የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
Ir al canal en Telegram
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Mostrar más2 621
Suscriptores
+124 horas
+227 días
+3830 días
Archivo de publicaciones
6 ቀን ቀረው! #ሆሳዕና_በአርያም
በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወዲያውም ወደ እርስዋ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። (ማር 11:2)
አህያዋ ለተቀደሰ ዓላማ እንደተመረጠች እኛንም እግዚአብሔር ወደ ፅድቁ መንገድ ይጠራናል።
#አቤቱ_እባክህ_አሁን_ አድን!
#ሆሳዕና #PalmSunday
ማስታወቂያ
በሆሳዕና በዓል ዕለት በተለያዩ መስተንግዶ ለማገልገል የተመዘገባችሁና ፈቃደኛ የሆናችሁ፤ ስለ አገልግሎታችን ገለጻና ውይይት ለማድረግ ዛሬ ማክሰኞ ከ11:30 ጀምሮ እንድንገኝ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
መስተንግዶ ክፍል
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
+8
በትላንትናው እለት በእለተ ኒቆዲሞስ መጋቢት 28/2017 ዓ.ም ለበዓለ ሆሳዕና ቅድመ ዝግጅት ከተለያየ ደብር የመጡ ሕጻናት በደብራችን ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ የስዕል ውድድር አከናወኑ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
+9
የሰንበት ትምህርት ቤታችን ፍኖተ ብርሃን በጎ አድራጎት ክፍል ከጥቁር አንበሳ ጊቢ ጉባኤ የህክምና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን በዕለተ ኒቆዲሞስ በደብራችን ውስጥ የህክምና እርዳታ ለሚፈልጉ ምዕመናን የህክምና አገልግሎቱን በነጻ አከናውኗል። ለታመሙት ምህረትን ይላክልን ላገለገሉትም አገልግሎታችሁን ይቀበልልን።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ሃና ለወጉ ወንድም አርፎ ክፍለ ሐገር ቀብረው የተመለሱ በመሆኑ እህታችንን እና ቤተሰቦቿን በመደወል እንድናጽናናቸው የምትችሉ አባላት ደግሞ መኖሪያ ቤታቸው ጀሞ 3 በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። የወንድማችንን ነፍስ ይማርልን ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ጥንተ ስቅለቱ ለመድኀኔዓለም
መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች ጨረቃም ደም ሆነች ከዋክብት ረገፉ።
ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡
በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡
ስለስሙ በመመስከራችሁ ብቻ ያለምንም በደል በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ዘንድ ኑ እርሱ ንጹሐ ባሕርይ ሲሆን እንደ ወንጀለኛ እንደ በደለኛ ተሰቅሎ ሞቷልና ሞቱን እያሰብን እናልቅስ መታሰቢያውንም እናድርግ።
የአምላካችንን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋራ ተባብረን ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤው ከእርሱ ጋራ ለመተባበር ያብቃን። አሜን
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ጥንተ ስቅለቱ ለመድኀኔዓለም
መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች ጨረቃም ደም ሆነች ከዋክብት ረገፉ።
ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡
ማስታወቂያ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለት በዓል በሠላም አደረሰን እያልን
ለሆሳዕና በዓል አገልግሎት ለመስጠት የተመዘገባችሁ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት፣ የወላዲተ አምላክ ወጣቶች ማሕበር፣ የሜዲሲን ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች፣ የተስፋ ተክለሃይማኖት ወጣቶች ማሕበር በአገልግሎታችን ዙሪያ ለመወያየት በ27/07/2017 ቅዳሜ ከ11:30 ጀምሮ በደብራችን ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተገናኝተን እንድንወያይ በአክብሮት ጠርተናችኋል።
ሠላመ እግዚአብሔር አይለየን!
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
''ምስጢረ ተክሊል''
ክፍል ሁለት
በመ/ር ያሬድ ብርሃኑ
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 20/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እንደቀጠለ ነው አሁን ደግሞ በቀን ሁለት ምዕራፍ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ 2ኛ ተሰሎንቄ ከ 1-3
1ኛ ጢሞቴዎስ ከ1-6
2ኛ ጢሞቴዎስ ከ1-4
ቲቶ ከ1-3
ድረስ ንባባችንን እንቀጥል ።
መልካም የንባብ ጊዜ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በጣም አስቸኳይ የስራ ዕድል ማስታወቂያ
ለሰ/ት/ቤታችን አባላት ብቻ
======================
የስራው ዓይነት:- የሒሳብ ስራ
ፆታ:- ሴት
የድርጅቱ ዓይነት :- ማተሚያ ቤት
አድራሻ :- ተክለሃይማኖት
ደሞዝ :- በስምምነት
ስልክ :- 0931-14-44-44
ማሳሰቢያ:- የሰንበት ት/ት ቤታችን አባላት የሆናችሁና የስራ ዕድል ሲመጣልን እያለፈን በመሆኑ እንድናገናኝዎ የምትፈልጉ ወይም ይህ መረጃ የማይደርሳቸውና የሚያስፈልጋቸውን አባላት የምታውቁ ከታች በተቀመጡ ስልኮች በመደወል እንዲያስመዘግቡ በትህትና እንጠይቃለን።
0912-41-97-72 ዮናስ ይርዳው
0913-00-60-86 መቅደስ ቀፀላ
0966-25-87-38 ዮሐንስ ትዳሩ
የበጎ አድራጎት ክፍል
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
¡Ya disponible! Investigación de Telegram 2025 — los principales insights del año 
