Joseph Math Tutor
Ir al canal en Telegram
Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/oavDFT_BLNM?si=-8fh6SmrX2jSsmC- Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580
Mostrar más2 176
Suscriptores
+224 horas
+1337 días
+33630 días
Archivo de publicaciones
2 177
I will ask the section on whether it is possible or not for private students and tell you. Please wait patiently.
2 177
መጀመሪያ ማስታወቂያው ላይ የተለቀቀው ሊንክ እስከአሁን እየሰራ ባይሆንም ትላንት የተለቀቀው ከዚህ በታች ያለው ግን እየሰራ ይገኛል። ግቡና በእሱ ተመዝገቡ።
🔗 Link:
https://stu.astu.edu.et
2 177
🔗 የምዝገባ LINK፡
https://stuoexam.astu.edu.et👉 ሊንኩ ተከፍቶ ምዝገባ የሚጀምረው ነገ ነሐሴ 25 ፣ 2018 ዓ.ም ነው። ☝ የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን ስለሆነ ፣ ሊንኩ እንደተከፈተ በአቅራቢያችሁ የሚገኘውን የፈተና ጣቢያ ለመያዝ አስቀድማችሁ ተመዝገቡ። አለበለዚያ ሩቅ ቦታ ሊደርሳችሁ ይችላል። @astujmt2019
2 177
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡- በድህረ ገፃችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
· የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
· በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
· ለፈተና የሚቀርቡት የአመልካቾች ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡
· አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም (ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
· ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡
· አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
· የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡
· በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡
· በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል፡፡
· በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
· በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ከታች የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡
www.astu.edu.et; www.aastu.edu.et
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
2 177
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2019 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
===============================፡
በ2019 ዓ.ም አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስ እና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና ኦንላይን (Online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡
የምዝገባ ጊዜ፡-
- ከነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡
- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ https://stuoexam.astu.edu.et ወይም www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
2 177
Repost from Joseph Math Tutor
በ2019 ወደ ASTU መግባት የምትፈልጉ ስለ ASTU ሙሉ መረጃ እና የምትማሩበትን መጽሐፎች ለማግኘት Join ያድርጉ።
ወደ ASTU መግባት ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ #Share አድርጉ።
ማንኛውንም ያላችሁን ጥያቄ ግሩፑ ውስጥ መጠየቅ ትችላላችሁ።
2 177
#LAST_YEAR
በ2017 የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ይህን ይመስል ነበር። በዘንድሮ ዓመት ከዚህ ከፍ ይላል ተብሏል።
1.የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 216/600
2.የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 204/600
3.ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 192/600
4.ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 192/600
5.ማህበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ለሁለቱም ጾታ 160/500 ሆኗል።
@joseph_maths_tutorial
2 177
በ2019 ወደ ASTU መግባት የምትፈልጉ ስለ ASTU ሙሉ መረጃ እና የምትማሩበትን መጽሐፎች ለማግኘት Join ያድርጉ።
ወደ ASTU መግባት ለሚፈልጉ ጓደኞቻችሁ #Share አድርጉ።
2 177
ውጤት መታየት ጀምሯል:: ዉጤታችሁን በእነዚህ አማራጮች ማየት ትችላላችሁ::
1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
መልካም ዕድል 🙏🥰👌
2 177
+1
" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
2 177
ስለ ASTU ሙሉ መረጃ እንደሰጠዃችሁ ተስፋ አለኝ። በቀጣይ ደግሞ የመጀመሪያ ዓመት ላይ ለምትማሯቸው ትምህርቶች የሚሆኑ Materialoch እልክላችኋለሁ።
እስከዚያው ASTU መግባት ለሚፈልጉ ተማሪዎች #Share በማድረግ አዳርሱ።
@Joseph_maths_tutorial
@astututorials
2 177
Repost from Joseph Math Tutor
#AASTU_&_ASTU_#Entrance_#Exam_#Part_#2
https://youtube.com/watch?v=8CmqzvInRFU&si=sqYGn6vdsxYZCO0t
