es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 949 suscriptores, ocupando la posición 5 320 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 235 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 949 suscriptores.

Según los últimos datos del 19 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 398, y en las últimas 24 horas de -2, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 24.35%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.55% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 882 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 682 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 25.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 20 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 949
Suscriptores
-224 horas
+1577 días
+39830 días
Archivo de publicaciones
#መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱንና ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18 በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡- ፨ #በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡ ፨ #ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡ ፨ #መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ #መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ #38_ዓመታት_መጽናት_እንጂ ስሙ አይደለም፡፡ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡ ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡ አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡ በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡ #ቅዱስ_ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (#የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ #የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ #ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡ በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡ † በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9 † የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13 † ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ † ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡ † የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡ † ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

የሰንበት ት/ት ቤታችን የ2 ዓመታት ጥያቄ ዛሬም #_በብጹዕ_አቡነ_መልከጸዴቅ_የአዲስ_አበባና_የጉራጌ_አህጉረ_ስብከት_ሊቀ_ጳጳስ የሰ/ት/ቤቱ ጥያቄ #_የመጨረሻ_ውሳኔ_አገኘ #_ውሳኔው የመጣው በ10/07/2013 ዓ.ም ቢሆንም አፈጻጸሙን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በሽምግልና እንዲያልቅ ስንጥር እስከዛሬ ድረስ ውሳኔውን ሳናሳውቃችሁ ቆይተናል ****************************** በ29/06/2013 ዓ.ም ሰ/ት/ቤቱ ፣የአጥቢያው ምዕመናን ፣ የአጥቢያ ሰንበት ት/ት ቤቶች ፣ የአካባቢው ወጣቶች በጋራ በመሆን ወደ ሐገረ ስብከት በመሄድ ጥያቄያችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ብጹዕነታቸውም በቃል ማብራሪያ የቀረቡትን ሃሳቦች በተገቢው መንገድ ከተመለከቱና ከሰሙ በኋላ የማያዳግም ውሳኔ ለመስጠት በአካልም ሄጄ ማየት አለብኝ ብለው ደብራችን ላይ በመገኘት የደብሩ አስተዳደርና ማኅበረ ካህናት የሚሉትን አማራጮች እንዲሁም በሰንበት ት/ት ቤታችን በኩል የቀረቡ አማራጮችንም በአካል ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ በ10/07/13 ዓ.ም በደብዳቤ #ቁጥር 3008/13/2013 ለደብራችን በተጻፈ ደብዳቤ ሰንበት ት/ት ቤቱ #_በመደበኛነት_የመዋዕለ_ሕጻናቱ_ግቢ_እንዲሰጠው ፣ በመዋዕለ ሕጻናት ውስጥ በመማር ላይ የሚገኙት ሕጻናት እንዳይበተኑ ደብሩ ቦታ አፈላልጎ የመማርያ ቦታ እንዲያመቻችላቸው ተወስኗል፡፡ #_ብጹዕ_አባታችን የብጹዕነትዎ ቡራኬ ይደርብንና በየካቲት 29/2013 ዓ.ም ፡- ከ 2ዓመታት በላይ በሰ/ት/ቤቱና በደብሩ አስተዳደር መካከል የቆየውን አለመግባባት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አመራር ና ውሳኔ እንዲሰጡን ለመጠየቅ ወደ ሃገረ ስብከትዎ ስንመጣ ምንም እንኳ ለአቤቱታችን እንግዳ ቢሆኑም የሚመሩት ሃገረ ስብከት የቤተክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ባሳየ መልኩ ከሁለታችንም ወገን ችግሩን በዝርዝር ከመስማት ባለፈ ሳይውሉ ሳያድሩ ደብራችን ድረስ ተገኝተው ሁሉንም በአይንዎ ተመልክተው ቆራጥ አመራር እና ፈጣን ውሳኔ ስለሰጡን ለእርስዎ ለብጹዕ አባታችን ያለን ክብርና አድናቆት ታላቅ ነው፡፡ በሁሉም የቤተክርስቲያናችን ችግሮች ይህ አይነት ቆራጥ አመራርና ውሳኔ ያስፈልጋልና ከዚሁ አንጻር የወሰዱትን እርምጃ የሃገረ ስብከቱን ገጽታ በእጅጉ ከፍ አድርጎ ያሳየ ነውና #_ምስጋናችን_ይድረሶት፡፡ እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜና ሰፊ ጤና ይስጥልን፡፡ የሃገረ ስብከታችን ዋና ስራ አስኪያጅ #_መምህር_አካለወልድ_ተሰማ እንዲሁም ዋና ጸሐፊ #_መ/ር_ታዲዮስ እና የሃገረ ስብከቱ የሰንበት ት/ት ቤቶች ማደራጅያ ዋና ክፍል ሃላፊ #_መ/ር_ዳዊት ወደ ሀገረ ስብከቱ በአመራርነት ከመጣችሁበት ጊዜ ጀምሮ በእኛና በደብሩ መካከል ይቀርቡ የነበሩትን ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ሳትሰለቹ በመስማት ውሳኔ ሰጥታችኋል፡፡ በተጨማሪም ያሉትን ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ትልቁን ድርሻ ተወጥታችኋልና ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡ #_የአ.አ_ሰ/ት/ቤቶች_አንድነት_የስራ_አመራር_አባላት ምንም እንኳ ኃፊነታችሁ ቢሆንም ከእኛም በላይ ጉዳዩን የራሳችሁ አድርጋችሁ ሙሉ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ይህ ውሳኔ እንዲገኝ ያበረከታችሁት አስተዋጽኦ ለታሪክ የሚቀመጥ ነውና #_እናመሰግናችኋለን፡፡ በደብራችን የጠፋው ሰላም እንዲመለስ ተቆርቁራችሁ ልትሸመግሉን የመጣችሁ አባቶችና ወንድሞች ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ በሽማግሌነት ያኑራችሁ፡፡የአጥቢያችን ወጣቶችና ምዕመናን እንዲሁም በቅርብ የምትገኙ ሰንበት ት/ት ቤቶች በተለይ ( ወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ #ፍቁረ_እግዚእ ሰ/ት/ቤት ፣ #ገነተ_ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰ/ት/ቤት ፣ #ምስካየ_ኅዙናን ተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት ፣ ደብረ ታቦር ቅዱስ ሚካኤል ሰ/ት/ቤት ፣ ደብረሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ዕፀ ጳጦስ ሰ/ት/ቤት) የሰ/ት/ቤቱ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው ያገባናል ይመለከተናል ብላችሁ ለሰጣችሁን ድጋፍ እና ለተወጣችሁት ኃላፊነት ሁሉ ከልብ እናመስግናለን፡፡ #_ውድ_የደብራችን_አባቶች በተገኘው ውሳኔ አሸናፊና ተሸናፊ የለም ይልቁንም ቋሚ የህጻናትና ወጣቶች መማርያ ቦታ ውሳኔ ተሰጠበት እንጂ ፡፡ ክርክራችን ደግሞ የሰ/ት/ቤቱ የመማርያ ቦታ ከዚህ ይልቅ ያኛው ይሻላል የሚል የአባትና የልጅ ነው፡፡ ብጹዕነታቸው ደግሞ ይህንን ክርክር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን የሚመለከተውን ሁሉ አናግረው በአካልም ቦታው ድረስ ተገኝተው የመጨረሻ ፠ ግራ ቀኙ በደንብ የታየበት ፤ ሁሉንም የማይጎዳ ውሳኔ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ውሳኔ ለ3ኛ ጊዜ የመጣ ዉሳኔ ነው ፡፡ ስለሆነም ከዚህ በኃላ በመካከላችን የተፈጠረውን አለመግባባት በፍጹም እርቅ አስወግደን ውሳኔውን በጋራ ተረባርበን አስፈጽመን ደብራችንን ወደ ቀደመ ሰላሙ እንድንመልሰው ሰ/ት/ቤቱ ዛሬም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ስለ ሁሉም ነገር ክብር #_ለመድኃኔዓለም! #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል #በየረር ተራራ እየነደደ ነው በየረር ተራራ የረር ቅዱስ ቴዎድሮስ … የየረር ሦላሴና የየረር በአታለማርያም ገዳም ደን እየነደደ ነው ፡፡ እሣቱ ሰው ሰራሽ መሆኑ ከምስሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እስከ መሠረቷ ድረስ ፈጽሞ አፍርሱ የሚሉትን ጎስቋሎችን የሚበቀላቸው አምላካችን ብፁዕ ነው፡፡ /መዝ. 136/ xበጀውኃ ከተማ የሚገኝ የሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እየነደደ ነው ሰሜን ሸዋ፤ከሸዋ ሮቢት አለፍ ብሎ #በጀውኃ ከተማ የሚገኝ #የሊቀ_ሰማዕት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ቤተ_ክርስቲያን_ተቃጥላል:: ካህናቱ ታርደዋል ፣ ምእመናንም ታርደዋል ፣ የክርስቲያን መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። #መዝሙረ ዳዊት 73፤ ‹‹#መቅደስህንም_በእሳት_አቃጠሉ፤ … #አቤቱ_ተነስ_በቀሌንም_ተበቀል፡፡›› ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንጸልይ ‹‹ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ!፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: ማቴ. 10፥28:: ። #share Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem