Mereja መረጃ
Ir al canal en Telegram
2 937
Suscriptores
-424 horas
-157 días
-2830 días
Archivo de publicaciones
2 937
ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች ለስራ ወደዚህ አከባቢ በመምጣት የሚኖሩ ኦሮመኛ ተናጋሪ አርሶ አደሮች ከፋኖ ጋር ለመጋጨት ተሰጥቷቸው የነበረውን 2 ብሬን እና ከ20 በላይ ክላሽንኮፍ መሣሪያዎች በሙሉ ፍላጎታቸው ማስረከባቸውንና ከዚህ በኋላ ከፋኖ ጎን በመቆም በሰላም ለመኖር መስማማታቸው ተመላክቷል።
በተመሳሳይ ዜና በጃማ ወረዳ ፋጅ ንዑስ ወረዳ የ152ኛ ክፍለ ጦር አርበኞች ከሕዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት፡ ነዋሪዎቹ ለትግሉ ያላቸውን ሙሉ ደጋፊነትና አረጋግጠዋል ሲል የ15ኛ ኮር ቃል አቀባይ መረጃዉን ማድረሱን ዕዙ በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
2 937
የበላይ ዘለቀ ዕዝ አርበኞች ከማዕከላዊ አርማጭሆ እስከ ከደራና አንዳቤት ድረስ በወሰዱት ጥብቅ እርምጃ የጠላት ጦርን በማሽመድመድ ከፍተኛ ድል ተቀዳጁ!
89 የአገዛዙ ወታደሮች በተደመሰሱበት በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳው ውጊያ፡ ማሰሮ ደንብ ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ስትውል፡ 15 ክላሽንኮቭን ጨምሮ አንድ ወታደራዊ ቦቲ ተሽከርካሪና አንድ ወታደራዊ ፓትሮል በአርበኞቹ እጅ ገብቷል።
በሌላ በኩል በፋኖ የጦር ንድፍና የበላይነት እየተመራ በደራ እና አንዳቤት ወረዳ በተደረገ ተጋድሎ የጠላት ኃይል ዙሪያ ገባውን ተከቦ በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ኪሳራን መከናነቡን ለማረጋገጥ ተችሏል።
2 937
+1
ዙ23ቱ ወድሟል/ ኮሎኔሉ ተገድሏል!
የምኒልክ ዕዝ አርበኞች በወገል ጤና ከተማ ቻይና ካምፕ በሰፈረው የአገዛዙ ጦር ላይ ላለፉት አራት ቀናት የከበባ ማጥቃት ባማካሄድ የጠላትን አንድ ክፍለ ጦር መበታተናቸውንና ከበባውን ለመስበር የተንቀሳቀሱ የጠላት ተጨማሪ ሁለት ሬጅመንቶችን ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸው ተገለጸ።
አገዛዙ በድሮንና በጦር ጄት ታግዞ ከበባውን ለመስበር ያደረገው ሙከራ መክሸፉ የተነገረ ሲሆን፡ በውጊያው አንድ የኮሎኔልነት ማዕረግተኛን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መደምሰሳቸውና የጠላት ሜካናይዝድ መሣሪያዎች መውደማቸው ተመላክቷል።
ከወደመው ሜካናይዝድ መካከል አንድ ፀረ አውሮፕላን ዙ23 መሣሪያን ጨምሮ ሌሎች መሣሪያዎችና ወታደራዊ ኦራሎች እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ ተችሏል።
VIDEO በምስራቅ ግንባር ደላንታ እና ተሬ የተደመሰሱ የአገዛዙ ወታደሮች አስከሬን በእሳካቫተር ማሽን እየታፈሱ በጅምላ ሲቀበሩ የሚያሳይ ስለሆነ፡ ነፍሰጡር ሴቶች+ህፃናት+ከድንጋጤ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሕመምና ተያያዥ ያለባቸው ሰዎች ባያዩት ይመከራል።
2 937
📌የአማራ ብሔርተኝነት ስትራቴጂካዊ ምሥጢርና የነፃነት መንገድ!
የአማራ ብሔርተኝነት የቁጣ ስሜት ወይም የጊዜያዊ ብስጭት ውጤት አይደለም፣ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መዋቅሮችን ጥልቀት ባለው መልኩ የመረዳት ፍሬ የሆነ አገራዊና ህልውናዊ ንቃት ነው።
ይህ ንቃት ሲበራልህ፣ ታሪክን በሆይ ሆይታ ሳይሆን ከወንድምና እህቶችህ ጋር የጥናት ቡድን አዋቅረህ የኢትዮጵያን የታሪክ መስመር መስመር በጥንቃቄ ታነበዋለህ። በአማራ ህዝብ ላይ የታወጀው ጦርነትና ፀረ-አማራ ትርክት ዛሬ እንዳልተጀመረና የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ለዚህ ትርክት ነፍስና ሥጋ የሰጠ ክስተት እንጂ፣ ፀረ-አማራ ዘመቻው በቄሳራውያን ቀደም ብሎ የተበተነ መርዝ መሆኑ ፍንትው ብሎ ይታይሃል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዘመናዊነት፣ በተለይም የአስተዳደር መዋቅሩና የትምህርት ሥርዓቱ በምዕራባውያን አስተሳሰብ እንዴት እንደተቀረፀና ይህም መዋቅር በመጨረሻ ሀገር አፍራሹን አብዮት መውለዱ እንዳልቀረ በግልጽ ታስተውላለህ።
በዚሁ የንቃት መንገድ ውስጥ ስታልፍ፣ ለአማራ ይቆረቁሩ ነበር እየተባሉ በስማቸው የሚማልላቸው ታሪካዊ አገዛዞች በራሱ በአማራ ህዝብ ላይ ያደረሱት በደልና መረሳት ይገለጥልሃል። በትምህርት፣ በጤናና በሌሎች መሰረተ-ልማቶች እነ በሸዋ፣ ወሎ፣ ጎጃምና ጎንደር እንዴት ተረስተው እንደኖሩና አገዛዞቹ በሌሎች አካባቢዎች ከተሞችን ሲከትሙ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ፋብሪካዎችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሲገነቡ እንደኖሩ ትረዳለህ።
የደርግን ወታደራዊ አምባገነንነት አምርረህ እንድትቃወም የሚያደርግህ እውነታም ያው አገዛዝ የጥቁር አማራ ልሂቃንን ጨርሶ፣ ንብረትና ቤታቸውን ወርሶ ማለፉ ነው። ከራዛ ዘመቻ እስከ ሶማሊያ፣ ከኤርትራ እስከ ሰሜኑ አካባቢዎች በየጦር ሜዳው ያለቀውና የተሰውረው በአመዛኙ የአማራ አርሶ አደርና የደሃው ልጅ እንደነበር ስለምትረዳ፣ እውነታው ሳይገባቸው ያንን ጨካኝ አምባገነን መንግስቱ ኃይለማርያምን «መንጌ» እያሉ የሚያቆላምጡትን በከፍተኛ ትዝብት ታያቸዋለህ።
በአሁኑ ወቅት ያለው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ ከፋፍሎና አዳክሞ ለዘመናት አንበርክኮ ለመግዛት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለና የዘር ማጥፋት አደጋው ዋና ምንጭ እንደሆነ ፍንትው ብሎ ይታይሃል። ይህንን አጠቃላይ መዋቅራዊና ታሪካዊ ጭቆና ለመመከትና ለመሻገርም ተዝቆ የማያልቅ ሀብታችንና የመጨረሻው የህልውና ዋስትናችን ብሔርተኝነታችን እንደሆነ ታረጋግጣለህ።
የአማራ ብሔርተኝነት በፅኑ አደረጃጀትና አስተሳሰብ ላይ እስከተገነባ ድረስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አደገ አላደገ፣ ፈላጭ ቆራጩ አብይ አህመድ ድሮንና ዘመናዊ መሳሪያ ታጠቀ አልታጠቀ፣ ወይም አገዛዙ ሪዞርት አለማ በትግሉ ግስጋሴና ድል አድራጊነት ላይ የሚፈጥረው አንዳች ተፅዕኖ እንደሌለ ፍንትው ብሎ ይገለጥልሃል። ምክንያቱም የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች ሊመልስ አይችልምና የሕልውናችን፣ የነፃነታችንና የራሳችንን ዕድል በራሳችን የመወሰን ጥያቄያችን ሙሉ በሙሉ እስካልተመለሰ ድረስ ትግላችን መቀጠሉ አይቀርም።
በዚህ ታሪካዊ የትግል ሂደት ውስጥ ከድሮንም በላይ ድሮን፣ ከተዋጊ ጀትም በላይ ጀት፣ ከከበዱ መሳሪያዎች ሁሉ በላይ መሳሪያችን - የተቀናጀው፣ የነቃውና ያልተሸነፈው ብሔርተኝነታችን ነው።
ትግላችን ያሸንፋል! (
Mulugeta Anberber
2 937
በወገል ጤና ከተማ ላለፉት አራት ቀናት ከባድ የከበባ ማጥቃት ሲያካሂድ የቆየው ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በጠላት ላይ እጅግ ከፍተኛ ኪሣራ በማድረስ አንፀባራቂ ድል ተቀዳጀ!
የትብብር ለሕልውና አካል የሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በምስራቅ ግንባር አኩሪ ገድል ፈፅሟል።
በምኒልክ 1ኛ ዕዝ 102ኛ እና 16ኛ ኮሮች የተወጣጡ ውስን አሃዶች በጠላት 11ኛ ዕዝ ስር የምትገኘው 16ኛ ክፍለጦርን በማዘዣ ጣቢያዋ ወገልጤና ቻይና ካምፕ ላይ ለአራት ቀናት በመቁረጥ በወሰደው እርምጃ ክፍለጦሯን መበታተን ችሏል።
አገዛዙ ከሰው አልባ ተዋጊ ድሮን ጀምሮ የጦር ጄትና ሌሎች ሜካናይዝ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ ከበባውን ለመስበር ያደረገው ሙከራ ከሽፎ ጦሩ የአፈር ሲሳይ ሆኖ ቀርቶበታል።
በተጨማሪም ይሄንን ከበባ ለመስበር መነሻቸውን ከተንታ አጅባር ያደረጉ በ11ኛ ዕዝ 204ኛ ኮር ከ35ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሬጅመንቶች እንዲሁም ከ84ኛ ክፍለ አንዲት ሬጅመንት ይዞ ለመግባት ቢሞክርም፡ ነገር ግን በዕዙ አርበኞች ተቆርጦ ሁለቱ ሬጅመንቶች ሙሉ በሙሉ ሲደመሰሱ አንድኛው ሬጅመንት በ101ኛ ኮር አናብስቶች ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ተበታትኗል።
ደላንታ ላይ ተቆርጣ ጥብቅ እርምጃ የተወሰደባት 16ኛ ክፍለጦር ከውስን አሃዶቿ በስተቀር ስትደመሰስ አንድ ዙ23ን ጨምሮ ሌሎች ሜካናይዝድ መሣሪያዎቿንና ወታደራዊ ንብረቷን ማውደም ተችሏል።
በተጋድሎው ከተደመሰሱ የክፍለጦሯ ወታደሮች መካከል አንድ ኮሎኔልን ጨምሮ ማዕረጋቸውን ለጊዜው በውል መለየት ያልተቻለ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙበት ለማረጋገጥ ተችሏል።
በውጊያው ከፍተኛ ኪሳራ የተከናነበው የአገዛዙ ኃይል ከትናንት ጥቅምት 04/2019 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ ወገልጤና ከተማን በድሮን ሲደበድብ አድሮ የዋለ ሲሆን በተጨማሪም ተዋጊ ሚግ በመጠቀም ከተማዋንና በዙሪያዋ የሚገኙ የእርሻ ሰብልና የንፁኋን መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።
በዚህም ህፃናትን ጨምሮ ንፁኋኖችን በገፍ ገድሏል፣ የቤት እንስሳትን ጨፍጭፏል እንዲሁም ሀብት ንብረት አውድሟል።
ከምስራቅ ግንባር አስተባባሪዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በድል ያጠናቁት የጀብደኛው 1ኛ ምኒልክ ዕዝ አሃዶች በአሁን ሰዓት ስትራቴጂክ ቦታዎችን በመቆጣጠር ተጨማሪ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመፈፀም ላይ ናቸው ሲል ዕዙ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
2 937
ምስራቅ ግንባር!
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ተንታ አጅባር ላይ በወሰደው እርምጃ ካለቀው በተጨማሪ እድል ቀንቷቸው የተማረኩ የአገዛዙ ወታደሮች።
2 937
የሕወሓት ሠራዊት በትግራይ ቆላ ተምቤን፣ በሰባት ሕጉም፣ በጭላ እና በአግበ ቀጠናዎች በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ የጠላት ኃይልን መደምሰሱ ተገለፅ።
የውስጥ ማስተካከያ አድርጎ ወደ ጠንካራ የፀረ-ማጥቃት እርምጃ በተሸጋገረ ቅፅበት በፊና ሩባ አካባቢ የአገዛዙን አንድ ሙሉ ሬጅመንት ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር መደምሰስ የቻለው ሕወሓት ኃይል፡ አሁን ደግሞ በማዕከላዊ ትግራይ የጠላት ጦርን ቆርጦ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን አስታውቋል።
የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት ቦታዎችን በመቆጣጠር "ድል ተቀዳጀሁ" በማለት ስሁት ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም፡ በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን ከተገለፀው በተቃራኒ የሆነና ከባድ እልቂት እያስተናገደ መሆኑን በገሃድ ያሳየ ነው ሲሉ የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
2 937
በምስራቅ ግንባር እየተካሄደ ባለው ከባድ ውጊያ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር አሃዶች በወሰዱት የስቦ መምታት እርምጃ ሁለት ሬጅመንት ሙሉ የጠላት ጦርን ደምስሰው አንፀባራቂ ድል ተቀዳጁ።
አርበኞቹ በወሰዱት መብረቃዊ እርምጃ ሁለት ሬጅመንት ሙሉ የጠላት ሠራዊትን ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ በማድረግ ሲደመስሱ፡ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችን ማርከው ታጥቀዋል።
በደላንታ ወረዳ ላለፉት አራት ቀናት ተቆርጦ ለሚገኘው ኃይል እገዛ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ ከነበረው የጠላት ጦር መካከል ነው ሁለት ሬጅመንት ሙሉ ወታደር በጀግኖቹ ክንድ እንደጨው ሟሙቶ የቀረው።
2 937
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ከደራ-አንዳቤት እስከ ማዕከላዊ አርማጭሆ ቀጣና በጠላት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ተፈጸመበት !
በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ከማዕከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ እስከ ደራና አንዳቤት ቀጣናዎች በተካሄዱ አውደ ውጊያዎች በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ አካላዊ፣ ቁሳዊና ሞራላዊ ስብራት አድርሷል።
በ305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ከተማ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ምት አሳርፎበታል። ጥቅምት 04/2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ሲካሄድ ባደረው በዚህ አውደ ውጊያ፣ የጠላት ምሽግ የነበረችውን የወረዳዋን መቀመጫ ማሰሮ ደንብ ከተማ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ሲሆን፣ ጠላት የሚመካበት የኮንክሪት ምሽግም በመሰባበር:-
➛48 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣
➛41 ጥምር ኃይሉ ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ቁስለኛ አስተናግዷል፤
➛15 ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣
➛1 ቦቲ መኪና እና 1 ፓትሮል የጠላት መኪና ተማርኳል።
ተጨማሪ ኃይል ከጎንደር የተንቀሳቀሰለት ይህ ጠላት ኩርቢ ላይ ደፈጣ በመጣል በሌሎች የኮሩ አሀዶች እንዲመታ ተደርጓል።
በሌላ በኩል በደራ እና አንዳቤት ወረዳዎች አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር፣ በጣና ገላውዴዎስ ክፍለ ጦር እንዲሁም በኮሩ ቃኝና መሐንዲስ ሰራዊት ቅንጅት ሰፊ ቀጠና የሸፈነ አውደ ውጊያ አድርጓል። ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ በቁርጠት፣ ቢደዝ እና ወጆ አካባቢዎች በደፈጣ የተጀመረው ይህ አውደ ውጊያ አድማሱን በማስፋት እስከ ማታ 10:00 ሰዓት ድረስ የዘለቀ መደበኛ አውደ ውጊያ ሆኖ ውሏል።
በጠጅ መረር ማርያም፣ በአምባ ኪዳነ ምሕረት፣ በሽሮ አቦ፣ በአረጊት ገዳም፣ በወንዲራር ተራራ፣ በወይራ ተራራ፣ በሾላየ ማርያም፣ በኪዳነ ምሕረት፣ በቁርጠት፣ በቢደዝ፣ በወጆ፣ በአረቂ ወንዝ፣ በወንድ ይራድ፣ በደብረ ገሊላ እና በሌሎችም አጎራባች ቦታዎች የተካሄደ ሲሆን፣ በጠላት ኃይል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
ምንጭ፦በአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
2 937
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ አመራሮች ከምዕራብ በለሳ አርባያ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ!
በመድረኩ በከተማዋ የሚስተዋሉ መልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ በቀጣናው የሚታዩ ችግሮችን በማስተካከል ህዝባዊ አንድነትን ማጠናከር፣ የፋኖን ወቅታዊ የትግል ቁመና ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መገምገም፣ እንዲሁም ማህበረሰቡ ለትግሉ የሚያደርገውን ደጀንነትና አጠቃላይ የትግሉን ሂደት በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በዚህ ህዝባዊ ውይይት የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሰብሳቢ አርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ፣ የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አዳነ ፀጋ እንዲሁም ሌሎች የዕዝ ፣የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች ተገኝተዋል።
በውይይቱ የተሳተፉት የከተማው ነዋሪዎች የማህበረሰብ ተወካዮች ፣ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች መድረኩ ወቅታዊና አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በሰራተኞች ደህንነት ምክንያት በመሰራት ያሉ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ፕሮጀክቶች (መንገድ፣የውሃ ) ሳይስተጎሉ ስራቸውን እንዲጠናቀቅ ጥበቃ ማድረግ፣ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ፣ ህዝባዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከአደጋና ከጉዳት እንዲጠበቁ አመራር መስጠት፣ ህዝቡ ማህበራዊ ፍትህ እንዲያገኝ ማስቻል፣ ህዝባዊ አደረጃጀቶች ታጋዩን ዘርፈ ብዙ ድጋፉ እንዲያደርጉ ተልዕኮ መስጠት እና ወታደራዊ አደረጃጀቶችን ማስተካከል ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
በተጨማሪም በቀጣናው የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ግልጽ የሆነ የዕዝ ሰንሰለትና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ እንደሚገባ የተናገሩት የውይይቱ ተሳታፊዎች ፣ የሚደረጉ ህዝባዊ የሎጅስቲክስ ድጋፎች በተቀናጀ ሁኔታ እንዲመሩ አመራር መስጠት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በውይይቱ የተሳተፉት የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ በመስጠት፤ በቀጣይ ትኩረት የሚሹና መስተካከል ያለባቸውን ስራዎች በመለየት አስፈላጊውን የእርምት እርንምጃ መውሰድ ተገቢ መሆኑን አጽንኦት ሰጠዋል።
ምንጭ፦የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ 3ኛ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
2 937
የግዳን ወረዳ ዋና ከተማ ሙጃን ጨምሮ ወታደራዊ ስትራቴጂክ ቦታ የሆነችው ወንዳች ከተማን የምኒልክ ዕዝ ተቆጣጠረ!
በምስራቅ ግንባር እየተደረገ በሚገኘው ዘመቻ በወሎ ቤተአማራ ሰፊ አካባቢዎችን ያካለለ ከፍተኛ ዉጊያ እየተደረገ ሲሆን የአገዛዙ ሀይል የፋኖን ክንድ መቋቋም ተስኖት እየሸሸ ይገኛል።
በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ የወረዳው ዋና ከተማ ሙጃን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን የጀብደኛዉ የምኒልክ 1ኛ ዕዝ 13ኛ ኮር ሠራዊት ተቆጣጥሯል ሲል ምኒልክ ዕዝ በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
2 937
አፋብን ምስራቅ ግንባር ጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝ በአገዛዙ ግብስብስ ሰራዊት ላይ ድል ማድረጉን ቀጥሏል!
ከተንታ ወደ ተሬና ጉና የተባሉ ቦታዎች ተንቀሳቅሶ የነበረዉ የጠላት ኃይል በስቦ መምታት ስልት የተመታ ሲሆን የትብብር ለሕልውና አካል የሆነው አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 101ኛ ኮር ወደ ገዥ ወታደራዊ መሬት ስቦ በማስገባት የጠላትን ሁለት (02) ሬጅመንት (ሻለቃ) ሙሉ የጠላት ኃይልን በገባበት አስቀርቶታል።
በወሎ ቤተ-አማራ ከፍተኛ ዉጊያዎች እየተደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት አገዛዙ በእጁ ያለውን ማንኛውንም የሰማይ እና የመሬት መሳሪያ ቢጠቀምም የጀብደኛው ምኒልክ 1ኛ ዕዝን ሠራዊት ከባድ ምት መቋቋም አቅቶት የበረሃ ሲሳይ እየሆነ ይገኛል።
በደቡብ ወሎ ዞን አጅባር እና ተንታ የነበረውን ሀይሉን ለቃቅሞ ወደ ጉና እና ተሬ ያንቀሳቀሰው ጠለት ድል ሳይቀናው ያሰማራው ሰራዊት በ101ኛ ኮር ነበልባሎች ተደምስሷል።
የ101ኛ ኮር አሃድ የሆኑት አይበገሬዎቹ የ11ኛ እና 15ኛ ክፍለጦሮች ተናዳፊ ተዋጊዎች በወሰዱት እርምጃም ሰብዓዊና እና ቁሳዊ ጉዳት ደርሶበት ተበታትኗል።
በዚህ ግንባር የብልፅግናው አገዛዝ ያሰማራው የ11ኛ ዕዝ 204ኛ ኮር 35ኛ ክፍለጦር 2ኛ እና 3ኛ ሻለቆች እንዲሁም ከ84ኛ ክፍለጦር አንድ ሻለቃ ቢያሰማራም የ35ኛ ክፍለጦር ሁለቱ ሻለቃ ተደ*ም*ስሰዉ ቀሪዉ ሙትና ቁስለኛቸውን ሳያነሳ በየበረሀው ተበትኖ ሸሽቷል።
በዚህ መብረቃዊ ተጋድሎና አውደውጊያ፥
✔️ ብሬን ሁለት (02)
✔️ ስናይፐር አንድ (01)
✔️ ክላሽንኮቭ ስልሳ አምስት (65)
✔️ የክላሽንኮቭ ተተኳሽ = 6570
✔️ የብሬን ተተኳሽ = 5065
✔️ የእጅ ቦንብ = 20 እንዲሁም በርካታ ወታደራዊ ሻንጣዎች መረከብ ተችሏል።
የተማረከ የሰው ሀይል ሰላሳ አምስት (35) እንዲሁም ወታደራዊ አመራሮች የተደመሰሱ ሲሆን ሶስት (03) የ10 አለቃ ማዕረግ ያላቸው እና አንድ (01) የ50 አለቃ ማዕረግ ያለው የአገዛዙ ወታደራዊ አመራርሮች መማረካቸውን የ101ኛ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል መረጃውን አድርሷል ሲል ዕዙ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
2 937
በደቡብ ግንባር በቀጠለው ተጋድሎ የአሳምነው ዕዝ አርበኞች በመንዝ ማማ ሞላሌ ከተማ በመሸገው የብልፅግና ቅጥረኛ ሠራዊት ላይ በወሰዱት እርምጃ መስመራዊ አዋጊዎችን ጨምሮ 18 ወታደራዊ መሪዎችን መደምሰሳቸው ታውቋል።
በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ ከሰሞኑ በቀጠለው ተጋድሎ በመንዝ አውራጃ ታላቅ ጀብዱ አየሰራ ግስጋሴውን ቀጥሏል።
ትናንት ጥቅምት 4 ከማለዳው ጀምሮ በተሰራ ጀብዱ በመንዝ ሞላሌ ከተማ 18 የሚደርሱ የስረዕቱ ወታደራዊ አዋጊወች ሲደመ*ሰሱ በቁጥሩ ብዙ የሆነ የኮማንዶ ጦር እና የክልሉ አድማብተናን ጨምሮ ሚሊሻዎች መደም*ሰሳቸው ተረጋግጧል ።
በዚህም አውደ ውጊያ የተ*ገደሉ የአገዛዙ አገልጋይ ሰራዊት በጅምላ በሞላሌ ከተማ የተቀበሩ መሆኑ ተገልጿል።
የአገዛዙ ሰራዊት ከውጊያ ሸሽተው ሂወታቸውን ለማትረፍ እጅ የሰጡ ሲኖሩ ቀሪው ራሱን የሚከላከልበትን እድል ለመጠቀም ከደብረብርሃንና ከሰላድንጋይ ከተሞች ሀይል ሲያጓጉዝ ለመዋል ተገዷል።
በዚህ አወደ ውጊያ ከባድ መሳርያዎችን ከድሮን እስከ መድፍ በብዛት ሲጠቀም የዋለ ቢሆንም በወገን ሀይል ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን የግንባር መረጃችን ገልጿል።
የፀረ-ህዝቡ አገዛዙ ሰራዊት ምሽግን የሰባበረው ጀብደኛው ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ የፋኖ ሰራዊት የብልፅግናን ቅጥረኛ ሰራዊት ምርኮኛና ሙ*ት ሲያደርጉት ፤ የተበተነው ሰራዊት እየተለቀመ በመሆኑ ለተበተነው ለብልፅግና ጦር ከመደምሰስ በአፋጣኝ እንደጓዶቻችሁ እጅ እድሰጡ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው 5ኛ ዕዝ መልዕክት ማስተላለፉን ዕዙ በህዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
