es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 049 suscriptores, ocupando la posición 5 274 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 238 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 049 suscriptores.

Según los últimos datos del 30 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 511, y en las últimas 24 horas de 3, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 23.32%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.33% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 742 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 658 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 29.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 31 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 049
Suscriptores
+324 horas
+1077 días
+51130 días
Archivo de publicaciones
መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት #‹‹እኔ በሕመም የምሠቃይ በሽተኛ ነኝና አቤቱ ይቅር በለኝ!፤ #አጥንቶቼም ታውከዋልና ፈውሰኝ፤ ከዚህ የተነሣ ነፍሴ እጅግ ተጨነቀች››፡፡ አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱንና ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18 በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡- ፨ በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡ ፨ ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡ ፨ መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ 38 ዓመታት መጽናት እንጂ ስሙ አይደለም፡፡ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡ ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡ አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡ በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡ በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9 የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13 ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡ የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡ ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ /ምንጭ፦ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 5 አንድምታ/ ፨፨፨ወስብሐት ለእግዚአብሔር፨፨፨

መሐሮሙ እግዚኦ ለአግብርቲከ ወለአእማቲከ እለ ሆሩ ኀበ ሀገረ ኬንያ በንሥረ ሠረገላ ዘአእረፉ በሃገረ ቱሉ ፎራ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንና ምዕመናኗ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝቦች እንዲህ ናቸው ሐዘንና በጋራ የሚያዝኑ፤ ልቅሶን አብረው የሚያጽናኑ፡፡ 'የሞተ ሰውስ አረፈ ነገር ግን ነፍሱ ታርፍ ዘንድ መታሰቢያውን አውጣለት’ /ሢራክ 38 ፥ 3/

የሰው ጭንቅላቱ ትግሬ፥ አንገቱ ዐማራ፥ ወገቡ ኦሮሞ፥ ክንዶቹ ጉራጌ፥ እግሩ ደቡብ፥ ዐይኑ ቤንሻንጉል ፥ ታፋው ሺናሻ፥ ደረቱ ሱማሌ፥ ታፋው ቅማንት፥ ትከሻው አፋር፥ ክርኖቹ አገው፥ …….. ቢሆኑ፤ ሁሉም አካላት ካልተባበሩና ካልተናበቡ ሰው ሊሆንና ሊባል እንደማይችል ሁሉ፤ በኢትዮጵያ የምንገኝ ከ80 በላይ ቋንቋ የምንናገር ካልተደማመጥንና ካልተናበብን ኢትዮጵያ አንሆንም፥ አንባልምም፡፡ የዘረኝነት ጭቅቅትና ቆሻሻ የሚለቀውና የሚወገደው በጾምና በጸሎት ነው፡፡ /በ06/07/2011ዓ.ም. ከተካሄደ የከዐርብ ጕባኤ የተወሰደ/ #1123ኛ_ሳምንት_የዐርብ_ጕባኤ_በተለመደው_ሰዐት_ዛሬ_ መጋቢት_13_ይቀጥላል፡፡ ** የሰው በርካታ አካላት አሉት (212 አጥንቶች፤ 600አካቢ የሥጋ ክፍሎች /Mussels/ ፤ እጅግ በጣም ብዙ ነርቮች፤ ሌሎችም ብዙ የብዙ ብዙ የሰውነት አካላት ያሉት ነው፤ ከዕለታት አንድ ቀን ሁሉም እኔ እበልጥ ፥ እኔ እበልጥ /ነፋስ ማስተንፈሻን ከነመፈጠሯም ረስተዋት/ ሲፎካከሩ እርሷ ግን ዝም ብላ ቆየች፤ ጭቅጭቁና ንትርኩ እያገረሸና እየበሳበት ሄደ እንጂ መፍትሔ አለመምጣቱን ያየችው የነፋስ መውጫ ቀዳዳም ትዕግትስቷን ስለተፈታተኑት ነፋስ እንዳይወጣ ከለከለች፤ በዚህ ጊዜ ሁሉንም ጭንቅ ያዘው፤ እንኳን ሊጨቃጨቅ ለራሱ ሕልውናም የሚያሰጋው ሆነና ጭቅጭቁን ትቶ ማሪን አስተንፍሺን፥ ተጨንቀን ልንሞት ነው፤ እንስማማለን፤ ተስማምተንም እንደማመጣለን አሉ፤ …. እርሷም ከልባቸው እስኪመለሱ ትምህርት ሰጥታ ይቅር አለቻቸው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ከ80 በላይ ቋንቋ ተናጋሪዎችም ከእነዚህ የሰውነት ክፍሎቻችን ትምህርት ወስደን መደማመጥና መናበብ ከምንጊዜውም በላይ ያስፈልገናል፡፡

የኢትዮጵያን ምሥጢራት ከጥራዝ እስከ ጥራዝ ያጠኑት፤ ከልጅነት /ከ7 ዓመታቸው/ እስከ እውቀት በታላቁ ገዳማችን ገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ያደጉት ፥ የተማሩትና የመነኮሱት፥ በዋልድባ ያሉ በርካታ ምሥጢራትን የቀሰሙት፤ .... ኀዋላ ምስካዬ ኅዙናን ገዳምን ለበርካታ ዓመታት ያስተዳደሩት፤ ወደ ውጭ በመውጣት የPHD ትምህርት የተማሩት፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የቅርስ ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት፤ ፫ት መጻሕፍትን የከተቡት ምሁሩና ሊቁ ፥ ተመራማሪውና ተጠያቂ የኾኑት አባት አባ ተሥፋ ሥላሴ ሞገስ አርፈዋል፤ ቀብራቸውም ዛሬ መጋቢት ፲፪ ፳፻፲፩ ዓ.ም. በደብረ ዘይት ሂዲ ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከ፱ - ፲ ሰዐት ይፈጸማል፨ ወተቀወልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ (ሂዲ ካህን መልከ ጼዴቅ)፤ አብዕዎ ተሥፋ ሥላሴ፨

አንብብዋ ለዛቲ ጦማር እምጥንታ፥ እስከ ተፍጻሜታ፤ በትዕግስት (ይህችን ጽሑፍ በትዕግስት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አንብቧት)፤ ብዙ ጥቅም ታገኙበታላችሁና፡፡ #ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፲፩_ #ሰይጣን_በውኃ_ምንጮች_ለምን_እንደሚያድር፤ #ነገሥታት_መኳንንትንና_መሣፍንትን_በምን_እንደሚፈትናቸው፡፡ #ጳጳሳትንና_መነኰሳትን_በምን_እንደሚፈትናቸው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በውሃ ምንጮች እንደምታድሩ ሰዎች የሚናገሩት እውነት ነውን? አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ አዎ እውነት ነው አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ የምታድሩት በምን ምክንያት ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ የፈጣሪያቸውን ሕጉንና ትእዛዙን ቢያፈርሱና ስሙንም ባይጠሩ፥ የእኛን ፈቃድ ቢፈጽሙ፥ በስማችን ጠርተው ቢያመልኩን ነው እንጂ፤ በመልካም ምግባር ሆነው በፍጹም ሃይማኖት የእግዚአብሔርን ስም ቢጠሩ ኃይል የለንም፡፡ #እኛ_ብዙ_ዓይነት_በሽታን_አእምሮ_ማጣትን_እብደትን_እናመጣለን፡፡ #ሰውን_ባሳመምነው_ጊዜ_ሄዶ_በእኛ_ስም_ሲጠመቅ_ከበሽታው_ይድናል፡፡ #በዚህም_ስመ_ክርስትናው_ትጠፋለች፡፡ #ሰዎች_የታመመው_ሲድን_ባዩና_በሰሙ_ጊዜ_እኛን_ያመልካሉ፡፡ #ባላወቋት_መንገድ_አሳስተን_እናጠፋቸዋለን፡፡ #መንፈሳውያንን_መንፈሳዊ_በማስመሰል_እናጠምዳቸዋለን፡፡ #መንፈሳዊ_በሚመስል_ነገር_የተጠመዱ_ከእኛ_አያመልጡም_አለው፡፡ /ማቴ.፯፥፲፭፤ ፳፬፥፲፩/ አባ ጳውሊ፤ አስቀድመህ ለነገሥታት፥ ለመኳንንት፥ ለስልጣናት፥ ለታላላቆቹ ለመሳፍንት፥ ለሊቃውንት አልቅስ ያልከኝ ስለምንድን ነው አለው፡፡ ሰይጣን፤ ሹመታቸው ታላቅ እንደመሆኑ ኃጢአታቸውም ብዙ ነውና፡፡ በሹመት ራስን ከፍ ማድረግን፥ ውዳሴ ከንቱን፥ ትምክሕትን፥ ትዕቢትን እናመጣባቸዋለንና፡፡ መሻርን መድከምን ሞትን እንዳያስቡ እናደርጋቸዋለንና፡፡ ቀናውን ፍርድ ትተው በመማለጃና በአድልዎ እንዲፈርዱ፤ የማስተዋል አእምሯቸውን እናጠፋዋለንና፡፡ እውነተኛውን ፍርድንና ቀናውን መንገድ ይተዋሉ ፤ ስለዚህ ዘወትር ድሆችን፥ ደካሞችን ያስለቅሳሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ፈቃድ እናርቃቸዋለን ፤ ስሙን እንዳይጠሩ እናደርጋቸዋለን ፤ ትምክሕትን፥ ትዕቢትን፥ ገንዘብ መውደድን በልባቸው እናሳድርባቸዋለን፡፡ በዚህ ምክንያት ጦርነት አሥነስተው እርስ በርሳቸው ይጋደላሉ ፤ የእነርሱ መከራ ለታላቁም ለታናሹም ለሀገሩ ሁሉ ይተርፋል፡፡ በኃጢአታቸውም ይጠፋሉ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተ የተረገምክ፤ በሊቃነ ጳጳሳት ፥ በጳጳሳት ፥ በኤጲስ ቆጶሳትስ ላይ ምን ምክንያት አግኝተህ ትዋጋቸዋለህ አለው፡፡ ሰይጣን፤ ከሁሉ አብልጠው ብርን ፥ ወርቅን ፥ ገንዘብን እንዲወዱ አደርጋቸዋለሁ፡፡ #ለማይገባው ሥልጣነ ክህነትንም በገንዘብ እንዲሰጡ ፤ ለነዳያን ለድሆች እንዳያዝኑ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ለሌላው የሚያስተምሩትን የሕጋቸውን ጎዳና እንዳያስተውሉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ዘወትር ኃላፊውን የምድር ተድላ ደስታ እንዲያስቡ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ጠብን ፥ ጥላቻን በልቡናቸው አሳድራለሁ ፤ አንዱ ጓደኛውን በቅናት እንዲከሰው አደርጋለሁ፡፡ #ለጸሎትም በቆሙ ጊዜ ጠባቸውን እንዲያስቡ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ቂማቸውን እንዳይረሷዋትም አንዱ ባልንጀራውን እንዲረግም አደርጋቸዋለሁ፡፡ #ኃላፊውን ገንዘብ ለመሰብሰብ እንዲተጉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት እኔ የማሳያቸውን የልብስ ዓይነት የልብስ ይለብሳሉ፡፡ ዳግመኛም በገዳም የሚኖሩትን መነኮሳት አብልጬ እጣላቸዋለሁ፤ የኅሊና ጦር አመጣባቸዋለሁ፡፡ #ከእንቅልፍ_በነቁ_ሰዓት_ወይም_ለጸሎት_ሲነሡ_የውዳሴ ከንቱና የቅንዓት የትምክሕት ሐሳቦችን አመጣባቸዋለሁ፡፡ ድካማቸውን ከንቱ አደርጋለሁ፡፡ በጾማቸውና በተጋድሏቸው እንዳይጠቀሙ አደርጋቸዋለሁ፡፡ #በበአታቸው_በአንድ_ቦታ_እንዳይጸኑ_አደርጋቸዋለሁ፡፡ በሥራ ላይ ያሉትንም ሥራቸውን እንዲያመልኩና እኔ እበልጣለሁ እንዲሉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ በዚህ ሥራቸው ትቢትን ፥ ትምክሕትን ፥ ውዳሴ ከንቱ አመጣባቸዋለሁ፡፡ #የዚህ_ዓለም_ተድላና_ደስታ_እንዲወዱ በማድረግ እዋጋቸዋለሁ፡፡ #የውሸት_ሕልም_በማሳየት አሳስታቸዋለሁ፡፡ #የመምህሮቻቸውን_ትእዛዝ_እንዳይቀበሉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ከልባቸው ትሕትናንና ታዛዥነትን የምትጠቅም#የአበውን_ምክር_መስማትን_አጠፋባቸዋለሁ፡፡ እንደ መቃብር በውጫዊ እይታቸው ያማሩ በውስጣቸው ግን ኃጢአትን ርኵሰትን የተሞሉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ አንድ ስንኳ ሳላስቀር ከእግዚአብሔር ቸርነት ፈጽሜ እስከ ማርቃቸው ድረስ ባለኝ ዐቅሜ ሁሉ እዋጋቸዋለሁ፡፡ እነሆ የጠየቅኸኝን ክፉ የሆነች የማሳት ምስጢሬንና የክፋት ሥራዬን ሁሉ ምንም ሳልደብቅህ ያለ ፈቃዴ ነገርሁህ አለው፡፡ #ቅዱሳን ሰይጣንን እንደሚያዙት፤ ቀሲስ አባ ጳውሊ የሰይጣንን ምሥጢር ስላውጣጣው እንዳይተናኰሉት ስለመጠየቁና የነገሩት እውነት መሆኑን፤ የነገሩትም ወደፊት እንደሚፈጸምና በጽሑፍ እንዲቀመጥ ማድረጉን…….. ክፍል ፲፪.… ይቀጥላል ነገ ዐርብ ይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

ከማኅሌት እስከ ሠርክ ጕባኤ፤ መስቀለ ኢየሱስ፤ መጋቢት 10 በደብራችን ይህንን ይመስላል፤ ከአዲስ አበባ ውጭና ከኢትዮጵያ ውጭ ላላችሁና በመንፈስ በዓሉን ላስታወሳችሁ፤ በአካል ላልተገኛችሁ እንዲሆን ነው፡፡

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፲_ #ሰይጣን ያልበደሉትን ሰዎች ለምን እንደሚፈትናቸው፤ በኋላኛው ዘመን ደጋግ ነገሥታትና መኳንንት፤ ንጹሐን ካህናት ፥ ሊቃውንትና መምህራን ፤ ጳጳሳትና ቆሞሳት እንደሚታጡ፤ መነኰሳትም የሰይጣን ወዳጅ እንደሚሆኑና ይህን ለማራቅ መጸለይ እንደሚገባ፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተን ያልበደሉህን ሰዎች እንዲህ የምታደርገው ለምንድን ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ሃይማኖታቸው የቀና፥ ሥነ ምግባራቸው ያማረ ስለሆነ እንቀናባቸዋለን፡፡ ስለዚህ አሕዛብ ክፉ ሥራቸውን አይተው ሃይማኖታቸውን እንዲነቅፏት ለማድረግ ነው አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ከሕይወትና ከመልካም ሥራ የተለየህ ክፉ ባላጋራ፤ ኀጢአት በእነርሱ ላይ ከወዴት ትመጣለች? የዓመፅ መገኛ፥ የኃጢአት መኖሪያ፥ የጽድቅ ጠላት አንተ ነህ እንጂ አለው፡፡ /ዮሐ.፰፥፵፫/ ዲያብሎስ፤ የዓመፅና የክፋት ሁሉ መገኛ ብሆንም፤ የኀጢአት ፈጻሚዋ እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ #የማቀርብላቸውን_የክፋት_ሥራ_ካልተቀበሉኝ_እነርሱን_በኃይል_ማስገደድ_አይቻለኝም፡፡ ነገር ግን በብዙ ዘዴና ተንኮል ሥራዬን እንዲቀበሉ አቀርብላቸዋለሁ፡፡ #ለመልካም_ሥራ_መንፈሳዊና_አስተዋይ_ካልሆኑ የክፋት ሥራዬን ሳይመረምሩ ይቀበሉኛል፡፡ እነርሱን ለማሳት አመች ጊዜና ወቅት ሳገኝ ከመልካም ሥራ ሁሉ አርቃቸዋለሁ፡፡ በክፉ ሥራ ፈጽሜ እገዛቸዋለሁ፡፡ ለእያንዳንዳቸው በመካከላቸው ዘወትር ጠብ፥ ክርክር ይሆናል፡፡ የነፍሳቸውንና የሥጋቸውን ረብ ጥቅም አጠፋለሁ፡፡ ቃሌን ትእዛዜን አንቀበልም ብለው ቢያሸንፉኝ #በትንሽ_ኃጢአት_እቀርባቸዋለሁ፡፡ በልቡናቸው ሐሜትን፥ ነቀፋን አሳድርባቸዋለሁ፡፡ በመሥዋዕቱ ፊት በቤተ መቅደስ የማይገባ ሥራ እንዲሠሩና እንዲናገሩ አደርጋቸዋለሁ፡፡ በክፉ ሥራቸው ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ዳግመኛ #ሕዝቡ_ቀሳውስቱንና_ካህናቱን_ሊቃውንቱንም_እንዲነቅፉ_አደርጋለሁ፡፡ ሁላቸውንም ከጽድቅ ሥራ ሰንፈው ለኃጢአት ሥራ እንዲተጉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ንስሐ እንዳይገቡ በውስጣቸው ፍርሐትን ፥ ትምክሕትን ፥ ስንፍናን አሳድርባቸዋለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት የወንድሞቻቸውን ኀጢአት እንጂ የራሳቸውን ኀጢአት አይናዘዙም፡፡ በዚህ ምክንያት ለበደላቸው ስርየት የለውም፡፡ ከኀጢአት እንዳይርቁ በእነርሱ ላይ የማላመጣው ምክንያት የለም፡፡ ምክሬን ከሰሙኝ ፈጽሜ የክርስቶስን ጸጋ አሳጣቸዋለሁ አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ይህንን ሰምቶ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ሰይጣንም፤ አባ ጳውሊ ሲያለቅስ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ይስቅበትም ጀመር፡፡ እንደ አንተ ካህናት ናቸውና ስለ እነርሱ ታለቅሳለህን አለው፡፡ በእውነቱ ማልቀስ ከወደድክ ስለ ደጋግ ነገሥታትና ስልጣናት ፥ ስለ መኳንንትና ስለ ሊቃውንት ፥ ስለ መሳፍንትና ስለ ገዢዎች መታጣት ፊትህን ጸፍተህ አልቅስ፡፡ ዳግመኛም ስለ ንጹሐን ሊቃነ ጳጳሳትና ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ፥ ስለ ቆሞሳትና ስለ ሁሉም ደጋግ ንጹሐን ካህናት መታጣት አልቅስ፡፡ አብዝተህም ስለ ቤተክርስቲያንና ስለ ገዳማት አልቅስ፡፡ ይልቁንም በገዳማት ስለሚኖሩ ስለወንድሞችህ መነኰሳትና ስለ እኅቶችህ መነኰሳይያት ፈጽመህ አልቅስ፡፡ #በኋላ_ዘመን_ዘመዶቼና_ወዳጆቼ_አደርጋቸዋለሁና_አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ በምን ሥራ እንዲህ ታደርጋቸዋለህ? አለው፡፡ ሰይጣንም፤ እነርሱ ራሳቸው በፈቃዳቸው ጎዳናዬን ሁሉ ይከተላሉና ፤ ፈቃዴንም ይፈጽማሉና ፤ የማሳስባቸውን ይሠራሉና ፤ ቃሌን አይተላለፉምና ፤ መዐዛዬንም ይወዳሉና ነው አለው፡፡ ቅዱስ አባ ጳውሊ፤ ይህንን የሰይጣን ነገር በሰማ ጊዜ ታላቅ ሐዘን አዘነ፡፡ ያን ጊዜ ሰይጣንን እንዲህ አለው፡፡ አንተ የተረገምህ ክፉ ርኩስ እነሆ! ሌላ የክፋትህን ምክንያት እጠይቅሃለሁና እንዳትሸሽገኝ እምልሐለሁ አለው፡፡ ሰይጣን፤ ታላቅና ኃያል በሆነ ፤ ብርሃንን በፈጠረ በእርሱ ማልኩ፡፡ ከአንተ ምስጢሬን ልሸሽግ ብወድም አልቻልኩም፡፡ ምንም ፈጽሞ ልዋሽህ ስልጣን የለኝምና የምትጠይቀኝ ምንድን ነው? አለው፡፡ #ሰይጣን በውኃ ምንጮች ለምን እንደሚያድርና ነገሥታት፥ መኳንንትንና መሣፍንትን በምን እንደሚፈትናቸው… ክፍል ፲፩.… ይቀጥላል ረቡዕ ይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/

እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ፤ በመጋቢት 10 በመስቀለ ኢየሱስ ክብረ በዓል ላይ ከንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ጀምሮ በአዲስ አበባ በብቸኝነት ክብረ በዓሉ በሚከበረው በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም እንገናኝ፡፡ (በነገራችን ላይ በዚህ ደብር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አገልጋይ ካህናቱ የመድኀኔ ዓለምና የመስቀል አገልጋይ ካህናት ተብለው በ2ት የተመደቡና የመስቀል አገልጋይ ካህናትን ደመወዝ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሚከፍለው ቤተ መንገሥት ነበር፡፡) በከሰዓት በዋይዜማው፤ በሠርክ፤ በሠርክ ጕባኤ ማታ በማኅሌቱ፤ ሌሊት በሰዐታቱ፤ ንጋት ላይ በኪዳኑ፤ ረፋድ ላይ በዑደተ ታቦተ ሕጉ፤ በ6 ሰዐት በቅዳሴው፡፡ በመስቀለ ኢየሱስ ክብረ በዓል ላይ እንገናኝ፡፡ ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀል ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት፡፡›› በቀራንዮ መካን አይሁድ የቀበሩት የሕይወት የመድኒት መስቀል ነው፡፡

ምኵራብ፤ ሦስተኛው ሳምንት ሦስተኛ ሳምንት ምኵራብ ይባላል፡፡ ጌታ በምኵራብ ማስተማሩን የሚዘከርበት ሳምንት ሲሆን ‹‹ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ›› የሚልና ይህን የመሰለ ጌታ በምኩራብ ማስተማሩን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን በኢሩሳሌም የአይሁድ ቤተመቅደስ ነበራቸው፡፡ ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተመቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሰሩ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ ሐዋርያት በሚያስተምሩበት ወቅት ከአንዳንድ ቦታዎች በቀር በምኵራቦች ገብተው ወንጌልን አስተምረዋል፡፡ በብሉይ ዘመን ቢያንስ ዐስር የጎለመሱ ወንዶች (የቤተሰብ ኃላፊዎች) በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመስራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ዋናው ቤተ መቅደሱ ያለው በኢየሩሳሌም ብቻ ነበር፡፡ በምኵራብ ውስጥም የኦሪት የሕግ መጻሕፍትና በቅዱሳን ነቢያት የተጻፉ ጽሑፎች በብራና ጥቅልል ይገኛሉ፡፡ ምዕመኑ እንዲሰማቸው እንደ መድረክ ባለ ቦታ ላይ ካህናትና መምህራን ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር፡፡ በኦሪቱ ምኵራብን የሚመሩት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሲገኝ፤ በመግረፍ ወይም ከምኵራብ በማስወጣት ሊቀጡ ስልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር ጥቅሎችን በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትዕዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡ በየሰንበቱ ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስበው አምልኮታቸውን ይፈጸሙ ነበር፤ በአምልኮታቸው ውስጥም ጸሎት፤ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፤ ስብከትና ቡራኬ ነበር፡፡ በዚህ በምኩራብ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰንበት ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፤ ሕሙማንን ፋውሷል፡፡ የኢሳይያስን መጽሐፍ ምዕራፍ ፷፩ን አንብቧል፡፡ በዚህ በዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት(ምኵራብ) የሚታሰበውም ይህ ነው፡፡ ፨ ‹‹ወደ አደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሳ፡፡›› ሉቃ. 4፥16 ፨ ‹‹ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር፡፡›› ማቴ. 13፥52 ፨ ‹‹ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፡፡››ማር 6፥1 ፨ በዕለቱ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡ ምንባባትም፤ ጌታችን ቤተ መቅደሱን የንግድ ማዕከል ያደረጉትን ዓይቶና አዝኖ ነጋዴዎቹን ከነመንጋቸው በጅራፍ እንዳስወጣቸውና ‹‹ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን እኔ እሠራዋለሁ፡፡›› ብሎ ስለመ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ማስተማሩን የሚገልጽ ነው፡፡ ፨፨፨ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፨፨፨ በዕለቱ ሌሊት የሚባለውን መዝሙር፤ ጠዋት በቅዳሴ የሚነበቡትን ምንባባት፥ የሚሰበከውን ምስባክ (መዝሙረ ዳዊት)፥ የሚነበበውን ወንጌል፥ የየትኛው ቅዳሴ እንደሚቀደስ አቅርበንላችኀዋል፨