላንተ ያው እየተያየን
በሳቅ በፈገግታ ጨዋታ እየቃኘን
ለምን አታገባም ምንድነው ሚስጥሩ
አግዶ የያዘህ የፍረሀት እጥሩ
ለምን አይፈታም ጥብቅህ ቁጥሩ
ምክንያት አታብዛ ጭራሽ አንግባባም
ሙስሊሙ ወንድሜ ለምን አታገባም
💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎
✍ ወንድም አቡ ሹራ Ahmed
ቻናሏን ጠቅ አርጓት👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4612
https://t.me/Sobabilalmesjid/4612
አዝነንም፣ተደስተንም፣አግኝተንም አጥተንም፣ከስረንም እንድሁም አትርፈንም.. ... ሁሌም አልሐምዱሊላህ!!!
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
✍ እናቱን ለሚወድ ብቻ
🎂ደርሰሽ ለጡረታ
የዘጠኝ ወር ቤቴ
ኑሪልኝ እናቴ
የደስታ ማጀቴ
ውስጤ ነሽ አንጀቴ
🍢 እማየ🍢
ችግር አይቅረብሽ ኑሪ በደስታ
ተፈጥሮሽ ልዩ ነው የጀሊል ስጦታ
ሀቅ፣ሽን መጠበቅ ዛሬ ላይ ብረታ
በእጀ ላንከባክብሽ ደርሰሽ ለጡረታ
⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤⛤
🎤 በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ካሳየ
ቻናሏን እናሳድጋት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
https://t.me/Sobabilalmesjid/4645
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
🌹 ፈገግ በሉልኝ 🌹
በበፊቱ ግዜ ነው ይባላል። ታሪኩ እናም አራት የገጠር ሰዎች በጀመዓ እየሰገዱ ነበር ከዛም ልክ ሩኩዕ ሲያረጉ አንዱ ወይኔ ወገቤን አለ ሁለተኛው ደሞ የወግብን ነገር አታንሳው ይለዋል። ንግግራችውን የሰማው ሶስተኛ ሰው ሶላት ላይ አይወራም ይላቸዋል ከሁሉም የባሰው አራተኛዉ አንተ ራስህ ሶላት ላይ አኮ ነህ ብሎት እርፍ
አውነተኛ ታሪክ የሆነ ነው።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሑሴን ባይኖር ኖሮ አላህም አይመለክ፣ ነብዩም አይታወቁም ነበር ይላል ይሄ ሺዒ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
إياكم والغلوَّ في الدينِ فإنما أهلَك مَن كان قبلَكم الغلوُّ في الدينِ
"በሃይማኖት ውስጥ ድንበር ማለፍን ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም ከእናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው በሃይማኖት ውስጥ ያለው ድንበር ማለፍ ነው።" [አን-ነሳኢይ፡ 3057]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ስለ ክብርህ ስትል ተዋቸው
~
የሰው ልጅ አመል እንደ መልኩ ብዙ አይነት ነው። ብዙ ደግ የመኖሩን ያህል በየትኛውም ሁኔታ መጥፎህን ብቻ ለማውራት ያሰፈሰፈ አለ። ልቡ በክፋት የተሞላ። በጎህን ሲያይ ይከፋዋል። ሰዎች በመልካም ቢያነሱህ ያመዋል። ያለ ስምህ ስም ይሰጥሃል። ያለ ግብርህ ያሸክምሃል። በሌለህበት ያውልሃል። ያለህን መልካም ይገፍሃል። ክፉህን ቢያይ ይቦርቃል። ሰዎች ቢያወግዙህ አታሞ ይመታል። ይቅርታህ አይዋጠውም። ዝምታህ አይጥመውም። ምላሽህም አይመቸውም። የቱንም ብታደርግ አታስደስተውም። ስህተት ቢያገኝ ጭራና ቀንድ አውጥቶለት ቆርጦ፣ ቀጣጥሎ ጭራቅ ያደርግሃል። ንግግርህን ፈፅሞ ባላሰብከው መልኩ ተርጉሞ ራሱ አጣሞ በተረዳው ላይ ተመርኩዞ ነብር ግስላ ሆኖ ይነሳብሃል።
በቃ! አንዳንዱ ባህሪው የውሻ አይነት ነው። ባለፍክ ባገደምክ ቁጥር ይጮሃል። "ዋው!" ማለትን የመተንፈስ ያህል ኖርማል አድርጎታል። ብትነካውም ይጮሃል። ብትተውም ይጮሃል። እንዲያውም ውሻ ሲያይህ ነው የሚጮኸው። ይሄኛው ሳያይህም ይጮሃል። "አትርሱኝ" ባይ ነገር ነው። በሌለህበትም፣ ሳታስታውሰውም ይጮሃል። በየትኛውም ሁኔታ ሊነድፍህ ስለተዘጋጀ ተያያዥ ጉዳይ እስከሚያገኝ አይታገስም። ይበላዋል። ያሳከዋል። ስለ ጦሃራ ስታወራ "ዋው!" ስለ ተውሒድ ስትናገር "ዋው!" ስለ ራስህ ብታነሳ "ዋው!" ራሱ የሚደግፈውን ሃሳብ ብታነሳም "ዋው!" ከማለት አይመለስም። ብትመልስለት አገር በጩኸት ያቀጣጥላል። ዝም ስትለውም ወይ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ወይ "አሸነፍኩ" ብሎ ይጮሃል።
እና ምን ይሻላል? ጩኸቱን ላታስቆመው ነገር አትጨነቅ። እርሳው። ሰላምህ ያለው እሱን ከመርሳት ነው። ሊፈትንህ ይችላል። ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ ግን የበለጠ ፈታኝ ነው። አሕመድ ሻኪር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
"የማያውቅ ሁሉ ይወቅ! ምድር ላይ ሞኞች ብዙ ናቸው። እና አንድ ሰው ከሞኝ ለሚንፀባረቅ ሞኝነት ሁሉ የሚበሳጭ ከሆነ በብስጭቱ ሰበብ ብሶት መከፋቱ ይራዘማል። ሞኞችን ያሻቸውን ይበሉ ተዋቸው። ለክብርህ ስስት ይኑርህ። ክብርህ ለሞኞች ምላስ ተብሎ የሚመነዘር ከመሆን በላይ ውድ ነውና።"
[መጅሙዑል መቃላት፡ 1/579]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (አቡ ሁዘይፋ)
