قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Ir al canal en Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
907
Suscriptores
-224 horas
-127 días
+4630 días
Archivo de publicaciones
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ባለፈው ዓመት ምን ያህል ኪታብ አንብባችኋል? በዚህስ ዓመት ምን አሰባችሁ? በተለይ የሸሪዐ እውቀትን በመማርና በማስተማር ላይ የተሰማራችሁ? የማያነብ ጧሊበል ዒልም ሊለወጥ አይችልም። የእውቀት ትጥቅ ለመታጠቅ፣ የግንዛቤ አድማስን ለማስፋት፣ ከጥራዝ ነጠቅ አስተሳሰብ ለመራቅ፣ የሌሎች ጭፍን ተከታይ ከመሆን ለመትረፍ ማንበብ ወሳኝ ነው። ከሸይኽ ወይም ኡስታዝ ላይ የምትማረው ዋና መሰረት ቢሆንም እዚህ ላይ ብቻ አትንጠልጠል። ማንም ቢሆን ሁሉን ኪታብ አይማርም። የፈለገ ቢሆን የምትማረው ውስን ነው። ከዚያ በኋላ ጥልቅ የሆነ የራስ ጥረት ያስፈልጋል። መሰረታዊ ነጥቦችን ከሸይኽ ከቀሰሙ በኋላ ሳይሰለቹ ማንበብ ይገባል።
ደግሞም መጠየቅ ጥሩ ቢሆንም በትንሽ በትልቁ ሰው ላይ ጥገኛ መሆን አይገባም። በራስ መጣር፣ መድከም ያስፈልጋል። ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ-ሸይኽ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ጊዜ ከዳኞች አንዱ ወደ ክቡር አያቴ ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ኢብራሂም (አላህ ይዘንላቸውና) በፍርድ ቤት የዳኝነት ስራው ላይ ስለገጠመው አንድ ጉዳይ ብይን (ሑክም) ሊጠይቃቸው ደብዳቤ ጻፈ። ሸይኹም በሁለት መስመር ብቻ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦
'ይህ ጉዳይ በሁሉም የዑለማእ ኪታቦች ውስጥ የታወቀ ነው፤ ነገር ግን አንተ ሰነፍ ስለሆንክ አትመረምርም (አታነብም)። ሰላም።' "
[ሙሂማቱን ፊ ጦለቢል ዒልም]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
ማንኛውም አይነት ከሸሪዓ ጋር የማይጋጩ የስራ
ማስታወቂያዎችን በአንድ ቻናል ላይ በነጻ
ማስተዋወቅ እንዲሁም ስራ ለማግኘት ከፈለጉ
Halal Jobsን ይቀላቀሉ!👇
ድንበር ያለፈ ፍቅር ለቀይስም አልጠቀመው።መጅኑኑ ለይላ(የለይላ እብድ) አስባለው!!!
◦ውድቀት ስህተቶቻችንን መርምረን ለቀጣይ ጉዟችን እንደ ትምህርት የምንወስድበት ማዕከል ነው።
◦በተስፋ መቁረጥ አልጋ ላይ መተኛትህ ከፍታ ላይ እንድትደርስ አያደርግህም፤
◦ስኬት የሚገነባው ፈፅሞ በማይሰበር የፅናትና የቆራጥነት ክንድ ብቻ ነው።
#ስለዚህ ወደ ግብህ መድረስ ከፈለግክ፣ራስህን ከተስፋ መቁረጥ እስር ቤት ነፃ ማውጣት ግድ ይሆንብሀል።
=https://t.me/Abulabas1444
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ህይወት ማለት ህመም የሌለበት ጉዞ ሳይሆን፣ በህመም ውስጥም ተስፋን ሰንቆ መጓዝ ነው። እንባ ቢኖርም ፈገግ ማለት፣ ስንወድቅም ዳግም ለመነሳት መዘጋጀት ነው።
Repost from የተለያዩ ግጥሞች ማስቀመጫ,❝የሰርግ .የኽትሚያ... ❞
ማሳሰቢያ ❌❌
ለቻናል ባለቤቶች በሙሉ wave ስትገቡ እያያችሁ ግቡ እባካችሁ በስመ waver ቻናላችሁ የኢኸዋን እና ተክፊር ሀጃዊራ ቅልቅል ያለ ነገር እየተለቀቀ ነው ያለው እኛ በነፃ wave የምናሳድገው ጥርት ያለ ዳዕዋ በሰለፎች መንገድ ታሰፋፋላችሁ በሚል ነው ። ካልሆነ ምን ጥቅም አለው ሰለዚህ ቻናላችሁ ላይ የሚለቀቅ wave ከሱና የወጣ ከሆነ ከእኛ Wave የምናስወጣ መሆኑን እንገልፃለን ።
እስከ አሁን ጥርት ያለ የሱና ሰዎችን የሰበሰቡት ከእኛ ውጭ አንድ ነው የማቀው ሌላው እጂግ የተበላሸ ነው ። ሰለዚህ እናተርፋለን እያልን እንዳንከስር ልብ እንበል።
ከታች ያሉትን ሁሉቱን waver ለመጠቀም ሞክሩ ። 👇👇👇
@Darutewhiid_wave
@Selefya_wave
Repost from Mohammed saied (ሙሐመድ ሠዒድ)
--🎤 خطبة الجمعة 🎤--
🍒“የጁሙዓ ኹጥባ˝
🌴 በሸይኽ ሠዒድ ሙሐመድ 🎤
🕌 ከሃዋ መስጂድ
🌴 አሸዋ ሜዳ ከሶሬሳ ጀርባ
══════ ❁ ══════
https://t.me/Mohammedseid21
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
«አንተ አቡል ዐስ ሆይ፤ ለመሆኑ የእኛ መለያየት እንዲህ ቀለለህ?» አለችው...
ይህች ቃል የነብዩ(ﷺ) ውድ ልጅ ዘይነብ፣ ለትዳር አጋሯ ለአቡል ዐስ ኢብኑ ረቢዕ የሰነዘረችው የናፍቆት ቃል ናት።
የዘይነብ የሞት ሰዓት ሲቃረብ፣የአቡል ዐስ ዓለም በድቅድቅ ጨለማ ተዋጠ። የምድር ሕይወት ትርጉም አጥታ ታየችው። ሞቷን ሲሰማ የመነጨው ከባድ ለቅሶና ጩኸት፣
ልቡ ውስጥ የነበረውን ጥልቅ ፍቅርና የደረሰበትን የውስጥ ስብራት የሚያሳይ ነበር።
ያዩትን ሁሉ የሚያዝኑት ታላቁ ነብይ (ﷺ) በአማቻቸው ከባድ ስቃይ ልባቸው ተነክቶ፣ በሩህሩህ እጃቸው እየዳበሱ ሊያፅናኑት ሞከሩ። እርሱ ግን እንባው እየጎረፈ፣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለ፦«ወላሂ አንተ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ያለ ዘይነብ ይህችን ዱንያ መኖር አልችልባትም!» አላቸው።
በእርግጥም ያለ እርሷ መኖር አልቻለም። የልብ ስብራት፣ የናፍቆት እሳትና የፍቅር ቁስል ሰውነቱን ቀስ በቀስ አደከመው። ዘይነብ በሞተች በዓመቱ፣ እርሱም ይህችን ዓለም ተሰናብቶ ተከተላት።
◈ምን ማለት ፈልጌ መሰላችሁ...በፍቅር መጎዳትንና የመለያየትን ስቃይ መቼም ቢሆን ቀላል አድርገን ልንመለከተው አይገባም።ቀስ በቀስ ሰውን የሚያደክም፣ አልፎ ተርፎም ለህልፈት የሚዳርግ ኃይል አለው። አላህ በሃላሉ ያብቃቃችሁ!
--
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from ተቀርተው ያለቁ ደርሶች
የኡስታዝ አቡል ዐባስ ደርሶች፦
1- ተንቢሃት
2- ኪታቡ ተውሒድ
3- ሠላሠቱል ኡሱል
4- መኻሪጀል ሑሩፍ
5- ሚፍታሑ ተጅዊድ
6- ሂዳየቱል ሙስተፊድ
7- አልቃዒደቱ ኑራኒያህ
8- መንዙመቱል ኢልቢሪ
9- አልጀውሀረቱል መክኑናህ
10- ኹላሶቱ ኑሪል የቂን ጁዝ 1
11- መንዙመቱ ቱሕፈቲል አጥፋል
12- ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
13- ኡሱሉ ሲታ
የዘመን መለወጫ በዓል እኛን ሙስሊሞችን አይመለከትም‼️
እኛ ሙስሊሞች ሌላው ይቅርና ኢስላማዊ የሆነውን የሒጅሪያ አቆጣጠርን ዘመን መለወጫ የማናከብር፤ በሸሪዓችን የታዘዝነውን እንጂ ያልታዘዝነውን የማንፈፅም ጥንቁቅ ህዝቦች ነን።
©
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
⭕️👉ለውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አላህ አፍያ ያድርገውና አድርሱልኝ።✅
<<አንተን ክፉ አይንካህ>>
የነብያት ወራሽ ዳዒ ነህ ታታሪ፤
የኢስላም ወታደር ባጢል አባራሪ።
የሱና ሳተና የቢዲዓ ጠላት፤
በሁጃ ተውበህ ሀቅን ያፀናሀት፤
ባጢልን አባረህ አጭደህ የወቃሀት።
በእኔ ጭልፍ ሆሄ በአጭር አማረኛ፤
ሊደርስህ ባይችልም ተራ ፈረሰኛ፤
ላንጎራጉር ብየ እንደመንገደኛ፤
ሲሰማኝ ቋጠርኳት ከውስጤ ማደኛ።
የኔ ጀግና ብየ ባወሳህ አልጠግብም፤
አንበሰና ነህ ብልህ አንጀቴ አይገግብም።
የሀበሻው ኮከብ ስጦታው ይደንቃል፤
በማራኪ አንደበት ዒልምን ያስታጥቃል ።
#አህባሽ ግሳንግሱ ብቅ ሲል ሀበሻ፤
በሎጅክ ለማጥመቅ ሲያሳጣ መድረሻ፤
ወገቡን ሰበረው በሁጃ መዶሻ።
ተዕዊል እና ተዕጢል አንግቦ በውስጡ፤
ሹብሀ እየነዙ ምድር ሲቀውጡ፤
የሱናን ሰው ጠልተው ከሀገር ሲያስወጡ፤
ሲያስገርፉ አሳስረው ዋሽተው ሲያናውጡ።
የነብዩን መንገድ ገርሳሹ ሲበዛ፤
ውሸትን ተዋጋው ቆልቶት እየነዛ፤
ቁርአን ሀድስን ከሰለፎች መቅጃ፤
ኢጅማዕን አስፍሮ አጣቅሶ ማስረጃ፤
አበረከተልን ሹብሀን ማስወገጃ፤
ጀግናው የኔ ዑስታዝ ድንቅ ኢብኑ ሙነወር፤
ኢላማው አይስትም ሁጃው ሲወረወር።
ሱፍያን፣አህባሽን ድባቅ ያስገባቸው፤
ከአርሹ በላይነው ብሎ ፃፈባቸው።
የአህባሾች መሪ "ሀሰን ታጁ" ሲዋሽ፤
ከኢኽዋኖች መጥቶ በመውሊድን ሲቀረሽ፤
እርምት አረገበት የታሪኩን ግድፈት፤
በማስረጃ አድርጎ ውሸትን ቀበራት።
በሱና ስም ሰርገው ፊልም ለሚሰሩ፤
ተገቢ ያልሆነን ተግባር ላሰመሩ፤
አደብ አስያዛቸው በውብ መነፀሩ።
ሀጃዊራ ዘልቃ ያለ አግባብ ስትቀረሽ፤
የሁጃ ጦር ስሎ በደሊሉ ጥንቅሽ።
አልበያንን ከትቦ እያሰጣ ቀንጣሽ፤
ከታላላቆቹ ማስረጃን አጣቃሽ፤
አንተኮ ነህ ጀግናእውነትን አስታዋሽ።
አካሄዱ በሳል ንግግሩ ቁጥብ፤
ምክሩ አንጀት አርስ ነው ልብን የሚያረጥብ፤
በምን ፊደል ላውሳው በምን ቃላት ነጥብ፤
ብቻ ማር ያዘንባል ጀግና ነው እንደ ንብ።
ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤
ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤
ወዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤
አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ፤
ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤
ድምፅ ባለው ፅሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ፤
የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ ፤፦
የተክፊርን ቅሪት ወገቡን የቀጨው፤
በአንድ ንግግሩ መንጋውን ያጋጨው፤
አንድ ኳስ ወርውሮ "ሽ" ያነጫነጨው።
ለሀቅ ዘብ ቆሞ ለፍትህ የሚኖር፤
ለሱና ኻድም ነው የኢስላም መምህር።
ልክ እንደ ፔንዱለም ፊትና ሲያናውጠን፤
ድንገት ተከስቶ አካቦ ሲውጠን፤
ፈጥነህ በመመከት እረፍት የምሰጠን።
አላህ ይጠብቅህ ከመከራ ከጭንቅ፤
ከሴረኞች ተንኮል ከአይሁድ ከሙናፊቅ።
ሻፊ ነው ጌታችን በቶሎ ያሽርህ፤
ወንጀልክን አብሶ በኸይር ያበሽርህ።
የአንተን ሀላፊነት የለም የሚተካህ፤
የሀበሻው ኮኮብ አንተን ክፉ አይንካህ።
✍بقلم أبي شورى أحمد
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
~
እንዴት ናችሁ ወንድሞች እህቶች? ሰሞኑን ከደርስ የራቅኩት ባለቤቴ በወሊድ ምክንያት ሆስፒታል ገብታ ስለነበር ነው። ማታ ከመግሪብ በኋላ በሰላም ወደ ቤት ገብተናል አልሐምዱ ሊላህ። ደርስ እየገባሁ ያልነበረው ከቤት ራቅ ስላልኩ በሚመች ሁኔታ ላይ ስላልነበርኩ ነው እንጂ ህመሜ ተመልሶብኝ አይደለም። ያሰባችሁልኝ በሙሉ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን። አላህ ከክፉ ይጠብቃችሁ።
አሁንም ጠንከር ያለ ጉንፋን ድምፄን ስለዘጋኝ ምናልባት ለውጥ ከሌለኝ ጥቂት ተጨማሪ ቀናት ላልገባ እችላለሁ። እናንተን የሰጠኝ ጌታ አልሐምዱ ሊላህ። ጁዚቱም ኸይረን፣ ወኩፊቱም ሸረን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
رَبِّي إِنَّهُ يَوْمُ الْجُمُعَةِ، خَيْرُ الْأَيَّام عِنْدَكَ, فَاكْتُبْ لَنَا الْخَيْرَ فِيهِ، وَأَسْعِدْ قُلُوبَنَا، وَيَسِّرْ لَنَا أُمُورَنَا كُلَّهَا يَا اللَّهُ.
ጌታዬ ሆይ! ይህ የጁምዓ ቀን ነው፤ አንተ ዘንድ ከቀናት ሁሉ በላጩ ነው። ስለዚህ በውስጡ ለእኛ መልካሙን ጻፍልን፤ ልቦቻችንንም አስደስት፤ ጉዳዮቻችንንም በሙሉ አግራራልን ያ አላህ።
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
وكان السلف يبكون مع التقوى، وأنت تضحك مع الذنوب
አጅብ!
✍️ ደጋጎች ሰለፎች አላህን ከመፍራታቸው ጋር ያለቅሱ ነበር። አንተ ግን ከወንጀል ጋር ሁነህ ትስቃለህ።
ኢብኑል ጀውዚይ
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
مَنْقُولٌ مِنْ قَنَاةِ أَخِينَا أَبِي حَرَمَيْنَ، رَحِمَهُ اللهُ وَغَفَرَ لَهُ.
Repost from N/a
የዲን እውቀታችንን የምናዳብርበት
የተለያዩ ጥያቄ ና መልሶች
ቁርዓን እና ሀዲስ የምታገኙበት📖
🧩 ምርጥና ተወዳጅ ቻናል ✨
# ተቀላቀሉ ✅👇
Repost from N/a
🌀 ለኢስላማዊ ቻናል ባለቤቶች በሙሉ👇
👉ኑ በነፃ 💯 ቻነል እናሳድጋለን
ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥
ለ ተወሰኑ ቻነሎች ብቻ ቦታ አለን 🏃♂➡️
📌1k Subscribers ✅ 📌5k Subscribers ✅ 📌10k Subscribers ✅ 📌15k Subscribers ✅ 📌20k Subscribers ✅ 📌25k Subscribers ✅ 📌30k Subscribers ✅ከ 1000 በታች አንቀበልም ❤️🔥 🌀 ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ ... ........ 👇👇........... ...... @FaizDS @FaizDS ፍጠኑ ትንሽ ቦታ ነዉ ያለን በቀን 1 post ብቻ ስለሆነ በጣም አሪፍ ነዉ
🌺 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌺
📢 بُشْرَى سَارَّةٌ لِجَمِيعِ طُلَّابِ الْعِلْمِ!
بِفَضْلِ اللَّهِ تَعَالَى، يَسُرُّنَا إِعْلَامُكُمْ عَنْ إِقَامَةِ دَوْرَةٍ عِلْمِيَّةٍ مَكَّثَفَةٍ لِمُدَّةِ شَهْرٍ كَامِلٍ عَبْرَ الْإِنْتَرْنِت لِقِرَاءَةِ وَتَدَارُسِ الْكُتُبِ الْعِلْمِيَّةِ. فُرْصَةٌ ذَهَبِيَّةٌ لِزِيَادَةِ حَصِيلَتِكُمُ الْعِلْمِيَّةِ وَالدِّينِيَّةِ وَأَنْتُمْ فِي بُيُوتِكُمْ عَبْرَ التِّلِيجْرَامِ!
---
📚 الْكُتُبُ الْمُقَرَّرَةُ وَالأُسْتَاذَانِ الْفَاضِلَانِ:
1️⃣ الأُسْتَاذُ أَبَلُ خُبَيْب
📖 الْكِتَابُ: *الْفِرْقَةُ النَّاجِيَةُ وَالطَّائِفَةُ الْمَنْصُورَةُ*
✍️ الْمُؤَلِّفُ: الشَّيْخُ مُحَمَّدُ بْنُ جَمِيل زَيْنُو (رَحِمَهُ اللَّهُ)
2️⃣ الأُسْتَاذُ أَبُو عِمْرَان مُرَاد
📖 الْكِتَابُ: *نُورُ التَّوْحِيدِ وَظُلُمَاتُ الشِّرْكِ*
✍️ الْمُؤَلِّفُ: الشَّيْخُ سَعِيدُ بْنُ عَلِيِّ بْنِ وَهْفٍ الْقَحْطَانِيُّ (رَحِمَهُ اللَّهُ)
---
⏰ مَوَاعِيدُ وَنِظَامُ الدُّرُوسِ:
* 📅 الأَيَّامُ: مِنْ السَّبْتِ إِلَى الْخَمِيسِ (يَوْمِيًّا مَا عَدَا الْجُمُعَةَ)
* 🕒 التَّوْقِيتُ: مِنْ السَّاعَةِ 2:00 إِلَى 3:00 لَيْلًا (بِتَوْقِيتِ إِثْيُوبِيَا)
* ⏱ مُدَّةُ الدَّوْرَةِ: شَهْرٌ وَاحِدٌ فَقَطْ
* 📱 الْمَكَانُ: عَبْرَ التِّلِيجْرَامِ
---
📌 لِلتَّسْجِيلِ وَلِلْمَزِيدِ مِنَ الْمَعْلُومَاتِ:
* 📩 التَّوَاصُلُ عَبْرَ التِّلِيجْرَامِ: @[ @Abushura12 ]
*سَاهِمُوا فِي نَشْرِ الْخَيْرِ، فَـ"الدَّالُّ عَلَى الْخَيْرِ كَفَاعِلِهِ"*
https://t.me/sobabilelmesjide/10751
https://t.me/sobabilelmesjide/10751
------------➵➵➵➵----------------------------
🌺 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ 🌺
📣 አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች በሙሉ!
በአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ፈቃድ፣ ለቀልብዎ ሰኪና የሚሆን የአንድ ወር ታላቅ የኦንላይን የኪታብ ኮርስ አዘጋጅተንልዎታል። ባሉበትቦታ ሆነው በቴሌግራም የዲን እውቀትዎን የሚያስፉበት ወርቃማ እድል! 📚 የሚቀሩ ኪታቦች እና የሚያቀሩ ኡስታዞች፦ 1️⃣ ኡስታዝ አቡል ሁበይብ 📚 ኪታብ፦አል-ፊርቀቱናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራ ✍️ ፀሐፊ፦ ሸይኽ ሙሐመድ ጀሚል ዘይኑ (ረሂመሁላህ) 2️⃣ኡስታዝ አቡ ኢምራን ሙራድ 📖 ኪታብ፦ኑሩት-ተውሒድ ወዙሉማቱሽ-ሽርክ ✍️ ፀሐፊ፦ ሸይኽ ሰዒድ ኢብኑ አሊ ኢብኑ ወህፍ አል-ቀህጣኒ (ረሂመሁላህ) ⌚️ የቂርአቱ ፕሮግራም እና ሰዓት፦ • 🗓 የሚሰጥባቸው ቀናት፦ ከቅዳሜ እስከ ሐሙስ (ከጁሙዓ ውጭ በየቀኑ) • 🔜 ሰዓት፦ ማታ ከ2:00 – 3:00 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር) • ⏱ የቆይታ ጊዜ፦ ለአንድ (1) ወር ብቻ የሚቆይ • 📱 ቦታ፦ በሶባ ቢላል መስጅድ ቴሌግራም ግሩፕ 📌 የምዝገባ ሁኔታ እና ለበለጠ መረጃ፦ • 📩 በቴሌግራም ለማነጋገር፦ @[@Abushura12 ] • ይህንን ኸይር ስራ ለሌሎች ወንድምና እህቶች በማጋራት (Share) የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ! 🔤🔤🔤📎https://t.me/sobabilelmesjide/10751 🔤🔤🔤📎https://t.me/sobabilelmesjide/10751
