قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Ir al canal en Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
903
Suscriptores
-124 horas
-127 días
+4430 días
Archivo de publicaciones
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
.. በአንተነትህ ፅና.
ፈፅሞ አትላላጥ ሌሎችን ለመምሰል፡
የዋህ በመሆንህ ታመምና ቁሰል፡
ተሰቃይ ግደለም በጧትም በማታ፡
ዝቅ በል አትፍራ ሰው ከመሆን ተርታ፡
ግን ተስፋ እንዳትቆርጥ ብቻ እንዳትረታ፡
በችግር መሀል ነው #የስኬት ምስረታ፡
..እየነገርኩህ ነው..!!
አዛኝነትህን የበለጠ አራራው፡
ተሰበር ግደለም ቁስልህን አትፍራው፡
መከራ ውስጥ ነው ስኬት የሚሰራው፡
..እየነገርኩህ ነውኮ...‼️
ጨካኞች ያታሉህ ይስበሩህ እንደ ገል፡
ብቻ ወድቀህ አትቅር በድጋሜ ታገል፡
በጠላቶችህ ቀስት እንዳትሸነገል፡
በወጣትነትህ ንቃ ከመሸምገል፡
..እየነገርኩህ ነው..
ብቻ በተቻለህ መልካም ነገር ስራ፡
ሌሎችን አትምሰል ባንተነትህ ኩራ፡
ራስን መሆን ነው የጀግኖች አዝመራ፡
....አንድ ሰው ብዙ ጊዜ ተሳስቶ ነበር።
የነካው ሥራ አይሳካም፣ ያመነው ሰው ይከዳዋል፣ የጣለው እርምጃ አይሰምርም።
በዚህ ተደራራቢ ክስተት የተማረረው ሰው
አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ሰው እንዲህ አለው፦
"ልጄ ሆይ፦
ሕይወት አንተን እየቀጣችህ አይደለም፤ እያስተማረችህ ነው።" አለው
ይህኔ ወጣቱ የገባው አንድ እውነት ነበር።
በሕይወት የሚያጋጥሙን ችግሮች ሁሉ እኛን ለማጠንከር ይመጣሉ እንጂ ለመስበር አይመጡም።
....ዛሬ የምታለቅስበት ነገር ነገ ለሌላ ሰው የምትናገረው ትምህርት ይሆናል።
🔰ስለዚህ...!!
የወደቅክ ከሆነ ተነስ።
የተሳሳትክ ከሆነ ተማር።
የተከዳህ ከሆነ ጥበብ አግኝ።
የዘገየብህ ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ።
ምክንያቱም ሕይወት ሽልማት የምትሰጠው ፈጥኖ ለሚሮጥ ሳይሆን፣ ቢወድቅም እንኳ ተነስቶ ለሚቀጥል ሰው ነው።
.......ዛሬ አትበሳጭ አሁን የምታልፍበት መንገድ ነገ የምትኮራበት ታሪክ ሊሆን ይችላል።
....የፋሩቅ አባት....✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኽ ሆይ! ኡስታዝ ሆይ! አላህ በቁርአንና በሐዲሥ ዒልም ካከበረህ በኋላ ለፖለቲከኛ ጆሮህን ሰጥተህ፣ አፍህን ከፍተህ አትከታተል። ደጋሚ ናቸው፣ ቀልብህን ያበላሹታል። ምንም ያላደረጉህን ምስኪኖች በዘራቸው ልዩነት እንድትጠላ ያደርጉሃል። የራሱን የዘረኝነት ቆሻ ^ሻ አሸክሞ መስጂድና መጅሊስ ይዘህ እንድትገባ በማድረግ ያረክስሃል። እሱ የቅንጦት ህይወት እየኖረ አንተን ግን አኺራህን ብቻ ሳይሆን ዱንያህንም ያሳጣሀል።
በተለይ የሃገራችን ፖለቲከኛ የደም ነጋዴ እንደሆነ በተደጋጋሚ አይተነዋል። በቅንጦት ቤቱ ያለው ቀርቶ ጫካ ውስጥ ያለው ሳይቀር አላማው አዱኛ እንደሆነ እያየን ነው። በቅርቡ የአንድ "ታጋይ" ቪዲዮ እያየሁ ነበር። እጁ ላይ ያሰረው ውድ ሰዓት ነው። በመቶ ሺዎች የሚገመት ዋጋ ያለው ሞባይል ይዟል። የሁለቱም እጆቹ ጣቶች በወርቅ ተንቆጥቁጠዋል። ይሄ ያየነው ነው። ያልታየውስ? በዚህ ዘመን "ትግል" ቢዝነስ ሆኗል። እየዘረፈ፣ እያገተ በተለያዩ ከተማዎች ውስጥ ቤቶችን፣ መሬቶችን፣ ፎቆችን የገዙት ቀላል አይደሉም። እንደዚህ ጨው የቀመሱ አካላት በቀላል ያርፋሉ ተብሎ አይጠበቅም። በሕዝብ ስም የሚምለው ሁላ የገዛ ወገኑን አላላውስ አላንቀሳቅስ ብሎ ደም እንባ ሲያስለቅስ እያየን ነው።
ሸይኽ ሆይ! ኡስታዝ ሆይ! "ሰዎች ይሰሙ ይሆን?" ብለህ ሳትጨነቅ የዘረኝነትን አደጋ አስተምር። ወጣቱ የምላሰ ጮሌ ፖለቲከኞች ባሪያ ከመሆን ወጥቶ ለራሱም፣ ለቤተሰቡም በሚጠቅም መስመር ላይ እንዲሰለፍ ደጋግመህ ተጣራ። በዘር ጥላቻ ተሞልቶ ሌሎችን ማጥቃት ከአኺራ በፊት ዱንያን ሲያበላሽ እያየን ነው። በዚህ ዘመን የግፍ ክፍያ እጅ በጅ ሆኗል። ደካሞችን የፈጁ ሁሉ ዘግናኝ አወዳደቅ ወድቀዋል። በጅምላ የፈጁ በጅምላ ረግፈዋል። በጥላቻ ያፈናቀሉ፣ በቀያቸው መረጋጋት አቅቷቸዋል። ከቅጣት ብትር የተረፉትም አዙሪቱ አይለቃቸውም። ከአኺራ በፊት ብድር በምድር ሲሆን እያየን ነው። ነገ ደግሞ የከፋ ነው።
ዱዓቶች ሆይ! ለማስተማር፣ ለወገን ለመድረስ ጀግኖችና ቆራጦች ሁኑ። በፈሳድ መብዛት ተስፋ አትቁረጡ። የተጠራቀሙ ድምፆች ብዙ ርቀት ያስተጋባሉ። አላህ ያለላቸውን ልቦች ያነቃሉ። በቅድሚያ ግን ራስን መለወጥ ያስፈልጋል። እኛ ሳንለወጥ ለሌሎች መድረሱ ሩቅ ነው። የሌለው አይሰጥም።
ምስሉ ላይ ያለው ፅሁፍ፦
|
"የኔ ውድ የሶባሕ እናት! የቤቱን ቁልፍ እዚያ ላይ አስቀምጬልሻለሁ። በኸይር እንገናኝ" ይላታል፣ ሊገድላት እያጠመደ።
የመልእክቱ ባለቤት ከፊርማው አጠገብ "የሶባሕ አባት ነኝ" ይላል። ወዳጅ መሳይ ጊ Nጥ!
የአብዛኛው ፖለቲከኛ ምክር እንደዚህ ነው። በገዛ ወገኑ ላይ ቂም ያረገዘ እስከሚመስል መሞቻውን ነው የሚያዘጋጅለት። ደጋግሞ ሞቱን ጉዳቱን እያየ እንኳን አይደነግጥም። አላህ ይገላግለንና።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል።
ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል።
ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from تَحْتَ ظِلِّ الْعَرْش
በዚህ ዘመን በየ አቅጣጫው ተከፋፍሎ የሚላተመው አካል ትልቁ ችግሩ የተቅዋ መቅለል ያመጣው የኢንሷፍ ችግር ነው።እራሱ ጋር ያለ ችግር ይደብቃል ሌላውን ያጠቃል !
🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሓፊዘሁላህ
~ t.me/Darutewhide
ስለተናገርክ፣ስላስተማርክ ብቻ አንተ የተሻልክ ነህ ማለት አይቻልም !!
በዚህ ዘመን መለኪያ እየሆነ ያለው ዝና፣ የ"ተከታይ" ብዛት እና የመሳሰለው ከንቱ ነገር ነው....
አፈር ይብላ ዝና !
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑር
https://t.me/MerkezulimamiAhmed
Repost from Abu useymin (Mohammed Ali)
علينا أن نحرص على ألا نتكلم إلا بعد محاسبة للنفس، هل هذه الكلمة تنفعني يوم القيامة حين ألقى الله جل وعلا أو تضرني؟ فإن كانت مما ينفع أَقْدَم، وإن كانت تضر أَحجَم، وإن كان لا هذا ولا هذا فمن حسن إسلام المرء تركه ما لا يعنيه، ويدخل في الكلام الكتابة.
-----
سلسلة المحاضرات العلمية والتربوية للشيخ عبدالكريم الخضير - ص١٣٦ 📖
