es
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 368 suscriptores, ocupando la posición 5 616 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 192 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 368 suscriptores.

Según los últimos datos del 25 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de -4, y en las últimas 24 horas de -1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 20.07%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 8.16% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 085 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 254 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 17.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 26 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

15 368
Suscriptores
-124 horas
+357 días
-430 días
Archivo de publicaciones
#ጥምቀት_በኢትዮጵያ ፤ ፠ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠመቀው የንግሥት ሕንደኬ በጅሮንድ አቤላክ(ባኮስ) ‹‹እነሆ ውኃ አለ፣ ታድያ መጠመቅን ማን ይከለክለኛል?›› /የሐዋ. ፷፥፳፱-፴፮/ ብሎ በሐዋርያው ፊልጶስ በተጠመቀ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ሥርዐት ግን ተስፋፍቶ የቀጠለው በነገሥታቱ በአብርሃ ወአጽብሐ (315-351ዓ.ም.) የቤተ መንግሥቱ ጃንደረባ በነበረውና ኋላ ጳጳስ በሆነው በፍሬምናጦስ(አባ ሰላማ) ዘመን ነው፡፡ በዓሉ ግን አሁን በምናከብረው ዓይነት ስዕላዊ በሆነ መልኩ መከበር የጀመረው ከማኅሌታዊው ቅዱስ ያሬድ ዜማ መስፋፋት ጋራ በአፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (530-544ዓ.ም.) እንደሆነ ይነገራል፡፡ ፠ ገዳማቱና አድባራቱም በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የውኃ ምንጮች በተናጥል በመውረድ በዓለ ጥምቀትን ያከብሩ ነበር፡፡ ተቀራርበው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያሳድሩ ዐዋጅ የታወጀው፥ ትእዛዝ የተላለፈው በጻድቁና በጠቢቡ ንጉሥ ላልይብላ(1140-1180ዓ.ም.) ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በዚሁ ዘመን የነበሩት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአኵሱም በመቀለና በመርጡለ ማርያም ያሉ ጥምቀተ ባሕሮችን ባርከዋል፤ በአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን ደግሞ በአቡነ ተክለሃይማኖት አሳሳቢነት ሥርዐተ ጥምቀቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዐዋጅ ታውጇል፡፡ እስከ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ድረስም ታቦታቱ ዕለቱን ጠዋት ወጥተው ማታ መለሱ ነበር፤ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ታቦታቱ በዋዜማው ጥር 10 ከሰዐት በኋላ ወደ ትምቀተ ባሕር ወርደው እንዲያድሩ፤ አገሩንም በኪደተ እግር እንዲባርኩ፤ በሄዱበት መንገድም እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ቀጥሎም አፄ ናዖድ ሕዝቡ ታቦታቱን አጅቦ ወደ ጥምቀተ ባሕር እንዲሄድ በዐዋጅ አስነገሩ፡፡ ይህ ሥርዐትም እስካሁን ከኛ ዘንድ ደርሷል፡፡ በዘመናት ውስጥም የጥምቀት በዓል ሲከበርባቸው ከነበሩ ቦታዎች ዐበይቶቹን ለመጥቀስ ያህል፤ #በአኵሱም_የንግሥተ_ሳባ_መዋኛ_ ‹‹#ማይ_ሹም›› #በጎንደር_የአፄ_ፋሲል_መዋኛ_ገንዳ #በቅዱስ_ላሊበላ_የዮርዳኖስ_ወንዝ #በሸዋ_የአፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_ፍርድ_መስጫ_አደባባይ #44ት #ታቦታት_የሚያድሩበት_የሸንኮራ_ሜዳ ‹‹#ኢራንቡቴ_ጥምቀተ_ባሕር›› #በአዲስ_አበባ_የጃንሆይ_ሜዳ_ (ጃንሜዳ) #በአዲስ_አበባ_የእንጦጦ_ማርያምና_ቅዱስ_ራጕኤል_ታቦት_ማደሪያ #ኀሙስ_ገበያ_ሜዳ ዐበይቶቹ ናቸው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ #በዓለ_ጥምቀት #Holy_Ephipany

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ #በዓለ_ጥምቀት #Holy_Ephipany

በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ #አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ ፠ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹#ባሕረ_ጥምቀት(#ጥምቀተ_ባሕር_››) (#የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡ #ሥርዐተ_ከተራ ፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡ ፠ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ *ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ *የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤ *መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ *እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ *ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ *የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ *ሕዝቡም ደግሞ ‹‹#ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ›› እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ የጀብዱነት ሽልማት ያለው በሽልማቱ አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ **ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (#የምራት_ባለተረኛ) “#ወረደ_ወልድ_እምሰማያት_ውስተ_ምጥምቃት_፤ #በፍሥሓ_ወበሰላም” (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው #ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹#አንሺዎች_›› ይባላሉ፡፡ የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዐት ነው፡፡ በዚያን ዕለት ምሽት ፈቃደኛ የሆኑ ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ ባልቴቶችና ኮረዳዎች ሕፃናትም ጭምር እዚያው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ስለሚያድሩ እንደ የዕድሜ ደረጃቸው ማለትም በልጅነት ዕድሜ ላይ ያሉት በሀገር ባህል ዜማ ሲያመሰግኑ ፥ እናቶችም ታቦቱን የሚያሞግስ ግጥም እየገጠሙ ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ በከተሞች ደግሞ ስበከተ ወንጌልና መዝሙር ሲዘመር ያድራል፡፡ #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤ #ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ #ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ #ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ #ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ #ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/ #ጥምቀቱ_የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡ ትም በልጅነት ዕድሜ ላይ ያሉት በሀገር ባህል ዜማ ሲያመሰግኑ ፥ እናቶችም ታቦቱን የሚያሞግስ ግጥም እየገጠሙ ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡ በከተሞች ደግሞ ስበከተ ወንጌልና መዝሙር ሲዘመር ያድራል፡፡ #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤ #ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ #ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ #ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ #ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ #ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/ #ጥምቀቱ_የሞቱ፤ አርአያ፤ የመቃብሩ አምሳል ነው፡

#ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር #ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ? #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት #ሥርዐተ_ከተራ ……. (#ያንብቡ) #ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡ #ከተራ_ለምን_ተባለ? በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ #ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ #አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ #አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡ ፠ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹#ባሕረ_ጥምቀት(#ጥምቀተ_ባሕር_››) (#የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡ #ሥርዐተ_ከተራ ፠ ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡ ፠ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜ፤ *ባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡ *የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን፤ *መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡ *እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡ *ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጽናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ደባትር ሃሌታ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡ *የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡ *ሕዝቡም ደግሞ ‹‹#ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ›› እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥ የጀብዱነት ሽልማት ያለው በሽልማቱ አጊጦ፥ ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡ **ነገር ግን ሴቶችና ልጆች እንደፈለጋቸው ከፊትም ከኋላም ሆነው ይሄዳሉ፡፡ ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ የዓመቱ #ተረኛ_ደብር (#የምራት_ባለተረኛ) “#ወረደ_ወልድ_እምሰማያት_ውስተ_ምጥምቃት_፤ #በፍሥሓ_ወበሰላም” (እግዚአብሔር ወልድ በሰላምና በደስታ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከሰማያት ወደ መጠመቂያው ወረደ) የሚለው #ሰላም ተመርቶ በአግባቡ ከተለዘበ በኋላ ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡ በክብረ በዓሉ ላይ ግሱን ለመቃኘትና ለማሸብሸብ፣ ማኅሌት ለመቆም፣ ቅዳሴ ለመቀደስና ሌላውንም ሥርዐት ለመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው ተረኛ ደብር (የምራት ባለተረኞች) ሲሆኑ ለቀጣዩ (ለከርሞ) ዓመት ተረኞች የሚሆኑና በአሁኑ ዓመት የምራት ባለተረኞችን የሚረዱት ገዳማትና አድባራት ደግሞ ‹‹#አንሺዎች_›› ይባላሉ፡፡ የከተራ ዕለት የየአጥቢያው ሕዝብ በየዓመቱ ተራ እየገባ ራት ከየአካባቢው ስለሚያመጣ ያ ሲበላና ሲጠጣ ከቆየ በኋላ ወዲያው የሌሊቱ ጸሎት(ስብሐተ ማኅሌቱ) በተረኛው ደብር ካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራል (እንደ ቀጨኔ ባሉ ታላላቅና የሊቃውንት መፍለቂያ አድባራት ተረኛ ቢሆኑም /በጥምቀተ ባሕሩና በቤተ ክርስቲያናቸው ጭምር/ ባይሆኑም በቤተ ክርስቲያናቸው ማኅሌቱን ቆመውና ቅዳሴውን ቀድሰው ያድራሉ)፡፡ ቅዳሴው የሚቀደሰው ከሌሊቱ 7-9 ሰዐት ነው፡፡ በዚያን ዕለት ምሽት ፈቃደኛ የሆኑ ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ ባልቴቶችና ኮረዳዎች ሕፃናትም ጭምር እዚያው በጥምቀተ ባሕሩ ዙሪያ ስለሚያድሩ እንደ የዕድሜ ደረጃቸው ማለ#ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር #ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ? #በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት #ሥርዐተ_ከተራ ……. (#ያንብቡ) #ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡ #ከተራ_ለምን_ተባለ? በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተክላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ

ꔰበ1959 ዓ.ም የተወሰደ (የተነሳ) ፎቶ ፤ ꔰ ꔰ ꔰአነ ውእቱ ኖላዊ ሔር ꔰ ꔰ ꔰ መድኀኔዓለም ዘደብረሰላም ꔰጥምቀት ሲመጣ ትዝ የሚለን በፎቶ የምትመለከቱት ይህ የደብራችን መለያ የሆነው የጥልፍ ሥዕል ፤ 57 ዓመታትን አገልግሎናል ፡፡ #ፎቶውን ላጋሩን ለ፤ ሂስትሪክ ኢትዮጵያ ትሩ ካሜራ ሌንስን እጅግ አድርገን እናመሰግናልን ፤ ፎቶውን መረጃ ያደረገው ‹‹ National Library of Australia›› ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #ክብረ_በዓላት #Feast_of_the_lord #በዓለ_እግዚእነ #በዓለ_ጥምቀት #Holy_Ephipany