es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 382 suscriptores, ocupando la posición 5 568 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 195 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 382 suscriptores.

Según los últimos datos del 04 julio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 23, y en las últimas 24 horas de -1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 22.11%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 9.42% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 401 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 449 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 20.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 05 julio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 382
Suscriptores
-124 horas
-107 días
+2330 días
Archivo de publicaciones
እንኳን አደረሳቹህ ✤✣✤ #በዓለ_ልደቱ_ለሐዲስ_ሐዋርያ_ፀሐይ_ማር_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት #ታኅሣሥ_24_1196ዓም_በሰሜን_ሸዋ_ቡልጋ_ጽላልሽ_እቲሣ_ተወልደው_በአጠገቡ_በምትገኛወ_ደብረ_አጋዕዚት_ክርስትና_ተነሡ፡፡ #አባታቸው ቅዱስ ጸጋ ዘዓብና እናታቸው ቅድስት እግዚእ ኀረያ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው በአካባቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻንና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡ #በ7ት ዓመታቸው ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ከተቀበሉ በኋላ እግዚአብሔር በክህነት ሕዝቡን እንዲያገለግሉ መረጣቸው፡፡ ከዮዲት ጉዲት በኋላ ሃገራችን ሰሜኑና ደቡቡ ተቆራርጧል፤ የሐሳብን ልዕልና የሚያመጣው የመንፈስ ልዕልና ተዳክሟል፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያን የሚዋጅ ሐዲስ ሐዋርያ ያስፈልግ ነበርና አምላካችን አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ጠራ፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀብለው በጽላልሽ አካባቢ በክህነት ከአባታቸው ጋር አገልግለዋል፡፡ አባታቸው ሲያርፉ በወንጌሉ ማንም ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ያለውን ሁሉ ትቶ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ ያለውን በመከተል ሀብታቸውን ለድኾች መጽውተው በሸዋና በዳሞት በስብከተ ወንጌል አገለገሉ፡፡ ከዚያም፤ #በመጀመርያ ደቡብ ወሎ ቦረና ላይ ገዳማቸውን ደብረ ጎል ገድመው ወደሚገኙት ታላቁና ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን ወደኾኑት ጻድቅ አባት አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ዐሥር ሁለት ዓመታት በትምህርትና በሥራ (በአርድእትነት) አሳልፈዋል፡፡ በዚያም ዋሻ ፈልፍለው አስደናቂ ሕንፃ ሠርተው ነበር፡፡ #በ1216 ዓ.ም. አካባቢ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገሳም ገብተዋል፤ በዚሁ ገዳምም ከመመንኰሳቸው በፊት ሰባት ዓመት ከመነኰሱም በኋላ ሦስት ዓመት በድምሩ ለ10 ዓመታት በትምህርት፣ በእደ ጥበብ ሥራ፣ በአገልግሎትና ሥርዐተ ምንኵስናን እያጠኑ ቆይተዋል፡፡ #ከሐይቅ ወጥተው በዘመኑ በሥርዐተ ምንኵስናና በትምህርት ብሎም በጥበበ እድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ወደ ነበረው ወደ ደብረ ዳሞ በመሄድ በየገዳሙ አበምኔት ከሆኑት ከአቡነ ዮሐኒ ዘንድ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ሥርዐተ ምንኵስናና ጥበበ እድ ሲማሩ ለ12 ዓመታት ቆዩ፡፡ ያነጹት ፍልፍል ድንጋይ ዋሻ፣ መጻሕፍት ሲጽፉ ቀለማቸውን ያስቀምጡባቸው የነበሩትን ሽንቁሮች ዛሬም በደብረ ዳሞ ማየት ይቻላል፡፡ #በደብረ ዳሞ የነበራቸውን ቆይታ ጨርሰው በገመድ ሲወርዱ ሰይጣን በቅንዐት መጥቶ ገመዱን በጠሰባቸው እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወቅት የሚበሩበትን እንደ መላእክት ክንፍ ሰጣቸው፡፡ #ለአምስት ዓመታት #አኵስምን_ዋልድባን እንዲሁም ሎሎች የትግራይ ገዳማትን እየተዘዋወሩ ሲመለከቱ ቆዩ #ከሸዋ በወጡ በሃያ ሁለት ዓመት (እድሜያቸው ሃምሳ ሁለት ሲሆን) ለበለጠው ክብር እና ርእይ በግብጽ በኩል ወደ ኢየሩሳሌም ተሻገሩ፡፡ #ከኢየሩሳሌም ሲመለሱ በሐይቅ በኩል አድርገው ደብረ ጎልን ተሳልመው በሚዳ እና በመርሐ ቤቴ በኩል ወደ ሸዋ በመምጣት ከዮዲት ዘመን በኋላ በመንፈሳዊ ሕይወት የተጎዳውን ሸዋን እና ደቡብ ኢትዮጵያን በመዘዋወር ለዐሥር ዓመታት ያህል አስተምረዋል፡፡ #አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተግተው በማስተማራቸው የተኛው ሁሉ ነቃ፣ የደከመው በረታ፣ የጠፋውም ተገኘ፡፡ ሐዋርያትን ለማፍራት እንዲችሉ አንድ ገዳም ለመመሥረትና ደቀ መዛሙርትን ለማስተማር አሰቡ፡፡ እናም ወደ ደብረ አስቦ ገዳም ገቡ፡፡ ቦታውን አስተካክለው እና ከደብረ ዳሞ እና ከሐይቅ የተከተሏቸውን ጥቂት ደቀ መዛሙርት ይዘው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ልክ እንደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ሁሉ ሦስቱን ነገሮች ያካተተ አገልግሎት ጀመሩ፡፡ ምንኵስና፣ ትምህርትና ሥራ፡፡ መነኰሳቱ መንፈሳዊ ትምህርት ይማራሉ፤ በሕገ ገዳም ይመራሉ፤ ለራሳቸው እና ለአካባቢው ሕዝብ ርዳታ የሚሆን እርሻ ያርሳሉ፡፡ #ደቀ መዛሙርትን አፍርተው፣ ገዳማቸውን አደራጅተው፣ ስብከተ ወንጌልንም አስፋፍተው ካደላደሉ በኋላ በሕይወታቸው የመጨረሻ ዓመታት ወደ ደብረ አስቦ ዋሻ ገብተው በአንድ እግራቸው በጾም እና በጸሎት ተወሰኑ፡፡ #አገልግሎታቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን 1297 ዓ.ም. በ99 ዓመታቸው ዐረፉ፡፡ ✤✤ #እቲሣ_ገዳም_ #በቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃና አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተመሠረተ፤ ሲመሠረትም በታቦተ ኢየሱስና አርባዕቱ እንስሳ ነው፤ #ሊቀ ካህናት አበይድላ ከአኵስም 300 ታቦታትና 300ካህናት ይዞ መጥቶ በጽላልሽ የተቀመጠባት ናት፤ #ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት የተወለዱባት (የተወለዱባት ጠፍጣፋ ደንጊያ አሁንም በቦታው አለች)፣ #አባታቸውና ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእኀረያ የተወለዱበት፤ ኋላም ክብሩ አጽማቸው ያረፈበት ነው፡፡ #ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ቅዱስ ላሊበላ 7 ዓመት ጸልዮባታል፤ #ተሰዓቱ ቅዱሳን 20 ዓመት የጸለዩበት፤ #ሐርቤ በሚባለው ቦታ ላይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ 7 ዓመት ጸልየውበታል፤ #ታቦተ ጽዮን 12 ዓመት (ከ9ሺህ ሕዝብ) ጋር መጥታ ኖራበታለች፤ #በአምሳለ ሲዖል የተሠራ አስደናቂ የጨለማ ዋሻ ያለበት ነው፤ #ብዙ የታሪክ ቅርስ ያለበት ነው፤ #በቅዱስ ሚካኤልና ጸጋ ዘአብ ቤተ ክርቲያን ውስጥ ካየን በኋላ፤ እዚሁ ቦታ በሚገኘው ፈዋሽ ጠበል ተጠምቀንና ጠጥተን ጕዟችንን ወደ #ቦታው_ከአአ_በቅርብ_ርቀት_በደብረ_ብርሃን_መንገድ_አሌልቱ_ከተማ_ላይ_በመታጠፍ_ይገኛል፡፡ #ሥርዐተ_ማኅሌቱን_እንደየደብራችሁ ይትበሃል እንድትጠቀሙበት በማሰብ ሁሉንም (በላይ ቤትና በታች ቤት) (#ዘአባጃሌ_ተክለ_ሃይማኖትና_ዘአደባባይ_ተክለሃይማኖት) አዘጋጅተነዋል፡፡ ጸሎትና በረከታቸው፤ ረድኤትና ምልጃቸው በመላው ሕዝበ ክርስቲያንና በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ አድሮ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ /የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሰሌዳ መጽሔት / Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

ዝማሜ ፤ «ገብርኤል መልአክ» ፤ በሰንበት ት/ቤት መዘምራን «ታኀሣሥ 19 ፤ 2013 ዓ.ም የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል» በyouTube ገጻችን ይመልከቱ፤ https://youtu.be/q-sIXLDktHM

ዝማሜ ፤ «ገብርኤል መልአክ» ፤ በሰንበት ት/ቤት መዘምራን «ታኀሣሥ 19 ፤ 2013 ዓ.ም የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል» በyouTube ገጻችን ይመልከቱ፤ https://youtu.be/_amtQEm79Pk

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል ወረብ ፤( የታኀሣሥ 19 | 2013 ዓ.ም) እምዕቶነ እሳት ፤ በደብረሰላም ሊቃውንት ፤ በYouTube ገጻችን ይመልከቱ(1080p) https://youtu.be/p3H4kxjbnM8

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል ወረብ ፤( የታኀሣሥ 19 | 2013 ዓ.ም) እምዕቶነ እሳት ፤ በደብረሰላም ሊቃውንት ፤ በYouTube ገጻችን ይመልከቱ (1080p) https://youtu.be/p3H4kxjbnM8

፨ #ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራተ_ገብርኤል … #በስድስተኛውም_ወር_መልአኩ_ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡፡ …… መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ያጸናሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡ መልአኩም ከእርሷ ሄደ… /የሉቃስ ወንጌል 1፥26-38/ #ይህቺም_ዕለት_የበዓላት_ሁሉ_በኵር_ናት፤ በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሯልና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን፡፡ /ስንክሳር ዘታኅሣሥ 22/ ——- #በመዲና ከተማችን በአዲስ አበባ ታኅሣሥ_22_ብሥራት_የሚከበርባቸው፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ (ኋላ ቅድስት ማርያም እየተባለ በመጠራት ላይ ያለ) ሲሆን በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ካልዕ መልክአ ቅዱስ ገብርኤልን በማኅሌት በመቆም ይከበራል፡፡ —————— የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው
#ይኩነኒ_በከመ_ትቤለኒ_ (#እንደ_ቃልህ_ይሁንልኝ_)፤ #ታኅሣሥ_22_ብሥራት_ … በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ፡፡ …… መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ያጸናሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም። እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች፡፡ መልአኩም ከእርሷ ሄደ… /የሉቃስ ወንጌል 1፥26-38/ ይህቺም እለት የበዐላት ሁሉ በኵር ናት፤ በእርሷም የዓለም ድኅነት ተጀምሯልና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስም ከቸር አባቱና ይቅር ባይ ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ለዘላለሙ ይሁን አሜን፡፡ /ስንክሳር ዘታኅሣሥ 22/ በመዲና ከተማችን በአዲስ አበባ ታኅሣሥ_22_ብሥራት_የሚከበርባቸው፤ ፠ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል) ፠ መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ (ኋላ ቅድስት ማርያም እየተባለ በመጠራት ላይ ያለ) ሲሆን በታላቁ ደብራችን በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ካልዕ መልክአ ቅዱስ ገብርኤልን በማኅሌት በመቆም ይከበራል፡፡

የ2012 ዓ.ም እና የቀደሙ ዓመታት የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል ድባብ በደብራችን ፤ ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን::

እንኳን አደረሳቹህ #ታኅሣሥ_፲፱ #በዓለ_ቅዱስ_ገብርኤል፤ #ወሥርዐተ_ማኅሌት፡፡ ቅዱስ ገብርኤል፤ #ሊቀ_መላእክት_በመላእክት_ሁሉ_ላይ_የተሾመ_ነው_ሄኖክ_10፥14 #የአርባብ_የ10ሩ_ነገደ_መላእክት_አለቃ_ነው #ከከበሩ_መላእክት_አንዱ_ነው_ሄኖክ_6፥7፤ #አካሉ እንደ ቢረሌ የሚመስል (ጽሩይ የሆነ) ፥ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ የሆነ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነው፡፡/ዳን.10፥5-9/ #መልአከ_ራማ_ዘራማ_ልዑል_ነው፤ (የራማ ልዑል ነው) #አብሣሬ_ትስብእት_ነው፤ #መጋቤ_ሐዲስ_ነው፤ #በእግዚአብሔር_ፊት_የሚቆም_መልአክ_ነው_ሉቃ_1፥19፤ #ለቅዱሳን_እውቀትን_የሚገልጽላቸውና_ከአላውያን_የሚታደጋቸው_ነው_ /ድርሳነ_ገብርኤል/ #መልአከ_ሰላሞሙ_ወመልአከ_ኪዳኖሙ_መልአከ_አድኅኖ_መልአከ_ኀይል_መልአከ_ፍስሐ (የሰላም መልአክ ፥ የኪዳን መልአክ፥ አዳኝ መልአክ፥ ኀያል መልአክ ፥ የደስታ መልአክ ነው) #ከሣቴ ጥበብ (ጥበብን የሚገልጽ ነው) /ት.ዳን./ #ናዛዜ_ኅዙናን_ (ያዘኑትን_የሚያጽናና_) መልአክ_ነው፨ ✤ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፤ የወልደ እግዚአብሔርን መወለድ አብሥሯልና፨ አንድም የሁለት ቃለት ጥምር ነው እነዚህም ገብር እና ኤል ሲሆኑ ትርጕማቸውም ገብር አገልጋይ ማለት ሲሆን ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው፤ በተገናኘ ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ /የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል የአምላክ አገልጋይ/ ማለት ነው፡፡ ✼ ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኃይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኃይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፥5-9) ነቢዩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ የተናገረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ ነበር፡፡ ፠ “እነሆ ከዋነኞቹ አለቆች” አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”(ዳን.10፥13) ብሎ በተናገረው ንግግሩ በመላእክት ላይ የተሾሙ ሌሎች አለቆች እንዳሉ ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምደር ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” (ቈላ.1፥16) በማለት ይዘረዝራቸዋል፡፡ ከዚህ ተነሥተን መላእክት በተለያዩ ዐበይት ነገዶች የተከፈሉና ለእያንዳንዱም ነገድ የራሱ የሆነ አለቃ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከ100ው ነገደ መላእክት መካከል ከበታቹ የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉት፤ ከተማቸውም በሰማየ ራማ ነው፡፡ ✼ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ፤ እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን ቅዱስ ገብርኤል በመቃወም ‹‹ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ (ነአምሮ) ለአምላክነ “አይዟችሁ ፈጣሪያችን እስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት ጸንተን እንቁም፡፡” (አክሲማሮስ ገጽ.35) በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል በተወዳጁ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ዲያብሎስን ተዋግተው ድል እንዲያደርጉ ወደ ጥልቁ እንዲጣል አድርጓል ራእ12፥7፤ ነቢዩ ኢሳይያስ በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፤… በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምድር ጥልቅም ትወርዳለህ” (ኢሳ.14፥16) በማለት ገለጠልን፤ ወደ ምድር የጣሉት በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል መሪነት እነ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡ ✼ ቅዱስ ገብርኤል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ከሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው ብሏል (ሉቃ 1፥19)፤ ✼ ታላቁ ነቢይ ሄኖክም ስለ ነገረ መላእክት በተናገረበት አንቀጽ እንዲህ ሲል መስክሯል ‹‹በአበቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡›› ሄኖክ 6፥7፤ ‹‹በሦስተኛውም በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ሄኖክ 10፥14 እያለ የመልአኩን ክብር ተናግሯል፡፡ ** ቅዱስ ገብርኤል መንፈሳዊ እውቀቱን የሚያካፍላቸው መልአክ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ነገር ግን ያደረጋቸው ተዓምራቶች በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በመልክኡ፣ በድርሳኑ፣ በተአምሩ፣ …. የተጻፉ ቢሆንም፤ ✤✼ #ታኅሣሥ_19 #ካደረጋቸው_ተራዳኢነት_ዋናውን_እንደከሚተለው_እናያለን_፤ ፠ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) ያዳናቸው ያዳነበት ቀን ነው፡፡ አናንያና(ሚሳቅ)፣ አዛርያ(ሲድራቅ) እና ሚሳኤል(አብደናጎ) የፋርስ ባቢሎን ንጉሥ የነበረው ናብከደነፆር በዱራ(አዱራን) በሚባል ስፍራ ላይ ላቆመው ጣየዖት ምስል ስገዱ ሲላቸው …. የምናምነው አምላክ ያድነናል፤ ባያድነን እንኳን (አምላካችን በእሳት ሰማዕት እንድንሆን ፈቃዱ ቢሆነረ አንኳን) አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም ብለውታል፡፡ ንጉሡም ወደ እቶን እሳት እንዲጣሉ አድርጓቸዋል፤ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት ግን ከእቶን እሳቱ የልብሳቸው ዘርፍ እንኳን እሳት ሳይነካው ከእሳቱ ድነዋል፡፡እኛንም ያድነን አሜን:: እንዲሁም ታኀሣሥ 19፤ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘሀገረ_ቡርልስ_በዓለ_ዕረፍቱ_ እንዲሁም #ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ስነ_ኢየሱስ_ (#ገዳማቸው_በሰሜን_ጎንደር_ትክል_ድንጋይ_አካባቢ_የሚገኘው_) #በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው_፡፡ የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem