ብርሃን ፍለጋ{نور الهدى}
رفتن به کانال در Telegram
"በወንጀል ጨለማ ለዛለች ነፍስ፣ወደ አላህ ብርሃን የምታደርገው ጉዞ።ቀልብን የሚያርሱ ምክሮችና የንቃት ጥሪዎች።"የቀልብ ረፍትና የነፍስ ስንቅ ፍለጋ።ለማንኛውም ጥያቄ፣ አስተያየት ወይም ምክር እዚህ ያገኙናል፦ @BerhanFelega_Contact_bot
نمایش بیشترکشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
309
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
-130 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '260
در 0 کانالها
سپتامبر '26
+19
در 3 کانالها
Get PRO
اوت '26
+53
در 5 کانالها
Get PRO
ژوئیه '26
+76
در 12 کانالها
Get PRO
ژوئن '26
+17
در 6 کانالها
Get PRO
مه '26
+227
در 4 کانالها
Get PRO
آوریل '260
در 15 کانالها
Get PRO
مارس '26
+1
در 2 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 02 اکتبر | 0 | |||
| 01 اکتبر | 0 |
پستهای کانال
ቀኑን በሰላም አውሎ አሁን ላደረሰን አላህ ምስጋና ይገባው! አልሀምዱሊላህ።
"ቢስሚከ ረቢ ወዷዕቱ ጀንቢ ወቢከ አርፈዑህ..."
(ጌታዬ ሆይ! በስምህ ጎኔን አሳረፍኩ፤ በስምህም አነሳዋለሁ...)
ያረብ! በድካም ለዋሉት እረፍቱን፣ ለታመሙት ሽፋውን፣ ለተጨነቁት ፈረጃውን የምትለግስበት የተባረከ ምሽት አድርግልን።
🌟 መልካም ምሽት!
🔗 ሼር ያድርጉ ➪ @BerhanFelega
| 2 | 🔥 ቆፍጠን በል! በሐቅ ላይ አቋም ይኑርህ!
ወንድሜ ሆይ! ሃይማኖትና መንሐጅ የጨዋታ እቃ አይደሉም። ዛሬ ላይ ትልቁ ፈተና የዒልም ማነስ ብቻ ሳይሆን የጽናትና የአቋም መሸርሸር ነው።
ለሰው ብለህ አታዳላ፤ ለማንም ብለህ አትለሳለስ! ሐቅ አንድ ብቻ ናት—እሷም በነቢዩ ﷺ እና በሶሐቦች መንገድ (በሰለፎች አሰረ-ፍኖት) ላይ መጓዝ ብቻ ናት።
እዚያም እዚህም የምትለከሰከሰዉ እስከ መቼ ነው?
"ሰለፊይ ነኝ" እያልክ በቃላት እየተጫወትክ፡
በአንድ በኩል ከሐቅ መንገድ ጋር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አየር በነፈሰበት አቅጣጫ ከሚነዱት ጋር አብረህ አትወዝወዝ!
የሰዎችን ወገንተኝነትና ሙገሳ ፍለጋ ስትል ሐቅን አታደብዝዝ፤
ለሆድህ፣ ለስምህ ወይም ለጥቅምህ ብለህ የያዝከውን ቀጥተኛ መንሐጅ አትሸጥ!
ወንድ ከሆንክ በሐቅ ላይ ቆፍጠን በል!
የሰለፊያ መንገድ የጽናት መንገድ እንጂ የአጋጣሚዎች መጠቀሚያ አይደለም።
ዱኒያ አጫጭርና አታላይ ናት። ዛሬ በሰዎች ዘንድ ለመወደድ ብለህ የምታደርገው መለስለስና ማቻቻል፡ ነገ አላህ ፊት ሲቆም አንዳች አይጠቅምህም።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይላል፡
«በታዘዝከው ነገር ላይ ቀጥ በል!» (ሁድ፡ 112)
ተውሂድን ይዘሃል? ቀጥ በል!
ሱናን ጨብጠሃል? አትወዝወዝ!
ቢድዓንና ጥመትን ትተሃል? አትለሳለስ!
ሰው ቢደሰትም ቢጠላም፤ ዓለም ቢከተልህም ቢተውህም—አንተ ግን በሐቅ ላይ እንደ ተራራ ጸንተህ ቁም። ዱኒያ በቅርብ የምታልፍ ህልም ናት፤ አታላይ ሽንገላዋ አይዝጋህ።
ወንድሜ ሆይ! ራሰህን ፈትሽ… ዛሬውኑ አቋምህን አስተካክል!
@Abu_Mahi_Ibnu_Idris
@Abu_Mahi_Ibnu_Idris | 30 |
| 3 | 🍯 አዲስ እና ንፁህ የተፈጥሮ ማር ይፈልጋሉ? 🍯
ለጤናዎና ለቤተሰብዎ የሚሆን፣ ምንም አይነት ቅይጥ የሌለው፣ ተፈጥሯዊ ጣዕሙና መዓዛው እንደተጠበቀ የተቆረጠ አስተማማኝ ማር ይዘንልዎ መጥተናል።
✨ የእኛ ማር ልዩ የሚያደርገው፡
100% ተፈጥሯዊና ንፁህ ማር
ለጤና፣ ለምግብነት እና ለህክምና ተመራጭ
ጥራቱን የጠበቀና በተፎካካሪ ዋጋ የቀረበ
ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡
📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ]
➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy]
🚚 አሁኑኑ ይደውሉልን፤ ባሉበት ቦታ እናደርሳለን!
ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!
🔗 የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦
https://t.me/Al_Faiz_online_shopping | 45 |
| 4 | የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ልጆች
~
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ስድስት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ በድምሩ ሰባት ልጆች ነበሯቸው።
[ሀ] የ"ኣሉ ሸይኽ" (የሸይኽ ቤተሰብ) ዝርያ የቀጠለባቸው አራት ልጆች ናቸው።
ዛሬ ድረስ በሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ "እከሌ ኣሉ ሸይኽ" እየተባሉ የሚጠሩት የእሳቸው ዝርያዎች ናቸው። ይሄ የእሳቸው ዝርያ የቀጠለው በአራቱ ልጆቻቸው በኩል ሲሆን፣ ሁሉም ታላላቅ ዐሊሞችና ዳኞች ነበሩ። እነሱም፦
1. ሸይኽ ሑሰይን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦
ከአባታቸው በኋላ በዲርዒያህ ከተማ ውስጥ ዳኛ (ቃዲ) ሆነው አገልግለዋል። ታላቅ ዐሊም እና የዲርዒያህ መስጂድ ኢማም ነበሩ።
* ከእሳቸው የ"ኣሉ ሑሰይን" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ ተዘርግቷል።
2. ሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1224 ሂ.)፦
ከታላላቅ ዐሊሞችና ፀሐፊዎች አንዱ ነበሩ። ዲርዒያህ ውስጥ ቃዲ የነበሩ ሲሆን፣ ዲርዒያህ ከግብፅ በተነሳው የኦቶማን ቱርክ ጦር ስር ስትወድቅ ወደ ግብፅ ተወስደው እዚያው ሞተዋል።
* ከእሳቸው በኩል የ "ኣሉ ዐብዲላህ" (የሑሰይን ቤተሰብ) ቅርንጫፍ የተገኘ ሲሆን፣ "ተይሲሩል ዐዚዝል ሐሚድ" የተሰኘውን ታዋቂው የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁት ልጃቸው ሱለይማን ብኑ ዐብዲላህ ናቸው።
3. ሸይኽ ዐሊይ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1245 ሂ.)፦
ታላቅ የፊቅህ ዐሊምና አላህን ፈሪ ሰው ነበሩ። የዳኝነት ሹመት ቢቀርብላቸውም አልተቀበሉም።
* ሙሐመድ ከተሰኘው የእሳቸው ልጅ የ "ኣሉ ዐሊይ" ወይም "ኣሉ ሙሐመድ" ቅርንጫፍ ተገኝቷል።
4. ሸይኽ ሐሰን ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦
አባታቸው በሕይወት እያሉ ነው የሞቱት። ነገር ግን "ፈትሑል መጂድ" የተሰኘውን ታዋቂ የኪታቡ ተውሒድ ሸርሕ ያዘጋጁትን ልጃቸውን ዐብዱረሕማን ብኑ ሐሰንን ተክተው አልፈዋል። ከእሳቸው የ"ኣሉ ሐሰን" ቅርንጫፍ ተዘርግቷል።
[ለ] ሌሎች ልጆች (ዝርያ ያልቀጠለባቸው)
1. ሸይኽ ኢብራሂም ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ (1250 ሂ.)፦
እውቀት ያላቸው ዐሊም ነበሩ። በዲርዒያህ የማስተማሪያ ሐለቃህ ነበራቸው። በኋላም ወደ ግብፅ ሄደው እዚያ ነው የሞቱት።
2. ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦
በልጅነታቸው በአባታቸው የሕይወት ዘመን ነው የሞቱት።
3. ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ብኒ ዐብዲልወሃብ፦ የተከበረች ዐሊማ (የእውቀት ባለቤት) የነበረች ሲሆን ተማሪዎችን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተምሩ ነበር። ዲርዒያህ በኦቶማን ጦርነት በወደቀች ጊዜ ተሰዳ ቆይታ በመጨረሻም በሪያድ ከተማ ሞታለች።
አስተውሉ! ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ከአንድኛው በስተቀር ልጆቻቸውን በሙሉ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች ስም ነው የሰየሟቸው። ዐብዱላህ፣ ኢብራሂም እና ፋጢማ በቀጥታ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጆች ስም ሲሆን ሐሰን እና ሑሰይን ደግሞ የልጅ ልጆቻቸው ስም ነው። ዐሊይ ደግሞ የነብዩ ዐለይሂ ወሰለም የአጎት ልጅ እና አማቻቸው የሆነው የታላቁ ሶሐቢይ ስም ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor | 44 |
| 5 | ካላገባሃት ህይወቷን አታበላሽ!
በአንድ ሴት ልጅ ህይወት ውስጥ ከሁሉ በላይ ውድ የሆኑ ሶስት ነገሮች አሉ፡ ጊዜዋ፣ ንጹህ ስሜቷ እና የተስፋ ህልሟ። እነዚህን ነገሮች በምክንያት አልባ ቁማር የምትጫወትባቸው ከሆነ፥ ህይወቷን እየገደልካት እንደሆነ እወቀው።
ፍቅር ማለት የስሜት ማረፊያ እንጂ የጊዜ ማሳለፊያ አይደለም።
አንድን ሴት "እወድሻለሁ" ብለህ ወደ ህይወትህ ስታስገባ፥ የወደፊት ተስፋዋን፣ ውድ እድሜዋንና ሙሉ ልቧን በእጅህ ላይ እያስቀመጠች እንደሆነ አትዘንጋ።
ጊዜዋን አታባክንከእሷ ጋር የረጅም ጊዜ የወደፊት ህይወት የመገንባት እውነተኛ እቅድና ዝግጁነት ከሌለህ፥ ለዓመታት በአየር ላይ አንጠልጥለህ አታቆያት። የሴት ልጅ እድሜና እድል አይጠበቅም። አንተ ልብህን እስክታዘጋጅ ድረስ እሷ ከሌሎች እውነተኛ አላማ ካላቸው ሰዎች ጋር ልትመሰርት የምትችለውን ህይወት ታደናቅፍባታለህ።
በስሜቷ አትጫወት ዛሬ ደስ ሲልህ ቀርበህ፣ ነገ ደግሞ ሲሰለችህ ወይም ሌላ አማራጭ ስታገኝ በሩን ዘግተህ አትውጣ። ያቆሰልከው ልብ እና ያፈሰሰችው እንባ የወደፊት ሰላምህን እንደሚያጣው አትዘንጋ።
ውሳኔ ይኑርህ ወንድ ማለት ሀላፊነት የሚወስድ ነው! የምትፈልጋትን ሴት በፍቅር አጅበህ፣ በክብር ወደ ቤትህ የማስገባት ፍላጎትና ወንድነት ከሌለህ፥ ገና ከመጀመሪያው ከህይወቷ መንገድ ላይ ዞር በል።
የሰውን ልጅ ህይወት ሰብረህ፣ ህልሟን አጨልመህ እና የወደፊት ተስፋዋን አበላሽተህ በሰላም መኖር አትችልም።
"ያልዘራኸውን አታጭድም" እንደሚባለው ሁሉ፥ የዛሬው የእጅህ ስራ ነገ በህይወትህ መንገድ ላይ ይመጣብሃል።
ወንድ ከሆንክ ውሳኔ ይኑርህ፡ በክብር አግባት፣ ወይም በክብር መንገድዋን ልቀቅላት! ህይወቷን አታበላሽ!
ላኩላቸው ለእነዚያ.......
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris | 45 |
| 6 | قال الشيخ محمد ابن عبد الوهاب رحمه الله
"""رحم الله امرءا عرف قدر نفسه ووقف عند حده """
አላህ ይዘንላቸውና ሸይኽ ሙሃመድ ኢብኑ አብዲል ወሃብ እንዲህ ይላሉ """ አላህ ይዘንልት የራሱን ቀድር አውቆ ድንበሩ ላይ የቆመን ሰው"""" ይላሉ
ዛሬ በሶሻል ሚዲያ ዘመን ትልቁ ፈተናችን precisely የዚሁ ንግግር መጣስ ነው። ብዙዎቻችን ባልተማርንበት፣ እውቀቱ ባልተሰጠንና ባልመረመርነው ጉዳይ ሁሉ ላይ ፈታዋ ሰጪ፣ ተቺና ብይን አስተላላፊ ሆነናል—ሚዲያው ስለሰጠን መድረክና ስላገነነን ብቻ።
የራሱን አቅምና ደረጃ (ቀድር) ማወቅ፣ እንዲሁም የማያውቁትና የማይመለከቱት ነገር ላይ አፍን መሰብሰብ (ድንበር ላይ መቆም) ትልቅ ጥበብና ኢማን ነው። ሰሃቦችና ታላላቅ ኡለማኦች ለአንድ ፈትዋ ወይም የዲን ጥያቄ እንኳን እርስ በእርስ ይገፋፉና ይፈሩ የነበረውን ያህል፣ ዛሬ ግን ያለ እውቀት መናገር እንደ አርበኝነትና እንደ እውቀት በሚቆጠርበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን።
አላህ እውነተኛውን የእውቀትና የሂክማ መንገድ ይምራን፤ የራሳችንን አቅም አውቀን ድንበራችንን ከሚጠብቁትና አላህ ካዘነላቸው ባሮቹ ያድርገን።
https://t.me/BerhanFelega
https://t.me/BerhanFelega | 854 |
| 7 | ይህ የወንድማችን አቡ ማሒ የስራ ቻናል ነዉ
ሼር እያደረጉ ይቀላቀሉ
https://t.me/Al_Faiz_online_shopping
https://t.me/Al_Faiz_online_shopping | 95 |
| 8 | 🌸 ለሴቶች የቀረበ ድንቅ መፍትሔ! 🌸
የወር አበባ በሚመጣበት ጊዜ የሚሰማችሁን የማህፀን እና የሆድ ቁርጠት (Period Cramps) ሕመም በቃ ለማለት ዝግጁ ናችሁ?
ይህ ዘመናዊ እና ገመድ አልባ የወገብ እና የሆድ ማሳጅ የሕመም ስሜትን በፍጥነት ያስታግሳል!
✨ የመሳሪያው ልዩ ባህሪያት፦
➠ ሙቀት እና ንዝረት (Heating & Vibration): በሚሰጠው ስሙቅነት እና ቫይብሬሽን ሕመሙን ያቪዛል።
➠ ገመድ አልባ (Cordless): የትም ቦታ ይዘውት ለመንቀሳቀስ እና ለመጠቀም በጣም አመች ነው።
➠ 4 የንዝረት ደረጃዎች (4 Vibration Levels): እንደፍላጎትዎ ማስተካከል የሚያስችሉ 4 ደረጃዎች አሉት።
➠ የሙቀት መጠን መቆጣጠሪያ: የሙቀት መጠኑን (በሴንቲግሬድ) በመስኮቱ ላይ እያዩ ማስተካከል ያስችላል።
Type-C ቻርጀር: አብሮት በሚመጣው የ Type-C ቻርጀር በቀላሉ የሚሞላ።
🚚 ያሉበት ቦታ ድረስ እናደርሳለን!
ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡
📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ]
➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy]
📍 አድራሻ፡ [ወሎ ኮምቦልቻ/ደሴ]
✨ በፍጥነት ይዘዙ፣ ህመምዎን ያቅልሉ! | 94 |
| 9 | ሉምዐቱል ኢዕቲቃድ لمعة الاعتقاد.apk | 76 |
| 10 | بدون متن... | 85 |
| 11 | 🔥 የብዙ በሽታዎች ሰበብ የሆነው ድንቅ የማሳጅ ጫማ (Acupressure Massage Slippers)! 🦶✨
ቀንዎን ሙሉ በድካም፣ በእግር ወይም በጀርባ ህመም ያሳልፋሉ? የእንቅልፍ እጣትስ አስቸግሮዎታል?
ከእንግዲህ መፍትሄው በእጅዎ ነው! በቀን ከ 20 እስከ 30 ደቂቃ ብቻ በመጫማት ሙሉ ሰውነትዎን ዘና ያድርጉ።
💡 የዚህ ድንቅ ጫማ ጥቅም፦
✅ የደም ዝውውርን ያፋጥናል — የሰውነትን የደም ዝውውር በማስተካከል ቅልጥፍና እና ንቁነትን ያጎናፅፋል።
✅ ነርቮችን ያነቃቃል — በጫማው ላይ ያሉት 41 ልዩ አኩፓንቸር ነጥቦች (Springs) ከእግር ስር ያሉትን ዋና ዋና ነርቮች በማነቃቃት የሰውነት ክፍሎችን ስራ ያቃናሉ።
✅ ህመምና ድካምን ያስወግዳል — የእግር፣ የጀርባ፣ የጡንቻ መሸማቀቅ እና የመገጣጠሚያ ህመሞችን በፍጥነት ያስታግሳል።
✅ ጥሩ እንቅልፍ ይሰጣል — የአእምሮ ውጥረትን በመቀነስ ሰላማዊ እንቅልፍ እንድታገኙ ይረዳል።
ቤት ውስጥ እየተዟዟሩ ወይም ስራ ቦታ ላይ በቀላሉ በመጠቀም ለአካልዎ ሙሉ እረፍት እና ጤናን ይስጡ!
🛒 አሁኑኑ ይዘዙ፤ ለራስዎም ሆነ ለወላጆችዎ ምርጥ ስጦታ ነው!
ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡
📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ]
➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy]
📍 አድራሻ፡ [ወሎ ኮምቦልቻ/ደሴ]
✨ በፍጥነት ይዘዙ፣ ህመምዎን ያቅልሉ! ✨
ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!
🔗 የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦
https://t.me/Al_Faiz_online_shopping
🔏 የቴሌግራም ግሩፓችንን ሊንክ
https://t.me/Al_aaayaa | 96 |
| 12 | ቀጥታ ስርጭት!
◇ ሰይድ ቁጥብ ማን ነው?
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=abaae191d35c62b5f9 | 71 |
| 13 | «ጌታዬ አላህ ሆይ! ከ አንተ ውጭ ማን አለኝ?»
በጨለማና በጭንቅ ሰዓት ነፍሴ የምትረጋጋው፣ የሰው ሁሉ ደጅ ሲዘጋብኝ የሚከፈተው ያንተ ደጅ ብቻ ነው።
ሰዎች ችግሬን አያውቁም፤ ቢያውቁም እንኳን ሙሉ በሙሉ ሊረዱኝ ወይም ሊረዱኝ አይችሉም።
አንተ ግን ሳይነግሩህ የምታውቅ፣ ሳያዩህ የምትሰማ፣ የልቤን ስብራትና የውስጤን ብቸኝነት በአዛኝነተህ የምታክም ጌታዬ ነህ።
አለም ሁሉ ጀርባውን ቢሰጠኝ፣ ተስፋዎች ሁሉ ቢጨልሙብኝ እንኳን አንተ ከእኔ ጋር ካለህ ምንም አልጣሁም።
ልቤ በሀዘን ሲከብድ «እኔ ከአንተ ቅርብ ነኝ» የሚለው ያንተ ቃል ተስፋ ይሆንልኛል።
እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ «ያ አላህ» ስልህ፣ ይቅርታህና እዝነትህ ከእኔ ጥፋትና ጭንቀት እጅግ እንደሚበልጥ አስባለሁ።
እጅህን ወደ እርሱ ዘርጋ፣ የልብህን በሙሉ ለእርሱ ንገረው፤ አላህ የተሰበረን ልብ በከንቱ አይመልስም።
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris | 109 |
| 14 | 📢 መልካም ዜና ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ!
መርከዝ መናሩ-ሱና በኦንላይን (Online) የሚሰጣቸውን የቋሚ ኪታብና የተፍሲር ትምህርቶች ለመከታተል የሚፈልጉ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀምሯል።
ትምህርት ቤታችን በተፍሲር ዘርፍ የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎቹን የትምህርት ማረጋገጫ (ሸሀዳ) በመስጠት ያስመረቀ ሲሆን፣ በአቂዳ ዘርፍ ደግሞ ላለፉት 4 ዓመታት ሲማሩ የቆዩ ተማሪዎችን በአላህ ፈቃድ ከወር በኋላ የሚያስመርቅ ይሆናል።
በመሆኑም በዚህ የታላቅ እውቀት ማዕድ ላይ ባሉ የተወሰኑ ክፍት ቦታዎች ቀድመው እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል።
{የመምህራን እና የትምህርት መርሃ-ግብር መረጃ}
➠የተፍሲር ትምህርት፦ በሸይኽ አቡ አማር አወል ቢን አህመድ የሚሰጥ
➠የዐቂዳ ትምህርት፦ በአቡ ዑበይዳ የሚሰጥ
{የትምህርት ቀናት፦} ከጁሙዓ ውጭ በየቀኑ (ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ እርማት ያካተተ ነው)
{ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች}
◈ ቁርኣንን በነዞር (በምልከታ) ቀድሞ ያጠናቀቀ/ች
◈ ጥሩ አደብና ኢስላማዊ ሥነ-ሥርዓት የተላበሰ/ች
◈ ያለፈቃድ ከትምህርት የመቅረት ልማድ የሌለው/ላት
◈ የግሩፑን ደንብና መመሪያ በጥብቅ የሚያከብር/ የምታከብር
◈ ትምህርቱን በየቀኑ ሙራጃዐ (ክለሳ) እያደረገ/ች በጥራት የሚከታተል/ የምትከታተል
📲[ የምዝገባ አድራሻዎች]
●ለቁርኣን ተፍሲር ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Hawie71
● ለዐቂዳ ትምህርት ለመመዝገብ፦ @Ferst6335
ማስታወሻ፦ ቦታዎቹ ሳይሞሉ ቀድመው ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ! | 75 |
| 15 | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት
ሁለተኛው ፕሮግራም
ተ
ጀ
መ
ረ
ገባ ገባ በሉ ሸር ሸር አድርጉ
በኡስታዝ አቡ አዩብ ሀፊዘሁሏህ ተአላ
https://t.me/abuhaider_aliyy | 22 |
| 16 | ✨ ከስራ ደክሞዎት ቤት ሲገቡ የሚያስተንፍሱበት ምርጥ መፍትሔ! 💆♂️💆♀️
የአንገት፣ የጀርባ ወይም የወገብ ህመም እና ድካም ተሰምቶዎታል?
ይህንን ዘመናዊ የአንገት እና የሰውነት ማሳጀር (Neck & Body Massager) በመጠቀም ድካምዎን በአጭር ጊዜ ያስወግዱ!
🔥 ማሽኑን ልዩ የሚያደርጉት ባህሪያት፡
✅ የሙቀት ኤፌክት (Heat Function): ከማሳጁ ጋር ተያይዞ በሚሰጠው ሙቀት የደም ዝውውርን ያፋጥናል፣ የጡንቻ መወጠርን ያዝናናል።
✅ ብዙ አገልግሎት (Multi-functional): ለአንገት፣ ለወገብ፣ ለእግር እና ለሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚሆን።
✅ በቻርጅ የሚሰራ (Rechargeable): በቻርጅ የሚሰራ በመሆኑ የትም ቦታ ይዘውት ለመንቀሳቀስ ይመቻል።
✅ ለመጠቀም በጣም ቀላልና ምቹ!
💡 ለሁሉም የቤተሰብ አባል አስፈላጊ የሆነ ምርጥ እቃ!
🚚 ያሉበት ቦታ ድረስ በነፃ/በፍጥነት እናደርሳለን!
👉 ለማዘዝ አሁኑኑ ያነጋግሩን፡
📞 ስልክ፡ [09 12 89 98 94 ]
➠ቴሌግራም[@Abu_Meymuna_Al_Asseriy]
📍 አድራሻ፡ [ወሎ ኮምቦልቻ/ደሴ]
✨ በፍጥነት ይዘዙ፣ ህመምዎን ያቅልሉ! ✨
ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) ያድርጉ!
🔗 የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ፦
https://t.me/Al_Faiz_online_shopping
🔏 የቴሌግራም ግሩፓችንን ሊንክ
https://t.me/Al_aaayaa | 104 |
| 17 | እስኪ የላይክ challenge በሉ ለእህታችን ኡሙ ሓቲም እና ኡሙ ፈዉዛን ላይክ አድርጉቸዉ
👇👇👇👇👇
http://t.me/FKR_ESKE_JENET/13523
= t.me/FKR_ESKE_JENET/13513 | 95 |
| 18 | أَمْ يَحْسُدُونَ النَّاسَ عَلَىٰ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ
ይልቁንም ሰዎችን አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን።
የሰው ስኬት በአላህ ውሳኔ እንጂ በማንም ጥረት አይቀየርም። ዛሬ በምቀኝነትና በክፋት ሌሎችን ከመደገፍ የታቀበ ሰው፣ ነገ የራሱን መልካም ዕድልና እርዳታ ሊያጣ እንደሚችል ማስታወስ ይገባል። እባክዎታችሁ ልባችሁን አጽድታችሁ እና ከምቀኝነት ርቃችሁ በዚህ ሊክ በመግባት ላይክ አድርጉልኝ! 👇
https://t.me/FKR_ESKE_JENET/13605 አትርሱ 👍👍ብቻ
https://t.me/FKR_ESKE_JENET/13513 አትርሱ 👍👍 ብቻ | 105 |
| 19 | ጀዛኩሙላሁ ኸይረን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቅህ!
ይህ ማሳሰቢያ ለእያንዳንዳችን ትልቅ የንቅናቄ ደወል ነው።
በእውነትም ከሸይኽ ወይም ከኡስታዝ የሚቀሰመው ትምህርት የመነሻ ቁልፍ እንጂ የመጨረሻው ማጠቃለያ አይደለም።
ይህ ያነሳኸው ነጥብ የብዙዎቻችንን ሕመም የነካ፣ የእውቀት መንገድ (ጦለቡል ዒልም) ላይ ለሌለንም ላሉም ሰዎች ትልቅ የቤት ሥራ የሚሰጥ ድንቅ ማስታወሻ ነው።
የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ በጣም ያስደነግጣል! “አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አታነብም” የሚለው የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም ምላሽ ለእያንዳንዳችን የተላከ የግሳጼ መልእክት ነው።
ዛሬ እኛም በተመሳሳይ የፍለጋ እና የማንበብ ሰነፍነታችን ምክንያት በትንሽ በትልቁ የሰዎችን ጊዜ እያባከንን፣ የራሳችንን አእምሮ ከማንበብ እና ከማንቆርቆር አግደነዋል።
ኡስታዝ በሩን ይከፍትልናል፤ በሩን አልፈን የዒልሙን ማዕድ የምንጎበኘውና የምንመገበው ግን በራሳችን ጠንካራ የንባብና የጥናት ጥረት ነው።
የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ ታሪክ ደግሞ ጥገኛ የመሆንን አደጋና የራስን ጥረት አስፈላጊነት በግልጽ ያሳያል።
እንደ አላህ ፈቃድ፣ ያለፈው ዓመት የነበረንን ክፍተትና ድክመት አምነን በመቀበል፣ ከዚህ ቀንና ዓመት ጀምሮ ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለዒልምና ለንባብ ለመስጠት መጣር አለብን።
ወንድሞችና እህቶች! ሰነፍ መሆን የተፈጥሮ ግዴታችን አይደለም፤ ልማዳችን ነው፤ ልማድን ደግሞ በትግል መለወጥ ይቻላል። እውቀት በምኞትና በስነ-ስርዓት አልበኝነት አይገኝም።
የቀረበውን ምክር መነሻ በማድረግ ራሳችንን ለመለወጥ ተግባራዊ የሆነን እርምጃዎች መውሰድ ግድ ይለናል፦
የደርስ አጥባቂነት (ኢስቲቃማ)፦
በየቀኑ የምንከታተላቸውን የቂርአት ደርሶች ያለ ምክንያት አለማቋረጥና በሰዓቱ መገኘት። ደርስ ማቋረጥ የጅህልና መጀመሪያ ነው።
የቀን ተቀን የንባብ ፕሮግራም ማውጣት፦ "ጊዜ ሲኖረኝ አነባለሁ" የሚል ሰው ፈጽሞ አያነብም። ይልቁንም በቀን ቢያንስ ከ1 እስከ 2 ሰዓት ለግል ንባብና ሙራጃዐ (ክለሳ) የተወሰነ ቋሚ ጊዜ መመደብ።
ከጥራዝ ነጠቅነት መራቅ፦ አንድን ኪታብ ስንጀምር ከመጨረሻው ሳናደርስ ወደ ሌላ አለመሸጋገር። ኪታቦችን ከነሐሺያቸውና ከነሸርሃቸው በጥልቀት መመርመር።
ማስታወሻ መያዝ ፦ በምናነብበትና በምናጠናበት ጊዜ አዳዲስ ነጥቦችን፣ የዑለማዎችን ልዩነቶችና ማስረጃዎችን በደብተር ላይ ማስፈር።
የንባብ ባህልን ማዳበር፦ በትንሽ በትልቁ ሌላውን ሰው ከመጠየቅ በፊት፣ ራሳችን ኪታቦችን ገልጠን የመፈለግና የማጣራት ልምድ ማሳደግ።
የእውቀት መንገድ በትግል እና በሶብር እንጂ በምቾት እና በፍላጎት አይገኝም። ዛሬ ወጣትነታችንን በቲክቶክ ስክሪን ላይ ከምናጠፋው፣ ነገ ለአል-ኢስላምና ለኡምማው የሚጠቅሙ፣ ጥራዝ-ነጠቅ ያልሆኑ ባለሙሉ እውቀት ጧሊቦችን ለመሆን አሁኑኑ መነሳት አለብን።
ባለፈው ዓመት ያጣነውን ጊዜ አንመልሰውም፤ የዚህን ዓመት እድል ግን በቁርጠኝነት እና በማንበብ እንጠቀምበት!
አላህ እውነተኛና ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን፤ ከስንፍናም ይጠብቀን!
ወንድሞቼ! ይህንን መልእክት ለእናንተ ስጽፍላችሁ እኔ ከእናንተ በላይ አውቄ ወይም የበላይ ሆኜ አይደለም፤ ነገር ግን ኡስታዝ የላከው መልዕክት ልቤን ስለነካውና ለእኔም ለእናንተም ትልቅ ማስታወሻ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ነው:: አፉ በሉኝ፤ አላህ ሁላችንንም ወደ መልካሙ መንገድ ይመራን፣ ሰነፍነታችንንም አስወግዶ ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰን።"
«الرَّاجِي رَحْمَةَ رَبِّهِ، العَبْدُ الفَقِيرُ: أَبُو مَاحِي بْنُ إِدْرِيس»
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris | 102 |
| 20 | ባለፈው ዓመት ምን ያህል ኪታብ አንብባችኋል? በዚህስ ዓመት ምን አሰባችሁ? በተለይ የሸሪዐ እውቀትን በመማርና በማስተማር ላይ የተሰማራችሁ? የማያነብ ጧሊበል ዒልም ሊለወጥ አይችልም። የእውቀት ትጥቅ ለመታጠቅ፣ የግንዛቤ አድማስን ለማስፋት፣ ከጥራዝ ነጠቅ አስተሳሰብ ለመራቅ፣ የሌሎች ጭፍን ተከታይ ከመሆን ለመትረፍ ማንበብ ወሳኝ ነው። ከሸይኽ ወይም ኡስታዝ ላይ የምትማረው ላይ አትንጠልጠል። ማንም ቢሆን ሁሉን ኪታብ አይማርም። የፈለገ ቢሆን የምትማረው ውስጥ ነው። ከዚያ በኋላ ጥልቅ የሆነ የራስ ጥረት ያስፈልጋል። መሰረታዊ ነጥቦችን ከሸይኽ ከቀሰሙ በኋላ ሳይሰለቹ ማንበብ ያስፈልጋል።
ደግሞም መጠየቅ ጥሩ ቢሆንም በትንሽ በትልቁ ሰው ላይ ጥገኛ መሆን አይገባም። ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ጊዜ ከዳኞች አንዱ ወደ ክቡር አያቴ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም (አላህ ይዘንላቸውና) በፍርድ ቤት የዳኝነት ስራው ላይ ስለገጠመው አንድ ጉዳይ ብይን (ሑክም) ሊጠይቃቸው ደብዳቤ ጻፈ። ሸይኹም በሁለት መስመር ብቻ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦
'ይህ ጉዳይ በሁሉም የዑለማእ ኪታቦች ውስጥ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አትመረምርም (አታነብም)። ሰላም።' "
[ሙሂማቱን ፊ ጦለቢል ዒልም]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor | 76 |
