es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Ir al canal en Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

El canal ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 13 971 suscriptores, ocupando la posición 1 696 en la categoría Transporte y el puesto 2 547 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 13 971 suscriptores.

Según los últimos datos del 25 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 146, y en las últimas 24 horas de 2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 35.85%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 17.39% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 5 008 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 430 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 25.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 26 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Transporte.

13 971
Suscriptores
+224 horas
+277 días
+14630 días
Archivo de publicaciones
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የድሬዳዋ የመንገዶች ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የተቋሙን 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በጋራ አከበሩ ድሬዳዋ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሰረተበት 75ኛ ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓል በድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ በመንገድ አውታር (ኔትወርክ) አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤቶች በጋራ አዘጋጅነት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ። በጋራ በተሰናዳው በዚህ ታሪካዊ የክብረ-በዓል መድረክ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲስትሪክቱ ሠራተኞች፣ የድሬዳዋ መንገድ አውታር አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ የድሬዳዋ፣ የጅግጅጋ እና የጎዴ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አጋር አካላት ታድመዋል። በዕለቱ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ መሐመድ፤ ድሬዳዋ የወጪና ገቢ ንግድ የሚከናወንበት ዋና መሥመር እንዲሁም የነጻ ገበያ ቀጠና መገኛ መሆኗን አስታወቁ። በመሆኑም ዲስትሪክቱ፣ የመንገድ አውታሩና የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ በጋራ በመሆን የአካባቢው የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላፍታም እንዳይቋረጥ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ ከእነዚህ የልማት መዋቅሮች ጋር ያለው አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጡት አቶ ሙስጠፋ፤ የአካባቢውን ሆነ የሀገሪቱን የልማት ውጥኖች ዕውን ለማድረግ ወደፊትም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋሉ፤ ለመላው የተቋሙ ሠራተኞችና መሐንዲሶችም ለሀገር ውለታቸው የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ሙሉቀን ዘርጋው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሲቋቋም ከነበረበት ውስን የመንገድ ሽፋን ተነስቶ ዛሬ ላይ ሰፊና ዘመናዊ የመንገድ አውታር መዘርጋት መቻሉን አብራሩ። በዚህ ሂደት ውስጥ የድሬዳዋ ዲስትሪክት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጀርባ አጥንት የሆኑትን እንደ አዋሽ-ድሬዳዋ እና አዋሽ-ሚሌ ያሉ የኢትዮ-ጂቡቲ የመንገድ ኮሪደሮች ሳይዘጉ በትጋትና በንቃት ዘብ እየጠበቀ እንደሚገኝ አስገነዘቡ። አያይዘውም በከፍተኛ የሀገር ሀብት የተገነቡ መንገዶችን በጥራት መጠበቅ፣ የመንገድ ደኅንነትን ማስከበር እና የሕዝብ ሀብትን በኃላፊነት በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ኢንጅነር ሙሉቀን መልዕክት አስተላልፈዋል። የድሬዳዋ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በአምስት ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሥር የሚገኙ ማኅበረሰቦችን የሚያስተሳስር ሰፊ የመንገድ አውታር ያስተዳድራል። ተቋሙ በደንገጎ፣ በሂርና፣ በአዋሽ እና በጅጅጋ/ቀብሪደሃር ሴክሽኖቹ አማካኝነት ድንገተኛ የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ሲከሰቱ በራስ-ኃይል ፈጣን ምላሽ በመስጠት የትራንስፖርት ፍሰቱ እንዳይስተጓጎል በቁርጠኝነት ይሠራል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የወላይታ ሶዶ መንገድ ዲስትሪክት፣ መንገድ ኔት ወርክና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ት ቤት የኢመአን የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከበሩ ወላይታ ሶዶ፣ ጥቅምት 11 ቀን 2019 (ኢመአ)፡የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሠረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል የወላይታ ሶዶ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት በጋራ በመሆን በድምቀት አክብረዋል። በበዓሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መንግሥቱ ትግሮ እንዲሁም የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ይልማ ሃይለማርያምን ጨምሮ ከተለያዩ ዞኖች የተጋበዙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የክብር እንግዶችና የዲስትሪክቱ የቀድሞ አንጋፋ ሠራተኞች በክብር ታድመዋል። መርሐ ግብሩ በሀገር ሽማግሌዎች የምርቃት ሥነ ሥርዓት በይፋ የተከፈተ ሲሆን፣ የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመሠረተ ልማት አማካሪ አቶ ይልማ ሱንታ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋሙ ባለፉት 75 ዓመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት ለሀገሪቱም ሆነ ለክልሎች ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለማኅበራዊ ግንኙነት መሳለጥ እንዲሁም ጠንካራ የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን ለመገንባት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል። የዲስትሪክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሐብታሙ ኃይሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ፣ ለቀድሞ አንጋፋ ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል። በንግግራቸውም ላለፉት 75 ዓመታት በሠራተኛው ጠንካራ የሥራ ትጋት ይህንን ታላቅ የበዓል ዕለት ለማክበር በፊታቸው መቆማቸውን ገልጸው፤ ዛሬ የተመዘገበው የልማት ምዕራፍና ስኬት ሙሉ በሙሉ የእነሱ ድምር ውጤት መሆኑን ተናግረዋል። በመቀጠልም የዲስትሪክቱ የመንገድ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሱራፈል ሚካኤል ባደረጉት ንግግር፤ ተቋሙ ሀገሪቱን በመንገድ መሠረተ ልማት ለማስተሳሰር ባከናወናቸው ታላላቅ ተግባራት ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አክለውም፣ የወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የአካባቢውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ከዋና ዋና ማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ ከጤና እና ከንግድ ማዕከላት ጋር የሚያገናኙ ወሳኝ የፌደራል መንገዶችን በባለቤትነት በመንከባከብ፣ የጥገናና የደረጃ ማሻሻያ ሥራዎችን በጥራት በማከናወን ረገድ ግንባር ቀደም አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዕለቱም የቀረበው ታሪካዊ የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ፤ በታላቅ ሀገራዊ ፍቅርና መስዋዕትነት መንገድ ለመክፈት ይከፈል የነበረውን ታላቅ ዋጋ ያሳየ ሲሆን፣ ለአዲሱ ትውልድ የአገልግሎት ጽናትንና ሙያዊ ሥነ ምግባርን የሚማርበት የትውልድ ቅብብሎሽ ድልድይ ሆኗል። በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይም ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ካገረገሉ አንጋፋ ሠራተኞች መካከል ለተመረጡት የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የቢሾፍቱ - ጨፌ ዶንሳ - ሰንዳፋ መንገድ ግንባታ ሥራ በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10/2019 (ኢ መ አ):- የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክረው የቢሾፍቱ - ጨፌ ዶንሳ - ሰንዳፋ መንገድ ግንባታ ዋና ዋና ሥራዎች በተያዘው ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው። በአጠቃላይ 53 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ የመንገድ ፕሮጀክት፥ ከቢሾፍቱ ወደ ሰንዳፋ ለመጓዝ በአዲስ አበባ በኩል ይደረግ የነበረውን የ83 ኪሎ ሜትር ርቀት በ30 ኪሎ ሜትር የሚያሳጥር ነው። ይህም የአካባቢውን ማኅበረሰብ የጉዞ እንግልትና ወጪ በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። ከዚህም ባለፈ አካባቢው ከፍተኛ የጤፍ፣ ስንዴ እና ሽንብራ ምርት የሚመረትበት በመኾኑ፥ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ቢሾፍቱና አዲስ አበባ ገበያዎች ለማውጣት ብሎም የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመሳብ ትልቅ ፋይዳ አለው። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከዚህ ቀደም ከሥራ ተቋራጩ የአቅም ውስንነት እና ከወሰን ማስከበር መዘግየት ጋር ተያይዞ በተያዘለት ጊዜ እንዳይጠናቀቅ እንቅፋት ገጥሞት የነበረ ቢኾንም፥ አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት ሥራው በሁለት ሎት ተከፍሎ በሁለት ተቋራጮች በመከናወን ላይ ይገኛል። ይህም በአፈጻጸሙ ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲታይ አድርጓል። በዚህም መሠረት የመጀመሪያው ሎት ከቢሾፍቱ ከተማ መነሻውን አድርጎ እስከ ጨፌ ዶንሳ መግቢያ ድረስ ያለው 24 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በሀገር-በቀሉ ራማ ኮንስትራክሽን በመከናወን ላይ ይገኛል። ሁለተኛው ሎት ደግሞ ቀሪውን የዋና መንገድ ክፍል እና በጨፌ ዶንሳ ከተማ ውስጥ የሚሠራውን 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውስጥ አገናኝ መንገድ ጨምሮ በአጠቃላይ 28 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው። ግንባታውን የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በማከናወን ላይ ይገኛል። አሁን ላይ ከአጠቃላይ የመንገዱ ክፍል ውስጥ 30 ኪሎ ሜትር ያህሉን አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ተጠናቅቋል። በቀሪው የመንገድ ክፍል የአፈር ቁፋሮ እና ሙሌት እንዲሁም የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ ግብዓት የማምረት ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው። የመንገድ ግንባታው ከፌደራል መንግሥት በተመደበ አጠቃላይ 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወጪ ነው በመከናወን ላይ የሚገኘው። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ - ጀማ ወንዝ የሲሚንቶ ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሥራ በይፋ ተጀመረ። አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 06 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢመአ)፦ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የሚገኘው    የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ - ጀማ ወንዝ  የሲሚንቶ ኮንክሪት  መንገድ የግንባታ ፕሮጀክት ሥራ በይፋ ተጀመረ። የሰሜን ሸዋ ዞን እና የእንሳሮ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደብረ ብርሃን አካባቢ ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተወካዮች በተገኙበት የግንባታ ሥራው በይፋ ተጀምሯል። ይህ 20 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚሸፍነው የመንገድ ፕሮጀክት ሥራ የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ሕብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ ተቋራጭ የሚያከናውነው ሲሆን፤ የጥራት ቁጥጥርና የማማከር ሥራውን ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን በአማካሪ መሐንዲስነት በኃላፊነት ይከታተለዋል። ፕሮጀክቱ  በኮንትራት ውሉ መሰረት በ14 ወራት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።   ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ  የለሚ-አለምከተማ -ደጎሎ የመንገድ ፕሮጀክት አካል እንደመሆኑ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር አይነተኛ ጠቀሜታ አለው። ከዚህም ባለፈ  ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋነኛ ጥሬ ዕቃ የሆኑትን የኖራ ድንጋይ እና ጂፕሰም በከፍተኛ ፍጥነትና ቅልጥፍና ለማጓጓዝ ያስችላል።    በተጨማሪም በለሚ ከተማ ዙሪያና በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነቡ ፋብሪካዎች የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ለማቅረብ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል። የመንገዱ የጎን ስፋት በቀበሌ መቀመጫዎች 12 ሜትር እንዲሆን የተደረገ ሲሆን፣ በገጠር አካባቢዎች ደግሞ ከ8 እስከ 10 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ይገነባል። የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ  በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳና የበጀት ገደብ ውስጥ በጥራት ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ፣ የሚመለከታቸው የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የመንግሥት መዋቅሮች እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ ለግንባታ ሥራው አስፈላጊውን  ድጋፍና ትብብር እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያሳስባል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኢመአ አልማዝ ኢዮቤልዩ እና የሻሸመኔ ዲስትሪክት የተመሰረተበት 74ኛ በዓል ተከበረ ሻሸመኔ፣ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢመአ)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ እና የሻሸመኔ ዲስትሪክት የተመሠረተበት 74ኛ ዓመት በድምቀት ተከብሯል። በመርሓ ግብሩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሻሸመኔ ከተማ መስተዳድር ተወካይ፣ የግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጆች፣ የሻሸመኔ ዲስትሪክት እና የመንገድ አውታር ኃላፊዎች እንዲሁም ሠራተኞች ተገኝተዋል። የሥራ ኃላፊዎቹ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሁለቱን ታሪካዊ የምስረታ በዓላት በጋራ ማክበሩ ባለፉት ዘመናት የተመዘገቡ ስኬቶችን ከመዘከር ባለፈ፣ በቀጣይ የሕብረተሰቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ቃል የሚገባበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የሻሸመኔ ዲስትሪክት ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከገበያ፣ ከጤና እና ከማኅበራዊ ተቋማት ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን ሲገነባ፣ ሲጠግንና ሲንከባከብ መቆየቱን ገልጸዋል። “መንገዳችን ኃላፊነታችን” በሚለው መርህ መሠረትም በቀጣይ የጀመሯቸውን ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት ለማዋል ቁርጠኛ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ ላለፉት 75 ዓመታት የተጓዘበትን እና ያከናወናቸውን ሥራዎች የሚያሳዩ ታሪካዊ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ለበዓሉ ተሳታፊዎች ቀርቧል። በክብረ በዓሉ ማጠቃለያ ላይ ተቋሙን በቅንነትና በውጤታማነት ላገለገሉ ሠራተኞች የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቷል። የሻሸመኔ ዲስትሪክት የደቡብ የምስራቅና የሀገሪቱን መካከለኛ ክፍሎች የሚያስተሳስሩ ቁልፍ የፌደራል መንገዶችን ከመገንባት ባለፈ፤ ዘመናዊ የጥገና እና የደረጃ ማሻሻያ ሥራዎችን በዋናነት ሲያከናውን ቆይቷል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የአዘዞ - ጎንደር መንገድ ግንባታ ማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ጎንደር፣ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም. (ኢመአ)፦ ከመዲናችን አዲስ አበባ 640 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የጎንደር ከተማ፣ የ12.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የአዘዞ - ጎንደር መንገድ ግንባታ ማጠናቀቂያ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ። የነባሩ መንገድ የጎን ስፋት ጠባብና ለትራፊክ ምቹ ባለመሆኑ፣ በመንገዱ ተጠቃሚዎች ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በመስመሩ ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረት፣ መንገዱ ደረጃውን በጠበቀ የአስፋልት ኮንክሪት ሲገነባ ቆይቶ አሁን ላይ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይደርሳል። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ 1.8 ቢሊዮን ብር ወጪ በጎንደር የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ ሥራው 92 በመቶ ተጠናቋል። የመንገዱ የማማከርና የቁጥጥር ሥራም «ዳቤክ ኢንጂነሪንግ» በተባለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር (ኃ/የተ/የግ/ማ) በመከናወን ላይ ነው። የአዘዞ - ጎንደር መንገድ በዋናነት የጎንደር - መተማ መስመር መግቢያና መውጫ እንደመሆኑ መጠን፣ የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ተለያዩ መንደሮች የሚያስገቡ የመገንጠያ መንገዶች የአስፋልት ሥራ፣ የዋናው መንገድ የ4 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ፣ የቀለም ቅብና የትራፊክ ምልክት ተከላ የመሳሰሉ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ብቻ ይቀሩታል። መንገዱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ፣ በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ማዕከላት ለማድረስና የቱሪዝም መዳረሻዎችን ይበልጥ ለማነቃቃት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን በዋና ዳይሬክተርነት ተረከቡ፤ ለማኔጅመንቱ የሥራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጡ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢመአ)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ኢመአ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ፣ ከቀድሞው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን ጋር ይፋዊ የሥራ ርክክብ ፈጽመዋል። በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቀድሞው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋሙ ከመንግሥት የተሰጠውን ከፍተኛ ኃላፊነት በብቃት ከመወጣት አኳያ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም የተቀመጡ ዕቅዶችን በሚጠበቀው ደረጃ ከማስፈጸም አኳያ የተቋሙ አዲሱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ ከማኔጅመንቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ሙሉ እምነታቸውን ገልጸው፣ ለመላው የተቋሙ የሥራ ባልደረቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የሥራ ርክክቡ ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አዲሱ ዋና ዳይሬክተር በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተቋሙ አማካሪዎች፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና ከፍተኛ ዳይሬክተሮች ጋር የትውውቅና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ማስቀመጫ መድረክ አካሂደዋል። በመቀጠልም የኢመአን አጠቃላይ መዋቅር፣ የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ፣ በሂደት ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እንዲሁም አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴን የሚያሳይ ስትራቴጂካዊ ተቋማዊ መረጃ (Organizational Overview) ለአዲሱ ዋና ዳይሬክተሩ ቀርቧል። በተለይም በየምክትል ዋና ዳይሬክተሮቹ ሥር የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች ስላሉበት ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም፣ የሥራ ፍሰትና አጠቃላይ የአሠራር ሁኔታ ዝርዝር ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ የቀረበውን ተቋማዊ መረጃ ካደመጡ በኋላ ለማኔጅመንት አባላቱ የሥራ መመሪያና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ባስተላለፉት መመሪያ፤ ይህንን አንጋፋ ተቋም ይበልጥ በማዘመን አዳዲስ መንገዶችን በመገንባት፣ ነባሮቹን በማጠናከርና በመጠገን ረገድ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አሳስበዋል። አያይዘውም የፕሮጀክቶችን ጥራት ማረጋገጥ፣ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና በጀት እንዲጠናቀቁ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፣ እንዲሁም የውስጥ አሠራር ቅንጅትን ማጠናከር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል። የተቋሙን ስኬታማ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠልም መላው የማኔጅመንት አባላትና የሥራ ኃላፊዎች በቁርጠኝነትና በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (BSc) ያገኙ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ተቋም በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን (MSc) አግኝተዋል። ወደዚህ ኃላፊነት ከመምጣታቸው አስቀድሞም የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በብቃት መምራታቸው ይታወሳል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 01/2019 (ኢ መ አ):- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ኢንጅነር
ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 01/2019 (ኢ መ አ):- ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾመዋል። ኢንጅነር ሽመልስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን (BSc) ያገኙ ሲኾን፣ በተመሳሳይ ተቋም በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅመንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል። የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኾነው ከመሾማቸው አስቀድሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት መርተዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሥራ አስኪያጅ እና በኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኮርፖሬሽን በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በቅንነትና በብቃት አገልግለዋል። ኢንጅነር ሽመልስ እሸቱ የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያሎት እያልን በተቋማችን የላቀ ስኬትና ውጤት እንዲያስመዘግቡ መላው የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ከጎንዎ መሆናችንን እንገልፃለን።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በደብረ ማርቆስ የመንገድ ዘርፍ ተቋማት በጋራ ተከበረ ደብረ ማርቆስ (ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ኢመአ) የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል ከሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እያከበረ የሚገኝ ሲሆን፣ የደብረማርቆስ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ እና የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት በጋራ በመሆን በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል። በጋራ በተዘጋጀው የዚህ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የልማት አጋሮች እና የሥራ ተቋራጮች ተገኝተዋል። በተጨማሪም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ በዲስትሪክቱ ሥር ያሉ የደጀን፣ የቡሬ፣ የቻግኒ እና የባሕር ዳር ሴክሽኖች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የሦስቱም ተቋማት የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በጋራ በዓሉን አክብረዋል። የደብረ ማርቆስ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ቶማስ ወርቁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዕለቱን መርሃ ግብር አስጀምረዋል። ሥራ አስኪያጁ በንግግራቸው ወቅት ኢመአ ባለፉት 75 ዓመታት በርካታ የመንገድ ሥራዎችን በማከናወን አገርን ከአገር፣ ክልልን ከክልል ያስተሳሰረ መሆኑን ገልጸው፤ ይህንን የልማት ሥራውን በጋራና በትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። በዝግጅቱ ልዩ የፎቶ አውደ ርዕይ በጋራ በማዘጋጀት ለእይታ አቅርበዋል። በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ከታሪክ ማስታወሻነት ባለፈ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሚገነባቸው መንገዶች፣ ድልድዮች፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎች እንዲሁም ከአመሠራረቱ ጀምሮ በደብረ ማርቆስ የመንገድ ዘርፍ ተቋማት ያሉ የመንገድ ሀብቶችና የሥራ እንቅስቃሴዎች ለተመልካች ቀርበዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ኢንጅነር መሐመድ አብዱራሕማን የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ መስከረም 28 ቀን 2019 (ኢ መ አ):- የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደርን ላለፉት 4 ዓመታት በዋና ዳይ
ኢንጅነር መሐመድ አብዱራሕማን የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚንስትር ሆነው ተሾሙ አዲስ አበባ፣ መስከረም 28 ቀን 2019 (ኢ መ አ):- የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደርን ላለፉት 4 ዓመታት በዋና ዳይሬክተርነት የመሩት ኢንጅነር መሐመድ አብዱራሕማን ከመስከረም 28፣ 2019 ጀምሮ በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የከተማ እና መሰረተ-ልማት ሚንስትር ሆነው ተሹመዋል። ኢንጅነር መሐመድ አብዱራሕማን ተቋማችንን ከጀማሪ ባለሙያነት አንስተው በተለያዩ የኃላፊነት እርከኖች እና በመጨረሻም በዋና ዳይሬክተርነት በመሩበት የረጅም ዓመታት አገልግሎታቸው፣ በሀገራችን የመንገድ መሠረተ-ልማት ታሪክ የራሳቸው ጉልህ አሻራ አኑረዋል። በተለይም የእሳቸው አመራር የመንገድ ዘርፉን በማስፋፋት፣ ዘመናዊ የፕሮጀክት አመራር ሥርዓትን በመዘርጋት እንዲሁም የኮንስትራክሽን ዘርፍ ተዋንያኖች አቅም በማጎልበት እና በማዘመን ረገድ የነበራቸው ሚና እጅግ የላቀ ነው። ሙያውን ከታችኛው መዋቅር ጀምረው በጥልቀት ማወቃቸው፣ ተቋማችን ፈታኝ የሆኑ ታላላቅ ብሔራዊ ፕሮጀክቶችን በስኬት እንዲወጣ አስችሎታል። ተቋማችን ለኢንጅነር መሐመድ አብዱራሕማን "እንኳን ደስ አልዎት" እያለ፣ አዲሱን ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት በላቀ ስኬት እንዲወጡ ከልብ ይመኛል!