መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞ አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ @Mente8 ተጠቀሙ
Mostrar más📈 Análisis del canal de Telegram መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
El canal መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች (@melikt_weg_gitim) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 14 135 suscriptores, ocupando la posición 6 134 en la categoría Religión y espiritualidad y el puesto 2 512 en la región Etiopía.
📊 Métricas de audiencia y dinámica
Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 14 135 suscriptores.
Según los últimos datos del 05 noviembre, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 569, y en las últimas 24 horas de -1, conservando un alto alcance.
- Estado de verificación: No verificado
- Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 0.65%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 0.91% de reacciones respecto al total de suscriptores.
- Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 92 visualizaciones. En el primer día suele acumular 129 visualizaciones.
- Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 3.
📝 Descripción y política de contenido
El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
“✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞
አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ @Mente8 ተጠቀሙ”
Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 06 noviembre, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Religión y espiritualidad.
መድኃኔዓለም#ጥቅምት_27 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔ ዓለምን በዓል በደማቁ ታከብራለች ይህም የለውጥ በዓል ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ነው። ነገር ግን እንደዛሬዉ በግለሰቦች ፈቃድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሳይጣስ በፊት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች መጋቢት 27 ቀን ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዐቢይ ጾም ደግሞ ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን ከድሆች ጋር እንድናከብረው በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ሠርተውልን ነበር። በሞቱ ሞታችንን ያስወገደ፣ በኀዘኑ ኀዘናችንን ያራቀ በለቅሶው ዕንባችንን ያበሰ፣ ከወደቅንበት ያነሳን፣ ጠላታችንን ከመንገዳችን በመስቀሉ ጠርቆ ያስወገደ፣ በደሙ የቀደሰን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአይሁድ ተንኮልና ክፋት በሐሰት ተወንጅሎ 6666 ጊዜ ተገርፎ 41 ጊዜ በብረት ዘንግ አናቱን ተመቷል። በምራቁ ዕውር የሚያበራ ምራቅ ተተፋበት ሥጋው አልቆ ደሙ ፈሶ አጥንቱ ይቆጠር ነበር ስለ ሁላችንም እርሱ ታመመ ስለሁላችን እርሱ ሞተ መስቀል ተሸክሞ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ወድቆ ተነሳ። አይሁድ በወንጀለኛው በርባን ፋንታ ክርስቶስ ይሰቀል በርባን ይፈታ በማለት መድኃኒታቸውን ሰቀሉት ይሆን ዘንድ ግድ ነውና በቀራኒዮ አደባባይ በማዕከለ ምድር የዓለም መድኃኒት ተሰቀለ። አይሁድ በውስጣቸው ባደረ ጠላት ዲያቢሎስ ምክንያት ክፋት ጭካኔያቸው የበዛ ሆነ አዳኝ መድኃኒት ህይወት ፍቅር ተስፋ የሆነውን ክርስቶስ በክፋት ተነሳስተው ቢሰቅሉትም ለእኛ ግን መዳን ሆነልን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን የምንድን ሆንን። በክርስቶስ ሞት ሞታችን ተወግዶ ህይወት አገኘን በነፃነት እንኖር ዘንድ ነፃ አወጣን ተስፋችን መታመኛችን ኃይላችን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር የሆነ በመስቀል ሞት ነፃነታችንን አውጆ የዲያቢሎስ ክፋትና ተንኮል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶ #ተፈፀመ በማለት ነፍሱን ሰጠ ዛሬ በቀደመው ክብሩ በዙፋኑ አለ ለማማለድ ሳይሆን ለመፍረድ አማላጅነት የአገልጋዮቹ የቅዱሳን ተግባር ነውና። ጌታ : ሆይ : ወሰን : ስለሌለው : ፍቅርህ : እናመሰግንሃለን። እንኳን አደረሳችሁ
