es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ንቁ ትውልድ-Niku Twld

ንቁ ትውልድ-Niku Twld

Ir al canal en Telegram

እኛ ንቁ ትውልዶች ነን!

Mostrar más
2 165
Suscriptores
-124 horas
-27 días
-3630 días
Archivo de publicaciones
ዛሬ ጥቅምት 11 የዓለም የዜማ ደራሲ፣ የቤተክርስቲያን ብርሃንና ሊቅ የሆነው የካህኑ የቅዱስ ያሬድ ወርሃዊ መታሰቢያ ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳቹ🙏 ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በጥንታዊቷ የሥልጣኔ ማዕከል አክሱም (ትግራይ) በ505 ዓ.ም ሲሆን አባቱ  ይስሐቅ እናቱ ደግሞ ክርስቲና  ትባላለች። ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ለቤተክርስቲያን ቅርብ የነበሩ ደገኞች ነበሩ። ያሬድ ገና በሰባት ዓመቱ አባቱ ስለሞቱበት፣ እናቱ ወደ አጎቱ ወደ ጌዴዎን (የአክሱም ጽዮን ገበዝ ለነበሩት) ወሰደችው። ያሬድ መጀመሪያ ላይ ትምህርት በጣም ይከብደው ነበር፤ እንዲያውም መማር አቅቶት ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ወጥቶ ወደ ማይኪራህ ሲሄድ ነበር ያችን ትል ያያት። ከሷም ታላቅ ትምህርት ተማረ። ትሏ ስድስት ጊዜ ወድቃ በሰባተኛው ዛፍ ላይ ወጥታ ፍሬዋን ስትበላ አየ። "ይህች ደካማ ትል ይሄን ካደረገች፣ እኔስ ለምን ተስፋ እቆርጣለሁ?" ብሎ ወደ መምህሩ ተመለሰ። እግዚአብሔርም አእምሮውን ከፈተለት፤ በዓለም ላይ ወደር የሌለው ሊቅ ሆነ። ሦስት መላእክት በወፎች አምሳል መጥተው ወደ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ወሰዱት። በዚያም መላእክት እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበትን ዜማ ሰማ። ያሬድም ወደ ምድር ተመልሶ ያንን ሰማያዊ ዜማ ለሦስት ከፈለው፦ ግዕዝ፣ ዕዝል እና አራራይ። ከዚያ ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር ሰማያዊ ዜማ መሰማት ጀመረ። አንድ ቀን ቅዱስ ያሬድ በንጉሥ ገብረ መስቀል ፊት ቆሞ ሲዘምር፣ ንጉሡ በዜማው ተመስጦ በያዘው የጦር ዘንግ የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው። ሁለቱም ግን በመንፈሳዊ ተመስጦ ውስጥ ስለነበሩ ደሙ እስኪፈስ ድረስ ምንም አልተሰማቸውም ነበር። ንጉሡ በድንጋጤ "የፈለግከውን ለምነኝ እሰጥሃለሁ" አለው። ያሬድም "ከዚህ ዓለም ተለይቼ በጸሎት እንድኖር ፍቀድልኝ" ብሎ ለመነ። ከዛም ቅዱስ ያሬድ ወደ ሰሜን ተራሮች በመሄድ በጸሎትና በጾም ተወሰነ። በስተመጨረሻም ግንቦት 11 ቀን በ 571 ዓ.ም በ 66 ዓመቱ ደብረ ሐዊ ከተባለው በሰሜን ተራራ  ላይ እንደ ነቢዩ ኤልያስና እንደ ቅዱስ ሄኖክ ሞትን ሳይቀምስ በክብር ተሰውሯል። ያሬድ የዜማ መጻሕፍትን (ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ዝማሬ፣ምዕራፍና መዋሥዕት እንዲሁም 8ቱን የዜማ ምልክቶች (ድፋት፣ሂደት፣ቅናት፣ይዘት፣ቁርጥ፣ጭረት፣ርክርክና ደረት  ) ያዘጋጀ ታላቅ የጥበብ ሰው ነው። የሊቁ ቅዱስ ያሬድ በረከትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን🙏

ዛሬ ጥቅምት 9 በቅድስናና በተአምራት የደመቁት የኢትዮጵያዊው ፃድቅ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ወርሃዊ መታሰቢያ ነው ። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ🙏🙏 አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የተወለዱት በ፲፬ኛው (14ኛው) ክፍለ ዘመን ሲሆን የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡ወላጆቻቸው መልአከ ምክሩና ወለተ ማርያም ይባላሉ። ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ለየት ያለ መንፈሳዊ ጥም የነበራቸው ጻድቁ፣ በወጣትነታቸው ዓለምን ንቀው ለገዳማዊ ሕይወት ራሳቸውን ሰጥተዋል። ጻድቁ "እስትንፋሰ ክርስቶስ" የሚለውን ስም ያገኙት በቀጥታ ከጌታችን ሲሆን የስማቸው ትርጓሜ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ወይም የክርስቶስ እስትንፋስ ማለት ነው፡፡ ጌታችንም እንዲህ አላቸው፦ "ከእንግዲህ ስምህ እስትንፋሰ ክርስቶስ ይሁን፤ እኔ በሕይወት እስትንፋሴ ቀድሼሃለሁና።" ጌታችንም እጅግ የሚያስደንቅ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፦ ስምህን ለጠራ፣ ዝክርህን ለዘከረና በቃል ኪዳንህ የተማፀነውን ሁሉ እምርልሃለሁ፣ በዓልህን ያከበረውንና ገድልህን የጻፈውን፣ ያጻፈውንና ያነበበውን ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት አኖርልሃለሁ ። መታሰቢያቸውንም ላደረገ እናት፣ አባቱ ሲኦል ቢገቡ ስለ ዝክራቸው ከሲኦል አውጥተው ገነት እንዲያስገቡ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል ። አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በኢትዮጵያ ምድር በብዙ ገዳማትና በረሃዎች እየተዘዋወሩ በከባድ ተጋድሎ ኖረዋል። በተለይም በጣና ባሕር ዳርቻና በተለያዩ ደሴቶች ላይ በታላቅ ትዕግሥትና ጸሎት አሳልፈዋል። ስለ ሰው ልጅ ድኅነት ሲሉ ሌሊቱን ሙሉ በውኃ ውስጥ ቆመው በመጸለይና በስግደት ሥጋቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተዋል። ዘጠኝ ዓመትም በዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ ህዝብ ፀልየዋል። በሄዱበት ሁሉ ህዝቡን በማስተማር፣ የታመሙትን በመፈወስና አጋንንትን በማውጣት የታወቁ ነበሩ። በዘመኑ በነበሩ ነገሥታትና በህዝቡ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። ጻድቁ የሰው ልጅ ሁሉ በንስሐ ተመልሶ ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ያላቸው ፍላጎት እጅግ ታላቅ ነበር። "የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።" መዝ 112:6 የታላቁ ጻድቅ የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በረከታቸውና ቃል ኪዳናቸው ከሁላችን ጋር ይሁን🙏

ጸሐፍትና ፈሪሳውያን አንዲት ሴት ስታመነዝር ይዘው ወደ ጌታችን አመጧት። በሙሴ ህግ መሠረት በድንጋይ ተወግራ መሞት እንዳለባት እየጮሁ "አንተስ ምን ትላለህ?" ብለው ጠየቁት። ዓላማቸው እርሷ ላይ መፍረድ ብቻ ሳይሆን፣ እርሱንም በቃሉ ለመጥለፍ ነበር። ሴቲቱ ተስፋ ቆርጣለች፤ በዙሪያዋ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ድንጋይ ጨብጠዋል፤ ዓይኖቻቸውም በቁጣ ደም ለብሰዋል። ጌታችን ግን ወዲያው አልመለሰላቸውም። ይልቁንም ዝቅ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ መጻፍ ጀመረ። ሊቃውንት እንደሚነግሩን፣ ጌታችን በዚያች ሰዓት በምድር ላይ ይጽፍ የነበረው የእነዚያን ከሳሾች ድብቅ ኃጢአት ነበር። አጥብቀው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ አንዲት ቃል ተናገረ፦ "ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት።" ዮሐ 8:7 ጌታችን ይህን ብሎ እንደገና ዝቅ ብሎ መጻፍ ጀመረ። በዚያች ቅጽበት የእያንዳንዳቸው ኃጢአት በግንባራቸው ላይ በግልጽ መታየት ጀመረ። የያዙትን ድንጋይ ጥለው መሸሽ ጀመሩ። ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ታናናሾቹ ድረስ እርስ በእርሳቸው ተያይተው እየተሸማቀቁ ሴቲቱንና ጌታን ብቻቸውን ትተዋቸው ሄዱ። ጌታችን ቀና ብሎ ሴቲቱን ብቻዋን ቆማ አገኛት። "አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን?" አላት። እርሷም "ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ" አለች። ጌታችንም ሃጥያተኞችን ሊፈልግ የመጣ ነውና የህይወት ቃል ሰጣት፦ "እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ።" በሌሎች ላይ ድንጋይ ከመወርወራችን በፊት የገዛ ግንባራችን ላይ የተጻፈውን ኃጢአት እንመልከት። የሰው ጉድፍ ከማየት፣ የራስን ምሶሶ ሃጥያት ማፅዳት ይሻላል። በሰዎች ላይ ከመፍረዳችን፣ሌሎችን ከመንቀፋችን በፊት ራሳችንን እንመርምር! መልካም ቀን🙏

photo content

አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን "ረፍዷል! ነገሩ አብቅቷል! ተስፋ የለም!" የምንልባቸው ጊዜያት አሉ። የአልዓዛር ታሪክ ግን ለእግዚአብሄር "ዘግይቷል" የሚባል ነገር እንደሌለ ትልቅ ማሳያ ነው። አልዓዛር ታመመ እህቶቹ ማርታና ማርያም ወደ ጌታችን መልዕክት ላኩ። እርሱ ግን ወዲያው አልመጣም። አልዓዛር ሞተ፤ ተቀበረም። ድንጋይ ተገጠመለት። አራት ቀናት አለፉ። በሰውኛ ስሌት አራት ቀን ማለት "ተስፋው ሙሉ በሙሉ አብቅቷል፣ ሥጋውም መሽተት ጀምሯል" ማለት ነው። ጌታችን ሲመጣ ማርታ እንዲህ አለችው፦ "ጌታ ሆይ፤ አንተ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወንድሜ ባልሞተ ነበር።" ይህ የብዙዎቻችን ጩኸት ነው። ነገር ግን ጨምራ እንዲህ አለች፦ "አሁንም ቢሆን ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ።" ጌታችን ወደ መቃብሩ ቀረበ።በመቃብሩ ፊት ቆሞ በዙሪያው ያለውን ሥቃይ፣ እንባና ጥርጣሬ ተመለከተ። "ረፍዷል" አሉት።ከሞት ፍጻሜ በላይ ማየት አልቻሉም ነበር። እሱ ግን "ድንጋዩን አንሱ" አለ። ማርታ "ጌታ ሆይ፤ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታልና ይሸታል" ብላ ተከራከረች። ጌታችን ግን እንዲህ አላት፦ "ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር ታያለሽ አላልሁሽምን?" ጸሎት አደረገ፤ ከዚያም በታላቅ ድምፅ "አልዓዛር ሆይ፤ ወደ ውጭ ና!" ብሎ ተጣራ- ዮሐ 11:43። ከመቃብሩ ጨለማ ውስጥ እንቅስቃሴ ተሰማ። አራት ቀን ሙሉ ሞቶ የነበረው ሰው፣ ገና በመግነዝ እንደተጠቀለለ ወደ ፊት መጣ። ያ የሞተው፣ የተገነዘውና የሸተተው አልዓዛር በህይወት ተነስቶ ወጣ! ሞት የህይወትን ቃል መቋቋም አልቻለም። ማርያምና ማርታ በታላቅ ስሜት ተንበረከኩ፤ እንባቸው ከእንግዲህ የሀዘን ሳይሆን የአድናቆትና የደስታ ሆነ። እኛ "ረፍዷል" የምንለው ሰዓት ለጌታችን ክብሩን የሚገልጥበት ትክክለኛ ሰዓቱ ሊሆን ይችላል። ዛሬ በህይወትህ የሞተ የሚመስልህ ነገር ከፈጣሪ በላይ አይደለም። ጌታችን "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ" ብሎ የተናገረውን ቃል በተግባር ያሳየበት ተአምር ነው። አራት ቀን ስለሞተ 'ይሸታል' ተብሎ ተስፋ የተቆረጠበት አልዓዛር፣ በህይወት ተነስቷል። በአንተም ህይወት የሞቱብህን ተስፋዎች፣ የሸተቱብህን ነገሮችና ድንጋይ የተገጠመባቸውን ጉዳዮች ጌታ ዛሬም ሊያስነሳቸው ይችላል። ብቻ እመን! ፈጽሞ የማይመለስ ሁኔታ፣ የማይጠገን ህይወት የለም። መልካም ምሽት🙏

ሰላም ለቃልኪ፦ የተበተነ ልቡናን ለሚሰበስብ ቃልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የኃጢአት ደዌን ለሚፈውሰው መድኃኒት ለሆነው እስትንፋስሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ፣ ለደከሙትም መጽናኛ የሆንሽ
ሰላም ለቃልኪ፦ የተበተነ ልቡናን ለሚሰበስብ ቃልሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ የኃጢአት ደዌን ለሚፈውሰው መድኃኒት ለሆነው እስትንፋስሽም ሰላምታ ይገባል፡፡ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ፣ ለደከሙትም መጽናኛ የሆንሽ ቅድስት አርሴማ ሆይ ጨለማው በማይገፋ እሳቱም በማይጠፋ በጭንቅ ቀን በታመነው ቃል ኪዳንሽ ፈጽመሽ አድኚኝ፡፡ 🙏 መልክአ ቅድስት አርሴማ

📖 ፊልጵስዩስ 2፥13 ደግሞ "ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና" በማለት ያጸናናል። አንተ ብቻ ውስጣዊ ውሳኔ አድርገህ የመጀመሪያዋን እርምጃ ለመውሰድ ፍቃደኛ ሁን፤ የቀረውን ጉልበት፣ መነሳሳትና አቅም መንፈስ ቅዱስ ይሰጥሃል። ኃይልና ብርታት የእርሱ መሆኑን አውቆ በጸሎት መንፈስ ቅዱስን እርዳታ መጠየቅ ያስፈልጋል። ✨ ስንፍና ጊዜህን ብቻ ሳይሆን ዘመንህን፣ ነጻነትህን፣ ደህንነትህንና የነገ ማንነትህን የሚሰርቅ ሌባ ነው። ዛሬ ትንሽ መስሎ በሚታየው ስራ፣ በትምህርትህ ወይም በህይወትህ የምትተጋ ከሆነ፣ እግዚአብሔር ነገ በብዙ ላይ ይሾምሃል። 📖 ምሳሌ 12፥24፦ "የትጉዎች እጅ ትገዛለች፤ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።" 👇 ከእነዚህ 10 መፍትሔዎች ውስጥ ዛሬውኑ መተግበር የምትጀምረው የትኛውን ነው? ክፍል 1: https://web.facebook.com/share/p/19X1PCMmBq/ #ትጋት #ስኬት #መንፈሳዊ_ሕይወት #ጊዜ #ራስን_ማሻሻል #ስንፍናን_ማሸነፍ #ክርስቲያን #ኦርቶዶክስ

#ከስንፍና_እንዴት_እንውጣ? 1. ሁሉ ነገር ፍጹም እስኪሆን አትጠብቅ (Perfectionism)፦ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች "ሁሉ ነገር የተስተካከለ ሲሆን እጀምራለሁ" ወይም "በደንብ ካልሰራሁት አልጀምረውም" በማለት ጊዜያቸውን ያባክናሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ 📖 መክብብ 11፥4 ላይ "ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም" በማለት ጥልቅ ሚስጥር ይነግረናል። አየሩ ጸጥ እስኪል ወይም ደመናው እስኪገፈፍ የሚጠብቅ ገበሬ መቼም ዘር አይዘራም። አንተም ሁኔታዎች ሁሉ 100% የተመቻቹ እስኪሆኑ አትጠብቅ፤ ባለው ሁኔታ ጀምር፣ እግዚአብሔር በመንገድህ ላይ ያስተካክለዋል። 2. የ"አንድ ጀንበር" የለውጥ ሙከራን ተው፦ ብዙ ጊዜ ስንፍናችንን ስንገነዘብና ስንጠላው፣ በአንድ ቀን ውስጥ ሁሉንም ነገር ለመቀየር እንሞክራለን። "ከዛሬ ጀምሮ በቀን አስር ሰዓት እሰራለሁ" ወይም "በጭራሽ አላርፍም" የሚሉ ከባድ ቃሎችን ለራሳችን እንገባለን። ነገር ግን ይህንን ግዙፍ ግብ ማሳካት ሲያቅተን፣ የሞራል ስብራት ይገጥመንና ተስፋ ቆርጠን ወደባሰ ስንፍና እንመለሳለን። 📖 መክብብ 5፥5 "ተስለህ ከማትፈፅም ባትሳል ይሻላል" እንደሚል፣ ራስህ ላይ የማይቻል ጫና አትፍጠር። የህይወት ለውጥ የሚመጣው በአንድ ጊዜ በሚደረግ ግዙፍና ድንገተኛ ዘለላ ሳይሆን፣ በየቀኑ በምታደርገው ትንሽ ግን የማያቋርጥ ጥረት ነው። 📖 ምሳሌ 6፥6 ላይ "አንተ ታካች፥ ወደ ጉንዳን ሂድ፤ መንገዷንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን" ይላል። ጉንዳን አለቃ ሳትፈልግ፣ ነገር ግን በየቀኑ ትንሽ በትንሽ በመስራት የክረምቱን ዝግጅት ትጨርሳለች። አንተም ከዚህች ትንሽ ፍጡር ትልቅ ጥበብ ተማር። 3. ውድቀትን መፍራት (Fear of Failure) አቁም፦ ብዙ ጊዜ ሰነፍ የምንመስለው ስራ ጠልተን ብቻ ላይሆን ይችላል፤ "ብጀምርና ባይሳካልኝስ? ሰዎች ቢስቁብኝስ?" የሚለው ፍርሃት እግራችንን አስሮት ይሆናል። ነገር ግን ሐዋርያው ጳውሎስ 📖 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7 "እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና" ይለናል። ስህተት ለመስራት አትፍራ፤ ባለመስራት ከሚመጣው የዘላለም ጸጸት ይልቅ፣ ሞክሮ መውደቅ ነገን የሚያስተካክል ትልቅ ትምህርት ይሰጣል። 4. የጓደኛ እና የአካባቢ ተጽዕኖን መርምር (ስንፍና ተላላፊ ነው)፦ አብረሃቸው የምትውላቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜያቸውን በወሬ፣ በስራ ፈትነት እና ያለምንም አላማ የሚያሳልፉ ከሆነ፣ አንተም ሳታውቀው የእነሱን ባህሪ ትወርሳለህ። 📖 ምሳሌ 13፥20 ላይ "ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል" ይላል። አካባቢህንና አብረኸው የምትውለውን ሰው ካልመረጥክ፣ የቱንም ያህል ትጉህ ለመሆን ብትሞክር ይከብድሃል።ጊዜህን የሚሰርቁብህንና ለስንፍና የሚያጋልጡህን ቁሳቁሶች፣ ጓደኞችና ልማዶች ከፊትህ አርቅ። 5. የሕይወት ራእይና ዓላማ ይኑርህ፦ የት እንደምትሄድ ካላወቅህ፣ ከተቀመጥክበት ለመነሳት ምንም የሚያነሳሳ ምክንያት አይኖርህም። 📖 ምሳሌ 29፥18 "ራእይ ከሌለ ህዝብ መረን ይሆናል (ይጠፋል)" ይላል። ከስንፍና እስራት ለመላቀቅ፣ ጌታ በህይወትህ እንዲያደርግ የምትፈልገውንና ልትደርስበት ያሰብከውን ትልቅ ስዕል (ራዕይ) በግልጽ ማወቅ አለብህ። ራዕይህ ከጠዋቱ እንቅልፍህ የሚቀሰቅስህ የህይወትህ ማንቂያ ደወል ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን የግድ የማንወዳቸውን ግን ሃላፊነት የሆኑብንን ስራዎች መስራት ይኖርብናል። በዚህ ጊዜ ሐዋርያው ጳውሎስ 📖 ቆላስይስ 3፥23 ላይ "ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፤" ያለውን አስብ። ስራውን ባትወደውም፣ በስራው ላይ የምታሳየው ታማኝነትና ትጋት ግን የራስህን መልካም ስብዕና (Character) ይገነባል።ይህ አሁን የምትሰራው አሰልቺ ስራ ወደ ትልቁ ህልምህ መሸጋገሪያ ድልድይ መሆኑን አስብ። ስለዚህ ስራውን ሳይሆን፣ ስራው የሚያደርስህን ትልቅ ግብ (ራዕይ) እያሰብክ ስንፍናህን ታሸንፋለህ። 6. አቋራጭ መንገድን አትፈልግ፦ ሰነፍ ሰው ሁልጊዜ ላብ ሳያፈስ፣ ሳይደክምና ዋጋ ሳይከፍል በአቋራጭ መክበርን ይፈልጋል። ጊዜውን ሰጥቶ ከማጥናት ወይም ከማገልገል ይልቅ፣ ተአምር ብቻ ይጠብቃል። 📖 ምሳሌ 28፥19 ላይ "መሬቱን የሚያርስ ሰው እንጀራ ይጠግባል፤ ከንቱ ነገሮችን (አቋራጮችን) የሚከታተል ግን ድህነት ይተርፈዋል" ይለናል። እውነተኛ በረከት የሚመጣው በእግዚአብሔር መንገድ፣ ደረጃ በደረጃ በሚደረግ ትጋት እንጂ በቁማር ወይም በአቋራጭ አይደለም። 7. ራስን አብዝቶ ከመውቀስ ተቆጠብ (ወድቆ መነሳትን ልመድ)፦ በለውጥ ሂደት ውስጥ አንዳንዴ ተመልሰህ ልትወድቅ ወይም በስንፍና ልትሸነፍ ትችላለህ። በዚህ ጊዜ "እኔ ተስፋ የለኝም" ብለህ ራስህን አትቅጣ። 📖 ምሳሌ 24፥16 ላይ "ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ይነሣማል" ይላል። ስንፍና አንዴ ቢያሸንፍህ፣ ተስፋ ሳትቆርጥ ራስህን ይቅር በልና አቧራህን አራግፈህ በፍጥነት ወደ ትጋትህ ተመለስ። አንድን ከባድ ስራ ስታጠናቅቅ ደግሞ ለራስህ ትንሽ ሽልማት ስጥ። ለምሳሌ የምትወደውን ነገር አድርግ ወይም ለጥቂት ደቂቃዎች ዘና በል። ይህ አእምሮህ ስራን ከደስታ ጋር እንዲያያይዘው ያደርገዋል። 8. ቋሚ የሕይወት ልማድ (Habits) ገንባ፦ ብዙ ጊዜ ሰዎች ስንፍናን ለማሸነፍ በስሜትና በጉልበት ብቻ ይነሳሉ። ነገር ግን የሰው ልጅ የፍቃድ ጉልበት እንደ ሞባይል ባትሪ በዋለ ባደረ ቁጥር የሚያልቅ ነው። ስለዚህ ስሜትህ ሲነሳሳ ብቻ ለመስራት አትሞክር። ስንፍናን በዘላቂነት ለማሸነፍ በየቀኑ የምትተገብረው ትንሽ ግን ቋሚ የሆነ የህይወት ስርዓት (Habit) ያስፈልግሃል። 📖 ዳንኤል 6፥10፦ ዳንኤል በባቢሎን ምርኮ ሳለ በቀን ሦስት ጊዜ የመጸለይ ቋሚ ልማድ (ሥርዓት) ነበረው እንጂ፣ ስሜት ሲመጣለት ብቻ አልነበረም የሚጸልየው። 💡 የ2 ደቂቃው ሕግ (The 2-Minute Rule)፦ ማንኛውም ስራ ከሁለት ደቂቃ ያነሰ ጊዜ የሚወስድ ከሆነ፣ አሁኑኑ ስራው (ለምሳሌ፦ እቃ ማስተካከል፣ ኢሜይል መመለስ፣ ወዘተ)። ይህ ልምድ ስራዎችን ሳያከማቹ ወዲያው የመጨረስ ባህልን ያዳብራል። 9. መነሳሳትን (Motivation) አትጠብቅ፦ ሰነፍ ሰው ሁልጊዜ "ውስጤ ስሜቱ ሲመጣ እሰራዋለሁ" ይላል። ነገር ግን እውነተኛው ህግ የሚሰራው በተገላቢጦሽ ነው። መጀመሪያ ስራውን ስትጀምር፣ የትጋት ስሜቱና መነሳሳቱ አብሮህ ይከተላል። ውኃ ከጉድጓድ ለመሳብ መጀመሪያ ፓምፑን በእጅህ መንቀሳቀስ እንዳለብህ ሁሉ፣ ስሜት ባይኖርህም እንኳን የመጀመሪያዋን ትንሽ እርምጃ መውሰድ አለብህ። 📖 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥10፦ "ሊሠራ የማይወድ አይብላ።" (ክርስትና የትጋት ሕይወት ነው።) 🩺 አካላዊ ዝግጁነት፦ ንቁ ለመሆን ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ያስፈልጋል። በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ በቂ ውኃ መጠጣትና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ስንፍናን ያባርራል። 10. በእግዚአብሔር ጸጋ መደገፍ፦ እንዴት አድርጌ ነው የራሴን ስንፍና የማሸንፈው?" ብለህ ልትጨነቅ ትችላለህ። ትልቁ የምስራች ይህ ነው፦ ብቻህን አይደለህም! ሐዋርያው ጳውሎስ 📖 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥10 ላይ "ከሁላቸው ይልቅ አብዝቼ ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም" ይላል።

tplf.mp463.20 MB

photo content

ዛሬ ጥቅምት 5 የፃድቁ አባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ🙏 አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከአባታቸው ከቅዱስ ስምኦን እንዲሁም ከእናታቸው ከቅድስት አቅሌሲያ በገብርኤል ብስራት መጋቢት 29 ተፀንሰው፣ ታህሳስ 29 በደቡባዊ ግብፅ በንሂሳ አውራጃ ተወለዱ። ከእናት ከአባታቸው ጋር ሶስት ዓመት ከኖሩ በኋላ መላዕክት እየመሩት ወደ ገዳም ወጣ የእናቱን ጡት አልጠባም የዚህን ዓለም ጣዕም አላወቀም። በዛም በብርድና በሀሩር ሳይበገሩ፣ እንደ ሰማይ ወፍ ሳይዘሩና ሳያጭዱ፣ ልብስ ሳይለብሱ፣ ከሰው ተለይተው ለፈጣሪ እየተገዙ ለ300 ዓመት ቆዩ ከዛም ወደ አስራት ሀገራቸው ኢትዮጵያ በመምጣት በዝቋላና በምድረ ከብድ በታላቅ ተጋድሎ 262 ዓመት እህል ሳይበሉ፣ ውሃ ሳይጠጡ ኖረዋል። 100 ዓመት የኢትዮያን ህዝብ ማርልኝ ብለው በዝቋላ ሀይቅ ቁልቁል ተዘቅዝቀው ፀልየዋል። በምድር ላይ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ መላዕክት ኖሩ። ንዑድ ክቡር አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከዚህ ከኀላፊው ዓለም በሞት የሚለይበት ቀን በደረሰ ጊዜ ታመመ ብዙ ስውራን ባህታውያን ወደ እርሱ መጡ ስማቸውም ፍሬ ቅዱስ፣ ዘርዐ ብሩክ፣ያዕቆብ፣ብንያም፣ዮሴፍ ይባላል። አባታችን ታመውም ቢሆን የአምላክን ምስጋና እና ለኀጥአን ምህረትን ከመለመን አላቋረጡም። ሌሊት ስድስት ሰዓት በሆነም ጊዜ ከሰማይ ታላቅ የነጎድጓድ ድምፅ ተሰማ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ፣አስራ ሁለቱን ሐዋርያት፣አስራ አምስቱን ነቢያት፣ በመከራው የመሰሉት ሰማዕታትን ፣አገልጋዮቹ ፃድቃንን መላዕክቱንም አስከትሎ ወደ አባታችን መጣ። ጌታችንም የታመንክ አገልጋዬ ለስምህ መታሰቢያ ቃልኪዳኔን አፀና ዘንድ እነሆ ወደ አንተ መጣሁ አለው መታሰቢያህን ያደረገውን ፣ስምህን የጠራውን፣በፀሎትህ የተማመነውን፣የገድልህን መፅሀፍ የፃፈውን፣ያፃፈውን፣ያነበበውን፣ በፅኑ ልብ አምኖ የሰማውን ሁሉ፣ እስከ ዘላዓለም ድረስ በማይጠፋ በሰማያት ባለ በህይወት መጽሀፍ እኔ ስሙን እጽፋለሁ። ለቤተክርስትያንህ መባ የሚያገባውን ይኸውም ስንዴ፣ዘይት፣እጣን፣ዘቢብ፣ ሌላውንም ንዋየ ቅድሳት በመታሰቢያህ ቀን ያቀረበውን እኔ ሀጥያቱን ይቅር እለዋለሁ። ተደላ ደስታ በሚደረግበት በሺው ዘመን ከእኔ ጋር አስቀምጠዋለሁ ። ለድሆች፣ ለጦም አዳሪዎች የሚራራውን፣ለተራበ የሚያበላውን፣ለተጠማ የሚያጠጣውን፣ጥቂትም ቢሆን ብዙም ቢሆን በአንተ ስም አምኖ ይህን ሁሉ ያደረገውን፣ እኔ በመንግስተ ሰማያት የህይወትን እንጀራ ከአንተ ጋራ አበላዋለሁ። በአንተ ስም የታረዘውን የሚያለብስ፣ የተቸገረውን የሚረዳ፣በመታሰቢያህ ቀን ያዘነውን የሚያረጋጋ፣ባለጽጋም ቢሆን፣ ድሃም ቢሆን፣ ሀጥያቱ የበዛም ቢሆን ሀጥያቱን ትቶ በፀሎትህ ከታመነ የቀደመ በደሉን አላስብበትም፣ የእዳ ደብዳቤውን እደመስስለታለሁ እንዳልበደልም አደርገዋልሁ። ዝክርህን የሚያደርገውን ብቻ የምምርልህ አይደለም እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ እንጂ። ዳግመኛም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠውን ቃል ኪዳን እሰጥሃለሁ መታሰቢያህን ዝክርህን የሚያደርግ፣ እናት አባቱ ሙተው ወደ ሲኦል ከወረዱ በኋላ ከሲኦል አውጥቼ ነፍሳቸውን ለአንተ እሰጥሃለሁ አለው። ከእንግዲስህ ወዲህ ወደ ብርሃን ቤቶች ግባ 12 የብርሃን አክሊልም ሰጠው ከዚ በኋላ ከእርሱ ተሰወረ። በጴጥሮስና በጳውሎስ በዓል በመጋቢት አምስት እሁድ ቀን አረፈ። የመላዕክት ሰራዊትም በክብር፣ በብዙ ምስጋና፣በዕልልታ በነጋሪት ድምፅ ወደ ብርሃን ቤቶች ነፍሱን አስገቧት። በአርያምም ታላቅ ደስታ ሆነ። የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታውና ቸርነቱ፣ የአባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከቱና ረድኤቱ በእኛ በልጆቹና በመላው ህዝበ ክርስትያን እንዲሁም በሀገራችን በኢትዮጵያ፣ ለዘለዓለሙ ፀንቶ ይኑር ። አሜን! የፃድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው መጋቢት 5 የዕረፍት በዓላቸው ዐቢይ ፆም ውስጥ ስለሚውል ቅያሪ ሆኖ ነው:: ምንጭ፡- ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

#ስንፍና_ምንድነው? ስንፍና እግዚአብሔር የሰጠንን ውድ ጊዜ፣ ጉልበትና ተሰጥኦ እንዳንጠቀም የሚያደርግ፣ እንደ ከባድ ብርድ ልብስ ተጭኖ ከቦታችን እንዳንንቀሳቀስ የሚያስር መንፈሳዊና ስጋዊ ድካም ነው። ልክ ያልታረሰ ማሳ አረም እንደሚሞላው፣ ሰነፍ ሰውም ጥሩ ነገር ለመስራት ምኞት እያለው በተግባር ግን ምንም አይሰራም። 📖 ምሳሌ 26፥14፦ "በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዟዟር፥ እንዲሁ ታካች በአልጋው ላይ ይመላለሳል" (ይህ ቃል የሰነፍን ሰው ሕይወት በግልጽ ያሳየናል።) ስንፍና የስጋ ብቻ አይደለም፤ ነፍስህንም ያደነዝዛል። መጸለይ ሲያቅተህ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ሲከብድህ፣ እና መልካም ለማድረግ ስትታከት መንፈሳዊ ስንፍና ወርሶሃል ማለት ነው። 📖 ሮሜ 12፥11፦ "ለሥራ ከመትጋት አትለግም፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ" (መንፈሳችን ሁልጊዜ የነቃና ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ መሆን እንዳለበት ይመክረናል።) 10 የስንፍና መገለጫዎችና ባህሪያት፦ 1. "ነገ እሰራዋለሁ" የሚለው የዘገየ ማታለያ (Procrastination) ስንፍና ሁልጊዜ ፊት ለፊት መጥቶ "አትስራ" አይልህም። ይልቁንም "ዛሬ እረፍና ነገ ትሰራዋለህ" በሚል ጣፋጭ የውሸት ቋንቋ ያታልልሃል። "ነገ" የሰነፎች መደበቂያ ዋሻ ነው። የነገው ቀን የኛ ስለመሆኑ እርግጠኞች አይደለንምና ዛሬ ማድረግ የምትችለውን ዛሬውኑ ፈጽም። 📖 ምሳሌ 24፥33-34፦ "ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥ ጥቂት እጅን አጣምሮ ማረፍ፤ ድህነትህ እንደ ወንበዴ... ይመጣብሃል።" 2. የሌለ ምክንያትና ፍርሃት መፍጠር (Excuses) ሰነፍ ሰው ስራ ላለመስራት ሁልጊዜ አሳማኝ የሚመስል ሰበብ አለው። 📖 ምሳሌ 22፥13፦ "ሰነፍ፡— አንበሳ በውጭ አለ፤ በአደባባይም እሞታለሁ ይላል።" ስንፍና ትንንሽ መሰናክሎችን እንደ ትልቅ ገዳይ አንበሳ አጋንነህ እንድታይና ፍርሃት ውስጥ ገብተህ ቤትህ እንድትቀመጥ ያደርግሃል። 3. እጅ የሌለው ምኞት (ባዶ ሕልም) ሰነፍ ሰው ምንም አይፈልግም ማለት አይደለም፤ እንዲያውም ብዙ ትልልቅ ሕልሞችና ምኞቶች አሉት። ነገር ግን ያንን ሕልሙን እውን ለማድረግ ጣቱን አያነሳም። ምኞትህ በላብና በድካም በተግባር ካልተተረጎመ የልብ ሕመም ሆኖ ከመቅረት አያልፍም። 📖 ምሳሌ 21፥25፦ "የሰነፍ ምኞት ትገድለዋለች፥ እጆቹ መሥራትን እንቢ ብለዋልና።" 4. የእግዚአብሔርን ስጦታ መቅበር ስንፍና ዝም ብሎ መተኛት ብቻ አይደለም፤ ስንፍና ማለት እግዚአብሔር በውስጥህ ያስቀመጠውን ልዩ ተሰጥኦ፣ ጥበብና አቅም አውጥተህ ለዓለም ሳታካፍል መሬት ውስጥ መቅበር ማለት ነው። 📖 ማቴዎስ 25፥26፦ ጌታ አንድ መክሊት (ተሰጥኦ) ተቀብሎ መሬት ውስጥ የቀበረውን አገልጋይ ሲቆጣው "አንተ ክፉና ሰነፍ ባሪያ!" ብሎታል። 5. ስንፍና ቋሚ ማንነት ሳይሆን የተገነባ ልማድ ነው ማንም ሰው ከእናቱ ማሕፀን ሰነፍ ሆኖ አይወለድም። ስንፍና በየቀኑ "አምስት ደቂቃ ልተኛ"፣ "ይህንን ነገ እሰራዋለሁ" በሚሉ ትንንሽ ውሳኔዎች የተገነባ የሕይወት ልማድ ነው። ራስህን "እኔ ሰነፍ ነኝ" ብለህ አትኮንን፤ ይልቁንም ትንንሽ የትጋት ልማዶችን በመገንባት ይህንን መጥፎ ልማድ መቀየር ትችላለህ። 📖 ሮሜ 6፥16፦ ለማንኛውም ነገር ብንታዘዝ የእርሱ ባሪያዎች እንደምንሆን ያስተምረናል። 6. ውሸተኛ ትጋት (Productive Procrastination) አንዳንዴ ሰነፍ ሰው ቀኑን ሙሉ በስራ "ሲንቀሳቀስ" ሊውል ይችላል፤ ነገር ግን የሚሰራው መስራት ያለበትን ዋናውንና ከባዱን ስራ ሸሽቶ፣ ቀላልና ምንም ፋይዳ የሌላቸውን ጥቃቅን ነገሮች ነው። ስንፍና የሕይወታችንን ትልቁን ዓላማ ወደ ጎን ትተን ጊዜያችንን በትርፍ ነገሮች እንድናቃጥል ያታልለናል። 📖 ማቴዎስ 23፥23፦ ጌታ ፈሪሳውያንን "ቁም ነገር ያለውን... ተዋችሁ" እንዳላቸው። 7. የአእምሮ ስንፍና (Mental Laziness) አካላዊ ጉልበትህ እየሰራ አእምሮህ ግን ሰነፍ ሊሆን ይችላል። አዳዲስ ነገሮችን ለማንበብና ለመማር፣ ጠለቅ ብሎ ለማሰብ፣ ወይም ከባድ የሆኑ የሕይወት ጥያቄዎችን ለመጋፈጥ መታከት የአእምሮ ስንፍና ነው። ማስተዋልህን ሳታሳድግ በቀላሉ የተገኘውን መረጃ ብቻ መቀበል ሌላኛው የስንፍና እስራት ነው። 📖 ምሳሌ 18፥15፦ "የአስተዋይ ልብ እውቀትን ታገኛለች።" 8. ስንፍና ራስን መጥላት ነው እኛ ሰነፍ የምንሆነው ራሳችንን ስለምንወድና ለአካላችን ስለምንሳሳ ይመስለናል። ነገር ግን ለራስህ የወደፊት ሕይወት፣ ክብርና ጸጋ የማትተጋ ከሆነ በእውነቱ ራስህን እየጠላህ ነው ማለት ነው። እውነተኛ ራስን መውደድ መገለጫው ለነገው ማንነትህ ዛሬ ዋጋ መክፈልህ ነው። 📖 ምሳሌ 15፥32፦ "ተግሣጽን የሚጠላ ነፍሱን ይጠላል።" 9. የማይመለሰውን ጸጋ (ጊዜን) ማባከን ገንዘብ ቢጠፋ በመስራት ሊገኝ ይችላል፣ ጤና ቢታወክ ሊታከም ይችላል፤ በስንፍና የባከነ ጊዜ ግን መቼም አይመለስም። ስንፍና የተሰጠህን የሕይወት ሰዓት በከንቱ የሚበላ ሌባ ነው። 📖 ኤፌሶን 5፥15-16፦ "ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ (ጊዜን በአግባቡ ተጠቀሙ)፤ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ።" 10. ዕረፍትና (Rest) ስንፍናን (Laziness) አለመለየት ዕረፍት ቅዱስ ነው፤ ሰውነትን ያድሳል። ነገር ግን ስንፍና ማለት ከመስራት በፊት ለማረፍ መሞከር ማለት ነው። ሰነፍ ሰው ድካም ሳይኖረው ሁልጊዜ ዕረፍት ይፈልጋል። እውነተኛ ጣፋጭ እንቅልፍና ዕረፍት የሚመጣው ከቀኑ ትጋት በኋላ መሆኑን አትርሳ። 📖 መክብብ 5፥12፦ "የሚሠራ ሰው... እንቅልፉ ጣፋጭ ነው።" ስንፍና ራስን በማታለል የሚጀምር፣ ዋናውን ስራ ትቶ በሌላ መባዘንና አእምሮን አለማሰራት ሲሆን በመጨረሻም ያለንን የሚያፈርስና ህይወትን በምሬት የሚሞላ መርዝ ነው። ጊዜህን ብቻ ሳይሆን ዘመንህን፣ ነጻነትህን፣ ደህንነትህንና የነገ ማንነትህን የሚሰርቀውን ይህንን ሌባ ዛሬውኑ በትንንሽ የትጋት እርምጃዎች ማሸነፍ ጀምር። 👇 ከእነዚህ 10 የስንፍና ወጥመዶች ውስጥ እርስዎ በብዛት የሚታገሉት ከየትኛው ጋር ነው? ሃሳብዎን ያካፍሉን! በቀጣይ የስንፍና መንስኤና መፍትሄውን ይዘን እንመጣለን። ከእኛ ጋር ሁኑ🙏 #ትጋት #ስንፍና #ጊዜ #መንፈሳዊ_ሕይወት #ክርስቲያን #ስኬት #ጥበብ #ኦርቶዶክስ

ዛሬ ጥቅምት 4 የደገኞቹ፣የወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ነገስታት የአብርሃ ወአጽብሃ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ🙏 አብርሃ ወአጽብሃ በ፬ኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያን በጋራ የገዙ መንታ ነገሥታትና ወንድማማቾች ናቸው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮና ታሪክ መሠረት፣ ክርስትናን የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት አድርገው ያወጁና በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን ያነጹ ቅዱሳን ነገሥታት ተብለው ይዘከራሉ። አባታቸው ንጉሥ ታዜር ይባላል። እናታቸው ንግሥት ሶፍያ (በሌላ ስሟ አህየዋ) ትባላለች። ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን በቅድስናና በንጽሕና የሚያገለግሉ ደጋግ ሰዎች ነበሩ። ንጉሥ ታዜርና ንግሥት ሶፍያ ለብዙ ዘመናት ልጅ ሳይወልዱ የቆዩ መካኖች ነበሩ። በዚህም ምክንያት ልብ በሚነካ ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ይጮኹ ነበር። ንግሥት ሶፍያ በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘውን የነቢዩ ሳሙኤል እናት የሐናን ታሪክ አርአያ በማድረግ፣ ፈጣሪ ልጅ እንዲሰጣት በጋራ ምክክር ሱባኤ ገባች። እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ መልአኩን ላከላቸው። መልአኩም ለሀገርና ለሃይማኖት መብራት የሚሆኑ መንታ ልጆችን እንደምትወልድ አበሰራት። ወንድማማቾቹ ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ በአንድ ቀን ተጸነሱ፣በአንድ ቀን ታሕሳስ ፳፱ (29)ቀን በ፫፲፪ (312)ዓ/ም ተወለዱ። ነገሥታቱ ከመጠመቃቸው በፊት ስማቸው ኢዛና (ዕዛና) እና ሳይዛና (ሰዓዛነ) ነበር። በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ በአቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ፍሬምናጦስ) እጅ ሲጠመቁ ስማቸው ተቀየረ አብርሃ ማለት «እንደ መብራት ብርሃን አበራ» ማለት ሲሆን፣ አጽብሃ ማለት ደግሞ «ሌሊቱን አስነጋ፣ ንጋትን አመጣ» ማለት ነው። ይህ ከውልደታቸው ጀምሮ የታየው አስደናቂ አንድነት በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አልተለያቸውም። በታሪካቸው «በአንድ ልብ በአንድ ሃሳብ» ሆነው፣ በንግሥና ዙፋን ላይ እንኳ በአንድ ላይ ተቀምጠው ህዝባቸውን በፍትሕና በርትዕ ያስተዳድሩ ነበር። ነገሥታቱ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ወንጌልን ያስፋፉ ሲሆን፣ በጥቅሉ ፹፮ (ሰማንያ ስድስት) አብያተ ክርስቲያናትን እንዳነጹ በታሪክ ይነገራል። ከአክሱም ጽዮን ማርያም ቀጥሎ፣ በእነሱ ስም የሚጠራውና በትግራይ ክልል ውቅሮ አቅራቢያ የሚገኘው አስደናቂውና ውቅሮሽ የሆነው የአብርሃ ወአጽብሃ ፍልፍል ገዳም (Rock-hewn church) ዋነኛው የታሪክ ምስክር ነው። አብርሃ ወአጽብሃ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በአንድነት፣ በፍቅርና በአንድ መንበር (ዙፋን) ላይ ሆነው ሀገሪቱን እንደመሩ ሁሉ፣ የሞታቸውም ፍጻሜ ከአንድነት የተለየ አልነበረም። ዕድሜያቸውንም ሙሉ ለሙሉ ለሀገር አንድነትና ለክርስትና ሃይማኖት መስፋፋት ሰጥተዋል። ታላቁ አብርሃ በ374 ዓ ም ጥቅምት 4 ቀን እለተ እሁድ ዐረፈና ተቀበረ፡፡ ወንድሙ አጽብሐ ደግሞ ጥቅምት 4 ቀን 379 ዓ ም ዐረፈ፡፡ የቅዱሳን ነገሥታቱ ቅዱስ ሥጋ (አስከሬን) ዛሬም ድረስ ታሪካዊ ምስክር ሆኖ በትግራይ ክልል ውቅሮ አቅራቢያ በሚገኘውና በእነሱ ስም በሚጠራው ውቅሮሽ በሆነው የአብርሃ ወአጽብሃ ፍልፍል ገዳም ውስጥ ይገኛል። የሁለቱ ነገሥታት አስከሬን ሳይበሰብስና ሳይለወጥ (በክብር) በሳጥን ተቀምጦ በገዳሙ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ለጎብኚዎችም ለበረከት ይታያል። ይህ ቦታ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ጥንታዊና አስደናቂ የቅርስና የሃይማኖት ስፍራዎች አንዱ ነው። የአብርሃ ወአጽብሐ ረድኤታቸው፣ በረከታቸውና አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።አሜን🙏

ዛሬ ጥቅምት 3 የእናታችን የእመቤታችን በዓታ ማርያምና የቅዱስ ፋኑኤል ወርሃዊ መታሰቢያ ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳቹ🙏 ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ለብዙ ዘመናት ልጅ አጥተው ያዝኑ በሰው ዘ
ዛሬ ጥቅምት 3 የእናታችን የእመቤታችን በዓታ ማርያምና የቅዱስ ፋኑኤል ወርሃዊ መታሰቢያ ነው። እንኳን አደረሰን አደረሳቹ🙏 ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ለብዙ ዘመናት ልጅ አጥተው ያዝኑ በሰው ዘንድም ይናቁ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ አለም ሁሉ የሚድንበትን ድንግል ማርያምን ሰጣቸው። እነርሱም "ልጅ ብናገኝ ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ አድርገን እንሰጣለን" ብለው የተሳሉትን ስእለት አልረሱም። ድንግል ማርያም የሦስት ዓመት ህፃን ስትሆን፣ ወላጆቿ ስእለታቸውን ለመፈጸም ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ይዘዋት ሄዱ። ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ በደስታ ተቀበላት። በቤተ መቅደስም ውስጥ ለ12 ዓመታት ስትኖር ምግቧ ከሰማይ የሚወርድ ሰማያዊ መና፣ መጠጧም የህይወት ውሃ ነበር። ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል በብርሃን ክንፎቹ እየጋረዳት፣ ሰማያዊ ምግብ እየመገባት በቅድስና አደገች።   በልዑል እግዚአብሔር እጅ ከቅዱሳን መላዕክት ጋራ በአንድነት ለተከናወነ ተፈጥሮህ ሰላምታ የሚገባህ ከሰዎች ላይ ዘወትር ሰይጣናትን የምታሳድድ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ፋኑኤል ሆይ ርኩሳን አጋንንትን ወደ እኔ እንዳይቀርብ ገስጸህ ታስወግዳቸው ዘንድ እለምንሃለሁ። በዓታ ማርያም ለሀገራችን ሰላምን፣ ለኛም ፍቅርንና አንድነትን ታድለን። አሜን🙏