A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
الذهاب إلى القناة على Telegram
إظهار المزيد
📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
تُعد قناة A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU (@aahdabofficial) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 33 115 مشتركاً، محتلاً المرتبة 322 في فئة العقار العقاري والمرتبة 1 077 في منطقة Ethiopia.
📊 مؤشرات الجمهور والحراك
منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 33 115 مشتركاً.
بحسب آخر البيانات بتاريخ 26 سبتمبر, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار 277، وفي آخر 24 ساعة بمقدار 8، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.
- حالة التحقق: غير موثّقة
- معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 28.06%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 16.68% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
- وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 9 289 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 5 521 مشاهدة.
- التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 0.
📝 الوصف وسياسة المحتوى
وصف القناة غير متوفر.
بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 27 سبتمبر, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة العقار العقاري.
33 115
المشتركون
+824 ساعات
+1557 أيام
+27730 أيام
أرشيف المشاركات
አርዓያነት ያለው የማህበራት ቤት ግንባታ አፈጻጸም በቃሊቲ ሳይት
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳር ቢሮ
የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!!!
ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ነበር።
ዛሬ ግን የዜጎቻችንን ክብር ወደ ጠበቀ ውብ የመኖሪያ ቤትና ስፍራ ተሸጋግረው በደስታ ሲኖሩ ማየት ወደር የሌለው ደስታ ይሰጣል።
ግን ዋናው ጥያቄ በሀገራችን ዋና ከተማ ውስጥ እንዴት ብዙ ዜጎቻችን እንደዛ አይነት አስቸጋሪ አኗኗር ውስጥ ለዓመታት ኖሩ? ዛሬስ ሁሉም በዚህ ፍጥነት እየተለወጠ ያለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡
መልሱ ፡- ይህን ስራ እውን ያደረግነው ብዙ አካላትን በማስተባበርና በመደመር ነው። ከያለበት ያለውን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ሳንሰስት ደምረናል። የተወሰኑት በፋይናንስ ሲደግፉን፣ ሌሎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በዲዛይን እና በግንባታ ስራው ላይ በንቃት በበጎ ፍቃድ ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቻችንም ለተሻለ ልማት የለውጥን ተስፋ ሰንቀው ትልቅ ትብብር አድርገዋል።
ይህ ሁሉ ጥረት አንድ ላይ ተደምሮ ትልቅ አቅም በመሆን ይህን የመሰለ የመኖሪያ መንደር እና አካባቢን ፈጠረ። ቅጠል ተራም ታሪኩ ተቀየረ።
ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ላይ ተደምሮ ይህንን አዲስ ሰፈር የፈጠረው መሬት፣ ሰዉም፣ ገንዘቡም፣ እውቀቱም የእኛው ነው። ትርጉሙ አንድ ቦታ ላይ ንፁህ የመኖሪያ ስፍራ ከማግኘት እጅግ የላቀ ነው። ይልቁንም ለጋራ ራእይ እየተባበርን፣ በቅንነት፣ በትጋት እና እውነተኛ አገልጋይነት አብረን ስንሰራ ብዙ ሀብቶቻችን ተደምረው የሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ፣ የዜግነትን ክብር የሚያልቁ ፣ አዳዲስ እድል እና ሀብት ይፈጥራሉ።
ስለዚህ በማንኛውም ነገር በጋራ እንቁም፤ ትብብራችንንም ይበልጥ እናጠናክር። ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት በመተማመን አብረን እንትጋ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
+9
በአራት ወር ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ከቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ የተቀየረዉ የመኖሪያ ስፍራ ምን ምን አካቷል?
👉 በ11 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች
👉 በአራት ወራት ዉስጥ የተገነቡ 960 ቤቶች
👉 ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች
👉 በውስጡ የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣
👉 የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥
👉 የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ
👉 ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች
👉 ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤
👉 እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ: በአስከፊ የእሳት አደጋ የተጎዳ አካባቢ ነበር
👉 “መርካቶ የበጎነት መንደር “ አካባቢዉን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸውን እንደ ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ ያሉ ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።
ቅጠል ተራን ወደ ንፁህ አረንጓዴ ለዜጎች ክብር የሚመጥን መኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገን
በቅጠል ተራ 960 ቤቶችን በአራት ወር ዉስጥ ገነብተን ከቦታው ላይ ለተነሱ ነዋሪዎች መልሰን አስተላልፈናል።
ቅጠል ተራ ለመኖር እጅግ ምቹ ያልነበረ፤ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፤ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ በመሆኑ የሰው ህይወትም በአስከፊ ሁኔታ በእሳት አደጋ ያጣንበት አካባቢ ነበር።
ዛሬ ግን እጅግ ያማሩ፥ ዘመናዊና ሁሉንም ነገር የተሟሉላቸው ባለ 9 ወለል የሆኑ ብዛታቸው 9 ህንጻዎችን 960 ቤቶች ተገንብተው ወደ ምቹ መኖሪያ አካባቢ ተቀይሯል።
"የመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር" በ11, 000 ካሬ ሜትር ላይ የተገነቡ G+8 የሆኑ ዘጠኝ (9 )ብሎኮች በአጠቃላይ 960 ቤቶች ያሉት ሲሆኑ፣ ሰፊ የስራ እድልን የሚፈጥሩ 371 የንግድ ሱቆች በውስጡም የህጻናት የመጫወቻ ስፍራ፣ የስፓርት ማዘውተሪያ( የኳስ ሜዳ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፥ የሰውነት ማጎልመሻ ቦታዎች) ፥ ለነዋሪዎች የመኪና ማቆምያ ፓርኪንግ፥ ለኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፥ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ፥ዘጠኙም ብሎኮች ላይ የጋራ መጠቀሚያ ሰገነት፥ ሊፍት፥ የፍሳሽና የኤሌክትሪክ መስመሮች በዘመናዊ መልክ ተሟልተው ተገንብተዋል።
ይህ በመርካቶ የበጎነት የመኖሪያ መንደር የሰው ህይወትን የሚቀይር ፥ መርካቶ አካባቢን “ተራ” በሚል ስያሜ የተሰጣቸው ( ቅጠል ተራ፣ ጭድ ተራ፣ ገብስ ተራ፣ ሳር ተራ፣ ቦንብ ተራ … ወዘተ) ጎስቋላ አካባቢዎችን ወደ ውብ አካባቢ የመለወጥ ጉልህ ማሳያ ነው ።
ቃል በተግባር ማለት ይህ ነው፥ እንደዚህ ዓይነት የተወሳሰበ ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ለሰው ልጆች የሚመጥኑ፥ ነዋሪዎች የክብር ኑሮ እንዲኖሩ፥ ህይወታቸውን የሚቀይሩ ተግባራትን ያለ እረፍት 24/7 በመፈፀም ነዋሪዎች አዲስ ህይወት እንዲጀምሩ ማድረግ ነው ።
የስራዎቻችንን ማዕከል ሁሉ ሰው ተኮር አድርገን፥ ከተማችን ውብ ፅዱ፥ ለነዋሪዎቻችን የተመቸች ከተማ እንድትሆን ያለ እረፍት የመስራት ተግባራችን ይበልጥ አጠናክረን
እንቀጥላለን።
ካላችሁ አካፍላችሁ ከከተማ አስተዳደራችን ጎን በመሆን የበጎ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ፥ ዛሬም በቅጠል ተራ የበጎነት መንደር እንድንቀይር ያገዛችሁን በተለይ ፕሮፌሰር ሰናይት ፍስሃ፥ በግንባታው የተሳተፋችሁ ሁሉ በነዋሪዎች ስም ከልብ እናመሰግናለን ።
ቅጠል ተራ ወደ “መርካቶ የበጎነት መንደር “ ተቀይፘል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡
እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡
መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡
እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡
ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡
መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡
በቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በየወሩ እየተዘጋጀ ለንባብ የሚበቃው ዜና መፅሔት የወርሀ ነሀሴ ዕትም እነሆ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
ለማህበር ቤት ተጠባባቂ ምዝገባ
https://forms.gle/iUFViVf7RyVU8jvv6
አርአያነት ያለው የማህበር ቤት ግንባታ እንቅስቃሴ በቃሊቲ ሳይት
በከተማችን አዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት ከተዘረጉ የቤት ልማት መርሃ ግብሮች መካከል የማህበራት ቤቶች ግንባታ አንዱ ሲሆን ፣ በአሁኑ ወቅት የግንባታ ሳይቶች ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛል።
በ70/30 መርሃ ግብር የተደራጁ 65 ማህበራት በ7 ሳይቶች ግንባታ እያካሄዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 50 የሚሆኑት ግንባታቸውን በነቃ ሁኔታ በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የማህበር ቤቶችና ህንጻዎች ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢ/ር ቢልሱማ ተመስገን ይገልጻሉ፡፡
ዳይሬክቶሯ እንዳስታወቁት፤ ቢሮው የመሬት አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የዲዛይንና የፋይናንስ ብድርን ከማመቻቸት በተጨማሪ ቀጣይነት ያለው ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
በቃሊቲ ወርቁ ሰፈር ሳይት ከሚገኙ 9 ማህበራት አንዱ የሆነው የ"እፎይታ" ማህበር ቤት ግንባታ አፈጻጸም ለሌሎች ማህበራት ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። ለዚህ ስኬት ዋናው ምስጢር የአማካሪው፣ የስራ ተቋራጩ እና የማህበሩ ተቀናጅቶና ተናቦ መስራት መሆኑን የጠቀሱት ኢ/ር ቢልሱማ፣ አፈጻጸሙ የማህበር ቤት መርሃ ግብር ፍሬ እያፈራ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
የፕሮጀክት ማናጀሩ ኢ/ር ብርሃኑ ጎሹ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ከተጀመረ 1 ዓመት የሞላው መሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት የስትራክቸራል ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው የብሎኬት እና የማጠናቀቂያ (finishing) ስራዎች በፈጣን ሁኔታ እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የግንባታውን ጥራትና ደህንነት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት አማካሪ መሐንዲሱ ኢ/ር ሰለሞን፣ ለግንባታው የሚገቡ ቁሳቁሶች በሙሉ ጥብቅ የላቦራቶሪ ፍተሻና ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው አረጋግጠዋል።
የማህበሩ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት በላቸው የአባላቱ የቤት ባለቤት የመሆን ጉጉት ከፍተኛ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ቁርጠኝነት በመኖሩም ግንባታው በዚህ ፍጥነት ወደ ፍጻሜ በመቃረቡ በማህበሩ አባላት ዘንድ ትልቅ ደስታ መፈጠሩን ገልጸዋል።
መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab
በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።
ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።
ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+9
የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ2019 ዓ.ም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን አከባበር በተመለከተ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ ስለበዓላቱ ምንነት፣ ትውፊት፣ ሀገራዊ ጠቀሜታ፣ አከባበር እና ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ጉዳዮች በሰፊው ተዳሷል፡፡
መድረኩ ላይ በዓላቱ አከባበር ወቅት ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችን በሞቅታና በኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት ባህል በመቀበል፣የአካባቢን ጽዳት መጠበቅና የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን በማጠናከር አስተዋጽኦ ማደረግ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የህዝቦችን ወንድማማችነት እና አንድነት የሚያጠናክሩ ታላላቅ ሀብቶች መሆናቸውን በመጠቆም፣ የበዓላቱ አከባበር በሰላም እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሰራተኞችና ህብረተሰቡ የድርሻቸውን መወጣት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab
+1
በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት።
🇪🇹 🇨🇳
Conversations with China’s President Xi Jinping on the sidelines of the BRICS Summit.
🇪🇹 🇨🇳
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
