es
Feedback
A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

Ir al canal en Telegram

📈 Análisis del canal de Telegram A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU

El canal A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU (@aahdabofficial) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 33 115 suscriptores, ocupando la posición 322 en la categoría Bienes inmuebles y el puesto 1 077 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 33 115 suscriptores.

Según los últimos datos del 26 septiembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 277, y en las últimas 24 horas de 8, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 28.06%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 16.68% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 9 289 visualizaciones. En el primer día suele acumular 5 521 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 0.

📝 Descripción y política de contenido

No se ha proporcionado la descripción del canal.

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 27 septiembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Bienes inmuebles.

33 115
Suscriptores
+824 horas
+1557 días
+27730 días
Archivo de publicaciones
አርዓያነት ያለው የማህበራት ቤት ግንባታ አፈጻጸም በቃሊቲ ሳይት መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም   በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው  ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!!! ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ነበር። ዛሬ ግን የዜጎቻችንን ክብር ወደ ጠበቀ ውብ የመኖሪያ ቤትና ስፍራ ተሸጋግረው በደስታ ሲኖሩ ማየት ወደር የሌለው ደስታ ይሰጣል። ግን ዋናው ጥያቄ  በሀገራችን ዋና ከተማ  ውስጥ እንዴት ብዙ ዜጎቻችን እንደዛ  አይነት  አስቸጋሪ አኗኗር ውስጥ  ለዓመታት  ኖሩ? ዛሬስ ሁሉም በዚህ ፍጥነት  እየተለወጠ ያለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡ መልሱ ፡- ይህን ስራ  እውን ያደረግነው ብዙ አካላትን በማስተባበርና በመደመር ነው። ከያለበት ያለውን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ሳንሰስት ደምረናል። የተወሰኑት በፋይናንስ ሲደግፉን፣ ሌሎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በዲዛይን እና በግንባታ ስራው ላይ በንቃት በበጎ ፍቃድ ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቻችንም  ለተሻለ ልማት  የለውጥን ተስፋ ሰንቀው ትልቅ ትብብር አድርገዋል። ይህ ሁሉ ጥረት አንድ ላይ ተደምሮ ትልቅ አቅም በመሆን ይህን የመሰለ የመኖሪያ መንደር እና አካባቢን  ፈጠረ። ቅጠል ተራም ታሪኩ ተቀየረ። ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ላይ ተደምሮ ይህንን አዲስ ሰፈር የፈጠረው መሬት፣ ሰዉም፣ ገንዘቡም፣ እውቀቱም የእኛው ነው። ትርጉሙ አንድ ቦታ ላይ ንፁህ የመኖሪያ ስፍራ ከማግኘት እጅግ የላቀ ነው። ይልቁንም ለጋራ ራእይ እየተባበርን፣ በቅንነት፣ በትጋት እና እውነተኛ አገልጋይነት አብረን ስንሰራ ብዙ ሀብቶቻችን ተደምረው የሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ፣ የዜግነትን ክብር የሚያልቁ ፣ አዳዲስ እድል እና ሀብት ይፈጥራሉ። ስለዚህ በማንኛውም ነገር በጋራ እንቁም፤ ትብብራችንንም ይበልጥ እናጠናክር። ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት በመተማመን አብረን እንትጋ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአራት ወር ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል? 👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9
+9
በአራት ወር ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል? 👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች 👉 በአራት ወራት ዉስጥ የተገነቡ 960 ቤቶች 👉 ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች 👉 በውስጡ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ 👉 የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ 👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ 👉 ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች 👉 ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ 👉 እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ: በአስከፊ የእሳት አደጋ የተጎዳ አካባቢ ነበር 👉 “መርካቶ የበጎነት መንደር “ አካባቢዉን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸውን እንደ ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ ያሉ ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።

ቅጠል ተራን ወደ ንፁህ አረንጓዴ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገን በቅጠል ተራ 960 ቤቶችን በአራት ወር ዉስጥ ገነብተን ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች መልሰን አስተላልፈናል። ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ በመሆኑ የሰው ህይወትም በአስከፊ ሁኔታ በእሳት አደጋ ያጣንበት አካባቢ ነበር። ዛሬ ግን እጅግ ያማሩ፥ ዘመናዊና ሁሉንም ነገር የተሟሉላቸው ባለ 9 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎችን 960 ቤቶች ተገንብተው ወደ ምቹ መኖሪያ አካባቢ ተቀይሯል። "የመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር" በ11, 000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች በአጠቃላይ 960 ቤቶች ያሉት ሲሆኑ፣ ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች በውስጡም የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ፥ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች በዘመናዊ መልክ ተሟልተው ተገንብተዋል። ይህ በመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር የሰው ህይወትን የሚቀይር ፥ መርካቶ አካባቢን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸው ( ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ) ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ። ቃል በተግባር ማለት ይህ ነው፥ እንደዚህ ዓይነት የተወሳሰበ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለሰው ልጆች የሚመጥኑ፥ ነዋሪዎች የክብር ኑሮ እንዲኖሩ፥ ህይወታቸውን የሚቀይሩ ተግባራትን ያለ እረፍት 24/7 በመፈፀም ነዋሪዎች አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ማድረግ ነው ። የስራዎቻችንን ማዕከል ሁሉ ሰው ተኮር አድርገን፥ ከተማችን ውብ ፅዱ፥ ለነዋሪዎቻችን የተመቸች ከተማ እንድትሆን ያለ እረፍት የመስራት ተግባራችን ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን። ካላችሁ አካፍላችሁ ከከተማ አስተዳደራችን ጎን በመሆን የበጎ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ፥ ዛሬም በቅጠል ተራ የበጎነት መንደር እንድንቀይር ያገዛችሁን በተለይ ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ፥ በግንባታው የተሳተፋችሁ ሁሉ በነዋሪዎች ስም ከልብ እናመሰግናለን ። ቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ ተቀይፘል ! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡ እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡ ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡ መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡ እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡ ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡ መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

በቢሮው የኮሙኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት በየወሩ እየተዘጋጀ ለንባብ የሚበቃው ዜና መፅሔት  የወርሀ ነሀሴ ዕትም እነሆ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት        ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aahdab

በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ https://forms.gle/iUFViVf7RyVU8jvv6
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ https://forms.gle/iUFViVf7RyVU8jvv6

አርአያነት ያለው የማህበር ቤት ግንባታ እንቅስቃሴ በቃሊቲ ሳይት በከተማችን አዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት ከተዘረጉ የቤት ልማት መርሃ ግብሮች መካከል የማህበራት ቤቶች ግንባታ አንዱ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት የግንባታ ሳይቶች ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛል። በ70/30 መርሃ ግብር የተደራጁ 65 ማህበራት በ7 ሳይቶች ግንባታ እያካሄዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 50 የሚሆኑት ግንባታቸውን በነቃ ሁኔታ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የማህበር ቤቶችና ህንጻዎች ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢ/ር ቢልሱማ ተመስገን ይገልጻሉ፡፡ ዳይሬክቶሯ እንዳስታወቁት፤ ቢሮው የመሬት አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የዲዛይንና የፋይናንስ ብድርን ከማመቻቸት በተጨማሪ ቀጣይነት ያለው ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። በቃሊቲ ወርቁ ሰፈር ሳይት ከሚገኙ 9 ማህበራት አንዱ የሆነው የ"እፎይታ" ማህበር ቤት ግንባታ አፈጻጸም  ለሌሎች ማህበራት ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። ለዚህ ስኬት ዋናው ምስጢር የአማካሪው፣ የስራ ተቋራጩ እና የማህበሩ ተቀናጅቶና ተናቦ መስራት መሆኑን የጠቀሱት ኢ/ር ቢልሱማ፣ አፈጻጸሙ የማህበር ቤት መርሃ ግብር ፍሬ እያፈራ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል። የፕሮጀክት ማናጀሩ ኢ/ር ብርሃኑ ጎሹ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 1 ዓመት የሞላው መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት የስትራክቸራል ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የብሎኬት እና የማጠናቀቂያ (finishing) ስራዎች በፈጣን ሁኔታ እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የግንባታውን ጥራትና ደህንነት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት አማካሪ መሐንዲሱ ኢ/ር ሰለሞን፣ ለግንባታው የሚገቡ ቁሳቁሶች በሙሉ ጥብቅ የላቦራቶሪ ፍተሻና ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው አረጋግጠዋል። የማህበሩ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት በላቸው የአባላቱ የቤት ባለቤት የመሆን ጉጉት ከፍተኛ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ቁርጠኝነት በመኖሩም ግንባታው በዚህ ፍጥነት ወደ ፍጻሜ በመቃረቡ በማህበሩ አባላት ዘንድ ትልቅ ደስታ መፈጠሩን ገልጸዋል።        መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት        ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aahdab                                                                              

ማስታወቂያ ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ
ማስታወቂያ ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎ ‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያን
በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎ ‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ። ‎ ‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው። ‎ ‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው። ‎ ‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አከባበር በተመለከተ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ ስለበዓላቱ ምንነት፣ ትውፊት፣ ሀገራዊ ጠቀሜታ
+9
የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አከባበር በተመለከተ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ ስለበዓላቱ ምንነት፣ ትውፊት፣ ሀገራዊ ጠቀሜታ፣ አከባበር እና ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ጉዳዮች በሰፊው ተዳሷል፡፡   መድረኩ ላይ በዓላቱ አከባበር ወቅት ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችን በሞቅታና በኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት ባህል በመቀበል፣የአካባቢን ጽዳት መጠበቅና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በማጠናከር አስተዋጽኦ ማደረግ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡ የውይይቱ ተሳታፊዎች የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የህዝቦችን ወንድማማችነት እና አንድነት የሚያጠናክሩ ታላላቅ ሀብቶች መሆናቸውን በመጠቆም፣ የበዓላቱ አከባበር በሰላም እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሰራተኞችና ህብረተሰቡ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት        ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aahdab

በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት። 🇪🇹 🇨🇳 Conversations with China’s President Xi Jinping on the sidelin
+1
በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት። 🇪🇹 🇨🇳 Conversations with China’s President Xi Jinping on the sidelines of the BRICS Summit. 🇪🇹 🇨🇳 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)