en
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
3 931
Subscribers
+4524 hours
+1767 days
+1 15530 days
Posts Archive
ጉና ክፍለ ጦር የዓምሐራ ፋኖ በሥማዳ መዳረሻ ወገዳ ከተማና ዙሪያ ገባው ድልን ተቀዳጅቷል❗ [የካቲት 01/2018ዓ.ም] ዓምሐራን የነካ የለውም በረካ እንዲል የቤተ ዓምሐራው ዓምሐራ በዓምሐራ ሕዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥፋትን ሲፈጽም የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ጠርንፎ ለመውጣት በተዘጋጀበት ሰዓት የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የባዬው መልካሙ፣ የፍቃዴ አለባቸው፣ የአበበ፣ የሸጋው (ገብርዬ)ና ጥንቅሹ የግብር ልጅ የሆነችው ጠንካራዋና አይበገሬዋ እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ እና የሢሣይነው ራዕይ አሥቀጣይ የሆነችው ሥማዳ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ በጋራ የተቀናጀ አውደ ውጊያን ሲያደርጉ ውለዋል። የዓምሐራ ፋኖ የአገዛዙን የተለያዩ ምሽጎችን በክንዱ ሰባብሯል፤ ተቆጣጥሯል። ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እሥከ ቀኑ 11:00 በዋለው እልህ አሥጨራሽ ትንቅንቅ የዓምሐራ ፋኖ ድልን ተቀዳጅቷል። ዓምሐራ ፋኖ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የአካል፣ የቁሥና የሥነልቦና ኪሳራ አድርሷል። የአገዛዙ ታጣቂዎችና የአገዛዙ የቡድን መሣሪያ እሥከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ ምርኮ ሆኗል። የወገዳ ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጠላት የምጽአት ቀን ይደርሥለት ዘንድ ''ሸረፍ ጎዴ'' ተራራን እየተማጸነ ይገኛል። በኮንክሪት የተሰራው የአቦ ምሽግ በዓምሐራ ልጆች ተጋድሎ ተሰብሯል። የጠላት ብዙዎቹ ምሽጎች ሲሰባበሩ ጠላት የመጨረሻ መዳኛዬ ወዳለውና የቁም ምሽግ ወደሰራበት ''ሸረፍ ጎዴ'' 360° ተራራ ሩጦ ገብቷል። ጠላት ሸረፍ ጎዴ ተራራን አድነኝ ሲል በተማጽኖ ይገኛል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊ አፋብን ሰሜን ዓምሐራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ የካቲት 01/20178ዓ.ም

የብልፅግና ካዝናና የጦር ካንፕ ባዶውን እየቀረ ነው!!! 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ✔️ አያሌው ደመቀና ደጉ ደረበ የተባሉ ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከአዴትና ከባህርዳር አንድ
+1
የብልፅግና ካዝናና የጦር ካንፕ ባዶውን እየቀረ ነው!!! 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ✔️ አያሌው ደመቀና ደጉ ደረበ የተባሉ ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎች ከአዴትና ከባህርዳር አንድ ሁለት እግርና አንድ ሰደፍ ክላሽ በመያዝ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦርን ተቀላቀሉ። ➯ በሌላ ዜና :- ✔️ በቀን 01,06,2018ዓ.ም የብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት መነሻውን መኮድ በማድረግ የ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎችን ለማጥቃት ወደ ባህርዳር ዙሪያ ተንተላ ይጎዲ ቀበሌ የተንቀሳሰቀሰው የጠላት ሀይል ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ልዩ ስሙ ተንተላ ይጎዲ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ በ22ኛ ክፍለጦር ሻለቃዎች በተደረገበት ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት የተበሳጨው ሰው በ*ላው የፋሽስቱ ሰራዊት ሞላ ሳለ የተባለ የ60 አመት ንፁሀን አዛውንትን ባህርዳር ዙሪያ ይጎዲ ቀበሌ ላይ በግፍ እረሽኗል። ፋኖ አማረ ጌታቸው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ገልጿል ግንኙነት! የካቲት 01,2018ዓ.ም ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

የዐብይ አህመድ አገዛዝ በግንባር ከባድ ሽንፈት ሲገጥመው ንጹሃን ላይ ወዳተኮረ ጅምላ ፍጅት ተሸጋግሯል ኔትዎርክ እና የስልክ አግልግልት በማቋረጥ ልዩ የማጥቃት ዘመቻ የከፈተው የዐብይ አህመድ ሰራዊት
+2
የዐብይ አህመድ አገዛዝ በግንባር ከባድ ሽንፈት ሲገጥመው ንጹሃን ላይ ወዳተኮረ ጅምላ ፍጅት ተሸጋግሯል ኔትዎርክ እና የስልክ አግልግልት በማቋረጥ ልዩ የማጥቃት ዘመቻ የከፈተው የዐብይ አህመድ ሰራዊት በአጠመበት ግንባር ሁሉ እየተማረከና ሙትና ቁስለኛ እየሆነ መበተኑ በፈጠረበት ስጋት በዐብይ አህመድ ትዕዛዝ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ የሥርዓቱን ተራ ሽፍታነት የሚያሳይ ነው።  የንጹሃን አርሶአደሮችን ቤት በከባድ መሳሪያ ማፍረስና ማቃጠል፥ ከግንባር ፈርጥጦ ያመለጠው ሰራዊት ከተማ ላይ ንጹሃንን መረሸን ዋነኛ ተግባሩ በማድረግ የጦር ወንጀል መፈጸሙን ቀጥሏል። እያንዳንዱ በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየፈረሰ ያለው የአርሶ አደር ቤት እና ቤት ለቤት የመረሸን ተግባር በማስረጃ መሰነዱ ይቀጥላል።  ይህ የወንጀል ፋብሪካ የሆነ አገዛዝ ምን እየፈጸመ እንደሆነ ዓለም ሊያውቀው ይገባል።

አፋብን| ቴዎድሮስ ዕዝ የካቲት 01/2018 ዓ.ም __፩ 201ኮር ድልን ተቀዳጀ። በአማራ ህዝብ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ቆርጦ የተነሳው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በየግንባሩ እያስመዘገበ ያለው ድል ቀጥሏል። የአገዛዙ ሠራዊት በጀግኖች ፋኖዎቻችን እና ነቅቶ በታጠቀው አርሶ አደር ክንድ ክፉኛ እየተመታ መሣሪያውን እያስረከበ ይገኛል። በሰከላ ግንባር፦ ከአበስከን ወደ ብር አዳማ ሲንቀሳቀስ የነበረው የብልጽግና ሠራዊት በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆች አይቀጡ ቅጣት ደርሶበታል። ሠራዊቱ ካረፈበት ጦር ሠፈር እስኪገባ ድረስ በፋኖ ብርቱ ክንድ ሲገረፍና ሲናዘዝ ውሏል።    በአርሶአደሩ እና አዳኞቹ መሳሪያን መማረክ የቻሉ ሲሆን አረመኔው ሰራዊት ደግሞ የደረሰበት ሽንፈት ሕዝብ እንጨፍጭፍ አናስጨፈጭፍም በሚሉ መካከል በተነሳ ተኩስ ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። __፪ 102ኛ ኮር በርካታ የአገዛዙ ሀይልን በደፈጣ ጥቃት  ተደመሰሰ         ➡️1ኛ በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም  ከፍኖተ ሰላም  ወደ ጂጋ ሆዳንሽ እንቅስቃሴ የነበረ የጠላት ሃይል ላይ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እና 1ኛ ሻለቃ ከንጋቱ  12:00 ሰዓት ላይ በወሰዱት  የደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የጠላትን ሀይል ተደመስሷል። ዘራፊውና ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ወራሪ ሀይል መነሻውን ከፍኖተሳላም ወደ ሆዳንሻ በሚንቀሳቀስበት ሰአት በጦር ጠበብቶቹ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር በወሰዱት የሁለቱ ሻለቃዎች የተቀናጀ የደፈጣ ጥቀታ ዘጠኝ(9) የጠላት ሀይል የተደመሰሰ ሲሆን ከ15 በላይ የጠላት ሀይል ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።        ➡️2ኛ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ክ/ጦር በቀን በቀን 29/05/ 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00  ከፈረስቤት ከተማ ወደ ዳማ ቀጠና መንቀሳቀስ ላይ በነበረው የጠላት ሀይል ላይ በሻለቃ 3 በወሰደችው መብረቃዊ ጥቃት ታላቅ ጀብድ ፈፅሟል።ወደ ዳማ ማርቆስ የመጣውን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት ሲያስጨንቁት የዋሉ ሲሆን አስከሬኑን ሳያነሳ ወደ መጣበት ፈርጥጧል። ይህ በእንዲህ አንዳለ  የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99 ክ/ጦር የሻለቃ 4 ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከሻለቃ 3  ጋር በመናበብ ወደ ደጋ ዳሞት ፈረስ ቤት ከተማ በመግባት በጠላት ኃይል ላይ በወሰዱት ጥቃት በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።             አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            የካቲት 01/2018 ዓ.ም

ሰበር የድል ዜና‼️ ደቡባዊ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከጠዋቱ 2:20 እስከ 10:00 ሰዓት በተደረገ ው*ጊያ የአብይን ሰራዊትን በመደምሰስ ፋኖ ሙሉ በሙሉ ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማን ተቆጣጥሯ
ሰበር የድል ዜና‼️ ደቡባዊ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ከጠዋቱ 2:20 እስከ 10:00 ሰዓት በተደረገ ው*ጊያ የአብይን ሰራዊትን በመደምሰስ ፋኖ ሙሉ በሙሉ ስማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማን ተቆጣጥሯል !! አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ✅

#ኑ_ፋኖን_ተቀላቀሉ‼️ ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም የአድማ ብተና አባላት ከኦህ
#ኑ_ፋኖን_ተቀላቀሉ‼️ ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል:: ከዚህ ጋር ተያይዞም የአድማ ብተና አባላት ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር ሆነን ወገናችንን አንወጋም በማለት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 1/2018 ዓ.ም

ከአርባያና ከደጎማ የፈረጠጠው የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ክፉኛ ተመታ። ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ጎንደር ብርጌድና ጥቁር አንበሳ
ከአርባያና ከደጎማ የፈረጠጠው የአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ክፉኛ ተመታ። ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ.ም የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ጎንደር ብርጌድና ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ድል በር ብርጌድ ከቃሃሪ እስከ ጭንጫየ የሸፈነ አውደ ውጊያ በማድረግ ጡት ቆራጩን የአብይ ኃይል ሙት ቁስለኛና ምርኮኛ ተደርጓል። በድንገት ከፍተኛ ምትን ያስተናገደው ጠላት እግር አውጭኝ ፈርጥጦ ማክሰኝት ከተማ ሊገባ ችሏል። ➧ በዚህ ውጊያ ከተገኙ ድሎች መካከል ➧ 08 የሞተ /3 መከላከያ ፣ 5ሚሊሻ / ➧ 02 የተማረከ /1 ፖሊስና 1 ሚሊሻ / በድል በር ብርጌድ ተመርከዋል። -- ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል እስከ ወዲያኛው በክንደ ፈርጣማዎቹ ፋኖዎች እንዲያሸልብ ተደርጓል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን። አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አብነት ሞላ ጥር 01/2018 ዓ.ም

አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ገድል ተሰርቷል!! አገዛዙ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት በሸዋ አማራ ላይ የሰነዘረው ጥቃት ከሺፏል። በሸዋ ሁሉም ቀጠናዎች በሚባል ደረጃ የተጀ
አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ገድል ተሰርቷል!! አገዛዙ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት በሸዋ አማራ ላይ የሰነዘረው ጥቃት ከሺፏል። በሸዋ ሁሉም ቀጠናዎች በሚባል ደረጃ የተጀመረው መጠነ ሰፊ ማጥቃት በሰራዊታችን ጠንካራ ክንድ ተመክቷል።የፋሺስቱ አገዛዝ ከምስራቅ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አስተዳደር ከተቋቋመው የገዳ ኮማንዶ እና የሪፐብሊክ ኮማንዶ እንድሁም ባህር ሃይል በማዝመት በመላው ሸዋ ከፍተኛ ወረራ እየተካሄደ ሲሆን የአፋብን ከፍተኛ አመራር ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት ተጨባጭ የአፀፋ እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረግ!! ሰሞነኛው የብልፅግና አገዛዝ በሁሉም የአማራ ቀጠናዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል ስለሚችል ሁሉም በየደረጃው ያለው አመራር ጠንካራ ዝግጁነት ሊኖረን ይገባል!! መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ያሸንፋል!!

የኦሮሙማ ስራ ሲገለጥ ፀረ ገዳማውያን ፀረ መነኮሳት ፀረ ቤተክርስቲያን ፀረ ሰው ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ ። እሔው እንሂ መናኒያን አባት አሁን ምን አድርገው ነው ? የሳዊሮስ ስራ ሲገለጥ እሔው ነው
+1
የኦሮሙማ ስራ ሲገለጥ ፀረ ገዳማውያን ፀረ መነኮሳት ፀረ ቤተክርስቲያን ፀረ ሰው ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ አማራ ። እሔው እንሂ መናኒያን አባት አሁን ምን አድርገው ነው ? የሳዊሮስ ስራ ሲገለጥ እሔው ነው🥺😥 📝አሳዛኝ ዜና በአሰቦት ገዳም 👉 እጅግ ልብ የሚሰብር ሀዘን ጥር 28,  2018ዓ.ም አሰቦት ገዳም በዓታቸው ውስጥ ተገድለው የተገኙት ባሕታዊ አባ መብራቱ ፣ ለብቻቸው ዘግተው የሚኖሩ ባሕታዊ ነበሩ ፣በመሳሪያ ተገድለው ነው እንደተገኙ የመረጃ ምንጮች ከቦታው አድርሰውናል ፣ 👉 ይህን ድርጊት ማን ፈጸመው ? ግድያው  በር ዘግተው ለቤተክርስቲያን እና ለሀገር በሚጸልዩ  መናንያን ላይ መሆኑ ልብ ይሰብራል፣ ይህ ለምንደኞች ካህናት በሀገርም በውጭም ላሉ ምን ላይመስላቸው ይችላል ፣ ግን እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣል ፣ የአባታችን በረከት በሁላችን ላይ ይደር 🙏

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር "ሰባት ለሰባ" ክፍለ ጦር በኢፍራታ ግድም ወረዳ ድል ተቀዳጀ!! ​በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስር የሚንቀሳቀሰው የደቡብ አማራ ቀጠና፣ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር "ሰባት ለሰባ" ክፍለ ጦር አናብስቶች በኢፍራታ ግድም ወረዳ፣ ፈርድ ውሃ ቀበሌ ላይ በወሰዱት ወታደራዊ እርምጃ ድል አደርጉ። ​ከአንድ ወር በፊት በግፍ የተሰዋውን የክፍለ ጦሩን ቃኘ መሪ ​አርበኛ ሸጋው ግርማን በማስታወስ የክፍለ ጦሩ ንስሮች ዛሬ ጠዋት 12:00 ስዓት በፈርድ ውሃ ቀበሌ ላይ ካምፕ መሽጎ ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ በነበረው የአረመኔው አብይ አህምድ ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻ ኃይል ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር ሙትና ቁስለኛ በማድርግ ድልን ተጎናፅፋዋል። በመሆኑም አይቀጡ ቅጣት የተቀጣው የብአዴን ቅጥርኛ ሚሊሻዎች ላይ ሙትና ቁስለኛ አድረገው የተወሰኑት ደግሞ እስከ ወዲያኛው መሰናበታቸው ተረጋግጧል፦ 1,​ሞገስ ክፈተው 2,​ቸርነት አደፍርስ 3,​ቻለው ጥላሁን 4,​ዳምጠው ጌቱ እና 3 ሶስት በስም ያማይታወቁ ባንዳ ሚሊሻወች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል ​የተማረኩ የጠላት የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ​1 ባለ ሁለት እግር (2) ሁለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ​2 , አንድ m14 መሳሪያ ከሙሉ ትጥቅ ጋር በመማረክ ደማቸውን መልሰዋል። በመጨረሻም ​የአካባቢውን ህዝብ ለአንድ ዓመት ያህል በከባድ እንግልትና በዝርፊያ ሲሰቃይ የነበረው የፈርድ ውሃ ቀበሌ ህዝብ በታልቅ ክብር ፋኖን እንኳን መጣችሁልን ብሎ አብልቶ አጠጥቶ አጋርነቱን አሳይቷል። የወገኖቻችንን ደም በከንቱ እንደፈሰሰ አይቀርም" በሚል ቃል በገቡት መሰረት፣ የጥፋት ኃይሎችን የማጽዳት ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ​ድል ለአማራ ህዝብ! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ይካቲት 01/06/2018 ዓ.ም

ውድ ቤተሰቦቻችን የፊስቡክ አካውንት በእየግዜው እየተዘጋ ተቸግረናል አዲሱን ፔጃችን ይወዳጁን!! https://www.facebook.com/share/1AbHjgfmgK/

ቀን፦01/06/2018 ዓ/ም አስቸኳይ መግለጫ አፋብን ሰ/አ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ለአገዛዙ እጅ በሰጡ(ምህረት በገቡ)የፋኖ አባላትን በተመለከተ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ውስጥ ከገባ 30 ወራትን አስቆጥሯል። በመሆኑም በዚህ የትግል ወቅት ብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን እያስተናገደ እዚህ ላይ ደርሷል። የአማራ ፋኖ የነበሩበትን ውስጣዊ ችግሮች በተለይም አንድ መሪ ያለው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ግቦችን ማሳካት የሚችል አማራዊ ድርጅት ለመመስረት ፈተናዎች ገጥመውን የቆየ ቢሆንም ድርጅታዊ ምስረታው በፅናትና በማጥራት እውን ሊሆን ችሏል። በዚህም እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን እያልን የዚህን ድርጅታዊ ምስረታ ተከትሎ በዝርፊያ፣እገታና ሌሎች ወንጀሎችን በመፈፀም ትግላችንን ሲያንቋሽሹ የነበሩ ፋኖ ያልሆኑ የፋኖን ለምድ የለበሱ ወደ ግብር አባታቸውን በምህረት ስም እጅ መስጠታቸው ለድርጅታችን መልካም ቢሆንም እነዚህ እኩይ አላማ ያላቸው ግለሰቦችንና ቡድኖችን በተመለከተ አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ተፈፃሚ የሚሆን የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። 1. ታጋይ በመምሰል የአመራርነት ቦታ ላይ የነበሩትን በተመለከተ 1.1.የኮር፣የክ/ጦር፣የብርጌድ አመራር የነበረ 1.2.ከላይ በተ.ቁ "1.1" የተቀመጡ አመራር የነበሩ የተቋም የቡድን መሳሪያ ለጠላት ያስረከበ/ቡ 1.3.ለሁለተኛ ጊዜ የአማራን ህዝብ ክደው እጅ የሰጡ 1.4.የፋኖ የሃለፊነት ቦታ ላይ ተቀምጦ ንፁሀንን የገደለ የዘረፋ ሰንሰለት ዘርግቶ ህዝብን ሲያሰቃይ የነበረ ከላይ በተ.ቁ 1 ውስጥ ከ(1.1-1.4 )የተገለፁትን ክህደት የፈፀመ ባንዳ ለምድ ለባሽ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። የተወሰደውን የተቋም ንብረት አንዳች ሳይጓደል እናስመልሳለን። እነዚህን አካላት ከጡት ቆራጩ መንግስት ነኝ ባይ ጋር ያደራደረ የቤተሰብ አባላት፣ የሀገር ሽማግሌና የሀይማኖት አባት ላይም ተመጣጣይ እርምጃ እንወስዳለን። 2.የፋኖ አመራር ነን በሚሉ ባንዳዎች ተታልለው/ተሸውደው በተወሰዱ/እጅ የሰጡ የፋኖ አባላትን በተመለከተ 2.1አባሉ የነብስ ወከፍ ንብረት የወሰደም ይሁን ያልወሰደ ንብረቱን በመያዝ በቀጥታ ለኮር አመራሮች ብቻ በማሳወቅና በማግኘት አስፈላጊውን የታሕድሶ ስልጠና ይወስዳል ይህን ካላደረገ እርምጃ ይወሰድበታል። ይህንን ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች ተላልፎ ምህረት የገቡትን/እጅ የሰጡትን ግለሰቦችና ቡድኖች ከኮሩ ትዕዛዝ ውጭ የሚቀበል ክ/ጦር፣ብርጌድ፣ሻለቃ፣ እንዳይኖር እያሳወቅን ከዛሬ ጥር 27/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። ➜በመጨረሻም መላው የድርጅታችን አመራሮችንና አባላት፤ የክ/ጦር አመራሮች፣ታጋዮቻችንና የትግላችን ደጋፊዎች ትግላችን መራራ ቢሆንም በተፈጠረው አንድነት ደስ እንዳላችሁና ድላችን ቅርብ መሆኑን ተረድታችሁ በአጋርነታችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። @ልባሙ ፋኖ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጎንደር --አማራ --ኢትዮጵያ የካቲት 01/2018 ዓ.ም ልባሙ ፋኖ @highlight #facebookviral

#ጠላት_በደፈጣ_ተመታ‼️ በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ ከፍኖተ ሰላ
#ጠላት_በደፈጣ_ተመታ‼️ በዛሬዉ እለት በቀን 01/06/2018 ዓ.ም  የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ እንዲሁም 1ኛ ሻለቃ ከፍኖተ ሰላም ወደ ጂጋ ሆዳንሽ ከተማ ሲገባ የነበረን ሃይል ከንጋቱ  12:00 ሰዓት አካባቢ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጠላትን ሀይልን መደምሰስ እና ማቁሰል ተችሏል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!         ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ 77ተኛ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ 01/ዐ6/2018 ዓ.ም

የደጋው መብረቅ ኮር ቀኛዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለሶስተኛ ዙር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመረቁ‼️ አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር ለበርካታ ወራቶች ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ፋኖዎች የካቲት 1/2018 ዓ/ም የኮሩ አመራሮች በተገኙበት መድረክ ላይ አስመርቋል! ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በርካታ እግረኛ ፋኖዎችን ለሶስተኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን በዚህ የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የደጋው መብረቅ ኮር የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አርበኛ ብርሃን አረጋ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የእንኳን ደሳላችሁ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን "የአማራ ህዝብ የብረት አጥር ናችሁ!! የአማራን ህዝብ ጥላት የሚያጠቃው በእናተ አስከሬን ላይ ተረማምዶ ነው። ስለዚህ እናተ የአማራ ህዝብ መታፈሪያና መከበሪያ የብረት አጥር ናችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት ያስተላለፈ ሲሆን:: የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ መኩሪያ አጋዡ(መምህሩ) "እናተ አማራ ናችሁ! በአማራዊ የሞራል ልዕልና ቁማችሁ የተገኛችሁ!" በማለት ለተመራቂዎች መልክት አስተላልፈዋል። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ በለጠ መኩሪያው በበኩላቸው ለተመራቂ ፋኖዎች የአማራን ህዝብ ነፃ የማውጣት ሀላፊነት የዚህ ተመራቂ ጭምር ነው ሲሉ ለተመራቂዎች አሳስበዋል። በዚሁ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የአሰልጣኞች ምስጋናና እየፈፀሙት ላለው ህያው ገድል የሽልማት ፕሮግራም የተበረከተ ሲሆን፤ይህ የአሰልጣኞች ማነሻሻ የምስጋና እውቅና ለቀጣይ የተልዕኮ መሰላል ይኖን ዘንድ ታስቦም የተደረገ ነው። እየተዋጋን እንሰለጥናለን እየሰለጠን እንዋጋለን! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ እዝ የካቲት 1/2018 ዓ.ም 01/ዐ6/2018 ዓ.ም

ሲነግሩት ያልሰማን እያየ ቅበረው ✊ ደጋ ዳሞት - ያስተፋል ሀሞት ከፈረስ ቤት ከተማ ከሌሊቱ 11:20 ጀምሮ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ለመክበብ ቢሞክርም
+1
ሲነግሩት ያልሰማን እያየ ቅበረው ✊ ደጋ ዳሞት - ያስተፋል ሀሞት ከፈረስ ቤት ከተማ ከሌሊቱ 11:20 ጀምሮ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ለመክበብ ቢሞክርም በክንደ ነበልባሎች ቀምሶ ሬሳውን እንኳን ሊቀብር ቀርቶ ቁስለኞችን ትቶ  ከቆፈረው ጉድጓድ ገብቷል። ቀጣይ በዜና ደግሞ የአሳምነው አናብስቶች ድልን እንመለሳለን እስከዛ ሸርና ጆይን በማድርግ አጋርነታችሁን አሳዩን

አገዛዙ የግንኙነት መስመሮችን ዘግቶ ሲቪሊያንን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል የካቲት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከአፋብን የተሰጠ መግለጫ ትላልቅ ከተሞችን የሚያገናኙ አውራ መንገዶችን በመዝጋት በህዝቡ ላይ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ሲያደርስ የቆየው የብልፅግና አገዛዝ በከባድ መሳሪያወች ሲቪሊያንን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛል። ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት በጀኔራል አድማሱ አለሙ እና በጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ የሚመራው 11ኛ ዕዝ እና ቀጠናው ላይ የተሰማራው ሪፐብሊካን ጋርድ ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌወች ድሮን፣ ቢኤም እና መድፍን በመጠቀም ከ 100 (አንድ መቶ) በላይ ንፁሃንን በግፍ ጨፍጭፏል፤ ከአርባ በላይ መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ አውድሟል፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳትን ገድሏል።በዚህ ጥቃት የአንድ ቤተሰብ ስድስት አባላትም በቤታቸው ባሉበት ተጨፍጭፈዋል። በተመሳሳይ ግዜ ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳም የአገዛዙ ሰራዊት ከኦሮምያ ልዩ ዞን ታጣቂወች ጋር በመቀናጀት በፈፀመው ጭፍጨፋ በበርካታ ሲቪሊያን ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በማድረግ ከ20 በላይ ንፁሃንን ገድሏል፤ በርካታ ቤቶችን አውድሟል፤  እንዲሁም የቤት እንስሳትን ዘርፏል። በምስራቅ ጎጃም ሸበል በረንታ ወረዳም ምንም አይነት ውጊያ በሌለበት የአርሶ አደር መንደሮችን በመድፍ ደብድቧል። በመሆኑም ይህ አረመኔ አገዛዝ እንደ ህዝብ ያወጀብንን የዘር ማጥፋት ጦርነት መመከት ብሎም መቀልበስ አማራጭ የሌለው የትውልዱ ግዴታ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ መላው ህዝባችን ለህልውናው በጋራ እንዲታገል ጥሪ እናቀርባለን። በተጨማሪም የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን በሰሜን ሸዋ፣ በምስራቅ ጎጃም እና በደቡብ ወሎ አዋሳኝ ቦታወች ሙሉ በሙሉ በመዝጋት አረመኔው አገዛዝ በንፁሃን ላይ ያነጣጠሩ ተመሳሳይ ወንጀሎችን በመፈፀም ላይ ስለሆነ መሠል ጥቃቶችን ለመከላከል ህዝቡ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። አገዛዙ የዓለም አቀፍ የጦርነት ህግ መሰረታዊያን የሆነውን ንፁሃንን ከጥቃት የመጠበቅ ግዴታን በመተላለፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ በመሆኑ የአፍሪካ ህብረት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፣ የተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ዘር ማጥፋት የሚገዳችሁ እና ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ ይህንን የጦር ወንጀል በመቃወም የሰብአዊነት ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ