ASTU Network ®️
Ir al canal en Telegram
🛜 ASTU Network ®️ ➲ Join us || @ASTU_Network || || @ASTU_Network_Group || 📚 Library: @ASTU_Network_Library 👁🗨 We are here to keep you updated! ➲ Admin 📩 👤 @NS_Nazu Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷] |➲| @ASTU_Network
Mostrar más5 174
Suscriptores
+1124 horas
+1517 días
+23430 días
Archivo de publicaciones
5 174
I created an ASTU Gallery topic in our ASTU Network Library group. You can get 700+ photos of ASTU and its environment.
🔗 Get it here 👇
ASTU Gallery 🖼
|➲| @ASTU_Network
5 174
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።
የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።
ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
5 174
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
5 174
በChina እየተዘጋጀ ባለው የHumanoid robot ውድድር ብዙ አስገራሚ ነገሮች እየታዩ ነው።
በዚህ ውድድር ላይ የአለማችን ፈጣኑ ሰው የUsian Bolt የ100 ሜትር ሪከርድ ተሰብሯል።
የቻይናው ስማርትፎን እና ቴክኖሎጂ አምራች ኩባንያ Honor ያበለጸገው Lightning የተሰኘው ባለ ሁለት እግር Humanoid ሮቦት 100 ሜትርን በ9.39 ሰከንድ በመጨረስ ታሪካዊ ውጤት ማስመዝገቡ ተዘግቧል።
ይህ ሰዓት ጃማይካዊው ፈጣን ሯጭ ዩሴን ቦልት እ.ኤ.አ. በ2009 የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ያስመዘገበውን የ9.58 ሰከንድ የሰው ልጆች ክብረ ወሰን በ0.26 ሰከንድ የሚያሻሽል ነው።
Lighting ከዚህ ቀደም በሚያዝያ ወር በተካሄደው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን (21 ኪሎ ሜትር) ላይ ተሳትፎ 50 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቶ እንደነበር ይታወሳል።
የስፖርት ባለስልጣናት ይህ ሰዓት በሮቦት የተመዘገበ በመሆኑ ከሰው ልጆች ኦፊሴላዊ የዓለም አትሌቲክስ ክብረ ወሰን ጋር በቀጥታ እንደማይመደብ ቢገልጹም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ውስጥ የታየ ታላቅ እመርታ መሆኑ ተነግሯል።
@bighabesha_softwares
5 174
#Fun 😸
I am breaking the deal for the ASTU Dating ad, quitting it, and returning the money because I just can't be comfortable with it. Lmao! 😅
.
5 174
#NGAT_Schedule
የ2018 ዓ.ም መጨረሻ ዓመት ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የፈተና መስጫ መርሐግብር፦
ፈተናው በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
@tikvahuniversity
5 174
የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድም እና እህቶቻችን... 🙂
እንኳን ለ1501ኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የሰላም እና የበረከት ይሁንላችሁ።
መልካም በዓል! ☪
|➲| @ASTU_Network
5 174
ለሁሉም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አሳቴዩ) የመፈተኛ ጣቢያ ለመፈተን ምርጫችሁ ላደረጋችሁ የሀገር አቀፍ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች በሙሉ!
=================
የሀገር አቀፍ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከነሃሴ 20/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይሰጣል።
ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያችን (አሳቴዩ) የመፈተኛ ጣቢያ ለመፈተን ምርጫችሁ ላደረጋችሁ ተመዝጋቢዎች በሙሉ፤
ስም ዝርዝራችሁን፣ የመፈተኛ ክፍላችሁን እና የመፈተኛ መርሃ ግብር ከዚህ ማስታወቂያ ጋር የተያያዘ ስለሆነ በመርሃ ግብሩ መሰረት መፈተን የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
5 174
Repost from 𝐀𝐒𝐓𝐔 𝐄𝐧𝐭𝐞𝐫𝐭𝐚𝐢𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 ™️
POV: ቅዳሜ መግለጫ ሰጥተው ውጤቱን ሰኞ ወይም ማክሰኞ እንለቃለን ሲሉ...
*G12th ውጤት እስኪለቀቅ be like... 😅
.
5 174
ውጤት መቼ ይታያል ?
ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።
በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
5 174
የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና ዋና መረጃዎች‼️
📊 የማለፊያ ውጤት
• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።
• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።
• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
🏫 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88
➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።
💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ
• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።
🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ
🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2%
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።
🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ
• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት
• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት
• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት
📌 በአጠቃላይ፦ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል። በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።
[አዩዘሀበሻ]
=====================
💎⬇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
5 174
#National_Exam_Result
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት፦
ተፈጥር ሳይንስ
ወንድ - 591.6 ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት (አዳማ)
ሴት - 583 አገው ምድር ት/ቤት (እንጅባራ)
ማኅበራዊ ሳይንስ
ወንድ - 576.2 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት
ሴት - 569.1 ቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት
@tikvahuniversity
5 174
ከፍተኛ ውጤት !
በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 576.2 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ተመዝግቧል።
በሴት 569.1 ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
5 174
#National_Exam_Result
| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ለተማሪዎች ይላካል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላ እና ቅበላ ካደረጉ በኋላ ሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች ቶሎ ጥሪ እንዲያደርጉ እየሠራን ነው። መስከረም 05/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመር የሚለውን ለመጠበቅ እንፈልጋለን።
@tikvahuniversity
5 174
" የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ዘንድሮ ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል። " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
5 174
#National_Exam_Result
በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።
ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70,544 ወይም 12.8% የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።
በመላ አገሪቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 88 ትምህርት ቤቶች 100% ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁ ሲሆን፣ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።
@tikvahuniversity
