fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

رفتن به کانال در Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
318
مشترکین
-424 ساعت
-77 روز
+5430 روز
آرشیو پست ها
♦️♦️♦️እህቴ ሆይ…አቤት ብለሽ ማንበብ እንደጀመርሽ ተስፋ አደርጋለሁ 📌መልካም የሆነን ባል ለረጅም ጊዜ ስትጠብቂ ቆይተሻልን? ብዙ ጊዜ በሌሊት እጆችሽን ወደ ሰማይ አንስተሽ፣ በእንባ ዓይኖችሽን ሞልተሽ፣ “ያ አላህ! የእኔ ተራ መቼ ነው? በሩን አንኳክቶ ወደ ሕይወቴ የሚገባው ሰው መቼ ነው?” ብለሽ ይሆናል። 📍ጓደኞችሽ አንድ በአንድ ሲዳሩ አይተሽ ይሆናል። አንቺ ግን አሁንም ትጠብቂያለሽ። 🔷ሰዎችም ልብሽን በሚያሳምሙ ቃላት፦ “መቼ ነው የምትዳሪው?” “ለምን እስካሁን ዘገየ?” ብለው ይጠይቁሽ ይሆናል። ነገር ግን እህቴ ሆይ፣ ማንም ሰው ሊያውቀው የማይችለውን አንድ እውነት አስታውሺ፦ አላህ አልረሳሽም! እንባሽን ያውቃል። የልብሽን ህመም ያውቃል። የምስጢር ዱዓሽን ይሰማል። ማንም ሰው የማያውቀውን ያንቺን ልብ ያውቃል። አንቺ ገና ያላወቅሽውን ሰው እንኳን አላህ ያውቀዋል። ስለዚህ የትዳርሽ መዘግየት እንዲሰብርሽ አትፍቀጂ። ይልቁንም ወደ አላህ የሚያቀርብሽ ይሁን። 📍ሌሊት ሰዎች በተኙበት ጊዜ ተነሺ። ሁሉም ዝም ባለበት ጊዜ ከአላህ ጋር ተነጋገሪ። እጆችሽን አንስተሽ እንዲህ በይ፦ “ያ አላህ! ማንኛውንም ወንድ አልፈልግም። አንተ ለእኔ የመረጥከውን ሰው እፈልጋለሁ። ያ አላህ! አንተን የሚፈራ፣ ሶላቱን የሚጠብቅ፣ ቁርአንን የሚወድ፣ በእኔ ላይ የሚራራ፣ የሚያከብረኝ እንጂ የማያዋርደኝ፣ ስሳሳት በርኅራኄ የሚመክረኝ፣ ስደክም የሚያግዘኝ፣ በአንተ መታዘዝ ላይ የሚረዳኝን ባል ስጠኝ።” ከዚያም የነበዩ ሙሳን عليه السلام ዱዓ አስታውሺ፦ ﴿رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنْزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ﴾ “ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ወደ እኔ ለምታወርደው ማንኛውም መልካም ነገር በጣም ተፈላጊ ነኝ።”                       እህቴ ሆይ… ምናልባት ዛሬ በመዘግየቱ ታለቅሺ ይሆናል፤ ነገ ግን ወደ ኋላ ተመልሰሽ፦ “ያ አላህ! ያኔ ያንን ሰው ለምን አልሰጠኸኝም ብዬ ነበር፤ አሁን ግን ለምን ከእሱ እንደጠበቅኸኝ ገባኝ። አልሐምዱሊላህ!” ትዪ ይሆናል። ምናልባት የምትፈልጊው ሰው አላህ ላንቺ የማይስማማ መሆኑን ያውቃል። ምናልባት እሱ የልብ ሰባሪሽ ይሆን ነበር። ምናልባት ዲንሽን ያዳክም ነበር። ምናልባት ልጆችሽ የማይገባቸውን ነገር እንዲያዩ ምክንያት ይሆን ነበር። አንቺ ግን አታውቂም፤ አላህ ያውቃል። ስለዚህ አንድ በር ሲዘጋ አታልቅሺ፤ ምናልባት ከኋላው ያለውን ጉዳት አላህ እያራቀልሽ ይሆናል።            አደራ አደራ ...... በትዳር መዘግየት ምክንያት የማይመችሽን ሰው አትቀበዪ። የትዳር ጉዳይ የአንድ ቀን ደስታ ብቻ አይደለም። ትዳር ዕድሜ ነው። ትዳር ቤተሰብ ነው። ትዳር ልጆች ናቸው። ትዳር ዲን ነው። ትዳር የወደፊት ሕይወት ነው። ስለዚህ ከገንዘብ፣ ከውበትና ከማዕረግ በፊት ዲንና መልካም ሥነ-ምግባር ተመልከቺ። ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إذا جاءكم من ترضون دينه وخلقه فزوجوه» “ዲኑንና ሥነ-ምግባሩን የምትወዱት ሰው ወደናንተ ከመጣ አጋቡት።”                እህቴ ሆይ…እያነበብሽ ነዋ አላህ የጻፈልሽ ነገር በፍጹም አያመልጥሽም። ሰዎች ቢያግዱት ይመጣል። ሩቅ ቢሆን አላህ ያቀርበዋል። ጊዜው ቢዘገይ ጊዜው ሲደርስ ይመጣል። አላህ ያልጻፈልሽ ነገር ግን ሰዎች ሁሉ ቢሰበሰቡ ሊያገኙልሽ አይችሉም። ስለዚህ እንዲህ በይ፦ “ያ ረቢ! እኔ በአንተ እተማመናለሁ። ለእኔ ምረጥልኝ፤ እኔ ለራሴ የማላውቀውን አንተ ታውቃለህ። ለእኔ የሚሆነውን አንተ ምረጥ።” ከዚያም ልብሽን አሳርፊ። አትጨነቂ። አትቸኩዪ። ተስፋ አትቁረጪ። የአላህን ምሕረት አትጠራጠሪ። ምክንያቱም… እንባሽን ያየ አላህ አለ። ዱዓሽን የሰማ አላህ አለ። ልብሽን የሚያውቅ አላህ አለ። ዕጣሽንም በእጁ የያዘ አላህ አለ። በመጨረሻም አላህ ሆይ! በሙስሊም ሴቶች ልብ ውስጥ ያለውን፣ አንተ ብቻ የምታውቃቸውን ምኞቶች ፈጽምላቸው። አላህ ሆይ! ለእነርሱም ሳሊህ ባሎችን ስጣቸው፤ በዲናቸው ላይ የሚረዷቸውን፣ የሚያከብሯቸውን፣ የሚወዷቸውንና በእነርሱ ጉዳይ አንተን የሚፈሩትን ስጣቸው። አላህ ሆይ! የተሰበረ ልብ ካለ አጽናው። ብቸኛ ልብ ካለ አጽናናው። የሚጠብቅ ልብ ካለ በመልካም ነገር አስደስተው። አላህ ሆይ! ከእያንዳንዱ መጠበቅ እፎይታን፣ ከእያንዳንዱ ዱዓ መልስን፣ ከእያንዳንዱ ሐዘን ደስታን ስጣቸው። አላህ ሆይ! ባል የሌላት አንዲትም ሴት አትተው፤ ለእሷ የሚሆን ሳሊህ ባል ስጣት። የተሰበረ ልብ አትተው፤ ጽናትና ደስታ ስጠው። አላህ ሆይ! በኢማን፣ በፍቅር፣ በምሕረትና በሰላም የተሞሉ ቤቶችን ስጣቸው።                  አሚን ያ ረብ ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

የማለዳ መልእክት (49) ~ ልጆቻችን አካዳሚ ትምህርት መማራቸው እና በዚህ ላይ መጎበዛቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ላይ ማገዝና ሞራል መስጠትም ተገቢ ነው። ይሄ የሚሆነው በዲናዊ ትምህርት ሂሳብ ከሆነ ግን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው። * ልጆቻችን ሶላት ይሰግዳሉ ወይ? ቁርኣን እና ሌሎችም ኢስላማዊ ትምህርቶችን ይማራሉ ወይ? በዚህ በኩል ከሌሉ በአካደሚ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ትርጉም የለውም። እንዲያውም ሊጎዳቸው ይችላል። ዲናቸውን ካላወቁ በየትምህርት ዓይነቶቹ ውስጥ የተሰነቀሩ ብልሹ አስተሳበቦችን ሳያመዛዝኑ ይውጣሉ። የዲንን ዋጋ እና የአለማመንን አደጋ በቅጡ ስለማይለዩ እንደዋዛ ከኢስላም ሊወጡ ይችላሉ። ስማቸው የሙስሊም የሆኑ ግን ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን በየዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሉ። የአካደሚ ትምህርት ደረጃቸው የሚያላብሳቸው ትእቢት ስላለ ምክር ለመስማትም ዝግጁ አይደሉም። (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስማቸው የሙስሊም የሆኑ፣ ግን ከነ ጭራሹ እስልምና ውስጥ የሌሉ፣ ሰው ግን ሙስሊም አድርጎ የሚያስባቸው ሁለት ዶክተሮችን አውቃለሁ።) * በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ልጆችን ማበረታታትና መሸለም ጥሩ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያ ያደርግንበት መንገድ ግን በጣም የተጋነነ ነው። ቁርኣን ሒፍዝ የጨረሱ፣ በተለያዩ ሃገራት ለአመታት ተንከራተው ጥሩ የዒልም ደረጃ ላይ የደረሱ ደረሶችን ግን ዞሮም የሚያያቸው የለም። ከስር እየመጡ ላሉት ተተኪዎች ምንድነው እያስተላለፍን ያለነው? ይህንን የተራራቀ አቀራረባችንን እያዩ ለዲናቸው ትኩረት ይሰጣሉ ወይ? * የዲን ትምህርት ለምን የትርፍ ጊዜ ትምህርት ይሆናል? ክረምት ብቻ፣ ቅዳሜና እሁድ ብቻ፣ ... እየሆነ ነው። ለአካደሚው ግን ሁለ ነገራችንን እየሰጠን ነው። በግል ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለን እናስተምራለን። መጥፎ ነገር የማያዩበት የተሻለ ድባብ ያለበት ግቢ መምረጣችን ይሁን። ለቁርአን ትምህርት ግን የዚያን ግማሽ እንኳን ከፍለን ማስተማር አንፈልግም። ለአካደሚ ትምህርቱ ተጨማሪ ከፍለን አስጠኚ እናደርጋለን። ለቁርኣንና ኪታብ ትምህርቶች ግን የረባ ቦታም የለንም። እነዚህ ነገሮች ከጊዜያዊ ትኩረታችን መራራቅ ባለፈ በልጆቹ አእምሮ ላይ እያስቀመጥነው ያለው ነገር ይበልጥ አደገኛ ነው፡፡ የዲን ትምህርት መማር ያን ያህል አንገብጋቢ እንዳልሆነ በተግባር እያሰርፅንባቸው ነው። በዚህ ላይ ሶላት አለመስገድ ሲጨመርበት፣ ክፍተታቸው የበዙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ከሆነ፣ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አፍላ እድሜ ላይ ሲደርሱ ለመግለፅ የሚሰቀጥጥ ኪሳራ ይደርሳል። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 05/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

❝ድንግል ስላልሆንኩ ትዳርን እፈራለሁ ላለች እህት የተላከ መልእክት!❞ ~ ውድ እህቴ ሆይ! ሰው ነሽና ተሳስተሻል፤ አማኝ ነሽና ተፀፅተሽ ወደ ጌታሽ ሮጠሻል። አላህ ደግሞ ተውበት አድራጊዎችንና ወደ እርሱ የሚመለሱትን እጅግ ይወዳል። ታዲያ ይቅር ባዩ ጌታሽ በራሕመቱ የሸፈነልሽን ስህተት ይዘሽ፣ ዛሬም ድረስ ራስሽን የምትወቅሺውና የሐላሉን የትዳር በር በራስሽ ላይ የምትቆልፊው እስከ መቼ ነው? እውነተኛው ንፅህና የተውበት እንባ ያጠበው የልብ ንፅህና ነው። ረሱል (ﷺ) «ከወንጀሉ የተመለሰ ሰው ልክ ምንም ወንጀል እንዳልነበረው ነው» ብለውናል። ሸይጣን ሁለት ጊዜ ያጠቃሻል፦ 1.  በመጀመሪያው ወቅት ወደ ወንጀል እንድትገቢ አታሎሻል፤ 2. ዛሬ ደግሞ «አንቺ ድንግል አይደለሽም፣ ስለዚህ ለትዳር ብቁ አይደለሽም፣ ነገ ትዋረጃለሽ» እያለ በተስፋ መቁረጥ እና በብቸኝነት ወጥመድ ውስጥ እንድትኖሪ ይፈልጋል። ● ጥያቄ 1፡ «ቢክራ ሳልሆን እንዴት አገባለሁ? ለማግባት ብቁ ነኝ?» - ምላሽ፡- አዎን፣ ሙሉ በሙሉ ብቁ ነሽ! ትዳር በኢስላም ለድንግሎች ብቻ የተፈቀደ ሸቀጥ አይደለም። የነቢያችን ﷺ ሚስቶች ከእናት አዒሻህ በስተቀር ሁላቸውም ቀደም ሲል ያገቡ (ቢክራ ያልነበሩ) ናቸው። በሸሪዓው ሚዛን የሴት ልጅ ትልቁ ክብር የሚለካው በዲኗ፣ በስነ-ምግባሯና አላህን በመፍራቷ እንጂ በአንድ የአካል ሽፋን ብቻ አይደለም። ● ጥያቄ 2፡ «ለሚጠይቀኝ ሰው ያለፈውን ህይወቴን መንገር አለብኝ?»   - ምላሽ፡- ፈጽሞ የለብሽም! ኢስላም ያለፈን ወንጀል መዘርዘርን ያወግዛል። አላህ በምህረቱ የሸፈነልሽን ነውር ለሰው መግለጥ «ሙጃሀራህ» (ወንጀልን ይፋ ማድረግ) ስለሚሆን ይከለከላል። ማንም ሰው መርማሪ ፖሊስ ሆኖ የቀደሞ ህይወትሽን ሊመረምር አይፈቀድለትም፤ አንቺም የመናገር ምንም ዓይነት ሸሪዓዊ ግዴታ የለብሽም። ● ጥያቄ 3፡ «ወንዱ 'ቢክራ መሆን አለባት' ብሎ በግልፅ ቢያስቀምጥስ?»   - ምላሽ፡- አንድ ወንድ ድንግልናን ጥብቅ መስፈርት አድርጎ ካስቀመጠ፣ መዋሸት አያስፈልግሽም፤ በዚያው ልክ ደግሞ «እኔ እኮ  እንዲህ ሆኜ ነው ያጣሁት…» ብለሽ ራስሽን አትግለጪ። አጭሩ መልስ፦ «እኔና አንተ በመስፈርት አንጣጣምም፤ አላህ የተሻለውን ይስጥህ» በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጊው። ● ጥያቄ 4፡ «ወንዱ ስለ ድንግልና ምንም ካላነሳስ?»   - ምላሽ፡- ወንዱ ስለ ቢክራ ምንም ካላነሳና ትኩረቱ ስነ-ምግባርሽ፣ ዲንሽና አብሮ መኖር ላይ ከሆነ፤ ጉዳዩን ፈጽሞ ማንሳት  አያስፈልግሽም። ጥያቄውን በደስታ ተቀብለሽ ወደ ኒካህና ወደ ትዳርሽ መሻገር ሙሉ በሙሉ ይፈቀድልሻል። ስለዚህ ይህንን ጉዳይ ለጓደኛ፣ ለቤተሰብም ሆነ ለማንም ሰው አትናገሪ። በአንቺና በአላህ መካከል የቀረ ሚስጥር ይሁን። ከአሁን በኋላ የሚመጡትን የትዳር ጥያቄዎች «ቢክራ ስላልሆንኩኝ» በሚል ሰበብ ብቻ ውድቅ አታድርጊ። ወንዱ ቅድመ-ሁኔታ እስካላደረገው ድረስ፣ እንደማንኛውም ሴት ኢስቲኻራህ አድርገሽ ተቀበይ። «ያ አላህ! በምህረትህ ሸፍነኸኛልና በትዳሬም ውስጥ ነውሬን ሸፍንልኝ፤ የሚያከብረኝንና ወደ አንተ የሚያቀርበኝን ሷሊሕ ባል ወፍቀኝ» በማለት ዘወትር ዱዓ አድርጊ። አብሽሪ! --- t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1

📣አድስ ወሳኝ ሙሐደራ ርዕስ: የወንድማማችነት ፀጋ እና የመልካም ወንድም ደረጃ... 🎙በአቡ ሒቢቲላህ ሑሰይን ኢስማኢል t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

📌ጥሩ የሚነበብ መፅሀፍ ልጠቁማችሁ..!! ━━━━━━።◈።━━━━━━━ 📚 የኪታቡ ስም፦ 🌿 "قصص الزاهدين والزاهدات" (የዱንያን ብልጭልጭ የናቁና ችላ ያሉ ደጋግ የአላህ ወንድና ሴት ባሮች ታሪክ) ✍🏻 አዘጋጅ፦ ሸይኽ ማህሙድ አል-ሚስሪ ሐፊዘሁላህ ታሪክና ቂሳዎች በሰው ልጆች ነፍስ ውስጥ እጅግ ጥልቅና ዘላቂ የሆነ ተፅዕኖ አላቸው። ታሪክም እንደየ አይነቱ ይለያያልና... በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የምናገኘው በተለምዶ የታሪክ መፅሀፍ ተብለው በሚዘጋጁ ድርሳናት ላይ እንደምናገኘው አይነት እከሌ የሚባለው ሰው በዚህ ቀን እና ቦታ ላይ ተወልዶ እንደዚህ ሆነ፤ ከዚያም እንደዚህ ሰራ፤ በስተመጨረሻም እከሌ በሚባለው ቀን ሞተ እያለ የሚያትት አይደለም! ይልቅ ሌትና ቀናቸውን ለጌታቸው ፍቅር ስለተዋደቁ፣ የዱንያን ጊዜያዊ ክብርና ስልጣን እርግፍ አድርገው በመተው ከአላህ  ጋር ብቻ በዒባዳ ስለከረሙ ደጋግ ቀደምቶች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ስላሳለፏቸው እጅግ ሳቢና አጓጊ የሆኑ አጋጣሚዎች፣ ሁላችንም ልንላበሳቸው ስለሚገቡ ታላላቅ ስብዕናዎች፣ እንዲሁም ሕይወትን የሚቀይሩ ወርቃማ ትምህርቶችና ምክሮችን የያዘ መፅሀፍ ነው። ጠቅለል ስናደርገው በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ከቁስ እና ከስሜት ባርነት ነፃ ወጥተን፣ የዛለች ነፍሳችንን እንዴት በዒባዳና በዚክር መፈወስ እንደምንችል አቅጣጫ የሚሰጠን ኮምፖስ ነውና ጊዜ ሳታባክኑ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ መክተባ ሄዳችሁ ብትሸምቱት ስል ወንድማዊ ግብዣዬ ነው😊!! ፒዲኤፉን በዚህ ታገኙታላችሁ!👇🏻 https://t.me/Abuhatim7/2528 ✨@Abuhatim7

📕قصص الزاهدين والزاهدات ✍🏻الشيخ - محمود المصري ✨@Abuhatim7

Repost from Temari News
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤ ✔ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 18 – 19/2019 ዓ.ም 📚ለትምህርት መፅሐፍት 💻
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ፤ ✔ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 18 – 19/2019 ዓ.ም 📚ለትምህርት መፅሐፍት 💻 @Temari_Notes 💻 @Temari_Notes 📣ለትምህርታዊ መረጃዎች 💻 @TemariNews 💻 @TemariNews

ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም! ~ አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ? አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ? ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም። ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት! (قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ) "ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60] ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ? (إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ) "ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120] ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?! · ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው። ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።) ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!" · አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል! · ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor

⛔️ አንዳንድ ሰዎች ከዓይናችን ይርቃሉ… ከልባችን ግን አይርቁም። ምክንያቱ ባይገባንም፣ በአካል ሳናያቸው፣ በቅርበትም ሳናውቃቸው፣ እንዲሁ ነፍሳችን አጥብቃ የምትወዳቸው ሰዎች አሉ። አንድ ቀን እንኳን ከእነሱ ጋር ሳንቀመጥ፣ እጃቸውን ሳንይዝ፣ ፊታቸውን በዓይናችን ሳናይ፣ በልባችን ውስጥ የሆነ ልዩ ቦታ ይኖራቸዋል። ልባችን ከእነሱ ጋር ይመታል፤ መንፈሳችን አብሯቸው ይጓዛል፤ ስማቸውን ስንሰማ ፊታችን ይፈካል፤ ድምፃቸውን ስንሰማ ውስጣችን ይረጋጋል፤ ሲጨነቁ እኛም እንጨነቃለን፤ ሲደሰቱ ምክንያቱን ሳናውቅ እኛም እንደሰታለን። አንዳንድ ሰዎች ከእኛ በጣም ርቀው ሳሉ፣ ከአንዳንድ በየቀኑ ከምናያቸው ሰዎች ይልቅ የበለጠ የቀረቡን ይሆናሉ። ይህ የልብ ግንኙነት ነው፤ ቦታ የማይለካው፣ ርቀት የማይበግረው፣ ጊዜም በቀላሉ የማያጠፋው። 🌿 ምናልባት አላህ አንዳንድ ሰዎችን ከመንገዳችን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ እኛ ግን እነሱ ለምን ወደ ልባችን እንደገቡ ምክንያቱን ላናውቅ እንችላለን። ምናልባት አንድ ቀን የማናየውን ደስታ በቃላቸው ሰጥተውን ይሆናል፤ ምናልባት በጭንቀት ጊዜ አንድ ቃላቸው ልባችንን አጽናንቶ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ ያለምንም ምክንያት ነፍሳችን ከነፍሳቸው ጋር ተስማምታ ይሆናል። እንግዲህ ለእነዚያ ከሩቅ ሆነው በልባችን የሚኖሩ ሰዎች… አላህ ይጠብቃችሁ። አላህ ልባችሁን ያሳርፍ። አላህ ደስታችሁን ያብዛ። እና ከእውነት የምትወዷቸው ሰዎች ጋር በመልካም ጊዜና በመልካም ሁኔታ አብሮ ያኑራችሁ። አንዳንድ ሰዎችን መውደድ በቅርብ ስለምናያቸው አይደለም፤ ልባችን ለእነሱ ቦታ ስለሰጣቸው ነው። 💭 እና አንድ ቀን ያ ርቀት ተወግዶ፣ የምትናፍቁትን ሰው በዓይናችሁ እያያችሁ በአጠገባችሁ የምትስቁበትን ቀን አላህ ያምጣላችሁ። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

⁉እራሳችንን በእራሳችን በቁርኣን እናክም! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ✍[ ክ ፍ ል አ ን ድ] ✳️ብዙ ሰዎች በተለያዬ ምክንያት ሩቃ ቤት በመፈለግ በጣም ሲቸገሩ ይስተዋላል! በተለይ ከሃገር ወጭ የሚኖሩ እህትና ወንድሞች! ! ልክ እንዲሁ ሐገር ውስጥ ያሉትም ቢሆን " ታማኝ " ሩቃ ቤትን ስለሚፈልጉ እነርሱም በፍለጋ ይቸገራሉ .. በጣም ችግሩ የጠናባቸው ደግሞ "በኢንተርኔት ሩቃ "አስደርገው " ብራቸውን "ሲበዘበዙ ይስተዋላል ! ▪️✅ ሁሉም ሰው ማዎቅ ያለበት ነገር አላህን መፍራትና ዱአ ማብዛት ፣ ለበሽታዎች ሁሉ ፈውስ መሆን ዋነኛው ሰበብ ቁርአን ነው። ከቁርኣን መገለጫዎች መካከል አንዱ ደግሞ "ሺፋእ/ መድሃኒትነቱ" መሆኑ ነው። ➖አላህም(ሱብሃነሁ ወተዓላ) ፈውስነቱን ሲገልፅ ⤵️ ከቁርኣንም ለምእመናን <መድኀኒትና> እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡ ይላል وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا ❗️ቁርኣን፣ነቢያዊ ዚክርና ዱዓዎች (ሩቃ) ለሁሉም አይነት በሽታና ችግሮች መፍትሄ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ↘️ እናም ማንኛውም በቁርኣን ፈውስነት የሚያምን ግለሰብ ፋቲሓንና ሌሎችንም አጫጭር (በቀላሉ መቅራት የሚችላቸውን) ሱራዎች እንኳ ቢሆን እየቀራ ለራሱ " ሩቃ "ማድረግ ይችላል። 📌ራስን በራስ ለማከም ካልተቻለና ነገሩ ከጠና ሩቃ አድራጊ ፍለጋ ርቆ ለመሄድ ሳንገደድ፤ በቤተሰብ፣ አሊያም በዘመድና በጎረቤት ማስደረግ ይቻላል። ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈ ነገርግን ከዚህ ካለፈ በዲን የተሻለ እውቀት እና አላህን በመፍራት ወደ የሚታዎቁ የሩቃ ሃኪም ቤት መሄዱ መልካም ነው። 📚ለህክምና ዋናው ነገር ብዙ መቅራቱ ሳይሆን አላህን በሚፈራና ተወኩል ባለው ልብ፣ በቁርኣን ፈዋሽነት አምኖ ፋቲሓን እና ሙአዊዘተይን ወዘተ.. በነቢያዊ ዱአ እና አዝካሮችን በመቅራት ለመዳን በቂ ሰበብ ነው!። ነቢዩና ﷺ ሰሓቦቻቸውም በነዚህ ምእራፎች ሩቃ ያደርጉ እንደ ነበር ብዙ መረጃዎች ያስረዳሉና። 🤲 የላቀውና ከፍ ያለው አላህ ለታመመ ሁሉ ፈውሱን ቅርብ ያድርግለት 🤲 አሚን ✍ ወንድማችሁ ኡስማን ሰዒድ (አቡ አመቲረህማን) 🎓 የሩቃ ትምህርቶችን ለማግኘት ⬇️ https://t.me/alruqyehsheriyeh https://t.me/alruqyehsheriyeh ˢʰᵃʳᵉ    ⌲ ይ ቀ ጥ ላ ል !!

​ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፡- ​"የማንኛውም ሕዝብ (ኡመት) አስተዋይ ሰዎች በሙሉ በዚህ ነገር ላይ ተስማምተዋል፦ እውነተኛ ድሎት (ጸጋ) በድሎት አይገኝም፤ ምቾትን የመረጠ ሰው እውነተኛ እረፍት ያመልጠዋል። እንደየ መከራው መጋፈጥና እንደ ችግሮቹ ትዕግስት መጠን ደስታውና እርካታው ይጨምራል። ​ዓላማ ለሌለው ሰው — እውነተኛ ደስታ የለውም፤ ​ትዕግስት ለሌለው ሰው — እርካታ የለውም፤ ​መከራን ላልቀመሰ — ድሎት የለውም፤ ​ድካምን ላላየም — እረፍት የለውም፤ ​ይልቁንም አንድ ባሪያ (ሰው) ለጥቂት ጊዜ ቢደክም ለረጅም ጊዜ ያርፋል። ለአንድ ሰዓት ያህል የትዕግስትን መራራነት ቢታገስ፣ ይህ ትዕግስቱ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት (ጀነት) ይመራዋል። በዘለዓለማዊው ዓለም ውስጥ ባለጸጋዎች የሚኖሩበት ጸጋ በሙሉ የአንድ ሰዓት ትዕግስት ፍሬ ነው። አላህም ታጋዥ ነው፤ በአላህም እንጂ ጥንካሬ የለም።"

#ማስታወሻ! #ለቀጣሪዎች፦ የቅጥር ማስታወቂያ በነፃ ነው የምንለቀው ማለት የተላከልን ማስታወቂያ ሁሉ ያለምንም ማጣራት ፖስት ይደረጋል ማለት አይደለም። አሰፈላጊ የሆኑ ማጣሪያዎች በሙሉ ይደረጋሉ። #ለሰራተኞች፦ ለስራ ብቁ ናችሁ ወይም ስራ ከመጀመራችሁ በፊት መሰልጠን አለባችሁ ብለው ቅድመ ክፍያ ብር የሚጠይቋችሁ ድርጅቶች ካሉ ፈፅሞ እንዳትከፍሏቸው። ከቻላችሁ ወድያው በ @HalalJobsEthbot በኩል አሳውቁን። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ነግርያቹሀለው። ስራ አገኛለሁ በሚል ጉጉት እንዳትሸወዱ። === Halal Jobs ቴሌግራም👉 t.me/HalalJobsEth

Repost from N/a
➲ የሱና ቴሌግራም ቻናላችሁን እና ግሩፓችሁን ባጭር ግዜ ዉስጥ በነፃ ማሳደግ የሚያስችል ዌቭ ጀምረን 100 ቻናሎችን ሰብስበናል አልሃምዱሊላህ አሁን ደሞ ከ5ሺ በላይ ተከታይ ላላቸው ቻናሎች እድሉን አምጥተናል ከ5k subscribers በላይ ያላቹ አሁኑኑ አናግሩን በነፃ ነዉ ፈጥነው ያስመዝግቡ የሱና ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  👉 @Quran_mylife1 የሱና መስፈርት የማያሟሉ ቻናሎችን አንቀበልም

አልተፈታም ህልሜ /=====================/ አንደበቴ አፍታቶ ሲሳነው መናገር፡ ጊዜው ተራመደ ሳልሰራ ቁም ነገር፡ ጎዳናው ጠፋብኝ ካደባባይ ቆሜ፡ ዲብቅ ሚስጥር ሆኖ ሳይፈታ ህልሜ፡ ኑሮ ትርጉም ሲያጣ ሲሆን እንቆቅልሽ፡ አነባሁ አምርሬ ህይወት አዘንኩብሽ፡ ሳልኖር እየኖርኩኝ ሳያመኝ ታምሜ፡ አለሁ እስከ ዛሬ አልተፈታም ህልሜ፡ _ ውስጤ እየተከፋ አንጀቴ እያረረ፡ ለሰወች እያልኩኝ የግል ሀሳቤ እየተቀየረ፡ እንደ እኔ አስተሳሰብ ህይወት መች ተኖረ፡ በበቂ ምክንያት ችግር ሆኖ ይፋ፡ እኔ እያለቀስኩኝ ሰው እንዳይከፋ፡ በሀሳብ ማዕበል ውስጤ እየተገፋ፡ የነገን እያሰብኩ አለሁኝ በተስፋ፡ ሀሳቤ ነበረ እምነቴን ማስፋፋት፡ ጀግና ወጣት መሆን ጥንቁቅ ከኹኀራፋት፡ በፍቅር ለመኖር የፍቅር ሰው ሆኘ፡ አዕምሮየ አስቦ ልቤ እንደተመኘ፡ ሆነብኝ በዐክሱ ዛሬ ምን ተገኘ፡ ተስፋ አልቆርጥም ዛሬም ምኞቴ ይሳካል፡ የዛሬው መከፋት በደስታ ይተካል፡ ውስጠቴ ንፁህ ነው እያልኩ አስባለሁ፡ አላህ እስከሚሻ በተስፋ እኖራለሁ፡ ተውሒዲ ሱናን ይዠ ምን ያስጨንቀኛል፡ የውስጥ ስሜቴ አይዞህ ይለኛል፡ ጓደኛ ቢጠፋም ውስጤ ያፅናናኛል፡   ውስጤ ይመክረኛል፡  እንዲህም ይለኛል፡ የትናንት ወዳጂህ ዛሬ ቢሆን ባዳ፡ በየ ደረሰበት ስላንተ መጥፎነት ወሬውን ቢነዳ፡ ቆም ብለህ አስብ አሰታውስ ያላህን ቃል፡ በእምነትህ ጠንክር ሀዘንህ ይርቃል፡ ትክክል ነህ በነገር መወጋት ያማል! ያስጨንቃል ልብንም ያደማል! ግን ከወሬኞች በላይ አንተ ራዕይ አለህ፡ እነርሱ ሲያወሩ አንተ ተለይተህ፡ ለአላማህ ስራ የተግባር ሰው ሆነህ፡ የነገረኞች ቃል እንደ እሬት ቢመርም፡ ለሚጮኸው ሁሉ አይወረወርም፡ ዛሬ ያስተከዘህ ነገ ላይ ይፈካል፡ አብሽር አትጨነቅ ምኞትህ ይሳካል፡  ኢንሻ አላህ አብሽር ጠንከር በል ራስህን አፅናና፡ ከጌታህ በስተቀር ባይተዋር ነህና፡ ሰው ያለውን ይበል በተውሒዲህ ፅና፡ የልቤ ትርታ ይህንን ሲመክረኝ፡ እኔም ተረጋጋሁ ውስጤንም ደስ አለኝ፡ ትልቅ ተሰፋን ጫንኩኝ ከሀዘን ርቄ፡ በወደፊት እቅድ ደስታየን ናፍቄ፡ ህልሜ እውን ይሆናል ቆርጨ ወሰንኩኝ፡ አዛኙን ጌታየን እየተማፀንኩኝ፡ ነገር ግን ዛሬ ላይ! በወደፊት ህልሜ እጂጉን ብደሳም፡ በአላህ ተወክየ እንደሚስተካከል ወስኘ ብነሳም፡ ፈተናወች በዝተው ብተኛም ታምሜ፡ በችግሬ ጊዜ ቢርቀኝ ወንድሜ፡ ተስፋ አልቆርጥም እንጂ አሁን ባለሁበት  አልተፈታም ህልሜ፡ 17- 07- 2011 አ.ል (ኑረዲን  አል_አረቢ)

ይቅርታ! ሰዎች ሲበድሉን፣ ይቅርታ ሲጠይቁን «ለምን ወዲያው ይቅር አልኳቸው?» እያልን ራሳችንን እንወቅሳለን። ጤናማና ሰብአዊ ስሜት ያለው አእምሮ እንኳ ሳይቀር የጥፋተኛውን ይቅርታ ወዲያውኑ መቀበል አቅቶት ሲቸገር ይስተዋላል። ይህ የሆነበት ዋናው ምክንያት የጥፋቱ ስሜት ከቃሉ ይልቅ በውስጣችን ጥሎት ያለፈው ቁስል ከባድ ስለሆነ ነው። የጥፋቱ ስሜት ውስጣችንን እንዲህ ይጎዳዋል፦ መተማመን ሲሰበር በሰዎች ግንኙነት ውስጥ ዋጋው ከፍተኛው ነገር መተማመን ነው። አንድ ሰው ሲበድለን፣ የጥፋቱ ክብደት ብቻ ሳይሆን ያመነበትና የተመካበት ልባችን መክዳቱ ዋነኛው ጉዳት ነው። ይቅርታ መጠየቅ የጠፋውን ነገር በቅጽበት መልሶ መገንባት አይችልም። መተማመን እንደ አበባ ቡቃያ ነው፤ ጊዜ፣ እንክብካቤ እና ታጋሽነት ይፈልጋል። የተፈጠረው ክፍተት እና ድካም እያንዳንዱ ስህተት እና በደል በሰው ልብ ላይ የስነ-ልቦና ድካም ይፈጥራል። «ለምን እንዲህ አደረገ?» የሚለው ጥያቄ፣ ያሳለፍነው መመረር እና ውስጣዊ ጭንቀት አእምሯችንን ያደክሙታል። ይቅርታን ለማድረግ ሲሞከር እንኳን ውስጣችን ዝግጁ የሚሆነው ያ የደረሰን ድካም ሲቀልና አዕምሯችን እረፍት ሲያገኝ ነው። ጊዜን የሚጠይቅ የፈውስ ሂደት ቁስል ሲነካ ወዲያው እንደማይድን ሁሉ፣ የልብ ስብራትም የራሱ የሆነ የፈውስ ጊዜ አለው። ይቅርታ የሚጠይቅ አካል «ይቅርታ አድርግልኝ» ሲል፣ የተበዳዩ አካል ውስጣዊ ሰላም ግን ወዲያውኑ ሊመለስለት አይችልም፤ ልቡ የደረሰበትን ጉዳት አብጥሮ ለማየትና ያንን ስሜት ለማስተናገድ ጊዜ ይሻል። ይህ ሁሉ ሆኖ፣ ይቅርታ ማድረግ የደካሞች ሳይሆን የጠንካሮች መለያ መሆኑ ይታወቃል፤ ነገር ግን ያንን ይቅርታ ከመቀበል በፊት ውስጣችንን ማዳመጥ ቅንጦት ሳይሆን የግድ የሚል ፍላጎት ነው። ቁስሉ ሳይደርቅና ውስጣችን ሳይረጋጋ የሚሰጥ ይቅርታ ባዶ ሊሆን ይችላል። በመሆኑም፣ ይቅርታችሁን ከመቀበል በመዘግየታችን እንዳያማችሁ—እራሳችንን እስከምናስታግስ እንጂ ይቅርታችሁን ሳንቀበል አንቀርም። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

የማለዳ መልእክት (48) ~ መጅሊስ በታሪኩ ከመንግስት ተፅእኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ለዚህ ዋናው ምክንያት መጅሊሱ ላይ የሚቀመጡ አካላት ባህሪ ሳይሆን የፖለቲከኞቹ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው። ከዚያ የሚቀመጡ ሰዎች ድባቡን ያዩና ከ "አየር ንብረቱ" ጋር ራሳቸውን ያስማማሉ። የ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ብጥብጥ ምክንያት ከጥቅም ግጭት ባለፈ የመንግስት አካላት ፍላጎት ከጀርባ ነበር። በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ አካላት የተሻለ የመንግስት ድጋፍ እንዳላቸው ያስቡ ነበር። ኋላ ላይ አሕ^ባሽ ከሊባኖስ ተጋብዞ የገባውም ከመጅሊስ ሰዎች ፍላጎት ባለፈ የመንግስት ፍላጎት ስለነበር ነው። ዛሬ ላይ ያለው የፖለቲካውን ነፋስ ተከትሎ የመጣው የመጅሊስ ለውጥም ያለቀለትና የማይነካ አይነት አይደለም። ነገ ሊቀየር ይችላል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ አንዳንድ ደስ የማይሉ ሽታዎች ያሉ ይመስላል። መጅሊስ ላይ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ይህንን ተገንዝበው ለህዝባችን ዐቂዳውን ማስተማር ላይ ወይም ለማስተማር ምቹ ድባብ እንዲኖር ማድረግ ላይ መሬት የረገጠ ስራ ሊሰሩ ይገባ ነበር። ነበር የምለው በተግባር እየሆነ ስላላይደለ ነው። በተለይ አማራ ክልል ላይ ከ'ኮስሞቲክ' ስራዎች በመውጣት ዛሬ ላይ ቆፍጠን ብሎ መስራት ይሻል ነበር። ነገሮች ቢቀያየሩ ተፅእኖው ከሌሎች አካባቢዎች ይለያል። ሌላው ቢቀር ለተሻለ መስለሓ ብላችሁ የገባችሁ ወገኖች ራሱ ከልብ በመመካከር ህዝብ ላይ ብትሰሩ መልካም ነው። ጊዜው አሁንም አልረፈደም። ብዙ መራመድ የሚያስችላችሁ አቅም ባይኖራችሁ እንኳ በአቅማችሁ ልክ የምትችሉትን ሳትሰሩ ጊዜው እንዳያልፍ ብታስቡበት ይሻላል። እውነት ለመናገር በተበላሸ ዐቂዳውም ቢሆን ሳይልፈሰፈስ ቆፍጠን በማለት እና መሬት የወረደ ስራ በመስራት በኩል ከመጅሊስ ተቋማት የተባረረው አሕ^ባሽ የተሻለ ትጋት አለው። አሕ^ባሽ የመጅሊሱ መዋቅር በእጁ ሳለም ያለምንም ይሉኝታ ህዝብን ለመለወጥ እስከ ደም ጠብታ ታግሏል። የያዘው ዐቂዳ ክር^ፋትና የመንግስት ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ነው ወደ ህዝብ ልብ ከመግባት እንቅፋት የሆነበት። ከመሆኑም ጋር ለብልሹ ዐቂዳው በመዋደቅ ላይ ከመጅሊሱ ደጅ ርቆም አልቆመም። ዳግም ከተመለሰም ከቀደመው የበለጠ እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል። ያ እንዳይሆን ወይም እውን ቢሆን እንኳ ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ፖለቲከኛ ተደግፎ መተኛት ሳይሆን ህዝብን ትክክለኛውን አስተምህሮት ማስታጠቅ ነው የሚገባው። የሹማምንትን ጫና ለመጋፈጥ ወይም ለመቀነስ ትክክለኛው መንገድ ደሞ ከአላህ በታች ህዝብን ማንቃት ነው ሁነኛው ስራ። አላህ ልብ ይስጠን። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ክብር ለዑለሞቻችን! ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲ አል–ዓባድ ሐፊዞሁላህ፦ በዚህ ዘመን ከታላላቅ የሰለፊያ ዑለሞች መካከል በዒልምም ሆነ በእድሜ ከግንባር ቀደም የሚቆጠሩ ታላቅ የሐዲስ ሊቅ ናቸው። አይደለም ሸይኽ ዐብዱልሙሐሲን ይቅርና ተማሪዎቻቸው በዚህ ዘመን በእድሜም ሆነ በዒልም አቻ የሌላቸው ናቸው። ከተማሪወቻቸውም መካከል፦ 1.የየመኑ ሙሐዲስ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ሙቅቢል አል–ዋዲዒይ ረሒመሁላህ 2.ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል–መድኸሊይ ረሂመሁላህ 3.ሸይኽ ዑበይድ አል–ጃቢሪይ ረሂመሁላህ 4.ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሱሐይሚይ  ሐፊዘሁላህ ይገኙበታል። ✍🏻 ኢብኑ ሙሐመድዘይን

📍 تفريغ دورة دراسات في المنهج (بصيغة pdf) للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله ዐረበኛ የምትችሉ ኪታቡን አውርዳችሁ ብታነቡት በአላህ ፍቃድ እጅግ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ። የተዳሰሱ  ነጥቦች፦ 1, መንሀጀ ሰለፍ 2, በዘመኑ ያሉ ጠማማ አንጃዎች 👉 ተብሊግ 👉 ኢኽዋን 👉 ዳዒሽ 3, ኢስላምን ያስጠሉ ግለሰቦች (ሐሰን አል–በና፣ሰይድ ቁጥብ፣አቡ አዕላእ አል–መውዱውዲ)  እና ሌሎችም የጥመት መሪዎች ረድ የተሰጠበት ዳሰሳ አካቶ ይዟል። ኪታቡ ከላይ እተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰፋ ባለሁኔታ ስለመንሀጅ የተዳሰሰበት ጥሩ ትምህርት ነው። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን። አሚን። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444