ru
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Открыть в Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Канал Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 368 подписчиков, занимая 5 616 место в категории Религия и духовность и 2 192 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 368 подписчиков.

Согласно последним данным от 25 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило -4, а за последние 24 часа — -1, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 20.07%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 8.16% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 3 085 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 1 254 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 17.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 26 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Религия и духовность.

15 368
Подписчики
-124 часа
+357 дней
-430 день
Архив постов
#ጥር_15_በ2ት_ዓመት_ከ9ኝ #ወሩ_ሰማዕትነትን_የተቀበለው_ቅዱስ_ቂርቆስ_በ3_ዓመት_ከ1_ወር_ከ3#ቀኑ_አንገቱን_በሰይፍ_ተቆርጦ_ሰማዕትነትን_የተቀበለበት_በዓለ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው #ስምህ_በተጠራበት_ቤተ_መቅደስህ_በታነጸበት_ስዕልህ_ባለበት_ቦታ_ሁሉ_የሕፃናት_እልቂት_የከብት_በሽታ_የእህል_እጦት_ረሀብ_ቸነፈር_አይደርስም የሚል ቃልኪዳንም ጌታችን ገብቶለታል፡፡ #በገባለት ቃል ኪዳንም መሠረት በመዲናችን #በአዲስ_አበባ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን የሰው እልቂት የከበት በሽታ ገብቶ በነበረበት ወቅት የቂርቆስ ደብር #መካነ_ሰማዕት ሲተከል የሰውም በሽታ ርቋል፥ የከብት እልቂትም አቁሟል፡፡ #በጎንደር_ደብረ_መንክራት_ቅዱስ_ቂርቆስ_ቤክ_ደግሞ_#ጽዋ_ማስደፋት_ የሚል ሥርዐት አለ በዚህ ሥርዐትም የሰረቀውን ሰው ቅዱስ ቂርቆስ የሚያጋልጥበትና አሁንም ድረስ የሚታይ አስደናቂ ተዓምር ነው፡፡ ፠ የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ሲባሉ፤ የተወለደው በዘመነ ሰማዕታት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በኅዳር 15 ቀን ነው፡፡ የትውልድ ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ አንጌቤን ይባላል፡፡ ፠ አንጌቤናይት ብጽዕት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለ መኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር፤ በዘመኑ የነበረው መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ‹‹ለጣዖቴ ስገጂ›› ብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም ‹‹ሕፃኑ ልጄ መጥቶ ይመስክር›› ብላ ስትናገር ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ‹‹ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደው›› ብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡ ፠ ንጉሡም እጅግ ተቆጥቶ 40 ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ 40 ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን (ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል) በውስጡ አስጨመረ፤ የእሳቱ ድምፅ እንደ ነጎድጓድ እስኪሰማ፥ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ እስኪያንጸባርቅ ድረስ ሆነ፡፡ የፍላቱም ኃይል 14 ክንድ ያህል እየዘለለ ወጣ፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ በዚያን ጊዜም 11,004 እስረኞች ከእስር ወጥተው እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ጊዜ "እናቴ ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ ድንጋፄም አይደርብሽ" እያለ ከብሉይና ከሐዲስ እየጠቀሰ እንድትጸና አስተማራት፡፡ ፠ እናቴ ሆይ አናንያ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳናቸው እግዚአብሔር እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትፈልጊ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡... እያለ አብዝቶ መከራት፡፡ ነገርግን በዚህም ምክር እናቱን መመለስና ለሰማዕትነት ማዘጋjት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ መጸለይ ጀመረ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ ይህች ባርያህ ከምትክድ ከሕይወት መጽሐፍ እኔን ፋቀኝ...›› ብሎ ጸለየ፡፡ በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከእርሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፤ በመንግሥተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ሰጠኝ፡፡ የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈጽምና ድል እንነሣ›› አለችው፡፡ የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ እያለች እየነገረችው ሳለ አንሠተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርንም የሚበጥስ መሣሪያ ነበረበት፡፡ ወዲያውም የራማው ልዑል ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት ፈጽሞ አበረደው፡፡ ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አለ፡፡ እንደ ውኃም ሆነ፡፡ ፠ ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ፤ * በአፍና አፍንጫቸው መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳቸውም እንዳውም ምግብ ሆነላቸው፡፡ * ጨውና በርበሬ በዐይናቸው አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካቸውም፡፡ * ዐሥራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች፤ ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል፥ ሰባቱን በቂርቆስ አካል ውስጥ (ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ፥ ሁለቱን በዓይኖቹ፥ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ፥ አንዱን በልቡ) ተከሉ፤ አሁንም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ፈወሳቸው፡፡ * በ4 ችንካሮች ላይ አስቀመጧቸው፤ መልአኩ ፈወሳቸው * የራስ ጠጕራቸውን ከቆዳቸው ጋር ገፈው በእሳት ውስጥ ጨመሩት፤ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ፈወሳቸው፡፡ * በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ ሰቀሏቸው፤ መልአኩ አዳናቸው፡፡ (ሐምሌ 19 ቀን የምናከብረው ክብረ በዓል ከላይ ያሉትን ሁሉ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ለቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ የተራዳበትን በማሰብ ነው፡፡) ፠ ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ3 ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ፠ በመጨረሻም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር 15 ቀን በ3 ዓመት ከ1 ወር ከ3 ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀበለ፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ፠ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፤ ሄሮድስ ላስፈጃቸው 144,000 የቤቴልሔም ሕፃናትም አለቃቸው ነው፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር 16 ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡ በዚሁ ዕለት የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች የሆኑ 11,004 ሰዎች የጌታችንን ክብር እየመሰከሩ በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ፠ #በነገታው_በጥር_16ም #እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ_በክብር_ያረፈችበት_ነው (ምንጭ፤ የቀ.ደ.ሰ መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰሌዳ መጽሔት፣ ከገድላት አንደበትና ዝክረ ቅዱሳን) ሥርዐተ ማኅለሌቱን ከዋይዜማው ጀምሮ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ ወረቦቹን፣ እስመ ለዓለም፣ አቡንና ሰላሙን በድምፅ ከፈለጋችሁ በቴሌግራም ገጻችን ያገኛሉ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን #Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...

ስብስብ ስም ዝርዝር የውሸት የተሾሙት ዝርዝር 1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ 2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረ
+4
ስብስብ ስም ዝርዝር የውሸት የተሾሙት ዝርዝር 1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ 2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ 3. አባ ሽኖዳ ።።።።።።።።። አለም ገና ኢየሱስ አስተዳዳሪ 4. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ።።።።።።። ወለቴ ዮሐንስ አስተዳዳሪ 5. አባ ገብረ ኢየሱስ ።።።።።። አለም ገና ሚካኤል አስተዳዳሪ 6. አባ ገብረማርያም ነጋሳ ።።።።። የኦሮምያ ቤተ ክህነት መስራች 7. አባ ጳውሎስ ከበደ ።።።።። የሐረር ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረና በተሐድሶነት የተባረረ 8. አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ።።።።።።። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ መምህር ይቀጥላል. .....

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ። (ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፩፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ) መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :- 1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል። 2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። 3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

#ወአቀቦሙ_ከመ_ብንተ_ዐይን_ለጻድቃን ፤ #እለ_ሎቱ_ተቀንዩ_በሕይወቶሙ ። * የታላቁ ሊቅ #የቀኝ_ጌታ_ተክለ_ያሬድ_አሰፋ ሥርዓተ ቀብር ፥ ሲያገለግሉበት በቆዩበት ደብር ፤ በቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም ተፈጽሟ ል ። * የታላቁ መምህራችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሐቅ እቅፍ ያኑርልን ። ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት www.finotehiwotsundayschool.com

መረጃውን በአግባቡ ለማጋራት ሰፊ ማስረጃ ይሻል። ለጊዜው ግን ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና የነፈገው "በ፬ ብፁዓን አባቶች" በወሊሶ ዛሬ በማለዳ እየተፈጸመ ያለው የ፳፭ መነኮሳት "ሲመተ ጵጵስና” ነው። * በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምስካየ ኅዙናን መድኃኒአለም ገዳም የበላይ አማካኝነት 25 ኤጲስ ቆጶሳትን እየሾሙ እንደሚገኝ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ !!!

ጥር 14 ፤ በዓለ ልደቱ ለአቡነ አረጋዊ #በአዲስ አበባ የሚከበርባቸው ጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከ ልጅ ሰጣቸው እሱም አቡነ አረጋዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሕገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየጸና እየበረታ አደገ፡፡ ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል/አረጋዊ/ ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሔደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም “ልጄ ሆይ አንተ የንጉስ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኰሰህ ለመኖር ይቻልሃልን” አለው፡፡ መሉ ታሪኩን እዚህ ያንብቡ ---> https://t.me/medihanaelem/7405 ወይም በፌስቡክ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/posts/3026138151037596 #በአዲስ አበባ የሚከበርባቸው 1. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዘነበ ወርቅ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ጦር ኀይሎች → ዘነበ ወርቅ፤ 2. ምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስና አቡነ አረጋዊ ገዳም፡፡ (ሳሪስ አቦ) አድራሻ፤ አቃቂ ክፍለ ከተማ፥ ሳሪስ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ /ማዘጋጃ/ → ሳሪስ አቦ፡፡ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፩ ዐበይት #ገዳማትና_አድባራት፡፡ 1. ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ፤ አድራሻ፤ ትግራይ፥ እንትጮ፤ (የታክሲ ምንጭ ፤ ገዳማትና አድባረት ገጽ) /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ኢትዮጵያውያን_ቅዱሳን #Ethiopian_Saints #ክብረ_በዓላት #Feasts https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw?list=PLYnv13n3p2aiKs_HETafC3vSIGZozB3oF

የቀኝ ጌታ ተክለ ያሬድ አሰፋ አጭር የሕይወት ታሪክ ። ቀኝ ጌታ ተክለ ያሬድ አሰፋ በ1933 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ክፍለ ሀገር ጃማ ወረዳ አህያ ፈጅ ቁስቋም ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በአካባቢያቸው ከሚገኘው ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን ፊደልና ጸዋትወ ዜማ የተማሩ ሲሆን በመንዝ ክፍለ ሀገር ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ከየኔታ አክሊሉ ዘንድ ዜማ ተምረዋል። ከዚያም በኤሊሻማ መድኃኔዓለም ከመልአከ ብርሃን ቤተ ማርያም ግዛው የተክሌ አቋቋም የተማሩ ሲሆን በመቀጠልም በሰደድኩላ ሚካኤል በቅዳሴ መምህርነት አስመስክረዋል። ቀኝ ጌታ ተክለ ያሬድ አሰፋ ለቤተ ክርስቲያን ትምህርት ካላቸው ብርቱ ፍላጎት የተነሳ የቅኔ ትምህርታቸውን በጎጃም ብቸና ጊዮርጊስ የተማሩ ሲሆን ከዚያ ተመልሰውም በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ከየኔታ በትረ ማርያም ዘንድ አስቀጻይ ሆነው የተክሌ አቋቋም ሲማሩ ቆይተው በ1965 ዓ/ም ወደ እንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል በመምጣት በቅዳሴ መምህርነት አገልግለዋል። ቀኝ ጌታ ተክለ ያሬድ አሰፋ ከሕዳር 1967 ዓ.ም ጀምሮ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ መምህር በመሆን ወደ ደብሩ ከመጡ በኋላ እስከ 1974 ዓ.ም በቅዳሴ መምህርነት አገልግለዋል። በማያያዝም የአካባቢ ወጣቶችን ፊደል በማስቆጠር ብዙ ልጆችን አፍርተዋል። ከዚያም ወደ ቅኔ ማኅሌት ሥራ ተዛውረው በቅኔ ማኅሌቱ ቀኝ ጌታ ሆነው ተሾመው ለ7 አመታት ደብሩን ያገለገሉ ሲሆን እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ለ አርባ ስምንት አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መድኃኔዓለምን ሲያገለግሉ ኖረው ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም በተወለዱ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ለረዥም ዓመታት ባገለገሉበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በነገው ዕለት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ይፈጸማል። ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

#ዜና_ዕረፍት ቀኝጌታ ተክለያሬድ አሰፋ ከ1933 - 2015 ዓ.ም ‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ ፥ 38 * የደብራችን ታላቅ አገልጋይ ቀኝጌታ ተክለያሬድ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈዋል ፡፡ *ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸውም ነገ ቀን 14 / 05 / 2015 ዓ.ም ባገለገሉበት ደብር በቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም #ከ7-8 ሰዓት ይፈጸማል ። *የአባታችንን ነፍስ ፥ አምላካችን መድኀኔዓለም ከደጋጎቹ አባት ከአብርሃም ከይስሓቅ ጋር ይደምርልን ! #ቀብር_ከሰባት_ሰዓት_እስከ_ስምንት_ሰዓት ። /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com