es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 615 suscriptores, ocupando la posición 5 302 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 181 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 615 suscriptores.

Según los últimos datos del 07 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 51, y en las últimas 24 horas de 11, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 7.91%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 4.59% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 1 235 visualizaciones. En el primer día suele acumular 716 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 10.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 08 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 615
Suscriptores
+1124 horas
+707 días
+5130 días
Archivo de publicaciones
"ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ስምዖን አረጋዊ የካቲት 8 ፤ የጌታችን ከከበርች ልደት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ የገባበት ዕለት ኾነ ፡፡ በዓሉ ከጌታችን ንዑስ በዓሎች መኻከል አንዱ ነው ፡፡ ++++ የካቲት 8 ፤ ልደተ ስምዖን አረጋዊው ፣ ካህን ፣ ጻድቅ ፣ ነቢይ ፡፡ በዓሉ የመድኀኔዓለም ቢሆንም ስምዖን አረጋዊ አማናዊ ድኅነት አግኝቶበታልና ፣ በእርጅና ምክንያት ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ሲኖር ታድሶበታልና እንደ 30 ዓመት ጎልማሳም ዘሏልና በዓሉ ይከብራል ። ስምዖን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ ሁሉ የድኅነት ባለቤት ኾኖበታልና በዓሉ ይከብራል ። ++++ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ የኦሪትን ሕግ ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ ። ይህም ሕግን ሊፈጽም እንጂ ሊያፈርስ አለመምጣቱን በቃልም ፣ በግብርም የገለጠበት በዓል መኾኑን ያስረዳናል። ሥርዓቱን ለመፈጸም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጌታቸውን ይዘው፣ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ ። ++++ የስምዖን አረጋዊ ነገርም እንኽ ነው .. ዓለም በተፈጠረ በ5,200 ዓመታት በጥሊሞስ የተባለ ንጉሥ በግሪክ ነግሦ ነበር። ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ የገዛው መሆኑን ገልጦ፣ የቀረው ነገር አለመኖሩን ሲናገር ባለሟሎቹ በእሥራኤል ጥበብ የመላባቸው 46 መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን አላስተረጎምክም አሉት። እስራኤልን አስገብሮ ስለነበር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 የአይሁድ ሊቃውንት ጋር አስመጣ። አይሁድ ተንኮለኛ መኾናቸውን ስለሚያውቅ 36 ድንኳን እንዲዘጋጅ አድርጎ ኹለት ኹለቱን መድቦ፣ የየድንኳኑን ሊቃውንት የሚቆጣጠሯቸው አንዳንድ ጠባቂዎች ጨምሮ እንዲተረጕሙ አዘዛቸው። በዚህ ምክንያት በ284 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት 46ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ወደ ልሳነ ጽርዕ (ግሪክ) በ70ው ሊቃናት ተተረጐሙ። ከ70 ሊቃናት በመኻከል አንዱ የነበረው #ስምዖን ምሁረ ኦሪት ነበር። ይተረጕም ዘንድ መጽሐፈ ኢሳይያስ ደረሰው። ታዲያ ይህ ሊቅ የትንቢቱን መጽሐፍ እየተረጎመ ሳለ ምዕራፍ ፯ ላይ ሲደርስ የሕይወቱን አቅጣጫ ወደ ዘላለማዊ በረከት የሚያሳድግ ልዩ ገጸ ንባብ ገጠመው ። እርሱም “ ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነኾ ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 የሚል ነበር። ስምዖንም "እንዴት ድንግል ትፀንሳለች?" ብሎ "ድንግል" የሚለውን "ሴት" ብሎ ቀይሮ " ሴት ትፀንሳለች " ብሎ ለማረም ይሞክርና አመሻሽ ላይ ስለነበር እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት ሲነቃ የቀየረው ተቀይሮበት " ድንግል ትጸንሳለች" የሚል ሁኖ ያገኘዋል። ተሳስቼ ነው ብሎ አሁንም ሊያበላሽ ሲሞክር መልአኩ ሦስት ጊዜ አርሞበት በሦስተኛው መልአኩ ራሱ ተገልጦለት "ይህችን ድንግል ሳታይና ልጇንም ታቅፈህ ሳትባረክ አትሞትም" ( የተጠራጠርከውን ሳታይ አትሞትም ብሎ ብሎ ነግሮት ) ተሰወረ። አረጋዊ ስምዖንም ከዚያች ዕለት ጀምሮ መድኅን ክርስቶስ እስከሚወለድ ለ284 ዓመታት ከአልጋ ጋር ተጣብቆ ኖረ። አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ወጡ ። በዕለቱም መልአከ እግዚአብሔር አረጋዊ ስምዖንን ቀስቅሶ ተስፋ የሚያደርገው አዳኝ ክርስቶስ መምጣቱን ነገረው። በዚህ ጊዜ አረጋዊ ስምዖን አካሉ ታድሶ፣ እንደ 30 ዓመት ወጣት እምር ብሎ ከአልጋው ተነሣ። በፍጥነትም ወደ መቅደስ ገባ። መድኀኔዓለምን ከድንግል ማርያም ተቀብሎ በመታቀፍ "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" (" ጌታ ሆይ፥ አን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤ ይኽም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ፳ኤል ክብር ነው።" (ሉቃ 2÷29-32) ) በማለት ጸለየ። አምላኩም ጸሎቱን ሰምቶት በዛሬው ዕለት ዐረፈ። ከበዓሉ በረከት ይክፈለን። አሜን!! የሊቁ ስምዖን አረጋዊ በረከት እና ምልጃ አይለየን ! በዓለ ስምዖን በዐይቢይነት ሜላት ደብረ ገነተ ኢየሱስ ይከብራል ፡፡ ጐንደር -- › አንዳቤቴ ወረደ -- › ገነተ ኢየሱስ በ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት ልዕልት ሜላተ ወርቅ ያሰተከለችው ደብር ነው ፡፡ +++ በዓሉ በኢየሱስ ስም የተሰየሙ አድባራትና ገዳማት ላይ ይከበራል ! +++ አንዲት ቤተክርስቲያን ፣ አንድ ሲኖዶስ ፣ አንድ ፓትርያርክ ፡፡ +++ / በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ / #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

#ዜና_ዕረፍት ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ከ1971 - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት ‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38 * የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም
#ዜና_ዕረፍት ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም ከ1971  - 2015 ዓ.ም በአገልግሎት ‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡››  ሲራክ ፥ 38 * የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ሊቀ ስዩማን ኃይለ ማርያም  ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፡፡ * ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው የሚፈጸምበትን ዕለት እና ሰዓት እናሳውቃለን ። *የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን ! #የሥርዓተ ቀብር ሰዓቱን የምናሳውቅ ይኾናል  ። /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com

++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት አባ ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሢኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል። በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ። በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሁኑን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል ።

#ሰበር_ዜና #ይቅርታ ጠየቁ ፨፨፨፨፨፨፧፨ ፨፨፨፨፨፨ ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለማስገባት ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚገኙ ሰምተናል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን።

መምህር ምሕረተአብ አሰፋ እና የማንቂያ ደውል አገልጋዮች ዲ/ን አማኑኤል አያሌው እንዲሁም ዲ/ን ኪሩቤል አሰፋ በዛሬው ዕለት ታፍነዋል ! Memeher Mehreteab Assefa and Mankiya D
+1
መምህር ምሕረተአብ አሰፋ እና የማንቂያ ደውል አገልጋዮች ዲ/ን አማኑኤል አያሌው እንዲሁም ዲ/ን ኪሩቤል አሰፋ በዛሬው ዕለት ታፍነዋል ! Memeher Mehreteab Assefa and Mankiya Dewol servants D/N Amanuel Ayalew and D/N Kirubel Assefa were kidnapped today !

የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ የሆነው አበበ ሞቅ ያለው ትናንት የካቲት 2/2015 ዓ.ም ከመሥሪያ ቤቱ ለምሳ ሲወጣ በጸጥታ ኃይሎች ተወስዷል። መምህር አበበ ማክሰኞ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በነበረው ስብሰባ ላይ መንግስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለው ጫና ተቀባይነት የለውም በማለት ትችት ማቅረቡና ትናንት ሐሙስ ጥቁር ልብስ ለብሶ በሥራ ገበታው ላይ መገኘት ለእስር እንዳበቃው ለመረዳት ተችሏል። አበበ በሃይማኖቱ ምክንያት መታሠሩ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን አደራ እና ያስተማረችውን ትምህርት ተግባር ላይ ማዋሉ ነውና መታሠሩን መድኃኔዓለም ለበረከት ያድርግለት። ክርስትናን በማሠርና በማሳደድ ማጥፋት አይቻልምና የሚመለከተው አካል መምህር አበበንም ሆነ በሌሎች አጥቢያዎች የታሠሩ ክርስቲያኖችን እንዲፈታ እንጠይቃለን። አንዲት ቤ.ክ አንድ መንበር አንድ ፓትርያርክ

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት የተፈጠረውን ችግር ለያስወግድ እንደተስማማ እና እሥር እንግልት በአስቸኳይ እንዲቆም ፣ የታሰሩት እንዲፈቱ ከስምምነት ላይ መደረሱን አሳውቋል ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት የቤተክርሰቲንን ወሳኔ እንደሚቀብል ነገር ግን አሠራሩን ለማስተካከል ጊዜ አንደሚፈል ተናግረዋል ፡፡ የካቲት 5 ቀን የተጠራወም ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል ይህሞ የኾነው ቤተክርስቲያን ለሰላም ምንጊዜም በሯ ክፍት መኾኑን ለማሳየት ነው ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ የተጀመረው አንድነት ጸሎት እና ምሕላ ዘወትር እንዲቀጥል አሳስቧል ፡፡ ከዚህ በኋላ ከመንግሥት ጋር የሚደረጉትን ውይይቶች በየጊዜው እንደሚያሳውቅ እና ዘወትር በንቃት እንድንከታተል እና ቤተክርስቲያንችንን በትጋት እንድንጠብቅ አሰቀውቋል ፡፡ http://www.finotehiwotsundayschool.com

ቤተክርስቲያኗ መግለጫው እንደሚሰጥ እና ምዕመኑ ተረጋግቶ እንዲጠብቅ አሳስባለች። በአሁን ሰዓት ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫውን ይሰጣል ተብሏል። ጉዳዩ ትልቅ አጀንዳ ስለሆነ እና ትልቅ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ መግለጫው የዘገየ ሲኾን መግለጫው እስኪሰጥ ምዕመናን ተረጋግተው እንዲጠብቁ ቤተክርስቲያና መልዕክቷን አስተላልፋለች። ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሲሰጥ 7ኛው ሲሆን ትላንት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በተደረገው ውይይት ስለተገኘው አጠቃላይ መፍትሔ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። http://www.finotehiwotsundayschool.com

የአርብ ጉባኤ በአውደ ምሕረት የካቲት 2015 ዓ.ም ። #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_ፓትርያርክ።

በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር የነበረውን ውይይት በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው ጥያቄያችን መብታችን ይከበር ሕግ ይከበር ነበር። ያ ካልሆነ ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን እንደሚያደርጉ መወሰናቸውን አስታውሰዋል። አክለውም በዛሬው ስብሰባ ጥያቄያችንን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበናል ያሉ ሲሆን በነገው ዕለት በጉዳዩ ላይ ሙሉ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። በመጨረሻም አቋማችን እንደጸና ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ጥያቄያችን እስካልተመለሰ ድረስ ተጋድሏችን ይቀጥላል ብለዋል።