cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ፣ ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው። ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ። ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ። አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ ያድርገን። ቻናሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት 👉 @NejaLobete 👈

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 170
Suscriptores
+624 horas
+477 días
+4830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

"አንተ ጠዋት ተንስተህ ፊትህን ስታጥብ ሌላኛው ደግሞ ጠዋት ተንስቶ ኩላሊቱን የሚያሳጥብ አለና ምንም ባይኖርህም ጤናህን አሟልቶ ለሰጠህ ጌታህ ሁሌ አመስግነው" !!                          አልሐምዱሊላህ በል!!
Mostrar todo...
👍 8
ምነው ዝም አላችሁሳ! ወይስ የአቅማችሁን እየሰደቃችሁ ነው?
Mostrar todo...
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ ውድና የተከበራችሁ የቻናሌ ተከታታይ ወንድምና እህቶች ዛሬ ሁላችሁንም ላስቸግራችሁ ፈለኩኝ እሱም ምንድነው አንድ በጣም የተቸገረች እህታችሁን ሁላችሁም በቻላችሁት አቅም እንድትረዷት እላለሁ። እህታችን የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ባለቤቷ ደግሞ ለውትድርና ወይም ለምልሻነት ኮርስ ይሰጠሃል ብለውት ወደ ጦር ሃይሎች ወደ ሚገኘው ካምፕ ወስደውት መጀመሪያ አከባቢ ይደውል ነበር አሁን መደወል ካቆመ ሁለት አመት እየሆነ ነው ብላለች።ፎቶውንም ይዤ ወደ ካምፑ ሄጄ ስጠይቃቸው እኛጋ የለም አሉኝ ትላለች።እና በጣም እንደተቸገረች ነው የነገረችኝ።የቤት ኪራይ 3000 ብር የምከፍለው።ስራም የለኝም። የቤት ኪራይ የሁለት ወር ተደራቦብኛል።አከራይዋ የማትከፍዪ ከሆነ ቤት ልቀቅልኝ ብላለች። በጣም ስትጨቀጭቀኝ አጃምባ አንድ እህቴ አለች እሷም ቤት ፈርሶባት ተከራይታ ነው የምትኖረው ሲጨንቀኝ እሷ ጋ ነው ያለሁት።ሶስተኛ ቀኔ ነው ትላለች እህታችን! እኔም ነገሩን በማውቀው ሰው ለማጣራት ሞክሬ ነበር እውነትም በጣም እንደተቸገራች ነው የነገሩኝ። ስለዚህ ሁላችሁም በምትችሉት ተባበሯት ባረከሏሁ ፊኩም! ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን! ስም:- ሸሚማ ሱልጣን አብዶ የአካውንት ቁጥሯ:- 1000460707308
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ውድ የ #ተከታታዮቻችን በሙሉ የምንፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉን #UNMUTE ካደረጉት እንዳሉም አይቆጠርም🤷‍♀ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት 👍 #UNMUTE❗️ የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን  MUTE ✅ ላይ በማድረግ ያግዙን ኢንሻ አላህ ሁላችሁም ታደርጋላችሁ ብዬ አስባለሁ። @AbuMeryemNeja
Mostrar todo...
👍 8👌 1
🔈 #ተጠንቀቁ ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ። " ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦ - ስራው ምንድነው ? - በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ? - የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን ! - ባለበት ሀገር ሕጋዊ ስርዓት የተመዘገበበትን ፋይል አሳዩን ! ብላችሁ ጠይቋቸው። ከዚህ ውጭ በተድበሰበሰ ሁኔታ " ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው የምታገኙት " በሚል ብቻ መረጃ ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ የውጭ ሂደት ብታቋርጡ መልካም ነው። አንዳንድ ስለ ገንዘብ እንጂ ፍጹም ስለ ሰው ህይወት የማያሳስባቸው ደላሎች እና ኤጀንሲዎች በርካታ ወጣቶችን እያታለሉ መጀመሪያ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ሌላ ምንም ደህንነቱ ወዳልተረጋገጠ ሀገር እየላኩ ሰዎችን በማጭበርበር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች እያስገቧቸው ነው። በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል። የወጣትነት ጊዜያችሁ ሳያልፍ ህይወታችሁን ለማሻሻል ብላችሁ እጅግ ተቸግራችሁ ፤ ቤተሰብም አስቸግራችሁ ብዙ ብር ከፍላችሁ ወደ ውጭ ሀገር የምትሄዱ ልጆች ስለምትሄዱበት ሀገር እና ስራ በደንብ አጣሩ አንብቡ። ዘመኑ  የቴክኖሎጂ  ነውና በስልካችሁ ላይ ገብታችሁ የምትሄዱበት ሀገር ስላለው ደህነት፣  ስላለው የስራ ሁኔታ ፣ እናተም ትስሩታላችሁ ስለሚባለው ስራ በደንብ አረጋግጡ። በኦንላይን የማያታውቁት ሰው ወይም በማስታወቂያ " ለስራ ወጣቶችን እንፈልጋለን " ሲሉ አትመልሱላቸው። ⚠️ በቀጣይ " ጠቀም ያለ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ነው ! " እየተባለ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በብዛት ወጣቶችን በማዘዋወር አንዳንድ ድርጅቶች እያስገቡ ወጣቶችን የሚያሰሯቸውን የኦንላይን ማጭበርበር  / Online Scam / ድርጊት አይነቶችን በዝርዝር እንዳስሳለን። 📝 tikvahethiopia t.me/AbuMeryemNeja
Mostrar todo...
Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ፣ ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው። ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ። ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ። አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ ያድርገን። ቻናሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት 👉 @NejaLobete 👈

👍 2
አልሐምዱሊላህ ተፈተዋል። በትላንትናው እለት ሜክሲኮ አከባቢ ላይ ዳዕዋ በሚያደርጉበት ጊዜ የታሰሩ የነበሩ ወንድሞቻችን አሁን ተፈተዋል። በዱዓችሁ ከጓናቸው የነበራችሁ ወንድም እና እህቶቻችን ጀዛኩሙላሁ ኸይራ። ነገር ግን ይህ ጉዳይ ወጥ መፍትሄ ልናበጅለት የሚገባ ነገር መሆኑን መዘንጋት የለብንም!!
Mostrar todo...
👍 9
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ በዛሬው እለት በጎዳና ዳዕዋ ላይ የሚንቀሳቀሱ ኡስታዞች መታሰራቸውን ሰምተናል። ነገሩን አላህ ቀለል እንዲያደርግላቸው እና ቶሎ እንዲወጡ መልካም ዱዓችሁ አይለያቸው!! የታሰሩት ወንድሞቻችን ስም ዝርዝር 1 ስራጅ ሳሊም፣ 2 ሙባረክ ላሌጋ 3 አብዱልሰመድ  ዑመር 4ዩሱፍ ሙሐመድ 5 አስረስ ሰብስቤ 6 ዐብዱልባሲጥ ከማል አሁን ቄራ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ናቸው የሚመለከተው አከል ጉዳዩን ክትትል መድረግ አለበት ።
Mostrar todo...
👍 10 1
ኢትዮ ቴሌኮም ለ3 ቀናት የሚቆይ ነፃ የዳታ፣የድምፅና የፅሁፍ ጥቅል ስጦታ አበርክቷል። ተጠቀሙ! ለሌሎችም ሼር አድርጉ! እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!! በ2016 በጀት ዓመት 93.7 ቢሊዮን ብር ገቢ በማግኘት የዕቅዳችንን 103.6% ማሳካታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው! እርስዎም የስኬታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ከነገ ሐምሌ 5- 7/ 2016 ዓ.ም ለ3 ቀናት የሚቆይ 1 ጊ.ባ ዳታ፣ 25 ደቂቃ የድምጽ እና 50 አጭር መልዕክት የምስጋና ስጦታ አበርክተንልዎታል፡፡
Mostrar todo...
👍 6😁 6🤣 1
አንድን ሰው ስትወደውም ስትጠላውም ምክንያት ይኑርህ። ውዴታህም ጥላቻህም ድንበር ያለፈ አይሁን። በልክ ይሁን። ምክንያቱም አንድን ሰው ስትወደው ውዴታህ ድንበር ያለፈ ከሆነ ያ ሰው የፈለገ ነገር ቢሰራ ያ ነገር ሁሌም ላንተ ትክክል ይመስለሃል። ግልፅ የሆነ ጥፋት ብያጠፋ እንኳን ለዛ ነገር ሌላ ምክንያት ትፈልግለታለህ። በተቃራኒው አንድን ሰው ስትጠላው ወይም ለዛ ሰው ያለህ ጥላቻ ድንበር ያለፈ ከሆነ ደግሞ ያ ሰው የፈለገ ትክክል የሆነ ነገር ቢሰራ እንኳን ላንተ ምንም አይመስልህም። ያንን ነገር ውድቅ የሚታደርግበትን መንገድ ትፈልግለታለህ። ነገሩ ትክክል መሆኑን ውስጥህ ከማወቁም ጋር ግን ያንን ነገር ለማስተባበል ብዙ ጥረት ታደርጋለህ። ይህ ምቀኝነትም ነው። አንድን ሰው ስትወደውም ስትጠላውም ምክንያት ካለህ፣ ውዴታህም ሆነ ጥላቻህ በልክና ድንበር ያላለፈ ከሆነ ግን ያ ሰው መልካም ሲሰራም በሰራው ስራ ልክ ትወደዋለህ። ስህተትም ሲሰራ በስህተቱ ልክ በጥፋቱ መጠን ትጠለዋለህ። ስትወደውም ሆነ ስትጠላው ምክንያት ይኖረሃል። በልክ ትሆናለህ። ውዴታህም ሆነ ጥላቻህ ድንበር ያለፈ አይሆንም። 🖌ወንድማችሁ:- አቡ መርየም የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ። 👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈
Mostrar todo...
Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ፣ ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው። ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ። ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ። አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ ያድርገን። ቻናሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት 👉 @NejaLobete 👈

👍 2
- የምትሄድባቸው መንገዶች ሁሉ ስኬትም ሆነ ውድቀት ሊኖራቸው ይችላሉ፣ የቁርአን መንገድ ግን በየትኛውም አቅጣጫ ብትመጣበት በምንዳ የተከበበ ነው!። ሀታ! በርሱ መንተባተቡ ራሱ ትመነዳበታለህ። 🖌Abdurehman Aman 👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈
Mostrar todo...
Abu Meryem Channel (አቡ መርየም ቻናል)

ተውሒድና ሱና የአንድነት ምንጭ ሲሆኑ፣ ሺርክና ቢድዓ ደግሞ የልዩነት ምንጭ ናቸው። ስለዚህ ተውሒድና ሱና አጥብቀህ ያዝ። ሺርክና ቢድዓ ደግሞ በእጅጉ ራቅ። አላህ ቁርኣንና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች መንገድ አረዳድ ተረድተው ከሚጓዙ ምርጥ ባሮቹ ያድርገን። ቻናሉን ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። ለስተያየትና ጥቆማ እንዲሁም እርምት 👉 @NejaLobete 👈

👍 8
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.