ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
الذهاب إلى القناة على Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
إظهار المزيد4 418
المشتركون
+1224 ساعات
+287 أيام
+1 15930 أيام
أرشيف المشاركات
🎯ታላቅ የተቋውሞ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው!
ፋሽስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ የዐማራውን ዘር በጅምላና ባደባባይ የማጥፋትና የማጽዳት ዓላማውን በመቃወም ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ድምፃችንን የማሰማት ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪ እያቀረብን፦
ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በስቴት ዲፓርትመንት በሠዓቱ በመገኘት ለወገኖቻችን ድምጽ እንድንሆን በአጽንኦት እናሳስባለን።
ቀን: ረቡዕ October 15 ,2025 ሠዓት: 9:00AM ቦታ : State Department አድራሻ: 2201 C St NW DC 20451 ሠዓት: 9:00AM
የሰልፉ አዘጋጆች
1. የዐማራ ዳያስፖራ ግሎባል ፎረም
2. ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት
3. የዋሽንግተንና አካባቢው የዐማራ ማህበር
4. የዲሲ ግብረሃይል
5. የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የዐማራ ትዕይንተ ህዝብ አስተባባሪ
6. የዲሲ የጋራ ግብረ ኃይል
ከአማራ ሚዲያ ካውንስል ጋር በጋራ በመተባበር
ድል ለሕዝባችን!
ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በድል ተጠናቀቀ!
በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ መስከረም 14/2018 ዓ.ም የተጀመረው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በበርካታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ታጅቦ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ተቋጭቷል::
ዘመቻው፣ መስከረም 14/2018 ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት በአምስቱም ኮሮች በተመሳሳይ ሰዓት ውጊያ በመክፈት ከጀመርንበት ቅጽበት አንስቶ የአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ፡-
ምስራቅ አማራ ኮር 1፣ ምስራቅ አማራ ኮር 2፣ ላስታ አሳምነው ኮር፣ ልጅ ዕያሱ ኮር፣ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ የዕዙ ልዩ ዘመቻ እንዲሁም በአንዳንድ ቀጠናዎች በቅንጅት የድርጅታችን አካል የሆኑት ቴዎድሮስ ዕዝ፣ አሳምነው ዕዝ፣ በላይ ዘለቀ ዕዝ እና መላው የሰራዊታችን አባል፣ በየደረጃው የሚገኙ የኃይል አመራሮች እና የዕዛችን ሥራ አስፈጻሚ አመራሮች 24/7 እረፍት አልባ የውጊያ ተሳትፎና አመራር በመስጠት የኀልውና ትግሉን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ማስገባት ተችሏል፡፡
ዘመቻው ታቅዶ ወደተግባር ከተገባበት ጊዜ ጀምሮ የድርጅታችን አፋብኃ ቀጠናዊ አመራሮች የሞራል ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ፤ የዘመቻው አካል በመሆን የጠላትን እንቅስቃሴ በመገደብ አልፎም ባደረግናቸው የጋራ ውጊያዎች፣ የአማራ ሕዝብ የኀልውና ትግል መሪ ድርጅት እንደተፈጠረ በተግባር አሳይተናል፡፡
ለ18 ቀናት ያለ እረፍት በዘለቀው ዘመቻ አባ ናደው በርካታ የነፍስ ወከፍ የቡድንና መካናይዝድ ጦር መሳሪያዎችን ከበርካታ ተተኳሽ ጋር እንዲሁም ከ20 በላይ ወታደራዊ ተሽከርካሪ በምርኮ የተገኘበት ሲሆን፤ ጠላት አምስት ክፍለጦሮቹ የተበተኑበት፤ ውጊያን አቅደው የሚመሩ የውጊያ መሃንዲሶቹን ጨምሮ በርካታ መስመራዊ መኮንኖቹን ያጣበት፤ በመቶዎች የተማረኩበትና በሽዎች ሙትና ቁስለኛ የሆነበት ስኬታማ ዘመቻ እንደነበር በግምገማችን አረጋግጠናል፡፡
የአማራ የኀልውና ትግል ከጀመረበት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ጠላት ካስተናገዳቸው ኪሳራዎቹ እጅግ የከበደውን ኪሳራ በዘመቻ አደም አሊ አስተናግዷል፡፡
ፋኖ በርካታ ወረዳዎችን፣ ከተማ አስተዳደሮችንና ሰፊ ቀጠና የተቆጣጠረበት፣ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር በሰፊው የዘረጋበት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጣይ እንደ አማራ፣ አፋብኃ በሚያውጀው ዘመቻ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ትልቅ ፍንጭ የሰጠንበት አቅማችንን ለወዳጅ ጠላት ያሳየንበት ልዩ ዘመቻ ነበር፡፡
በጥቅል ግምገማችን በዘመቻው የፋኖ የኀልውና ትግል አዲስ የትግል ምዕራፍ የደረሰበት በመሆኑ በተመዘገበው ድል ሰራዊታችንና ድርጅታችን ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነው መላው የአማራ ሕዝብና የአማራ ትግል ደጋፊዎች እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
ከምንም በላይ የአማራ ፋኖ ትግል ዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎችን እንደሚያከብር፣ በምርኮኛ አያያዙ ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብ በማሳየት ትግላችን ራስን የመከላከል፣ እንዲጠፋ የተፈረደበትን ሕዝብ ኀልውና የማዳን ተልዕኮ እንደሆነ በተግባር ማስመስከር ችለናል፡፡
ነፃ በወጡ ከተሞችና የወረዳ ማዕከላት ደማቅ አቀባበል ያደረገልን ሕዝባችን፣ በተሳትፎው የትግሉ ባለቤትነቱን ዳግም አስመስክሯል!!
የአለም አቀፍ የሰብዓዊነት ሕግ (International humanitarian law) በሚደነግገው መሠረት ሰብዓዊ ክብራቸውን በጠበቀ ሁኔታ የያዝናቸው የቀድሞ የብልጽግና ሰራዊት አባላት ይህን ምስክራቸውን በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ አባላት ፊት መስክረዋል፡፡ ይህ አዲሱ የአማራ ኀልውና ትግል የታሪክ ምዕራፍ ነው፡፡
በቀጣይም እንደ ድርጅት በምናደርጋቸው ዘመቻዎች ለአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ ተገዢ ሆነን እስከ አራት ኪሎ ድረስ እንደምንዘልቅ ዳግም ማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
አጠቃላይ ባለፉት 18 ቀናት በዘመቻ አባ ናደው የተመዘገቡ ዝርዝር ቁጥራዊና ሌሎች መረጃዎችን የማጠቃለያ ሪፖርትን ይዘን እንመለሳለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ኀልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
የአገዛዙ የፀጥታ ማዋቀር በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ምስራቅ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ቀጣይ ስለሚኖረው ዘመቻ እና ተያያዝ ጉዳዮች አንገር ጉትን ከተማ ላይ መክሯል ።
በምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በተመራው ስብሰባ ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቀት ስለሆነ የኛ የደህንነት ሰወች በቀን ሰራተኛ ስም ፋኖ ወደ አሉበት ቀጠና ሂደዉ አስፈላጊውን መረጃ እንዲያመጡ በሚል ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
በመሆኑም ወቅት እየጠበቁ አማራው አመት ሙሉ የለፋበትን ሰብል እንዳይሰበሰብ እና መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለማድረግ ስለታሰበ ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ፀጉረ ልዉጦችንም ሲመለከት አስፈላጊው ምርመራ እንዲያርግ እናሳስባለን ሲል የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት ሀላፊ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ ገልጿል
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በአንድነት በወንድማማችነት ስለ ድርጅታዊ ቁመና ስለትግሉ ደካማ እና ጠይካራ ተግዳሮቶች አልፎም ስለጎንደርም ሆነ ስለአማራ አንድነት በቁርጠኝነት ለመስራት አብዝተው እየተወያዩ ይገኛሉ።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ምክትል ሰብሳቢ ዝምተኛው አማራ የትግሉ ዘብ አርበኛ ባየ ቀናው ለናፈቃቹህ ደግሞ እሄው ከቁርጠኛ አማሮች መካከል በክብር እየተገማሸረ ይገኛል!
ድል ለአማራ ህዝብ
በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተገናኘ የፋኖ ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ በሚል በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለመሠረት ሚዲያ ተናግረዋል።
"እስረኞቹ ከጠበቃቸው ጋር እንዳይገናኙ ተከለከሉ የተባለው ምን ያህል እውነት ነው?" ስንል ከጠበቆቹ አንዱ የሆኑትን አቶ ሰለሞን ገዛኽኝን ጠይቀናቸው ነበር።
አቶ ሰለሞን ጉዳዩ እውነት መሆኑን አረጋግጠው "እስረኞቹን አግኝተህ የሕግ አገልግሎት መስጠት አትችልም በሚል የተከለከልኩት እኔ ነኝ" ሲሉ ገልፀዋል።
"ከእስረኞቹ ጋር እንዳይገናኙ የተከለከሉበት ምክንያት ምንድን ነው?" ተብለው ከመሠረት ሚዲያ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ደግሞ "ካሳለፍነው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ድረስ በሽብር የተከሰሱ እስረኞቹን ለይተው ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በሚል በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከልክለናል" ሲሉ አቶ ሰለሞን አክለዋል።
ጠበቃው ጨምረውም "እንኳን ጠበቆቻቸው ቤተሰቦቻቸው ገብተው እንዳይጠይቋቸው ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
በሽብር ወንጀል የተከሰሱ እስረኞቹ ከሌላው በተለየ ሁኔታ ሕክምና ሳይቀር እየተከለከሉ ነው ያሉት ጠበቃ ሰለሞን በጠና ታመው አልጋ ላይ የዋሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል ዶክተር ካሳ ተሻገር ሕክምና እንዳያገኙ ከተከለከሉት እስረኞች ውስጥ አንዱ ናቸው ብለዋል።
ዶክተር ካሳ በጀርባ ዲስክ መንሸራተት ምክንያት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ የተናገሩት ጠበቃው ማረሚያ ቤቱ ለማሳከም ፍቃደኛ አልሆነም ብለዋል።
ይህንን በእስረኞቹ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጫና አስመልክቶ አቤቱታ ለማቅረብ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የጥበቃ እና ደኅንነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታን የጠየቁት አቶ ሰለሞን ተቋሙን የማይወክል እና ራሳቸውን የሥርዓቱ ተወካይ አድርገው በመቁጠር የማይገባ መልስ ሰጥተውኛል ብለዋል።
የእስረኞችን አቤቱታ እና የማረሚያ ቤቱን ያልተገባ መልስ በማጣቀስ በቀጣይ ሳምንት ፍርድ ቤት እንደሚከሱ የነገሩን አቶ ሰለሞን በዛሬው ዕለት በዚሁ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ መሪጌታ በላይ አዳሙ የተባሉ ደንበኛቸው በጥበቃ ፖሊሶች መደብደባቸውን እና በአሁኑ ወቅትም ሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
መሪጌታ በላይ በአማራ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የትጥቅ ትግል ትደግፋላችሁ በሚል ከታሰሩ ሦስት መቶ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።
ምንጭ - መሠረት ሚድያ
መረጃ ወለጋ ‼️
።።።።።
የአገዛዙ የፀጥታ ማዋቀር በሁለቱ የወለጋ ዞኖች ምስራቅ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ቀጣይ ስለሚኖረው ዘመቻ እና ተያያዝ ጉዳዮች አንገር ጉትን ከተማ ላይ መክሯል ።
በምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በተመራው ስብሰባ ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቀት ስለሆነ የኛ የደህንነት ሰወች በቀን ሰራተኛ ስም ፋኖ ወደ አሉበት ቀጠና ሂደዉ አስፈላጊውን መረጃ እንዲያመጡ በሚል ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
በመሆኑም ወቅት እየጠበቁ አማራው አመት ሙሉ የለፋበትን ሰብል እንዳይሰበሰብ እና መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለማድረግ ስለታሰበ ህዝባችን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና ፀጉረ ልዉጦችንም ሲመለከት አስፈላጊው ምርመራ እንዲያርግ እናሳስባለን ሲል የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኘነት ሀላፊ ዲ/ን ክንዱ አሸናፊ ገልጿል
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የስልጠና ጥሪ
በ.አ.ፋ.ብ.ኃ የ፫ኛ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር
የ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
➶➶ የስልጠና ጥሪ ➶➶
የፋኖ ወታደር በመሆን የዚህ ታሪካዊ የህልውና ትግል ባለቤቶች ሆናችሁ ታሪካችሁን በወርቅ ቀለም መፃፍ ወይም ማፃፍ ለናፈቃችሁ ዕድለኛ የዚህ ዘመን በየትኛውም ወታደራዊ ምልስ ወጣቶች የቀረበ የስልጠና ጥሪ፦
በመላው አማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ አማራ ጠል ሰራዊት አዝምቶ በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ከከፈተው ፋሽስቱ አብይ አህመድ ጋር እንደ ህዝብ እየተደረገ ያለውን ተጋድሎ በመረዳት የገጠመንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በጀመርነው የፋኖነት ትግል አሻራችሁን ማስቀመጥ ለምትፈልጉ የምልስ የኮማንዶ ስልጠና እና በህክምና አገልግሎት እንዲያገለግሉ የሚፈልጉ የጤና ባለሙያወችን ተቀብሎ ስልጠና ለመስጠት ብርጌዱ ሙሉ ዝግጂቱን ያጠናቀቀ መሆኑ ግልፅ ነው።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ወጣቶች ከመስከረም :-30/01/2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 07/02/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 8 ቀናት ውስጥ ማዕከል ድረስ መጣችሁ እንድትመዘገቡ ስንል አማራዊ ጥሪ እናስተላልፋለን ።
ሀ,የጤና ባለሙያ
፩, በህክምና ሙያ ተመርቀው በማነኛውም የጤና ተቋማት ውስጥ ሲያገለግሉ የቆየ/ች
፪, በህክምና ሙያ ተመርቀው coc/center of compitancy/ ወስደው ብቁ የሆነ/ች "ይመረጣል"
፫, በየትኛውም በጤና ሙያ ተመርቀው ህዝባችን የገጠመውን አደጋ ተረድቶ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች
ለ, ማንኛውም ወታደራዊ ስልጠና የወሰደ
፩. ፆታ አይለይም ሴቶች ይበረታታሉ
፪. ዕድሜ ከ18 አመት በላይ
፫. ሙሉ አካሉ ጤነኛ የሆነ/የሆች
፬. የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልዉና አደጋ የተረዳ/የተረዳች
፭.ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆ/የሆች
፮. ምንም አይነት የስነ ምግባር ችግር የሌለበት/ባት
፯. ምንም አይነት የወንጀል ተሳትፎ የሌለው/ላት
፰.በአፋብኃ ደንብ እና መመሪያ ተገዥ የሆነ/ች
፱. ከሚኖርበት አካባቢ መታወቂያ ያለውና ማቅረብ የሚችል
፲. ከዚህ በፊት በፋኖ ሰልጥናችሁ ባላችሁበት አካባቢ በብርጌዱ ቆዩ የተባላችሁ
ሐ, በመንግስት የፀጥታ መዋቅር ውስጥ የነበራችሁ
፩. ፓሊስ,ሚሊሻ,አድማ በትን,ሰላም አስከባሪ እና መከላከያ ሰራዊት ፪. በመንግስት መዋቅር ውስጥ በአመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩ በማገልገል ላይ የሚገኙ አመራሮች የመንግስት ሰራተኞች ጨፍጫፊውን ስርአት በመቃወም ከወዲሁ ከአማራ ህዝብ ትግል እንድትቀላቀሉ ብርጌዱ በአፅኖት ይጠይቃል።
ማሳሰቢያ ፦
° አዲስ ምልምል ሰልጣኝ በቅርብ ቀን ጥሪ የምናደርግ ስለሆነ ተዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁ እናሳውቃለን።
• ለምዝገባ ከተሰጠዉ ቀን ውጭ የመጣ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።
• መታወቂያ ያለው/ያላት
የ፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ
አዲስ ትውልድ ፣
አዲስ አስተሳሰብ ፣
አዲስ ተስፋ !!!
ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ሰላማዊ ነዋሪ መስሎ በመግባት ፋኖን ሲሰልል የነበረው የአገዛዙ መረጃ ደህንነት አባል እጅ ከፈንጅ ተያዘ!
የመረጃ ደህንነት አባሉ ስለ ፋኖ ወቅታዊ አቋም መረጃ ከመሰብሰብ ባለፈ የፋኖ አመራሮች የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ በማጥናት ለድሮን ጥቃት ሲያመቻች ነበር ተብሏል።
በአፄ ቴዎድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር ባሕር ዳር ብርጌድ ስር የሚገኙት የበላይ ሻለቃ አባላት ናቸው የአገዛዙ መረጃና ደህንነት አባሉን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሲል የክፍለጦሩ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ክፍል አስታውቋል።
ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ሰላማዊ ነዋሪ መስሎ በመግባት ፋኖን ሲሰልል የነበረው የአገዛዙ መረጃ ደህንነት አባሉ ሙሉ ስሙ ሃምሣ አለቃ ገብረ አብዝጊ ሮምሃ የሚባል ሲሆን፡ "አማራን የእንጨት ዱላ እንኳን እንዳይዝ አድርገን ትጥቅ እናስፈታዋለን" በሚል ንግግሩ በሚታወቀው የዐብይ አህመድ ምንጣፍ ጎታች የሆነው የምስራቅ ዕዝ አዛዥ የጄነራል መሐመድ ተሰማ የቅርብ ሰውና የዕዙ ስታፍ አባል እንደሆነ ቃሉን ለፋኖ መስጠቱን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ክፍል ያገኘው መረጃ ያመላክታል።
የደህንነት አባሉ፡ ፋኖ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ሰላማዊ ነዋሪ መስሎ በመግባት የፋኖ አሁናዊ አቋም ምን ይመስላል የሚለውን በመሰለል እና የምስራቅ ዕዝ ሰራዊትን መንገድ በመምራት እያገለገለ እንደነበር ነው የታወቀው።
በተጨማሪም ይሄው የመረጃና ደህንነት አባል፡ የፋኖ አመራሮች የሚንቀሳቀሱበትን ሁኔታ በማጥናት ለድሮን ጥቃት የማመቻቸት ተልዕኮ ተሰጥቶት እንደነበር ነው የተነገረው።
ነገር ግን የፋኖ መረጃና ደህንነት መዋቅር በአገዛዙ ሰላይ ላይ ጥብቅ ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ፡ በመጨረሻም እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር አውሎታል።
አባቶቻችን ለእኛ ያወረሱን ጥበብ ነው ፍቅር ነው። ለዚህም ነው ፋኖ የህዝብም የአባቶችም ፈለግን የተከተለ ነው ይህን ትውልድ ስለሚፈሩት ነው በእዬ ሚዲያው የሚያሸንፉን መስሏቸው የሚጮሁት
አይ አይሳካም የነአባቶቻቺንን ፍቅር መቼም አያደፈርሰዉም
መርጡለ ማርያም አስደናቂ ኦፕሬሽን ተሰርቶ ዉሏል
ፈጥኖ ደራሹ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦ መርጡለ ማርያም ከተማ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ የተሳካ ድምሰሳ አድርጓል።
የክፍለጦሩ የሳሙኤል አወቀ ልጆች ሁሉም ብርጌጆች በሚገርም መናበብ እና በጀግንነት ጠላትን በቦንብ ሲያደባዩት ዉለዋል።
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ
መስከረም 30/2018 ዓ.ም
ጠላት አውናይብ ላይ በተደረገዉ ከ6:00 ሰዓት በላይ በፈጀ እልህ አስጨራሽ ዉጊያ የፋኖን ጥይት እና ቦንብ መቋቋም ሲያቅተዉ አብዛሀኛዉ ሀይሉን ካስጨረሰ በኋላ ፋኖ አይተኩስብኝም በማለት የአዉናይብ ቤ/ክርስቲያንን ቁልፍ ሰብሮ በመግባት መቅደሱ ላይ ምሽግ ሰርቶ ይገኛል።
በተለያዩ ቦታዎች የቀጠለዉ ዉጊያ ዛሬ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ የክ/ጦሩ አካል የሆኑ አባይ ሸለቆ ብርጌድ አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድ ሶማ ብርጌድ እና የክ/ጦሩ መች ሀይል ጋር በጋራ ባደረጉት ኦፕሬሽን በርካታ ምሽጎችን በመስበር ጠላትን በየምሽጉ መቅበር ተችሏል።
ጀግኖቹ የቁርጥ ቀን የአማራ ልጆች በአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ወታደር ላይ ሙሉ ከተማዉን ከበባ በማድረግ ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን በጉናጉና ካንፕ፣ ዶማ ትምህርት ቤት፣አዉይናይብ ቤተክርስቲያን ፣ ኮሌጂ፣ ሆስፒታል እና ሸራፊት በተባሉ የተለያዩ ቦታዎች የሰፈረዉን የአብይ የግል ጠባቂ ሀይል በበርካታ አቅጣጫዎች በመክበብ ሲያራግፉት ዉለዋል።
የክ/ጦሩ ወታደራዊ አዛዦች ከብርጌድና ከሻለቃ አመራሮች ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ዘመቻ በወረዳዉ የነበረዉን በርካታ የአብይ ወታደር ሚሊሻ እና ፓሊስ ላይ በወሰዱት እርምጃ እጂ አልሰጥም ያለ ወደላይኛዉ ላይመለስ ሲሸኝ በሰላም እጁን የሰጠ በጀግኖች እንክብካቤ እየተደረገለት ይገኛል።
የአማራ ሆዳደር ሚሊሻ ስብስብ እና የአገዛዙ ታማኝ ጥምር ሚሊሾችን ጨምሮ መደበኛ የተባለዉ ከየጫት ቤቱ ታፍሶ የመጣዉ የምርኮኛዉ ብርሀኑ ጁላ ጦር መሄጃ አቶ ሲጨነቅ ዉሏል።
ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው የመከላከያ አመራሮች እና ታማኝ ካድሪዎችን ጨምሮ በጀግናው 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦር በተወሰደባቸው መብረቃዊ ጥቃት መደምሰሳቸው እና እጂ መስጠታቸዉ ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል አረንዛዉ ጎንቻ ብርጌድ ቡዛ ት/ቤት እና ቴክኒኩ ላይ ትንኮሳ ያደረገ ሲሆን በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዋል ሶማ ብርጌድ ጫን ያለዉ ሻለቃ ፈለገ ከተማ ላይ ደፈጣ በመጣል ዉጊያ ከፈታ ዉላለች።
ክብር በየአዉደ ዉጊያዉ ለአማራ ህዝብ ሲሉ የደምና አጥንት ዋጋ ለሚከፍሉ ሰመዓታት ይሁን
9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር
ህ/ግንኙነት
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳው ካሳ ኮር የካራ ማራ ክፍለጦር ዕጩ የፋኖ አባላትን እና የጤና ባለሙያዎችን በድምቀት አስመርቋል።
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳዉ ካሳ ኮር የካራማራ ክፍለጦር ለወራት ያሰለጠናቸዉን የፋኖ አባላት እና የጤና ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ስነስርዓቱ የአካባቢው ማህበረሰብ፣የኮር፣የክፍለጦር እና የብርጌድ እንዲሁም የሻለቃ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል ።
የሰዉ ኃይል አደረጃጀቱን እና አቅሙን በማሳደግ ሰፊ ቀጠናን መቆጣጠር የቻለዉ ካራማራ ክፍለጦር አዲስ የፋኖ አባላትን አሰልጥኖ ማስመረቁ ለቀጣይ የትግል ጉዞ ጉልህ ሚና እንዳለዉ ተገልጿል።
አዲስ ተመራቂ የፋኖ አባላት የቀጣይ የትግል ሂደት ለማፋጠን እና ትግሉን ለመቋጨት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
[ ጥብቅ ወታደራዊ መረጃዎች ]
ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ በጀነራል ዘውዱ ሰጣርጌ የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ሰራዊት በእነዚህ አካባቢዎች የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማረግ ወስነዋል።👇
ከኩታበር እስከ አምባሰል ፣ወርቃሪያ ፣ አባሰላማ_ግሸን ፤ዚሀልጎት ፤ ደሴ ዙሪያ ፤ አያታ_በር ፤ ሙሜ_ድጉጉሩ ፤ አያታ_በራራ አካባቢ የምትንቀሳቀሱ የወገን ሀይል አደረጃጀቶች ጥንቃቄ ታረጉ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን።
አለን 🙌
