es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Ir al canal en Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
915
Suscriptores
Sin datos24 horas
-67 días
+5630 días
Archivo de publicaciones
Repost from Dr. Seid Musa
✏️ [ ያልተረዳኸውን ለማስረዳት አትሞክር ]  መንሐጅ አስ-ሰለፍን በቅጡ ሳትረዳ ለማስረዳት ስትጋጋጥ አንድ ሰው መቼ ሱንይ እንደሚባልና መቼ ሙብተዲዕ እንደሚባል በመርህ ሳትማር በሰዎች ላይ ፍርድ ለመስጠት ስትሯሯጥ :- እመነኝ ትናንትና "ሱፊይ (አሕባሽ) ነው ብለህ እንድትወስን ትገደዳለህ።" ብለህ በድፍረት የፈረድክበትን ሰው ባህልህንም ቢሆን መሰረት አድርገህ "ጫት እያኘከ ሱሪ እየጎተተ ድቢ እየደበደበ ፂሙን ጋጦ ሲሄድ ያየነውን ሰው የሱና መገለጫውን ስላጠፋ እነኚህ ነገራቶች ያሉበት ሰው ማን እንደሆነ ስለምናውቅ ወደተዘየነበት ግሩፕ ወሽቀነው ቢያንስ ጠርጥረነው እንሄዳለን። ብለህ ዋለህ በጀብድ ትከትባለህ። አሁንም እመነኝ:- "መንሐጅህን ከቁርኣነና ከሐዲስ በሰለፎች አረዳድ እስካልጨበጥክ ድረስ ምንም ብትንጠራራ ከመዋለልና ከመዘላበድ አትወገድም።" = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/AbulbukhariSeid

​⛓️ «የወንጀል እስራት እና የዕንባ መፍቻ!» ​بسم الله الرحمن الرحيم ​ውድ ወንድሜ… የተከበርሽ እህቴ! ቆም ብለህአሰብክ ታውቃለህ ? ቆም ብለሽ አስበሽስ ታውቂያለሽ ? ወንጀል እጅና እግርን የማይታይ ሰንሰለት አግዶ የሚያስር፣ መንፈስን የሚያጠበብ፣ የልብን ብርሃን አጥፍቶ በጨለማ ክፍል ውስጥ የሚቆልፍ ከባድ እስራት ነው። ​ስንቶቻችን ነን በየቀኑ የሚደጋገሙ ጥፋቶቻችን ታስረን፡ ▾ ሶላት ለመስገድ ስንነሳ እግራችን የሚከብደን? ▾ ቁርኣን ለማንበብ እጃችንን ስንዘረጋ የሚዝልብን? ▾ ከአላህ ጋር ለመቀራረብ ስንል ልባችን ድርቅ ብሎ የሚፈታተነን? ​ይህ ሁሉ የሌላ ነገር ውጤት አይደለም—የወንጀል እስራት ነው! ​🔥 ወዳጆቼ ሆይ! አላህ ይዘንልንና… ለአንድ አፍታ እንኳ በሕይወታችን የሰራናቸውን ወንጀሎችና ጥፋቶች በቁጭት እሳትነት አቃጣይ ስሜት አስበናቸው እናውቃለን? ​አላህ እያየን፣ የሰጠንን ጸጋ በእጁ እየተቀበልን፣ በእሱ ላይ ደፍረን ስናመፅ የነበረበትን ጊዜ ስናስበው ልባችን አይነድም? እስከ መቼ ነው በዚህ የወንጀልና የእስራት እንቅልፍ ውስጥ የምንቆየው?» እስከ መቼ ነው በገዛ እጅህ የወንጀል ሰንሰለት እየተበተበህ የሸይጧን እና የነፍስህ ባሪያ ሆነህ የምትኖረው? እስኪ ንቃ! እስከ መቼ ነው በዚህ ውርደት ውስጥ የምትቆየው? ​ስንት ሌሊት ነው አላህ እየተመለከተህ በምስጢር ወንጀል ስትጨማለቅ ያደርከው? ሰዎች እንዳያዩህ በሩን ዘግተህ፣ መጋረጃውን ጣል አድርገህ፣ ስልክህን ደብቀህ ተደበቅክ… ነገር ግን የሰማይና የምድር ጌታ እያየህ እንደነበር አረሳኸውም? የሰዎችን እይታ ፈራህ፤ የአላህን እይታ ግን አቀለልከው! ከዚህ በላይ ምን የሚያስቆጭና የሚያሳፍር ውርደት አለ? ​እስኪ አስበው… ያንተን ጥፋትና ነውር አላህ ለሰዎች ቢገልጥብህ ኖሮ ዛሬ ማን ያከብርህ ነበር? ማን አብሮህ ይቆም ነበር? እሱ ግን ስትበድለው እንኳ ነውርህን ደብቆልህ፣ የአየር እስትንፋሱን ሳይከለክልህ፣ ጤናህን ሳይነጥቅህ እስከ ዛሬ ታገሰህ! ​አንተ ግን በምታገኘው እያንዳንዱ ጸጋ እሱን ስታመፅበት አልፈራህምን? በዓይንህ አላህ የከለከለውን ስታይ፣ በጆሮህ የተጠላውን ስትሰማ፣ በእግርህ ወደ ወንጀል ስትራመድ… «የሞት መልአክ አሁን በዚች ቅጽበት ነፍሴን ቢነጥቃት አላህ ፊት በምን ፊት እቆማለሁ?💦 » ብለህ አልደነገጥክም? ቁጭቱና ፀፀቱ አያቃጥልህም?💦 ​"ነገ እመለሳለሁ፤ ነገ ተውበት አደርጋለሁ፤ ገና ወጣት ነኝ..." እያልክ እራስህን አታልለህ አትተኛ! "ነገ አለህ… አንተ ግን በነገ ውስጥ ላይኖርህ ትችላለህ!" የሞት መልአክ በርህን ለማንኳኳት ያንተን ዕድሜ ማጠናቀቅ እንጂ ያንተን "ነገ እመለሳለሁ" የውሸት ምኞት አይጠብቅም። ​ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ! አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እኮ እንዲህ ይላል፦ ​«በላቸው፡- እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ አላህ ኃጢአቶችን ሙሉ በሙሉ ይምራልና። እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና።» (ዙመር፡ 53) ​ዛሬ የዚያን የጠነከረ ልብህን ዕንባ መፍቻ ቀን አድርገው! የአላህ ፍርሃት ከልብህ መንጭቶ በጉንጭህ ላይ የምታፈሳት አንዲት የቆጨች ዕንባ… አላህ ዘንድ እጅግ የተወደደች ናት። ያች ዕንባ የእስራትህን ሰንሰለት ስብርብር አድርጋ የምትጥል፣ የነፍስህን የቆሸሸ ገጽታ አጥባ የምታጠራ ልዩ አሲብ ናት። ​ዛሬውኑ ወስንወስኒ💦! ▾ እስኪ ​ወደ ኋላ ተመልከት፦ ያበላሸኸውን ታሪክ በቅን ተውበት እጠበው። ያለፉትን የጨለማ ቀናትህን፣ ከአላህ መንገድ የራቅክባቸውን ዓመታት፣ የወደቅክባቸውን አሳፋሪ ወንጀሎች አስባቸው። ነገር ግን ተስፋ ልትቆርጥ ሳይሆን፣ በቁጭትና በዕንባ ልታጥባቸው ወደ ኋላ ተመልከት! አላህ ያለፈውን ጥፋትህን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ በበጎ ሥራዎች የመለወጥ ቃል ገብቶልሃል። ታሪክህ ምንም ያህል ቢበላሽ፣ በአላህ እዝነትና በእውነተኛ ተውበት የማይታደስበት ምንም ምክንያት የለም፤ ዛሬ አዲስ ገጽ ክፈት!» ▾ ​አሁኑኑ ቁም፦ "ነገ" የሚባለውን የሸይጧን ማታለያ ቀለበት በጥስ። "ነገ እመለሳለሁ፣ ነገ እቀየራለሁ፣ ነገ ተውበት አደርጋለሁ..." እያልክ እራስህን አታታል! ሸይጧን ስንቱን በ"ነገ" ማታለያ ተስፋ እያሰጠ ቀስ እያለ ከቀጥተኛው መንገድ አወጣው? ስንቱ ሰው "ነገ እቀየራለሁ" እያለ ሳይቀየር በመጣበት ቅጽበታዊ ሞት ተነጥቆ ወደ ቀብር ወረደ? ​"ነገ" ያንተ አይደለችም፤ ዛሬ ግን በእጅህ ላይ ናት! አሁኑኑ ተነሥ፣ የወንጀልን ሰንሰለት በጥስና ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አድስ። አሁኑኑ ካልቆምክ፣ ነገ በሚባለው ሀሰተኛ ተስፋ ውስጥ ተሸውደህ እስከወደቅክበት ልትቀር ትችላለህ!» ▾ ​እጆችህን ዘርጋ፦ በብቸኝነት አላህ ፊት ተንበርከክና እውነተኛ ዕንባህን አፍስስ፤ ሰዎች በሙሉ በተኙበት፣ በዚያ በጨለመው የሌሊት ክፍለ ጊዜ፣ ማንም የማያይህና የማይሰማህ ቦታ ላይ በብቸኝነት ተንበርከክ። የሠራኸውን ነውር ሁሉ ለአላህ እያመንንክ፣ በሠራኸው ጥፋት ልብህ በቁጭት እየነደደ፣ እጆችህን ወደ ሰማይ ዘርጋ። ​ከዓይንህ የምታፈሳት አንዲት የቆጨችና ከአላህ ፍርሃት የተነሳች ዕንባ… የጀሀነምን እሳት ለማጥፋት ብቁ ናት! ጌታህ እኮ ከሰው ይልቅ ለአንተ አዛኝ ነው፤ እጆችህን ባዶአቸውን ወደ እሱ ዘርግተህ ባዶህን ሊመልስህ ያፍራል። ዛሬ በብቸኝነት አላህ ፊት አልቅሰህ ልብህን አርሳት፣ የወንጀልን ሰንሰለት በዚያች እውነተኛ ዕንባህ በጥስ!» "ጌታዬ ሆይ! ተመለስኩብህ፣ ተቀበለኝ" በለው! ​“ጌታዬ ሆይ! በወንጀል የቆሸሸችውን ነፍሴን፣ በምስጢር ያጠፋሁትን ጥፋቴን፣ የታከትኩበትን እድሜዬን ይዤ በደጅህ ወድቄአለሁና አትመልሰኝ! እስከ ዛሬ በባከነ መንገድ ላይ የተጓዝኩበት ይበቃኛል፤ እባክህ ማረኝ፣ ተቀበለኝ!” በለው!» «ወንድሞቼና እህቶቼ ሆይ! ይህንን ማስታወሻ ወደ እናንተ ስልክ፣ እኔ ከእናንተ የተሻልኩ፣ ከወንጀል የጠራሁ ወይም ከማንም በላይ አላህን የምፈራ ሆኜ አይደለም። እኔ ራሴ የወንጀልና የጥፋት ባሪያ፣ የአላህ ምህረትና እዝነት ከአንደበቴ በላይ እጅግ የሚያስፈልገኝ ምስኪን ባሪያ ነኝ። ​ነገር ግን ነፍሴንና እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር “አላህ ሁላችንንም ይማረን፣ ይዘንልን” ከሚል የልብ ቁጭት የተነሳ የቀረበ የወንድማማችነት ጥሪ ነው። ​አላህ እኔንም እናንተንም ከወንጀል እስራት አውጥቶ፣ በእውነተኛ ተውበት ልቦቻችንን ያድስልን፤ መጨረሻችንንም ያሳምርልን! 🤲» ​✍️ የጌታው ምህረት ከጃይ አቡ ማሒ ሙሐመድ ብን ኢድሪስ ​🔗 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/Deewaselefyya1448. https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega

ስለ لا إله إلا الله ተጀመረ በኡስታዝ አቡ ሀሳን قناة سلفية تهدف نشر السنة على فهم السلف الصالح والرد على أهل البدع والأهواء ممن لم ينتهج منهج السلف الصالح https://t.me/nuruya76 https://t.me/nuruya76

ሙሓደራ 245 መንሐጅ ነክ ጥያቄ እና መልስ 👉  ከ ለተሚዮች ጋር ያለው ልዩነት ምንድን ነው 👉 ስለ ሙመዪዓ ማብራሪያ 👉  የ አሕባሾች ብዥታ እና መልሶች 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ https://t.me/UstazKedirAhmed

Repost from Abu Hayder Aliy
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ዛሬ ጁሙዓ ነዉ የጁሙዓ ሱናዎች ➖➖➖➖➖➖➖ ↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة🌿🌿🌿 ➊ 💎الغسل ➋💎 الطيب ➌ 💎السواك ➍💎 لبس الجميل ➎💎 قراءة سورة الكهف ➏💎 التبكير لصلاة الجمعة ➐💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➊ 🌺መታጠብ ➋ 🌺ሽቶ መቀባት ➌🌺 ሲዋክ መጠቀም ➍ 🌺ጥሩ ልብስ መልበስ ➎ 🌺ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን ➏ 🌺ለጁመዓ ሶላት መጣድ ➐ 🌺በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿〰 «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ   🌺በሰለዋት በዚክር ያውለን ያረብ ﷺ 🌹 .................🌹 ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹🔹🔹🌹  ﷺ ﷺ ﷺ 🌹🔹🔹🌹 በነብዩ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ !!                 https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። አሏህ ስሙን የሰየመለት ነብይ የሕያ ይባላል ።

እኛስ የት ነን!? ይህ ድንቅ ታሪክ...ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) «ረውደቱል ሙሒቢን» በተሰኘው ድንቅ ኪታባቸው ላይ የጠቀሱት ክስተት ነው!! 🎙ከቀጥታ ስርጭት ዳዕዋ ላይ የተወሰደ- አቡ ሱፍያን t.me/AbuSufiyan_Albenan

ምን አይነት ጀግና ነህ የእውነት ታታሪ የነብያት ወራሽ የተውሂድ ተጣሪ አላህ ይቀበልህ ወላህ ኡስታዝ ሳዳት ቃላት የለኝም አንተን የምገልፅበት። ሁላችንንም ዳዕዋችንን እንምሰል እንሁን! ✍️ አቡ ሹራ አህመድ

አጠር ያለች እውነተኛ ታሪክ ​ከሰላሳ ዓመታት የትዳርና የጋራ ሕይወት በኋላ፣ የሰውየው እይታ በባለቤቱ ላይ በድንገት ተለወጠ። እርስ በእርስ ያገናኟቸው ረጅም ዓመታት በልቡም ሆነ በትዝታው ውስጥ ምንም ዓይነት ምልክት እንዳልተወ ያክል። ​አንድ ቀን ልጆቹን በዙሪያው ሰብስቦ፣ እናታቸው እንዳረጀች፣ ፀጉሯም በሽበት እንደነጣ ፣ እናም ለውጫዊ ገጽታዋ ትኩረት መስጠት እንዳቆመች ነገራቸው። አክሎም፣ እሱ ራሱን እንደሚንከባከብ፣ እናም ከእሱና በሰዎች ፊት ካለው ገጽታ ጋር የምትመጥን ወጣት ሚስት እንደሚፈልግ ተናገረ፣ ​ከዚያም ወደ እናታቸው ሄደው ሌላ ሴት ለማግባት የወሰነውን ውሳኔ እንዲነግሯት ጠየቃቸው። ነገር ግን ሚስቱ እንደጠበቀው በዜናው አልደነገጠችም፤ ምክንያቱም የባህሪውንና የፍላጎቶቹን  ሁኔታ ከዓመታት በፊት ታውቀው ነበር፤ ቃላቱን ከመስማቷ በፊትም በዓይኖቹ ውስጥ ያለውን ለውጥ ታይ ነበር። ልጆቿን በእርጋታ ተቀብላ እንዲህ አለቻቸው፦ «ማግባት ለእሱ ሸሪዐዊ  መብቱ ነው፤ በሐላል መንገድ እንደሆነ ካመነበት እኔ አልቃወምም፤  ​አለች።  ይህ በእሷ ላይ ሲያገባ የመጀመሪያው ጊዜ አልነበረም፤ ከዚህ በፊት ከአንድ ጊዜ በላይ አግብቶ ነበር፣ ነገር ግን ከመጀመሪያው ትዳሩ ውጭ ምንም ዓይነት ትዳር አልዘለቀለትም ነበር፤ እሱን የምትታገሰው እሷ ብቻ ነበረች። በጣም የሚቆጣ ነበር፣ ለትናንሽ ምክንያቶች ይቆጣ ነበር፤ ሆኖም ግን እርሷ አኩርፋ  ከቤቷ ወጥታ አታውቅም ነበር፣ ይልቅስ ሁልጊዜ ትታገስ ነበር። ሰዎች በትዕግሥቷ በተደነቁ ቁጥር እንዲህ ትል ነበር፦ «ኢንሻአላህ አንድ ቀን ሁኔታው ይስተካከላል!» ▢ ​በእርግጥም ሰውየው ከልጆቹ ዕድሜ ጋር የምትቀራረብ ወጣት ሴት አገባ፤ እንደማይመለስ  አድርጎም ከቀድሞ ቤቱ ራቀ። ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ #በአዲሷ_ሚስቱ ጥያቄ መሠረት፣ ፊት ለፊት ሳይጋፈጣት ወይም ለመጨረሻ ጊዜ ዓይኖቿ ውስጥ ሳይመለከት፣ የመጀመሪያ ሚስቱ ዘንድ የፍቺ ወረቀት ላከ።. ▢​ ከአዲሷ ሚስቱ ጋርም የጫጉላ ሽርሽር ለማድረግ ወደ አንዲት ሩቅ አገር ተጓዘ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ውብና በደስታ የተሞሉ መስለው የታዩትን ቀናት አሳለፉ። ወጣትና ውብ ስለነበረች የታደሰ የወጣትነት ስሜትን ትሰጠው ነበር፤ እሱም ደስታ በገንዘብ የሚገዛ መስሎት በገንዘብና በስጦታዎች በእንክብካቤ ይሸፍናት ነበር። ▢ ​ነገር ግን ወደ ቤታቸው እንደተመለሱ፣ ቀናቱ ድምቀታቸውን በሒደት ማጣት ጀመሩ፤ ሕይወትም ወደ ከባድ ልማድ፣ የማያልቁ ጥያቄዎችና እየጨመሩ ወደሚሄዱ ወጪዎች ተለወጠች። አዲሷ ሚስቱ ምንም ዓይነት እውነተኛ ኃላፊነት አይሰማትም ነበር፤ ወጪዎችን ለመቀነስ በሞከረ ቁጥር ተቆጥታ፣ ቤቱን ትታ ወደ ቤተሰቦቿ ትሄድ ነበር። እሱም በየጊዜው እሷን የማጣት ፍርሃት ስላደደረበት እሷን ለማስደሰት እጁን ይሰጥ ነበር፤ እሷ ደግሞ ወጣት መሆኗንና እንደፈለገች የመኖር መብት እንዳላት ታረጋግጥለት ነበር። ▢ ​ሕይወታቸው በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ እረፍትና ያለ እርጋታ ቀጠለ፤ አንድ ቀን ያወቀው እረፍት አሁን እንደሌለ እስከሚሰማው ድረስ። የቀድሞ ቤቱ በሰላምና በመዋደድ የተሞላ እንደነበር አስታወሰ፤ በአዲሱ ቤቱ ግን ከመልክና ከጩኸት በስተቀር ምንም አላገኘም። ​በመካከላቸው ያለው አለመግባባት እያደገ ሄዶ ወደ ተዘጋ መንገድ እስኪደርስ ድረስ፤ ሁለተኛው ትዳርም በስነ-ልቦናና በገንዘብ ካደከመውና ባዶ እጁን ካስቀረው ረጅም ትግል በኋላ በፍቺ ተጠናቀቀ።💔 ​በዚያን ጊዜ ብቻ ነበር የጣላትን ሴት ዋጋ የተረዳው፤ በወጣትነት ቅዠት መንገድ ላይ ያባከነው የረጅም ዓመታትና የጋራ ሕይወት ጸጸት አሸነፈው። ​በልቡም እንዲህ አለ፦ «የሰማይ ቅጣት በኔ ላይ የወረደ ይመስላል!» ▢ ​ከዚያም በተሰበረ ድምፅ ወደ ልጆቹ ደውሎ እንዲህ አላቸው፦ «መፍትሔ መፈለግ አለባችሁ፣ የፈትዋ ሰዎችንም ጠይቁ። ተጸጽቻለሁ፣ ወደ እናታችሁና ወደ ቤቴ #መመለስ_እፈልጋለሁ፤ ውበት ብቻውን ደስታን እንደሚፈጥር ባሰብኩ ጊዜ ተሳስቼ ነበርና!»💔 ​ልጆቹም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ «አባታችን ሆይ! ነገሩ ተጠናቋል  ምንም ዓይነት መፍትሔም የለም!» ​ከዚያም የእናታቸውን መልእክት አስተላለፉለትና እንዲህ አሉት፦ «እሷ ደህና እንደሆነች፣ ከ አንተ በኋላ ዛሬ እጅግ ደስተኛ እንደሆነች፣ ሕይወቷን የሚያበላሽ ምንም ነገር እንደሌለ፣ እና እፎይታ ከሰማይ እንደመጣላት እንድንንገርህ ነግራናለች።» ▢ ​ሰውየውም ያጣት ጊዜ ብቻ ዋጋዋን የተረዳትን ውድ ኃብት  ዘግይቶ ከተረዳ በኋላ፣ እጆቹን በጸጸት እየነከሰ ቀሪ ሕይወቱን አሳለፈ። ተፈፀመ

በጣም ደስ የሚል፣ ልብን የሚያረካ ታላቅ ደስታ! የኡስታዝ ሳዳት ከማል ወንድም ተውበት አድርጓል። ከነበሩት ስህተቶች ታርሞ ወደ አላህ ተመልሷል።

قُـلْ لِلَّذِي اتَّـخَـذَ الـتَّـجَـهُّـمَ مَـرْكَـبًـا وَ رَآهُ دِيـنًـا و ارْتَــضَـاهُ مَـذْهَــــبًـا وَ لِـمَـذهَبِ الأَبـــرَارِ صَارَ مُـكَـذِّبـًـا إنْ كَانَ تَـابِـعُ أَحـمَــــدٍ مُـتَـوَهِّــبًـا فَـأَنـا الـمُــــقِـرُّ بِـأَ نَّـنِـي وَهَّـــابِي

👉ዱንያ ማለት እንዲህ ናት! ትኖራለህ - ትሞታለህ ታገኛለህ  - ታጣለህ ትደሰታለህ - ታዝናለህ ትስቃለህ   - ታለቅሳለህ ትበላለህ  - ትራባለህ ትወደሳለህ -ትወቀሳለህ ትዋደዳለህ -ትጣላለህ ትከበራለህ - ትዋረዳለህ ትወሳለህ  -  ትረሳለህ ታተርፋለህ - ትከስራለህ ዱንያ ማለት ይህች ናት። ለዚህ ሁሉ ሁነኛ መፍትሄው #ትዕግስት ማድረግ ነው። አላህ በሁሉም ነገር ትዕግስት ከሚያደርጉ ባሮቹ ያድርገን።

ደዕዋ ላይ ላለኸው ወገኔ ~ በደዕዋ ሂደትህ ላይ ጠላት አታብዛ። ከሁሉ ጋር አትጋጭ። በተለይ በአካባቢህ ደዕዋው ገና ዳዴ ላይ ከሆነ የማህበራዊ ሚዲያን ደዕዋ ወይም የተሻለ ድጋፍና መሰረት ያላቸውን አካባቢዎች አካሄድ ምሳሌ እንዳታደርግ። አቅምህን አገናዝብ። ደዕዋህን የፍጥጫ አታድርገው። የአካባቢህን ተጨባጭ ተረዳ። ተማሪዎችህ በችኮላ ለደዕዋው እንቅፋት እንዳይሆኑ ተቆጣጠር። ሁሉን ባንዴ አሳካለሁ ብለህ አታስብ። ብዙ ያሳደደ አንድ አይዝም። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኢብኑል ቀይም 📿 እንዲህ ብለዋል፦ «በሰዎች ሙገሳና አድናቆት የተፈተነ፣ አላህ ነውሩንና ወንጀሉን በመሰወሩ የታለለ፣ እንዲሁም አላህ በሚሰጠው ጸጋዎች ቀስ በቀስ ወደ ጥፋት የሚሳብ «ሙስተድረጅ» ስንቱ አለ! እነዚህ ሁሉ ቅጣቶችና ውርደቶች ሆነው ሳለ፣ መሃይሙ ሰው ግን እንደ ክብርና ድንቅ ስጦታ ይቆጥራቸዋል።»
📚الدَّاء و الدَّواء/لابن القيم رحمه الله( 119 )
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

✨ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ህብረት✨ 📜 ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት! 📜 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 በታላቅ ደስታ ና ፍቅር፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመምረጥ እኛን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ላላችሁ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታችንን እናቀርባለን። 🗓 የቅበላ ጊዜና የአቀባበል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር የሚከናወነው ጥቅምት 3 እና 4 ቀን 2019 ነው። በእነዚህ ቀናት፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ለእናንተ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሞቅ ያለና ደማቅ አቀባበል ያደርግላችኋል። በሰላም ወደ ግቢ እንድትገቡ እና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታገኙ የበኩላችንን እንወጣለን። 🤝 የእናንተ ትብብር ያስፈልገናል! ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት፣ የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት እና የአቀባበል ቡድናችን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግላችሁ፡ የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ: https://forms.gle/F7gwvpVVsnsj843Z6 ውድ አዲስ ገቢዎች፣ እኛን በቀላሉ ለማግኘት እና የተሟላ አገልግሎት ለመቀበል፣ ማንነታችሁን ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ የቀና ትብብራችሁን በአክብሮት እንጠይቃለን።እንዲሁም ሙስሊም መሆናችሁን ለማሳወቅ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ስልኮች እየደወላችሁ የአቀባበል ቡድናችንን እንድታነጋግሩ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📌 የአካባቢ ምደባ ማስታወሻ ወደ ግቢ ከመምጣታችሁ በፊት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ይለዩ፡- ✅ Natural Science ተማሪዎች፡- ወደ Main Campus ትመጣላችሁ። ✅ Social Science ተማሪዎች፡- ወደ Techno Campus ትመጣላችሁ። 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች ወደ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትመጡ አስፈላጊውን መረጃ ለማግኘት ወይም የአቀባበል ቡድናችንን እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡-              📚   Main campus =>ሀሰን      ☎️        090 632 6702 =>አቡዱረዛቅ           ☎️    0942213321 =>ነቢል       ☎️   096 999 0090 =>ጂፋር    affan orromo          ☎️  +251972575000                                                      💻 Techno campu       =>ዐማር ☎️+251925882521                        =>መስዑድ affan oromo ☎️  +251937517651  =>አስዓድ   ☎️   0963298664       🧕 ለሴት እህቶች ልዩ ማስታወቂያ: የእህቶችን ስልክ ቁጥር ለምትፈልጉ እህቶች ብቻ፣ በስልክ ቁጥር ☎️ +251925882521 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።    🌹  አላህ   በሰላም ያገናኘን 🤲🌹 🎉መልካም የዩኒቨርሲቲ ቆይታ እንመኛለን!🎉

በአላህ ይዣችኋለሁ፣ነብዩን የሚወድ ... ሼር ያድርግ ለሚሉ ሰዎች መልስ 🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር !! 🍃https://t.me/abujemila25

ወዳጄ ሆይ፣ እውነተኛው መለያየት በዋነኛነት በሞት አይሆንም፤ እኛም አላህ ከፈቀደ በአኺራ እንገናኛለን። እውነተኛው መለያየት ግን አንዳችን በጀነት ሲሆን ሌላችን በእሳት ውስጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ፣ አንድ ቀን በወንጀል ላይ ብታየኝ ሳትሰለች ምከረኝ፦ አላህን ፍራ! በለኝ። ለወንጀል አውሬ አትተወኝ አደራ። ምናልባት ከአንተ የምሰማው አንድ ቃል ለመዳኔ ምክንያት ይሆናል። አላህ እንዲህ ብሏል፦ [በዚያ ቀን ወዳጆች ከአላህ ፈሪዎች በስተቀር አንዳቸው ለሌላቸው ጠላቶች ይሆናሉ።] [አዝ-ዙኽሩፍ፡ 67] ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ለዘመዶ በመላክ ያድርሱ።