ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 831 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 692,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 487 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 831 名订阅者。

根据 05 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 25,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 40.81%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.12% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 645 次浏览,首日通常累积 2 230 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 12。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።”

凭借高频更新(最新数据采集于 06 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 831
订阅者
+224 小时
+67 天
+2530 天
帖子存档
የጅማ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ ጽ/ቤት እና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የኢመአን 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከበሩ ጅማ፣ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም(ኢመአ): የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ኢመአ) የ75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የሚገኙ የጅማ የመንገድ ጥገና ዲስትሪክት፣ የመንገድ ኔትወርክ (አውታር) አስተዳደር እና የአካባቢው የመንገድ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት በጋራ በመሆን በተለያዩ ደማቅ መርሃ ግብሮች አክብረዋል። ይህ ክብረ በዓል በጅማ አካባቢ የሚገኙ የተቋሙን መዋቅሮች ትስስር ያሳየ ሲሆን፣ በዕለቱ የባለድርሻ አካላት ተወካዮች፣ የሦስቱም መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች እንዲሁም ተቋሙን ለረጅም ዓመታት በታማኝነት ያገለገሉ አንጋፋ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መሠረት ደጀኔ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ይህ የ75ኛ ዓመት በዓል የጋራ ስኬቶችን የምንዘክርበት ብቻ ሳይሆን የነገውን ጉዞ በበለጠ አቅምና አንድነት የምናቅድበት ልዩ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንገድ ጥገናና ግንባታን ማጠናከር፣ የመንገዶችን ጥራትና ዘላቂነት ማሳደግ እንዲሁም የሠራተኞችን ደህንነትና አቅም መገንባት የሁሉም ዘርፎች የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ ተናግረዋል። ኢንጂነር መሠረት አክለውም፣ “የጀመርነውን የልማት ጉዞ ይበልጥ በማፋጠን ሀገራችን በመንገድ አውታር የተገናኘችና የበለፀገች እንድትሆን ሁላችንም በጋራ መትጋት ይኖርብናል” ብለዋል። የጅማ የመንገድ አውታር (ኔትወርክ) አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ኢንጂነር ቦጋለ ሽፈራው በበኩላቸው፣ ይህ በዓል በጋራ የተያዙ ትልልቅ ዕቅዶችን ለማሳካት የሚደረጉ ጥረቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል ትልቅ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ የነደፋቸውን የመንገድ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በአግባቡ በመተግበር፣ ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ አሠራሮችን በማጠናከር የመንገድ ጥገናን በጥራትና በተደራሽነት ደረጃ ለማስፋፋት የጋራ ርብርብ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ለዚህም ስኬት ሌት ተቀን ለደከሙ የዲስትሪክቱ አመራሮች፣ መሐንዲሶች፣ ቴክኒሻኖች፣ የማሽን ኦፕሬተሮችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችም ምስጋና አቅርበዋል። በዕለቱ ተቋሙ ባለፉት ዓመታት በመንገድ ጥገና፣ በኔትወርክና በፕሮጀክት ማኔጅመንት ዘርፍ ያከናወናቸው አበይት ሥራዎችና ያለፉባቸው የሥራ ሂደቶች የተዳሰሱ ሲሆን፣ ካለፈው ተሞክሮ በመነሳትም በቀጣይ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተሻለ አቅምና ጥራት ለመወጣት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል አከበረ ኮምቦልቻ፣ መስከረም 21 ቀን 2019 (ኢመአ): የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተመሰረተበትን 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል ከሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዋና መስሪያ ቤት፣ በማሰልጠኛ ተቋማት እና በመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶች እያከበረ ይገኛል። የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክትም ይህንን የምስረታ በዓል የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ፣ የወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የአካባቢው የፀጥታ አካላት፣ የዲስትሪክቱ እና የሴክሽን የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አክብሯል። በወቅቱ የዲስትሪክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደሳለኝ ሰይፉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የዕለቱን መርሃ ግብር ያስጀመሩ ሲሆን፣ አስተዳደሩ ባለፉት 75 ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። ስራ አስኪያጁ አክለውም ዲስትሪክቱ ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ከሁሉም የመንገድ ጥገና ዲስትሪክቶች ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ሲያስመዘግብ የቆየ መሆኑን በመግለፅ፣ ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አበርክቶ ላደረጉ የዲስትሪክቱ የስራ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙ ባለድርሻ አካላት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም ለዲስትሪክቱ የስራ አፈፃፀም ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የስራ ቡድኖችና ባለድርሻ አካላት የእውቅና ሽልማት ከተሰጠ በኋላ የዕለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

መልካም በዓል!!!!
መልካም በዓል!!!!

የትኖራ ወጀል መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ ደብረ ማርቆስ፤ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የየትኖራ ወጀል የአስፋልት መንገድ መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ሰሜን ሸዋን ከምስራቅ ጎጃም (ከደጀን ወረዳ እስከ ጎዛምን ወረዳ) እንዲሁም የየትኖራ ታዳጊ ከተማን ከወጀል ታዳጊ ከተማ የሚያገናኘው ይህ መንገድ የ2 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ቀድሞ የነበረው የመንገዱ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪና ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋዎችን ያስተናግድ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግንባታው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። የመንገዱ ስፋት በገጠር፣ በቀበሌ እንዲሁም በወረዳ 7.3 ሜትር ሆኖ ተገንብቷል። ይህ ፕሮጀክት መጠናቀቁ በአካባቢው የሚመረቱ የግብርና ምርቶችን በቀላሉ ለማጓጓዝ የሚያስችል ሲሆን፣ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚሆኑ የግብዓት አቅርቦቶች እንዲሳለጡ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል። በተጨማሪም የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማነቃቃት አዲስ ተስፋ ይዞ መጥቷል። በግንባታው ሂደት ላይ እንደ ጸጥታ፣ የወሰን ማስከበር (በተለይም ለተለዋጭ መንገድ መሬት መልቀቅ)፣ የአስፋልት ኮንክሪት የሚጓጓዝበት ርቀት፣ የሲሚንቶ፣ የብረት እንዲሁም የነዳጅ እጥረት የመሳሰሉ ተግዳሮቶች አጋጥመው በሥራው ፍጥነት ላይ ጫና ፈጥረው የነበረ ቢሆንም፣ እነዚህን ችግሮች በቁርጠኝነት በመቅረፍ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆን ተችሏል። ለፕሮጀክቱ ከአንድ መቶ አርባ ሚሊዮን (140,000,000) ብር በላይ በጀት የተመደበለት ሲሆን፣ የስራ ተቋራጭነቱን የደብረ ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በኃላፊነት ሲወጣ፣ የደብረ ማርቆስ መንገድ አውታር ቅ/ፅ/ቤት ደግሞ የአማካሪነት ሚናውን በሚገባ ተወጥቷል። የጠረጋ፣ የአፈር ቆረጣና ሙላት፣ የሰብ ቤዝ፣ የቤዝ ኮርስ ንጣፍ እንዲሁም ሙሉ የ2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል:: በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

መልካም አዲስ ዓመት! ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት መንገዳችን፣ ኃላፊነታችን
መልካም አዲስ ዓመት! ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት መንገዳችን፣ ኃላፊነታችን

የዶዶላ - ሰብስቤ ዋሻ - ባሌ ሮቤ - ጎባ መንገድ ጥገና በተጠናከረ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2/2018 (ኢ መ አ):- ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት የሚያስተናግደው የዶዶላ - ሰብስቤ ዋሻ - ባሌ ሮቤ - ጎባ መንገድ ጥገና ፕሮጀክት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል። ይህ የመንገድ ኮሪደር የባሌ ዞን ከተሞችን የምጣኔ-ሀብትና ማኅበራዊ ትስስር ከማጠናከሩም በላይ፣ ከፍተኛ የግብርና ምርት የሚንቀሳቀስበትና ወደ ባሌ ብሔራዊ ፓርክ የሚወስድ ዋና መስመር ነው። ይሁንና በኮሪደሩ ላይ በሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ምክንያት የሚፈጠረው ከፍተኛ የትራፊክ ጫና፣ የአፈሩ ተለዋዋጭ ባሕሪና የከርሰ-ምድር ውኃ መፍለቅ መንገዱን በመጉዳቱ ለአሽከርካሪዎችና ለአካባቢው ማኅበረሰብ የትራንስፖርት ፈተና ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት መንገድ አውታር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በራስ-አቅም የጥገና ሥራውን እያከናወነ ይገኛል። የጥራት ቁጥጥርና የማማከር ሥራውን ደግሞ ኢንስራድ ሲቪል ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ ከሂትኮን ኢንጂነሪንግ ጋር በጋራ እያከናወኑት ነው። በአሁኑ ወቅት ከ5 ኪሎ ሜትር በላይ የአስፋልት መደረብ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፤ የአፈር ቆረጣ፣ የድንጋይና አፈር ሙሌት፣ የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ፣ የውኃ ማፋሰሻ ጥገና፣ የስትራክቸር፣ የመንገድ ዳር ምልክቶችና የደኅንነት ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከፌደራል መንግሥት በተመደበ 225 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ የሚገኘውን ይህንን ፕሮጀክት በቀጣዩ በጀት ዓመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ የታቀደ ሲሆን፣ ለዚህም የሚያስፈልጉ የግብዓትና የሰው ኃይል ዝግጅቶች ተጠናቀዋል። የመንገዱ መጠገን ቀደም ሲል ይስተዋል የነበረውን እንግልት በመቅረፍ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰፍን ያደርጋል። ከዚህም ባለፈ በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን እንደ ስንዴ፣ ገብስ እና ጤፍ ያሉ የሰብል ምርቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ ለማቅረብ እንዲሁም የባሌ ብሔራዊ ፓርክን የቱሪስት ፍሰት ይበልጥ ለማነቃቃት ጉልህ ሚና ይኖረዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የመንገድ ፈንድ በ2018 በጀት ዓመት 28 ቢሊዮን ብር ሰበሰበ፤ በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቀደ ቢሾፍቱ፣ ነሐሴ 29/2018 ዓም(ኢመአ): የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከመንገድ ፈንድ የጥገና በጀት ድጋፍ ከሚደረግላቸው የሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የመንገድ ኤጀንሲ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሲያካሂድ የቆየውን የምክክር ውይይት አጠናቀቀ። በውይይት መድረኩ የመንገድ ፈንድ የ2018 በጀት ዓመት ገቢ አፈጻጸም 28 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተገለጿል፤ በ2019 በጀት ዓመት ደግሞ ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዷል። የፈንዱ ገቢ ምንጮች በነዳጅ ላይ ከሚጣል ታሪፍ፣ ከቅባትና ዘይት ታሪፎች፣ የሀገሪቱን ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች ክፍያ፣ ከአመታዊ ክብደትን መሰረት ካደረገ ዓመታዊ የፈቃድ ማደሻ እንዲሁም ከክብደት ወሰን በላይ ጭነት ቅጣቶች የሚገኘውን ገቢ ናቸው። በመንገድ ፈንድ የሚደገፉ 72 ኤጀንሲዎች ከአመታዊ ዕቅድ ዝግጅት እስከ ክፍያ አፈጻጸም ድረስ ባሉት ሂደቶች ላይ በቴክኒክ፣ በኦዲትና በአማካሪዎች አማካኝነት የቅርብ ክትትል  ይደረግባቸዋል። በተጨማሪም ኤጀንሲዎቹ በአማካሪዎቹ ስራው በትክክል መሰራቱን አረጋግጠው  በሚልኳቸው የምስክር ወረቀቶች (ሰርተፍኬቶች) ላይ ተመስርቶ ክፊያ ይፈጸማል፣ ቁጥጥርም ይደረጋል። የመንገድ ኤጀንሲዎቹ አጠቃላይ አፈጻጸም ከዕቅድ በላይ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት እያጋጠሙ ያሉ  የበጀት ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም፣ የግብዓት ዋጋ መጨመር፣ አንዳንድ አካባቢ የሚስተዋለው የጸጥታ  ሁኔታና መሰል ችግሮች በሥራዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳደረዋል። በተላይ የጥገና በጀት ማነስ፣ የነባር ግንባታ ማሽነሪዎች ዕድሳት መዘግየት እና የአዳዲስ ማሽነሪዎች ግዢ አለመፈጸም አፋጠኝ መፍትሄ የሚፈልጉ መሆናቸው ተጠቁሟል። ችግሮቹን በዘላቂነት ለመፍታትም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው ተመላክቷል። በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል መንግሥቴ ባስተላለፉት መልእክት፤ ከመንገድ ፈንድ የሚመደበውን በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋልና አስፈላጊውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። አያይዘውም የፋይናንስና የሥራ አፈጻጸም ሰነዶች የሚረጋገጡበት ጠንካራ ሥርዓት መዘርጋትና ተፈጻሚ ማድረግ፣ እንዲሁም ለሕብረተሰቡ የተሳለጠ የመንገድ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከክልልና የከተማ መስተዳድር ኤጀንሲዎች ጋር ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው ቢሾፍቱ ፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኢመአ)— የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በመንገድ ፈንድ የጥገና በጀት ድጋፍ ከሚደረግላቸው የሁሉም ክልሎች እና የዋና ከተማ መስተዳድሮች የመንገድ ኤጀንሲዎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚያካሂደው ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሀመድ አብዱራህማን እንደገለጹት፤ የመድረኩ ዋና ዓላማ የሥራ አፈጻጸሞችን በበጎ ጎን ማየት ብቻ ሳይሆን በሥራ ሂደት ውስጥ ያጋጠሙ የአሠራር ክፍተቶችን በግልጽ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው። በመድረኩ ያለፈው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በዝርዝር የሚገመገም ሲሆን፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ይደረግበታል። ዋና ዳይሬክተሩ የመንገድ ግንባታና ልማት በአገሪቱ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው የመሠረተ ልማት ዘርፎች ቀዳሚው እና የልማት ጉዞውን ለማፋጠን የሚያገለግል ቁልፍ ምሰሶ መሆኑን ገልጸዋል። በመንግሥት ልዩ ትኩረት ምክንያት ዛሬ ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድ መዋቅሮች በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋታቸውንና አሁንም በስፋት እየተገነቡ መሆናቸውን አብራርተዋል። መንገድ የተራራቁ ሕዝቦችን በማገናኘት፣ ለአርሶ አደሮች ምርት ገበያ፣ ለትምህርትና ለጤና ተደራሽነት፣ ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለቱሪዝም ዕድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም አክለዋል። ይሁን እንጂ የተገነቡ መንገዶች በዲዛይናቸው መሠረት የረጅም ዘመን አገልግሎት እንዲሰጡ ወቅታዊ ጥገና ሊደረግላቸው እንደሚገባ ኢንጂነር መሀመድ አሳስበዋል። መሠረተ ልማቱ ለብልሽት ከተጋለጠ ለተሽከርካሪ መለዋወጫ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማናር በሀገር ሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና ስለሚፈጥር፣ ቀጣይነት ያለው የጥገና ሥራና ቋሚ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህን የፋይናንስ ፍላጎት በዘላቂነት ለመመለስ መንገድ ፈንድ ከ28 ዓመታት በፊት ራሱን ችሎ መቋቋሙን ያስታወሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ተቋሙ ከነዳጅ፣ ከቅባትና ዘይት ታሪፎች፣ የሀገሪቱን ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ተሽከርካሪዎች ክፍያ፣ ከፈቃድ ማደሻና ከክብደት ወሰን በላይ ጭነት ቅጣት ገቢዎችን በመሰብሰብ ዓላማውን በስኬት እያሳካ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ መንገድ ፈንድ በአዋጅ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሥር መደራጀቱ ደግሞ ለሥራ ቅልጥፍና ትልቅ ዕድል መፍጠሩ ተብራርቷል። በ2019 በጀት ዓመት ከመንገድ ፈንድ የገቢ ምንጮች የሚሰበሰበውን ገቢ በመገመት ለፌደራል፣ ለክልል እና ለከተማ መንገድ ኤጀንሲዎች ለመደበኛና ለወቅታዊ ጥገና፣ ለከባድ (መልሶ) ጥገና፣ ለመንገድ ደኅንነት እንዲሁም የኤጀንሲዎችን አቅም ለመገንባት የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች ግዢ የሚውል በጀት መደልደሉም በዚሁ መድረክ ተገልጿል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads