fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 318
مشترکین
-824 ساعت
-117 روز
-8230 روز
آرشیو پست ها
🇷🇺🇺🇸🇺🇦 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋል፣ በነበረን ጥሩ የስልክ ጥሪ ነግሮኛል። ዘለንስኪም ጦርነቱን አሁን ማቆም ይፈልጋል። ብዙ ሰው ከሚያስበው በላይ ወደዚያ እየተጠጋን ነው። በአንካራ የኔቶ ስብሰባ ይህን እናነሳለን። *-*-*- ፑቲን ለማቆም የጣረውን ያህል ቢጥር፣ ዘለንስኪ አሁን እናቁም ብሎ ቢቆርጥለት፣ ትራምፕ የፈለገውን ያህል ጦርነቱ በሰላም ሊፈታ ነው ቢል፣  አውሮፓዊያን ጦርነቱ እንዲቆም አይፈልጉምና ጦርነቱ አይቆምም። አውሮፓዊያን (እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን) ጦርነት ማቆም አይፈልጉም። በመጪው ኔቶ ስብሰባ፣ ይህን ነው ለትራምፕ የሚሉት "ሩሲያ እየደቀቀች ነው፣ ጊዜ ስጠን እንጨርሳት።" ትራምፕ፣ ሩሲያ ጋር መገናኘት የሚችለው በስልክ ብቻ ነው። ካልሆነ በሦስተኛ ወገን ነው። ፊት ለፊት እንኳ እንዳይገናኙ አውሮፓዊያን ድልድዩን አፍርሰውባቸዋል። በስልክና በሦስተኛ ወገን ደግሞ የምታመጣው ምንም ለውጥ የለም። ጦርነቱ ይቀጥላል!

ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ፑቲን ጦርነቱን ማቆም ይፈልጋል፣ በነበረን ጥሩ የስልክ ጥሪ ነግሮኛል። ዘለንስኪም ጦርነቱን አሁን ማቆም ይፈልጋል። ብዙ ሰው ከሚያስበው በላይ ወደዚያ እየተጠጋን ነው። በአንካራ የኔቶ ስብሰባ ይህን እናነሳለን። *-*-*- ፑቲን ለማቆም የጣረውን ያህል ቢጥር፣ ዘለንስኪ አሁን እናቁም ብሎ ቢቆርጥለት፣ ትራምፕ የፈለገውን ያህል ጦርነቱ በሰላም ሊፈታ ነው ቢል፣ አውሮፓዊያን ጦርነቱ እንዲቆም አይፈልጉምና ጦርነቱ አይቆምም። አውሮፓዊያን (እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን) ጦርነት ማቆም አይፈልጉም። በመጪው ኔቶ ስብሰባ፣ ይህን ነው ለትራምፕ የሚሉት "ሩሲያ እየደቀቀች ነው፣ ጊዜ ስጠን እንጨርሳት።" ትራምፕ፣ ሩሲያ ጋር መገናኘት የሚችለው በስልክ ብቻ ነው። ካልሆነ በሦስተኛ ወገን ነው። ፊት ለፊት እንኳ እንዳይገናኙ አውሮፓዊያን ድልድዩን አፍርሰውባቸዋል። በስልክና በሦስተኛ ወገን ደግሞ የምታመጣው ምንም ለውጥ የለም። ጦርነቱ ይቀጥላል!

🇺🇸⚽️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በባሎጉን ቀይ ካርድ ላይ
- ቀይ ካርድ ምን እንደሆነ አላውቅም ነበር። ሳውቅ "እየቀለድክ ነው?" አልኩት። ዳኛው ዝም ብሎ እጁን ወደ ላይ ያወጣል። እሺ፣ ከዚያ ያንተን ምርጥ ተጫዋች በሚቀጥለው ሳምንት ወይም በሚቀጥለው ጨዋታ እንዳትጫወት ይላል። ይሄ እኮ ብዙ ሥልጣን ነው፣ ብዙ አምባገነንነት ነው። ያ በጣም አስፈሪ ነው። ግን ከዚያ የዳኛውን ያለፈ ታሪክ ተመለከትኩ እና ያን ያህል ጥሩ እንዳልነበረ ተረዳሁ።

🇺🇦 ዩክሬናዊያን፣ በስተመጨረሻ ስለታችን ሰመረ። ስንጠብቀው የነበረው ቀን፣ ይኸው ሆነ ዛሬ፣ የኦምስክ ነዳጅ ማጣሪያን አገኘነው፣ 3000 ኪ.ሜ ገብተን መታነው፣ እያሉ በመደሰት ላይ ናቸው። ኦምስክ ነዳጅ ማጣሪያ የሩሲያ ግዙፉ ነዳጅ ማጣሪያ ነው።

🇺🇸🇷🇺🇺🇦❗️ ትራምፕ ፑቲን ጫናው እየተሰማው ነው እና በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲያበቃ ይፈልጋል። ሰዎች ከሚያስቡት በላይ ወደ ጦርነቱ ማብቂያ እየተቃረብን ነው።

🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ ሀሪ ኬን በጣም ጎበዝ ተጫዋች ነው። ጎልፍ አብረን ተጫውተናል። በጣም ጎበዝ ጎልፍ ተጨዋች ነው።

🇮🇱🇹🇷 ኔታንያሁ፣ ትራምፕ ለቱርኩ መሪ F-35 ተዋጊ ጀቶችን እንዳይሸጥለት ተናገረ። ምክኒያቱም፣ 'ኤርዶጋን' አሜሪካን ስለሚጠላ፣ ግማሽ የኔቶ አባል የሆነችውን ሳይፕረስን ስለወረረ" ብሏል።

+3
🇮🇷 እንዲህ ዓይነትን ሕዝብ ለማሸነፍ ከባድ ነው፣ ይቅርታ አሜሪካ። ትራምፕ ይደነቃል በዚህ አጋጣሚ፣ ቶሎ ብሎ እጥፍ ብሏል። እንደ እነ ቡሽ እንደገባበት ቀርቶ ቢሆን፣ ምናልባት የአሜሪካ ኃያልነት እስከወዲያኛው ይሰበር ነበር። በማምለጡ አሜሪካንን ነው ያስመለጠው። ኢራን፣ እንደሌሎቹ አይደለችምና።

🇺🇦❌🇷🇺 - ዛሬ ንጋት ላይ፣ የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ ውስጥ ትልቁ የኦምስክ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። ➡️ ማጣሪያው ከዩክሬን ግዛት 2,700 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ➡️ በዚህ ምስል፣ ከድሮኖቹ አንዱ እየተሽከረከረ ዒላማው ላይ ሲወድቅ ይታያል።

🇺🇦❌🇷🇺 - የዩክሬን ድሮኖች በክራይሚያ፣ በብራያንስክ ክልል እና በአዞቭ ባህር ውስጥ በርካታ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች ጨምሮ በአንድ ጀምበር 47 ወታደራዊ ኢላማዎችን መተዋል። በአዞቭ ባህር ውስጥ ወደ ክራይሚያ ቤንዚን ጭነው ይጓዙ የነበሩ ሁለት የመርከብ ታንከሮችን መተትዋል። እያንዳንዱ ታንከር ወደ 7,000 ቶን ነዳጅ ይዞ ነበር፣ ይህም ወደ 200 የሚጠጉ የባቡር ፍርጎዎች ጋር እኩል ነው። በመሬት ላይ በከርች ውስጥ የነዳጅ መጋዘን በእሳት ተቃጥሏል፣ በከርች አቅራቢያ የኔቦ-ዩ ራዳር ወድሟል። ሁለት S-400 "Triumph" የአየር መከላከያ ዘዴዎችም፣ እንዲሁ ወድመዋል - አንደኛው በግላዞቭካ ክራይሚያ እና ሌላው በኮሴንኪ ብራያንስክ ክልል ውስጥ።

+3
🇷🇺⚡️🇺🇦 ኪየቭ ክፉኛ ተጎድታለች። የአየር መቃወሚያ ሲስተሞቿ፣ ምሽቱን ሁሉም የሩሲያ ሚሳዬሎች፣ ዒላማቸው ላይ ከመውደቃቸው አንፃር፣ እጅግ የተዳከሙ ይመስላሉ። የዛሬው ሌሊቱን ጨምሮ፣ የዚህ የሁለት ሦስት ቀን የሩሲያ ጦር ሠራዊት እርምጃ የሚነግረን ሌላው ነገር፣ ጦሩ ግንባሩን እያሰፋ እንደመጣ ነው። ከተለመደው ምሥራቅ ዩክሬን ተሻግሮ ወደ ሰሜንና መካከለኛው ምሥራቅ እየገፋ መሆኑ እና ከዚህ በፊት የጥይት ድምፅ ሰምተው የማያውቁ የዩክሬን ከተሞች አሁን እንዲሰሙ እያደረጋቸው እንደሆ ነው። ዩክሬን፣ በወጥ መሳነት በማጠር ስትከላከላቸው የነበሩ የተለያዩ ግንባሮችን፣ አሁን አሁን ሩሲያዎች እየሰነጠቁ በመከፋፈል ሊበታትኗቸው እየሞከሩም ይመስላሉ በብዙ ቦታዎች። ግንባሩ አንዴ ከተናደ ወይም collapse ካደረገ፣ ከባድ ነው ለዩክሬን። ከዚያ በኋላ ሽሽት ብቻ ይሆናል።

🇨🇺 የኩባ ፕሬዝዳንት፣ ኩባ የአሜሪካን ጥቃት እንደማትፈራ እና "በተዘናጋንበት እንዳንጠቃ ወይም እንዳንሸነፍ እየተዘጋጀን ነው" ሲል ተናግሯል። ፕሬዝዳንቱ አክሎም፣ ኩባውያን "ለአብዮቱ" ለመሞት እና "እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ድረስ ለመዋጋት" ፈቃደኞች ናቸው ፣ መብታቸውን ፣ ነፃነታቸውን እና ሉዓላዊነታቸውን ለማስጠበቅ" ብሏል። *-*-*- በዓለም ምናልባት ከማንኛውም ሀገር በበለጠ ኩባና ኩባዊያን አሜሪካንና ምዕራቡን ዓለ ተቋቁመው ኖረዋል። በሌላ አባባል፣ ጫናን መቋቋም ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስተማሪ ናቸው። በኢኮኖሚ ማዕቀቡም፣ በንግድ እገዳውም፣ በውትድርና ጫናውም … ሁሉንም አልፈውታል። አሜሪካና ምዕራባዊያንን መቋቋም የምትችል ሀገር ጥቀስ ብባል፣ ኩባ top 3 ናት። ኩባ፣ ጠላቶች ቆርጠው ከመጡብሽ፣ እንደ ምንም ብለሽ የሆነ መተላለፊያ ባሕር ፈልጊና ተንፈራግጠሽም ቢሆን ዝጊ። ትከበሪያለሽ!

🇺🇦 ኪየቭ ምሽቱ

🇺🇦⚡️🇷🇺 ተጨማሪ የተለያዩ ሚሳኤሎችን፣ አሁንም፣ ሩሲያ ወደ ኪየቭ አስወንጭፋለች። በከተማው ከፍተኛ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ቀጥለዋል። እንደ ምንጮች ዘገባ፣ 15 ከባባድ ፍንዳታዎችን በ10 ደቂቃ ውስጥ መስማታቸውን ተናግረዋል። በብዙ የከተማው አካባቢ ውሃ እና መብራት እንደጠፋ ተዘግቧል።

🇷🇺⚡️🇺🇦 በሩሲያ ጦር ከሰዓታት በፊት የተተኮሱ፣ በርካታ ዚርካን፣ እስክንድር እና ባለስቲክ ሚሳዬሎች፣ አሁን ኪየቭ ወርደዋል። በብዙ የከተማው ቦታዎች ከፍተኛ ፍንዳታዎች ይሰማሉ።

🇺🇸🇮🇹 ትራምፕ፣ በጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ጆርጂያ ሜሎኒ ላይ፣ "የእገዳ ትዕዛዝ ያስፈል(ገኛል)" በማለት አሹፎባታል። በሁለቱ መካከል፣ በፈረንሳይ ተደርጎ ከነበረው የG7 ስብሰባ በኋላ፣ የ
🇺🇸🇮🇹 ትራምፕ፣ በጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ ጆርጂያ ሜሎኒ ላይ፣ "የእገዳ ትዕዛዝ ያስፈል(ገኛል)" በማለት አሹፎባታል። በሁለቱ መካከል፣ በፈረንሳይ ተደርጎ ከነበረው የG7 ስብሰባ በኋላ፣ የተነሳው የቃላት ጦርነት እንደቀጠለ ነው።

🇺🇦⚡️ዩክሬን በሩሲያ ላይ በቀጠለችው ጥቃት፣ በዚህ ሰዓት፣ 310 የድሮን መንጋዎችን ወደ ክራይሚያ እና ምዕራብ ሩሲያ አቅጣጫዎች ልካለች።
🇺🇦⚡️ዩክሬን በሩሲያ ላይ በቀጠለችው ጥቃት፣ በዚህ ሰዓት፣ 310 የድሮን መንጋዎችን ወደ ክራይሚያ እና ምዕራብ ሩሲያ አቅጣጫዎች ልካለች።

🇮🇱🇮🇳🇺🇸 ኔታንያሁ፣ አሁን ላይ እስራኤልን የምትደግፍ የመጨረሻዋ ሀገር አሜሪካ ነች፣ የሚለውን የምክትሉን JD Vanceን አባባል፣ እንደማይስማማበት ተናገረ። ይህን ያለው ዛሬ ከFOX NE
🇮🇱🇮🇳🇺🇸 ኔታንያሁ፣ አሁን ላይ እስራኤልን የምትደግፍ የመጨረሻዋ ሀገር አሜሪካ ነች፣ የሚለውን የምክትሉን JD Vanceን አባባል፣ እንደማይስማማበት ተናገረ። ይህን ያለው ዛሬ ከFOX NEWS ጋር በነበረው ቆይታ ነው። ኔታንያሁ፣ "ሕንድ የምትባል ትንሽ ሀገርን ጨምሮ ብዙ ወዳጆች አሉን። 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ አላት እና ከዚያ ከፍተኛ መጠን ያለው ድጋፍ እናገኛለን። በፌስቡክ ላይ በሕንድ ውስጥ ካሉ ሰዎች ከፍተኛ ድጋፍ በሚያሳዩ መልእክቶች እጥለቀለቃለሁ፣ ብሏል። *-*-*- ለአሜሪካ እኮ ሌላው ሀገር እና ሕዝብ፣ እንደ ሀገር እና ሕዝብ የሚቆጠር አይደለም። አሜሪካ ማለት፣ "የፈረንሳይ ሕዝብ ስንት ነው ስትባል ቤተሰቧን ቆጥራ 100 ብንሆን ነው እንዳለችውና የሕዝቡ ቁጥር 5 ሚሊዮን ነው ስትባል፣ "ትርኪ ምርኪውን" ቆጥራችሁ ነው እንዴ? እንዳለችው የፈረንሳይ ንግሥት ናት። እና JD VANCE አልተሳሳተም። አሁን እስኪ ሕንድ፣ ላዎስ፣ ሲሪላንካ፣ ታንዛኒያ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ አብይ አሕመድ እና ምናምንቴዎች ይወዱኛል ብለህ በአደባባይ ብታወራ …ኧረ። ለምን መሰላችሁ፣ እንዲህ ያሉ ሀገሮች ቢወዷችሁ ወይም ቢጠሏችሁ፣ ምንም ማምጣት ስለማይችሉ ነው። እሴት አይጨምሩላችሁም።  

—🇽🇰/ 🇺🇸 የኮሶቮ ኢማም በፕሪስቲና በሚገኘው መስጊድ የአሜሪካን የነጻነት ቀን ለማክበር የዩናይትድ ስቴትስን ባንዲራ ከፍ አድርጎ ሰቅሏል። God Bless America አላህ አሜሪካን ይባርክ፣ እያለም ዘምሯል።