ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Open in Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Show more4 416
Subscribers
+1224 hours
+287 days
+1 15930 days
Posts Archive
ሠው ለሆነ ሁሉ ልብ ያደማል!😥
ይህ ወጣት ፦👇
'' ... ከቀናቶች በፊት አማራ ክልል ወንድሜ በፋኖ ተገድሏል። እናቴም አልሠማችም። አሁን ደግሞ እኛም ከ 3 ቀን በኃላ ትገባላችሁ እየተባልን ነው። እኔ ራሴን አጥፍቼ እናቴ ሬሳዬን እንኳ በአይኗ አይታ ትቅበር። የወንድሜንም የኔንም ሀዘን እንደት ነው የምትችለው ? አማራ ክልል ከገባሁ እኔም አልተርፍም!'' ነው የሚለው አሉ! 😢
#ኦሮሚያ
የሠው ልጅ ህይወት ኦዲት የማይደረግባት አሳዛኝ ሀገር - #ኢትዮጵያ!
ከትግራዩ ጦርነት ጀምሮ ሚሊየኖች ያለእረፍት ይረግፋሉ! አሁንም ግን አንዱ ሳያልቅ ሌላ የእልቂት ድግስ የሚደግስ እንጂ መተላለቅን የሚያስቆም አልተገኘም!😥
ሰበር !!ጀነራል መድፍ ተከሰከሰ !!
የ602ኛ ኮር አዛዥ ጀነራል ሶፊያን አህመድን አጅቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ ጀነራል መድፍ ሲጎትት የነበረ ኦራል ቢቸና ከተማ ወጣ ብሎ እነከርከር ላይ ተገልብጧል።
ኦራሉ ላይ የነበሩ የአረመኔው አባላት በሙሉ ተፈጥፍጠዋል። እስካሁን የ6 መኬ አስከሬን ተነስቷል። የተቀሩት ከባድ እና ቁስለኛ ሆነዋል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምኒልክ ዕዝ ምክትል ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ ሞገስ አባራው እና የዕዙ የሕክምና መምሪያ ኃላፊ ፋኖ አቡበከር ሰኢድ በማርቲን ታልማን የሚመራውን የቀይ መስቀል ልዑክ በመቀበል በፋኖ ዘንድ የነበራቸው ቆይታ እንዲሳለጥና የፋኖን ጥብቅ የሆነ የምርኮኛ አያያዝ ዲስፕሊን ለቀይ መስቀል እንዲሁም ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲደርስ ላደረጋችሁት ስራ ምስጋና ይገባችኋል።
ሰበር የድል ዜና‼️
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ብሩኬ ደምሴ ክፍለ ጦር ታሪካዊቷን ወረኢሉ(ዋሲል) ከተማን ተቆጣጥሯል።
ዝርዝሩን እንመለስበታል💪💪💪
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
በረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ በጠላት ላይ ጥቃት ፈጸመ!
ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክ/ጦር የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ አናብስቶች በሆስፒታል በኩል ደብረ ኤልያስ ከተማ ዘልቀው በመግባት በመግባት በወራሪው የብልጽግና ሠራዊት ከፍተኛ ጥቃት ፈጽመዋል።
በድንገት ከጠላት ምሽግ የተከሰቱት ቀስተኞቹ የቀስተ ደመና ብርጌድ አናብስቶች በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ወጥተዋል።
መረጃው የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ነው።
ድል ለአማራ ፋኖ!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር
+1
"....በዚህ የአማራ የህልውና ትግል ከአንገታም አንገታም ወንድሞቻችን በተጨማሪ ለማየት የሚያሳሱ እህቶቻችንም እየተገበረበት ያለ ትግል በመሆኑ በትግሉ የምትቀልዱትን ታጋይ እና ደጋፊዎችን የእነሱ አጥንት እሾህ ሁኖ የሚወጋቸው ይመስለኛል።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የሰሜን አምባራስ ክፍለጦር አርበኝት ፋኒት መቅደስ መሰዋትነትን ተቀብላለች!!
ክብር ከተጀመረ እስካሁን በየቀኑ እየወደቁ ላሉ ለትግሉ ሰማዕታት ይሁንል!
አማራ በልጆቹ መሰዋትነት ነገ ነጻ ይወጣል✊
[ ከደጋጎች ጎን እረፊ እህቴ ]🙏
ሰበር!
የ602ኛ ኮር አዛዡን ሶፊያን አህመድ የተባለን ግለሰብ አጅቦ የነበረው እና ጀነራል መድፍ ሲጎትት የነበረ ኦራል ቢቸና ከተማ እነከርከረ ዳገት
ተገልብጦ ተንኮታኩቷል።
ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም
የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አገልጋይ የዞን ሚሊሻ ፅ/ቤትን ሀላፊ አቶ ገበሬው ሰማ እና የዞን ሰላምና ደህንነት ሀላፊ አጅቦ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኦራል በቢቸና ከተማ እነከርከር ዳገት ጥቁር አስፖልት እነከረከር ዳገት ላይ #ኦራሉ ተገልብጦል።በዚህም የደረሰ ጉዳት:-
➤ 6 የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ሞተዋል
➤ከ15 በላይ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ መሆናቸው ተረጋግጦል።
የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት አባላት ሲሞቱ ቁስለኛ በአንቡላስ እያጎጓዘ ይገኛል። ያቃተው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ከጥቅምት 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባወጣው እቅድ መሰረት ሚሊሻ፣ፖሊስ፣አድማ ብተና እና የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊትን በጥምረት በማቀናጄት ለመጨረሻ ኦፕሬሽን በሚል እሳቤ በቢቸና ከተማ ብሌን ካፌ/ሆቴል ላይ ስምምነት አካሄደዋል።
በንፁሀን ደም እጃቸው የተጨማለቁት የአረመኔው ብልፅግና አገዛዝ ሆዳም ካዲሪዎች ከደ/ማረቆስ ከተማ ተነስተው ቢቸና ከተማ የተገኙት የሸበል ተወላጁ የዞን ሚኒሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገበሬው ሰማና ሌሎች የዞን ሰላምና ደህንነት ሀላፊዎችን ለማጀብ 1ፔንፒ፣1 ዙ-23 ፣1 ሞርተር፣7 ፖትሮልና ሌሎች በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በመያዝ አገዛዙ ይጠቀምባቸው ከነበሩት ኦራሎች ውስጥ አንዱ ኦራል ቢቸና ከተማ እነከረከር ዳገት ተገልብጦ በኦራሉ ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ አገልጋዮች በሙሉ መሞታቸው ተረጋግጦል።
የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ከቢቸና ደ/ወርቅ ሚኒሻ፣ፖሊስና አድማ ብተናውን ከፊት በማሰለፍ በሜካናይዝድ መልኩ ከቀን ወደ ሌሊት ዘመቻ በማዘጋጀት የትኛውም የፋኖ ኃይል ወዳለበት ቀጠና ላይ በሌሊት በመግባት ከበባ፣ደፈጣ፣ ቆረጣና መሰል የጥቃት ኢላማ እቅድ ማውጣታቸውን አረጋግጠናል።
በመሆኑም በዛሬው እለት ከቢቸና የረዝ ወይራ ጠልማ ደብር ወረቅ ፔንፔ እና መድፍ በመያዝ ሲያደርጉት የነበረው የማደናገሪያ እንቅስቃሴ ለሌሊት ማጥቃት ምቹ ሁኔታዎችን ለመንደፍ የተደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።
ማሳሰቢያ👇ከዚህ ጋር ተያይዞ በየትኛውም የፋኖ ቀጠናዎች ላይ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ከውስጥ ባንዳ ተላላኪ ጭምር ጥብቅ ጥንቃቄና ቅድመ ዝግጅት እንድታደረጉ እናሳስባለን።የአረመኔው አገዛዝ ራዊት የሌሊት ማጥቃት እቅዱ መያዙን በማንኛውም ቀጠና የምትገኙ የፋኖ ኃይሎች እንዲሁም በስምተኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር እና ዘጠንኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር ቀጠና ስር የሚተዳደሩ ንፁስ ከተማና የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ገዳእያሱ፣ገብሲት፣ወይንዬ፣ወፍጡማ፣ጉቢያ በቆቁኃ፣ተስካረ ማርያም፣ዛንበራ፣የዳማ፣ጀረምስ፣ ናብራ፣ደ/ኢየሱስ፣ ቅድስጌ፣ዲማ፣ የቀበሀና፣ መንግስቶ፣ገደብ፣መጢያና መሰል የትኛውም ቦታዎች ላይ ጥብቅ ጥንቃቄ እንድታደረጉ በጥብቅ እናሳስባለን።
አዲስ ትውልድ ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!
ጥቅምት 01/2018 ዓ.ም
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ ምትኩ
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
🎯ታላቅ የተቋውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው!
ፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ የዐማራውን ዘር በጅምላና ባደባባይ የማጥፋትና የማጽዳት ዓላማውን በመቃወም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድምፃችንን የማሰማት ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪ እያቀረብን፦
ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በስቴት ዲፓርትመንት በሠዓቱ በመገኘት ለወገኖቻችን ድምጽ እንድንሆን በአጽንኦት እናሳስባለን።
ቀን: ረቡዕ October 15 ,2025 ሠዓት: 9:00AM ቦታ : State Department አድራሻ: 2201 C St NW DC 20451 ሠዓት: 9:00AM
የሰልፉ አዘጋጆች
1. የዐማራ ዳያስፖራ ግሎባል ፎረም
2. ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት
3. የዋሽንግተንና አካባቢው የዐማራ ማህበር
4. የዲሲ ግብረሃይል
5. የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የዐማራ ትዕይንተ ህዝብ አስተባባሪ
6. የዲሲ የጋራ ግብረ ኃይል
ከአማራ ሚዲያ ካውንስል ጋር በጋራ በመተባበር
ድል ለሕዝባችን!
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በድል ተጠናቀቀ!
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14/2018 ዓ.ም የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በበርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ታጅቦ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተቋጭቷል::
ዘመቻው፣ መስከረም 14/2018 ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በአምስቱም ኮሮች በተመሳሳይ ሰዓት ውጊያ በመክፈት ከጀመርንበት ቅጽበት አንስቶ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ፡-
ምስራቅ አማራ ኮር 1፣ ምስራቅ አማራ ኮር 2፣ ላስታ አሳምነው ኮር፣ ልጅ ዕያሱ ኮር፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ የዕዙ ልዩ ዘመቻ እንዲሁም በአንዳንድ ቀጠናዎች በቅንጅት የድርጅታችን አካል የሆኑት ቴዎድሮስ ዕዝ፣ አሳምነው ዕዝ፣ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና መላው የሰራዊታችን አባል፣ በየደረጃው የሚገኙ የኃይል አመራሮች እና የዕዛችን ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች 24/7 እረፍት አልባ የውጊያ ተሳትፎና አመራር በመስጠት የኀልውና ትግሉን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ማስገባት ተችሏል፡፡
ዘመቻው ታቅዶ ወደተግባር ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ የድርጅታችን አፋብኃ ቀጠናዊ አመራሮች የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ፤ የዘመቻው አካል በመሆን የጠላትን እንቅስቃሴ በመገደብ አልፎም ባደረግናቸው የጋራ ውጊያዎች፣ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል መሪ ድርጅት እንደተፈጠረ በተግባር አሳይተናል፡፡
ለ18 ቀናት ያለ እረፍት በዘለቀው ዘመቻ አባ ናደው በርካታ የነፍስ ወከፍ የቡድንና መካናይዝድ ጦር መሳሪያዎችን ከበርካታ ተተኳሽ ጋር እንዲሁም ከ20 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በምርኮ የተገኘበት ሲሆን፤ ጠላት አምስት ክፍለጦሮቹ የተበተኑበት፤ ውጊያን አቅደው የሚመሩ የውጊያ መሃንዲሶቹን ጨምሮ በርካታ መስመራዊ መኮንኖቹን ያጣበት፤ በመቶዎች የተማረኩበትና በሽዎች ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ስኬታማ ዘመቻ እንደነበር በግምገማችን አረጋግጠናል፡፡
የአማራ የኀልውና ትግል ከጀመረበት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ጠላት ካስተናገዳቸው ኪሳራዎቹ እጅግ የከበደውን ኪሳራ በዘመቻ አደም አሊ አስተናግዷል፡፡
ፋኖ በርካታ ወረዳዎችን፣ ከተማ አስተዳደሮችንና ሰፊ ቀጠና የተቆጣጠረበት፣ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በሰፊው የዘረጋበት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣይ እንደ አማራ፣ አፋብኃ በሚያውጀው ዘመቻ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትልቅ ፍንጭ የሰጠንበት አቅማችንን ለወዳጅ ጠላት ያሳየንበት ልዩ ዘመቻ ነበር፡፡
በጥቅል ግምገማችን በዘመቻው የፋኖ የኀልውና ትግል አዲስ የትግል ምዕራፍ የደረሰበት በመሆኑ በተመዘገበው ድል ሰራዊታችንና ድርጅታችን ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና የአማራ ትግል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
ከምንም በላይ የአማራ ፋኖ ትግል ዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንደሚያከብር፣ በምርኮኛ አያያዙ ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብ በማሳየት ትግላችን ራስን የመከላከል፣ እንዲጠፋ የተፈረደበትን ሕዝብ ኀልውና የማዳን ተልዕኮ እንደሆነ በተግባር ማስመስከር ችለናል፡፡
ነፃ በወጡ ከተሞችና የወረዳ ማዕከላት ደማቅ አቀባበል ያደረገልን ሕዝባችን፣ በተሳትፎው የትግሉ ባለቤትነቱን ዳግም አስመስክሯል!!
የአለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ (International humanitarian law) በሚደነግገው መሠረት ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ ሁኔታ የያዝናቸው የቀድሞ የብልጽግና ሰራዊት አባላት ይህን ምስክራቸውን በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ አባላት ፊት መስክረዋል፡፡ ይህ አዲሱ የአማራ ኀልውና ትግል የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡
በቀጣይም እንደ ድርጅት በምናደርጋቸው ዘመቻዎች ለአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ ተገዢ ሆነን እስከ አራት ኪሎ ድረስ እንደምንዘልቅ ዳግም ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
አጠቃላይ ባለፉት 18 ቀናት በዘመቻ አባ ናደው የተመዘገቡ ዝርዝር ቁጥራዊና ሌሎች መረጃዎችን የማጠቃለያ ሪፖርትን ይዘን እንመለሳለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
የአገዛዙ የፀጥታ ማዋቀር በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ምስራቅ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ቀጣይ ስለሚኖረው ዘመቻ እና ተያያዝ ጉዳዮች አንገር ጉትን ከተማ ላይ መክሯል ።
በምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በተመራው ስብሰባ ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቀት ስለሆነ የኛ የደህንነት ሰወች በቀን ሰራተኛ ስም ፋኖ ወደ አሉበት ቀጠና ሂደዉ አስፈላጊውን መረጃ እንዲያመጡ በሚል ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
በመሆኑም ወቅት እየጠበቁ አማራው አመት ሙሉ የለፋበትን ሰብል እንዳይሰበሰብ እና መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለማድረግ ስለታሰበ ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ፀጉረ ልዉጦችንም ሲመለከት አስፈላጊው ምርመራ እንዲያርግ እናሳስባለን ሲል የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት ሀላፊ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ ገልጿል
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በአንድነት በወንድማማችነት ስለ ድርጅታዊ ቁመና ስለትግሉ ደካማ እና ጠይካራ ተግዳሮቶች አልፎም ስለጎንደርም ሆነ ስለአማራ አንድነት በቁርጠኝነት ለመስራት አብዝተው እየተወያዩ ይገኛሉ።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢ ዝምተኛው አማራ የትግሉ ዘብ አርበኛ ባየ ቀናው ለናፈቃቹህ ደግሞ እሄው ከቁርጠኛ አማሮች መካከል በክብር እየተገማሸረ ይገኛል!
ድል ለአማራ ህዝብ
በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተገናኘ የፋኖ ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ በሚል በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለመሠረት ሚዲያ ተናግረዋል።
"እስረኞቹ ከጠበቃቸው ጋር እንዳይገናኙ ተከለከሉ የተባለው ምን ያህል እውነት ነው?" ስንል ከጠበቆቹ አንዱ የሆኑትን አቶ ሰለሞን ገዛኽኝን ጠይቀናቸው ነበር።
አቶ ሰለሞን ጉዳዩ እውነት መሆኑን አረጋግጠው "እስረኞቹን አግኝተህ የሕግ አገልግሎት መስጠት አትችልም በሚል የተከለከልኩት እኔ ነኝ" ሲሉ ገልፀዋል።
"ከእስረኞቹ ጋር እንዳይገናኙ የተከለከሉበት ምክንያት ምንድን ነው?" ተብለው ከመሠረት ሚዲያ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ "ካሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ድረስ በሽብር የተከሰሱ እስረኞቹን ለይተው ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በሚል በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከልክለናል" ሲሉ አቶ ሰለሞን አክለዋል።
ጠበቃው ጨምረውም "እንኳን ጠበቆቻቸው ቤተሰቦቻቸው ገብተው እንዳይጠይቋቸው ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በሽብር ወንጀል የተከሰሱ እስረኞቹ ከሌላው በተለየ ሁኔታ ሕክምና ሳይቀር እየተከለከሉ ነው ያሉት ጠበቃ ሰለሞን በጠና ታመው አልጋ ላይ የዋሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶክተር ካሳ ተሻገር ሕክምና እንዳያገኙ ከተከለከሉት እስረኞች ውስጥ አንዱ ናቸው ብለዋል።
ዶክተር ካሳ በጀርባ ዲስክ መንሸራተት ምክንያት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ የተናገሩት ጠበቃው ማረሚያ ቤቱ ለማሳከም ፍቃደኛ አልሆነም ብለዋል።
ይህንን በእስረኞቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጫና አስመልክቶ አቤቱታ ለማቅረብ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የጥበቃ እና ደኅንነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታን የጠየቁት አቶ ሰለሞን ተቋሙን የማይወክል እና ራሳቸውን የሥርዓቱ ተወካይ አድርገው በመቁጠር የማይገባ መልስ ሰጥተውኛል ብለዋል።
የእስረኞችን አቤቱታ እና የማረሚያ ቤቱን ያልተገባ መልስ በማጣቀስ በቀጣይ ሳምንት ፍርድ ቤት እንደሚከሱ የነገሩን አቶ ሰለሞን በዛሬው ዕለት በዚሁ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ መሪጌታ በላይ አዳሙ የተባሉ ደንበኛቸው በጥበቃ ፖሊሶች መደብደባቸውን እና በአሁኑ ወቅትም ሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
መሪጌታ በላይ በአማራ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የትጥቅ ትግል ትደግፋላችሁ በሚል ከታሰሩ ሦስት መቶ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።
ምንጭ - መሠረት ሚድያ
መረጃ ወለጋ ‼️
።።።።።
የአገዛዙ የፀጥታ ማዋቀር በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ምስራቅ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ቀጣይ ስለሚኖረው ዘመቻ እና ተያያዝ ጉዳዮች አንገር ጉትን ከተማ ላይ መክሯል ።
በምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በተመራው ስብሰባ ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቀት ስለሆነ የኛ የደህንነት ሰወች በቀን ሰራተኛ ስም ፋኖ ወደ አሉበት ቀጠና ሂደዉ አስፈላጊውን መረጃ እንዲያመጡ በሚል ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
በመሆኑም ወቅት እየጠበቁ አማራው አመት ሙሉ የለፋበትን ሰብል እንዳይሰበሰብ እና መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለማድረግ ስለታሰበ ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ፀጉረ ልዉጦችንም ሲመለከት አስፈላጊው ምርመራ እንዲያርግ እናሳስባለን ሲል የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት ሀላፊ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ ገልጿል
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የስልጠና ጥሪ
በ.አ.ፋ.ብ.ኃ የ፫ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር
የ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
➶➶ የስልጠና ጥሪ ➶➶
የፋኖ ወታደር በመሆን የዚህ ታሪካዊ የህልውና ትግል ባለቤቶች ሆናችሁ ታሪካችሁን በወርቅ ቀለም መፃፍ ወይም ማፃፍ ለናፈቃችሁ ዕድለኛ የዚህ ዘመን በየትኛውም ወታደራዊ ምልስ ወጣቶች የቀረበ የስልጠና ጥሪ፦
በመላው አማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ አማራ ጠል ሰራዊት አዝምቶ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ከከፈተው ፋሽስቱ አብይ አህመድ ጋር እንደ ህዝብ እየተደረገ ያለውን ተጋድሎ በመረዳት የገጠመንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በጀመርነው የፋኖነት ትግል አሻራችሁን ማስቀመጥ ለምትፈልጉ የምልስ የኮማንዶ ስልጠና እና በህክምና አገልግሎት እንዲያገለግሉ የሚፈልጉ የጤና ባለሙያወችን ተቀብሎ ስልጠና ለመስጠት ብርጌዱ ሙሉ ዝግጂቱን ያጠናቀቀ መሆኑ ግልፅ ነው።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ወጣቶች ከመስከረም :-30/01/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 07/02/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 8 ቀናት ውስጥ ማዕከል ድረስ መጣችሁ እንድትመዘገቡ ስንል አማራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን ።
ሀ,የጤና ባለሙያ
፩, በህክምና ሙያ ተመርቀው በማነኛውም የጤና ተቋማት ውስጥ ሲያገለግሉ የቆየ/ች
፪, በህክምና ሙያ ተመርቀው coc/center of compitancy/ ወስደው ብቁ የሆነ/ች "ይመረጣል"
፫, በየትኛውም በጤና ሙያ ተመርቀው ህዝባችን የገጠመውን አደጋ ተረድቶ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች
ለ, ማንኛውም ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ
፩. ፆታ አይለይም ሴቶች ይበረታታሉ
፪. ዕድሜ ከ18 አመት በላይ
፫. ሙሉ አካሉ ጤነኛ የሆነ/የሆች
፬. የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልዉና አደጋ የተረዳ/የተረዳች
፭.ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆ/የሆች
፮. ምንም አይነት የስነ ምግባር ችግር የሌለበት/ባት
፯. ምንም አይነት የወንጀል ተሳትፎ የሌለው/ላት
፰.በአፋብኃ ደንብ እና መመሪያ ተገዥ የሆነ/ች
፱. ከሚኖርበት አካባቢ መታወቂያ ያለውና ማቅረብ የሚችል
፲. ከዚህ በፊት በፋኖ ሰልጥናችሁ ባላችሁበት አካባቢ በብርጌዱ ቆዩ የተባላችሁ
ሐ, በመንግስት የፀጥታ መዋቅር ውስጥ የነበራችሁ
፩. ፓሊስ,ሚሊሻ,አድማ በትን,ሰላም አስከባሪ እና መከላከያ ሰራዊት ፪. በመንግስት መዋቅር ውስጥ በአመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩ በማገልገል ላይ የሚገኙ አመራሮች የመንግስት ሰራተኞች ጨፍጫፊውን ስርአት በመቃወም ከወዲሁ ከአማራ ህዝብ ትግል እንድትቀላቀሉ ብርጌዱ በአፅኖት ይጠይቃል።
ማሳሰቢያ ፦
° አዲስ ምልምል ሰልጣኝ በቅርብ ቀን ጥሪ የምናደርግ ስለሆነ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ እናሳውቃለን።
• ለምዝገባ ከተሰጠዉ ቀን ውጭ የመጣ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
• መታወቂያ ያለው/ያላት
የ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ
አዲስ ትውልድ ፣
አዲስ አስተሳሰብ ፣
አዲስ ተስፋ !!!
