es
Feedback
Assaye Derbie

Assaye Derbie

Ir al canal en Telegram

📈 Análisis del canal de Telegram Assaye Derbie

El canal Assaye Derbie (@asayede) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 14 365 suscriptores, ocupando la posición 2 646 en la categoría Bloques y el puesto 2 349 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 14 365 suscriptores.

Según los últimos datos del 19 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -151, y en las últimas 24 horas de -7, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 37.94%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.81% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 5 450 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 553 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 39.

📝 Descripción y política de contenido

No se ha proporcionado la descripción del canal.

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 20 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Bloques.

14 365
Suscriptores
-724 horas
-337 días
-15130 días
Archivo de publicaciones
AFPO's Draft Manifesto Jan33 (1).pdf1.14 MB

photo content
+4

አፋሕድ የድርድሩን አጀንዳ ለማስቀየስ አስቦ በለቀቀው፣ ከአብን በኮረጀውና ማኒፌስቶ በሚል ሥም በለቀቀው የድርድር ሰነድ በፋኖ ደም ኢትዮጵያ ትቅደም ማለቱን፣የአማራን የሥልጣን ጥያቄ መካዱንና ከአማራ ብሔርተኝነት በተቃራኒ መሰለፉን ተረድቻለሁ።

ክሷ ምን ቢሆን ጥሩ ነው? "የጥበብ ሥራዎችሽ ውስጥ የአማራ ባሕልና ወግ ይበዛበታል"😁
ክሷ ምን ቢሆን ጥሩ ነው? "የጥበብ ሥራዎችሽ ውስጥ የአማራ ባሕልና ወግ ይበዛበታል"😁

ለወትሮው ከሚዲያ የማይጠፉ የፋኖ መሪዎች በሥማቸው ድርድር ሲካሄድባቸው ምነው ድምጻቸው ጠፋ? የአማራ የብሔርተኝነት ትግል በሐሳዊ ኢትዮጵያኒስት ሲጠለፍ ምነው ደብዛቸው ጠፋ?

እኅታችን ቀለብ ስዩም ትክክለኛውን የትግል መስመር ይዛ ትግል ጠላፊዎችን እየታገለቻቸው ነው። እና Subscribe በማድረግ አበረታቷት። 👇 https://youtu.be/hTu2lzMrqEk?si=pw6pUyv0rbnNce26

"የሽምቅ ውጊያው እንደ "ድል ለዲሞክራሲው" አልቀለለውም። ለዚያ ነው የተደራደረው።" ጄኔራል ተፈራ

https://youtu.be/LUUj746Gv_M ልዩ ቃለመጠይቅ ➻ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ➻ አርበኛ እሸቴ ባዬ ➻ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ➻ አርበኛ ባዬ ቀናው

"አሳዬ" የተባልኩት እኮ ያለምክንያት አይደለም ብዬ ልጎርር እንዴ? 🤣ለማንኛውም ግን እንደ አንድ አማራ በዋናነት ታርጌት የተደረገውን የጎጃም አማራ ያመላከተኝና ከእነሱ ጎን አሰልፎ "የዘመነ ተላላ
"አሳዬ" የተባልኩት እኮ ያለምክንያት አይደለም ብዬ ልጎርር እንዴ? 🤣ለማንኛውም ግን እንደ አንድ አማራ በዋናነት ታርጌት የተደረገውን የጎጃም አማራ ያመላከተኝና ከእነሱ ጎን አሰልፎ "የዘመነ ተላላኪ" ያስባለኝ አምላክ ይክበርልኝ፡፡

በወቅታዊ ጉዳይ ከማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው አንግበው የአማራን ሕዝብ ለዳግም ባርነት ለመዳረግ በሞቱ የሚደራደሩ የአይሁድ ሸንጎ ማኅበርተኞችን ትናንት በአደባባይ ሕዝባችንም ሠራዊታችንም የተመለከተው የአደባባይ ሐቅ ነው። የብልጽግና ሥርዓት በቅብብሎሽ የተረከበውን አማራ ጠልነት አተልቆ፣ አደርጅቶ፣ አጎምርቶ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ የማያውቅ እልቂት በአማራ ሕዝብና በአማራዊ ማንነት ላይ ውርጅብኝ በሆነበት በዚህ ሰዓት ላይ የአርበኝነት፣ የሐቅና የፍትሕ ትግላችንን በድርድር ሰበብ ለማይጠረቃ የፖለቲካ ፍትወታቸው መወጣጫ መሰላል ለማድረግ የሚሞክሩ  አካላትን ለሠራዊታችንና ለሕዝባችን መግለጥ እንወዳለን። ከፋፋይነት፣ ይሉኝታ የለሽ ነጣቂነት፣ ልጓም አልባ የሥልጣን ፍትወት ላይ የሚናውዙ አካላት ትግላችንን ትናንት በሕዝባዊ ግንባር፣ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ፋሕፍዴን ዛሬ ላይ ደግሞ  በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጭንብል ተሸፍነው ትግላችንን ለማቃለል፣ ለማሳነስ የሄዱበት ርቀት እጅጉን አሳዝኖናል። በደቡብ ወሎ ዞን፣ ዳውንት ወረዳ ልዩ ቦታው ኩርባክ በተባለ ቦታ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋና የወሎ የፋኖ ተወካዮች በሚል ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ፣ ከአብይ አሕመዱ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ንግግሮች መደረጋቸውን ከሂደቱ ጀምሮ በየተቋሞቻችን የመረጃና ደኅንነት ዘርፎቻችን በኩል ስንከታተለው የቆየነው ጉዳይ መሆኑን ሳንገልጽ አናልፍም። እሚገርመው ደግሞ እነዚህ አካላት ድርድሩን ሚዲያ ላይ ወጥተው በመሪያቸው በአቶ እስክንድር ነጋ እና በፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው በረ/ኘ/ር ጌታ አስራደ በኩል ገልጸውልናል። በዚህ መሠረት ከራሳቸው የሚዲያ ማብራሪያ ብቻ ተነስተን ተጠይቆችን በማቅረብ ሕዝባችንም ሆነ ሠራዊታችን ከዚህ እኩይ እሳቤ ራሱን እንዲጠብቅ እንፈልጋለን። የመጀመሪያው ተጠየቅ፦ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ረ/ፕ/ር ጌታ አስራደ፣ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ እና ከሸዋ ማንነቱን በውል ያላወቅነው ግለሰብ በድርድር ሰበብ የኅልውና ትግሉን የማይመጥን፣ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች በተወሰኑ ቡድኖች ፍላጎት ላይ ብቻ አንጠልጥሎ የጥድፊያው አንድምታ ምንድነው?፤ ያለሕዝብና ያለፋኖ ውክልና አማራውን ቀራንዮ አደባባይ ያቆመው ሥርዓት በተገኘበት መድረክ ላይ ለመገኘት ለምን ደፈራችሁ? ሁለተኛው ተጠየቅ፦ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሙሉ በሙሉ፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) ከሁለት ክፍለ ጦር ውጭ ሙሉ ለሙሉ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ከሦስት ክፍለ ጦር ውጭ ሙሉ ለሙሉ፣ የሸዋ ፋኖም አንድነት ለመፍጠር የንግግር ሂደት ላይ መሆኑ እየታወቀ ድርጅት የምትሉት ተቋም በምንታገልበት የአማራ ሰማይ ሥር የት ነው ያለው? ሕዝባዊ ድርጅት በሚል በዲጂታል ሚዲያው የሚለፈፈው ከሐቅ የራቀ፣ ሙሉ ለሙሉ ከፋፋይ፣ መሪዎቹም ከተወሰኑት ወታደራዊ መሪዎች በስተቀር በግብር የተገለጠ ጸረ አማራ አቋም ያላቸው ስለመሆናቸው ማብራሪያና መግለጫችው ኅያው ምስክር ነው። ታዲያ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የፋኖ ኃይል የያዘ ተቋም ነው የሚለው የእስክንድር ነጋ ንግግር የአማራን ሕዝብ የኅልውና ትግል ለማይጠረቃ ግለሰባዊ የሥልጣን ፍትወቱ መጠቀሚያነት እንጅ በእውነት ለአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል የወጣ ታጋይ አለመሆኑን ዳግም አረጋግጦልናል። ምክንያቱም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መሬት ላይ የሌለ የትግላችን መከፋፈያነት መጠቀሚያ ካርድ ለመሆኑ በየቀጠናው የሚገኙ ፋኖዎችን ጫፍና ጫፍ አቁሞ እስከማታኮስ የዘለቀ ርካሽ የፖለቲካ መቆመሪያ ድርጅት ስለመሆኑ የትናንት ገሐዳዊ ሁነቶች ያረጋግጣሉ። ድርድርም ውይይትም በመርኅ ላይ የተመሠረተ፣ ሐቀኛ የፖለቲካ ውክልናን የያዘ፣ የትግሉ መሠረተ ሃሳቦች ላይ የቆመ፣ የትግል ፍኖተ ካርታን በግልጽ በማስቀመጥ እነዚህን ሳይነጣጠሉ ሃሳብን የማቅረቢያ አመከንዮዎችን፣ ገሐዳዊ ሐቆችን ያለአንዳች የፖለቲካ ውስልትና በማቅረብ የሕዝብ ጥያቄ ማሸነፍ የሚችልባቸውን መደላድሎች መፍጠር ነው። ቅሉ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ረ/ፕ/ር ጌታ አስራደ፣ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ እና ከሸዋ አንድ ግለሰብ በጋራ የተገኙበት ሸንጎ በመርኅ ደረጃ የድርድርን መሠረተ ሃሳቦችን ያላሟላ መሆኑን ማረጋገጥ እንወዳለን። ከዚህ ጋር ተያይዞ በዚህ የንግግር ሂደት ላይ የተገኙ ዓለምአቀፍ ተቋማት መሬት ላይ ከሌለ ስብስብ ጋር መቀመጣቸው ሥርዓታዊ የዘር ማጥፋት ድርጊት እየተፈጸመበት ያለውን የአማራን ሕዝብ ያላከበረና የማይመጥን አካሄድ በመሆኑ በቀጣይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሐቀኛ እንዲሁም አካታች ውክልና ከሚሰጣቸው ልሂቃን ጋር ብቻ እንዲሆን መግለጥ እንወዳለን። በጥቅሉ ዳውንት ላይ የተካሄደው ድርድርም ይሉት ውይይት ሠራዊታችን የማያውቀው ምናልባትም የሚያወግዘው፤ ሕዝባችንን ያሳዘነ የፖለቲካ ቁማር ነው። ይህንን በድፍረት ለማለት የሚያስገድደን ጉዳይም ከእውነት የራቁ ድርጅታዊ ተረኮች (90% የፋኖ ኃይል የድርጅታችን አካል ነው፣ የወከልነውም ይህንን ግዙፍ ኃይል ያለው ፋኖ ነው) የሚሉ፣ የመርኅ፣ የፖለቲካ ውክልና፣ የተዓማኒነት እንዲሁም የአካታችነት የሚሉት ጥያቄዎችና መሰል ጉዳዮች ሲነሱ ውሃ የሚያነሳ ምላሽ የለም። መላው የአማራ ሕዝብ፣ መላው ሠራዊታችን፣ የሚዲያ አካላት ይህ ጉዳይ በቀላል የሚታይ ባለመሆኑ የአማራ ፋኖ በሸዋ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) እና የአማራ ፋኖ ቢዛሞ እዝ ሕዝባችንን ለዳግም ባርነት አሳልፎ የሚሰጥ አደረጃጀትንም ሆነ አስተሳሰብ አጥብቀን ከማውገዝ ባሻገር የምንታገለው ጉዳይ ነው። የአማራ ፋኖ በጎጃም የአማራ ፋኖ በሸዋ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ) የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር እና የወለጋ ክፍለ ሃገር ፋኖ እዝ (ቢዛሞ)