es
Feedback
Joseph Math Tutor

Joseph Math Tutor

Ir al canal en Telegram

Hello, welcome to Joseph Math Tutor channel! https://youtu.be/oavDFT_BLNM?si=-8fh6SmrX2jSsmC- Subscribe our youtube channel On tiktok : josephmathtutor Owner: Yosef Adefris @yosef_2580

Mostrar más
2 176
Suscriptores
+3724 horas
+1357 días
+33230 días
Archivo de publicaciones
Repost from Joseph Math Tutor
#AASTU_&_#ASTU_#Entrance_#Exam_#part_#1 https://youtube.com/watch?v=0SnSQAYXTe0&si=r2DEPuZuNLAOhjCJ

#ASTU_&_AASTU መግቢያ ፈተና ምን ይመስላል? አምና የ ASTU እና AASTU ፈተና ላይ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች ወተው ነበር 👇 👉 Chemistry > Questions about Robert Milikan > Maximum No of orbitals for l = 2 > Type of Crystals > Acid-Base Different Definition > Galvanic and Electrolytic Cells 👉 Maths > Find the domain and range of a given function > Matrix Multiplication questions: AX = B. A and B are given and X is unknown. > Mean, Mode, Median > Cosine Law > Derivative and Integration 👉 Biology > Blood Group > Transpiration > Food Samples (Protein and Lipid) > Convergent and Divergent Evolution 👉 Physics > The 5 kinematic equations > Vectors Algebraic Calculations > Frictional Force > Angular Acceleration 👉 English > Passage > Grammar > Vocabulary @Joseph_maths_tutorial @astututorials

#ASTU ሃይማኖታዊ ቻናሎች For freshman students 👉For protestant fellowship @Astuecsf @focussastu 👉For Orthodox ግቢ ጉባኤ @gibigubaye @Yaimora 👉For Muslim @astu_msj 👉For Adventist Fellowship @astupcmsda

📢 የካምፓስ የመጀመርያ አመት ቆይታ ......በትንሹ ❓ 📚 ፍሬሽማን መሆን እንደእናንተ ስብዕና ይወሰናል ። የተለያየ ሰው የተለያየ experience ነው ያለው ። ግን ብዙዎች ጋር የሚኖረውን የፍሬሾች የጋራ ኑሮ ቆንፅለን ለማየት እንጥራለን ...! 💡 ናፍቆት .....! 📚 አንዳንድ ከቤታቸው ሱቅ ለመላክ ካልሆነ ወጥተው የማያቁ ልጆች ድንገት ከቤተሰብ ሲርቁ ምናምን አይችሉም ይነፋረቃሉ ...ከሰው ጋር የማይግባቡ ዝጋታም ልጆች ስላሉ እነሱም ... ለብቸኝነት ሲጋለጡ ሊከብዳቸው ይችላል ። አንድ ነገር እወቁ ከምትወዷቸው ሰዎች መለየት ይሄ የመጀመርያቹ ሊሆን ይችላል ግን ብርቅ አይደለም ...አቅፎ የሚያስተዛዝን ፤ ህመምን የሚጋራ ደስታን የሚካፈል ጓደኛ ቤተሰብ ወዳጅ መለየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ግን ቻሉት በህይወታችሁ ነፍ ግዜ ከምትወዷቸው የህይወት አጋጣሚ ይለያቹሃል ። ካምፓስም የምታገኟቸው ልጆች ከአመታት ውብ የጓደኝነት ቆይታ በኃላ ትለያያላችሁ ። ናፍቆት ያለ ነው ግን መቻል ነው ። በካምፓስ ጥሩ ጓደኛ ያዙ ...እስክትለምዱት ነው ። ከዛ ይለቃቹሃል ። 💡 ምግብ ....! 📚 እንደ እናትህ ውይ ልጄ ተነስ ቁርስ ብላ ና ትተኛለህ  አቡኪያዬ ...ምናምን የለም በጠዋት ተነስተህ ሰልፍ ካልወጣህ ሲሞረሙርህ ይውላል ካፌ ሊያልቅም ይችላል ....ሻይ በዳቦ ለመብላት ይሄ ያክል ሰልፍ ልትልም ትችላለህ ግን በመክሰስ ሰዓት 12 ስለሆነ ራት የሚገረሰው ችከላ ካደርክ ይሞረሙራል...ዳቦ ራሱ ስንት ጣዕሙ ..ከረሃብ ይሻላል ። ሩዝ ፤ ፍርፍር ...ስላለ አትቸጋገር ....ግን ጥሩ ነገር መብላት የለመደ ሰው....ወይኔ ግቢው ጥሩ ባልቴት  የሌለው ይመስል ..ጥቅል ጎመን ብለው ቀጭን ሾርባ ጎመን ጣል ጣል ያለበት ሊያቀርቡ ይችላሉ ...ታዲያ አሪፍ ነገር የለመደ አይችልም 3000 ብር አከባቢ ይገጨውና ውጪ ይበላል .... ምግቡ እንደ ካምፓሱ ነው  በተለይ በቅርቡ የተከፈቱ አርሲ ፤ ቦንጋ ምናምን ምንም አይልም ባህርዳርም አሪፍ ነው ። ሃረማያማ በሳምንት አራቴ ነው ስጋ የምትግጡት ...ብቻ ብዙ ልጆች የጣፈጠ ነገር ለምደው እንደ ነገሩ የሚሰራው ምግብ አይጥማቸውም ። 💡 ጓደኛ መረጣ ...! "ጓደኛ መረጣ ላይ መጠንቀቅ አለባችሁ ። በጣም መጥፎ ሰዎችም ጥሩ ልጆችም ይኖራሉ ። ከሱሰኛ ፤ ጨባሽ ፤ ዘረኛ ..ራቁ..በቢሊዮን ማይል ራቁ ...ከእናንተ ጋር የሚሄድ ሰው ፈልጋችሁ ከዶርም ውስጥ አንድ የልብ ጓደኛ በቂ ነው ። ታዲያ ምንም መጥፍ ባህሪይ ቢኖርባቸው ከዶርም ልጅ አትጣሉ ...ትቸገራላችሁ ተንከባክባችሁ ....ተከባብራችሁ በፍቅር አርጉት ...ጓደኛ ምርጫችሁን ተጠንቀቁ ዝም ብሎ ሲያነብ የሚውል የሚተሽንም ሰው አትጠጉ በቃ አራዳ ሆናችሁ ማንበብ ሲኖርበት የሚያነብ ፈታ ግድ ሲል የሚፍታታ ነገሮች የሚገቡ ምርጥዬ ሰው ፈልጉ ። 💡 ሱስ.... 📚 ብዙ ሰዎች ካምፓስ በጓደኛ ምክንያት ያልሆነ ነገር ውስጥ ይገባሉ ይሄ መሆን የለበትም ...ምንም ቢሆን ሱስ አለም እንዳትገቡ ...ያለባችሁ ችግር ይበቃል ... አንዳንዴ ግዜ ሊተርፋችሁ የምትሰሩት ታጡም ይሆናል ...ጭራሽ ሱሰ ውስጥ ራሳችሁን እንዳታገኙ በርቱ ....! 💡 መወዛገብ ......! 📚 ከጠበቃችሁ በጣም የተለየ ነገር ሊገጥማችሁ ይችላል ....ያኔ ውዝግብ የተለመደ ነው ።ተሳስታችሁ የሰው ዶርም ከች ትሉም ይሆናል ።ብዙ ግዜ ልጆች እስኪለምዱ ድረስ እንዳይጠፋባቸው አንዴ ባየት መንገድ ብቻ ነው የሚጓዙት ....ሌላ አጭር መንገድ ቢኖርም አይሄዱም በረጅም ይሄዳሉ የፍሬሽ ነገር የተለመደ ነው ። በቃ በየስርቻው ሲዋሰቡ ፤ ትምህርት ብሎ መጥቶ አባቱን በሬ አሽጦ ፤ እናቱን ፆም አሳድሮ እሱ ጫት ቤት ፤ ቅምቀማ ስታዩት (2 or 3 ተማሪ እንዳይመስሏቹሁ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ተማሪ  .)...በቃ ላይብረሪው ውስጥ 3 ሰው ብቻ ስታዩ...ትደነግጣላችሁ ወይኔ ካምፓስ ልትሉም ትችላላችሁ ...!ለምግብ ሰልፍ ስታዩ ..ዋይፋይ ሰዎች ለሊት ሙሉ ሲጠቀሙ ስታዩ....በቃ ትወዛገባላችሁ ...ትምህርት ቤት ያላችሁ መሆኑ ትዝ የሚላችሁ ...የፈተና ሰሞን ነው ላይብረሪ 3 የነበረው ሰው መቀመጫ አጥቶ አንድ ወንበር  ለሁለት ተቀምጦ ስታዩ ...ዶርም አዳር ሲቸከል ስታዩ ይገባቹሃል ። 💡 የአስተማመር አይነት ....!. 📚 እንደ Highschol 40 ደቂቃ ሳይሆን 3 ሰዓት ሙሉ አንድ ሳብጀክት ትዳረቃላችሁ .....እሱም ደህና መመህር ካጋጠማችሁ ነው የሚገባችሁ ።  በቃሉ እየተጀነነ ሲያወራ የሚውል.... ኖት የሚቸከችክ  ...ደብተር ሁላ የሚያርም አለ ። የለመዳችሁት አይነት ...የመማር ማስተማር ሂደት ሲቀየር አትደናገጡ እንደ አየሩ መሆን ነው ። እስከትለምዱት ነው ። 💡 ሙድ መያዝ .....❗️ 📚 ፍሬሾች ገና ከመግባታችሁ ...የሲኒየሪዎች ነቆራ አይጣል በቃ ምንም ስለማታውቁ ...የማይሆን ነገር ሊነግራቹሁ ይችላል የመመዝገቢያ ቦታ ጠይቃችሁ ሽንት ቤት ሊሊሉካችሁ ይችላሉ ። ግን አይደብራችሁ እናንተም በተራቹሁ አየር ስለምትይዙ ....ፈታ በሉበት እስክትለምዱ አየር አታብዙ አትኳትኑ ልጎብኝ እያላችሁ አታካሉ ወሬ ሰብስቡ መጀመርያ ። የመጀመርያ ምግብ ካፌ ማሰታወሻ ፎቶ አንሱት ። 📚 ሁሉንም አውርተን አንጨርሰውም ....በቃ የቀረ ካለ ግቢ ታዩታላችሁ ፥ ብዙ አትጨናነቁ እኛም አለን አዳዲስ ነገር እንነግራቹሃለን ። አይዞን!

ይሄ እኔ የሰራሁት የ2016 ዓ.ም Mathematics Fast Track Exam ነው። ጊዜ ካገኘሁ የ2018 ዓ.ምን ለመስራት እሞክራለሁ👍

የ ASTU መምህራን       50 %   PHD       50 % Masters   ናቸው።

#ASTU #NG - Non Grade NG ምንድነው? ምን ሲሆን ነው NG የሚሰጠው?? ከጠየቃችኋቸው ጥያቄዎች መካከል ይሄ ጥያቄ ይገኛል። 👉 በአጭሩ NG የሚሰጣችሁ የ continuous assessment ጉድለት ካለባችሁ ነው። ለምሳሌ በተለያየ መንገድ Quiz ወይ ደሞ Test ካመለጣችሁ እና ከመምህራችሁ ጋር ተነጋግራችሁ ካላስተካከላችሁ ግሬዳችሁ NG ይሆናል። ምናልባት quiz አምልጧችሁ "ከ 5 ነው ይቅር" ብላችሁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እነሱ 0/5 ሳይሆን NG ነው ሚያደርጉት።   👉 አንዳንዱ አስተማሪ quiz or test ምናምን ያልተፈተነ ወይ ደሞ assignment ያላስገባ ተማሪ ያናግረኝ ይልና ስታናግሩት ያስተካክላል። አንዳንድ አስተማሪ ደግሞ ዝም ነው ሚለው ፣ አይናገርም ፤ ከዚያ NG አድርጎት እርፍ 🫠። 👉 ስለዚህ እንደዚህ አይነት የ continuous assessment ጉድለት ያለባችሁ ተማሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት ሁሉንም ነገር ካልጨረሳችሁ ተበላችሁ ማለት ነው። ከሚቀጥለው ሳምንት ውጪ አስተማሪዎችን ማግኘት ከባድ ነው። አስታውሱ ☝️:"F" Grade ከ "NG" ይሻላል።

#FastTrack #SpecialExam 1⃣.ፈተናዉ መቼ ይሰጣል? ፍሬሾች ልክ ግቢ ስትገቡ ከሁለት ወይም ከሶስት ሳምንት ቧኃላ ፈተናዉን መፈተን ለምትፈልጉ ተማሪዎች ማስታወቂያ ይወጣል ። ከዛ fast track መፈተን የምትፈልጉትን subject ትመርጣላችሁ ከ Chemistry, Maths, Physics ሶስቱንም ተፈትኖ ያለፈ ተማሪ pre enginering ሳይማር ቀጥታ 2ኛ አመት መሆን ይችላል (በ3ቱም ያለፈ ብቻ) ። 2⃣. ሶስቱንም subject ከ80 በላይ ባላመጣስ ብያንስ በ1ንዱ ባልፍስ ?  ሶስቱንም መፈተን አልፈልግም(የፈለኩትን ልፈተን) የሚል ተማሪ ወይም ደግሞ ሶስቱንም ተፈትኖ 1ዱን ወይም 2ቱን ትምህርቶች ብቻ ከ80 በላይ ያመጣ ተማሪ አንደኛ አመት ሆኖ ግን ከ80 በላይ ያመጣዉን subject class ገብቶ መማር ሳይጠበቅበት ዉጤቱ ይያዝለታል ። 3⃣. የከዚህ በፊት ፈተናዎች አሉ ? fast track በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ነዉ የምሰጠዉ ፎቶ ለማንሳት ማንም ሰዉ አይችልም ። ስለዚህ የሉም። 4⃣. የፈተናዎቹን ይዘት ምንድናቸው? የ2015 fast track ፈተና ይዘት ልንገራችሁ 👉Applied maths • 25 ጥያቄ አከባቢ ነበር ... 13 ባዶ ቦታ መሙላት , 12 workout  .... workout part • Matrix (determinant, inverse, equations) • Proving Continuity of functions • Application of derivatives (local maxima,minima, critical numbers, rates) • Integrations (substitution, by parts... • new concept blank space lay Hyperbolic function. 👉 Chemistry • 60 የምርጫ ጥያቄዎች ነበሩ ... እንደ ማትሪክ አይነት 👉Physics • 50 የምርጫ ጥያቄ .... ግን ሙሉ ጥያቄዎች workout ናቸው ... outstanding ያልሆነ ተማሪ ሰዓት ላይበቃው ይችላል። 5⃣. ፈተናዉ ከባድ ነዉ ወይ? ብዙም ከባድ የሚባል አይደለም ! ብዙ ተማሪዎች እንደምሉት ፈተናዉ የሚሰራ አይነት ነዉ ። physics ግን ምን አልባት..... 🥶😬 6⃣. ምን አይነት ማቴሪያል እንጠቀም ? 11& 12ኛ ክፍል ስትጠቀሙበት የነበረዉን .... Astu የገባ ተማሪ ሁሉ ምያነበዉ ልቦ-ለድ አለ ደራሲዉን ካወቃችሁት Begashaw ይባላል (applied maths) እሱንም መጠቀም ትችላላችሁ። ይህ 👆 እስከአሁን የነበረው አሰራር ነው ... በዚህ አመት የሚቀየር ነገር ይኑር አይኑር አይታወቅም 🤷‍♂️

#ASTU ወደ ዩኒቨርስቲው ዋና ዋና ዶክመንቶችን የኢንተራንስ ሰርተፍኬት ፣ ትራንስክሪብት እና የስምንተኛ ክፍል ካርድ የምታስገቡት ID ካርድ ስትወስዱ ነው። ለመመዝገብ temporary ሰርተፍኬት በቂ ነው። ስለዚህ አትጨናነቁ። ID ካርድ እስከምትወስዱ የተወሰነ ጊዜ ይፈጃል። በዛን ጊዜ ውስጥ የትምህርት ሚኒስቴር ሰርተፍኬት ይደርሳችኋል። ያኔ በኦርጅናሉ ሰርተፍኬት መመዝገብ ትችላላችሁ። ኦርጅናል ID ካርድ እስከምትወስዱ ድረስ የምትጠቀሙት temporary ID ካርድ ይሰጣችኋል። ካፌ ፣ ላይብረሪ የምትገቡት እሱን በመጠቀም ይሆናል። ስትመዘገቡ የምትነሱት ፎቶ ይኖራል። ዩኒቨርስቲው ነው ሚያነሳችሁ። ይህ የምትነሱት ፎቶ ግቢው እናንተን የሚያውቅበት ፎቶ ነው። በ ID ካርዳችሁ እና በፖርታላችሁ profile picture ላይ ይደረጋል።

ምን ታያላችሁ ❓ እኔ ለማዳ ነኝ ፤ አልነካችሁም። ፍሬሾች ናችሁ መሰለኝ ... እኔ ምፈልገው ተከባብሮ አብሮ መኖርን ብቻ ነው። — ከ ASTU ጅብ የተላለፈ መልዕክት 😂
ምን ታያላችሁ ❓ እኔ ለማዳ ነኝ ፤ አልነካችሁም። ፍሬሾች ናችሁ መሰለኝ ... እኔ ምፈልገው ተከባብሮ አብሮ መኖርን ብቻ ነው። — ከ ASTU ጅብ የተላለፈ መልዕክት 😂

በዓል ሲደርስ ከስንት ቀን በፊት ነው ምንወጣው ❓ 😅 You are about to join ASTU. But think you will celebrate your holidays. 🤔... maybe you might have listened to a motivational speaker saying "Think the impossible" 🤣🤣🤣 ምን መሰላችሁ ... ግቢው በዓል አያቅም። በእርግጥ ዝግጅት ግቢ ውስጥ ይዘጋጃል። ነገርግን ለበዓል ተብሎ የግቢው ካላንደር አይዛባም። ለምሳሌ በ 2017 ዓ.ም የሁለተኛ ዓመት የመጀመሪያ ሴሚስቴር ፋይናል ፈተና የሚሰጥበት ቀን በገና በዓል ላይ ይውላል። ለበዓል ብለው ትምህርት ይዘጋሉ የሚለውን አታስቡት።

Grade Calculate ማድረግ Grade እንዴት Calculate እንደሚደረግ አናውቅም post ይደረግልን ስትሉ ለነበራችሁ እንሆ አሰራሩን ይዤ ከች ብያለሁ 😊 Grade calculate ለማድረግ በመጀመሪያ 3 ነገሮችን ማወቅ ይጠበቅባችኋል:- እነሱም 1. የ እያንዳንዱን የትምህርት አይነት Crh (credit hours) In our case maths ብቻ ነው 4 crh ሌሎቹ 3 Crh ናቸው። Applied 1 ----------------- 4Crh English---------------------3Crh Physics--------------------3Crh Chemi----------------------3Crh Logic------------------------3Crh Python---------------------3Crh 2.በሁለተኛ ደረጃ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ነገር ደግሞ የእያንዳንዱ የ Grade ፊደላት ዋጋ ነው። ይሄም እንደሚከተለው ይሆናል A+ ---------- 4.0 A ------------ 4.0 A- ----------- 3.75 B+ ---------- 3.5 B ------------ 3.0 B- ----------- 2.75 C+ ---------- 2.5 C ------------2.0 C- -----------1.75 D ------------ 1 F ------------- 0 3. ሶስተኛ እና የመጨረሻው ደግሞ ማወቅ የሚጠበቅባችሁ ከመቶ ስንት ባመጣ እነዚህን ከላይ ነተጠቀሱትን Gradeኦች ይሰጠኛል የሚለውን ነው። ይሄም እንደሚከተለው ነው። 90 እና ከዛ በላይ = A+ 85 - 89 = A (85ትን እና 89ን ያካትታል) 80 - 84 = A- (80ን እና 84ትን ያካትታል) 75 - 79 = B+ (75ትን እና 79ን ያካትታል) 70 - 74 = B (70ን እና 74ትን ያካትታል) 65 - 69 = B-(65ትን እና 69ን ያካትታል) 60 - 64 = C+ (60ን እና 64ትን ያካትታል) 50 - 59 = C (50ን እና 59ን ያካትታል) 45 - 49 = C-(45ትን እና 49ን ያካትታል) 40 - 44 = D (40ን እና 44ትን ያካትታል) 39 እና ከዛ  በታች = F እሺ በስተመጨረሻ እንዴት አድርገን ነው Calculate ምናደርገው ❓... እሺ ለምሳሌ ተማሪ አየለች ተመስገን የሚከተለውን ውጤት አመጣች እንበል Maths 49.5 ( C- 🙆) መምህር ገነነ አዩን በጣም አበሳጭተዋታል😢 English 72 ( B  🐒) Physics 66 (B- Oops🙄) Chemi 94 ( A+...  chemoን እማ ተክናበታለች Logic 87  (A...አየሉ Logic ላይ ጥሩ ናት👏) Python 78 ( B+...Wow!) አሁን ምን እናረጋለን ... የ አዩን ውጤቶቾ በእያንዳንዱ ትምህርት Crh እናባዛቸዋለን Maths => 1.75 × 4 = 7 English => 3 × 3 = 9 Physics => 2.75 × 3 = 8.25 Chemistry => 4 × 3 = 12 Logic => 4 × 3 = 12 Pyhton => 3.5 × 3 = 10.5 ከዛ ተባዝተው የሚመጡትን ውጤቶች እንደምራቸዋለን 7 + 9 + 8.25 + 12 + 12 + 10.5 = 58.75 ተደምሮም የመጣልንን ውጤት ለ Crhኦቹ ድምር እናካፍለዋለን የ Crhኦቹ ድምር => 4 + 3 + 3 + 3 + 3 + 3 = 19 ስለዚህ 58.75/19 = 3.092 ( አየሉን እንዳይከፋት አስኪ 3.1 እንበልላት)

📒 ማስታወሻ/ደብተር 📔 እዚህ እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። እንደ high school ለእያንዳንዱ ትምህርት አንድ ደብተር ካላችሁም መብታችሁ ነው። ሁሉንም በአንድ ካላችሁም ትችላላችሁ። ዋናው ነገር የሚፃፍ ነገርን በትክክል ትፅፋላችሁ ወይ በቂ የሆነ ማስታወሻስ ትወስዳላችሁ ወይ የሚለው ነው። እኔ ምመክራችሁ ግን ባለ ብዙ subject ደብተር ግዙ። ይሄ በአንድ ላይ አራት እና አምስት subject የሚይዘውን ከገዛችሁ ምርጥ ነው። አስፈላጊ ሲሆን ሌላ ትጨምራላችሁ። ፁሁፍ እንደየአስተማሪው ነው። አንዳንዱ ሞጁሉን ይገለብጣል 😏 ... አንዳንዱ ደግሞ ብትለምኑትም ምንም አይፅፍም። ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ሁሉ ማይፅፍ አለ። በቃ ዝም ብሎ ይገባል ያወራል ከዛ ይወጣል ... እሱ ሲወጣ ሁልጊዜ ሰሌዳው ፅድት እንዳለ ነው 😅... እና እንደየራሳችሁ የንባብ ዘዴ ነው ማስታወሻ ሚያስፈልጋችሁ። በተለይ ደግሞ ወረቀት አስጠርዞ መጠቀም እዚህ ግቢ common ነው። ስለዚህ እንደሚመቻችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።

#ASTU #Grading_system (የ Grade ፊደላት ዋጋ) #Mark    #Letter_Grade   #Grade_Pt 1. (90 - 100)       A+                        4.00 2. (85 - 89)         A                           4.00 3. (80 - 84)         A-                          3.75 4. (75 - 79)         B+                         3.50 5. (70 - 74)         B                           3.00 6. (65 - 69)         B-                          2.75 7. (60 - 64)         C+                         2.50 8. (50 - 59)         C                           2.00 9. (45 - 49)         C-                          1.75 10. (40 - 44)       D                           1.00 11. (0 - 39)         F                            0.00 12.    I            Incomplete                   _ 13.  NG           Non Grade                   _

መምህራን 👨‍🏫 በምንም አይነት ሁኔታ ከአስተማሪ ጋር የማይሆን ነገር ውስጥ አትግቡ ፤ አትነካኩ። አስተማሪ አንዴ ከጠመዳችሁ አይፋታችሁም። Pls pls pls pls ከአስተማሪ ጋር ያላችሁን ግንኙነት በተቻለ መጠን መልካም ብቻ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጉ። አንዴ አይን ውስጥ ከገባችሁ ትቸገራላችሁ። አንዳንድ አስተማሪ ደግሞ መከራ በልታችሁ የምታመጡትን ግሬድ ሁሉ ገደል ሊከትባችሁ ይችላል። ስለዚህ ተጠንቀቁ። አስተማሪው በድሏችሁ እናንተ ይቅርታ ጠይቁ። "መብት አለኝ ፣ ሰርቼ ያገኘሁት ውጤቴ ነው ፣ ምን ያመጣል..." ምናምን የሚሉ ድንፋታዎች ገደል ከመክተት በስተቀር ምንም አይፈይዱም። በእርግጥ ብዙ ጊዜ የሚያናድድ ሁኔታ ሊገጥማችሁ ይችላል። ነገርግን እራሳችሁን በደንብ ተቆጣጠሩ። በሚገባ መምህራኖችን አክብሩ። ትልቅ ክብር ስጡአቸው። ትልቅ ሰው እየሆንኩ ነው 🫨 ፣ እራሴን መራለሁ እንጂ በማንም አልመራም 🫢፣ የራሴ ህግ ያለኝ 🤓 በራሴ ህግ የምመራ ሲግማ ነኝ 💀🤣... " ምናምን የሚሉ ቅዠቶች ውጤታቸው የማትፈልጉትን ነገር መማር ወይም ሻንጣ ተሸክሞ ወደ ቤት መሄድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ጠንቀቅ በሉ ፣ መምህራንን (ምንም አይነት ቢሆኑ) አክብሩአቸው ለማለት ያክል ነው።

#ASTU 🚪 የበር ቁልፍ 🔑 የዶርማችሁ በር ቁልፍ የሲሊንደሩ ቁልፍ ሲሆን ሎከር የምትቆልፉበት ደግሞ እንዲህ 🔐 አይነቱ ቁልፍ ነው። እናም ጠንከር ያለ የሎከር ቁልፍ ቢኖራችሁ ጥሩ ነው። የመጋዘን ቁልፍ ገዝታችሁ ደግሞ አልገባም እንዳይል 😁 ... ስለዚህ መጠነኛ ቁልፍ ግዙ።

#ASTU ፍሬሽማን ላይ ቻሌንጅ ሚያደርገው ብዙ ተማሪ ነው ወይስ ጥቂት ተማሪ ነው ❓ እውነት ለመናገር ሁሉም ተማሪ ማለት በሚቻል ደረጃ ጥሩ ውጤት ለማግኘት የማይፈነቅለው ድንጋይ ፣ የማይወጣው ተራራ ፣ የማይወርደው ሸለቆ የለም። ተኝቶ የሚያድር ተማሪ የለም። አስባችሁታል ስምንት / ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከላይብረሪ እየወጣችሁ በዛን ሰዓት ለማንበብ የሚገባ ተማሪ ስታገኙ ... 🫢🤭 ስለዚህ ቻሌንጅ አለ እናም ጠንከር ብላችሁ መዋጋት ነው። 🫡 በእርግጠኝነት ታሸንፋላችሁ 🔥

#ASTU ክሊኒክ 🏥 ክሊኒክ የምትታከሙት በነፃ ነው። ምናልባት የግቢው ካፌ ምግብ ካሳመማችሁ እና ጨጓራችሁ ላይ ጉዳት የማስከተል እድል ካለው ግቢው ለጤንነታችሁ ቅድሚያ ስለሚሰጥ ስፔሻል ተመጋቢ እንድትሆኑ ያደርጋል። ስፔሻል ተመጋቢ ማለት ተማሪዎች ከሚመገቡት መደበኛ ምግብ በጥራቱ እጅግ ከፍ ያለ ምግብ የሚመገብ ማለት ነው። የቤት ምግብ በሉት። እንደውም ከቤትም ይበልጣል ይላሉ 😁። ስፔሻል ተመጋቢ ትንሽ ስለሆነ እጥር ምጥን አድርገው መስራቱን አዘጋጆቹ ተክነውበታል 👌። ከመደበኛው ምግብ በጣም ይለያል ፤ ጣዕሙም እንዲሁም ሁሉ ነገሩ ይለያል።

#ASTU ማታ ማታ እስከፈለጋችሁበት ሰዓት ድረስ ላይብረሪ መቆየት ትችላላችሁ። በእርግጥ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ይዘጋል እናም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ማታ ላይ አንብባችሁ ስትመለሱ like 6 ፣ 7 ወይ 8 ሰዓት ላይ ብቻችሁን ባትሆኑ ይመረጣል። ሌባ አግኝቷችሁ ልትዘረፉ ትችላላችሁ (ይሄ ብዙም risk የለውም)። ምናልባት ጅቦቹ በብዛት አሉ በዛ ሰዓት። አይነኳችሁም። ግን ብቻችሁን ከሆናችሁ መፍራታችሁ እና መሸበራችሁ ስለማይቀር ከጓደኞቻችሁ ጋር ሆናችሁ አምሹ እንጂ ብቻችሁን አትሁኑ።