es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Ir al canal en Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

El canal Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 16 049 suscriptores, ocupando la posición 5 274 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 238 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 16 049 suscriptores.

Según los últimos datos del 30 octubre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 511, y en las últimas 24 horas de 3, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 23.32%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 10.33% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 3 742 visualizaciones. En el primer día suele acumular 1 658 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 29.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 31 octubre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.

16 049
Suscriptores
+324 horas
+1077 días
+51130 días
Archivo de publicaciones
አንኳን ለመስቀለ ኢየሱስ መጋቢት 10 በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ (ይህንን ያውቃሉ????? በአዲስ አበባ በብቸኝነት ከቀድሞ ጀምሮ የመስቀለ ኢየሱስ በዓል በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ክብረ በዓሉ እንደሚከበር፡፡ በዚሁ ደብር በቀደሙት ዘመናት አገልጋዮች የመድኀኔ ዓለምና የመስቀል አገልጋዮች ተብለው በሁለት ምድብ የሚያገለግሉ አገልጋዮች የነበሩ መኾኑን ፤ ** የመስቀል አገልጋይ ካህናት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ደመወዛቸው ከቤተ መንግሥት እንደሚከፈላቸው፤ ….) በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀል ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት፡፡ (የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም የቤቱ የመስቀል ወረብ) በሃገራችን ኢትዮጵያ መስቀልን በሚመለከት ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የደመራ መስቀል በዓል /መስከረም 16ና 17/ እንዲሁም መጋቢት 10 የመስቀለ ኢየሱስ በዓል ተያያዥነት ያላቸውና ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከጌታችን ሞትና ትንሣኤ በኋላ በቀራንዮ አደባባይ ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ጌታችንን የገነዙት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከቀራንዮ ወደ ጎልጎታ (ጌታችን ተቀብሮባት ወደነበረው መካነ መቃብር) ወስደው አኑረውታል፡፡ አበው ሐዋርያት ወደየሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱ የኢየሩሳሌሙ ጳጳስ ሐዋርያው ያዕቆብ በኃላፊነት እንዲጠብቀው አድርገዋል፤ ከየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱም በእግረ መስቀሉ ሥር እየተሰበሰቡ ይጸልዩ ነበር፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ጠዋትና ማታ በመስቀሉ ሥር ትጸልይ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች ታሪኩንና ቦታውን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን ክቡር መስቀሉን ለማየት ያመኑትም በረከት ለማግኘት ከየአቅጣጫው ይመጡ ነበር፡፡ በመስቀሉ ተዓምራት ብዙዎች ከተለያዩ ደዌ /በሽታ/ ተፈውሰዋል፡፡ ይህም በጣም ብዙ ሰዎች ክርስቶስን ወደ ማመን ስቧቸዋል፡፡ ይህን ድንቅ ሥራ የተመለከቱ የክርስቶስ ሰቃዮች /ሰቃልያነ ክርስቶስ/ በሁኔታው ባለመደሰታቸው ሕይወት የሆነውን የጌታ መስቀሉን ከጎልጎታ አንስተው ቀብረውት ለ300 ዓመታት ያህል የከተማው ጉድፍና ጥራጊ እየጣሉበት የተቀበረበት ቦታ ኮረብታ እስኪሆን ድረስ ቆይቷል ‹‹በቀራንዮ መካን ዘደፈኑ አይሁድ፤ መስቀልከ ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ መድኀኒት›› እንዲል፡፡ ሆኖም በ4ኛው መ/ክ/ዘመን ለክርስቲያኖች ነፃነት የሚያስብና የሚያስከብር ንጉሥ በሮም ተነሣ፡፡ የንጉሡም ስም ቈስጠንጢኖስ ይባል ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ይበልጥ እንዲወድ ያደረገው በጠላቱ በማክሴንዲዩስ (መክስምያኖስ) ላይ በዘመተበት ጊዜ ገና በጉዞ ላይ እያለ ‹‹በዝንተ ትእምርተ መስቀል ትመውዕ ፀርከ (በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ)›› የሚል በመስቀለኛ ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ በጠፈር ሰማይ አይቶ በመስቀል ምልክት ድል በማድረጉ ነው፡፡ የንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ የመስቀሉ ፍቅር ያደረባት፥ ታሪኩ በውስጧ የሰረጸባት ቅድስት እናት ነበረች ቈስጠንጢኖስም በዘመነ መንግሥቱ በትዕምርተ መስቀል ብዙ የድል ሥራ ስለሠራ ለመስቀሉ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት ነበረው፡፡ ንግሥት እሌኒም መስቀሉን ለማግኘት ሰው ብትጠይቅ የሚያውቅ አላገኘችም፡፡ በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ በመሆኑ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊና መቃርስ የሚባል ኤጲስ ቆጶስ አገኘች፡፡ ከእነዚህም አረጋዊው ኪራኮስ ዕድሜው የሸመገለና በእስራኤል ባህልና ደንብ ያደገ ነበር፡፡ እሌኒም እሱን ጠይቃ መስቀሉን ለማግኘት እንዲተባበራት ጠየቀችው ሆኖም ሊተባበራት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ረሃብና ጽም ስታበዛበት ግን የረሃብና የጽሙን መጽናት ተመልክቶ ከእነዚህ ከሦስት ተራሮች አንዱ እንደሆነ ነገራት፤ ከሦስቱ ተራራ የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሱባኤ እንድትይዝ ነገራት፤ ሱባኤም ያዘች፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ እንዲህ አላት ‹‹አንቺም ሰውም በከንቱ አትድከሙ እንጨት አሰብስበሽ፥ ደመራ አስደምረሽ፥ በእሣት አያይዘሽ፥ በፍሕሙ ላይ ዕጣን አፍስሽ፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን ተመልክተሽ ጢሱ ያረፈበትን ቦታ አስቆፍሪው›› አላት፡፡ እርሷም መልአኩ እንዳላት እንጨት አሰብስባ ደመራ አስደመረች ዕጣንም አፈሰሰችበት ጭሱም ሰማይ ደርሶ ወደ ምድር ሲመለስ ቦታውን አመለከታት ይህም የሆነው መስከረም 16 ቀን ነው፡፡ እኛ ደመራ ብለን የምናከብረው ይህን አብነት በማድረግ ነው፡፡ መስከረም 17 ቀን ማለትም የደመራ በዓል ማግስት የምናከብረው የመስቀል በዓል ደግሞ ንግሥት እሌኒ ደመራ አስደምራ እጣን አጢሳ (አስጢሳ) የመስቀሉን ቦታ ካወቀች በኋላ ቁፋሮውን ያስጀመረችበት ዕለት ስለሆነ ነው፡፡ ከቁፋሮውም በኋላ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ዳግመኛ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በእሌኒ ተነሳሽነት፤ በረዳቶቿ አጋዥነት ቁፋሮ በተጀምረ ከ5 ወር ከ23 ቀን በኋላ መስቀሉ መጋቢት 10 ተገኝቷል፤ ከ10 ዓመት በኋላም ቤተ መቅደሱ ታንጾ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡ መስቀሉም እንደቀድሞ ድውያንን ሲያድን፣ ለምጻምን ሲያነጻ፣ ሽባዎችን ሲያቀና፣ ሙታንን ሲያስነሳ፣ የማያምኑትን ወደ ማመን ሲመልስ ነበር፡፡ ዛሬም የክርስቶስ መስቀል በዓለም እያበራ ሕሙማንን እየፈወሰ ይገኛል፡፡ ይህ የጌታ ዕፀ መስቀልም በዓፄ ዳዊት ዘመን ወደ ሃገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በለያዩ ቅዱሳት መካናት (እንጦጦ ማርያም፣ ጋራ መድኃኔዓለም፣…..) ሲያርፍ ቆይቶ በስተመጨረሻው ‹‹አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል›› ተብሎ ለዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በተነገረው መሠረት በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም በክብር አርፏል፡፡ እኛንም በመስቀሉ ፈዋሽነት ይማረን የመስቀሉን ፍቅር በልባችን ይሳልብን አሜን፡፡ * "መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር: ያድኅነነ እምጸር" /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ * ‹‹ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።›› /ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ገላ.6፥14፣ 1ኛቆሮ.1፥18/ ***** እንደተለመደው ሥርዐተ ማኅሌቱንም አቅርበንላችኋል፡፡ እንደ መድኀኔ ዓለም ፈቃድ በዋይዜማ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታቱ በኪዳኑ፣ በዑደተ ታቦተ ሕጉና በቅዳሴው እንገናኝ፡፡ (ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታሪክ የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት ላይ የተወሰደ) ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

በድጋሚ የምሥራች፡፡ አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል!!፤ የለህም እንዳልል ጠበሉ ይፈልቃል፡፡ በድጋሚ የምሥራች የምሥራች፤ በደብራችን ከዚህ ቀደም 4ት ጠበሎች መፍለቃቸውን ዘግበን ነበር አሁን ደግሞ 5ኛ ጠበል ባለፈው ኀሙስ የካቲት 21 ፈልቋል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ዓይናቸው የበራላቸው ቊጥር ባለፈው ስንዘግብ 3ት ነበሩ አሁን ደግሞ በተጨማሪ 2ት ሰዎች ዓያናቸው በርቷል /አንዱ ወነድማችን ከጎጃም የመጣ ነው፡፡/ አንድ ሰው ከዐልጋ ላይ መነሳት የማይችል ተፈውሷል፡፡ የወገኑ ዓይን ሲበራለት የማይደሰት ማን አለ!!!????፡፡ ቸርነቱን ያላራቀብን ምሕረቱን ያበዛልን በፍቅሩ የጎበኘን የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ይመስገን፡፡ (ፎቶዎቹ፤ በደስታ ብዛት የካቲት 16 በብዚ ሺህዎች ለመጡ ምዕመናን በንፍሮ ውኃና በንፍሮ፤ በዳቦ በእንጀራና በጠላ ሲዘከር፤ ማኅበረ ጎዶልያስ ዝማሬ ሲያቀርቡ) ሲሆን የወደቁት ደግሞ በደቡብ (በጌዲኦ) በግጭት ምክንያት የወደቁ ወንድሞቻችንን ነው፡፡ የጠበሉን ቦታ በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁን፤ ከቀጨኔ መድኀኔ ዓም ቤተ ክርስቲያን በሁለገብ (በበሃ ሰፈር) በኩል ወደ 19ኝ (ሽሮ ሜዳ) መሻገሪያ ድልድዩ ጋር፡፡

እንዳያመልጥዎ ከመጋቢት 9-11 ልዩ ጕባኤ፤ የመስቀለ ኢየሱስ (መጋቢት 10) በአዲስ አበባ በብቸኝነት በሚከበርበት በታላቁ ደብራችን፡፡ ሥርዐተ ማኅሌቱን አስቀድመን ልከንላችኋል፤ እንደ አምላክ ፈቃድ ሁላችንም ከዋይዜማው ጀምሮ በማኅሌቱ፣ በሰርክ ጕባኤ፣ በሰዐታት፣ በኪዳን፣ በዑደተ ታቦተ ሕግና በቅዳሴ እንገናኝ፡፡ /በዕለቱ ማኅሌት ላይ በደብሩ ብቻ የሚባሉትንም ልዩ ልዩ ወረብ በአካል ተገኝተው በማዳመጥ ነፍስዎን ይመግቡ፤ ይመስጡ)

ልዩ ሳምንታዊ የጸሎትና የትምህርት ጕባኤ፡፡ የመሐረነ አብ ጸሎት በዐቢይ ጾም ባካህናት ማዕጠንት ጭምር ይካሄዳል፡፡ ዘወትር ዐርብ ከ11፡45-2፡00ሰዐት፡፡ ሲሳያ ለነፍስ ቃለ እግዚአብሔር፡፡

ልዩ ሳምንታዊ የጸሎትና የትምህርት ጕባኤ፡፡ የመሐረነ አብ ጸሎት በዐቢይ ጾም ባካህናት ማዕጠንት ጭምር ይካሄዳል፡፡ ዘወትር ዐርብ ከ11፡45-2፡00ሰዐት፡፡ ሲሳያ ለነፍስ ቃለ እግዚአብሔር፡፡

ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡ እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓለ_ዕረፍት_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ ላሊበላ፥ ለአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ( ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ተመልሰው ወደ ምድረ ከብድ በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፤ በግብፅ 300ዓመታት፥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ 262ዓመታት (በዋነኛነት በምድረ ከብድና በዝቋላ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን ገዘዛ አቦን መጥቀስ ይቻላል) ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባትም ምድረ ከብድ ገዳም ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከባድ/ ትብለሽ ተጠሪ አላት የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ (ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

ኦ እግዚኦ መሐሮሙ (አዕርፍ) ለነፍሰ አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አዕረፉ አመ አሚሩ ለወርኃ መጋቢት በሃገረ ኢትዮጵያ በአድያሚሃ ለደብረ ዘይት፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፡፡›› /ትንቢተ ኤርሚያስ 3÷7/ ‹‹#ሞት_ትልቅ_መምህር_ነው_የሚያስተውል_ካለ_!!!_፡፡››

ቅድስት፤ ሁለተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡ ‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡ ‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡ ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡ በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡ የዕለተ ሰንበት ክብር፤ በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8 በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡ ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡ ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና›› ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ (የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት)

#ከሰይጣን_ጋር_የተደረገ_ቃለ_ምልልስ (ተዋስኦተ ጳውሊ ምስለ ሰይጣን)፤#ክፍል#፱_ #የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችንን ሕዝቡን (በካህናት አንጻር)፤ ነገሥታት፥ መኳንንትና መሳፍንትን በምን እንደሚፈትናቸው፡፡ አባ ጳውሊ፤ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በምን ሥራ ትዋጋቸዋለህ አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ክፉ ሥራችንን ይዘን ወደ ቤተክርስቲያን እንገባለን፡፡ በካህናት መካከል ጠብን እንፈጥራለን፡፡ ሳቅንና ስላቅን ዋዛ ፈዛዛን እንዲያበዙ እናደርጋለን፡፡ በማሕሌትና በቅዳሴ ጊዜ ኩራትን፥ ትምክህትን፥ ትዕቢትን፥ ማንቀላፋትን፥ #ክፉ ሐሳብን በልባቸው እንዲያሳድሩ፤ የቅዳሴ የማሕሌት አገልግሎታቸውን እንዲተዉ እናደርጋቸዋለን፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ከቤተክርስቲያን እንዲሸሹ፥ እንዳያስቀድሱ፥ ከክብረ ምሥጢራት እንዳይሳተፉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ይኸውም የመጨረሻ ዘለዓለማዊ ክብራቸውና ሕይወታቸው የሆነው የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ አባ ጳውሊ፤ ይህንን የምታደርጉት ለምንድን ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ተስፋ ያደረጓትን መንግሥትና ስርየተ ኃጢአትን እንዳያገኙ ነው፡፡ #በቅዳሴ ጊዜ ኃጢአት የሚሰረይባትና ጸጋ የሚገኝባት ስለሆነ ፥ በሚቀድሱትና በሚያስቀድሱት ሁሉ ላይ ምሕረት ይወርዳልና፡፡ ስለዚህ ስለምንቀናባቸው ጥፋታቸውን እንጠባበቃለን ፣ እንሻለን ፤ ከመልካም ሐሳብ እንዲርቁ እናደርጋለን፡፡ በንጹሕ ልብ ሁነው የሚቀድሱ ካህናትና የሚያስቀድሱ ሁሉ በረከትን እንዳያገኙና የኃጢአት ስርየት እንዳይደረግላቸው እንጥራለን፡፡ በከንቱ ነገር እርስ በርሳቸው እንዲጣሉና በዚህ ምክንያት ቂም በቀል በልቡናቸው እንዲኖር እናደርጋለን፡፡ ተስፋ ያደረግዋትን ዘለዓለማዊ ሕይወትንም እንዲያጡና ሕይወታቸውም ኃጢአትና በደል የተሞላ ፍጻሜያቸውም ገሃነመ እሳት እንዲሆን እናደርጋለን፡፡ በልባቸው ውስጥ ቂምና ቅንዓትን ከአሳደርንባቸው በኋላ በዚህ ምክንያት ሥጋውንና ደሙንም እንዳይቀበሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ዘወትር በዚህ ምክንያት የኃጢአታቸውን ስርየት አያገኙም፡፡ ከእግዚአብሔር ምሕረትና ከዘለዓለም ጸጋና በረከት እናርቃቸዋለን፡፡ ከቤተ ክርስቲያን እንዳይደርሱ እንዳይገቡ የፈጣሪያቸውን ትእዛዝ እንዳይሰሙ እናደርጋቸዋለን፡፡ ዳግመኛም ጸሎታቸው ቁመታቸውና ድካማቸው ከንቱ እንዲሆን ሰዓታትና ማሕሌት በሚቆሙበትና በቅዳሴ ጊዜ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ እንዲዘባበቱ ትምክሕትን ትዝርኅትን በልባቸው እናሳድራለን፡፡ ከካህናትና ከሕዝብ መካከል ክርስትናቸው እንዲሻር እንደ ዓላውያን ሥርዓት በሥራይና በጥንቆላ በውሃ እንዲታጠቡ እናደርጋቸዋለን፡፡ ክፉ ሥራቸውንም መልካም አስመስለን እያሳያቸዋለን፡፡ በውስጣቸው ብዙ ወጥመድ እናስቀምጣለን፡፡ ከአንዲቱ ቢያመልጡ በሌላይቱ እንዲያዙ እናደርጋለን፡፡ በማሕሌት በሰዓታት በቅዳሴ ጊዜ በእውቀት እኔ እበልጣለሁ ፡ እኔ ላመስግን ፡ እኔ ልቀድስ ፡ እኔ ልዘምር ፡ እኔ ላንብብ እንዲሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ በዚህ ምክንያት እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ #ንጽሕና_ሳይኖራቸው_በድፍረት_እንዲያገለግሉ_እናደርጋቸዋለን፡፡ ቅንዓትና ሽንገላ ቂምና ትዕቢት በልባቸው እያለ ቅዳሴ እንዲገቡ እናደርጋለን፡፡ አንዱ በአንዱ ላይ እንዲዘባበትና እንዲታበይ እናደርጋለን፡፡ በክፉ ሥራቸው ያዩአቸውና የሰሙአቸው ሁሉ ተስፋ እንዲቆርጡ እናደርጋለን፡፡ ካህናትና ዲያቆናት ፣ ምዕመናንም በማይጠቅም ነገር እንዲጣሉ እናደርጋቸዋለን አለው፡፡ አባ ጳውሊ፤ አንተን ያልበደሉህን ሰዎች እንዲህ የምታደርገው ለምንድን ነው አለው፡፡ ዲያብሎስ፤ ሃይማኖታቸው የቀና፥ ሥነ ምግባራቸው ያማረ ስለሆነ እንቀናባቸዋለን፡፡ ስለዚህ አሕዛብ ክፉ ሥራቸውን አይተው ሃይማኖታቸውን እንዲነቅፏት ለማድረግ ነው አለው፡፡ #ነገሥታት፥ መኳንንትና መሣፍንትን በምን እንደሚፈትናቸው… ክፍል ፲.… ይቀጥላል ሰኞይጠብቁን/ /#ዋልድባ_ዋሊ_ገጽ/