Usmanic Islamic psychology/ ስለ ሰው ልቡና
Ir al canal en Telegram
- ኢስላማዊ የስነልቦና ምክሮች ፣ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶችን ያገኛሉ። - እውነተኛ የህይወት ታሪኮች - ስለ ኢስላማዊ ሳይኮሎጂ ይማራሉ። - ሳምንታዊ ሽልማቶች ለሁሉም በማጋራት የሙስሊሙ ኡማ የአይምሮ ጤና የሚጠበቅበትን ይህን ቻናል እናሳድግ ጥያቄ ለማቅረብ እና አገልግሎት ለማግኘት ሳይኮሎጂስት ኡስማን ሙስጠፋን@usmanoman ላይ ያናግሩ።
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
1 026
Suscriptores
Sin datos24 horas
+107 días
+37430 días
Carga de datos en curso...
Canales Similares
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Nube de Etiquetas
Sin datos
¿Algún problema? Por favor, actualice la página o contacte a nuestro gerente de soporte.
Menciones Entrantes y Salientes
---
---
---
---
---
---
Atraer Suscriptores
octubre '26oct '26
octubre '26
+26
en 6 canales
septiembre '26
+505
en 10 canales
Get PRO
agosto '26
+530
en 11 canales
| Fecha | Crecimiento de Suscriptores | Menciones | Canales | |
| 11 octubre | 0 | |||
| 10 octubre | +2 | |||
| 09 octubre | +5 | |||
| 08 octubre | +2 | |||
| 07 octubre | +2 | |||
| 06 octubre | +7 | |||
| 05 octubre | +3 | |||
| 04 octubre | +2 | |||
| 03 octubre | +2 | |||
| 02 octubre | +1 | |||
| 01 octubre | 0 |
Publicaciones del Canal
ኢስላማዊ የማንነት መፈተሻ ቅፅ መሙያ ከኢስላሚክ ሳይኮሎጂ / Islamic Personality Assessment
ይህ በብዙ ምርምር የተቀረፀ የአኽላቅ/ስነምግባር እና እምነት መፈተሻ በቀላሉ ሞልተው ሰለራስዎ ብዙ ማወቅ ይቻላሉ።
100 ሰዎችን የመፈተሽ ቻሌንጅ።
ጥቅሞቹ
-ከአላህ ጋር ያለንን ቅርበት ይለካል የራሳችንን ችግር እንድንፈትሽ ይረዳል
- ያለንበትን የስብእና ጥራት ደረጃ ይለካል።
- ከውጤቱ በመነሳት የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
- ስለ ራሳችን በደንብ እንድናውቅ ያግዛል።
ፎርሙን ለመሙላት
👇ሰማያዊን ፅሁፍ ይንኩ
ራስን ለማወቅ
| 2 | የኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ አባል በመሆን የሚገኙ ጥቅማጥቅሞች
- የኡስማኒክ ሳይኮሎጂ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ ማግኘት
- የሚኖሩ ስልጠናዎችን በቅናሽ ወይም በነፃ ማግኘት
- ካውንስሊንጎችን/ኢስላሚክ የማማከር አገልግቶችን በቀነሰ ዋጋ መጠቀም
- በማዕከሉ የሚሰጡ ኮርሶችን እና ፈተናዎችን በቀነሰ ዋጋ እና በነፃ ተፈትኖ ሰርተፍኬት ማግኘት
- ብዙ ሰዎች የሚታገዙበትን ይህን ኢስላማዊ የስነልቦና ማዕከል በማገዝ የሚገኝ ስነልቦናዊ እርካታ እና አኼራዊ ጥቅም
ለጊዜው ይህ የአባልነት ውል በየ ሁለት ወሩ የሚታደስ ሲሆን አንድ አባል የሆነ ሰው ጊዜው ከማለቁ በፊት ምንም አገልግሎቶቹን ካልተጠቀመ ያልተጠቀማቸውን አገልግሎቶች ሁሌም መጠቀም የሚችል ይሆናል።
"አባል በመሆን አብሮነታችሁን አሳዩን"
ታላቅ ኡማ በመገንባት ጉዟችን ላይ አብራችሁን ሁኑ!
ከላይ ፖሉ ላይ አባል ለመሆን ቃል የገባችሁ ሰዎች እንዲሁም አባል በመሆን አብራችሁን መጓዝ የምትፈልጉ የአባልነት መመዝገቢያ ቅፅ እና ዲጂታል መታወቂያ ስላዘጋጀን @usmanoman ላይ አናግሩኝ።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ካሉ አሳውቃለሁ ኢንሻአላህ!
ጀዛኩሙለሁ ኸይረን!! | 1 |
| 3 | ማለዳችሁን በታላቅ ራእይ ሙሉት
اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ
"አላህ በአንተ (ፍቃድ) ወደ ንጋት ገባን ፥ በአንተም አመሸን በአንተም ህያው ሆንን ፥ በአንተም እንሞታለን ወደ አንተም ተመላሾች ነን።
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 246 |
| 4 | እስቲግፋር ማድረግ ከጭንቀት ይገላግላል | 292 |
| 5 | ኢስቲግፋር ማድረግ ከጭንቀት ይገላግላል | 1 |
| 6 | በአላህ መንገድ የተወዳጁ ሰዎች
#ሱህባ
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 292 |
| 7 | https://t.me/usmanic_psychology | 1 |
| 8 | ይህን ቻናል ብዙ ሰው ጋር እንዲዳረስ boost የሚለውን በመንካት አሳድጉት ተጨማሪ አገልግሎቶችን እና ጠቃሚ ነገሮችን እናቀርብላችኋለን። ኢንሻአላህ!
https://t.me/usmanic_psychology?boost | 278 |
| 9 | ጥያቄ 6
"በፀፀት ራሴን እየቀጣው ነው እባክህ መፍትሔ ካለው ከዚህ ስቃይ ታደገኝ"
አሰላሙአለይኩም ወንድሜ በቅድሚያ ጭንቀታችንን የምንገልፅበትንና መፍትሄ የምንፈልግበትን ቦታ/ማዕከል ስላዘጋጀህልን ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ....። ጥያቄዬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።
እኔ የ23 አመት ወጣት ስሆን በጣም በትኩስነት የአፍላ አስራዎቹ እና ሀያ መጀመሪያ እድሜዬ አካባቢ ፥ በቅጡ ሳላገናዝብ የፈፀምኳቸውን ተግባራት ሳስብ በራስ መበሳጨት ፀፀት እና ወቀሳ ይሰማኛል ይህም ልቆጣጣረው የማልችለው ራስን የመጥላት ስሜት ራሴን ለማጥፋት እንስካስብ ድረስ ይወስደኛል።
አንዳንዴም ራሴን በመጥላት በብዙ ነገር ነፍሴን እጎዳለው ምግብ ባለመብላት ፣ ራስን በመጣል እና ለራሴ ጥሩ ነገር ባለማድረግ ...ያኔ ትንሽ ራሴን የቀጣሁት ይመሰለኛል።
አሁን ላይ ተውበት አድርጌ ራሴንም የበደልኳቸውንም ሰዎች ይቅርታ ጠይቄ ነው ምኖረው ግን ከህሊና ቅጣት አሁንም አልዳንኩም። ይህ የፀፀት ስሜት ተወኝ ስል ያገረሽብኛል ረሳሁት ስል ትዝ ይለኛል። በአጠቃላይ ሙሉ እረፍት የለውም ህይወቴ ምን ትመክረኛለህ
ባለፈ መጥፎ ተግባሩ በፀፀት የሚቀጣ ወንድምህ ካለሁበት
አመሠግናለሁ !
(መልሱን በቅርቡ ይጠብቁ ኢንሻአላህ!)
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 315 |
| 10 | በዱአ እናንኳኳ!
ይከፈታል
ኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ | 305 |
| 11 | ከመልሶቻችን ማራኪ አንቀፆች
ያለፉ ታሪኮቻችን እና የልጅነት ዘመን ጠባሳዎች አሁን ላለን ስብእና እና ማንነት የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ ቢችሉም የሰው ልጅ ግን ገደብ በሌለው የመለወጥ እና የመታደስ (resiliency) አቅሙ ምክንያት ራሱን መስራት መቀየር እና ከትናንትና ህመሙ በላይ መሆን ይችላል። | 306 |
| 12 | እስካሁን በኡስማኒክ ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ ተጠይቀው ስነልቦናዊ መልስ እና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ፖስቶች። የመረጡትን በመንካት ታነቡ ዘንድ ጋበዝኳችሁ!
1, ጥያቄ 1 የ 31 አመት ሴት ስሆን እስካሁን የትዳርን ወግ አላየሁም።
ለ ጥያቄ 1 የተሰጠ መልስ
2, ጥያቄ 2 እኔ የ 27 አመት ወጣት ወንድ ነኝ።በአንድ አሳሳቢ ነገር ተለክፍያለው።
ለጥያቄ 2 መልስ ክፍል 1
ለጥያቄ 2 መልስ ክፍል 2
3, ጥያቄ 3 ቅናት እና ምቀኝነት ፈተነኝ!
የጥያቄ 3 መልስ - ክፍል 1
ለጥያቄ 3 መልስ -ክፍል 2
4, ጥያቄ 4 ትምህርቴን ልማር ወይስ ላቋርጥ?
ለ ጥያቄ 4 የተሰጠ መልስ
5, ጥያቄ 5 "የማልቆጣጠረው ብስጭት ብዙ ነገሬን አመሳቀለ።"
ለ ጥያቄ 5 የተሰጠ መልስ
ጥያቄ ለመላክ ወይም አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ይፃፉልን። | 415 |
| 13 | Sin texto... | 300 |
| 14 | #2 ሽልማት የሚያስገኝ ጥያቄ
በትከሻው ይሸከሙኛል ፥ መራመድ አልችልም መስጊዱን የሀዘን ድባብ ሞልቼው እወጣለሁ ፥ ሰዎች ምህረት አገኝ ዘንድ ይለምኑልኛል
እኔ ማን ነኝ?
ከላይ የተጠቀሰውን ጥያቄ ቀድሞ በትክክል ለመለሰ ሳምንታዊ የ 780 ሜ.ባ የኢንተርኔት ፖኬጅ ሽልማት ያገኛል።
#ከኡስማኒክ_ኢስላሚክ_ሳይኮሎጂ | 286 |
| 15 | እውነተኛ ታሪክ…
~
•ነገሩ እንድህ ነው…ከጥቂት ወራት በፊት ኸውለት በነፍሷ ውስጥ ትልቅ ባዶነት ይሰማት ነበር። ወደ ጌታዋ መቅረብ፣ ቁርኣን መቅራትና ዲኗን ማወቅ ተጠማች። በዚህ መሃል ነበር በአንድ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ "ኡስታዝ" ተብሎ የሚጠራውንና በጣፋጭ አንደበቱ ቁርኣን የሚቀራውን ያንን ወንድም ያወቀችው። የእሱ የድምፅ ቅላጼና ስለ አላህ ፍቅር የሚናገራቸው ቃላት የኢማኔ መጨመሪያ ይሆናል የሚል ተስፋ በውስጧ አሳደሩ።
መጀመሪያ ላይ «ኡስታዜ ይህን አንቀጽ አብራራልኝ» በሚል ጥያቄ ጀመረች። እሱም በክብር መለሰላት። ቀስ እያለ ግን ጥያቄው ከዲን ወጣና «ዛሬ ውሎሽ እንዴት ነበር?» ወደሚል የግል ትኩረት ተቀየረ። «እንደ አንቺ ያለች ጠንካራ እህት ማግኘት መታደል ነው» የሚሉ የማባበያ ቃላት በዲን ካባ ተጠቅልለው መምጣት ጀመሩ።
ኸውለት ሳታስበው በዚያ ሰው ፍቅር ወደቀች። አሁን ቂርኣኑን የምትከታተለው ለአላህ ብላ ሳይሆን የእሱን ድምፅ ለመስማት ሆነ። ሌሊት ቆማ ስትሰግድ አላህን ከመለመን ይልቅ የኡስታዙ መልዕክት በስልኳ ላይ "Typing..." የሚል ምልክት ማሳያውን በጉጉት መጠበቅ ጀመረች። ሐያእ ቀስ በቀስ ተገፈፈ። በመካከላቸው ያለው ወግ አጎል ቀልድ እና ክልክል የሆኑ የፍቅር ቃላት ወረሩት።
ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ግን አንድ እውነት ተገለጠ። ያ "ኡስታዝ" የተባለው ሰው ለኸውለት የነበረው ፍላጎት በዲን ስም ስሜቱን ማርካት እንጂ እሷን ወደ አላህ ማቅረብ አልነበረም። እሷ ግን ልቧን ሰጥታዋለች። በሄደችበት ሁሉ እሱን ታስባለች። የቁርኣኑ ጥፍጥና ጠፋባት። ልቧ ደረቀ። ሶላቷ ላይ ትኩረት አጣች። የነፍሷ ሰላም ተናወጠ።
በመጨረሻም ያ የጠበቀችው ትዳር ሳይሆን መገለል ሆነ። ኡስታዝ ተብዮው ካለበት ቻናል እና ግሩፕ ጠቅላላ ወጣች። ያ ኡስታዝ ሌላ አዲስ ተማሪ አገኘና እሷን እንደ አሮጌ እቃ ወረወራት። ኸውለት ዛሬ ብቸኛ ናት።
በአንድ ወቅት ወደ አላህ ያቀርበኛል ብላ ያሰበችው ሰው፣ ዛሬ ከጌታዋ ያራቃት ትልቁ ሰበብ ሆነ። እንባዋ አይደርቅም፤ አበጃለሁ ባይ አጥፊ ገጠማት።ኸውለት ግን ከበፊቱ አሁን ላይ በ ኢማኗ በጣም ጥሩ ላይ ነች።ጠንክራለች። ቁርኣንም መሐፍዝ ጀምራ 15 ጁዝ ላይ ደርሳለች። ኸውለት… ታሪኳን እዚህ ላይ ላቁመው።
ልብሽን ጠብቂ፤ እሱ የአላህ ቤት ነውና!
©️/መንቁል | 304 |
| 16 | እውነተኛ ታሪክ…
~
•ነገሩ እንድህ ነው…ከጥቂት ወራት በፊት ኸውለት በነፍሷ ውስጥ ትልቅ ባዶነት ይሰማት ነበር። ወደ ጌታዋ መቅረብ፣ ቁርኣን መቅራትና ዲኗን ማወቅ ተጠማች። በዚህ መሃል ነበር በአንድ የቴሌግራም ግሩፕ ላይ "ኡስታዝ" ተብሎ የሚጠራውንና በጣፋጭ አንደበቱ ቁርኣን የሚቀራውን ያንን ወንድም ያወቀችው። የእሱ የድምፅ ቅላጼና ስለ አላህ ፍቅር የሚናገራቸው ቃላት የኢማኔ መጨመሪያ ይሆናል የሚል ተስፋ በውስጧ አሳደሩ።
መጀመሪያ ላይ «ኡስታዜ ይህን አንቀጽ አብራራልኝ» በሚል ጥያቄ ጀመረች። እሱም በክብር መለሰላት። ቀስ እያለ ግን ጥያቄው ከዲን ወጣና «ዛሬ ውሎሽ እንዴት ነበር?» ወደሚል የግል ትኩረት ተቀየረ። «እንደ አንቺ ያለች ጠንካራ እህት ማግኘት መታደል ነው» የሚሉ የማባበያ ቃላት በዲን ካባ ተጠቅልለው መምጣት ጀመሩ።
ኸውለት ሳታስበው በዚያ ሰው ፍቅር ወደቀች። አሁን ቂርኣኑን የምትከታተለው ለአላህ ብላ ሳይሆን የእሱን ድምፅ ለመስማት ሆነ። ሌሊት ቆማ ስትሰግድ አላህን ከመለመን ይልቅ የኡስታዙ መልዕክት በስልኳ ላይ "Typing..." የሚል ምልክት ማሳያውን በጉጉት መጠበቅ ጀመረች። ሐያእ ቀስ በቀስ ተገፈፈ። በመካከላቸው ያለው ወግ አጎል ቀልድ እና ክልክል የሆኑ የፍቅር ቃላት ወረሩት።
ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ግን አንድ እውነት ተገለጠ። ያ "ኡስታዝ" የተባለው ሰው ለኸውለት የነበረው ፍላጎት በዲን ስም ስሜቱን ማርካት እንጂ እሷን ወደ አላህ ማቅረብ አልነበረም። እሷ ግን ልቧን ሰጥታዋለች። በሄደችበት ሁሉ እሱን ታስባለች። የቁርኣኑ ጥፍጥና ጠፋባት። ልቧ ደረቀ። ሶላቷ ላይ ትኩረት አጣች። የነፍሷ ሰላም ተናወጠ።
በመጨረሻም ያ የጠበቀችው ትዳር ሳይሆን መገለል ሆነ። ኡስታዝ ተብዮው ካለበት ቻናል እና ግሩፕ ጠቅላላ ወጣች። ያ ኡስታዝ ሌላ አዲስ ተማሪ አገኘና እሷን እንደ አሮጌ እቃ ወረወራት። ኸውለት ዛሬ ብቸኛ ናት።
በአንድ ወቅት ወደ አላህ ያቀርበኛል ብላ ያሰበችው ሰው፣ ዛሬ ከጌታዋ ያራቃት ትልቁ ሰበብ ሆነ። እንባዋ አይደርቅም፤ አበጃለሁ ባይ አጥፊ ገጠማት።ኸውለት ግን ከበፊቱ አሁን ላይ በ ኢማኗ በጣም ጥሩ ላይ ነች።ጠንክራለች። ቁርኣንም መሐፍዝ ጀምራ 15 ጁዝ ላይ ደርሳለች። ኸውለት… ታሪኳን እዚህ ላይ ላቁመው።
ልብሽን ጠብቂ፤ እሱ የአላህ ቤት ነውና!
©️/መንቁል | 1 |
| 17 | "ፊታቸው በፈገግታ የተሞሸረ ለተመለከታቸው በሙሉ ደስታን የሚያጋባ የሀሴት ድግስ ነው። በትህትና የተቀመረ የማማር አክሊልል ደፍተዋል ፣ በነቢይነት ስክነት ሞገስ እና በሰውነት ጨዋ ማንነት ገፃቸው የረጋ ነው...።"
መሰል ውብ አንቀፆችን ስለ ውዱ (ﷺ) ነብይ የሚያገኙበትን 'ፍፁም ነብይ ፍፁም ሰው' መፅሐፍ በመግዛት ከመልእክተኛው ጋር በጥልቀት እና በውበት ይተዋወቁ።
ርእስ= ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ
ፀሀፊ = ኡስማን ሙስጠፋ
የህትመት ጊዜ= ነሀሴ 2015 ዓ.ል
መፅሐፉን ለማግኘት በቴሌግራም ዩዘርኔም @usmanoman ወይም በስልክ 0921390122/ 0912027023 ላይ ያናግሩን | 331 |
| 18 | ኢስላማዊ የህይወት ቀመር የግል የኦንላይን ምክክር እና የስልጠና ሰአት
(በብዙ በሰዎች ጥያቄ ምክንያት የተጀመረ አገልግሎት)
ርእሶቹ የሚያካትቱት
- ካለፈው የህይወት ጠባሳ እና ህመም ( trauma) በመዳን ሰላም እና ደስታ ያለው ኢስላማዊ ህይወት እንዴት እንምራ?
- ተሰጥኦን በማወቅ የህይወት ግብን የመለየት እና አላማ ያለው ኢስላማዊ የሁለት አለም ስኬት የሚያቀዳጅ ህይወት እንዴት እንኑር?
- ኢስላማዊ ቤተሰባዊ ህይወትን እንዴት እንገንባ
ከሱስ፣ ከመጥፎ ልማድ እና አመል እንዴት እንውጣ?ሌሎችም ....የተካተቱበት የግል እና የቡድን የስነልቦና ትምህርት እና ስልጠና
ለመመዝገብ @usmanoman | 329 |
| 19 | ኢማን እንደ መስታወት | 316 |
| 20 | ለ ጥያቄ 5 የተሰጠ ስነልቦናዊ ምላሽ
"የማልቆጣጠረው ብስጭት ብዙ ነገሬን አመሳቀለ ምን ትመክረኛለህ?
መልስ
ጠያቂያችን እንደገለፀችው ችላ በመባል አስተዳደግ በተፈጠረ የልጅነት ልብ ስብራት እና አሁን ደግሞ ብስጩነት በወለደው የህይወት ምስቅልቅል መሀከል ላይ ትገኛለች።
ስለ አስተዳደግ ከተነሳ አይቀር ስለ 'አሰተዳደግ አይነቶች' በቀጣይ ፅሁፍ የምናይ ሲሆን (ኢንሻአላህ) እህታችን እንደገለፀችው 'የተተወ ልጅ'ነት' (neglected childhood) የሚለው የአስተዳደግ አይነት ውስጥ እንዳደጉ ገልፀዋል።
ይህ የአስተዳደግ አይነት ምን አይነት ሰው ያፈራል?
በዚህ የአስተዳደግ ጥላ ውስጥ ያለፉ ሰዎች (ሁሉም ባይሆኑም) በቀጣይ ህይወታቸው ላይ ጤናማ የሆነ ግንኙነትን ከሰው ጋር ለመፍጠር ይቸገራሉ ፣ በራስ መተማመንን ማጣት እና ስሜታቸውን የማስተዳደር ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል።
በተጨማሪም:- የፍቅር ረሀብ ፣ ትኩረት መፈለግ፣ ፀበኝነት ፣ብስጩነት ፥ መሰል የተዛቡ የስሜት እና የማንነት ቀውሶችን ሊያዳብሩ ይችላሉ።(ይህ ችግር እገዛ ካገኘ እና በንቃት ከተከታተሉት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል)
ጠያቂያችን አሁን ትልቁ ችግሯ ልትቆጣጠረው ያልቻለችው ብስጭት መሆኑን አምና እሱንም ለመለወጥም መፈለጓ ትልቁ የመፍትሔው አንድ እርምጃ ነው።
የአሁኑ ኑሮዋንም አላህ በማመስገን የተሻለ መሆኑን ገልፃለች። ይህም ጥሩ የመለወጥ መደላድል ያለው የህይወት መልካም አጋጣሚ ላይ እንደምትገኝ ያሳያል።
እህታችን አሁን ያለባት ብስጭት ሙሉ መሠረቱ ልጅነቷ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም። ይህን መሠል ድምዳሜ ላይ መድረስ ምን አልባት ሀላፊነትን ላለመውሰድ እና አሁን እየሆኑ ያሉ ነገሮችን በሙሉ የሆነ አካል ላይ ለመደፍደፍ መንስኤ በመሆን ላለመለወጥ ትልቅ ሰበብ ሊሆን ይችላል።
ያለፉ ታሪኮቻችን እና የልጅነት ዘመን ጠባሳዎች አሁን ላለን ስብእና እና ማንነት የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ ቢችሉም የሰው ልጅ ግን ገደብ በሌለው የመለወጥ እና የመታደስ (resiliency) አቅሙ ምክንያት ራሱን መስራት መቀየር እና ከትናንትና ህመሙ በላይ መሆን ይችላል።
ይህ ሲባል ያለፉ ኑሯችን መንገድ ላይ ያጋጠሙንን ህመሞች ፣ ጥቃቾች ወይም የልብ ስብራቶች ከድነን በማፈን አይናችንን ጨፍነን እንዳልነበሩ እናስመስል ማለት አይደለም።
በትክክል ያለፈውን ጉዳት መለየት ሀዘናችንን እና ያልፍንበትን በማወቅ ራስን እና በደል አደረሱብን የምንላቸውን ሰዎች ይቅር ማለት እና ያለፈውን የህይወት ክፍልን ምዕራፍ መዝጋት ወይም መደምደሚያ (closure) ማበጀት ወደ ፊት ለመራመድ ትልቅ የመፈንጠሪያ ሀይል እና የህሊና እረፍት ይሰጣል።
እንደአስፈላጊነቱ ደግሞ ከባለሙያ (ከሙስሊም) ጋር መነጋገር ጠቃሚነቱ የጎላ ሊሆን ይችላል።
የጠያቂያችን ብስጩነት መጠኑን አልፎ ህይወቷን እስኪያናጋው ድረስ ከሄደ ከመደበኛው እና ተፈጥሯዊ የሆነ የመበሳጨት እርከን የተሻገረ የንዴት ባህሪ አለ የሚለውን ያመለክተናል።
እህታችን ከልጅነታቸው ጋር ያያዙት አሁን ላይ ያጋጠማቸው የብስጩነት መንስኤ መኖሩ ምን አልባት በልጅነታቸው ችላ በመባል ምክንያት እውቅና ያጣው የመደመጥ እና ሀሳብን እና ስሜትን የመግለፅ ውስጣዊ ፍላጎት የሚያዳምጠው አካል ሲያገኝ ራሱን እየገለፀ ሊሆን ይችላል የሚል መላምት አለኝ።
ግን ከዚህ ውጪ የሆነው ብስጭትን የመቆጣጠር እና ራስን የመግዛት ባህሪ ሁሌም ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት መረሳት የለበትም። መጠነኛ የሆነ ሀሳብን እና ንዴት የመግለጽ ባህሪ ተፈጥሯዊነቱ ሳይረሳ።
በመጨረሻም የዘመኑ ሳይንስ እና ኢስላሚክ ሳይኮሎጂ መፍትሔ የሚለውን የብስጭት መቆጣጠሪያ መንገዶች ለእህታችን በመጠቆም ለዛሬ ሀሳቤን በዚሁ አጠቃልላው።
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በታዋቂ ሀዲሳቸው 'ጀግና ማለት ብስጭቱን የሚገታ ነው' ሲሉ በሌላኛው ለብስጭት መፍትሄ ያሉት ሀዲስ ላይ ደግሞ 'አንድ ሰው ሲበሳጭ ቁሞ ከነበር ይቀመጥ ከተቀመጠ ይጋደም ይህም ለሱ ብስጭቱን ለመቀነስ መፍትሔ ይሆናል' ብለዋል።ሌላኛው መፍትሔ ውዱእ ማድረግ ነው።
የዘመኑ ሳይኮሎጂ የብስጭት መቆጣጠሪያዎች (anger management) ብሎ የሚያነሳቸው ነጥቦች ደግሞ ጥቂቶቹን እንይ:-
ከሚያበሳጨን አካባቢ ለትንሽ ጊዜ መራቅ ፣ ብስጭትን እንዳናከማች መነጋገርን መለማመድ ፣ ጤናማ አመጋገብ፣ ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት መጣር አተነፋፈስን በብስጭት ጊዜ መግራት እና ወደ ውስጥ ማሰብ (mindfulness) እና ሌሎችም ናቸው።
እህታችን የሚከተሉት የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እና ሀሳቦችን በመከተል አሁን ካሉበት ችግር በተወሰነ መልኩም ቢሆን በአላህ እገዛ እንደሚወጡ እናምናለን።
✍️ ኡስማን ሙስጠፋ ከኡስማኒክ ሳይኮሎጂ።
ለጥያቄ እና አገልግሎት ለማግኘት @usmanoman ላይ ያናግሩን | 368 |
