የአኺራ ተጓዦች☁️
Open in Telegram
ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ላይ ሱናን የሚደግፉ የሚያነቃቁ እና አሪፍ አሪፍ የሆኑ ስንቆችን እንለቃለን inshallah የሱና ቻናሎች መገኛ @bahruteka @shakirsultan @alateriqilhaq @abdulham
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
966
Subscribers
No data24 hours
+287 days
+13630 days
Posts Archive
966
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ
صباح الخير
مُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺﷺمُحَمَّد ﷺ ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺمُحَمَّد ﷺ
ዛሬ ጁመዐ ነው ሰለዋት አብዙ አህባቢ
966
اَلسَـــــــــــــــلاّمُ عَلَـَــــيـــــــكُمَ
وَرَحَمَتُــــــــــــــ اللَّهِ وَبَرَكَــــٰـــــــــــــــــاتَه
ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ አልፋችሁ በ219ኢ.አ ፍሬሽ እንዲሁም ሪሚድያል ተማሪ ለሆናችሁ ወንድም እህቶች በትንሹም ቢሆን ምክር ቢጤ ልሰጣችሁ ወደድኩ!!
ወደ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ለገባችሁ አዲስ ሙስሊም ተማሪዎች በመጀመሪያ አሏህ (ሱወ) አመስግኑት። ዩኒቨርሲቲ ከቀድሞው የትምህርት ቤት ቆይታ ፈጽሞ የተለየ፣ ነፃነት የሚበዛበት፣ የተለያዩ ሃሳቦችና አመለካከቶች የሚንጸባረቁበት ፈታኝም ምቹም ምዕራፍ ነው። በዚህ አዲስ ጉዟችሁ ዲናችሁን ይዛችሁ ድል አድራጊ ሆናችሁ እንድትወጡ ቁርአንና ሀዲስን መሰረት ባደረገ መልኩ መመራት ይኖርባችኋል።
➊.ዩኒቨርሲቲ የፈተናና የዕድል ማዕከል መሆኑ
ዩኒቨርሲቲ የዲን እውቀትና የዱንያ እውቀት የሚቀሰምበት፣ የሰው ልጅ እምነቱና አቋሙ የሚፈተንበት ቦታ ነው። አላህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል:
{أَحَسِبَ النَّاسُ أَنْ يُترَكُوا أَنْ يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ} "ሰዎች «አምነናል» በማለታቸው ብቻ የሚተው መሆናቸውን፣ እነሱም የማይፈተኑ መሆኑን አሰቡን?" (ሱረቱል አንከቡት፡ 2-3)ይህ አንቀጽ እንደሚያሳየው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስትገቡ የተለያዩ ፈተናዎች (የሃሳብ መዛባት፣ መጥፎ ጓደኞች፣ የጊዜ እጥረት) እንደሚገጥሟችሁ ታውቆ ጽናትን ይጠይቃል። ➋.ትክክለኛ ጓደኛ መምረጥ (የጓደኛ ምርጫ) በዩኒቨርሲቲ ሕይወት ውስጥ ስኬታማ መሆንም ሆነ መክሰር ከምታደርጉት የጓደኛ ምርጫ ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመልካም እና የመጥፎ ጓደኛን ምሳሌ ሲያስረዱ፦
"የመልካምና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ከያሚ (ሽቶ ነጋዴ) እና እንደ እሳት ነፊ ነው። የከያሚው ነገር ሽቶ ይለግስሃል፤ ወይም ከርሱ ሽቶ ትጠቀማለህ፤ ወይም መልካም ሽታ ታገኛለህ። የእሳት ነፊው ግን (ብረት የሚቀጥቅጥ) ልብስህን ያቃጥለዋል፤ ወይም መጥፎ ሽታ ታገኛለህ።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም)በመሆኑም አላህን የሚያስታውሱአችሁ፣ በትምህርት የሚያግዟችሁ እና ወደ ኸይር (መልካም ነገር) የሚጠሯችሁ ሰዎችን እንጂ ወደ ጥፋት የሚወስዷችሁን መጥፎ ጓደኞች መጠንቀቅ ይገባል። ➌.ዱንያዊና ዲናዊ ትምህርትን ማቀናጀት ዩኒቨርሲቲ የገባችሁት ዱንያዊ ትምህርት ለመማር ብቻ ሳይሆን፣ አላህን የምትገዙበትን ትክክለኛ እውቀት (ዲን) ይበልጥ ለማወቅ ጭምር ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ለሱ መልካምን የሻለት ሰው የዲንን እውቀት ይለግሰዋል።" (ቡኻሪ እና ሙስሊም) ከዘመናዊው ትምህርት ጎን ለጎን ቂርዓትና ደርስ መከታተል፣ ቁርአንንና የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና መቅሰም ለልብ ሰላም እና ከጥርጣሬዎች ለመጠበቅ እጅግ ወሳኝ መሳሪያችን ነው። ➍.በግቢ ውስጥ ያሉ ሰለፍይ ጀማዓዎችን መቀላቀል በዩኒቨርሲቲ ውስጥ እጅግ ብዙ ሐሳቦችና ጽንፈኛ ወይም አቅጣጫቸውን የሳቱ ቡድኖች አሉ። ከቁርአንና ከሀዲስ እንዲሁም ከመጀመሪያው ትውልድ (ሰለፎች) መረዳት ውጪ ያሉ አካሄዶችን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲከተሉ ሲያዝ፦
{وَأَنَّ هَذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَنْ سَبِيلِهِ} "ይህም ቀጥተኛ መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፤ መንገዶችንም አትከተሉ፤ ከቀጥተኛ መንገዱ ይለያያችኋልና።" (ሱረቱል አንአም፡ 153)እዚህ ላይ "መንገዶች" የሚለው ቃል ብዙኃኑን የተሳሳቱ አቅጣጫዎች የሚያሳይ ሲሆን፣ "መንገዴ" የሚለው ነጠላው ደግሞ ቁርአንንና ሱናን በሰለፎች ግንዛቤ የሚከተለውን ሰለፍይ ጀማዓ (ትክክለኛውን የሐቅ መንገድ) ያመለክታል። በኸይር ነገር ካልተጠመዳችሁ እና ትክክለኛውን እውቀት ካልያዛችሁ ዲናችሁ ይሸረሸራል። ከምንም በላይ አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር ከየትኛውም የቢድዓ ባለቤት ጀማዓም ሆነ ግለሰብ ርቃችሁ የሰለፍይ ጀማዓዎችን እንድትቀላቀሉ አደራ እላለሁ። ይህን ማድረጋችሁ ለሁሉም ነገር መፍትሄ የማግኘት እድላችሁ ቅርብ ነውና። ጠቅለል ሳደርገው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በዕውቀት፣ በሂክማ (ጥበብ) እና በመልካም ስነ-ምግባር ታንጻችሁ ውጡ። በጊዜያዊ የዱንያ ውበት እና ፈተናዎች ተሸውዳችሁ ዲናችሁን እንዳታጡ አላህን ፍሩ። ትክክለኛ ጓደኞችን ያዙ፤ የኡለማዎችን ደርስ አጥብቃችሁ ያዙ ተማሩ ወንድማማችነትን ፍጠሩ ። በትንሿም ብትሆን ይህን ይመስላል ለጓደኞቻችሁ #share አድርጉላቸው!! ወሏሁ አዕለም!! ✍ ወንድማችሁ አብደረህማን /አቡ ዩስራ 🔗ቴሌግራም ቻናል:- t.me/Quranrecitation02 t.me/Quranrecitation02
966
🔊#አዋጅ! #አዋጅ! #አዋጅ! 🔊
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🔵እነሆ የፊታችን ጁሙዓ ማለትም ነሀሴ 22/2018 አ. ል. {ረቢዓል አወል ١٥/١٤٤٨. هـ } በዓይነቱ ልዮ የሆነ ታላላቅ የሰለፍያ #መሻይኾች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ #የonline የዳዕዋ ፕሮግራም ተሰናድቶ አርሂቡ ይላቹሀል።
💺ተጋባዥ መሻይኾች
1,ሸይኽ ሀሰን ገላዉ {ከባህር ዳር}
2,ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል'ለተሚይ{ከስልጤ}
3,ሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ(ከባህርዳር)
4,ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን አስ'ስልጢ
(ከአዲስ አበበ)
5,ሸይኽ ጦሀ ኸድር (ከአዲስ አበባ)
6,ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን (ከኮምቦልቻ)
7,ሸይኽ ሙሐመድ ጀማል(ከኮምቦልቻ)
8,ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት {ከሀራ}
9,ሸይኽ ሑሰይን ከረም (ከሀራ)
10,ሸይኽ ሙባረክ (ከወልቅጤ)
✪ሌሎችም እንግዶች ይኖሩናል
🌍የፕሮግራሙ ቦታ
በሀራ ሰለፍዮች የቴሌግራም ግሩፕ
💻የፕሮግራሙ አዘጋጆች
የሀራ ሰለፍያ ጀመዓዋች
🕰የፕሮግራሙ ሰዓት
🇪🇹በኢትዮ. 3:00 pm
🇸🇦በሳዉድ. 9:00 pm
🇦🇪በዱባይ. 4:00 pm
📡ፕሮግራሙን ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi
https://t.me/haraselefi
👆👆👆👆👆👆👆👆
Join ይበሉ!
✅የፕሮግራሙ ቀን እስከሚደርስ #ሸር
ባማድረግ ለብዙ እህት ወንድሞች ተደራሽ እንድሆን የበኩላችንን እንወጣ።
🔵ባረከሏሁ ፊኩም!!!!
💻 ሌሎች መሻይኾቻችንና ዱዓቶቻችን ኢንሻ አሏህ በሌላ ፕሮግራም የምንገናኝ ይሆናል
966
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ
አላህ ፈቅዶ ይኸው አንግተናል።ዛሬ በእጃችን ያለው የስኬት መጀመሪያ ነው።ሁሉም ነገር በአላህ ፍቃድ እንደሚሆን አምነን አደርን ይኸው ነጋ። صباح الخير 👋
966
🌿 ሰለፍይ ሁኚ/ን 🌿
➺ሰለፍይ ሁኚ/ን
➺በቁርኣን ጽኚ/ና፣
➺ሱናን ተከተይ/ል፣
➺ተውሒድን አጥብቀሽ ያዢ/ዝ፣
➺ቢድዓን ተይ/ው፣
➺የሰለፍ ሶሊሕን መንገድ ያዢ/ዝ።
➺ሰለፍይነት ስም አይደለም፤
✦ እውቀትና ተግባር ነው።
966
👉 ሙሲባ ለፈተና ነው የሚመጣው !
ሙሲባ ሲመጣ ለፈተና ነው የሚመጣው የተፈታኙ ውጤት ደግሞ እንደሚከተለው ነው : –
– በሙሲባው ከተበሳጨና ከተቆጣ ሙሲባው ከአላህ የሆነ ቅጣት ነው ።
– ሙሲባ በደረሰበት ጊዜ ሶብር ካደረገ ለሀጢያቱ ማበሻ ነው ።
– ከሶብሩ ጋር አላህ ለሒክማው ነው ይህን ያደረገው የበለጠ ቢመጣስ ኖሮ ብሎ ከወደደ ደረጃው ከፍ ማድረጊያ ነው ።
የአላህን ጥበብ ከሚረዱ ባሮቹ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka
966
+1
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ
ውድ ሰለፊዮች እንኳን ደስ ኣላችሁ
ይህቺ አፕ በተሳካ ሁኔታ በplay store ተጭናለች ከዚህም ቦሀላ የምንሰራቸው አፖችን በፕሌይስቶር ስለምንጭን ሰርች ሲደረጉ ከፊት እንዲመጡ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ አምስት ኮከብ እንድትሰጡ በታለቅ አክብሮት እና ትህትና እያጠየቅን መላው ሰለፊይ የቻናል በልተቤቶች ለሌሎች እንዲደርስ ሼር መድረግን አትርሱ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.abdulrezak.tuhfetulatfal&utm_source=chatgpt.com
📲 አሁኑኑ አፑን ያውርዱ እና ለሌሎችም ያጋሩ።
🛠 የአፕ ማሰሪያ አገልግሎት ለማግኘት
👉 @JJ_selfy_app_developer
📢 ከ100 በላይ እስላማዊ አፕልኬሽኖችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/jj_app_developer
https://t.me/jj_app_developer
https://t.me/jj_app_developer
966
አንዳንዱ ገبይ የመውሊዱን ፍቁድነት በሰው ብዛት ሊመዝነው ይሞክራል !!ያወቀ ና የተማረ ግን አብዛኛው ሰው አሏህን በትክክል እንደማያመልክ ና መልዕክተኛውንም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም)በትክክል እንደማይታዘዝ የተነገረ መሆኑን ይረዳል ደሞም አብዛኛው ወጣት ልደት ለማክበር የመጣ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችሃል በእትዮው ኑሮ ውድነት የተነሳ የስጋ ናፍቆት ስለሚኖርበት ምናልባት ካገኘሁኝ ብሎ ነው የሚመጣው ወይም ወንዱ ሴት ሴቷ ወንድን ለማግኘት ብለው ነው የሚመጡት የተናገርኩ ያለሁት ግምት ወይም ውሸት እንዳይመስላችሁ ሪል ነው!!ያየነው ነገር ስለሆነ
966
አህያ አህያ ነው -- ብትለውም ሀሬ
ቋንቋ መቀያየር -- አያደርገውም በሬ
መውሊድም ቢድዐ ነው -- ብትለውም ሀሰና
ስያሜ ማሳመር-- አያደርገውም ሱና
ከነብዩ መንገድ -- የራቀ ነውና
✍ኢብኑ ኑሪ
@light_of_sunnah
966
መላው ኡማ የነቢዩን ﷺ ልደት (መውሊድ) ያከብራሉ።
መውሊድን ያላከበሩት ግን እነዚህ ብቻ ናቸው፦ ሰለ#ፊዮች፣ ወሃ#ቢዮች፣ መድኸ#ሊዮች፣ ኢብኑ ተይሚያ እና ሙሐመድ ቢን ዐብዱልወሃብ፣ተማሪዎቹ
እንዲሁም ነቢዩ ﷺ፣ ሶሐቦች፣ ታቢዒዮች እና አራቱ የፊቅህ ኢማሞች ናቸው።
እናንተ ከዬተኞቹ ናችሁ?
