es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Ir al canal en Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
906
Suscriptores
-124 horas
-127 días
+4430 días
Archivo de publicaciones
የሰለፎችን መንገድ በሁሉም ነገር መከተል ግደታ እንጅ ምርጫ አይደለም ታላቁ አሊም - ሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸሊይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ ፦ "فأوصيكم يا أخوة أن تسيروا في طريق السلف الصالح تعلماً وأخلاقاً ودعوة، لا تشدد لا غلو، دعوة يرافقها الحلم والرحمة والأخلاق العالية" - العلامة ربيع المدخلي رحمه الله (الذريعة (3/214)) "ወንድሞች ሆይ! በመልካም ቀደምቶች መንገድ እውቀትን በመፈለግ፣ መልካም ሥነ ምግባርን በመላበስ እና ወደ መልካም በመጣራት እንድትጓዙ እመክራችኋለሁ። አትጠብቁ፣ አታጋንኑ። ጥሪው ከትዕግስት፣ ከእዝነት እና ከከፍተኛ ስነምግባር ጋር ይሁን።" ምንጭ  (አል-ዘሪዐህ (3/214)) ይህ የሸይኽ ረቢዕ ረሂመሁሏህ ንግግር በውስጡ እነዚህን ምክሮች የያዘ ነው 👇👇👇 1. በመልካም ቀደምቶች መንገድ ላይ መጓዝ (السير على طريق السلف الصالح):   • መልካም ቀደምቶች ማናቸው ? መልካም ቀደምቶች ማለት ነብዩ ሙሐመድ ﷺእና ሶሓቦች (የነብዩ ባልደረቦች) ታቢዕዮች አትባዑ ታቢዕዮች ናቸው።   •  ምን ማለት ነው በመንገዳቸው ላይ መጓዝ? ይህ ማለት ቁርኣንንና ሐዲሶችን በተገቢው መንገድ በሰለፎች አረዳድ መረዳትና መተግበር ማለት ነው። እንዲሁም እነሱ የተላበሷቸውን መልካም ስነ ምግባሮች መከተል ማለት ነው። 2. እውቀትን መፈለግ (تعلماً):   •  የምን አይነት እውቀት? በእስልምና እውቀት ማለት ቁርኣንን፣ ሐዲሶችን እና ሸሪዓን (የእስልምና ህግጋት) መማር ማለት ነው።   •  ለምን እውቀት እንፈልጋለን? እውቀት አላህን በትክክል እንድንገዛ፣ መልካምን ነገር ከክፉው እንድንለይ እና በትክክለኛው የሰለፎች መንገድ እንድንጓዝ ይረዳናል። 3. መልካም ስነምግባርን መላበስ (وأخلاقاً):   •  ምን አይነት ስነምግባር? ትህትና፣ እውነትን መናገር፣ ቃልን መጠበቅ፣ ለሰዎች ደግ መሆን እና ሌሎችን ይቅር ማለት መልካም ስነ ምግባሮች ናቸው።   •  ለምን መልካም ስነምግባር ሊኖረን ይገባል? መልካም ስነምግባር የአላህን ውዴታ ያስገኝልናል፣ በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ያደርገናል፣ እናም ህይወታችንን ትርጉም ያለው ያደርገዋል። 4. ወደ መልካም ነገር መጣራት (ودعوة):   •  እንዴት ወደ መልካም ነገር እንጣራ? ሰዎችን በመልካም ቃል፣ በተግባር እና ለሰዎች አርዓያ በመሆን ወደ አላህ መንገድ ወደ ትክክለኛዋ የሰለፎች ጎዳና በመጣራት ነው።   •  ለምን ወደ መልካም ነገር እንጣራለን? ሙስሊም እንደመሆናችን ሌሎችን ወደ መልካም ነገር የመምራት የመጣራት ግዴታ አለብን። 5. ልክን መጠበቅ እና ማጋነን አለመኖር (لا تشدد لا غلو):   •  ምን ማለት ነው ልክን መጠበቅ? በእምነትም ሆነ በተግባር ጽንፈኛ አለመሆን።   •  ለምን ልክን መጠበቅ አለብን? እስልምና የሰለፎች መንገድ ቀላል እና ሚዛናዊ ሃይማኖት ነው። ማጋነን ወደ ጥመት ሊያመራ ይችላል። 6. ትዕግስት፣ እዝነት እና ከፍተኛ ስነምግባር (الحلم والرحمة والأخلاق العالية):   •  ለምን እነዚህ ነገሮች ያስፈልጉናል? ሰዎችን ወደ መልካም ነገር በምንጣራበት ጊዜ በትዕግስት፣ በስሜታዊነት እና በከፍተኛ ስነምግባር መሆን አለብን። በኃይል ወይም በጭካኔ ሰዎችን ልብ ማሸነፍ አንችልም። ስለዚህ በህይወታችን ውስጥ መልካምነትን እንድንከተል፣ ሌሎችን ወደ መልካም ነገር እንድንመራ፣ ሚዛናዊ እንድንሆን እና በሁሉም ነገር ላይ መልካም ስነምግባርን እንድንላበስ ያበረታታል። 📝 ወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ... https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

*دين الله بين الغالي فيه والجافي عنه* يقول الشيخ العلَّامةُ صالح بن فوزان الفوزان -حفظه الله تعالى- :- "هناك من يدعي أنه على مذهب السلف لكن يخالفهم، يغلو ويزيد، ويخرج عن طريقة السلف، ومنهم من يدعي أنه على مذهب السلف ويتساهل، ويضيع ويكتفي بالانتساب. الذي على منهج السلف يعتدل ويستقيم بين الإفراط والتفريط، هذه طريقة السلف لا غلو ولا تساهل، ولهذا قال الله تعالى: {... وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَنٍ...} فإذا أردت أن تتبع السلف لابد أن تعرف طريقتهم، فلا يمكن أن تتبع السلف إلا إذا عرفت طريقتهم وأتقنت منهجهم من أجل أن تسير عليه، وأما مع الجهل فلا يمكن أن تسير على طريقتهم وأنت تجهلها ولا تعرفها أو تنسب إليهم ما لم يقولوه ولم يعتقدوه تقول: هذا مذهب السلف. كما يحصل من بعض الجهال-الآن- الذين يسمون (سلفيين) ثم يخالفون السلف ويشتدون ويكفرون، ويفسقون ويبدعون، السلف ما كانوا يبدعون ويكفرون ويفسقون إلا بدليل وبرهان، ما هو بالهوى أو الجهل، أنك تخط خطة وتقول: من خالفها فهو مبتدع، فهو ضال، لا-يا أخي- ما هذا بمنهج السلف منهج السلف العلم والعمل، العلم أولاً ثم العمل على هدى، فإذا أردت أن تكون سلفياً حقاً فعليك أن تدرس مذهب السلف بإتقان، وتعرفه ببصيرة ثم تعمل به من غير غلو ومن غير تساهل، هذا منهج السلف الصحيح، أما الادعاء والانتساب من غير حقيقة فهو يضر ولا ينفع ". [من إجابات الشيخ على أسئلة الحضور في شرح العقيدة الطحاوية لعام ١٤٢٥،

የታላቁ ሀበሻዊ ዐሊም ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ አል ወለዊ አልቦረንይ ረሂመሁላህ ትምህርቶች በApp ተዘጋጅተው ቀርቦለዎታል።ለሌሎችም share እናድርግ።ባረከላሁ ፊኩም።

📢 አዲስ አፕ ተለቀቀ! 📖 የውርስ ህግን የተመለከቱ ትምህርቶች ✍️ 3ት ኪታቦችን በአንድ የያዘ App 🎙 የደርሱ አቅራቢ:- 🎧 ኡስታዝ አቡ ሒዛም አብዱረህማን ሰዒድ ━━━━━━━━━━━━ 1️⃣ منظومة القلائد البرهانية 👤 ሸይኽ መሀመድ አልቡርሃኒ 27 ክፍል 2️⃣ تقريب الفرائض 👤 ዶ/ር ዐብዱረህማን ቢን ሱለይማን አሽ-ሸምሳን 25 ክፍል 3️⃣ تلخيص فقه الفرائض 👤 ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን 10 ክፍል ━━━━━━━━━━━━ (PDF ከድምፅ ጋር     (ማስታወሻ መፃፍ ይቻላል (ያለ ኢንተርኔት ይሰራል (ጥራቱን በጠበቀ ድምፅ አሁኑን ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቀዳሽ ይሁኑ! 📡 ለተመሳሳይ ስራዎች ቻናላችንን ይቀላቀሉ 🔗 https://t.me/kasimApp      የኡስታዝን ቻናል ለማግኘት      https://t.me/durusuabihizam

Repost from Dr. Seid Musa
قال الشيخ إبراهيم المحيميد - حفظه الله تعالى - : "هذه البلاد المباركة أسسها المحمدان ابن سعود وابن عبدالوهاب على تحقيق الركن الأول في الإسلام قولا وعملا واعتقادا' ومضمونها الدعوة للتوحيد الصافي النقي أولا، ثم القضاء على البدع والمحدثات ' وسار ولاة أمورنا علماء وأمراء على هذا من ثلاثة قرون حتى هذه الساعة ' وأي دعوة لإحياء البدع والخرافات في ديار ابن سعود من أي شخص مهما كان منصبه الشرعي هي محاولة لهدم الأساس الذي قامت عليه هذه البلاد المباركة، وقدمت في سبيل دعوة الرسل النقية دماء زكية وهدمت مدنها " فمنذ تأسيسها لاقبور تعبد ولازوايا صوفية تقرر فيها البدع والمحدثات وستبقى بإذن الله هي الحصن الحصين لدعوة أهل السنة ' وانتشر هذه الأيام مقطع لصاحب منصب شرعي يؤصل لبدعة المولد النبوي ويساوي بين صلاة التهجد وبين الاحتفال بالمولد النبوي وأن لكلا الفعلين أصلا يستند عليه، ومستنده في تجويز المولد أن الله أمرنا بالفرح بفضل الله ورحمته' ولسان حاله يقول دعوا الناس يحتفلون بمولده من باب الفرح ' والجواب على هذه الشبهة من أوجه : الوجه الأول : أن صلاة التهجد ليست ببدعة من العمل، ووجه ذلك أن النبي فرض عليه قيام الليل في مكة حرسها الله، وواظب عليه، وفي المدينة كان يجتهد في رمضان عامة، والعشرة الأواخر خاصة، ما لا يجتهد في غيره، فعن أم المؤمنين عائشة - رضي الله عنها - قَالَتْ: كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ يَجْتَهِدُ فِي رَمضانَ مَا لا يَجْتَهِدُ في غَيْرِهِ، وَفِي العَشْرِ الأَوَاخِرِ منْه مَالا يَجْتَهدُ في غَيْرِهِ" فقيام الليل كان فرض عليه في أول الأمر ، ولايفهم من أحاديث الاجتهاد في رمضان إلا كثرة النفل " سواء سمي تهجدا أو لم يسم، سواء كانت تصلى متواصلة أو متقطعة ' السؤال أين وجه البدعة هنا ؟ الوجه الثاني : أما تجويزه لبدعة المولد استنادا لقوله تعالى (قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجمعون) وأن من الفرح الاحتفال بمولده فالجواب عنه أن الفرح عمل قلبي، والمولد عمل بدني، ومن شروط القياس استواء الفرع بالأصل. الوجه الثالث : قيام الليل صلاة والتهجد كذلك صلاة وتخصيصها بالعشر الأواخر لفعل الرسول وقيام المقتضى في كثرة التنفل لهذا الفعل وهو تحري ليلة القدر . الوجه الرابع : والله لو صح القياس لكان يتعين اليوم منعه لما يحدث في الموالد من غلو وبدع لا ترضي الله ورسوله' الوجه الخامس: التهجد دعاء وسجود وركوع ودموع وإنابة وتوبة، والموالد ضلالات ومحدثات ورقص وضرب بالدفوف وغلو لجناب الرسول . أين الثرى من الثريا ؟".

«ስም አልጠራም» ----------------- ደሊልና ስሜት የተምታታባችሁ፡ የምትበጠብጡን መንጋ መስርታችሁ፡ መስመር አትሳቱ ተው ስንላችሁ፡ ምክርን እንደ ቅናት እየቆጠራችሁ፡ እስከዛሬ ድረስ ምን አተረፋችሁ⁉️ ጥቅምና ጉዳት ፍፁም የማትለዩ፡ በሐቅ መረጃ የማትወያዩ፡ በጥላቻ ብቻ የምትሰቃዩ፡ ሆስፒታል ግቡና ከአንገት በላይ ታዩ፡ በምንኖርባት በዚህች ጠፊ ሀገር፡ ጎምዝዞ ቢመርም እውነትን መናገር፡ መከራ ቢዘንብም ወንዙን ለመሻገር፡ ከጫጩቶች መሐል ፈንግል ባይወራም፡ ስምን ከነቦታ ለመጥራት ባልፈራም፡ መንጋ ተፈታተሽ እኔ ስም አልጠራም፡ .....ኑር.... t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

فإن السلفية عمل وليست دعاوىٰ فَاسْتَمْسِكْ بِالَّذِي أُوحِيَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ وأما أقوال الناس فيك وافترائهم وظنونهم السيئة فمرض وهَمٌّ  يحملونه ويتأذون به هم وتسلّى بتسلية الله لك ولأمثالك إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِي بَيْنَهُم بِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْعَلِيمُ (78) فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ (79) سورة النمل لن يضروكم إلا أذى ينبغي أن ينزل السلفيون هؤلاء منزلة الكلاب تنبح هي ثم تسكت لكن الكلب إذا زجرته ورميت عليه زاد نباحاً فألقمه إن شئت عظماً لعله يسكت. أو كلما طن الذبابُ زجرته * ..... إن الذباب إذاً علَى لعزيز! أحسن لك أن لا ترد الجواب على اللئيم فالسكوت أضر عليه من الجواب لأن الجواب يفتح له المجال يسب ويشتم أكثر فأكثر. وصدق من قال: «ولقد أمرُّ على اللئيم يشتمني، فمضيت ثم قلت لا يعنيني» (ولا يقصدني) أيها السلفي፡ أثبت فإنك علىٰ الحق المبين.. ولا يغرنّك الأدعياء من #اللتمىين #والحدادىين الكذابين والمدسوسين المفتونين الذين يدّعون السلفية #زورًا #وتلبيسًا علىٰ الناس وعند الله تجتمع الخصوم "ሰለፍያ ማለት በተግባር የሚገለጽ እንጂ በባዶ የይገባኛል ጥያቄ (ወሬ) አይደለም።" (ወደ አንተ የተወረደውን አጥብቀህ ያዝ። አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና።) [ሱረቱል ዙኽሩፍ፡ 43] ሰዎች ስለ አንተ የሚናገሩት ንግግር፣ የሚያወሩት ቅጥፈት እና መጥፎ ጥርጣሬያቸው፤ እነሱው ራሳቸው ተሸክመውት የሚሰቃዩበትና የሚጎዱበት በሽታ እና ጭንቀት ነው። ስለዚህ አላህ ለአንተ እና ለመሰሎችህ በሰጠው መጽናኛ ተጽናና። (ጌታህ በመካከላቸው በፍርዱ ቀን ይፈርዳል። እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው። በአላህም ላይ ተመካ። አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።) [ሱረቱል ነምል፡ 78-79] (ማስከፋትን እንጂ ምንም አይጎዱአችሁም...) [ሱረቱ አሊ-ዒምራን፡ 111] ሰለፍያዎች እነዚህን ተሳዳቢ ሰዎች ልክ እንደሚጮህ ከዚያም ዝም እንደሚል ውሻ ሊቆጥሯቸው ይገባል። ውሻን በጮህክበት እና በተቆጣኸው ቁጥር ጩኸቱን ይጨምራል። ከፈለግክ ግን ዝም እንዲል አጥንት ወርውርለት። እንደተባለውም ግጥም፦ ዝንብ ባንጫጫ እና በጮኸ ቁጥር የምመልስለት ከሆነ...እንግዲያውስ ዝንቡ ትልቅ ክብር አገኘ ማለት ነዋ!!! ለመጥፎ ሰው መልስ አለመስጠትህ ለአንተ የተሻለ ነው። ዝምታ ከመመለስ የበለጠ ይጎዳዋል። ምክንያቱም መልስ መስጠትህ አብዝቶ እንዲሳደብ እና እንዲዘልፍ በር ይከፍትለታል። እውነተኛው ተናጋሪ ገጣሚ እንዲህ እንዳለው ነው፦ «አንድ ባለጌ ሲሳደበኝ አለፍኩት። መንገዴንም ቀጠልኩና እኔን አይመለከተኝም እኔን አስቦ አይደለም አልኩኝ።» አንተ ሰለፊ ሆይ! ፅና! አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና። ከሰዎች ዘንድ ሰለፍይ ነን እያሉ በውሸት እና በማደናገር ከሚሞግቱት አጭበርባሪ #ለተምዮች እንዲሁም ውሸታም ከሆኑ #ሐዳዲዮች ሰርገው ገቢዎች እና ፈተና ውስጥ ከወደቁት ሰዎች አትታለል። የሚሟገቱ ባለጋራዎች ሁሉ ነገ አላህ ዘንድ ይሰበሰባሉ።" የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

አላህዬ... አሁን ደስታቸው እና ምኞታቸው እውን ሊሆን ከተቃረቡት ባሮችህ አድርገን።🌹

ሰለፍያ vs ሰለፍዮች ከእድሜያችን አኳያ፤ ወጣቶች ነንና ከስህተት ባንርቅም፡ ምን እንኳ ከወንጀል፤ ....እንደ ሷሊሆቹ ባንጠነቀቅም፡ በመንሀጃችን ግን፤ እንኮራለን እንጂ አንሸማቀቅም፡ لسنا أهل مواسم واحتفالات وشعارات بل نحن أهل سنة واتباع وآثار እኛ የበዓላትና የመፈክር ሰዎች አይደለንም... ይልቁንም የሱናንና የትምህርቱ ተከታዮች የምንከተል ቀደምቶችን አርዓያ አድርገን የምንጓዝ ፋና ወጊ ትውልዶች ነን። ...ኑር....✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

     እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!!    ብቸኝነት ላደከማቸው፤ በኃላፊነት ሸክም ለተጫኑ፤ ረጅም ጊዜ በመጠበቅ ለሰለቹ፤ መጨረሻው በማይታወቅ መንገድ ፊት ለፊት በመቆም በፍርሃት ለተዋጡ ሁሉ...…… ከኡሙ ኢስማኢል ሀጀር የተላለፈ መልእክት;       "እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!"    ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም በጌታው ትዕዛዝ ምንም ዓይነት ሰው፣ ተክልም ይሁን ውሀ በሌለበት ምድረ በዳ ሸለቆ ከጨቅላ ህፃኗ ጋ ብቻዋን ትቷት ሄደ።   እሷ ግን ፍርሃቷን አልደበቀችም፤ የሌላት ጥንካሬ እንዳላትም አላስመሰለችም። ይልቁንስ እንዲህ ስትል ጠየቀች፦    "ይህንን እንድታደርግ ያዘዘህ አላህ ነውን???" የአላህ ትዕዛዝ መሆኑን ባወቀች ጊዜ;; በጉዞው አስቸጋሪነትም ይሁን በባይተዋርነት መከራ የማይናወጥ የፅናት ቃል ተናገረች;      "እንግዲያውስ አላህ አይተወንም!!"    ሀጀር ፈረጁ በየት በኩል እንደሚመጣላት አታውቅም ነበር: ግና ፈረጁ ያለው በማን አጅ እንደሆነ ጠንቅቃ ታውቃለች።    እንዲሁ ተቀምጣ ተኣምር እስኪመጣላት አልጠበቀችም፤ በሰፍዋ እና በመርዋ መሃል ተመላልሳ ሮጠች። አንዴ… ሁለቴ በተመላለሰችበት መንገድ ምንም ነገር ካለማግኘቷም ጋ ተስፋ ባለመቁረጥ ተመላልሳ በፍጥነት ትሮጣለች።    ፍርሃቷን ይዛ ትሮጣለች፤ ምንም ካለማግኘቷም ጋ እየሮጠች ትፈልጋለች። ይህ ሁሉ ሲሆን ልቧ ጌታዋ ላይ ከነበረው መተማመን አልተወገደም። በመጨረሻም……………      የዘምዘም ምንጭ ፈለቀ፤ የሀጀር ሩጫም እስከ ዕለተ ቂያማ ድረስ አላህ የሚመለክበት ስርዓት ሆኖ ቀጠለ። ትልቁ ትምህርት ያለው እዚህ ጋ ነው፦    ፈረጁ እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን ማለት: ከፍርሃት ነፃ መሆን ማለት አይደለም።    ባይሆን; ፍራቻህ አላህ ላይ ከሚኖርህ መተማመን የበለጠ ሀይል እንዲኖረው አለመፍቀድ ማለት ነው። ወዳጄ………    ዛሬ አንተም በራስህ ምድረ በዳ ሸለቆ ትሆን ይሆናል;    ማንንም በማያየው ብቸኝነት ውስጥ፤  ትከሻህን በሚያደቅ ኃላፍትና ስር፤  በጣም በሚያም መለያየት፤   ረዥም ጊዜ በቆየ መጠባበቅ፤  ከፊትህ በተዘጋጉ በሮች ወይም  አላህ ብቻ በሚያውቀው ውስጣዊ ትግል እየኖርክ ይሆናል። እናማ…………     የእፎይታ ጊዜ በመዘግየቱ "አላህ ትቶኛል" ብለህ እንዳታስብ!!     ያፈሰስካቸው እምባዎች ፍሬ አለማየትህ እርግጠኝነትህን እንዳይሸረሽረው!!   የምትችለውን ያህል ጥረት አድርግ፤ በእጅህ ያሉ እርምጃዎች ሁሉ ተግባራዊ አድርግ።    ከአንተ ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ነገሮች; የነገሮች ሁሉ ተቆጣጣሪ ለሆነው ስጥ!! ሀጀርን ተመልከት፦    ፍለጋዋ ስትጀምር ውሀው የቱጋ እንደሆነ አታውቅም ነበር፤ በአላህ ዕውቀት ግን ውሀው በጣም ቅርብ ነበር!!    በተስፋ መቁረጥ እና በእርግጠኝነት መሃል ያለው ልዩነትም ይህ ነው፦ መፍትሔው በማይታይህ መንገድ እየሄድክ በፅኑ ልብ;       "አላህ አይተወኝም!!" ማለት የሀጀር ጌታ የአንተም ጌታ ነው;    ከበረሃው እምብርት ዘምዘም ያፈለቀው አላህ: ለአንተም በመከራዎችህ መሃል በር የመክፈት ሀይል አለው!!    ከችግር በኋላ እፎይታ፤ ከመደናበር በኋላ እርጋታ እንዲሁም ከረዥም ጥበቃ በኋላ ፈረጅን የሚያመጣው እሱ ነው። መድረሻህን ስላልታየህ ብቻ; ጉዞህን አታቋርጠው!!     ምንም እንኳ እስካሁን ፈረጁ ጋ ባትደርስም: ምን አልባት ፈረጁ ከምታስበው በጣም የቀረበ ሊሆን ይችላል።          አብሽር አላህ አይተወንም!!!

⛔️ሱስ የሆነን ክፉ ወረርሽኝ‼️⛔️ ~ ስለ ሌሎች ጥፋት መናገር የሚፈልግ ሰው የመጀመሪያው የሚጠበቅበት ነጥብ ማስረገጥ ነው። የተነገረን ነገር የእውነት በተወራው መልኩ ነው ወይ? ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ማስረገጥ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው፣ #ዋጂብ። ➛አሉባልታ ላይ ተመስርቶ ማማት፣ ➛ፍረጃ ውስጥ መግባት፣ ➛ነገር ማራገብ፣ ➛ለመልስ መቸኮል...... ❶.ደኛ‼️ ከተቅዋ ጋር የሚሄድ አይደለም። ❷.ተኛ‼️ ከማንም በላይ የሚጎዳው እኛኑ ነው። ✅ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ كَفى بالمَرءِ كَذِبًا أن يُحَدِّثَ بكُلِّ ما سَمِعَ "አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ ከውሸት በኩል (ውሸታም ለመባል) በቂው ነው። " [ሙስሊም፡ 5] ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “በሰው ላይ መዋሸት ሰውየው ሙስሊምም ሆነ ካ^ፊር፣ መልካምም ሆነ አመፀኛ ሙሉ ለሙሉ ክልክል ነው። በሙእሚን ላይ መቅጠፍ ግን የከፋ ነው፡፡” [መጀመዑል ፈታዋ፡ 28/ 223] ውሸቱ ሰላም የሚያደፈርስ፣ ሰዎችን የሚያቆራርጥ፣ ደዕዋን የሚያሰናክል ከሆነ ደግሞ በሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂነት ስለሚኖር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 29 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

📌 هل أجاز شيخ الإسلام ابن تيمية الاحتفال بالمولد النبوي ؟ ينسب بعض دعاة البدع إلى الإمام ابن تيمية أنه يرى جواز الاحتفال بالمولد معتمدين في ذلك على عبارة ذكرها في الاقتضاء: وكذلك ما يحدثه بعض الناس إما مضاهاة للنصارى في ميلاد عيسى العلي وإما محبة للنبي ﷺ وتعظيما له، والله قد يثيبهم على هذه المحبة والاجتهاد، لا على البدع من اتخاذ مولد النبي ﷺ عيدا، مع اختلاف الناس في مولده؛ فإنَّ هذا لم يفعله السلف مع قيام المقتضي له وعدم المانع منه، ولو كان هذا خيرا محضًا أو راجحا لكان السلف أحق به منا، فإنهم كانوا أشد محبة لرسول الله وتعظيما له منا، وهم على الخير أحرص، وإنما كمال محبته وتعظيمه في متابعته وطاعته واتباع أمره وإحياء سنته باطنا وظاهرا ونشر ما بعث به والجهاد على ذلك بالقلب واليد واللسان؛ فإنَّ هذه هي طريقة السابقين الأولين من المهاجرين والأنصار والذين اتبعوهم بإحسان. وأكثر هؤلاء الذين تجدونهم حرصاء على أمثال هذه البدع - مع مالهم فيها من حسن القصد والاجتهاد الذي يُرجى لهم بهما المثوبة - تجدهم فاترين في أمر الرسول عما أمروا بالنشاط فيه، وإنما هم بمنزلة من يحلي المصحف ولا يقرأ فيه، أو يقرأ فيه ولا يتبعه، وبمنزلة من يُزخرف المسجد ولا يصلي فيه، أو يصلي فيه قليلا، وبمنزلة من يتخذ المسابح والسجادات المزخرفة ». هذا الكلام صريح في أنَّ المولد بدعة من البدع عنده؛ إذ قال: « لا على البدع من اتخاذ مولد النبي ﷺ عيدا »، وأكد ذلك بقوله في موضع آخر : « وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال أنها ليلة المولد، أو بعض ليالي رجب، أو ثامن عشر ذي الحجة، أو أول جمعة من رجب، أو ثامن شوال الذي يسميه الجهال عيد الأبرار = فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف ولم يفعلوها، والله سبحانه وتعالى أعلم » اهـ. فإذا اتضح وبان أنه صرح ببدعية الاحتفال بهذا اليوم فما معنى قوله: إنه يثاب ويؤجر ؟. يقال: إن كلامه صريح في أنَّ الإثابة على نية محبة رسول الله ﷺ وحُسن القصد لا على العمل، وذلك كقوله : ( إذا اجتهد الحاكم فأصابَ فَلَهُ أجران، وإذا اجتهد فأخطأ فله أجر واحد ، أخرجه الشيخان عن عمرو بن العاص وأبي هريرة. فهذا الحاكم أُثيب أجرًا واحدًا لحسن نيته كما أفاده الشافعي وغيره وإن كان العمل خطأ، ومثله المقلد فإنه إذا قلد من يثق به وعمل المولد ظنا منه أن فعله مشروع فهو لا يثاب على العمل لأنه أخطأ، وإنما على حسن النية والقصد. كما قال في موضع آخر : ( وإنَّما الذي أراده ربيعة - والله أعلم - أنَّ من كانت له نية صالحة أثيب على نيته وإن كان الفعل الذي فَعَلَهُ ليس بمشروع إذا لم يتعمد مخالفة الشرع، فهذا الدعاء وإن لم يكن مشروعًا لكن لصاحبه نية صالحة قد يثاب على نيته. فيستفاد من ذلك أنهم مجمعون على أنَّ الدعاء عند القبر غير مستحب، ولا خصيصة في تلك البقعة، وإنما الخير قد يحصل من جهة نية الداعي » اه. وعلى كل فليس لأحد أن ينسب إلى ابن تيمية القول بجواز الاحتفال بالمولد وأنه لا يبدعه، ثم لو قدر أن ابن تيمية ينفي بدعيته فإنه رحمه الله ليس حجَّةً ولا دليلا معصوما، وعليه فأقواله يُحتج لها لا بها. ✍️د. عبدالعزيز بن ريس الريس 📚المقدمات العشر في نقض أصول صوفية العصر ص ١٠٢

قال ناصر السنة الإمام أبو إسماعيل الهروي رحمه الله : "عرضت على السيف خمس مرات، لا يُقال لي: ارجع عن مذهبك، لكن اسكت عمّن خالفك، فأقول: لا أسكت" [سير أعلام النبلاء ٥٠٩/١٨]. አል ኢማም ናሲሩ ሱና አቡ ኢስማዒል አል-ሀረዊ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦ 👉"አምስት ጊዜ ለግድያ ቀርቤያለሁ። በዚህ ጊዜ ከአቋምህ (ከመዝሀብህ) ተመለስ አልተባልኩም፤ ነገር ግን አንተን ከሚቃረኑ ሰዎች ላይ ዝም በል እባል ነበር። እኔም <<ዝም አልልም!>> እል ነበር።" ምንጭ፦ ሲየሩ አዕላሚ ኑበላዕ (18/ 509]) ወንድሜ! ዝም ካልክ ሁሉም ወዳጅህ ነው። ከተናገርክ ግን ከመጠላትም አልፈህ ለእስርም ከዚያም አልፎ #ለግድያም ትጋለጣለህ።

የለተምዮች የመንሐጅ አረዳድ፦ ለተምይ፦ ለምን የእከሌን ሸይኽ ሂስ (ጀርህ) አንተ ዘንድ (ሰለፊ) በሆነው በእከሌ ሰው ላይ አትቀበልም?? ፍትሀዊ ሰለፍይ፦ አላሳመነኝም! ለተምይ፦ አንተ አላሳመነኝም በሚል ሰበብ እውነትን (ሃቅን) እየገፋህ ነው! ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ እሽ! ታዲያ አንተስ ለምን የሸይኽ ረቢዕን ሂስ (ጀርህ) በሸይኽ ሙሐመድ ብን ሃዲ ላይ አልተቀበልክም?? ለተምይ፦ ሸይኽ ረቢዕ ምንም መረጃ የላቸውም። ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ አንተምኮ ምንም መረጃ የለውም በሚል ሰበብ እውነትን (ሀቅን) እየገፋህ ነው። ለተምይ፦ አላሳመነኝም የሚለው ቃል ዑለማዎች ያወገዙት ቃል ነው። ፍትሐዊ ሰለፍይ፦ አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ በቁርዓኑ እንዲህ ብሏል፦ የሁድ ህዝቦችም የሁድን አሉት፦ የሁድ ሆይ! ግልጽ ማስረጃ አላመጣህልንም፤ እኛም አንተ ስላልክ ብቻ አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም። ተመልከት! እነሆ የዓድ ህዝቦች ለነብዩ የሁድ ግልጽ ማስረጃ አላመጣህልንም (አላሳመንከንም) እያሉት ነው። አይ ለተሞዎች! አጅብ ነው! አንዳንዶች ተቃዋሚህን የምትሞግትባቸው ቃላት በሸሪዓ ቃል በቃል የተቀመጡ (ተውቂፍይ) እንደሆኑ ያስባሉ። ወይም ደግሞ እነሱ እንደሚሉት ግዴታ እከሌ መረጃ የለውም ብለህ እንድትናገር ይፈልጋሉ። ይህንንም የሚያስቡት አንድ ሰው አላሳመነኝም ካለ፤ ያ አለማሳመን ሁልጊዜም በስሜት መነዳት እና በእልህ ላይ ብቻ የተገነባ ነው ከሚል የተሳሳተ እሳቤ በመነሳት ነው። ስለዚህ፦ በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ ጉዳይ ሞግቷቸው። መረጃ የለውም ማለታቸውን ካመኑበት የራሳቸውን መከራከሪያ አፈረሱ ማለት ነው።ከካዱ ደግሞ መልስ አጥተው #ተሸነፉ ማለት ነው። ቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444

Repost from N/a
🌀 ለቻነል ባለቤቶች በሙሉ👇 👉ኑ በነፃ 💯 ቻነል እናሳድጋለን ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥 ለ ተወሰኑ ቻነሎች ብቻ ቦታ አለን 🏃‍♂‍➡️          🧩Folder 1👇 🎯Above 300+ subscribers✅        🧩Folder 2👇 🎯 Above 500+ subscribers✅ 🧩Folder 3👇 🎯Above  1k+ subscribers✅ 🌀 ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ  ... ........  👇👇........... ...... @selluhi ለሽያጭ የቀረቡ ኢስላማዊ ቻናሎችም አሉ

«መጅኑኑ ለይላ » --------------------------- «ሲጀመር ስማቸው #ለይላ የሚባሉ ሴቶች ፍቅራቸው ከባድ ነው እናቴ #ለይላ ነችና ስሜታችን ቢለያይም በተወሰነ መልኩ #ቀይስን እኔ እረዳዋለሁ» ....ኑር...✍️ .....«🌷መጅኑኑ ለይላ🌷» ከፍቅር ቃሬዛ ወድቆ ለደከመ፡ ተስፋው ህልም ሆኖ ለተከረከመ፡ ፈውሱን ላላገኘ ድኖ ላልታከመ፡ ለይላን ላፈቀረ ለይላን ለታመመ፡ በሷ የተጎዳ በሷ የዘመመ፡ ህይወቱን ኗሙሉ ሌላ ያልጠቆመ፡ ለይላ ላይ ጀምሮ ለይላ ላይ ለቆመ፡ በህይወት እስካለ አያስብም ሌላ፡ የልቡ ብርሀን አንድ እሷ ነች ለይላ፡፡ ፍቅር በሚሉት ጉድ የተጠለፈ ሰው፡ እብድ ነው የሚሆን ውስጡን እየባሰው፡ አፍቃሪውን ማጣት ሰርክ እያስለቀሰው፡ እውነተኛ ሆኖ ማነው የሞከረው፡ ፍቅርን በተጨባጭ መንስ ነው የኖረው፡ ጠባሳ አስከትሎ ከሚሰረስረዉ፡ ከመዉደድ በሽታ ማነዉ ሚሽረዉ!! አያልቅም ቢነገር አይቻልም ይቅር፡ ረቂቅ ነው ጫፉ የዛ መጅኑን ፍቅር፡ ♦️.....መጅኑኑ ለይላ....!! የምን ደማከሴ የምን እጣን ቅጠል፡ የምን ማፅናኛ ነው የምን ቃል መቀጠል የምን ሌላ ምኞት የምን ውል ማንጠልጠል፡ አቢድ ያሰመረው ሀኪም የቀመመው፡ በለይላ ተለክፎ ለይላን ለታመመው፡ ሲያስባት ለኖረ ቀንም ሆነ ሌሊት፡ ለቀይስ አይነት መጅኑን ምኑ ነው መዳኒት!! መዳኒቷ እርሷ ነች መዳኒትም የለው! በሷ እንደታመመ በሷ ነው ሚድነው፡፡ .....አይ ፍቅር ..የስራህን ይስጥህ...‼️ የውደታን ሸማ የናፍቆትን ጠረን፡ የማፍቀርን ዋጋ በደማቁ አስምረን፡ የቀይስን ሁኔታ እንየው መርምረን፡ የአፍቃሪነት ሰንደቅ የታሪክ ውብ አርማ፡ የሙሀባ ወጀብ አስደናቂ ፊርማ፡ ፍቅሩን ሳያገኛት በዕብደት ቢለይም፡ ቀይስ ግን ፍቅሩ እንጂ እብደቱ አይታይም፡ ጠሸሸ አይባልም በፍቅር ያበደ፡ ቀይስ ነው አርዓያው ለይላን የወደደ፡ ናፍቆት በደም ስሩ ስር እየሰደደ፡ እንባው በፊቱ ላይ ቦይ እየቀደደ፡ በየጎዳናው ላይ ለይላን ያስታውሳል፡ አፍቃሪ ውብ ፍቅሩን መቼ እንደት ይረሳል፡ ዛፍና ቅጠሉ እሷን ይመስለዋል፡ ጣራ ግድግዳዋን ሔዶ ይስመዋል፡ ይህንን እያዩ ይሉታል ያመዋል፡ እሱ ከፍቅር ውጭ ሌላ ይታየዋል!?   ♦️መጅኑን....ለይላ....‼️ በንፁህ ልቦና ፍቅርን የወደደው፡ ከወዳጁ ርቆ መኖር የከበደው፡ ቀይስ ይባላል ስሙ በለይላ ያበደው፡ ልቡና ምላሱ አያስብም ሌላ፡ አብዶላታልና መኖር እስኪጠላ፡ ይሔ ነው በአጭሩ ያ መጅኑኑ ለይላ፡ ........ሲያሳዝን.....⁉️ ⛔️አፍቃሪ=ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ ♦️ማራኪ=ለይላ ቢንት መህዲ«የቀይስ የአጎት ልጅ እንደሆነች ይነገራል።» ስለ መጅኑን ለይላ የማያ'ቅ አለ ብዬ አላስብም።ግና ለፅሁፉ ድባብ መጅኑን ለይላን በመስመሮች ገድበን በወፍ በረር እንቃኘው እስኪ......ተከተሉኝ። አይመችም ኑሮው አይጥምም አየሩ፡ የሚወዱት ሰው ሄደው ካልዘየሩ፡ ተወደጅ በአፀፈው ካልመጣ ለፍቅሩ፡ ምኑ ላይ ነው ደስታው በዱንያ መኖሩ ! ....መጅኑን ለይላ የስነ-ግጥም ሰውና ከልቡ አፍቃሪ ነበር።  ትክክለኛ ስሙ ቀይስ ኢብኑ ሙለወህ ሲሆን "መጅኑን ለይላ"«የለይላ እብድ»ያሉት ለፍቅር ብለው ልባቸውን ከሰጡ ልብ ገባሪዎች አንዱ ስለነበር እና በለይላ ፍቅር አብዝቶ ስለሚመሰጥ ነው። .....ለይላ የሀብታም ልጅ፤መልኳም ልዕልትን የምታስንቅ ውብ እንስት ነበረች። ቀይስ ግን በተቃራኒው ትንሽዬ ጎጆ ቀልሶ የሚኖር ድሃ ነበር። ....ድሀ አፍቃሪ እንጂ በብዛት ፍቅሩን አያገኝም ግን እውነተኛ አፍቃሪ በብዛት ድሀ ነው ልበል....⁉️ ለይላና መጅኑኗ በየጫካው በየ ጋራ ሸንተረሩ ተሯሩጠው፣አፈር አቡክተው፣ጭቃ ጠፍጥፈው፣ውሃ ተራጭተው ያደጉ የፍቅር ተምሳሌቶች ናቸው። ......የሁለቱን ፍቅር ሀገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው የሚቀናበት ጉዳይ ሆነ።  የለይላ ቤተሰቦች ሀብታም ለሆነ ሰው እሷን መዳር ይፈልጉ ነበርና ከሚስኪኑ ቀይስ ይልቅ ለአንድ ባለፀጋ ይድሯታል። የእነዚህ ጣምራውያን ግንኙነትም አከተመ(ፍቅራቸው ባይቋጭም)!.... ከዕለታት አንድ ቀን የለይላ ውሻ አውላላ ሜዳ ላይ እያለከለከ ሲሄድ ቀይስ ይመለተከዋል። መጅኑንም ለይላ የት እንደደረሰች ለማወቅ ተከተለው።በመሀል ሀርመው ኢማም ተከትለው የሚሰግዱ ሰዎችን ሳያያቸው አቋርጦ ያልፋል። .....ሲመለስ ሰጋጆቹ ይይዙትና "አንተ!ያምሀል እንዴ⁉️ሰላታችንን አቋረጥክ እኮ‼️ብለው በቁጣ ስሜት ተናገሩት። .....በዚህ ጊዜ #አፍቃሪው #ቀይስ ዘመን ተሻጋሪ መልስ መለሰላቸው እንዲህም አለ:- ....እኔ የለይላ ፍቅር ባተሌ ነኝ።"እኔ ለይላን እንደምወዳት አላህን ብትወዱ ኖሮ፤እናንተን እንዳላየኋችሁ እናንተም እኔን አታዩኝም ነበር...በማለት ዘመን ተሻጋሪ ንግግሩን ታሪክ ያወሳለታል።    የዚህ ጀግና አፍቃሪ በፍቅር የተጎዳ ሰው ታሪኩ ብዙ ነውና እንዳስፈላጊነቱ ይቀጥላል...... የኔ ጥያቄ ግን....⁉️ ብዙ የፍቅር ታሪኮችን በወፍ በረር ለመቃኘት ሞክሪያለሁ...የሚገርመኝ አንድ ሚስጥር አለ ...በፍቅር ምክንያት #የሚያብደው፣ #የሚሞተው፣ #የሚታመመው፣ ህይወቱ የሚበላሸው ግን አብዛኛው #ወንድ ብቻ ነው ለምን...⁉️ .....ኑር...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ለጦሳ ማዶዎቹ አድርሱላቸው፦ 👉 ልብ በሉ የሸይኹን ንግግር መዐየን ከሆነ ተፍሲል(መለየት) ማድረግ ግድ እንደሆነ ይናገራሉ። 👉 አሁን ሰዎች ባጠቃላይ ሁጃ ደርሷቸዋል ካላችሁ ለምን ተውሂድ እና ሽርክን ታስተምራላችሁ??? 👈 ሸይኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንደእናንተ ሽርክ የሰራን ሰው በጅምላ ካፊር አይሉም። ይህ ድምፅ ምስክር ነው የሌላ ሸይኽን ንግግር እያስተማሩ ካላችሁ ኢጅማዕ የምትሉት ሙግት ብቻ ሊሆን ነው ።ነገርግን መጨረሻ ላይ የራሳቸውን አቋም ይናገራሉ لابد من التفصيل እያሉ ይናገራሉ ሁጃ የቆመበትን ሁጃ ካልቆመበት መለየት እንዳለብን ጠንከር አድርገው ይናገራሉ። እውነቱ ይህ ነው አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን በዛው ፀንተን የምንሞት ያድርገን።