قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Ir al canal en Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Mostrar másEl país no está especificadoLa categoría no está especificada
913
Suscriptores
-324 horas
-177 días
+5330 días
Archivo de publicaciones
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
እጅህ ላይ ምን አለ?
በጣም የሚገርመኝ አሏህ ሙሳን የጠየቀው ጥያቄ ነው። “ሙሳ ሆይ! ይህች በቀኝ እጅህ ያለችው ምንድናት?” ከሌለህ ነገር መነሳት አትችልም። ከህልም ዓለምህ ወደ ስራው ዓለምህ የሚያሸጋግርህ ነገር አሁን ያለህ ነገር ነው። ሙሳ እጅ ላይ የነበረው ብትር ነበር። የሚደገፍበት፣ ለፍየሎቹ ቅጠል የሚያረግፍበትና ሌሎች ጉዳዮችን የሚፈፅምበት። አንዳንድ የተፍሲር ሊቃውንት ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ? “አንዳንዴ አላህ ህይወትህ ውስጥ ተዓምር የሚሰራው እጅህ ላይ ባለው ነገር ነው። ለሙሳ በብትሩ ተዓምር እንዳሳየው ሁሉ።”
ባለህ ነገር ተንቀሳቀስ፣ ወደፊት ተራመድ !!
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
“ከማለፊያህ ለማረፊያህ”
ዛሬ መስከረም 17/2019 በአዲስ አበባ፣ ኢማሙ አሕመድ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from {أقوال أهل العلم}
ዛሬ እስቲ ስለ ብዕር ሰይፉ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጥቂት እንበል። ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር በብዙዎቻችን ዘንድ ልዩ ቦታ ያለውና በምክንያት የምንወደው የሐቅ አንደበት ነው። በተለይ እኔን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች የኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ስውር ሴራና ረቂቅ የጥፋት መንገዶች በሚገባ እንድንረዳ በየጽሑፎቹ የሚያቀርባቸው መረጃዎችና ትንታኔዎች ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገውልናል። በስሜትና በጭፍን ተከታይነት ተጋርዶ የነበረውን እውነታ በደሊልና በማስረጃ ገልጦ በማሳየት ለብዙዎች ከብዥታ መውጫ ሰበብ የሆነ ብርቱ ኡስታዝ ነው። ስለሆነም የጥመት አንጃዎችን ሴራ በማጋለጥና የሰለፎችን መንገድ በመጠቆም ረገድ በብዕሩ የከፈለውን ተጋድሎ ማውሳቱና ለሌሎችም ማሳወቁ ተገቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
በኢትዮጵያ የሰለፍያ የዳዕዋ መድረክ ላይ እንደ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ያለ የሐቅ ተሟጋችና በብዕሩ የጥመት አንጃዎችን ሴራ የሚያጋልጥ ሰው ማግኘት ለኡማው ትልቅ ፋይዳ አለው። እርሱ በመረጃ ጥልቀቱ የብዙዎችን የጥፋት ድንኳን የናደ የሰለፎችን መርህ መሠረት በማድረግ ለተውሒድና ለሱና ጥበቃ የቆመ ጽኑ ኡስታዝ ነው። በተለይ በዘመናችን የኢኽዋንና መሰል ሒዝቢያዎች ሴራ በረቀቀ መልኩ የሙስሊሙን ግንዛቤ ለመበከል በሚሞክሩበት ወቅት ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጭንብላቸውን በመግለጥና ስውር ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን ለአደባባይ በማብቃት ረገድ ያከናወነው ተግባር ድንቅ ኡስታዝ መሆኑን ያስመሰከረበት ነው። ታዲያ ይህ ኡስታዝ የብዙዎችን የሐሰት ገጽታ የገፈፈና ሐቅን በደሊል በማስደገፍ ለወጣቱ ትውልድ ግልጽ የሆነ የሰለፎችን መንገድ ያመላከተ ብርቱ መካሪ ነው።
የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብዕር ለሰለፊያ ዳዕዋ መከታ ሲሆን ለጥመት አንጃዎች ደግሞ አፋቸውን የለጎመና ጥመታቸውን ለአደባባይ ያወጣ የጽሑፍ ሰይፍ ነው። እርሱ በተለያዩ የዲን ጉዳዮች ላይ ካበረከታቸው ከአምስት በላይ የታተሙ መጽሐፍት በተጨማሪ የኢኽዋን አል-ሙስሊሚንን እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች የተደበቀ የፖለቲካ ሴራ ያጋለጠባቸው በርካታ አርቲክሎች (ጽሑፎች) በአማርኛ የዳዕዋ ጽሑፎች ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያላቸው ናቸው..... ብዙዎች ስም ማጥፋትንና ማግለልን በመፍራት ሐቅን ለመናገር በሚቆጠቡበት እንዲሁም በስሜት ተገፋፍተው የዲኑን መመሪያ በሚያለዝቡበት በዚህ ፈታኝ ዘመን እርሱ ግን ዛቻና ስድብ የማይበግረው የሐቅ ተሟጋች ኡስታዝ መሆኑን በተግባር አሳይቷል። የሚሰነዘሩበት ስድቦችና የሚቀነባበሩበት የሐሰት ዘመቻዎች ለሐቅ ያለውን ጽናት ይበልጥ ከማጠናከር ውጪ ቅንጣት ታህል ወደ ኋላ አላስሸሹትም።
አንዳንዴ ቆም ብለን ስናስተውል በዚህ በብዥታና በፈተና በተሞላ ዘመን እንደ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ያለ የጽሑፍ ሰይፍ የጥመት አንጃዎችን አፍ የሚለጉምና ጥመታቸውን በዝርዝር የሚያጋልጥ ብርቱ ሰው ማግኘት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እንረዳለን። እርሱ በተለይ በፖለቲካ መርዝና በሐሰተኛ አንድነት ስብከት ለሚጠለፉ የዋህ ሙስሊሞች በመረጃ የታጀበ ማብራሪያ በመስጠት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ ኡስታዝ ነው። የእርሱ ጽሑፎችና ትምህርቶች ለሐቅ ፈላጊዎች መረጋጋትን ለጥመት መሪዎች ደግሞ ውርደትን ያከናነቡ ናቸው። ከዚህ ኡስታዝ ዕውቀትና የጽናት አርአያነት በሚገባ መጠቀም ሥራዎቹን በጥልቀት ማንበብና የጥፋት ኃይሎችን ሴራ ማጋለጥ ከእያንዳንዱ የሱና ወዳጅ የሚጠበቅ ተግባር ነው።
ባጠቃላይ የኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር የብዕር ተጋድሎ ለዛሬው ትውልድ ትልቅ ትምህርት ያዘለ ነው። እርሱ ለሐቅ መቆም በምላስ ብቻ ሳይሆን በጽናትና በማስረጃ ጭምር መሆኑን በተግባር አሳይቶናል። የጥመት አንጃዎችን ሴራ በማጋለጥ ረገድ የከፈለው መስዋዕትነትና ለሚሰነዘሩበት ስድቦች የማይበገረው ጽናቱ ... እኛም በያዝነው የሰለፍያ መንገድ ላይ በዕውቀትና በቁርጠኝነት እንድንጓዝ ብርታት ይሆነናል። ስለሆነም ከዚህ ኡስታዝ ጽሑፎችና አርቲ ክሎች የምናገኘውን ዕውቀት ለራሳችን ከመጠቀም ባለፈ ለሌሎችም በማዳረስ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ኡስታዛችንን ከገባበት የጤና እክል በቅርቡ አውጥቶ ሙሉ ጤንነቱን እንዲመልስለት ዕድሜውን በሐቅ ላይ እንዲያረዝምለትና ለሰለፊያ ዳዕዋም ኩራት አድርጎ እንዲያቆየው የሁልጊዜ ዱእዋችን ነው። የጀመረው የሐቅ ጉዞ ፍሬ አፍርቶ የብዙዎችን ልቦና ከጥመት ጨለማ ወደ ሱና ብርሃን እንዲመልስ የአላህ እገዛ አይለየው። አላህ በዕድሜው በዕውቀቱና በቤተሰቡ ላይ በረካውን ያውርድበት።
{Abu salah}
T.me//Abu_suheyb_ibnu_jemal
T.me//Abu_suheyb_ibnu_jemal
ዐብዱ‘ላህ ኢብኑ ሙባረክ (ረሒመሁላህ) :–
« መልካም ሰዎችን እወዳለሁ ከእነርሱ አንዱ አይደለሁም። እኩይ ሰዎችን እጠላለሁ ከእነርሱ የከፋው ብሆንም።»
[ሲየር አዕላም አንኑበላእ መድብል #8]
ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺑﻦ ﺍﻟﻤﺒﺎﺭﻙ ، ﻳﻘﻮﻝ :
" ﺃﺣﺐ ﺍﻟﺼﺎﻟﺤﻴﻦ ﻭﻟﺴﺖ ﻣﻨﻬﻢ ﻭﺃﺑﻐﺾ ﺍﻟﻄﺎﻟﺤﻴﻦ ﻭﺃﻧﺎ ﺷﺮ ﻣﻨﻬﻢ "
[ ﺳﻴﺮ ﺃﻋﻼﻡ ﺍﻟﻨﺒﻼﺀ #8]
@ከሰለፎች አንደበት
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
“ከማለፊያህ ለማረፊያህ”
ዛሬ መስከረም 17/2018 በአዲስ አበባ፣ ኢማሙ አሕመድ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ትዳር እና ኢስላም 🌷🌹🥀
*
‟ብቻ ደጁ አልጥፋ!”
ወንጀሌ በዝቶብኝ ቲኒሺ ሲገስፀኝ፣
ነፍሴን መረን ትቼ ተመለሺ ሲለኝ፣
ረሂሙ ጌታ ከፈተናዎቹ በአንዷ ፈተነኝ፣
ሁሉም ጨለመብኝ መነሳት አቃተኝ፣
የጨለማው ግዝፈት ከኔላይ ቢደፋ፣
ፅልመቱን ለመግፈፍ ብደክም ብለፋ፣
ኡፍፍፍ! ብወጣ ወደላይ ወደታች ብደፋ፣
በአቅሜ የሚሆን መስሎኝ የሚጠፋ፣
ሞኝነት!! ለካ ደካማነኝ በቲኒሽ ምጠፋ፣
ፈትኖ አልተወኝ አሳየኝ በይፋ፣
ጌታዬ ሲመራኝ በሱ ሰጠኝ ተስፋ፣
እጄን ለመዘርጋት አይሻም ወረፋ፣
ሁልጊዜም ልጠይቅ ብቻ ደጁ አልጥፋ፣
ውድቀቴን ተመልካች አዛኙ ጌታዬ እሱ አያንቀላፋ።
በሀፅያቴ ብዛት ኮርኮም ቢያደርገኝ፣
አልልም ፈፅሞ አሏህ ጨከነብኝ፣
ፈልጎልኝ እንጂ ህይወቴ እንዲያምርልኝ፣
ቺክ ባይን ወዳድ እኔኮ ጌታ አለኝ።
እለምነዋለሁ ነጃ በለኝ ብዬ፣
ያላንተ መጠጊያ የለኝ አሏህዬ፣
እኔን ለኔ አተወኝ ጅል ነው መውደቂያዬ፣
ብሌኔ ሁንልኝ መልካሙን ማያዬ፣
ለልቤም ብርሀን ሁነኝ መቃኛዬ፣
መጥፎ እንዳይሆንብኝ የኔ መውደቂያዬ፣
እጠይቀዋለሁ ለምን ዝም እላለሁ ከቶ ለማን ብዬ፣
አንተ ይቅር ባይ ነህ ፈርጀኝ ጌታዬ።
✍️ቢንት_ፉላን💕
Repost from Fewaz tv ( ፈዋዝ ቲቪ )
ፍቅር እስከ ጀነት ✅
ፍቅር እስከ ጀነት ኢስላማዊ ቤተሰብ አመሰራረት፣ ሸሪዓዊ የልጆች አስተዳደግ፣ በረሱል (ﷺ) እና ሰሀቦች መካካከል ያለውን ምርጥ የፍቅር ታሪክ በሰፊ የሚዳስስ ቻናል ነው።
እንዲሁም የትዳር አመሰራረትና ትዳር ውስጥ ስለሚኖረን ግንኙነት ምርጥ ጥቆማዎችን እና ሀሳቦችን የሚያነሳ ቻናል ነው። ተቀላቅላችሁ ተጠቀሙበት !
ለሌሎችም አጋሩት 🍏✅
👇 👇 👇
t.me/FKR_ESKE_JENET
t.me/FKR_ESKE_JENET
t.me/FKR_ESKE_JENET
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
♦️♦️♦️ሰውን በተስፋ አታንከራትቱ
📍አንድ ሰው ወደ እናንተ ሲመጣ ገንዘብ ብቻ አይፈልግም፤ ተስፋ ይፈልጋል፣ መፍትሔ ይፈልጋል፣ ከልብ የሚያዳምጠውን ሰው ይፈልጋል።
📍የልቡን ብሶት፣ የቤተሰቡን ጭንቀት፣ የሥራ ማጣቱን እና የኑሮ መከራውን ከፍቶ ሲነግራችሁ በእናንተ ላይ እምነት አድርጎ ነው።
ከዚያ በኋላ ግን፦
“እንረዳሃለን፣ እናግዝሃለን፣ ሥራ እናስገባሃለን፣ ጉዳይህ የእኛ ጉዳይ ነው…”ብላችሁ ተስፋ ትሰጡታላችሁ። ነገር ግን ዛሬ ና፣ ነገ ና፣ ሳምንት ጠብቅ፣ ይሄን አድርግ፣ ያንን ሰው አግኝ እያላችሁ ለምን ታንከራትቱታላችሁ? የሰውን ጊዜ ማጥፋት ብቻ አይደለም፤ የልቡን ተስፋ ማድከም ነው። የማይሆን ከሆነ… “አይሆንም” በሉ። አዎ፣ እውነት አንዳንድ ጊዜ ትከብዳለች፤ ግን ከሐሰተኛ ተስፋ ትሻላለች። ሰው ግልጽ መልስን ይቀበላል፤ ነገር ግን የማያልቅ ጥበቃ ይሰብረዋል። 📍እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ ዛሬ የደረሳችሁበት ከመድረሳችሁ በፊት ምን ላይ ነበራችሁ? ማን እጁን ዘርግቶ አነሳችሁ? ማን አንድ በር ከፍቶ ዕድል ሆነላችሁ? እናንተም አንድ ቀን የሰው ደጅ የቆማችሁ ሰዎች ነበራችሁ። ስለዚህ ዛሬ ያንን ታሪክ አትርሱ። ለሰው ሰበብ ሁኑ ማድረግ ከቻላችሁ በተቻላችሁ መጠን አድርጉ። ማድረግ ካልቻላችሁ ግን በክብር ንገሩት። “አልችልም” የሚል እውነተኛ ቃል፣ “እንረዳሃለን” ከሚል ባዶ ተስፋ ይሻላል። ሰውን በተስፋ አታሰቃዩ። ችግሩን አታብዙበት። ተስፋውን አትጫወቱበት።
ዛሬ ለሌላው የምትሆኑት ሰበብ፣ ነገ ለእናንተ የሚመጣው ሰበብ ሊሆን ይችላል።ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba
Repost from قناة الشيخ توفيق البعداني ⟦ الـرَسْـمِـيـة ⟧
الصلاة 11فتوى رقم (3958): قضاء تارك الصلاة عمدًا فتوى رقم (3973): صلاة أربع قبل العصر فتوى رقم (3988): دخول المقابر بالنعال لعذر فتوى رقم (3989): زيارة المرأة للقبور فتوى رقم (4000): تأخير صلاة الظهر إلى وسط وقتها فتوى رقم (4012): الجمع بين الصلاتين في بلد الإقامة لمن نوى السفر فتوى رقم (4017): الصلاة على الجنازة في الأوقات المنهي عن الصلاة فتوى رقم (4019): رفع المسبوق يديه عند القيام من الجلوس فتوى رقم (4024): الصلاة في الحمام فتوى رقم (4026): تهاون إمام المسجد في صلاة الجماعة
ያ ኢላሂ እኔ ካንተ ዉጭ ማንም ረዳት የለኝም አንተዉ እርዳኝ ኸይሩን ነገር ሁሉ ወፍቀኝ ሸርን ነገር ሁሉ አርቅልኝ በእዝነትህ ያረብብ🤲
http://t.me/UmuAbais
አምላኬ ሆይ፤ ለትእዛዝህና ለመብትህ ተገቢውን ቦታ አልሰጠሁም፤ ከ አንተ ውጪ ሌላ አካል አለመንኩም።
አምላኬ ሆይ፤ ወደ በጎ ስራዎች ለመሮጥ አልቸኮልኩም፤ የታማኝነትን በር ለማንኳኳት አልተጋሁም።
አምላኬ ሆይ፤ ከሐሜት የራቅኩኝ ባልሆንም፤ ነብያቶችህንና የመረጥኳቸውን ባሮችህን ግን አልተሳደብኩም።
አምላኬ ሆይ፤ ከበርህ ከቶ አርቅም፤ ምክንያቱም ከአንተ ውጪ ሌላ ማውራት አልፈልግም።
አምላኬ ሆይ፤ ከበርህ ፈቀቅ አልልም፤ ምክንያቱም ከአንተ ውጪ በሌላ አካል አልደሰትም።
አምላኬ ሆይ፤ ስራዬ ልክ እንደ ውኃ ቅዠት ባዶ ነው፤ ልቤም አንተን ከማምለክ ባዶ ነው።
አምላኬ ሆይ፤ ሃጢያቴም ከአፈር ብዛት በላይ ብዙ ነው፤ አንተ ግን ይቅርታ ለማድረግና ላለመውቀስ ከሁሉ በላይ ባለቤት ነህ።
ስለዚህም በችሮታህና በልግስናህ ማረን፤ ይቅርም በለን፤ አንተ የልቅናና የማላቅ ባለቤት የሆንከው ሆይ!
Repost from قناة الشيخ د. إبراهيم المحيميد
حرم الله على النار وذريته كل من نصر
هذا الدين واو بكلمة أو دعوة بظهر الغبب
Repost from አቡ ዓብደሏህ(أبو عبد الله الولوي)🇸🇦
📢 አስቸኳይ የማስተላለፊያ ጥሪ!
ይህ የእውቀት ጥሪ ለሁላችንም ነው! 📚🌿
👉 መልዕክቱን በTelegram ሼር አድርጉ፤
👉 ያላዩትን ተማሪዎች እና የእውቀት ፈላጊዎችን በስልክ ደውላችሁ አሳውቁ። 📞
🤲 ምናልባት በእርስዎ ማስታወቂያ አንድ ሰው የእውቀት መንገድ ይጀምር ይሆናል።
⏰ ዛሬ ከመግሪብ በኋላ
🕌 መስጅደል አዝሀር — ጅብሪል ጎራ
ሼር ያድርጉ፣ ደውለው ያሳውቁ፣ አንድም ሰው እንዳይቀር! 🌿📚
بارك الله فيكم ونفع بكم 🤲
https://t.me/abuabdelah123
🌹 ፍቅር ሪዝቅ ነው… ያፈቀሩትን ማግኘት ደግሞ መድኃኒት ነው። 🥀
አንዳንድ ሰዎች ወደ ልባችን የሚመጡት በዕድል አይደለም፤ በአላህ የተጻፈ ሪዝቅ ሆነው ነው። ልብህ ያለምክንያት ለአንድ ሰው ሲያዘነብል፣ በእርሱ መገኘት ሰላም ሲሰማህ፣ ድምፁ የድካምህን ጫና ሲያሳርፍልህ… እነዚህ ሁሉ ልብ የሚገልጣቸው ስሜቶች ናቸው።
ፍቅር ማለት ሰውን ማየት ብቻ አይደለም፤ በልብ ውስጥ ለእርሱ ልዩ ቦታ መኖሩ ነው።
አንዳንዴ አንድ ሰው ከሺዎች መካከል ልዩ ይሆናል፤ ምክንያቱም ልብህ እርሱን ብቻ በሚያውቅ ቋንቋ ይገናኘዋል።
እና እንዴት ያለ በረከት ነው…
የምትወደው ሰው አንተንም ሲወድ፣ የምትፈልገው ሰው አንተንም ሲፈልግ፣ የምትናፍቀው ሰው አንተንም ሲናፍቅ!
ከሁሉም የሚያምረው ግን ፍቅሩ በሕላል መንገድ ሲጠናቀቅ ነው። ያኔ የብቸኝነት ምሽቶች ይረሳሉ፣ የመናፈቅ እንባዎች ይደርቃሉ፣ ረጅም ጊዜ የጠበቀው ልብም በሰላም ይሞላል።
ምክንያቱም ያፈቀሩትን ማግኘት መድኃኒት ነው፤ ከእርሱ ጋር በሕላል ሕይወት መጋራት ደግሞ የዚያ መድኃኒት ሙሉ ፈውስ ነው።
🌿ስለዚህ አንድን ሰው ከልብህ ከወደድከው፣ ሁሉንም ነገር በእጅህ ለማድረግ አትሞክር። ፍቅርህን አክብር፣ ልብህን ጠብቅ፣ አላህንም አመን።
ከተጻፈልህ ሰው አትሸሽም፤ ከአንተ ጋር እንዲኖር ካልተጻፈም በምንም ኃይል ወደ ህይወትህ አታስገባውምና።
አንዳንድ ፍቅሮች ወደ ሕይወታችን የሚመጡት ለመቆየት ነው፤ ሌሎች ደግሞ ለመማር። ነገር ግን አላህ የጻፈው ሰው ከሆነ… ርቀት፣ ጊዜ፣ መሰናክልና መጠበቅ ሁሉ በመጨረሻ መንገዱን ያገኛል።
ፍቅር ሪዝቅ ነው…
መናፈቅ ፈተና ነው…
መጠበቅ ሰብር ነው…
መገናኘት ግን ስጦታ ነው።
እና ከሁሉም በላይ፦
በሕላል መንገድ ያፈቀሩትን ሰው አግኝተው፣ “አላህ ሆይ፣ ይህን ሰው በሕይወቴ ውስጥ ስላስገባልኝ አመሰግንሃለሁ” ማለት… ከፍቅር በላይ የሆነ ኒዕማ ነው።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
ነቢዩ ﷺ አብዛህኛው ጊዜ ዝምታ የሚያበዙ፣ ያለ አስፈላጊነት የማያወሩና፣ በማይመለከታቸውም ነገር የማይናገሩ፣ ምንዳውን ከአሏህ በሚፈልጉበት ነገር ካልሆነ በስተቀር የማይናገሩ ነበሩ፤ አንድን ነገር ሲጠሉ ደግሞ በፊታቸው ላይ ይታወቅ ነበር።
📚ابن القيِّمt.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
||
የተስሒሑ ቲላዋ በሙሐመድ ሲራጅ
አል-ኬሚሴ|| √√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√
ከ1_30 ያሉትን በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ተከታተሉ┈──── ••⇣⇣┈──── ⇣⇣───⇣⇣─── ክፍል ❶ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/836 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➋ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/844 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❸ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/861 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➍ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/889 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❺ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/900 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❻ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/914 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❼ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/943 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❽ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/943 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➒ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/970 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❿ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/992 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓫ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1015 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓬ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1038 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓭ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1052 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓮ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1068 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓯ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1080 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓰ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1090 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓱ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1110 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓲ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1118 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓳ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1136 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓴ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1155 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❶ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1171 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➋ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1193 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❸ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1748 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➍ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1777 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❺ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1791 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❻ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1817 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❼ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2026 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❽ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2046 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➒ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2065 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❸⁰ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2830 የቴሌግራም ቻናል ↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️ 💙📎https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie 💙📎https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie
ደስታን_በዲናችን_ውስጥ_እንፈልግ_!!.m4a21.96 MB
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
🎙የዳዕዋ ፕሮግራም!
🔻በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ!
https://t.me/IbnuMunewor?livestream=7b970bcacee9ec3de3
