es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete 👈

የአኺራ ተጓዦች☁️

የአኺራ ተጓዦች☁️

Ir al canal en Telegram

ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ላይ ሱናን የሚደግፉ የሚያነቃቁ እና አሪፍ አሪፍ የሆኑ ስንቆችን እንለቃለን inshallah የሱና ቻናሎች መገኛ @bahruteka @shakirsultan @alateriqilhaq @abdulham

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
975
Suscriptores
+724 horas
+367 días
+15630 días
Archivo de publicaciones
✅ ከሰውነት መጀመሪያ የሚከረፋው ሆድ ነው ! يقول الصحابي الجليل جندب بن عبدالله البجلي – رضي الله عنه – " إن أول ما ينتن من الإنسان بطنه ، فم استطاعة أن لا يأكل إلا طيبا فليفعل " أخرجه الإمام البخاري في صحيحه ጁንዱብ ኢብኑ ዐብዱላሂ አል በጀልይ – ረዲየላሁ ዐንሁ – እንዲህ ይላል : – " (ከሰውል ልጅ አካል) መጀመሪያ የሚከረፋው ሆዱ ነው ። ጥሩ ( ሐላል ) ነገር እንጂ እንዳይበላ (ማድረግ) የቻለ ሰው ያድርገው " ። https://t.me/bahruteka

sticker.webp0.26 KB

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ صباح الخير مُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺﷺمُحَمَّد ﷺ ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺ ዛሬ ጁመዐ ነው ሰለዋት አብዙ አህባቢ

اَلسَـــــــــــــــلاّمُ عَلَـَــــيـــــــكُمَ وَرَحَمَتُــــــــــــــ اللَّهِ  وَبَرَكَــــٰـــــــــــــــــاتَه ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ አልፋችሁ በ219ኢ.አ ፍሬሽ እንዲሁም ሪሚድያል ተማሪ ለሆናችሁ ወንድም እህቶች በትንሹም ቢሆን ምክር ቢጤ ልሰጣችሁ ወደድኩ!! ወደ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ለገባችሁ አዲስ ሙስሊም ተማሪዎች በመጀመሪያ አሏህ (ሱወ) አመስግኑት። ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞው የትምህርት ቤት ቆይታ ፈጽሞ የተለየ፣ ነፃነት የሚበዛበት፣ የተለያዩ ሃሳቦችና አመለካከቶች የሚንጸባረቁበት ፈታኝም ምቹም ምዕራፍ ነው። በዚህ አዲስ ጉዟችሁ ዲናችሁን ይዛችሁ ድል አድራጊ ሆናችሁ እንድትወጡ ቁርአንና ሀዲስን መሰረት ባደረገ መልኩ መመራት ይኖርባችኋል። ➊.​ዩኒቨርሲቲ የፈተናና የዕድል ማዕከል መሆኑ ​ዩኒቨርሲቲ የዲን እውቀትና የዱንያ እውቀት የሚቀሰምበት፣ የሰው ልጅ እምነቱና አቋሙ የሚፈተንበት ቦታ ነው። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል:
​ {أَحَسِبَ النَّاسُ أَنْ يُترَكُوا أَنْ يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ} "ሰዎች «አምነናል» በማለታቸው ብቻ የሚተው መሆናቸውን፣ እነሱም የማይፈተኑ መሆኑን አሰቡን?" (ሱረቱል አንከቡት፡ 2-3)
​ይህ አንቀጽ እንደሚያሳየው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስትገቡ የተለያዩ ፈተናዎች (የሃሳብ መዛባት፣ መጥፎ ጓደኞች፣ የጊዜ እጥረት) እንደሚገጥሟችሁ ታውቆ ጽናትን ይጠይቃል። ➋.​ትክክለኛ ጓደኛ መምረጥ (የጓደኛ ምርጫ) ​በዩኒቨርሲቲ ሕይወት ውስጥ ስኬታማ መሆንም ሆነ መክሰር ከምታደርጉት የጓደኛ ምርጫ ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመልካም እና የመጥፎ ጓደኛን ምሳሌ ሲያስረዱ፦
​"የመልካምና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ከያሚ (ሽቶ ነጋዴ) እና እንደ እሳት ነፊ ነው። የከያሚው ነገር ሽቶ ይለግስሃል፤ ወይም ከርሱ ሽቶ ትጠቀማለህ፤ ወይም መልካም ሽታ ታገኛለህ። የእሳት ነፊው ግን (ብረት የሚቀጥቅጥ) ልብስህን ያቃጥለዋል፤ ወይም መጥፎ ሽታ ታገኛለህ።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
​በመሆኑም አላህን የሚያስታውሱአችሁ፣ በትምህርት የሚያግዟችሁ እና ወደ ኸይር (መልካም ነገር) የሚጠሯችሁ ሰዎችን እንጂ ወደ ጥፋት የሚወስዷችሁን መጥፎ ጓደኞች መጠንቀቅ ይገባል። ➌.​ዱንያዊና ዲናዊ ትምህርትን ማቀናጀት ​ዩኒቨርሲቲ የገባችሁት ዱንያዊ ትምህርት ለመማር ብቻ ሳይሆን፣ አላህን የምትገዙበትን ትክክለኛ እውቀት (ዲን) ይበልጥ ለማወቅ ጭምር ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: ​"አላህ ለሱ መልካምን የሻለት ሰው የዲንን እውቀት ይለግሰዋል።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም) ​ከዘመናዊው ትምህርት ጎን ለጎን ቂርዓትና ደርስ መከታተል፣ ቁርአንንና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና መቅሰም ለልብ ሰላም እና ከጥርጣሬዎች ለመጠበቅ እጅግ ወሳኝ መሳሪያችን ነው። ➍.በግቢ ውስጥ ያሉ ​ሰለፍይ ጀማዓዎችን መቀላቀል ​በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እጅግ ብዙ ሐሳቦችና ጽንፈኛ ወይም አቅጣጫቸውን የሳቱ ቡድኖች አሉ። ከቁርአንና ከሀዲስ እንዲሁም ከመጀመሪያው ትውልድ (ሰለፎች) መረዳት ውጪ ያሉ አካሄዶችን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲከተሉ ሲያዝ፦
​{وَأَنَّ هَذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَنْ سَبِيلِهِ} "ይህም ቀጥተኛ መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፤ መንገዶችንም አትከተሉ፤ ከቀጥተኛ መንገዱ ይለያያችኋልና።" (ሱረቱል አንአም፡ 153)
​እዚህ ላይ "መንገዶች" የሚለው ቃል ብዙኃኑን የተሳሳቱ አቅጣጫዎች የሚያሳይ ሲሆን፣ "መንገዴ" የሚለው ነጠላው ደግሞ ቁርአንንና ሱናን በሰለፎች ግንዛቤ የሚከተለውን ሰለፍይ ጀማዓ (ትክክለኛውን የሐቅ መንገድ) ያመለክታል። በኸይር ነገር ካልተጠመዳችሁ እና ትክክለኛውን እውቀት ካልያዛችሁ ዲናችሁ ይሸረሸራል። ከምንም በላይ አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር ከየትኛውም የቢድዓ ባለቤት ጀማዓም ሆነ ግለሰብ ርቃችሁ የሰለፍይ ጀማዓዎችን እንድትቀላቀሉ አደራ እላለሁ። ይህን ማድረጋችሁ ለሁሉም ነገር መፍትሄ የማግኘት እድላችሁ ቅርብ ነውና። ጠቅለል ሳደርገው ​ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በዕውቀት፣ በሂክማ (ጥበብ) እና በመልካም ስነ-ምግባር ታንጻችሁ ውጡ። በጊዜያዊ የዱንያ ውበት እና ፈተናዎች ተሸውዳችሁ ዲናችሁን እንዳታጡ አላህን ፍሩ። ትክክለኛ ጓደኞችን ያዙ፤ የኡለማዎችን ደርስ አጥብቃችሁ ያዙ ተማሩ ወንድማማችነትን ፍጠሩ ። በትንሿም ብትሆን ይህን ይመስላል ለጓደኞቻችሁ #share አድርጉላቸው!! ወሏሁ አዕለም!! ✍ ወንድማችሁ አብደረህማን /አቡ ዩስራ 🔗ቴሌግራም ቻናል:- t.me/Quranrecitation02 t.me/Quranrecitation02

👉ሰለፊይ ማስረጃ በዞረበት ይዞራል💪🏻 👉ኢኽዋን ስልጣን በዞረበት ይዞራል 👀 👉ሱፍይ ትሪ በዞረበት ይዞራል👀

👉የሰዎች አንተን ያለማወቅ አንተ ራስህን እንዳታውቅ እንዳያደርግህ ✍ኡስታዝ ባህሩ ተካ

🔊#አዋጅ! #አዋጅ! #አዋጅ! 🔊 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🔵እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ማለትም ነሀሴ 22/2018 አ. ል. {ረቢዓል አወል ١٥/١٤٤٨. هـ } በዓይነቱ ል
🔊#አዋጅ! #አዋጅ! #አዋጅ! 🔊   السلام عليكم ورحمة الله وبركاته  🔵እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ማለትም ነሀሴ 22/2018 አ. ል. {ረቢዓል አወል ١٥/١٤٤٨. هـ } በዓይነቱ ልዮ የሆነ ታላላቅ የሰለፍያ #መሻይኾች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ #የonline የዳዕዋ ፕሮግራም ተሰናድቶ አርሂቡ ይላቹሀል።    💺ተጋባዥ መሻይኾች  1,ሸይኽ ሀሰን ገላዉ {ከባህር ዳር}  2,ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል'ለተሚይ{ከስልጤ}   3,ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ(ከባህርዳር)  4,ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን  አስ'ስልጢ (ከአዲስ አበበ) 5,ሸይኽ ጦሀ ኸድር (ከአዲስ አበባ)  6,ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን (ከኮምቦልቻ)  7,ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል(ከኮምቦልቻ)  8,ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት {ከሀራ}  9,ሸይኽ ሑሰይን ከረም (ከሀራ)  10,ሸይኽ ሙባረክ (ከወልቅጤ)  ✪ሌሎችም እንግዶች ይኖሩናል    🌍የፕሮግራሙ ቦታ  በሀራ ሰለፍዮች የቴሌግራም ግሩፕ  💻የፕሮግራሙ አዘጋጆች የሀራ ሰለፍያ ጀመዓዋች   🕰የፕሮግራሙ ሰዓት  🇪🇹በኢትዮ. 3:00  pm 🇸🇦በሳዉድ. 9:00 pm 🇦🇪በዱባይ. 4:00 pm   📡ፕሮግራሙን ለመከታተል 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/haraselefi  https://t.me/haraselefi https://t.me/haraselefi https://t.me/haraselefi 👆👆👆👆👆👆👆👆 Join ይበሉ!   ✅የፕሮግራሙ ቀን እስከሚደርስ #ሸር ባማድረግ ለብዙ እህት ወንድሞች ተደራሽ እንድሆን የበኩላችንን እንወጣ። 🔵ባረከሏሁ ፊኩም!!!! 💻 ሌሎች መሻይኾቻችንና ዱዓቶቻችን ኢንሻ አሏህ በሌላ ፕሮግራም የምንገናኝ ይሆናል  

ራስህን አትጣው እንጂ ያጣኸውን በሙሉ ታገኘዋለህ።

صباح الخير 👌🏻 @nesiheti_linisa

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ አላህ ፈቅዶ ይኸው አንግተናል።ዛሬ በእጃችን ያለው የስኬት መጀመሪያ ነው።ሁሉም ነገር በአላህ ፍቃድ እንደሚሆን አምነ
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎ አላህ ፈቅዶ ይኸው አንግተናል።ዛሬ በእጃችን ያለው የስኬት መጀመሪያ ነው።ሁሉም ነገር በአላህ ፍቃድ እንደሚሆን አምነን አደርን ይኸው ነጋ። صباح الخير 👋

ነገ ሀሙስ ነውስ እየፆምን @nesihetulinisa

🌿 ሰለፍይ ሁኚ/ን 🌿 ➺ሰለፍይ ሁኚ/ን ➺በቁርኣን ጽኚ/ና፣ ➺ሱናን ተከተይ/ል፣ ➺ተውሒድን አጥብቀሽ ያዢ/ዝ፣ ➺ቢድዓን ተይ/ው፣ ➺የሰለፍ ሶሊሕን መንገድ ያዢ/ዝ። ➺ሰለፍይነት ስም አይደለም፤ ✦ እውቀትና ተግባር ነው።

👉 ሙሲባ ለፈተና ነው የሚመጣው ! ሙሲባ ሲመጣ ለፈተና ነው የሚመጣው የተፈታኙ ውጤት ደግሞ እንደሚከተለው ነው : – – በሙሲባው ከተበሳጨና ከተቆጣ ሙሲባው ከአላህ የሆነ ቅጣት ነው ። – ሙሲባ በደረሰበት ጊዜ ሶብር ካደረገ ለሀጢያቱ ማበሻ ነው ። – ከሶብሩ ጋር አላህ ለሒክማው ነው ይህን ያደረገው የበለጠ ቢመጣስ ኖሮ ብሎ ከወደደ ደረጃው ከፍ ማድረጊያ ነው ። የአላህን ጥበብ ከሚረዱ ባሮቹ ያድርገን ። http://t.me/bahruteka

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሰለፊዮች እንኳን ደስ ኣላችሁ ይህቺ አፕ በተሳካ ሁኔታ በplay store ተጭናለች ከዚህም ቦሀላ የምንሰራቸው አፖችን በፕሌይስቶር ስለምንጭን ሰርች ሲደ
+1
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሰለፊዮች እንኳን ደስ ኣላችሁ ይህቺ አፕ በተሳካ ሁኔታ በplay store ተጭናለች  ከዚህም ቦሀላ የምንሰራቸው አፖችን በፕሌይስቶር ስለምንጭን ሰርች ሲደረጉ ከፊት እንዲመጡ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ  አምስት ኮከብ እንድትሰጡ በታለቅ አክብሮት እና ትህትና እያጠየቅን መላው ሰለፊይ የቻናል በልተቤቶች ለሌሎች እንዲደርስ ሼር መድረግን አትርሱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.abdulrezak.tuhfetulatfal&utm_source=chatgpt.com 📲 አሁኑኑ አፑን ያውርዱ እና ለሌሎችም ያጋሩ። 🛠 የአፕ ማሰሪያ አገልግሎት ለማግኘት 👉 @JJ_selfy_app_developer 📢 ከ100 በላይ እስላማዊ አፕልኬሽኖችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/jj_app_developer https://t.me/jj_app_developer https://t.me/jj_app_developer

አንዳንዱ ገبይ የመውሊዱን ፍቁድነት በሰው ብዛት ሊመዝነው ይሞክራል !!ያወቀ ና የተማረ ግን አብዛኛው ሰው አሏህን በትክክል እንደማያመልክ ና መልዕክተኛውንም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)በትክክል እንደ
አንዳንዱ ገبይ የመውሊዱን ፍቁድነት በሰው ብዛት ሊመዝነው ይሞክራል !!ያወቀ ና የተማረ ግን አብዛኛው ሰው አሏህን በትክክል እንደማያመልክ ና መልዕክተኛውንም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)በትክክል እንደማይታዘዝ የተነገረ መሆኑን ይረዳል ደሞም አብዛኛው ወጣት ልደት ለማክበር የመጣ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሃል በእትዮው ኑሮ ውድነት የተነሳ የስጋ ናፍቆት ስለሚኖርበት ምናልባት ካገኘሁኝ ብሎ ነው የሚመጣው ወይም ወንዱ ሴት ሴቷ ወንድን ለማግኘት ብለው ነው የሚመጡት የተናገርኩ ያለሁት ግምት ወይም ውሸት እንዳይመስላችሁ ሪል ነው!!ያየነው ነገር ስለሆነ

አብሽሩ ሁሉም ነገር ያልፋል ان شاء اللہ🙌 መውሊድ ግን ከቢድዐነት አያልፍም👀 @nesihetulinisa

ሁለተኛው የቻናላችን የማስጠንቀቂያ video @light_of_sunnah

አህያ አህያ ነው -- ብትለውም ሀሬ ቋንቋ መቀያየር -- አያደርገውም በሬ መውሊድም ቢድዐ ነው -- ብትለውም ሀሰና ስያሜ ማሳመር-- አያደርገውም ሱና ከነብዩ መንገድ -- የራቀ ነውና ✍ኢብኑ ኑሪ @
አህያ አህያ ነው -- ብትለውም ሀሬ ቋንቋ መቀያየር -- አያደርገውም በሬ መውሊድም ቢድዐ ነው -- ብትለውም ሀሰና ስያሜ ማሳመር-- አያደርገውም ሱና ከነብዩ መንገድ -- የራቀ ነውና ✍ኢብኑ ኑሪ @light_of_sunnah