es
Feedback
𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️

𝗕𝗘𝗠𝗡𝗘𝗧 ✍️

Ir al canal en Telegram

✍️

Mostrar mĂĄs
6 394
Suscriptores
+1524 horas
+607 dĂ­as
+5630 dĂ­as
Atraer Suscriptores
julio '26
julio '26
+65
en 0 canales
junio '26
+196
en 1 canales
Get PRO
mayo '26
+148
en 0 canales
Get PRO
abril '26
+108
en 0 canales
Get PRO
marzo '26
+60
en 0 canales
Get PRO
febrero '26
+74
en 0 canales
Get PRO
enero '26
+73
en 1 canales
Get PRO
diciembre '25
+66
en 1 canales
Get PRO
noviembre '25
+100
en 0 canales
Get PRO
octubre '25
+73
en 0 canales
Get PRO
septiembre '25
+39
en 0 canales
Get PRO
agosto '25
+64
en 1 canales
Get PRO
julio '25
+101
en 1 canales
Get PRO
junio '25
+52
en 3 canales
Get PRO
mayo '25
+79
en 3 canales
Get PRO
abril '25
+62
en 4 canales
Get PRO
marzo '25
+148
en 3 canales
Get PRO
febrero '25
+125
en 4 canales
Get PRO
enero '25
+207
en 4 canales
Get PRO
diciembre '24
+398
en 3 canales
Get PRO
noviembre '24
+302
en 5 canales
Get PRO
octubre '24
+228
en 4 canales
Get PRO
septiembre '24
+130
en 4 canales
Get PRO
agosto '24
+511
en 5 canales
Get PRO
julio '24
+1 071
en 3 canales
Get PRO
junio '24
+945
en 4 canales
Get PRO
mayo '24
+783
en 3 canales
Get PRO
abril '24
+584
en 1 canales
Get PRO
marzo '24
+251
en 4 canales
Get PRO
febrero '24
+415
en 2 canales
Get PRO
enero '24
+176
en 1 canales
Get PRO
diciembre '23
+374
en 3 canales
Get PRO
noviembre '23
+754
en 6 canales
Get PRO
octubre '23
+487
en 2 canales
Get PRO
septiembre '23
+676
en 4 canales
Get PRO
agosto '23
+1 559
en 2 canales
Fecha
Crecimiento de Suscriptores
Menciones
Canales
07 julio0
06 julio+15
05 julio+14
04 julio+8
03 julio+7
02 julio+15
01 julio+6
Publicaciones del Canal
48ቱ የሃይል ህጎች The 48 Laws of Power (በሮበርት ግሪን የተጻፈው ታዋቂ መጽሐፍ) ስልጣንን ለማግኘት፣ ለመጠበቅ እና እራስን ለመከላከል የሚያስችሉ ስልቶችን ያብራራል። 48ቱ የሀይል ህጎች በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው፡ 📌ህግ 1 - 12፡ ራስን መደበቅ እና መሰረትን መጣል ህግ 1፡ መሪህን ወይም አለቃህን በጭራሽ አትብለጠው። ህግ 2፡ በጓደኞችህ ላይ ከመጠን በላይ አትተማመን፤ ጠላቶችህን እንዴት እንደምትጠቀምባቸው እወቅ። ህግ 3፡ አላማህንና እቅድህን ደብቅ። ህግ 4፡ ሁልጊዜ ከሚያስፈልገው በላይ አነስተኛ ነገር ተናገር። ህግ 5፡ ስምህን በጥንቃቄ ጠብቅ፤ በስምህ ላይ ብዙ ነገር ይወሰናልና። ህግ 6፡ በማንኛውም ዋጋ የሰዎችን ትኩረት ስብ። ህግ 7፡ ስራውን ሌሎች እንዲሰሩት አድርግ፤ ምስጋናውን ግን አንተ ውሰድ። ህግ 8፡ ሌሎች ሰዎች ወደ አንተ እንዲመጡ አድርግ፤ ካስፈለገ ማጥመጃ ተጠቀም። ህግ 9፡ በድርጊትህ እንጂ በክርክር አታሸንፍ። ህግ 10፡ በስጋትና በሀዘን ከተሞሉ (እድለቢስ) ሰዎች ራቅ። ህግ 11፡ ሰዎች በአንተ ላይ ጥገኞች እንዲሆኑ ማድረግን እወቅ። ህግ 12፡ ሰዎችን ለማንበርከክ ታማኝነትንና ልግስናን በስትራቴጂ ተጠቀም። 📌ህግ 13 - 24፡ የበላይነትን መያዝ እና ሰዎችን መምራት ህግ 13፡ እርዳታ ስትጠይቅ በምስጋና ሳይሆን በሰዎች ፍላጎትና ጥቅም ላይ ተመስረት። ህግ 14፡ እንደ ወዳጅ በመቅረብ እንደ ሰላይ መረጃ ሰብስብ። ህግ 15፡ ጠላትህን ፈጽመህ አጥፋው (ደቅቀው)። ህግ 16፡ ተደራሽነትህን በመቀነስ ክብርህንና ተሰሚነትህን ጨምር። ህግ 17፡ ሌሎች ሰዎችን በስጋት ውስጥ አቆይ፤ ባህሪህ የማይገመት ይሁን። ህግ 18፡ እራስህን ለመጠበቅ ምሽግ አትስራ፤ መገለል አደገኛ ነው። ህግ 19፡ የምትጋፈጠውን ሰው ማንነት እወቅ፤ የተሳሳተ ሰው ላይ አትነሳ። ህግ 20፡ ለማንም ወገን በግልፅ አትገዛ (ገለልተኛ ሁን)። ህግ 21፡ ሞኝ ለመምሰል ሞኝ ሁን፤ ከተፎካካሪህ በላይ ብልህ መሆንህን ደብቅ። ህግ 22፡ የእጅ መስጠት ስልትን ተጠቀም፤ ድክመትን ወደ ሀይል ቀይረው። ህግ 23፡ ሀይልህንና አቅምህን በአንድ አላማ ላይ አተኩር። ህግ 24፡ ፍጹም የሆነ የቤተ-መንግስት ሰው (ዲፕሎማት) ሁን። 📌ህግ 25 - 36፡ ተፅዕኖ መፍጠር እና ስልትን መቀየር ህግ 25፡ እራስህን እንደገና ፍጠር (የማንነትህ መሀንዲስ ሁን)። ህግ 26፡ እጆችህን ከቆሻሻ ስራዎች ንጹህ አድርግ። ህግ 27፡ ሰዎች እንዲከተሉህ የሰዎችን እምነት ተጠቀም። ህግ 28፡ ድርጊቶችን በድፍረት ጀምር። ህግ 29፡ እስከ መጨረሻው ድረስ አስቀድመህ እቅድ አውጣ። ህግ 30፡ ስኬቶችህ በቀላሉ የተገኙ አስመስለህ አሳይ። ህግ 31፡ አማራጮችን ተቆጣጠር፤ ሌሎች አንተ የመረጥከውን እንዲመርጡ አድርግ። ህግ 32፡ በሰዎች ቅዠትና ምኞት ላይ ተጫወት። ህግ 33፡ የእያንዳንዱን ሰው ደካማ ጎን (ብሎን) እወቅ። ህግ 34፡ ንጉሳዊ ባህሪ ይኑርህ፤ ንጉስ ለመሆን እንደ ንጉስ አስብ። ህግ 35፡ ጊዜን የመቆጣጠር ጥበብን እወቅ። ህግ 36፡ ልታገኘው የማትችለውን ነገር ናቀው፤ ችላ ማለት ትልቅ በቀል ነው። 📌ህግ 37 - 48፡ ስልጣንን ማጠናከር እና መጠበቅ ህግ 37፡ ማራኪ የሆኑ ትርኢቶችንና ምስሎችን ፍጠር። ህግ 38፡ እንደፈለግክ አስብ፤ ነገር ግን እንደ አብዛኛው ሰው ሁን። ህግ 39፡ አሳ ለማጥመድ ውሃውን አናውጠው (ጠላትህን አበሳጭ)። ህግ 40፡ በነጻ የሚሰጥን ማንኛውንም ነገር ንቀው (ነጻ ምሳ የለም)። ህግ 41፡ በትልልቅ ሰዎች ፈለግ ውስጥ ከመግባት ተቆጠብ። ህግ 42፡ እረኛውን ምታው፤ መንጋው ይበተናል (መሪውን ለይተህ አጥቃ)። ህግ 43፡ በሰዎች ልብና አእምሮ ላይ ስራ። ህግ 44፡ የመስታወት ስልትን በመጠቀም ጠላትህን ግራ አጋባው። ህግ 45፡ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ስበክ፤ ነገር ግን በአንድ ጊዜ ብዙ አትለውጥ። ህግ 46፡ ፍጹም መስለህ ለመታየት አትሞክር (ቅናት እንዳይቀሰቀስ)። ህግ 47፡ ካቀድከው በላይ አትሂድ፤ ካሸነፍክ በኋላ መቼ ማቆም እንዳለብህ እወቅ። ህግ 48፡ ቅርጽ አልባ ሁን (እንደ ውሃ ተለዋዋጭ ሁን) ። 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET

2
Sin texto...
120
3
🟡• ገንዘብ ሰርታቹ ህይወትቹን መቀየር ትፈልጋላቹ ❓ እንግድያውስ 💸 1X ቤቲንግ 💸 ተቀላቀሉ - JOIN በሉ እና ገንዘብ ስሩ 💰 🤑 🇬🇧 ለመቀላቀል 👉👇 JOIN https://t.me/
🟡• ገንዘብ ሰርታቹ ህይወትቹን መቀየር ትፈልጋላቹ ❓ እንግድያውስ 💸 1X ቤቲንግ 💸 ተቀላቀሉ - JOIN በሉ እና ገንዘብ ስሩ  💰 🤑 🇬🇧 ለመቀላቀል 👉👇 JOIN https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0
132
4
የሀገር ፍቅር መግለጫው "ኢትዮጵያ" አልበም በዓለም አቀፉ Billboard World Albums ሰንጠረዥ ላይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ የሀገራችንን ስም በአለም አደባባይ ያስጠራ ድንቅ ስራ ነው ። 🥰🥰�
የሀገር ፍቅር መግለጫው "ኢትዮጵያ" አልበም በዓለም አቀፉ Billboard World Albums ሰንጠረዥ ላይ 1ኛ ደረጃ በመያዝ የሀገራችንን ስም በአለም አደባባይ ያስጠራ ድንቅ ስራ ነው ። 🥰🥰🥰 9 ቀናት ብቻ ቀሩ .... ! 🌍📈 😍| @TEDYAFROETHIOPIA ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
1
5
የሆነው ሁሉ ሁኖ መጨረሻ ላይ ሕሊና አዕምሮን ፈልጋ ስትሔድ በሩን ዘግተው ሊያስቆሟት የሚሞክሩት እኒያው ደባል ሱሶቹ ነበሩ። የዚያኔ ግን ድክመቷን ብቻ ሳይሆን ድክመቶቹንም ጠንቅቃ ስለተረዳች ማናቸውም ሊያስቆሟት አልቻሉም። የወይን አበባዬ 📯 የወይን 🎶😊😊😊
365
6
የወንዶች ጉዳይን ከሳቅ በዘለለ መረዳት የሚፈልግ አንድም ጤነኛ ሰው ያለ አይመስለኝም። እኔ ግን ጤና ስለሚጎለኝ የወደድኩትን ነገር እስክጠላው ድረስ መጎርጎሬን አላቆምም። የመጀመሪያው ጥያቄዬ "ደራሲው የዋና ገፀባሕሪዎቹን ስም አዕምሮ እና ሕሊና ያለው ባጋጣሚ ነው?" የሚለው ነበር። በርግጥ ይሕ ጥያቄ ብቻውን ወደ ሌላ አለም ይወስደኛል ብዬ አላሰብኩትም። ምክኒያቱም ሌሎች ደራሲዎች እንዲህ አይነት ነገር የሚያደርጉት ከላይ ሲታይ ደስ ስላላቸው ብቻ ነው የሚሆነው። አድማሱ ግን የደበቀውን ታሪክ እንድናገኝበት ያስቀመጠልን ካርታ ነበር። ፊትለፊታችን ሁኖ የተሰወረው ስቶሪ ባጭሩ ይሕ ነው። አዕምሮ ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ሲል ሕሊናውን እየዋሻት ነው። እንዲዋሻት የሚተባበሩት ደግሞ ስድስት ደባል ሱሶች አሉበት😃 ላይሆን ይችላል...ይሕ ቲዎሪ ብቻ ነው። እስከሚያስኬደን ድረስ እንሒድበት🙂 ወዳጆቹ...እስከጥግ የሚገዙለት አንድ ነገር አላቸው። አንደኛው ያገኘውን የሚያገበሰብስ ሆዳም ነው። አንደኛው አላፊ አግዳሚውን የሚያስረግዝ ዘማዊ ነው። አንደኛው ሰርግ ቤት ሳይቀር ከመለኮስ የማይመለስ አጫሽ ነው። አንደኛው ከሰከንድ በፊት ያገኛትን ሴት ቂጧን ካልጨበጥኩ የሚል ሴሰኛ ነው። አንደኛው እቁብ ሲወጣለት ልብስ ልግዛ ሶፋ ልቀይር ሳይሆን "ዛሬ ይጠጣል!" የሚል ጠጃም ነው። አንዳቸውም በሰውነታቸው ላይ ሀይል የላቸውም። ህይወታቸው በሱሳቸው ዙሪያ ነው የሚያጠነጥነው። ሱሰኛ ብቻ ሳይሆን ሱስ ራሱ ናቸው። ግን አትጠሏቸውም። በጣም ነው የሚያዝናኑት። ሲጫወቱ ለምናያቸው ለኛ "ጓደኞቼ በሆኑ!" የሚያስብሉ ናቸው። ያው ሱስ ሱስን ይወዳልና አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው የመሰረቱት ማሕበርም አላቸው። የዚህ ማሕበር አስተባባሪ እና ዋና ፀሀፊ ቀጮ ነች። ቀጮ እንደሌሎቹ ሱስን አትወክልም። "ታዲያ ሱስ ካልሆነች ሱሶችን የምትሰበስባቸው እሷ ማነች?" ልትሉ ትችላላችሁ። ቀጮ ማለት ሴት ሁና ሳለ ራሷን እንደ ሴት የማታይ ሰው ነች። "ሴቶች" እየተባለ ሲወራ እንኳን እኔን ይመለከተኛል ብላ አትሰማም። ለዛም ነው ወንዶች ሴቶች ላይ ለሚፈፅሙት ተንኮል ተባባሪ ሁና የምትገኘው። ያ ማለት ግን ሴቶችን ትንቃለች ማለት አይደለም። የምትንቀው ራሷን ነው። አዕምሮን ስትመርቅ እንኳን "ቀጠን ያለችዋን፤ እንደ እንዝርት ተሽከርካሪዋን፤ እንደ ዳር ተወርዋሪዋን ያጋጥምህ!" ነው የምትለው። የሷ ምርጥ ሴት...እሷን የማትመስል ነች። ስለዚህ የነዚህ ሱሶች ሰብሳቢ የወረደ በራስ መተማመን ያላት እና ከተቃራኒ ወገን ተሰልፋ የምትዋጋ ፍጡር መሆኗ ስሜት ይሰጣል። ሱሶችን የሚጠራቸው ይሔ አይነቱ ራስ ጠልነት ነው'ና! (ቀጮ Insecurity ነች እያልኩ ነው ምዕመናን😭) አዕምሮም ወደነሱ የተሳበው በዚችው ጎኑ ነው። ማሕበራቸውን እንዲቀላቀል ያላደርጉት ጥረት አልነበረም። አንዱም አልሰራም። የሚወዳት ፍቅረኛው ከውጭ ለመጣ ሰው ጥላው መሔዷም ለሽንፈት አላበቃውም። ከዛ በፊትም ብዙ ሴት ጋ ተለያይቷል። ብርቁ አይደለም ፍቅሩን ማጣት። ለሽንፈት ያጋለጠው ከመሔዷ በፊት የጣለችበት ንግግር ነው። "አንተን ብዬ መቼም ከምመኛት አሜሪካ መቅረት አልችልም!!!" 😃 ይሕ ንግግር ጥላቻም የለውም። ርሕራሔም የለውም። ምርር ያለ እውነት ብቻ ነው።  ይሔንን እውነት ለመዋጥ አዕምሮን Pride ያንቀዋል። ያጥወለውለዋል። ስራ ትቶ መኝታ ላይ ይውላል። የዚያኔ ማሕበርተኞቹ ደም እንዳሸተተ ሻርክ ተቀላቀለንና ከሀዘንህ እናድንህ እያሉ ይዞሩታል። የደረሰበትን ሽንፈት እምደሚያስረሱት ደጋግመው ቃል ይገቡለታል። መፍትሔው ያለው በነሱ እጅ እንደሆነ ጨቅጭቀው ያሳምኑታል ልክ ሁነውም ይገኛሉ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከወደቀበት ተነስቶ መሳቅ መጫወት ይጀምራል። ሕሊናውን ከመዋሸት ቢሆንም ደስታው የተገኘው ከነበረበት መጥፎ ስሜት አንፃር ይሔ አስር እጥፍ የሚሻል መንገድ ይሆንለታል። "አሁንማ እንከባከብሀለን ቅድም እኮ ቅጥል ነው ስታደርገን የነበረው!" እያሉ የበለጠ ሰምጦ እንዲገባ ያበረታቱታል። ውሸቱ እንዲሰራ መንገዱን ያሳልጡለታል። ፅዋ ያነሱለታል። እጃቸውን ጭነው ይመርቁታል። ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ይሆናል። ችግሩ ይሔንን ስሜት ለማስቀጠል ሁሌም ጧት ተነስቶ አንድ አዲስ ውሸት መዋሸት አለበት። ዛሬ አለቃውን አታልሎ ከስራ የቀረ እንደሆነ ነገ ደግሞ የእህቱን ሽቶ ሰርቆ ቤቱን መበጥበጥ ይኖርበታል። ደባል ሱሶቹ ለሚሰጡት ደስታ በምላሹ ከሱ የሚጠይቁት ሕሊናን እንዲተኛት፤ በውሸት አለም ውስጥ እንዲያባክናት...ባጭሩ Corrupt እንዲያደርጋት ነው። እንደመጀመሪያዎቹ ጊዜያትም  ቶሎ ቶሎ አይስቁለትም። በሆነ ባልሆነው ነው የሚነጫነጩበት። "ታዲያ አዕምሮ ይሔ ሁሉ ውሸት ውስጥ ሲዋኝ ሕሊና እንዴት መጠርጠር ይሳናታል?" የሚለው ሁለተኛው ጥያቄዬ ነበር። እንግዲህ አዕምሮ የምናዬው የምንዳስሰው የማሰቢያ ማሽን ነው። ይሕን ማሽን የሚጠልፉትም የምናያቸው የምንዳስሳቸው አደንዛዥ ዕፆች ናቸው። ሕሊና ግን የማናያት፤ 'ማንዳስሳት...አዕምሯችንን እየወቀሰች በትክክለኛው መንገድ እንዲሔድ የምታስገድደው ስውር አለቃችን ነች። ህሊናን ሱስ አያሸንፋትም። እሷን ሚጠልፋት እንደሷ ለማዬት ለመዳሰስ የሚከብደው ዲያቢሎስ አልያም እርኩስ መንፈስ ነው። ሸዊት የምትጫወታት ገፀባህርይ (ማርታ) የምትወክለው ይቺን ከሕሊናችን ጆሮ ላይ የማትጠፋውን አንሾካሿኪ ድምፅ ነው🙂 ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአዕምሮ ውሸቶች የምትማልለው እሷ ነች እንጂ ሕሊና አልነበረችም። በፍቅሩ ተይዛለች። "ሶፋ ብናስቀይረው፤ ወርቅ ብናስገዛው" እያለቻት ነው ጆሮዋ ላይ ቁማ። ሐሳቧን ውድቅ እንዳታደርግባት ደግሞ ለቤተሰባችን ስንል ነው እያለች ታግባባታለች። ቤት የጋበዘችው ቀን ሶፋቸው መበላሸቱን ነግራ ልታስገዛው ስትሞክር አዕምሮ "እሰራዋለሁ!" ብሎ መዶሻ ነገር ፍለጋ ይገባል። ማርቲ አመዷ ቡን ብሎ "ምንም ነገር የለንም...ጎረቤትም የላቸውም!" ስትለው ሕሊና ተነስታ ከጠረንጴዛው ስር የተቀመጠውን ዘነዘና ትሰጠዋለች። የአዕምሮ እውነተኛ ማንነነቶች ፈንቅለውት በሚወጡበት ቅፅበቶች ሁሉ ሕሊናን ይማርካታል። በተቃራኒው ማርታን ያቅለሸልሻታል። ሁለቱ ያለ ሶስተኛ ወገን ብቻቸውን ሲገናኙ የሆነ ደስ የሚል ነገር አላቸው። አንዳቸው ላንዳቸው ነው የተፈጠሩት ያስብላሉ። መዋደዳቸውም ያስቀናል። ነገር ግን መሰረቱ ወሸት ላይ ነው'ና ሒሳቡ ሳይወራረድ ግኑኝነቱ ሊፀና አይችልም። አዕምሮ መቼም መቼም መቼም ቢሆን ከገባበት ክብ መውጣት አይችልም። ከገባበት ክብ ልታወጣው የምትችለው ሕሊናው ብቻ ነች። እሷ ደግሞ እሱን ማውጣት እንድትችል በቅድሚያ ጆሮዋ ላይ ያለችውን መንፈስ ጠንቅቃ መረዳት ይኖርባታል። መረዳት ብቻ ሳይሆን ንቃ መተው መቻልም አለባት። ያን ማድረግ እንድትችል መንፈሳዊ እገዛ ትፈልጋለች። ለዛ ነው የቤተክርስቲያኑ ትዕይንት ትክክለኛ ቦታ ላይ ገብቷል የምለው። አዕምሮ እንደልማዱ "ጌታዬ ውሸቴን የማስቀጥልበት ገንዘብ ስጠኝ!" አይነት ፀሎት ይፀልያል። እሷ ግን እውነቱን መኖር እንዲጀምሩ ነው የምትማፀነው። ጌታም የሕሊናን ልመና ሰምቶ የጠዬቀችውን ብርታት ይሰጣታል። ማርታ ያስጀመረቻትን ድራማ ትታ ሀቁን በማፍረጥረጥ አዕምሮን ከገባበት ስካር ታባንነዋለች። ነፍሱ ስትያዝ ይናዘዛል። መክፈል ያለበትን የንስሀ ዋጋ ይከፍላል። እውነቱን ማውራት ሲጀምር እሷም እንዳዲስ እየወደደችው ትመጣለች ።
359
7
Sin texto...
295
8
ዳርክ ሳይኮሎጂ (Dark Psychology) "#ዳርክ ሳይኮሎጂ" የሚለው ቃል ሰዎችን ለማታለል፣ ለመቆጣጠር እና ለመጉዳት የሚያገለግሉትን የስነ-ልቦና ዘዴዎች፣ ተግባሮች እና ሃሳቦች ለመግለጽ የሚጠቀ
ዳርክ ሳይኮሎጂ (Dark Psychology) "#ዳርክ ሳይኮሎጂ" የሚለው ቃል ሰዎችን ለማታለል፣ ለመቆጣጠር እና ለመጉዳት የሚያገለግሉትን የስነ-ልቦና ዘዴዎች፣ ተግባሮች እና ሃሳቦች ለመግለጽ የሚጠቀም ጽንሰ-ሐሳብ ነው። ይህ የስነ-ልቦና ክፍል ሰዎች እርስ በርስ የሚጠቀሙበትን ጥልቅ ግምቶች፣ የማያሻማ ጉዳቶች እና የስነ-ልቦና ጥቃቶች ያጠቃልላል። #ዋና ዋና አካላት 1. #ማኒፑሌሽን (Manipulation) · ሰዎችን ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ወይም እንዲሰሩ በማድረግ ላይ ያተኮረ · ዘዴዎች፦ ጋዝላይቲንግ፣ ግርግር፣ ስነ-ልቦናዊ ጫና፣ ማጭበርበር 2. #ናርሲሲዝም (Narcissism) · በራስ የተደገመ እምነት፣ ግላዊነት እና ሌሎችን አናሳ የማየት ባህሪ · ሌሎችን ለግላዊ ጥቅም ብቻ መጠቀም 3. #ማኪያቬላኒዝም (Machiavellianism) · ዓላማውን ለማሳካት ማንኛውንም ዘዴ (እንደ ማታለል፣ ማጭበርበር) መጠቀም · በስልጣን እና ቁጥጥር ላይ ያተኮረ 4. #ሳይኮፓቲ (Psychopathy) · ስሜት አለመኖር፣ ውድቀት እና የግብረ-ሰዶማዊ ባህሪ · በሌሎች ላይ ጉዳት ማድረስ ላይ ያለ ፍራቻ #የተለመዱ ዘዴዎች · ጋዝላይቲንግ (Gaslighting): የሰው እውነተኛነት እና አእምሮ እንዲጠራጠር ማድረግ · ማጭበርበር (Coercion): በግፊት ወይም አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ ማስገባት · ስነ-ልቦናዊ ዘብ (Psychological Warfare): የሰውን ስሜት እና አእምሮ ለመጉዳት የሚያገለግሉ ዘዴዎች #ተጽእኖዎች · የተጎዱት ሰዎች የራስ መገምገሚያ መቀነስ፣ የአእምሮ ጤና ችግሮች፣ የራስ ዋጋ መቀነስ · በግንኙነቶች፣ ቤተሰብ እና ስራ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ · የማህበረሰብ እና የሥራ ቦታ ውስጥ መበላሸት 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
502
9
🟡• ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ቻናሉን ከስር ያሉትን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉ
539
10
📚ርዕስ:- የዩትዩብ ምስጢሮች 📚 📝ደራሲ:-አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅ 📜ዘውግ:- ስለ ዩቲዩብ ቪዲዩ አሰራር 📖የገፅ ብዛት:- 158 📅 ዓ.ም :- 2017 💰የተቀመጠ ዋጋ :- 700 ብር 📚 የዩትዩብ ምስጢሮች 📚 📝ደራሲ:-አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅ 📜ዘውግ:- ስለ ዩቲዩብ ቪዲዩ አሰራር 📖የገፅ ብዛት:- 158 📅 ዓ.ም :- 2017 🖨size :- 47.6 MB 💰የተቀመጠ ዋጋ :- 700 ብር 👆አዘጋጅ:- @ambabooks 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
550
11
ይነበብ ‼️ “ እኛ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ፣ ደህና ሳንሆን እንኳን ‘ደህና ነኝ’ ማለት ግዴታ አድርገነዋል። ለራሳችን ስሜት ታማኝ መሆንን፣ እንዲሁም የሚሰሙንን የተለያዩ ስሜቶች ተረድቶ፣ ተቀብሎና ፈቅዶ ማስተናገድን አልተማርንም።" ሁልጊዜ 'ትሁት' ጨዋ ደግ ደስተኛ መስሎ መታየት’ የሚለውን ጭምብል መልበስ እንወዳለን። We need to say 'ደህና አይደለሁም፤ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም። ስፔስ እፈልጋለሁ፤ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ፤ ማውራት አልፈልግም።’ At the same time "እርዳታችሁ ያስፈልገኛል” ብለን የኛ የምንላቸውን ሰዎች እጅ መዘርጋትና እርዳታን መጠየቅ መልመድ አለብን። እርዳታ ሲባል ደግሞ ሁልጊዜ ከሰው የምንፈልገው ቁስ ብቻ አይደለም፤ እውነተኛ ፍቅር፣ የሞራል ድጋፍ፣ እቅፍ፣ ውድ ጊዜውን የሚሰጠን፣ ትከሻውን ተተርሰን እንድናለቅስ የሚፈቅድልን፣ “እኔ አለሁ” የሚለን፣ እና ስሜታችንን without judgment ያለ ምንም ፍርድ የሚያዳምጠን ሰውም ጭምር እንጂ! ድብርት Depression በፋይናንስ ወይም በገንዘብ እጥረት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን፣ እጅግ በጣም ውስብስብና በብዙ የተለያዩ ምክንያቶች ሊቀሰቀስ የሚችል የጤና ሁኔታ ነው። ብዙ ጊዜ ሰዎች “ቁሳዊ ፍላጎቱ የተሟላለት ሰው ለምን ይደብረዋል?” ብለው ያስባሉ፤ ይህ ግን ትልቅ ስህተት ነው። ለዚህ እኮ ነው ድብርት “የሀብታም ወይም የደሃ” ተብሎ የማይከፈለው። ትልቁ ስህተት ድብርትን ከሐዘን ወይም ከጭንቀት ጋር ማመሳሰል ነው። ሐዘን በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል ለምሳሌ ገንዘብ ሲጠፋ ወይም የቅርብ ሰው ሲታጣ...ድብርት ግን የአንጎል Chemical Imbalance ጭምር ስለሆነ፣ ሰውየው አልጋው ላይ ተኝቶ፣ ቪላ ቤት ውስጥ እየኖረ፣ እና ዙሪያውን በሰው ተከቦ እንኳ ሊያጠቃው ይችላል። ልክ ካንሰር ወይም የስኳር በሽታ ሀብታምና ደሃ ሳይል ሁሉንም እንደሚያጠቃው ሁሉ፣ ድብርትም የሰውን የባንክ አካውንት አይቶ አይመርጥም! ባጭሩ_"ገንዘብ ካለህ ደስተኛ ነህ " የሚለው ብሂል ማኅበረሰባዊ ተረት ነው። ማኅበረሰባችን ትዳርንና ልጅን እንደ ስነልቦና ሕክምና ማዘዣ Prescription የመቁጠር ትልቅ ስህተት አለበት። “ብዙ ጊዜ ወንድም ሆነ ሴት ጥሩ ያልሆነ ስሜት ውስጥ እንደገቡ ሲናገሩ_"ትዳር መሥርቱ፣ ከልጆቻችሁ ጋር ስትጫወቱ ትረሱታላችሁ” ይባላል። ይሄ ግን በፍጹም ትክክል አይደለም! ቤተሰብና ልጆች ያሉትም ሰው ቢሆን ይህንን የድብርት ስሜት ያስተናግዳል። ይህ የሚሆነው ደግሞ ልጆቹ ደስታ ስለማይፈጥሩለት ወይም ደስተኛ ቤተሰብ ስለሌለው አይደለም። ነገር ግን በተለይ ሴት ልጅ... ልጆችና ቤተሰብ ካላት “ደስተኛ መሆን ግዴታዋ እንደሆነ” ይታመናል፤ “ምን ጎደላት?” ይባላል። ይሄ ግን ፈጽሞ አግባብ አይደለም! ለዚህ እኮ ነው ካላገቡ ሴቶች ይልቅ ያገቡ ሴቶች በድብርት የሚሰቃዩት። እነሱ ራሳቸው ያሉበትን ስሜት ላያውቁት፣ ላይረዱትና ላይቀበሉት ይችላሉ። ምክንያቱም በተለምዶ “ልጆችና ቤተሰብ ያላት ሴት ደስተኛ መሆን አለባት፣ ልጆቿም ያስደስቷታል፣ ታዲያ ምን ጎድሏት ድብርት ውስጥ ትገባለች?” ተብሎ ስለሚታመን ነው። “ይህ አመለካከት በራሱ በሴቷ ላይ ሌላ ተጨማሪ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል፤ ምክንያቱም በአካባቢዋ ላሉ ሰዎች ይህንን ስሜቷን መንገርና መግለጽ እንኳን አትችልም። የሚረዳት አይኖርም፤ ብትናገርም “ምን ጎደለሽ?” ነው የምትባለው። እውነታው ግን... ሰው ሴት ስለሆነች ብቻ የምታስተናግደው የሆርሞንና የስሜት መዋዥቅ፣ mood swings እንዲሁም እሷን ይህንን ስሜት እንድትታገስ የሚያደርጉ ብዙ ተፈጥሯዊና ስነልቦናዊ ምክንያቶች አሉ። ትዳርና ቤተሰብ ግን ከዚህ የድብርት ስሜት አያድንም! ብዙ ጊዜ ማኅበረሰቡ “ብቸኝነት” የሚለውን ቃል የሚረዳው “ብቻን መሆን” ከሰው መለየት በሚለው ውጫዊ ትርጉሙ ብቻ ነው። እውነታው ግን “ብቸኝነት የሚሰማን ወዳጅና ዘመድ ስለሌለን አይደለም። በሰው ተከበን እንኳን... ምድር ላይ ከእኛ ውጪ ሰው የሌለ እስኪመስለን ድረስ፣ ጥልቅ የሆነ ባዶነትና ብቸኝነት ሊሰማን ይችላል። ካልተሳሳትኩኝ በ2020 ወይም በ2021 አካባቢ ነው፣ አልፎ አልፎ የማስተናግዳቸው ስሜቶች “ድብርት” Depression እና Mood swings እንደሆኑ ያወቅኩትና የተቀበልኩት። ከዛ በፊት ግን በወር አበባ መምጣትና መሄድ መካከል ባለው የሆርሞን ለውጥ ምክንያት የሚመጡ ስሜቶች ብቻ ይመስሉኝ ነበር። በ2020 ወይም በ2021 አካባቢ Whatever ፍልስጤማዊቷ ሞዴል Bella Hadid_አብዛኞቻችሁ የአቤል ተስፋዬ The Weeknd ፍቅረኛ በነበረችበት ጊዜ ታውቋታላችሁ—እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ ለረጅም ጊዜ ጓደኞቼ የሆኑ ሰዎች ደግሞ እኔ ቤላን ምን ያህል እንደምወዳት ያውቃሉ፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ በተለያየ ምክንያት ስለ እሷ ጽፌያለሁ። ቤላ ቆንጆ ብቻ አይደለችም፤ ወርቅ ልብ፣ ንጹሕና ረቂቅ ነፍስ ያላት ሴት ጭምር ናት። I love her badly በአንድ ወቅት በጣም በድብርት እየተሰቃየች እንደሆነ፣ ነገሮች ከቁጥጥሯ ውጭ እንደሆኑባት፣ እና የምታሳልፈውን ውጥረት፣ የሥራ፣ የግልና የማኅበራዊ ሕይወት ጫናዋን እያለቀሰች ኢንስታግራም ላይ ቪዲዮ ለቀቀች። ያደረገችው ትኩረት ለመሳብ Attention seeking ወይም እንዲታዘንላት ብላ አይደለም። እንደ አብዛኛው ካሜራ ፊት እንደሚያለቅስ ሰው ሳይሆን፣ እሷ የምታሳልፈው ችግር የሷ ብቻ እንዳልሆነ፣ የአብዛኛው ሰው በተለይ ደግሞ በየቤቱ ያለው የወጣቱ ችግር እንደሆነ ስለምታውቅ... “ብቻችሁን አይደላችሁም፣ በየትኛውም የሕይወት ደረጃ ላይ ብንሆን የዚህ ችግር ሰለባ ነን፣ እኛም ሰው ነን” እያለችን ነበር። That’s why I love her! በዚህ ፖስቷ ብዙ ሰው ተደሰተ፤ በርካታ ሰዎች በኮሜንት ላይ የውስጥ ብሶታቸውንና እያለፉበት ያለውን ችግር ገለጹ፤ አመሰገኗትም። አብዛኛው ሰው በግልጽ እንዴት በድብርት እንደሚሰቃይ፣ በተለያየ ሱስ ውስጥ እንደገባና ሕይወታቸው እንዴት ከባድ እንደነበር በነፃነት ያጋሩ ነበር። እኔም ከዚያን ወቅት ጀምሮ የሚሰማኝንና የማስተናግደውን ስሜት በጸጋ መቀበል፣ ማስተናገድ፣ እና በግልጽም በዚህ ስሜት ውስጥ እያለፍኩ እንደሆነ መናገር እንዳለብኝ ተረዳሁ። “የሆነ ጊዜ የኔ የምላቸውን ሰዎች እርዳታ ልፈልግ እችላለሁ፤ እቅፋቸውን፣ ትከሻቸውን፣ እንዲያዳምጡኝ... ወይም ደግሞ ውስጤ ያለውን ብስጭትና ንዴት የማወጣባቸው እንዲሆኑ እፈልግ ይሆናል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ብቻዬን መሆን ብቻ ይሆናል ፍላጎቴ። ወይም ደግሞ ፍጹም ከማያውቁኝና ደግሜ ከማላገኛቸው ሰዎች ጋር አእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱትን ነገሮች ማጋራትና ጊዜ ማሳለፍ ይሆናል የምመርጠው። ዋናው ቁምነገር... ራሴን ማዳመጥን፣ ለራሴ ጊዜ መስጠትን፣ እና የሚሰሙኝን የትኛውንም ስሜቶች በጸጋ ተቀብዬ እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድን ተምሬአለሁ። ይህንን ስሜት እናስተናግዳለን ማለት ግን “ዘላለም በዚህ ስሜት ውስጥ እንኖራለን” ማለት አይደለም። ለደቂቃዎች፣ ለሰዓታት፣ ለቀናት፣ ለሳምንታት ወይም ለወራት ሊሆን ይችላል። የጊዜ ገደቡ ምንም ያህል ይሁን ምን... ከዚህ ስሜት ወጥተን ሕይወታችንን እንቀጥላለን! ምክንያቱም We are human beings—ሮቦት አይደለንም !
693
12
🚨🚨 ገንዘብ አስቸኳይ ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽ ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL
🚨🚨 ገንዘብ  አስቸኳይ  ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽  ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0
166
13
ነብህ እና ፈላስፋ ማንም ሰዉ ድሀ እንዲሆን ወይም የሌሎች ባሪያ ተከታይ እንዲሆን የተበየነበት እጣ ፋንታ የለም። የውድቀቱም ሆነ ስኬቱ ሙሉ ምክንያት ራሱ ነው። በራሱ ላይ ያለው መረዳት አናሳ በመሆ
ነብህ እና ፈላስፋ ማንም ሰዉ ድሀ እንዲሆን ወይም የሌሎች ባሪያ ተከታይ እንዲሆን የተበየነበት እጣ ፋንታ የለም። የውድቀቱም ሆነ ስኬቱ ሙሉ ምክንያት ራሱ ነው። በራሱ ላይ ያለው መረዳት አናሳ በመሆኑ እንጂ ማንም የሆነውን እንዲሆን ቀድሞ የወሰነበት ነገር የለም። የትናንት ግንኙነታችን የሚናፍቀንን ያህል ደግመን ማሰብና ማስታወስ የማንፈልገው  የምንፈራዉና የምንጠላውም ትዝታ ይኖረናል። የታሰርንበትን የተደበደብንበትን የምንወደውን ሰው  ያጣንበትን የታመምንበትን ተቸግረን የተሰበርንበትን የመሳሰሉ ብዙ የተጎዳንባቸው ትናንቶችን ለማስታወስ አንደፍርም። በተቃራኒው ደስ የሚለንንና ብልጫ  ያየንባቸውን ትናንቶች ደግሞ እንናፍቃለን ለሰዎች ብናወራቸው ሞላ ያለ ክብር የሚያጎናጽፉን ለመሳሰሉት ትዝታዎች ናፍቆት ይኖረናል። እንደ ሀሳብ ደግሞ ተሽለን ያለፍንበት የእውቀትና የሙያ ጊዜ ይኖራል በሙያም ጥሩ የሰራንበት በእውቀትም የተሻለ መረዳት እንዳለን ማስታወስ የምንችለው የትናንት ልምድ ይኖረናል። እርሱንም ማሰባችን አይቀርም ሁለቱም የትናንታችን እኛነቶች ናቸው። ዛሬን ያደረጉን የየግል እድሜዎቻችን ናቸው። ሰዉ በተፈጥሮው በእነዚህ ሁለት የትናንት እሴቶቹ ይገነባል። ከሰዎች ጋር በኖራቸው ትዝታዎቹ ውስጥ የማኅበራዊነት ተፈጥሮውን ይማራል። በኖራቸው የየእለት ልምዶቹ ደግሞ በእውቀት ራሱን የሚያሳድግ አሳቢ ፍጡር መሆኑን ይመለከታል ። 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
667
14
🚨🚨 ገንዘብ አስቸኳይ ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽ ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL
🚨🚨 ገንዘብ  አስቸኳይ  ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽  ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0
631
15
You will get the analysis about backfire effect from page 116 to page 125. and There are also a lot of useful psychological points in the entire book The Humanist Road™ 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
694
16
የኋሊት መመለስ ውጤት (The Backfire Effect) ​በታዋቂው የስነ ልቦና ፀሀፊ ዴቪድ ማክሬኒ የተፃፈዉ “You Are Now Less Dumb” በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ካሰፈራቸው እጅግ አስገራሚ የሰው ልጅ የአስተሳሰብ ስህተቶች (Cognitive Biases) መካከል አንዱ የኋሊት መመለስ ውጤት (The Backfire Effect) ነው። ይህ ክስተት በዕለት ተዕለት ህይወታችን፣በፖለቲካዊ ክርክሮች፣ በሃይማኖታዊ እምነቶችና በማህበራዊ ግንኙነቶቻችን ውስጥ እኛ ሳናውቀው የአስተሳሰብ አድማሳችንን የሚያጥብብ ትልቅ ምሰሶ ነው። ​​በተለምዶ የሰው ልጅ አመክንዮአዊና ምክንያታዊ ፍጡር እንደሆነ ይታሰባል። ከአንድ እውነት ወይም እምነት ጋር የሚጋጭ የማያወላዳ ማስረጃና መረጃ ሲቀርብለት የቀደመ ስህተቱን አርሞ አዲሱን እውነት ይቀበላል ተብሎም ይገመታል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ ፍጹም ተቃራኒ ነው። ​እውነቱ ፦ አንድ በጽኑ የምናምንበትን አመለካከት የሚቃወም ጽኑ ማስረጃ ሲቀርብልን አመለካከታችንን ከመቀየር ይልቅ የቀደመ እምነታችን ይበልጥ እየጠነከረና እየገዘፈ ይሄዳል። ይህ ክስተት የስነ ልቦና ጠቢባን “የኋሊት መመለስ ውጤት” (The Backfire Effect) ብለው ይጠሩታል። ​ማስረጃው የቀደመ እምነታችንን ሊያፈርስ ሲመጣ አእምሯችን ያንን መረጃ እንደ አንድ ትልቅ አደጋና ጥቃት ነው የሚቆጥረው። በውጤቱም መከላከያ ግንቦችን በመገንባት የራሳችንን ሃሳብ ይበልጥ አጥብቀን እንድንይዝ ያደርገናል። ​ዴቪድ ማክሬኒ እንደሚያብራራው የሰው ልጅ አእምሮ ሁልጊዜም በዓለም ላይ የሚከናወኑ ነገሮችን ቀለል ባለ “የትረካ ታሪክ” (Narrative) መልክ መገንባት ይወዳል። ይህ የትርክት አዝማሚያ (Narrative Bias) የራሳችንን ማንነት እንድንቀርፅና በዓለም ላይ መረጋጋትን እንድናገኝ ይረዳናል። ​አንድ ሰው የገነባውን የማንነት ታሪክ ወይም ፅኑ እምነት የሚቃወም መረጃ ሲመጣ የሚከተሉት ሂደቶች ይከሰታሉ ​የአእምሮ አለመስማማት (Cognitive Dissonance)፦ ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ሃሳቦች በአእምሯችን ውስጥ ሲጋጩ ከፍተኛ የሆነ የጭንቀትና የውጥረት ስሜት ይፈጠራል። ይህንን ውጥረት ለማስወገድ አእምሯችን አዲሱን መረጃ ውድቅ ያደርገዋል። ​የማረጋገጫ አድልዎ (Confirmation Bias)፦ የኋሊት መመለስ ውጤት ከማረጋገጫ አድልዎ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የራሳችንን እምነት የሚደግፉ መረጃዎችን ብቻ መርጠን ስንሰበስብ የሚቃወሙንን ደግሞ ዓይናችንን ጨፍነን እናልፋለን። ​ባዮሎጂያዊ ምላሽ (Biological Response)፦ MRI የተደገፉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የአንድን ሰው እምነት የሚቃወም መረጃ ሲቀርብለት ምክንያታዊ አስተሳሰብን የሚመራው የአንጎል ክፍል የደም ዝውውር ይቀንሳል። አእምሯችን መረጃውን እንደ ጠላት ጥቃት በመቁጠር ራሱን ወደ መከላከያ ሁነታ (Defense Mode) ይለውጣል። ​​ይህ ክስተት በሰዎች መካከል በሚደረጉ ክርክሮች ላይ በግልጽ ይታያል። ለምሳሌ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከአንድ ሰው ጋር በሃይማኖት፣ በፖለቲካ ወይም በሳይንስ ዙሪያ ስንከራከር ግልጽና የማያወላዳ የቁጥር ወይም የታሪክ ማስረጃ ብናቀርብለትም፣ ግለሰቡ "እሺ ተሳስቼ ነበር" ሲል አይታይም። ይልቁኑም የቀረበዉ ማስረጃ ስህተት እንደሆነ ለመግለጽ ይበልጥ ይከራከራል፤ ክርክሩ ሲጠናቀቅም ከመጀመሪያው ይበልጥ በሃሳቡ ላይ የፀና ሆኖ ይወጣል። ​ማክሬኒ በመጽሐፉ ላይ እንደሚያሳየው እኛ የሌሎችን ሰዎች ስህተትና ምክንያታዊ አለመሆን በቀላሉ መመልከት እንችላለን። ነገር ግን ይህ እኛነታችንን የሚጠብቅ "የውስጥ ሴራ" በራሳችን አእምሮ ውስጥ ሲሰራ በፍፁም ልናስተውለው አንችልም። እነዚህን የአስተሳሰብ ስህተቶች በታቸለ መጠን ለመቅረፍ እንደ መፍትሄ የማስባቸዉ ነገሮች፦ አንደኛ pledge your loyality to evidence not dogma፤ከነገሮች ጋር ቁርኝት ከመፍጠር ይልቅ ማስረጃ ላይ ብቻ የተደገፈ ስነ ልቦናዊ ፍርድን ማዳበር። ሁለተኛ Be as detached as possible from all kind of ideology's or entities, the less attached you are the less biased you became .
705
17
Sin texto...
581
18
በስህተት 80,000.00 ብር የተላከለት ሰው እባክህ ተሳስቸ ነው እና መልስልኝ ያለው ሰው? 20,000 ብር ቆሪጨ ላክልህ አለው እሺ እባክህ 20,000 ቁረጥ እና 60,000.00 ላክልኝ አለው እና
በስህተት 80,000.00 ብር የተላከለት ሰው እባክህ ተሳስቸ ነው እና መልስልኝ ያለው ሰው? 20,000 ብር ቆሪጨ ላክልህ አለው እሺ እባክህ 20,000 ቁረጥ እና 60,000.00 ላክልኝ አለው እና በስህተት 600,000.00 ብር ተላከለት የህ ሰው ምን ማድረግ አለበት ? 😭🤣🤣🤣🤣🤣 ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
845
19
➠ርዕስ :- የማለዳ ስንቅ ➽ደራሲ:- አበራ ለማ ➨ዘውግ:- ስብስብ ሥራዎች ➪የመጀመሪያ ዕትም:- 1980 ዓ.ም ➲የገፅ ብዛት:- 107 ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬ 📚 |➜ ማጋራት አይዘንጋ ! ❤️ 📚📝 @BEMMNET 📚📝 @BEMMNET
924
20
🚨🚨 ገንዘብ አስቸኳይ ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽ ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL
🚨🚨 ገንዘብ  አስቸኳይ  ላስፈለጋቹ ብቻ ‼️ 😍➽  ብር አስቸኳይ ላስፈለጋቹ : እና ህይወታችሁን መለወጥ ለምትፈልጉ ብቻ ከታች JOIN በማለት • ተቀላቀሉን •💜👇👇 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0 https://t.me/+QJL3IPcL35E1YzI0
149