en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 378
Subscribers
-424 hours
+2487 days
+1 44230 days
Posts Archive
ማዳጋስካር  በውቅያኖስ የተከበበች ደሴት ናት። 360 ዲግሪ የሚለካ የባህር በር  ያላት መሆኗ ለእድገቷ ዋስትና አልሆናትም። ስዊዘርላንድ የባህር በር የላትም። በዓመታዊ ጥቅል ምርት ወይም በነፍስ ወከፍ ገቢ አሊያም በህዝቧ የኑሮ ደረጃ  ስትመዘን  ካደጉት አገሮች ምድብ የምትገኝ ናት።  የዘርፉ ምሁራን ወረቀቶች ዳሰሳ የባህር በር ለእድገት ዋስትናም ሆነ ቅድመ-ሁኔታ አለመሆኑን በተረጋገጠ አኳኃን ይነግሩናል። ኢትዮጵያ የዚህ ልዩ ሁኔታ የምትሆንበት ምክንያት የለም። የባህር በር ለኢትዮጵያ እድገት ቅድመ-ሁኔታ እና/ ወይም ዋስትና አይደለም። በተሟላ ችጋር ውስጥ የዘለቅነው፣ ወደ  ቅርቃርም የገባነው የባህር በር ስላልኖረን አይደለም፤ የባህር በር ቢኖረንም  ሁለንተናዊ እድገት  የምናገኝ ስለመሆኑ ማረጋገጫ አይሆንም። ይህ ማለት ግን የባህር በር ለማናቸውም አገር እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ  የለውም ማለት ከቶ አይደለም። የባህር በር ለአንድ አገር እድገት  ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ላይ ልዩነት የለም። ይህ የኃለኛውም ድምዳሜ ለኢትዮጵያም እውነት ነው። አገዛዙ የባህር በርን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እድገት የሚኖረውን ፋይዳ በሚመለከት በብዙ  ማሳሳቻዎችና  ማጭበርበሮች ሊፈጥረው የሞከረው ስምምነት የባህር በር ማምጣት <ሙዝ የመላጥ ያህል ቀላል ነው፤ የባህር በሩን ካገኘንበት ቀን ጀምሮም ኢትዮጵያ ልዕለ-ኃያልና የምድር ገነት ትሆናለች> የሚል ነው። ይህ እልም ያለ ውሸትና ዓይን ያወጣ ማጭበርበር ነው። የአራት ኪሎው የፖለቲካ አማተሮች  የወደብን ጉዳይ እያቀነቀኑ ሊፈጥሩት የሞከሩት ህሊናዊ ሁኔታ ፈጽሞ እውን ሊሆን የማይችል ነው። ምክንያቱ ደግሞ ይህ ትውልድ  ያ  ትውልድ አይደለም፤ ይህን ትውልድ ማወቅ በሚመስል  ልፈፋ፣ እውነት በሚመስል  ኡኡታ ልታሳስተው አትችልም። መንግስት የመረጃ ሞኖፖሊውን ብቻ ሳይሆን የተረክ የበላይነቱን ከተቀማ ብዙ ዘመን ያለፈው ፣ የመረጃ አብዮት ፈንድቶ  እልፍ  አቅሞችን የፈጠረ ቢሆንም እነ አብይ አህመድ አሊ ገና ድሮ  በጥራዝ ነጠቅነት በለቃቀሙት የእነ ማኪያቬሊ  ምክሮች በእጅጉ የተለወጠውን ሁኔታ ለመምራት የሚዳክሩ ሆነዋል። በውጤቱም  ሁኔታውን የሚከተሉ እንጅ ሁኔታ መምራት የማይችሉ  ሆነው አንዱ ቀላል ችግር ሌሎች ውስብስብ ችግሮችን እየፈጠሩ የችግሮች ድር የተከመረባት አገር አድርገዋታል። ይህ ትግል  የግለሰብ ወይም የቡድን ወይም የኃይሎች ትግል አይደለም። ትግሉ የትውልድ ትግል ነው- የትግሉ አሳቢዎች፣ ተላሚዎች፣ ፈጻሚዎች  እና ገምጋሚዎች  የአዲሱ ትውልድ  ዋኖች ናቸው። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ  ማለት  የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ቡድን  ጥሪ  አይደለም።በዚህ ልክ የሚባል የእድሜ ገደብም የለውም።  መደመር እንደሚባለው መፈክር የጨበጣ  ልፈፋ  ሳይሆን  የኢትዮጵያ ፖለቲካ የችግር ትንተና እና የመፍትሄ ትልም የታጨቀበት የዘመኑ ትውልድ  ስምምነት ነው።  መዋቅራዊና ስርዓታዊ ለሆነው የአማራ ህዝብ በደል፣ የህልውና አደጋ ውስጥ ገብቶ ለፈጽሞ መጥፋት  የተዳረገ ህዝብ  ልጆች  መሰረታዊ እና ዘላቂ  መፍትሄ ለማበጀት በተካሄደ  ማማጥ የተገኘ  የትውልዱ  አዋጅ  ነው።  ይህ ትውልድ  በከረሙ  ስልቶች ልትሸውደው የማትችል ከመሆኑ እኩል  የሚያውጀውን ትግልም የማትገዳደረው ብርቱ  ነው። ይህ ብርታቱ  የትግሉን የስር ምክንያቶች፣ ዓላማዎችና ግቦች  በጥልቀትና በጥራት  ከመገንዘቡ የተነሳ በያዘው የሞራል ልዕልና ምክንያትም ነው። በከረመው  ስሪት  እና  በአሁኑ አገዛዝ ላይ ያመጸው  ትውልድ  ከሌሎች አገራት አቻዎቹ የሚወስደው ትምህርትም የሚያቀብለው ቁም-ነገርም አለው። አገዛዝን የሚነቀንቁ እና የሚያስወግዱ  የዚህ ትውልድ  አመጾችን  በብዙ መልክእ፣ በልዩ ልዩ አቅጣጫ፣ በመንታ ስልቶች የሚመራ እንጅ  በነጠላ ጉዳይ እና በአንድ ዘንግ ብቻ የሚቆም አይደለም።  የትጥቅ ትግል  መሪዎች የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ ጥሪ ሲያደርጉ እንግዳ የሚሆነውም  የትውልዱን የመግባባት ጥልቀት ካለማወቅ፣ የተለወጠውን  ህሊናዊና ነባራዊ ሁኔታ ካለመገንዘብ እንዲያውም የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ አመጽ ትግል  የሚጠፋፉ  መሆናቸውን ከሚያምን የአስተሳሰብ  ውቅር የሚመነጭ ነው። የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊነት የሚጠፋፉ  አስመስሎ የሚተነትንን ብሄርተኝነት  ሲያቀነቅን የኖረ  ሁሉ  የትጥቅ ትግል እና የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል  የሚሞላሉ  ናቸው ሲባል  ግራ መጋባቱ የማይጠበቅ አይደለም። ይህ ትውልድ  የትግሉ ርዕዮተ-ዓለማዊ ቅኝት ብሄርተኝነት  ሲሆን  ብሄርተኝነቶቹ  በአዎንታዊ የታሪክ ትንተና እና በበጎ የህዝቦች መስተጋብር እይታ  ላይ የተመሰረተ  ነው። ይህ  የብሄርተኝነት ብያኔ <<እሳት እና ጭድ  ናቸው>> የተባሉትን እና <<ቋሚ-ጠላቶች ናቸው>> የሚባሉትን  የጸረ-አገዛዝ ትግሉን  ልዩ ልዩ ኃይሎችና ህዝቦች  ብቻ ሳይሆን  የሚጠፋፉና አብረው የማይቆሙ  ተደርገው የሚታዩትን የትግል ስልቶችም የሚያመጋግብበትን የትግል ቀመር አበጅቷል። የማዳካስካር  ወጣቶች  ለባህር በር  ሳይሆን ለነጻነትና ለዴሞክራሲ ወደ አደባባይ የወጡት የባህር በር ያላቸው በመሆናቸው ሳይሆን እጣ ፈንታቸውን የሚወስነው የመንግስታቸው  ተፈጥሮ፣ የአስተዳደሩም ዘይቤ  እነሱን የሚመስል ሲሆን ብቻ መሆኑን ስላወቁ ነው። በኢትዮጵያ ሁኔታም  ከአገዛዝ ተላቅቆ  በእኩልነት፣ በነጻነት፣ በአንድነት እና በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ  የህዝቦችን ህልውና፣ መብቶች እና ጥቅሞች  የሚያከብርና የሚያስከብር ስርዓትና መዋቅር መፍጠር እና መገንባት ለእድገት ቅድመ-ሁኔታ እና ዋስትናም ነው። ገዥ ስልት ሆኖ እየተተገበረ  ግዙፍ ድሎችን እያስመዘገበ ባለው  የትጥቅ ትግል  ማዕቀፍ  የሚመራ የህዝባዊ አመጽና ተቃውሞ  አስፈላጊና ተገቢ   ነው።  *** 1. የዘርፉ  ተንታኞች እና  ምሁራን የዛሬውን ትውልድ የሰላማዊ አመጽና ተቃውሞ  የትውልድ  ዜድ አብዮት(GEN Z REVOLUTIONS)  እያሉ የሚጠሩት ነው። ሀጅ ሁሴን ሀሰን ህዳር 11/2018 ዓ.ም

ብልፅግናው መራሽ መንግሥት በተለያዩ ክልሎች ወጣቶችን እያፈነ በግዳጅ እያፈሰ እንደሆነ ታወቀ‼️    አገዛዙ በእርግጥም ለአመታት ወጣቶችን ፥ እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ጭምር ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል በግዳጅ እያፈሰ ወደ ጦርነት እሳት እየማገደ፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዕልፍ የድሃ ልጆችን አስጨርሷል ። ወላጅ እናቶችና ቤተሰቦች "ልጆቻችን የት ናቸው ?..." ብለው የመጠየቅ መብት እንኳን አይፈቀድላቸውም ። የአገዛዙ ፖሊስ እና ደምብ አሰከባሪ ተቀጣሪዎች የድሃ ልጆችን አፍነው ከወሰዱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው፤ "ልጄ ለአቅመ-ውትድርና አልደረሰም ፥ በዚያ ላይ ያለፍላጎቱ ነው ተገዶ የተወሰደው...ወዘተ..." ለሚለው ጥያቄ፤ ምላሻቸው "ልጆቻችሁ እንዲለቀቁ ከፈላጋችሁ ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር ካልከፈላችሁ አንለቅም...." በማለት የታፋሽ ቤተሰቦችን በማጎሳቆል ያባርሯቸዋል ። እናት የልጆቿ ህይወት በአጭር እንደቀረ አስባ ተስፋ ከመቁረጥ ውጪ ምንም አይነት መፍትሄ እንደማታመጣ አውቃ እያነባች ትኖራለች ። ይህ መፍትሄ የታጣለት የአገዛዙ የአፈሳ ጉዳይ ዛሬም በእጅጉን ተባብሶ መቀጠሉ ከተለያዩ ክልሎች መረጃዎች እየወጡ ይገኛል ። በቢንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ላይ በቀን 05/03/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ከፍተኛ የሆነ አፈሳ በአገዛዙ ፖሊስ እና ደምብ አስከባሪ ቅጥረኞች ወጣቶች፣ ሴቶች፣ በእድሜ የገፉ እንዲሁም እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ጭምር በግዳጅ አስገድደው እያፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ እያስገቡ እንደሆነ ስማቸውን እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአከባቢው ነዋሪዎች ለከሰም ሚዲያ መረጃውን አድርሰዋል ። ነዋሪዎች በቆይታቸውም፤ "በብልፅግናው አገዛዝ የግዳጅ አፈሳ ምክንያት በነፃነት መንቀሳቀስና ማህበራዊ ኑሮዋችን መኖር አልቻልንም ፥ ከቤት እንኳን ወጥተን ወደ ሱቅ መሄድ ፥ የተለያዩ የባልትና ግብዓቶችን አለማግኘታችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጎናል..." ሲሉ ለጣቢያችን ቅሬታቸውን ያቀርባሉ ።  የብልፅግናው መንግሥት በበኩሉ፤ በተለያዩ የፕሮፖጋንዳ የሚዲያ መሣሪያው "ምንም አይነት አፈሳ አላደረግንም፤ ወደው እና ፈቅደው ነው 'የሀገር መከላከያ ሰራዊት'ን የሚቀላቀሉት ። ይህ ሁሉ የጠላት እና የአሸባሪዎች የሀሰት ወሬ ነው..." በማለት፤ ውሃ የማያነሳ ማስተባበያ እየሰጠ ይገኛል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በኦሮሚያ ክልል፡ በመርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ፣ በናዝሪት እና በሀረርጌ በተለያዩ አከባቢ እንዲሁም በሁሉም ክልል በሚባል ደረጃ በዚህ ወራት ብቻ ቁጥራቸው በውል የማይገመት እድሚያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ፥ በእድሚያቸው የገፉ ዜጎችን በግዳጅ ታፍሰው በብልፅግናው መንግሥት ተወስደዋል ። በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ፡ አቦምሳ ከተማ ዛሬ ማለትም፤ በቀን 11/03/2018 ዓ.ም "በአገዛዙ በፖሊስ እና በደምብ አስከባሪ አባላት በየመንገዱ የሚንቀሳቀሱትን ዜጎች በግዳጅ እያፈኑ እያፈሱ ወደ ወታደር ካምፕ (ማጎሪያ መጋዘን) እየወሰዱ እንደሚገኙ..." አንድ የከተማው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ አቤቱታቸውን ለከሰም ሚዲያ ተናግረዋል ። በአርሲ ዞን አከባቢ በተለያዩ ወረዳዎች በዚህ ወራት ብቻ በሺህ የሚቆጠሩ አማራ ኦርቶዶክሳውያን በግፈኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን መዘገባችን ይታወሳል ። በተለያዩ መዓዘናት በጦርነት ውጥረት ሲገጥመው፤ ምስኪን የድሃ ልጆችን ዛሬም በግዳጅ እያፈሰ ትውልዱን ለእሳት እራት እየዳረገው ይገኛል ። © በአበባየሁ ሰይፈ

መታሰቢያነቱ በአርበኛ ጌትነት መሳፍንት በሆነ ዘመቻ      ከ180  በላይ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሆነ።         ከ72 ሰዓታት በላይ ያስቆጠረው የሰሜን ጎንደር ቀጠና ውጊያ የራስ አሞራው ውብነህ እና የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች  በተለያዩ ግንባሮች አስደናቂ ድል በመጎናፀፍ በበላይ እየቋጨ ይገኛል።    ጀግናው አርበኛ ጌትነት መሳፍንትን ህልፈት ተከትሎ የቀጠናው ተዋጊ ሞራል ተናግቶልኛል በሚል ስሌት ከ4 አቅጣጫ ወደ ዳባት ወረዳ አጅሬ ጃኖራ ያመራው የጡት ቆራጩና ሴት ደፋሪው የዓብይ ግሪሳ በራስ አሞራው 3ኛ ኮር ሰራዊታችን በቆላማው የወገራ ጠገዴና አርማጭሆ እንዲሁም ዛሪማና ቦዛ አዋሳኝ መሬቶች እንደበረዶ ቀልጦ ቀርቷል። 🔸ተግተልቶሎ የመጣው ጠላት አራቡር ቀበሌ አቦ ገዳም፣ሞርጠጭ ፀበልና ወይራ ጊዮርጊስ ማለትም (7,9 እና 13 ቁጥር በመባል የሚታወቅ ልዩ  ቦታ ) ከ30 በላይ ሲደመሰስ 23 ቁስለኛ ሁነል።ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ተደርጓል።ቀሪው ወደ ዳባት ፈርጥጧል። 🔸በደባርቅ አቅራቢያ ጥራይና የተገረፈው የጠላት ኃይል ለጊዜው በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።መቋቋም ስላልቻለም ሸሽቶ ደባርቅ ተመልሷል። 🔸 አጅሬ ወንበርየ ሚካኤል፣አይረፈዳ ማርያም እና መድሃኒያለም እና ቻይና ካምፕ እና ተንሳየ በተሰኙ ልዩ ቦታዎች በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች የጌትነት መሳፍንት ወንድሞች የዓብይን ሰራዊት በእሳት ቆልተውታል።በርከት ባሉ ግንባሮች ላለመማረክ የሞት ሽረት ለመዋጋት ቢሞክርም በመጨረሻም የአረመኔው ወታደር የሬሳ ነዶ ተቆላልፎ ወደቀ።ከፊሉ ቆስሎ ሲማረክ ቀሪው ሸሽቶ ለማምለጥ ጥረት እያደረገ ይገኛል። ጀግናው ጌትነት መሳፍንት በወደቀበት አጅሬ ከ65 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ70 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። 3ኛ ቀኑን ቀኑን ያስቆጠረው የቀጠናው ፍልሚያ ተሳታፊዎች የራስ አሞራው ውብነህ ፫ኛ ኮር ድብ ጠለምት ቻይና ብርጌድ ጭና አጅሬ ብርጌድ ጭና በአርበኛ መለሰ ተሾመ የሚመራ ብርጌድ ሰ/አምባራስ ድፈን ብርጌድና ባበይ ልጃለም ብርጌድ አያሌው ብሩ አረደጃን ብርጌድን ጨምሮ ነዋሪው ህዝብ የተሳተፈበት ሰፊ ቀጠና የሸፈነ ፍልሚያ  በድምሩ ከ180 በላይ የኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከጥቅም ውጭ ማድረግ የተቻለበት በርካታ የጦር መሳሪያ የተማረከበት ድል ተመዝግቧል። መታሰቢያነቱ በአርበኛ ጌትነት መሳፍንት ስም እንዲሆን ሲሉ ያወጁት ተናዳፊዎች ራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ቀሪውን ጠላት ተከታትለው እየደመሰሱ ይገኛሉ።       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!         አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ          ህዳር 11/2018 ዓ.ም                ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

ግፈኛው የዓብይ ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!!    አፋብኃ በላይ ዕዝ    ደጃዝማች ፬ኛ ኮር   አርበኞች ክ/ጦር ማዕ/አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ እንዝልሽ ቀበሌ ጋብላ ከተማ አቅራቢያ ቻሌ መታኩስ የተሰኜ ልዩ ቦታ ዛሬ ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት 12:00 ሰዓት የዓብይ ፋሽስት ሰራዊት በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።    በርካታ ጠላት በረገፈበት የእንዝልሽ የደፈጣ ኦፕሬሽን የበላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር አርበኞች ክ/ጦር ከአራት ብርጌዶች የተወጣጣ ሰራዊት የድሉ ባለቤት ሲሆን ለጊዜው ቁጥሩ ያልተረጋገጠ በርካታ ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።ከፊሉ በድንጋጤ ጥልቅ ገደል ተንከባሎ ስለገባ የሟቹ እና የቁስለኛው መጠን በቁጥር ለማስቀመጥ ለጊዜው አዳጋች አድርጎታል። በእንዝልሽ ግንባር የተመታው ጠላት ተልዕኮው የከሸፈ ቢሆንም በአምስት አቅጣጫ ተጨማሪ ሰራዊት ገፍቶ በማስገባት ሞራሉን ለማካካስ ሙከራ እያደረገ ይገኛል።      በማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ከማሰሮ ደንብ ከተማ ውጭ በደጃዝማች ኮር ተጠርጎ ሸሽቶ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ነው።                 ህልውናችን በተባበረ ክንድ!!           አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ                 ህዳር 11/2018 ዓ.ም                  ህ/ግንኙነት መምሪያ

ከመምህራን ጋር ዉይይት ተካሄደ!! ‎ ‎የአፋብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ አቸፈር ወንድየ ከመምህራን ጋር ሰፊ ዉይይት ተካህዷል። ‎
+1
ከመምህራን ጋር ዉይይት ተካሄደ!! ‎ ‎የአፋብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ አቸፈር ወንድየ ከመምህራን ጋር ሰፊ ዉይይት ተካህዷል። ‎ በዉይይቱ!! ‎ ማነማነኛዉም መምህራን ራሱን ከማነኛዉም ፓለቲካ እራሱን ነፃ አድርጎ እንዲቀሳቀስና ስለ ትግሉ አጀማመርና ግስጋሴም ሰፋ ያለ ዉይይት ተካህዷል።

በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር አመራሮች ከ24ኛ ክ/ጦር አመራሮች ጋር ያለ ዕረፍት እየሰሩ ይገኛል!! የአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች የ24ኛ ክፍለ ጦር አመራሮችን ስምሪት በመያዝ ቀድሞ የተሰጡ የስራ አቅጣጫዎችን በመገምገም  ድጋፋቸውን እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን በቀድሞው የደባይ ጮቄ ብርጌድ በአሁኑ የደባይ ጮቄ ሻለቃ የኮር ከፍተኛ አመራሮችንና የክ/ጦር አመራሮችን እንኳን ወደ ታሪካዊት የጠላት መጋኛነ የወገን የአማራ መዳኛ የሆነችው ደባይ ጥላት ግን ወረዳ አንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ደማቅ አቀባበል አድርጋለች። በዕለቱም የክብር እንግዳ በመሆን የታደሙት በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የአደረጃጀት ዘርፍ የሆኑት አርበኛ ደርሳችሁ አትንኩት በዝግጅቱ መታደማቸው እንዳስደሰታቸው አውስተው በፋኖ ታሪክ ታላቅ የጀብድ ታሪክ ካላትና ሁሉም የፋኖ ከፍተኛ አመራር በጀግንነት ተጋድሎዋና ቁርጠኝነቷ ሊያዩዋት ሊጎበኞት ከሚፈልጓት ደባይ ጮቄ አንዷ መሆኗን አውስተው ቀጣይ ባለው መዋቅርም ይህንን የታሪክ ተጋድሎዋን እንደምታስቀጥል ያላቸውን ዕምነት አስቀምጠዋል።። በዕለቱም ሌሎቹም የ24ኛ  ክ/ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራሮች ያላቸውን ሃሳብ ተራ በተራ አስቀምጠዋል።በመጨረሻም  የማበረታቻ የሽልማት ስነስርዓት በማካሔድ የዕለቱ ዝግጅት ተቋጭቷል   ከዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ  አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

🔥#ሰበር_ዜና‼️ #ኮሎኔሉን ጨምሮ ሌሎች ምርኮኛ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና #ንፁሀኖች #በድሮን_ጥቃት_ተገደሉ‼️ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ ዙሪያ በፈፀመው ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት በዘመቻ አባ ናደው የተማረከውን የ12ኛ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ #ኮሎኔል-ዘሪሁን_ማሙየን ጨምሮ በርካታ #ንፁሃኖች #ሲሞቱ በርካቶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል:: ፋሽስቱ የብልጸረግና አገዛዝ ትናንትና ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ቡግና ወረዳ ቋሮ 2 ጊዜ፣ ብርኳኳ 1 ጊዜ፣ እና ብርኳ 1 ጊዜ ባጠቃላይ ከምሽት 12:40-5:30 ድረስ አራት ጊዜ የድሮን ጥቃት በመፈፀም በዘመቻ አደም አሊ (አባ ናደው) የተማረከውን ኮሎኔል ዘሪሁን ማሙየ ሌሎች ሶስት አብረውት የነበሩ ምርኮኞችን እና ያደረበትን ቤት ባለቤቶች ሁለቱን ጨምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች በርካታ ንፁሃኖች ሲሞቱ በርካቶች ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል:: ቤትና ንብረት ላይም ከባድ ጉዳትና ውድመት አድርሷል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የተማረኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እጃችን ላይ ያለን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ምርኮኞች ምግብና ውሃ የሚያቀርብላቸውና የሚመግባቸው ፋኖ፣ ጥበቃቸውም ፋኖ፣ የህክምና አገልግሎትም ሆነ ሌሎች ሰብዓዊ አገልግሎቶች የሚሰጣቸው ፋኖ፣ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በቀጣይም ተመሳሳይ የፋሽስቱ አገዝዝ ብልፅግና ጥቃቶች ሊፈፀሙባቸው እንደሚችሉ አለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቅልንና በተለይ ቀይ መስቀል ምርኮኞቹን እንዲረከበን ስንል በድጋሜ መልክታችንን እናስተላልፋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 11/ዐ3/2018 ዓ.ም

የምስራቅ አማራ ኮር 1 ኮር 2 እና የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ራያ ግንባር ላይ ትልቅ ድል አስመዘገቡ:: የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት በራያ ቆቦ በጮቢ ግንባር እና ተኩለሽ ግንባር በበርካታ እግረኛ ሰራዊት በቅርቡ ባስገባቸው ቻይና ሰራሽ ኦራል ላይ በተጠመዱ ሶስት 155 mm መድፎች፣ ቢ ኤም፣ ብረት ለበሶች፣ እና ዙ23 ታግዞ ህዳር 9/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀምሮ እስከ ህዳር 10/2018 ዓ.ም  ምሽት በተጠናቀቀው ተጋድሎ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ አስተናግዶ ወደ መጣበት ተመልሷል:: በተጋድሎው የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሃዶች ሃውጃኖ ክፍለጦር አሳምነው ክፍለጦር 2ኛ እና 5ኛ ሻለቆች እና ከኮር 2 ዲቢና ወርቄ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ በጥምረት ባደረጉት ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ ጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ እና ቀጠናውን በማስከበር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል:: በተጋድሎው ከባድ ሽንፈት የገጠመው የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት የገጠር መንደሮችና ታዳጊ ከተሞች ላይ ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍ በሰው ህይወት ላይ የሞትና የአካል ማጉደል አደጋ ሲያደርስ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል እንስሳቶች ተጨፍጨፈዋል ቤትና ንብረትም አውድሟል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 11/2018 ዓ.ም

የ4ኛ ክፍል ተማሪውዋ በአሸባሪው ሀይል ተደፍራ ተገድለች‼️ ======== 👉ተማሪ ቃልኪዳን አዲሱ ታፈረ የ14 አመት ህጻን ስትሆን የሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ4ኛ ክፍል
የ4ኛ ክፍል ተማሪውዋ በአሸባሪው ሀይል ተደፍራ ተገድለች‼️ ======== 👉ተማሪ ቃልኪዳን አዲሱ ታፈረ የ14 አመት ህጻን ስትሆን  የሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ4ኛ ክፍል ተማሪ ናት። በትናንትናው ዕለት ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ ሱቅ እየሰራች ባለበት ሰአት ለቃለ መጠይቅ ትፈለጊያለሽ በማለት ከምትሰራበት ሱቅ አስወጥቶ ወደ ጫካ ወስዷታል። 👉 አሸባሪው ሀይል ተማሪ ቃልኪዳንን ወደ ጫካ ከወሰዳት በኃላ አሽኳር በር ከተባለ የገጠር ቀበሌ ላይ በቡድን በመድፈር መረጃው እንዳይወጣ  በ3 ጥይት በመምታትና የተለያዬ የሰውነት አካሏን በጩቤ በመውጋት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏታል።      አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ለሟች ቤተሰብ መጽናናቱን ይመኛል‼️             አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!                  ህዳር  ፲፩/፳፻፲፰

አራት ወታደራዊ አዛዦች ከነ ወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪያቸው መደምሰሳቸው ተሰምቷል! 👉በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ላይ ፋኖ ስኬታማ ድሎችን እየተቀዳጀ መሆኑ ታውቋል! 👉በምዕራብ አማራ
አራት ወታደራዊ አዛዦች ከነ ወታደራዊ ፓትሮል ተሽከርካሪያቸው መደምሰሳቸው ተሰምቷል! 👉በምስራቅ አማራ ቀጠና ምዕራብ ወረዳዎች ላይ ፋኖ ስኬታማ ድሎችን እየተቀዳጀ መሆኑ ታውቋል! 👉በምዕራብ አማራ ቀጠና ጊዜያዊ የመንግስት መዋቅር ዝርጋታው በታሰበለት ጊዜና ሁኔታ እየተፈፀመ ነው ተብሏል! 👉አገዛዙ በደቡብ አማራ ቀጠና የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ትምህርት ቤትንና ሌሎች የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን እያወደመ መሆኑ ተሰምቷል! 👉በሰሜን አማራ ቀጠና ፋኖ በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ትላልቅ ድሎችን እየተቀዳጀ ነው! አገዛዙ አለኝ የሚለው ወታደራዊ ኃይል በተሰጠው የግዳጅ ቀጠና በገፍ እየወጣ መጥፋቱን ተያይዞታል። ወታደሮቹ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እየወጡ እጃቸውን ለፋኖ መስጠታቸውን ቀጥለዋል!

ጠላቶቻችንን አምርሮ መጥላት ብቻ ሳይሆን ምህረት የሌለው እርምጃ መውሰድ የድል ቀንን ያቀርባል‼️ በአብዮቱ መጀመሪያ ሰሞን "የምንታገለው ስርዓቱን እንጂ ወንድሞቻችንን አይደለም" ብለን በህይወት እን
ጠላቶቻችንን አምርሮ መጥላት ብቻ ሳይሆን ምህረት የሌለው እርምጃ መውሰድ የድል ቀንን ያቀርባል‼️ በአብዮቱ መጀመሪያ ሰሞን "የምንታገለው ስርዓቱን እንጂ ወንድሞቻችንን አይደለም" ብለን በህይወት እንዲኖሩ ፈቅደን ካድሬ፣ሚሊሻ፣እና ፖሊስን መተዋችን ያስከፈለንን ዋጋ መዘንጋት የለብንም!! መልካም ምሽት!

"ስም መስጠት፣ማጠልሸት እና ማሰይጠን ከዓላማችን አያስቆመንም" " በአበው ብሂል ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች ይጓዛሉ" የሚለው አባባል ለትግላችንና ለሰራዊታችን ስንቅ ከሆነ ቆይቷል። የፋሺስቱ አብይ አህመድ መንግስት እና የፀረ አማራ ሃይሎች ጥምረት በሆነው ሚዲያቸው ያልተተቼ የፋኖ አመራር እና ታጋይ የለም። የተቀናጀው ዘመቻ የጠላት የተለመደ አጀንዳ ነው። በከሸፈ ወሬ የሚደናገጥ አመራር እና ሰራዊት ከቶ አልፈጠርንም። እንደ ቀጠና ምስጉንና ጀግና ሰራዊትም በመፍጠራችን ኩራት ይሰማናል። በተለይም የምስራቅ አማራ ቀጠናን የፋኖ ሰራዊት እና አመራር በተደራጀ መንገድ በመንጋ አዝማቾች እና በመደበኛ የአገዛዙ ሚዲያዎች ሳይቀር ከፍተኛ ስም ማጥፋት፣ማጠልሸት፣ማሰይጠን እና ፍረጃ ተካሄዶብናል። እኛ ግን ዓላማችንን ዳር ለማድረሰ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክረን እንቀጥላለን። እኛም ሰራዊታችንም የተግባር እና የድርጊት ፈፃሚው አማራ ልጆች መሆናችንን በክንዳችን እናሰያለን!! ነገም ወደ ፊትም በተግባር ስራችን እና በዓላማችን የተሻለውን እያደረግን ወደ ፊትም የምንገሰግስ ይሆናል። ከፋሺስቱ ሃይሎች ጀርባ በትግላችንና በድርጅታችን ውስጥ የተደበቁ ምስለ አማራዎች እና ሸሪኮቻቼው በምስራቅ አማራ ቀጠና ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ እና ሰራዊት ላይ ስንጥቅ ለመፍጠር እዚህም እዛም የሚወራጩ ደቂቀ ብልፅግናዎች ብዙ ሲያወሩ እና አድስ ትርክት ለመፍጠር የሚያደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም። ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የመላው አማራን ትግል ተሸክሞ በርካታ ተግዳሮቶችን እያለፈ የመጣ ድርጅት እንጅ ምስለ አማራዎች እና የጠላት ተልዕኮ ተሺክመው ሜዳ ላይ እንደሚያቀርሹት ቀላል አይደለም። ትግላችን ደም የተገበረበት ነው ስንል ስህተትን እንደ ስራ እየቆጠሩ እና በደም የፀናውን ድርጅት በሃሰት እየከሰሱ ከደሙ ንፁህ ነኝ በማለት በአደናጋሪ የሚዲያ ሰዎች ትርክት በመፍጠር ተጨማሪ ቀውስ ፈጥረው የትግል አረም ለሆኑት ጲላጦሶች ነው። ስለሆነም በምስራቅ አማራ ቀጠና ወሎ/ቤተ ዐማራ/ ላይ ከጠላት ጋር እየሰሩ ወሎን ከመሰረታዊ የትግሉ አምበልነት ለማውረድ የሚደረገውን ፀረ ፋኖ እንቅስቃሴ በቀላሉ የምንመለከተው እንዳልሆነ ግን ሊታወቅ ይገባል። እኛ የአይበገሬ አማራዎች ስብስብ ነን። በትንኝ ንክሻ የምንጮህም አይደለንም። ሁሉንም መከራ ተሺክመን ለዓላማችን እና ለህዝባችን ታምነን እንሰዋለን። ጥቂቶች ግን ከጠላት እና ከጠላት ጀርባ በመሆን የከፈልነውን መስዋአትነት ለማሳነስ የሚደረጉትን ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በመርህ፣በተቋማዊ እና በድርጅታዊ መርሆች እንታገላቸዋለን!! የተልከስካሹች አጀንዳም የሚያስደነግጠን አይደለም ነገር ግን በስራዊታችንና በአማራዊ ስነ ልቦናችን ለሚመጡ ሁሉ ደግሞ ትግስት የለንም። የሚያስፈራን ነገር ቢኖር ከዓላማችን ማነስ ብቻ ነው። ለህሌናችን እና ለዓላማችን ታምነን በትግሉ ስበት ላይ እንደ ንስር የምንበር የአማራ ብሔራዊ ጀግና የጀ/አሳምነው ልጆች ነን መሆናችንንም ለአፍታ አንጠራጠርም🙏 ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ በ6 ኮሮች አሳባሳቢነት የተዋቀረ በአይበገሬው ዋርካው ምሬ ወዳጆ እየተመራ በጠላት ሰራዊት ላይ ድል እየተቀዳጀ   ነገም ወደፊትም የታላቁ አማራ ህዝብ ተቋም ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል። ሰነፎች፣ፈሪዎች እና የፓለቲካ ሙሰኞች 7/24 ስለ ምኒልክ ዕዝ የሚያወሩት በጠንካራ አማራዊ ጥንካሬያችን እንጅ በተለየ መልኩ እንዳልሆነም እንገነዘባለን። ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አደም አሊ /አባ ናደው/ያደረገው ተጋድሎ የጠንካራ ስራችን መገለጫ መሆኑም የሚታወስ ነው። ስለሆነም "ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች ይጓዛሉ" ስንል ጀብደኛው ዕዛችን በፋሺስቱ ሰራዊት እና በአገዛዙ ላይ የሚያደርገውን ጠንካራ አማራዊ ተጋድሎ አጠናክሮ ለድል እንደሚበቃም እርግጠኞች ስለሆን ብቻ ነው። የጠላት 3 ዕዞችን የተሸከመ ሰራዊት እና አመራር ለወሬኞች እና ለምስለ አማራዎች ጩኸት ጆሮም የምንሰጥ አንሆንም። ተግባር ብቻ🙏🙏 መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል። ስንከባበር እና ስንደማመጥ ከባዱ ቀላል ይሆናል። ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ ህዳር 11-03-2018 በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 55ክ/ጦር የአቸፈር ወንድየ አናብስቶች ጡት ቆራጩን የብልፅግና ቡድን ሲገርፉት ዉለዋል። ‎ ‎  ትናንት 10-03-2018ዓ.ም ማታ ላይ የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶችን ለማፈን ከሊበን-ወደ ይስማላ በማጠራቀም ጉዞዉን ወደ በለን አቅጣጫ ጉዞ አድርጎ ጉዞዉ ከሽፎበታል። ‎ ‎ ጉዞዉ የሸከፈበት ዘራፊና አዉዳሚ ስርዓት የግለሰቦችን ቤት እየገባ ዘርፏል፤የተጠገኑ ት/ት ቤቶችን አዉድሟል። ‎  ጉዞዉን ያከሸፉት የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶች በዛሬዉኑ ዕለት ማለትም በ11-03-2018ዓ.ም በለን ላይ ይህን ጡት ቆራጭ አረመኔ ስርዓት እቅዱን አክሽፈዉ ስስ ብልቱን ለይተዉ ከፀዋቱ 3:00ጀምሮ  እስከ ቀኑ 6:00 ዉግያዉ ተካህዷል። ‎  ምቱ የከበደዉ የጁላ ሰራዊት የተመታዉ ተመቶ ቀሪዉ እግር አዉጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ይስማላ ከተማ ተመልሷል። ‎  በዉግያዉም በዉል ያልታወቀ የጁላ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ተሸኝቷል። ‎  አንድ ሻንበል መሪና ብሬን ተኳሾችም ተሰናብተዋል። ‎ ‎አፋብኃ ምዕራብ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ክ/ጦር አቸፈር ወንድየ💪💪💪 ‎

በዘመቻ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ከ180 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደረገ! ለሦስተኛ ቀናት በዘለቀው በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ስም በታወጀው ዘመቻ፡ የራስ አሞራው ውብነህ እ
በዘመቻ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ከ180  በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደረገ!   ለሦስተኛ ቀናት በዘለቀው በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ስም በታወጀው ዘመቻ፡ የራስ አሞራው ውብነህ እና የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች  በተለያዩ ግንባሮች አስደናቂ ድል መጎናፀፋቸውን መረብ ሚዲያ ከበላይ ዘለቀ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል። በሰሜን ጎንደር ቀጠና በ4 አቅጣጫ ወደ ዳባት ወረዳ አጅሬ ጃኖራ ያመራው የጡት ቆራጩና ሴት ደፋሪው የዐብይ ግሪሳ በራስ አሞራው 3ኛ ኮር ሰራዊት በቆላማው የወገራ ጠገዴና አርማጭሆ እንዲሁም ዛሪማና ቦዛ አዋሳኝ መሬቶች እንደበረዶ ቀልጦ ቀርቷል። ተግተልቶሎ የመጣው ጠላት አራቡር ቀበሌ አቦ ገዳም፣ሞርጠጭ ፀበልና ወይራ ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ሲደመሰስ 23 ቁስለኛ ሁኗል።ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ተደርጓል።ቀሪው ወደ ዳባት ፈርጥጧል። በደባርቅ አቅራቢያ ጥራይና የተገረፈው የጠላት ኃይል ለጊዜው በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።መቋቋም ስላልቻለም ሸሽቶ ደባርቅ ተመልሷል። አጅሬ ወንበርየ ሚካኤል፣አይረፈዳ ማርያም እና መድሃኒያለም እና ቻይና ካምፕ እና ተንሳየ በተሰኙ ልዩ ቦታዎች በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች የጌትነት መሳፍንት ወንድሞች የዓብይን ሰራዊት በእሳት ቆልተውታል። ጀግናው ጌትነት መሳፍንት በወደቀበት አጅሬ ከ65 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ70 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቀጠናው ፍልሚያ በድምሩ ከ180 በላይ የኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ መቻሉን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።