cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

Journalist-at-large

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
107 450
Suscriptores
+3424 horas
+4417 días
+1 42730 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
#Update ባለፈው ሳምንት ጥቆማ የሰጠንበት ይህ በአደገኛ ሁኔታ ይገኝ የነበረ ፖል አሁን ተነስቷል 🙏🏽 @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1010 137🙏 94😁 10🤔 4
Photo unavailableShow in Telegram
ከ15 ሺህ በላይ ሰው ድምፅ የሰጠበት ውጤቱ ይህ ሆኗል! 89% ወይም 13,378= ጥሩ ሀሳብ ነው  11% ወይም 1,727= ይቅርብህ ተቃራኒ ሀሳብ ያለው ማንኛው አካል መድረክ የሚያገኝበት፣ መንግስታዊም ይሁን ከመንግስት ውጭ ያሉ አካላት መረጃ የሚያንሸራሽሩበት፣ ደጋፊውም ሆነ ተቃዋሚው እኩል የመናገር እድል የሚያገኝበት እና ከሁሉም በላይ ህዝብ አስተያየቱን፣ አቤቱታውን፣ ቅሬታውን እና ትዝብቱን የሚያካፍልበት ሚድያ ይኖረናል... መቼ እና እንዴት የሚለውን እየተነጋገርን እንፈፅመዋለን። አስተያየት ለሰጣችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 1966 267🙏 111🕊 25😁 17😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማህበራዊ ሚድያ ላይ በጎ ስራዎችን በመስራት ከንግዱ ማህበረሰብ ተጠቃሹ ቢጃይ ናይከር ነው የስራ ፈጠራ ሀሳቦችን ለህዝብ ከማጋራት እስከ መነሻ ካፒታል ማጋራት፣ ከበጎ አድራጎት የገንዘብ እርዳታ እስከ ስራ እድል ፈጠራ የተሳኩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። የንግዱ ማህበረሰብ ከቢጃይ የሚማረው ብዙ ነገር ያለ ይመስለኛል፣ በተለይ ተለቅ ተለቅ ያሉት የ Corporate Social Responsibility ከመወጣት አንፃር። አንዳንዱ ገንዘብ ወደ ውጭ ለማሸሽ ሲሞክር፣ ታክስ ለማጭበርበር ሲሯሯጥ እና ህገወጥ ስራ ውስጥ ሲሳተፍ ባየንበት አይን እንዲህ አይነት የንግድ ባለሙያ እና የአምራች ባለሙያ ስናይ ደግሞ ተስፋ እናደርጋለን። በርታ ወንድማችን። @EliasMeseret
Mostrar todo...
570👍 217🙏 25😁 10😱 7🤔 6
ከቅድሙ ፖስት የቀጠለ... ታድያ ምን ችግር አለው በወረቀት/በአካል ቢሆን ለምትሉ: - በዚህ ብዙ ነገር በሚሰማበት ወቅት እና ስልክ ይዞ ወደ ፈተና መሄድ በማይቻልበት ሁኔታ ወላጅ ብዙ ያስባል። ከዚህ ቀደም ለፈተና ሄደው ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው፣ የተዘረፉ እና የተለያየ አካላዊ ጥቃት የተፈፀመባቸው በተለይ ሴት ተማሪዎች እንደነበሩ እናስታውሳለን - የግል ተፈታኞች ላፕቶፕ አምጡ ተብለው ብዙ ሰው እቃውን ራሱ ሸጦ ኮምፒውተር 40 እና 50 ሺህ ብር የገዛ ብዙ ሺህ ቤተሰብ አለ - ተማሪዎች በስነልቦና ዝግጅታቸው ብዙ ግዜ ሰውተው በኦንላይን የሞዴል ፈተና ሲወስዱ ቆይተዋል፣ ይህ በራሱ ጫና ይኖረዋል
Mostrar todo...
👍 382😢 70 23😁 18
Photo unavailableShow in Telegram
በበይነመረብ (online) ለመፈተን ዝግጅት የጨረሱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ ከሰአት ደግሞ ፈተናው በተቃረበበት በዚህ ወቅት በአካል ትፈተናላችሁ እየተባሉ ነው "... የ12ኛ ክፍል ዩዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን በበይነመረብ ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያደረግን የቆየን ቢሆንም ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናው በበይነመረብ እንደማይሰጥ ተረጋግጧል" ይላል አንዱ አ/አበባ የሚገኝ ትምህርት ቤት ዛሬ የደረሰው ማሳሰቢያ። በርካቶች ሌሎችም ተመሳሳይ መልዕክት እየደረሳቸው እንደሚገኝ መረጃዎች ደርሰውኛል። "ይህ ሁሉ ተፈታኞች ላይ የሚያደርሰው የስነልቦና ጫና ያውቁት ይሆን?" ያሉኝ ወላጆች "ድርጊቱ በትውልድ ላይ መጫወት ነው" ብለው ገልፀውታል። ትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላንይ እና በወረቀት እንደሚሰጥ ተናግሯል። ይሁንና ዛሬ በአካል ትፈተናላችሁ የተባሉት በበይነመረብ ትፈተናላችሁ ተብለው እስከዛሬ የኦንላይን ሞዴል ፈተናዎችን ሲለማመዱ የቆዩ ተማሪዎች ናቸው። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 174😢 85😁 25 13🤔 12🙏 1
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋንጫ ስላነሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! አሁን የውድድር ወቅቱ ስላለቀ ለባንኩ አንድ ሙያዊ ምክር: የባንኩን ዋና የፌስቡክ ገፅ የተቋሙን አገልግሎቶች ለማስተዋወቅ፣ ከደንበኞች ጋር ለመገናኘት እና ባንክ ነክ መረጃዎችን ለመለዋወጥ አውላችሁ ስፖርታዊ ጉዳዮችን እና የቡድናችሁን ሳምንታዊ ጨዋታዎች የምትዳስሱበት ሌላ ገፅ (ለምሳሌ CBE Sport... ወዘተ) የሚል ብትከፍቱ የተሻለ ይሆናል፣ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችም ይህን ያሳያሉ። በተከታታይ 10 እና ከዛ በላይ ስፖርታዊ ዜናዎችን ብቻ በአንድ ኮሜርሻል ባንክ ኦፊሴላዊ ገፅ ላይ ማቅረብ ፕሮፌሽናል አሰራር አይደለም፣ እንደዛ ሊኖራቸው የሚገባው የስፖርት ቻናሎች ወይም የስፖርት ጋዜጣዎች ናቸው።  ከማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም ልምድ በመነሳት ያቀረብኩት ሀሳብ ነው፣ ሌሎችንም ሊጠቅም ይችላል። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 666😁 62 30🕊 7🙏 6🤔 4
Photo unavailableShow in Telegram
የባለፈው ወር (ጁን) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እጅግ ስኬታማ ነበር። እንዴት? - አዳዲስ አለም አቀፍ በራራዎችን ወደ ፍሪታውን (ሴራሊዮን)፣ ማኡን (ቦትስዋና) እና ዋርሳው (ፖላንድ) ጀምሯል - በሀገር ውስጥ ደግሞ ወደ አክሱም እና ነቀምቴ በረራ ያስጀመረ ሲሆን ሌሎች የሀገር ውስጥ የበረራ ቁጥሮችን (frequency) ጨምሯል (ይህ ሀገር ውስጥ ካለ ከየብስ ትራንስፖርት አደገኛነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ በቀላሉ ሊገመት ይችላል) - በስካይትራክስ (Skytrax) የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተሸልሟል - በአፔክስ (APEX) የመንገደኞች ሽልማት ደግሞ ከአፍሪካ ምርጥ የበረራ ወቅት መዝናኛ እና ዋይፋይ ያለው ተብሎ ተመርጧል - ወደ ኦጋዱጉ (ቡርኪናፋሶ)፣ ኮናክሪ (ጊኒ)፣ ኪሊማንጃሮ፣ ኪጋሊ፣ ዱዋላ፣ ሉቡምባሺ የሚደረጉ በረራዎች ቁጥር ጨምሯል ወይም በቅርቡ ይጨምራል #FlyEthiopian @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 381 44🕊 7🤔 3😢 3
የግፍ ግፍ...! ግለሰቡ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪ ነው። ለ15 አመት የጋሪ ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት በዝቅተኛ ስራ የሚተዳደር በአካባቢው ነዋሪ ታማኝና ታታሪ የሚባል ሰው ነበር። ክርስትና ላስነሳ ብሎ 'ቆላ' ወደሚባለው ስፍራ የዛሬ ወር ገደማ ግንቦት 27/2016 ከተወሰኑ ቤተሰቦቹ ጋር ሲጓዝ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ይይዟቸውን እና ከሌሎች ቀድመው ከታገቱ ሰዎች ጋር ይቀላቅሏቸዋል፣ ለመልቀቅም ግማሽ ሚልዮን ብር ይጠይቃሉ። ካዛም ወንድሞቹ ፌስታል ይዘው እየለመኑ እና ያላቸውን ጥሪት በሙሉ አሟጠው ሸጠው ገንዘቡ ይሰበስቡና እሱን ሰጥተው ወንድማቸውን ለማስለቀቅ ጉዞ ሲጀምሩ የአካባቢው ሚሊሺያዎች ያገኟቸው እና ከተዋጣው ብር ላይ 90,000 ብር ይወስዳሉ። የቀረውን ብር ይዘው መንገድ ሲቀጥሉ ደግሞ 'ልዩ ሀይል' ተብለው የሚጠሩ አካላት እጅ ይወቁ እና ሙሉውን ቀሪ ብር ይወስዱባቸዋል። ገንዘቡ ያልደረሳቸው አጋቾች ታድያ ይህን ታታሪ ግለሰብ ጨምሮ ሌሎች 20 ሰዎችን ገድለው፣ የተቀሩትን ደግሞ ይዘው ሸሽተዋል። ቤተሰብ ሀዘን ተቀምጦ ሰንብቷል፣ የአካባቢው ህዝብም ሆነ በስፍራው ያሉ የመንግስት አካላት ጉዳዩን በደንብ ያውቁታል (የግለሰቡን ስም እና ይኖርበት የነበረውን ከተማ አስቀርቼዋለሁ)። የግፍ ግፍ! @EliasMeseret
Mostrar todo...
😢 1390👍 106😱 49 17🕊 14🤔 13😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
በየትኛውም መስክ ላይ ያለ የሀገር ልጅ እንዲህ ሲሳካለት፣ ከፍ ሲል፣ በስራው ሲከብር ደስ ይላል። መልካም ግዜ ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች! #Rophnan #ChrisBrown @EliasMeseret
Mostrar todo...
912👍 348😁 32😢 23😱 22🤔 8🙏 4🕊 2
Photo unavailableShow in Telegram
ከዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ አንፃር በቅርብ አመታት ካየናቸው የመንግስት ተቋማት በአንፃራዊነት (በአንፃራዊነት የሚለው ቦልድ ሆኖ ይሰመርበት) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተሻለ መልኩ በቀዳሚነት ይጠቀሳል ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ላለፉት አምስት አመታት የመሩት ይህ ኮሚሽን በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በትክክል መዝግቦ አልያዘም፣ ICHREE የተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሊያጠና የተቋቋመው አለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን እንዲበተን አስተዋፅኦ አድርጓል እንዲሁም የተለያዩ መድልኦዎች አለበት የሚሉ ክሶች ተደጋግመው ይቀርቡበታል። ይህም ሆኖ ቢያንስ የመንግስት የፀጥታ አካላት እና የተለያዩ የታጠቁ ቡድኖች የመብት ጥሰት ሲፈፅሙ በስም በመጥቀስ፣ ቦታው ድረስ በመሄድ በማጣራት፣ ጉዳዩን ለሚድያዎች በተደጋጋሚ በማድረስ እና የሚያወጣው ሪፖርት አንፃራዊ ተአማኒነት እንዲኖረው እንደተደረገ በግሌ ይሰማኛል። ይህን የምለው የቀድሞው ኮሚሽን ምን ሲሰራ እንደነበር በቅርብ ስከታተልም ጭምር ነው። መጪው ግዜ ለኮሚሽኑ የተሻለ እንዲሆን እንመኝ። @EliasMeseret
Mostrar todo...
👍 624 63😁 35🤔 17🙏 6😢 5
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.