en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 378
Subscribers
-424 hours
+2487 days
+1 44230 days
Posts Archive
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር 55ክ/ጦር የአቸፈር ወንድየ አናብስቶች ጡት ቆራጩን የብልፅግና ቡድን ሲገርፉት ዉለዋል። ‎ ‎  ትናንት 10-03-2018ዓ.ም ማታ ላይ የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶችን ለማፈን ከሊበን-ወደ ይስማላ በማጠራቀም ጉዞዉን ወደ በለን አቅጣጫ ጉዞ አድርጎ ጉዞዉ ከሽፎበታል። ‎ ‎ ጉዞዉ የሸከፈበት ዘራፊና አዉዳሚ ስርዓት የግለሰቦችን ቤት እየገባ ዘርፏል፤የተጠገኑ ት/ት ቤቶችን አዉድሟል። ‎  ጉዞዉን ያከሸፉት የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶች በዛሬዉኑ ዕለት ማለትም በ11-03-2018ዓ.ም በለን ላይ ይህን ጡት ቆራጭ አረመኔ ስርዓት እቅዱን አክሽፈዉ ስስ ብልቱን ለይተዉ ከፀዋቱ 3:00ጀምሮ  እስከ ቀኑ 6:00 ዉግያዉ ተካህዷል። ‎  ምቱ የከበደዉ የጁላ ሰራዊት የተመታዉ ተመቶ ቀሪዉ እግር አዉጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ይስማላ ከተማ ተመልሷል። ‎  በዉግያዉም በዉል ያልታወቀ የጁላ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ተሸኝቷል። ‎  አንድ ሻንበል መሪና ብሬን ተኳሾችም ተሰናብተዋል። ‎ ‎አፋብኃ ምዕራብ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ክ/ጦር አቸፈር ወንድየ💪💪💪 ‎

በዘመቻ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ከ180 በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደረገ! ለሦስተኛ ቀናት በዘለቀው በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ስም በታወጀው ዘመቻ፡ የራስ አሞራው ውብነህ እ
በዘመቻ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ከ180  በላይ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደረገ!   ለሦስተኛ ቀናት በዘለቀው በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ስም በታወጀው ዘመቻ፡ የራስ አሞራው ውብነህ እና የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች  በተለያዩ ግንባሮች አስደናቂ ድል መጎናፀፋቸውን መረብ ሚዲያ ከበላይ ዘለቀ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል። በሰሜን ጎንደር ቀጠና በ4 አቅጣጫ ወደ ዳባት ወረዳ አጅሬ ጃኖራ ያመራው የጡት ቆራጩና ሴት ደፋሪው የዐብይ ግሪሳ በራስ አሞራው 3ኛ ኮር ሰራዊት በቆላማው የወገራ ጠገዴና አርማጭሆ እንዲሁም ዛሪማና ቦዛ አዋሳኝ መሬቶች እንደበረዶ ቀልጦ ቀርቷል። ተግተልቶሎ የመጣው ጠላት አራቡር ቀበሌ አቦ ገዳም፣ሞርጠጭ ፀበልና ወይራ ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ሲደመሰስ 23 ቁስለኛ ሁኗል።ሁለት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ከጥቅም ውጭ ተደርጓል።ቀሪው ወደ ዳባት ፈርጥጧል። በደባርቅ አቅራቢያ ጥራይና የተገረፈው የጠላት ኃይል ለጊዜው በውል ቁጥሩ ያልታወቀ ጠላት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።መቋቋም ስላልቻለም ሸሽቶ ደባርቅ ተመልሷል። አጅሬ ወንበርየ ሚካኤል፣አይረፈዳ ማርያም እና መድሃኒያለም እና ቻይና ካምፕ እና ተንሳየ በተሰኙ ልዩ ቦታዎች በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአባ ድፈን መሳፍንት ልጆች የጌትነት መሳፍንት ወንድሞች የዓብይን ሰራዊት በእሳት ቆልተውታል። ጀግናው ጌትነት መሳፍንት በወደቀበት አጅሬ ከ65 በላይ ጠላት ሲደመሰስ ከ70 በላይ ቁስለኛ ሁኗል። ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የቀጠናው ፍልሚያ በድምሩ ከ180 በላይ የኦህዴድ ብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ማድረግ መቻሉን የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

ሰበር ዜና አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝና አፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጁ። የጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት ከአጣዬ(ኤፌሶን) ከተማ ወጣ  ብላ በምትገኘው በርግቢ ቀበሌ ካንፕ አድርጎ በመቀመጥ ወንዶችን እየደበደበና አስሮ ገንዘብ እየጠየቀ ሴቶችን ደግሞ አስገድዶ እየደፈር እንደሆን በቅርቡ በዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል። ሆኖም በርግቢ መሸጎ ለወራት ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የቆየው 103ኛ አየር ወለድ ክፍለጦር ላይ ጀግናው የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እና ሽዋ ጠቅላይ ዕዝ ጥምር ሰራዊት በተቀናጀ የጋራ ተጋድሎ በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት ድባቅ ተመታ! በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር እና የ7ለ70 ክፍለጦር እንዲሁም የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከአፄ አምደ ጽዮን ኮር ራምቦ ክፍለጦር እና ሰባት ላእሰባ ክፍለጦር በተውጣጡ ሻለቆች ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ጀምሮ በወረዳው ላይ በአይነቱ ለየት ያለ በአራት አቅጣጫ በተካሔደው የተቀናጀ  ኦፕሪሽን አውደ ውጊያ የአገዛዙ ሰራዊት ክፉኛ ተመታ። እልህ አስጨራሽ በሆነው አውደ ውጊያ ፣በአመጃ  ገብርኤል፣ በበርግቢ ውሃ ታንከር እና በቴሌ ታወር አካባቢዎችን የሸፈነ ታላቅ ተጋድሎ የተደረገ ሲሆን ሰራዊታችን በተቀናጀ አንድነት የጠላትን አከርካሪ መስበር ተችሏል። በአውደ ውጊያው የአማራ ፋኖ ትግል የአንድነት ሃይል የታየበት የአፄ ዘረ ያዕቆብ ፩ ኮር የ7ለ70 ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ በሳራምባ ቴሌ ታወር፣ በካራ ለጎማ ፤ በተረተር አካባቢዎች እንዲሁም የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኑአምላክ ክፍለ ጦር ለማ ሻለቃና አይሻ ሻለቃ በአርብ ገብያና አጨብጭብ ተራራን በመያዝ የተቀናጀ አውደ ውጊያ ሽዋ ጠቅላይ ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦር ሞገሴ 1ኛ ሻለቃ እና ማንበግር 3ኛ ሻለቃ፤የሰባት ለሰባ የናሁሰናይ የሲኖ ሻለቃና አስማረ ዳኜ ሻለቃ ባደረጉት  ትንቅንቅ በርካታ የ103ኛ የአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አባላት ላይ የሰራዊት እና ቁሳዊ ጉዳት የደረሱበት ሲሆን፣ በቀጠናው የሚገኘው የጦር ወንጀለኛው የብልፅግናው ሰራዊት የየአሳምነው ክንድ ነበልባል ልጆች መቋቋም ሲያቅተው ከከሚሴ ከተማ ተጨማሪ ሃይል ቢያስገባም ከደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ ሊታደገው አልቻለም። በከሰያት አመጃ ገብርኤል ተራራው ላይ በሰፈረው የወራሪው ሰራዊት ላይ የራንቦ ክፍለጦር ሞገሴ 1ኛ ሻለቃ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ የጠላት ሃይልን በመረፍረፍ የክብር መስዋዕትነት የተከፈለበት በተናበበ የሻለቆች አንድነት ስኬታማ ውጤት ተጎናፅፈዋል። ከወትሮው ለያት ባለ መልኩ የአንድነት ድባብ የታየበት በፋኖ ሰራዊት በተናበበ የጥምር ሃይል በአገዛዙ ወታደሮች ላይ የጋራ ኦፕሬሽን ጠላት በሶስት አምቡ ሙትና ቁስለኛውን በመያዝ ወደ አጣዬ ከተማ እንዲመለስ የተደረገም ሲሆን ፣ የአጣዬ እና የከሚሴ ሆስፒታሎች ከቀላል እስከ ከባድ የ103ኛ የአየር ወለድ ክፍለጦር ቁስለኞች አባላቱ መሙሏታቸው  ተረጋግጧል። መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው።               " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል። ‎       ህዳር 07/ዐ3/2018 ዓ.ም

የአረመኔው ስርዓት በገዳም ልጃሞር ቀበሌ የአርሶ አደሮችን ሰብል ቃጠሎ እና ዘረፋ ፈጸመ... (ሕዳር 11/2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር) በሽንፈት ጎዳ
የአረመኔው ስርዓት በገዳም ልጃሞር ቀበሌ የአርሶ አደሮችን ሰብል ቃጠሎ እና ዘረፋ ፈጸመ... (ሕዳር 11/2018 ዓ.ም አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር) በሽንፈት ጎዳና ላይ የሚገኘው በቁጭ ከተማ መሽጎ የተቀመጠው ወራሪው ሰራዊት በትላንትናው ዕለት ማለትም ሕዳር 10 /2018 ዓ.ም ገዳም ልጃሞር ቀበሌ በመግባት የአርሶ አደሮችን ጤፍ ዘርፈው ሌላውን መሸከም ሲያቅታቸው ከ30 ኩንታል በላይ አቃጥለው እና በተጨማሪ ሶስት የቁም ከብቶችን በመግደል በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል። ከተዘረፈባቸው ግለሰቦች መካከል አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አለሰው ተፈሪ ፣አቶ ብርሄ ተገኘ፣ሙሌ ገላው ጤፍ እና የቤት እቃዎችን የተዘረፉ ሲሆን፣ የአቶ ድንበሩ አዲስን ሶስት የቁም ከብቶችን በጥይት በመግደል በአርሶ አደሮች ላይ መጠነ ሰፊ ዘረፋ መፈጸሙን የአካባቢው ፋኖዎች መረጃው አድርሰዋል። #ድል_ለዐማራ_ህዝብ ❗❗ ➤ዘገባውን ያደረስኋችሁ ጋዜጠኛ አይቸው ጌታሰው🙏🙏

"ስም መስጠት፣ማጠልሸት እና ማሰይጠን ከዓላማችን አያስቆመንም" " በአበው ብሂል ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች ይጓዛሉ" የሚለው አባባል ለትግላችንና ለሰራዊታችን ስንቅ ከሆነ ቆይቷል። የፋሺስቱ አብይ አህመድ መንግስት እና የፀረ አማራ ሃይሎች ጥምረት በሆነው ሚዲያቸው ያልተተቼ የፋኖ አመራር እና ታጋይ የለም። የተቀናጀው ዘመቻ የጠላት የተለመደ አጀንዳ ነው። በከሸፈ ወሬ የሚደናገጥ አመራር እና ሰራዊት ከቶ አልፈጠርንም። እንደ ቀጠና ምስጉንና ጀግና ሰራዊትም በመፍጠራችን ኩራት ይሰማናል። በተለይም የምስራቅ አማራ ቀጠናን የፋኖ ሰራዊት እና አመራር በተደራጀ መንገድ በመንጋ አዝማቾች እና በመደበኛ የአገዛዙ ሚዲያዎች ሳይቀር ከፍተኛ ስም ማጥፋት፣ማጠልሸት፣ማሰይጠን እና ፍረጃ ተካሄዶብናል። እኛ ግን ዓላማችንን ዳር ለማድረሰ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክረን እንቀጥላለን። እኛም ሰራዊታችንም የተግባር እና የድርጊት ፈፃሚው አማራ ልጆች መሆናችንን በክንዳችን እናሰያለን!! ነገም ወደ ፊትም በተግባር ስራችን እና በዓላማችን የተሻለውን እያደረግን ወደ ፊትም የምንገሰግስ ይሆናል። ከፋሺስቱ ሃይሎች ጀርባ በትግላችንና በድርጅታችን ውስጥ የተደበቁ ምስለ አማራዎች እና ሸሪኮቻቼው በምስራቅ አማራ ቀጠና ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ እና ሰራዊት ላይ ስንጥቅ ለመፍጠር እዚህም እዛም የሚወራጩ ደቂቀ ብልፅግናዎች ብዙ ሲያወሩ እና አድስ ትርክት ለመፍጠር የሚያደርጉት ሙከራ ተቀባይነት የለውም። ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ የመላው አማራን ትግል ተሸክሞ በርካታ ተግዳሮቶችን እያለፈ የመጣ ድርጅት እንጅ ምስለ አማራዎች እና የጠላት ተልዕኮ ተሺክመው ሜዳ ላይ እንደሚያቀርሹት ቀላል አይደለም። ትግላችን ደም የተገበረበት ነው ስንል ስህተትን እንደ ስራ እየቆጠሩ እና በደም የፀናውን ድርጅት በሃሰት እየከሰሱ ከደሙ ንፁህ ነኝ በማለት በአደናጋሪ የሚዲያ ሰዎች ትርክት በመፍጠር ተጨማሪ ቀውስ ፈጥረው የትግል አረም ለሆኑት ጲላጦሶች ነው። ስለሆነም በምስራቅ አማራ ቀጠና ወሎ/ቤተ ዐማራ/ ላይ ከጠላት ጋር እየሰሩ ወሎን ከመሰረታዊ የትግሉ አምበልነት ለማውረድ የሚደረገውን ፀረ ፋኖ እንቅስቃሴ በቀላሉ የምንመለከተው እንዳልሆነ ግን ሊታወቅ ይገባል። እኛ የአይበገሬ አማራዎች ስብስብ ነን። በትንኝ ንክሻ የምንጮህም አይደለንም። ሁሉንም መከራ ተሺክመን ለዓላማችን እና ለህዝባችን ታምነን እንሰዋለን። ጥቂቶች ግን ከጠላት እና ከጠላት ጀርባ በመሆን የከፈልነውን መስዋአትነት ለማሳነስ የሚደረጉትን ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በመርህ፣በተቋማዊ እና በድርጅታዊ መርሆች እንታገላቸዋለን!! የተልከስካሹች አጀንዳም የሚያስደነግጠን አይደለም ነገር ግን በስራዊታችንና በአማራዊ ስነ ልቦናችን ለሚመጡ ሁሉ ደግሞ ትግስት የለንም። የሚያስፈራን ነገር ቢኖር ከዓላማችን ማነስ ብቻ ነው። ለህሌናችን እና ለዓላማችን ታምነን በትግሉ ስበት ላይ እንደ ንስር የምንበር የአማራ ብሔራዊ ጀግና የጀ/አሳምነው ልጆች ነን መሆናችንንም ለአፍታ አንጠራጠርም🙏 ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ በ6 ኮሮች አሳባሳቢነት የተዋቀረ በአይበገሬው ዋርካው ምሬ ወዳጆ እየተመራ በጠላት ሰራዊት ላይ ድል እየተቀዳጀ   ነገም ወደፊትም የታላቁ አማራ ህዝብ ተቋም ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል። ሰነፎች፣ፈሪዎች እና የፓለቲካ ሙሰኞች 7/24 ስለ ምኒልክ ዕዝ የሚያወሩት በጠንካራ አማራዊ ጥንካሬያችን እንጅ በተለየ መልኩ እንዳልሆነም እንገነዘባለን። ምኒልክ ዕዝ በዘመቻ አደም አሊ /አባ ናደው/ያደረገው ተጋድሎ የጠንካራ ስራችን መገለጫ መሆኑም የሚታወስ ነው። ስለሆነም "ውሾች ይጮሃሉ ግመሎች ይጓዛሉ" ስንል ጀብደኛው ዕዛችን በፋሺስቱ ሰራዊት እና በአገዛዙ ላይ የሚያደርገውን ጠንካራ አማራዊ ተጋድሎ አጠናክሮ ለድል እንደሚበቃም እርግጠኞች ስለሆን ብቻ ነው። የጠላት 3 ዕዞችን የተሸከመ ሰራዊት እና አመራር ለወሬኞች እና ለምስለ አማራዎች ጩኸት ጆሮም የምንሰጥ አንሆንም። ተግባር ብቻ🙏🙏 መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል። ስንከባበር እና ስንደማመጥ ከባዱ ቀላል ይሆናል። ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ ህዳር 11-03-2018

በጦርነት ቀጠናዎች የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት በሕግም በሞራልም የሚያስጠይቅ ነው ሲል እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል። እናት ፓርቲ ቢቢሲ አማርኛው ዝግጅት እ.አ.አ ኖቬምበር 19 ቀን 2025 ጉዳት የደረሰባቸው እማኞችን በማቅረብ ዘገባ ሠርቶ ባቀረበው ላይ ነው መግለጫ የሰጠው። በአማራ ክልል ውስጥ በጦርነቱ ኹለት ዓመታት በሺዎች በሚቆጠሩ ሴት ሕጻናትን ጨምሮ 65 ዓመት እስከኾናቸው እናቶቻች ላይ ሲፈጸም የቆየውን ልብ ሰባሪ የኾነ ወሲባዊ ጥቃት እንዲኹም ዘግናኝ ድብደባና የሥነ ልቡና ጉዳት ተጠቂዎች ሕይወት ላይ ያጠነጠነ ዘገባ አንብበነዋል ሲል ነው እናት ፓርቲ የገለጸው፡፡ ከሰሜኑ በትግራይ ኃይሎችና በፌደራል መንግሥት መካከል በነበረው ጦርነት ጀምሮ መረጃው ይደርሰን ስለነበር ፓርቲያችን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እየተከታተለ ድምጽ ከማሰማት ቦዝኖ አያውቅም፡፡ በወቅቱም ይኽ አጸያፊ ተግባር በገለልተኛ አካል ተጣርቶ አጥፊዎቹ በጦር ወንጀል እንዲጠየቁ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል ሰሚ ባያገኝም ሲል ጨምሮ ገልጿል ፓርቲው፡፡ እንዲኹ ያለ ሃይባይ ግፉ ቀጥሎ በዚኽ ደረጃ ጭካኔውና ቁጥሩ በዝቶ እጅግ አሳዛኝ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ድርጊቱ በአገራችን እየተካሄደ ያለው ዘር ፍጅት ዘርፈ ብዙና መዋቅራዊ መኾኑን እንደማሳያ መጠቀስ የሚችል ነው፡፡ ከተለያዩ ታማኝ ምንጮች እንደምንሰማው አኹንም ቁጥሩ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የታፈኑ ድምጾች እንዳሉ ነው ብሏል እናት ፓርቲ፡፡ እናት ፓርቲም፤ ሰብዓዊ መብት ላይ የሚሠሩ ሀገር በቀልና ዓለማቀፍ ተቋማት ድርጊቱን በመኮነን በገለልተኛ አካል እንዲጣራና ጥፋተኞች ለሕግ እንዲቀርቡ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡  እንዲሁም ትኩረታቸውን ሴቶች ላይ አድርገው የሚሰሩ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልኾኑ ተቋማት በጦርነት ቀጠና የሚደርሰውን እጅግ አጸያፊ ጾታዊ ጥቃት ከበዓል ማድመቂያና ፖለቲካ ቅስቀሳ ባለፈ ስቃያቸውን የሚያቀል ጥረትና መፍትሔ እንዲያመጡና ድርጊቱን እንዲያወግዙ እንጠይቃለን ሲል ነው አገዛዙን የጠየቀው፡፡ በመጨረሻም ፓርቲው ለሕዝባችን ድምጽ መኾኑን እንደሚቀጥል እየገለጸ በዚኽ ፀያፍ ድርጊት የተሳተፉ አካላትን ነውር በጽኑ ያወግዛል፡፡ ጥቃቱ ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ፈጣን ሥነልቡናዊና አካላዊ ማገገምን  እየተመኘ ከጎናቸው እንደሚቆምም ቃል ይገባል ነው ያለው፡፡

መነሻውን ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያናና ሲቡ ስሬ ወረዳዎች ያደረገው የአገዛዙ ሰራዊት በ22መኪኖች በመጫን የአማራ ፋኖ በወለጋ ይገኝበታል ወደተባለው አቤደንጎሮ ወረዳ ውባንጭ ቀበሌ በቀን 08/2018ዓ.ም አመሻሹን ጨለማን ተገን በማድረግ ኔትወርክ በማጥፍት ለከበባ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ሰራዊት ትናንትና ጧት ማለትም ህዳር 09/2018ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወለጋ አካል የሆነው ጽናት ክ/ር ላይ በአምስት አቅጣጫ ሀይሉን አሰልፎ በከባባድ መሳርያ የታገዘ ከፍተኛ ጦርነት ቢከፍትም በአምስት አቅጣጫ የተከፈተባቸውን ከባድ ጦርነት በድርጅቱ ወታደራዊ አዛዥ በፋኖ አደም ተፈራ እዬተመሩ በደቂቃዎች ውስጥ አሰፍስፎ የቀረበውን የአገዛዙ ሰራዊት በመልሶ ማጥቃት ድምጥማጩን አጥፍተው የያዘውን ከነፍስ ወከፍ እስከ ቡድን መሳርያ ቀምተው አስክሬኑን እያስረከረከ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል። በዝህ የተደናገጡት ከፍተኛ የመከላከያና የዞን አመራሮች ወዲያውኑ ዙ23ን ጨሞሮ ከባባድ መሳርያ የያዘ ሰራዊት ከአቤደንጎሮ ወረዳ ከቱሉ ዋዩና ከቱሉ ጋና ከተሞች በአስቼኳይ እንዲጨሙር አደረጉ አሁንም ከስዓት በኋላ እንደገና አገርሽቶ ጦርነቱ ተጀመረ አሁንም የአደም ተፈራ የእጅ ስሬት የሆነችው ጽናት ክ/ር እስከ አፍንጫው ታጥቆ በትዕቢት ተወጥሮ የገባውን የአገዛዙ ሰራዊት አንገት ለአንገት ተናንቀው እያስጎሩት በነበረበት ስዓት ሌለኛ የአማራ ፋኖ በወለጋ አካል የሆነው ጌጤ ግርማ መብረቁ ክፍለ ጦር በአርበኛ አለፈ እዬተመራ ድንገት ከተፍ ብሎ ቆረጣ በመግባት 17ቱን የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ወዲያውኑ ወደማይመለሱበት በመሸኘት አስክሬናቸውን እያዝረከረኩ ወደ ኋላ እዲያፈገፍጉ በማድረግ ጽናት ክፍለ ጦር ላይ ያንዣበበውን የጥላት ሀይል አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳርያ በመቀበል በአንጻሩም ቢሆን እንዲያፈገፍጉና አሁንም እንደለመዱት ለአመራሮቻቸው እዬደወሉ እባካቹህ ድረሱልን የሚል የስቃይ ድምጽ እንዲያሰሙ ያደረጓቸው ሲሆን አመሻሹ ላይም ለሦስተኛ ግዜ በከጉዳያ ቢላ ወረዳ ከሉጎ ከተማ ተጨማሪ ሀይል እንዲገባ ተደርጎ ጦርነቱን ጨለማ ገላግሎታል። በአሁኑ ስዓትም ከፍተኛ ምትን ያስተናገደው የአገዛዙ ሰራዊት አስክሬኑንና ቁስለኛውን ሰብስቦ ምሽግ ውስጥ ተጨማሪ ሀይል እዬጠበቀ ይገኛል። ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ‼ ድል የጭቁን ህዝቦች ተስፋ ለሆነው ፋኖ‼ ህዳር 10/2018ዓ.ም ፋኖ ዳዊት አማረ የአማራ ፋኖ በወለጋ ህዝብ ግንኙነት መምርያ ክፍል ሀላፊ

ለጎንጅ ቆለላ ወረዳና አካባቢው ኗሪዎች ​ከሊዝ ጫራታ  ጋር በተያያዘ የተሰጠ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንደሚታወቀው አረመኔው የአብይ አህመድ ሰራዊት የአማራን ህዝብ አጠቃላይ በማህበራዊ፣ፓለቲካዊ ና ኢኮኖሚያዊ ጫና በማሳደር አማራን ዳግም እንዳይነሳ ለመቅበር ከአብራካችን በወጡ ሆዳም ካድሬዎች አስፈፃሚነት ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ሰሞኑን አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አጠፋለሁ ብሎ  የጡት ቆራጩ ስርዓት ያወጀውን ጦርነት በኢኮኖሚ ለመደገፍ የጎንጅ ቆለላ ወረዳ አ/አለም መሪ መዘጋጃ ቤት በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሊዝ መሬቶችን አጫርቶ ለመሸጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም:- 1ኛ ማንኛውም ተጫራች እነዚህን መሬቶች ተጫርቶ የሚገዛ ካለ ከአገዛዙ ጎን በመቆም ና በተዘዋዋሪ ለአገዛዙ የጦር መሳሪያ በማቅረብ በሁለት መንገድ ተጠያቂ እንደሚሆን እንዲያውቀው ማስጠንቀቅ እንፈልጋለን። 2ኛ   ይህንን የሊዝ መሬት የገዛ ሰው  ፋኖ ወረዳውን በተቆጣጠረ ስዓት መሬቱን እንደማያገኜው ወይም እንደሚነጠቅ አውቆ ከጫራታ መታቀብ እንዳለበት እያሳወቅን ይህንን የወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ማስጠንቀቂያ በቸለልተኝነት በማየት በዚህ ድርጊት የተሳተፈ ማንኛውም ባለሃብት ላይ ለሚወሰደው ርምጃ ኃላፊነት ራሱ የሚወስድ ይሆናል። የ102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ጎንጅ ቆለላ ወረዳ  የመንግስት አስተዳደር ኮምኒኬሽን ክፍል         ህዳር 11/2018 ዓ/ም

የአደረጃጀት ዜና! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሁለት ግዙፍ የ11ኛ እና የ22ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቀቀ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና
+4
የአደረጃጀት ዜና! በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ102ኛ ኮር ሁለት ግዙፍ የ11ኛ  እና የ22ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቀቀ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ተግባር  በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ። በዛሬው ዕለት የተጠናቀቁት ሁለቱ ግዙፍ ክፍለጦሮች  በአምስት  አምስት ውህድ ሻለቃ የተዋቀሩ ሲሆን  ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በሻለቃ የኔዓለም ዘለቀ፣በ50 አለቃ ታየ ብርሐኑ፣በፋኖ እስቲበል አለሙ፣ፋኖ እሸቱ ጌትነቴ እና በ102ኛ ኮር አመራሮች አስተባባሪነት ተጠናቋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ አፋብኃ|ቴዎ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ                  ህዳር 11/2018 ዓም

በአማራነታቸዉ ጡታቸዉ ለተቆረጡና ቆዳቸዉ ለተገፈፉት ሰማዕታት እህቶቻችን (ለባለምላይና ጓዶቿ) በካናዳ፤ ለንደን ኦንታርዮ ደብረ ኃይል ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ክብራቸውን በሚመጥን ሁናቴ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ፍትሐት ተካሄዷል። የጀግኖች ሰማዕታት እህቶቻችን ነፍስ በፃድቃን ጎን እግዚአብሔር ያስቀምጥልን!! ከስፋራው መረጃውን በአጭር ቪዲዬ አስደግፈው ልከውልናል።

በደላንታ ወረዳ ፀሐይ መውጫ ቀበሌ አከባቢ አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ በሦስት የአገዛዙ ወታደሮች ተደረፈች! በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ፀሐይ መውጫ ቀበሌ ልዩ ቦታው አዲሱ ጃኖስ ተብሎ በሚጠራው
በደላንታ ወረዳ ፀሐይ መውጫ ቀበሌ አከባቢ አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ በሦስት የአገዛዙ ወታደሮች ተደረፈች! በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ፀሐይ መውጫ ቀበሌ ልዩ ቦታው አዲሱ ጃኖስ ተብሎ በሚጠራው መንደር አንዲት የ10 ዓመት ታዳጊ በሦስት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት መደፈሯን ነው የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ታዳጊዋ በተፈፀመባት አሰቃቂ የጭካኔ ድርጊት ለተወሰኑ ቀናት ሳትነትቃ እራሷን ስታ መሰንበቷን ጣቢያችን ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች አክለው ገልፀዋል ። የታዳጊዋ ወላጆት ድርጊቱ የተፈፀመባት የ10 ዓመቷን ታዳጊ በእለቱ ወደ ወገልጤና ጤና ጣቢያ የወሰዷት ቢሆንም፡ ጤና ጣቢያው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎላት ሕክምናዋን ስትከታተል ሰንብታለች። በቀጠናው የሚገኘው የአገዛዙ ወታደሮች አዛዥ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቱ የተፈፀመባት ታዳጊ ወላጆችን፡ ጉዳዩን ወደ ሕግ እንዳይወሱት አስጠንቅቋቸዋል የተባለ ሲሆን፡ "ምን አልባትም ወደ ሕግ ብትሄዱም ምንም አታመጡም" ሲል ዝቶባቸዋል ነው  የአከባቢው ነዋሪዎች።

የመካነሰላሙ ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ በፍቃዱ(አባ ገንብር) ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጀምሮ ዛሬ ድረስ ቀፅናት በትግሉ ሜዳላይ የሚገኝ ወንድማችን ነዉ። ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ቅ
የመካነሰላሙ ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ በፍቃዱ(አባ ገንብር) ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጀምሮ ዛሬ ድረስ ቀፅናት በትግሉ ሜዳላይ የሚገኝ ወንድማችን ነዉ። ጀግንነት ብቻ ሳይሆን ቅንነት ያለዉ የትግል መሪ ነዉ ። ብሬን ሲተኩስ ለጉድ ነዉ ይሉታል።ሁሌም ከሰራዊቱ ፊት መግባት ነዉ ልማዱ ። ይህ ልማድ የቀደምቶቻችም የእነ ፊትአዉራሪ ገበየሁ አባ ጎራዉ መሆኑን ልብ ይሏል። እኔ እንዴት እንደምሞት ሄዳችሁ ለንጉሱ ንገሩት ብለዉ በጀግንነት የተሰዉት ፊትአዉራሪ ገበየሁ የአድዋ ተጋድሎ አይረሳም ።የአባቶቻችን ልጆች ነን። በነገራችን ላይ መሪዎች ዉጊያን አቀናጅቶ መምራት እና አሃዶች እንደተሳሰሩ ማድረግ እንጅ ከፊት ሆነዉ እንድዋጉ አይመከርም ።መሪ በፍፁም ዉጊያ ዉስጥ መግባት የለበትም። በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

በወታደር ቤት በስራ ላይ መጨቃጨቅ ያለ የነበረ የሚኖር ነው ። ስራ ሲሰራ ትጨቃጨቃለህ ሌላ ግን ምንም አይነት ችግር የለብንም። የምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ጠንካራ አደረጃጀት እና ሰፊ ቀጠና ይዞ በተግባር ሰርቶ የሚያስመሰክር ሃይል ነው፡ በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥🔥ወላጅ አልባው ታዳጊ🔥🔥 #እናቱን_በአረመኔው_የአብይ_ተላላኪወች_የተነጠቀው_ወላጅ_አልባህፃን በግልፅ በአማራ ህዝብ ላይ ወረራ ከፈፀመ ጊዜ ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ህፃናት በቡድንና በተናጠል ተደፍረዋል፣ ንፁሀን በከባድ መሳሪያና በድሮን ተጨፍጭፈዋል፣ በርካቶችም ተሰልፈው ተረሽነዋል፤ ንብረታቸው ወድሟል አካላቸውም ጎድሏል። #በዚህምክንያትም_ህፃናትያለአሳዳጊ_አረጋውያንም ያለ ጧሪ ቀባሪ ቀርተዋል። የአማራ እናቶች ለአመታት ማቅ ለብሰው ገመድ ታጥቀው መኖር ግዴታቸው ሆኗል፤ አማራነት ወንጀል የሆነበትን ዘመን ለመሻገር በርካታ የማይተመን ዋጋ እየከፈለ ነው አማራ፤ ወላጅ አልባ ከሆኑት ህፃናት መካከል አንዱ ህፃን በረከት ሙሉቀን ነው። #ገናየ1አመት_ከስድስት_ወርእያለ_አባቱበስራ ምክንያት ከአካባቢው ይርቃል እናቱ ጥጋብ አብየም ልጇን በብቸኝነት እያሳደገች ባለችበት ምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳርምድር ወረዳ ሰኞ ገበያ ከተማ ከምትሰራበት ቤት ገብቶ አማራንና አማራነትን ሲያንቋሽሽ ለምን እንዲህ ትላለህ ብላ ስትከራከረው አማራ ጀግና ህዝብ ነው ለምን አልሽኝ ብሎ በያዘው መሳሪያ ደብድቦ ግንቦት 22/2016 ዓ/ም ገደላት። #ህፃን_በረከትሙሉቀንም ከዚያን እለት ጀምሮ ቡናያ በተባለ በረሀማ አካባቢ የሚኖሩት አሮጊት አያቱ ወስደውት መኖር ከጀመረ ሁለተኛ አመቱን ይዟል። ህፃን በረከትን ለመርዳት የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩን በቀጥታ እናገናኛቹሀለን መረጃውን በቀጥታ ያደረሰን የ74ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ነው #የቴወድሮስ_እዝ_201ኛኮር_ህዝብግንኙነት አማራነት ወንጀል መሆኑ ቀርቶ መከበሪያ ማንነት ይሆናል‼️ አማራ ያሸንፋል!! በልጆቹ ተከብሮ ይኖራል!! ህዳር 11/2018 ዓ.ም በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ለህዝባችን ታማኝ ነበር ታማኝ ሆነን እስከመጨረሻው ይህንን ስረዓት ታግለን እንቀብረዋለን።100% እርግጠኛ ነኝ🙏 የህዝባችን መሳደደ፣የጅምላ እስር፣የጅምላ ግድያ፣የጅምላ እግታ አዕምሮችንን እረፍት ነሳው? እኛም እንደ ማነኛውም አማራ የመኖር ብታችን በሰላማዊ መንገድ ይፈታ መስሎን በምርጫም ካርድ ሞከርነው ምርጨውንም አጭበረበሩን ድምፃችንን በሰላማዊ ሰልፍች መፈክሮች አሰማን አልሆን አለ?በመጨረሻም በምላሱ እየቀባ አፉ ቅቤ ሆዱ ጩቤ እባብ መረዘኛ የሆነውን አብይ አህመድ ስረዓት ለመገርሰስ መሪያችን ራስ አርበኛው ዘመነ ካሴ በአደራጀው አደረጃጀት እራሳችንን ለመከላከል በህዝባዊ ፋኖ አደረጃጀት ታቅፈን ተሰባሰብን እኛ ሳንሰለጥን አብርን አሰልጥነን ጠንካራ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ የህዝባዊ የፋኖ አባላት አስመረቅን። ባንኩም ታንኩም ሁሉ ነገሩ በእጃቸው ነበር። ለህዝብ ሆ ብሎ የወጠውን የህዝባዊ ፋኖ አደረጃጀትን በንቀት መልኩ የብአዴን አመራር እና ብአዴናውያን አስተሳሰብ ያላቸው ሳቁብን ተሳለቁብ የከተማ ፋኖ እያሉ በየ በረንዳ ቡና ቤቱ የቡና መጠጫ እና መሳለቂያ አደረጉን መቀመጫም አሳጡን? ይሄው ይህንን ስረዓት በህዝብ አብዮት አፍረሰን የአባቶቻችንን ነፍጥ አንግበን ባንኩም ታንኩም ከታጠቀ ስረዓት ጋር ተፋልመን የሰለጠነ ወታደራዊ ሀይል ገንብተን መንግስታዊ መዋቅር ያለው አደረጃጀት ዘርግተን ህዝባችንን በታማኝነት እና በቅንነነት እየመራን እንገኛለን። ብአዴኖች እና የብአዴን አስተሳሰብ ያለቸው ደናቁርት አሁን ደግሞ ምን ይሉን ይሆን አይ ብአዴን? መልካም አዳር ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም💪💪💪 ትግሉ አልቋል የቀረን መቋጨት ነው 💪💪💪 ●ትርፋችን ሀገርን ከወራሪ፣ባንዳና ሰላቶ አስጠብቀው ለእኛ አስረክበው በክብር በጀግንነት እና በታማኝነት እንዳለፍት አባቶቻችን እኛም ታሪክ ሰረተን ትውልዱ በአማራነቱ ሳይሸማቀቅ የሚኖርባት ሀገር እንድትኖረን ሰረተን ማለፍ ነው አላማችን🙏🙏🙏 በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን። https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk