ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 954
مشترکین
+22224 ساعت
+3937 روز
+1 35930 روز
آرشیو پست ها
ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የፋኖ አመራር ቤተሰቦችን መዝረፍ ማሰር ማሳደዱንና ማፈናቀሉን አጠናክሮ ቀጥሎበታል‼️
አህመድ ሱማሌው ይባላል የባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረውና የምስራቅ አማራ ኮር 1 ዘመቻ መሪ የሆነው የአርበኛ እንድሪስ ጉደሌ ታላቅ ወንድም ነው:: የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ካድሬዎች የትውልድ ቀየውን አስለቅቀውት ወደ አዲስ አበባ ሄዶ ህይወትን እየገፋ ባለበት ፋሽስቱ አገዛዝ አዲስ አበባ ላይ አፍኖ 1700000 (አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሽ) ብር ቀምተውታል::
የአርበኛውን ወንድም የአገዛዙ ሰዎች አዲስ አበባ አፍነው በግፍ ከተቀበሉት ገንዘብ በተጨማሪም አሁንም ጦር ሃይሎች አስረው እየደበደቡትና ግፍ እየፈፀሙበት ይገኛል:: ይህ የሃገሪቱ መዲና ላይ የተፈፀመ ተግባር የብልፅግናን አገዛዝ አገር አቀፍ ዘረፋና ወንጀል በግልፅ የሚያሳይ መሆኑን ያሳበቀ ነው::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ትግላችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
02/ዐ6/2018 ዓ.ም
አፋብን የሚያቆመው እንደለለ አስመሰከረ ።
የደቡብ ጎንደር ጀግኖቻችን ዛሬ ብልፅግናን እንደ ተልባ እያንጫጩት፣ እንደ ኑግ እየወቀጡት ሲውሉ ከአያሌው መንበረ እስከ ይርጋ ሲሳይ፣ ከአረጋ ከበደ እስከ ተመስገን ጥሩነህ ድረስ እለቅሶ ላይ ናቸው እያሱ አባተ አፈረሰው የተባለው ፋኖ ብልፅግናን አፈራርሶ ከብሬን እስከ ዲሽቃ ፣ከክላሽንኮብ እስከ ስናይፐር ፣ከብር እስከ መኪና ተረክቦ በቁሙ ገሎታል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄን (አፋብን ) ምድር ላይ የሚያቆመው ምንም ሀይል እንደለለ ከጎንደር እስከ ሸዋ ከወሎ እስከ ጎጃም ፣ ከጋንቤላ እስከ ወለጋ እያሳየ ምላሳሞች እየጮሁ ስራዎቻችን በተግባር እያስመሰከረ ጉዞውን ሲቀጥል ዛሬ የካቲት 2/2018 በመቅደላ አደባባይ ዘረ ውባንተዎቹ የአባቶቻቸውን ታሪክ በመድገም ለሸዋ ጓዶቹ እየመጣን ነው ፣ ለወሎዎቹ ጠብቁን አብረን እንጓዝ ፣ለጎጃሜዎቹ ባህር ዳር እንዴት ናት መልዕክት አስተላልፈው ውለዋል ።
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫ፦
ለሁለት ዓመት ከሰባት ወር ገደማ በአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ ሲቀጠቀጥ የከረመኔው አረመኔ ስርዓት፤ የፋኖን ሀይል ‹‹አዳክሜያለው›› እያለ የከሰረ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ ቢከርምም፤ ሰሞኑን በሁሉም የአማራ ቀጠናዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ይገኛል።
ነጣጥለህ ምታው በሚል መርህ ሰሞኑን በሸዋ ወንድሞቻችን ላይ የተደራጀና የተጠናከረ ውጊያ ከፍቶ ንጹሀንን ዒላማ ያደረገ ጭፍጨፋ ቢፈጽምም፤ አይበገሬዎቹ የሸዋ አናብስቶች የስርዓቱን ኃይል እንደ ዘላን ላም ማርከው እየነዱ አሳይተውናል።
በተመሳሳይ መልኩ በጎንደር፣ በጎጃም እና በወሎ ቤተ አማራም ከፍተኛ መነቃቃትና ድርብርብ ጀብድ እየተሰራ የአረመኔው ስርዓት ዘቦች እየተገረፉ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም፤ የፋኖ ብርቱ ክንድ የበረታበት ሥርዓት፤ ሰሞኑን በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በሚደረገው ውጊያ፤ አንዳንድ ከተሞችን በውጊያ የተወሰኑትን ደግሞ ያለ ውጊያ እየለቀቃቸው ይገኛል።
ለምን ከተሞችን እየለቀቃቸው እንደሚወጣ ግልጽ የሆነ ነገር ባይኖርም፤ የተለያዩ መላምቶች ግን እየተሰጡ ይገኛሉ። የስርዓቱ ኃይል እየለቀቀ የሚወጣበት ምክንያት ተደርጎ እየተነገረ ያለው፤ በዋናነት የህውሐትና የሻዕቢያ ጥምር ሐኃል በሰሜን ምዕራብ አማራ በኩል ተከዜን ተሻግረው ለወረራ ሊመጡ ነው የሚል እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በምንም ይሁን በምን፤ እየተለቀቁ ያሉ ከተሞች እጣ ፋንታ ጉዳይ በአማራ ፋኖ እጅ ሆኗል። እነዚህ አሁን የስርዓቱ ኃይል እየለቀቃቸው ያሉ ከተሞች ስርዓቱ ይዞ በሚያስተዳድርበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ስርቆት፣ ዘረፋ፣ ግድያ፣ አስገድዶ መደፈር፣ ሙስና እና ሌሎች ብልሹ አሰራሮች በስርዓቱ ጋሻ ጃግረዎች ሲፈፀምባቸው የከረሙ ከተሞች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ለሚኒሻ ደመወዝና ለመከላከያ ድጎማ የሚል ድርብርብ ወጭ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ሲያስተናግዱ የኖሩ አካባቢዎች ናቸው። ይህ ህጋዊና ህገወጥ ሌቦች ሲመዘብሩት የኖረ ማህበረሰብ፤ እንደ ገጠሩ ማህበረሰብ እና ፋኖ እንደተቆቆጣጠራቸው ከተሞች ነፃነቱን አግኝቶ የሚኖርበትን ቀን ሲናፍቅ የቆየ ማህበረሰብ ነው።
በመሆኑም ወደ ከተማው የሚንቀሳቀስ የፋኖ ኃይል በሙሉ የሚያደርገው እንቅስቃሴ፤ የተጠና እና የማህበረሰብ ልጅነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ግድ ይላል። በመሆኑም ከተሞችን በምንይዝበት ወቅት፤ መተግበር ያለባቸው መመሪያዎችና ጥሪዎች እንደሚከተለው ይቀርባል፦
1/ እነደሚታወቀው ቀጠናው ከ2008 ዓ.ም ሃምሌ ወር ጀምሮ ለተከታታይ አስር ዓመታት ያለ ዕረፍት በጦርነት እየወደመ የሚገኝ አካባቢ ነው። በመሆኑም ለፋኖ መገልገያ የሚውል የስርዓቱ ሐብት ካለ በተቋምና በበላይ አመራር ይሁንታ መሰረት መጠቀም የማይከለከል ሆኖ፤ ከዚህ በዘለለ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ በእሳት ማቃጠል፣ማውደምና መዝረፍ ግን ፍፁም ለመንግስትነት ከሚታገል ኃይል የማይጠበቅ ተግባር መሆኑ ታውቆ፤ አንድም ንብረት በቃጠሎና በዘረፋ እንዳይወድም።
2/ በግል ቂም ተነሳስቶ ያለ ተቋም እና የበላይ ኃላፊ እውቅና፤ ማህበረሰብን አስሮ ማንገላታት ፍፁም የተከለከለ ነው። የተለየ የግል ጉዳይ ያለው አባል ካለ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ክስ መስርቶ አስፈርዶ በተቋሙ ማስቀጣት ይቻላል።
3/ ተቋምና የበላይ አካል በማያውቀው መልኩ፤ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር (አስገድዶም ሆነ በፈቃደኝነትም ቢሆን) ገቢ መሰብሰብ ፍፁም የተከለከለ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘና ከታመነበት፤ አስቻይነቱ በተቋም ተገምግሞ ህጋዊነቱን ጠብቆ መፈፀም ይቻላል።
4/ ለግዳጅ ወይም ለሌላ የግል ስራ በተቋምና በበላይ ኃላፊ የተፈቀደለት አካል ካልሆነ በስተቀር፤ ከተማ በማንኛውም ሰዓት ገብቶ መዝረክረክ ፍፁም የተከለከለ ነው። እንደ አስፈላጊነቱ ከከተማ ቅርብ እርቀት ተንቀሳቃሽ ካምፕ አዘጋጅቶ መቀመጥ ይቻላል።
5/ ሥርዓቱ የለቀቃቸው ከተሞች ላይ የድሮን ጥቃት ሊኖር ስለሚችል፤ ማህበረሰቡም አባሉም ባለመሰባሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ።
6/ለሥርዓቱ አገልጋዮች በሙሉ ለሚሊሻ፣ ለአድማ ብተና፣ ለመከላከያ ሰራዊት አባላትና በየደረጃው ላላችሁ የሲቪል አመራሮች በሙሉ፤ አስኪ በቃን ተገዳድለናል፤ በየቀኑ ዓላማ ቢስ ሞት ሞታችኋል፤ በእርግጠኝነት ለመማር ዝግጁ ከሆናችሁ እስካሁን በበቂ ሁኔታ ተምራችኋል፤ በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ መገዳደል አቁመን በጋራ እንድንታገል የተለመደ ጥሪያችን እያቀረብን፤ መታገል ለሚፈልግ በፍላጎቱ እንዲታገል ለማይፈልግ ደግሞ መደበኛ ኑሮውን እንዲኖር እንደምንፈቅድ ማሳስብ እንወዳለን።
7/ለማህበረሰቡ በሙሉ በፋኖ ስም ለሚንቀሳቀስ አባላችን በሙሉ የተለመደውን ትብብር ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አላስፈላጊ የሆነ ድርጊት የሚፈፅም አባል ሲኖር ግን አስፈላጊውን ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩ እና ወንጀልን በጋራ እንድንከላከል ማሳሰብ እንወዳለን።
8/ከበላይ ዕዝ ጋር የጋራ ኮሚቴ በማዋቀር ስራችን የጋራ በማድረግ የምንስራ ይሆናል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ
የካቲት 02 ቀን 2018 ዓ.ም
ጎንደር-አማራ- ኢትዮጵያ
206ኛ ኮር በመተከል አውራጃ ፓዊ ወረዳ ቀበሌ 21 በካምፕ ውስጥ በተጠረነፉ ሚኒሻና አድማ በትኖች ላይ በተፈፀመ የከበባ ጥቃት 13 ክላሽ ማርኳል።
===================================
በመተከል አውራጃ ፓዊ ወረዳ ቀበሌ 21 በካምፕ በተጠረነፉ ሚኒሻና አድማ በትኖች ላይ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር እና 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ 3:00 ሰዓት ባደረጉት አውደ ውጊያ ከ50 በላይ ክላሽ 2 ብሬን የተማረከ ሲሆን የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ 13 ክላሽና 200 ጥይት የያዘ የብሬን ሸንሸል ማርከዋል።
እጅግ ፈጣን በሆነው አውደ ውጊያ የጠላትን አስክሬን ያዝረከረኩት 105ኛ እና 206ኛ ኮር በካምፑ የተጠረነፈውን የጠላት ኃይል ሙሉ ለሙሉ ደምስሰውታል። በሔዱበት ጠላትን በማናዘዝ አኩሪ ተጋድሎ የፈፀሙት የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ የጠላትን ጠንካራ ምሽግ በመስበር አውደ ውጊያው በድል እንዲጠናቀቅ የተሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት ተወጠዋል።
ድንበር አልባ ተንቀሳቃሽ ጦር የገነባው 206ኛ ኮር በዛሬው አውደ ውጊያ ይህንን ጠንካራ ወታደራዊ አቅም ያስመሰከረ ሲሆን ከ105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር አሀዶች ጋር አኩሪ ድል ያስመዘገበችው የ34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ መስዋትነት በመክፈል ጭምር ከጠላት ጉሮሮ 13 ክላሽ ጨብጣለች።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ጀኔራሎች ጭኖ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ጥቃት ተሰነዘረበት።
ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆነችዉ እሸት ክፍለ ጦር ጀኔራሎችን እና የብልፅግና ተላላኪ የሲቪል አመራሮችን አሳፍሮ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ ጠቃት ሰነዘረችበት።
ጀኔረሎቹ እና የሲቪል አመራሮቹ ከ ሰቆጣ ከተማ የቆዩ ሲሆኑ ወደ ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ)ቀበሌ ለመግባት በ 2 ክፍለ ጦር ታጅበዉ እየመጡ እያለም በ ሀይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እየተገረፈ እንደምንም ኤሪፖርቱ ላይ ቢደርሱም እሸት ክፍለ ጦርም ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጋለታለች።
ጀኔራሎችን ጭኖ የነበረዉ አንቶኖፉ በመጀመርያዉ በረራ ትንኩሳ ሲደረግበት አቅጣጫዉን ስቶ የበረረ ሲሆን በድጋሜ ተመልሶ ኤሪፖርቱ ጋር ያረፈ ቢሆንም በሁለተኛዉ በረራ በከባድ መሳርያ እገዛ እንደምንም ብሎ ያለፈ ሲሆን እግረኛ ሰራዊቱ ከከባድ መሳርያዉ በተጨማሪ በ 3 አቅጣጫ ቢዘረጋም በአንደኛዉ አቅጣጫ ዘርግቶ የነበረዉ ግትልትል ሰራዊት በተለምዶ ሳይና በር ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል።
ትንቅንቁም በዛሬዉ ዕለት ማለትም የካቲት 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን ብዛት ያለዉ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሁኗል።
እሸት ክፍለ ጦር ከላሊበላ ኤሪፖርት(ሽምሽሃ) ቀበሌ በ10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ እምትገኝ ክፍለ ጦር መሆኗም አይዘነጋም።
በመጨረሻም የእሸት ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌም ''የአብይ አህመድ አፈ ቀላጤዎች በቅርቡ ከ ቱርክ እና ከአረብ አገር በ ክራይ በመጡ ድሮን እና ጀቶች በአየር ኃይል 90ኛ አመት ላይ ትርኢት ሲያሳዩ ''ሰማዩ የኛ ነዉ'' ያሉ ቢሆነም ሰማዩም ምድሩም የናንተ ሳይሆን የኛ ነዉ ሲል ተናግሯል''።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
❗️የሸዋ መረጃ❗️
ብልፅግና በሸዋ ቀጠና :-
1: የሪፐብሊካን ጋርድ 2 ክፍለጦሮች
2: የአየር ወለድ እና ኮማንዶ 6 ክፍለጦሮች
3:- የባህር ኃይል ኮማንዶ 1 ክፍለጦር
4:- የ6ኛ ዕዝ አካል የሆኑ እግረኛ ሁለት ክፍለጦሮች እንሳሮ እና በጅሩ በኩል።
5. እንዲሁም ከአድማ ብተና እና ሚሊሻ አሰማርቶ የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ በቀጠናው የስልክ ኔትወርክ በማጥፋት :-
6. ደብረዘይት ይገኝ የነበረውን የደቡብ ዕዝ አንድ ኮር ከ3ኛ መካናይዝድ ጋር በማቀናጀት በአፋር ዞሮ በከሚሴ በኩል ወደ ሸዋ ቆላማ ቦታዎች አስገብቷል።
7. የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ታጣቂዎችን ጨምሮ የዞኑን ሚሊሻዎች ወደ ራሳ፣ ቀወት፣ኤፍራታ ግድም እና ማጀቴ አካባቢ ሰምሪት ሰጥቶ እየተዋጋ ይገኛል።
ይሄ ተስፋ የቆረጠ የመከላከያ ሰራዊት የአፋብን ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጦር አዝምቶ አበክሮ እየሰራ ነው። እነሱን መደም*ሰስ ፍላጎት ቢኖረውም የገባው ሰራዊት ለራሱ እየተደ*መሰሰ እየተ*ማረከ ይገኛል።በአገዛዙ ላይም ትልቅ መደናገጥ ፈጥሯል።
ጋዜጠኛ አደራ ዘላለም(ባዶ እግር ሚዲያ)
ጀኔራሎች ጭኖ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ በአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ጥቃት ተሰነዘረበት።
ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳምነዉ ኮር ክንፍ የሆነችዉ እሸት ክፍለ ጦር ጀኔራሎችን እና የብልፅግና ተላላኪ የሲቪል አመራሮችን አሳፍሮ ሲበር በነበረ አንቶኖፍ ላይ ጠቃት ሰነዘረችበት።
ጀኔረሎቹ እና የሲቪል አመራሮቹ ከ ሰቆጣ ከተማ የቆዩ ሲሆኑ ወደ ላሊበላ ኤሪፖርት (ሽምሽሃ)ቀበሌ ለመግባት በ 2 ክፍለ ጦር ታጅበዉ እየመጡ እያለም በ ሀይሉ ከበደ ክፍለ ጦር እየተገረፈ እንደምንም ኤሪፖርቱ ላይ ቢደርሱም እሸት ክፍለ ጦርም ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጋለታለች።
ጀኔራሎችን ጭኖ የነበረዉ አንቶኖፉ በመጀመርያዉ በረራ ትንኩሳ ሲደረግበት አቅጣጫዉን ስቶ የበረረ ሲሆን በድጋሜ ተመልሶ ኤሪፖርቱ ጋር ያረፈ ቢሆንም በሁለተኛዉ በረራ በከባድ መሳርያ እገዛ እንደምንም ብሎ ያለፈ ሲሆን እግረኛ ሰራዊቱ ከከባድ መሳርያዉ በተጨማሪ በ 3 አቅጣጫ ቢዘረጋም በአንደኛዉ አቅጣጫ ዘርግቶ የነበረዉ ግትልትል ሰራዊት በተለምዶ ሳይና በር ላይ እምሽክ ተደርጎ ተበልቷል።
ትንቅንቁም በዛሬዉ ዕለት ማለትም የካቲት 2/2018 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን ብዛት ያለዉ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ ሁኗል።
እሸት ክፍለ ጦር ከላሊበላ ኤሪፖርት(ሽምሽሃ) ቀበሌ በ10 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ እምትገኝ ክፍለ ጦር መሆኗም አይዘነጋም።
በመጨረሻም የእሸት ክ/ጦር ወታደራዊ አዛዥ መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌም ''የአብይ አህመድ አፈ ቀላጤዎች በቅርቡ ከ ቱርክ እና ከአረብ አገር በ ክራይ በመጡ ድሮን እና ጀቶች በአየር ኃይል 90ኛ አመት ላይ ትርኢት ሲያሳዩ ''ሰማዩ የኛ ነዉ'' ያሉ ቢሆነም ሰማዩም ምድሩም የናንተ ሳይሆን የኛ ነዉ ሲል ተናግሯል''።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረበ መኮንን!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለውና ለሀገራችን ሕዝቦች ዋስትና የሚሆን ርዕዮተ-ዓለምን ያነገበ ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን! አሁን ከዚህ ኃይል ጋር ተሰልፋችሁ ለነጻነታችሁና ለሀገራችሁ የምትቆሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ።
❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በአሁኑ ወቅት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የትግል እንቅስቃሴ፣ ጠንካራ መሠረትና ግልጽ ራእይ የሰነቀ መዋቅር እየገነባ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ አሻራ ያለውና ለሀገራችን ሕዝቦች ዋስትና የሚሆን ርዕዮተ-ዓለምን ያነገበ ነው። ውድ ኢትዮጵያውያን! አሁን ከዚህ ኃይል ጋር ተሰልፋችሁ ለነጻነታችሁና ለሀገራችሁ የምትቆሙበት ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ።
ሰበር ዜና!
የምስራቅ አማራ እና የሰሜን አማራ መገናኛ የሆነችው ንፋስ መውጫ ጋይንት ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች!
በከተማዋ ዛሬ የካቲት 02/2018 ዓ/ም ሰዓታትን የፈጀ ከባድ ውጊያ ከተደረገ በኋላ በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
የብልፅግና መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ከአራት ወረዳዎች የተሰባሰበው የአድማ ብተናና የሚኒሻ እንዲሁም የፖሊስ ኃይል ከፋኖ ጋር ግማሽ ቀን የፈጀ ውጊያ ያደረገ ሲሆን፡ በመጨረሻም የፋኖን እርምጃ መቋቋም አቅቶት ገሚሱ ሲደመስስ ገሚሱ ደግሞ ከተማዋን ለቆ ፈርጥጧል።
ፀረ አማራው የብልፅግና አገዛዝ "በጋይንት ቀጠና ፋኖ እጅ ሰጥቶ አብቅቷል፣ ቀሪውን ደግሞ ደምስሼ ጨርሸዋለሁ" በሚል የበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ ባለበት ወቅት ነው ከተማዋ በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባችው።
የክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ከፊያለው ደሴ እስትንፋሶች በአሁን ሰዓት በከተማዋ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ካለ ለማጥራት የአሰሳ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል!
+1
ከተማረኩ የአብይ ወታደሮች መካከል በትንሹ ለቅምሻ ይችን እያያችሁ ቆዩ..!
እንመለስበታለን፡፡
ሁላችህም አፋብን እያላችሁ ኮምቱ ..!
የአደረጃጀት ዜና!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የኮር 2 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለበርካታ ቀናት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የኮርና የክ/ጦር ስያሜ በመቀየር እንዲሁም የአመራር መተካካትና አጠቃላይ ግምገማ አድርጓል።
በመሆኑም የበፊት ስሙ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 2 የነበረውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በማለት ቀይሯል።
ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር እንዲሁም በስሩ የሚገኙትን ሁሉንም ክፍለ ጦሮች በሰሩት ጀብዱ መሰረት የስም ስያሜ ሰጥቷል::
1ኛ.ዞብል አምባ ክፍለ ጦርን 12ኛ ክፍለጦር
2ኛ.ካላኮርማ ክፍለ ጦርን 49ኛ ክፍለጦር
3ኛ.ታጠቅ ክፍለ ጦር ዲቢና ወርቄ ባለሸርጡ ብርጌድ እና የኮር መካናይዝድ በአንድ ላይ በመበወዝ 65ኛ
ክፍለጦር በሚል ተሰይመዋል::
በመጨረሻም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅንቄ
(አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት ለወደፊት ለሚሰራቸው ተግባራት ጥልቅ ሂስ ግለ-ሂስ (ግምገማ) በማድረግ በቀን 28/05/2018 ዓ.ም አዳዲስ የስራ ሃላፊነትና የአመራር ሽግሽግ በአዲሱ የአደረጃጀት ሪፎርም በሚከተለው መልኩ ሰርቷል።
1.ዋና ሰብሳቢ...............አርበኛ ረዳ ውበቱ
2.ወታደራዊ አዛዥ............አርበኛ ጌታቸው መልኩ
3.ም/ወታደራዊ አዛዥ.........አርበኛ ዘውዱ ዳርጌ
4.ወታደራዊ አማካሪ.........አርበኛ ሻ/ል እንድሪያስ ሽፈራው
5. ዘመቻ መምሪያ ............አርበኛ ዋሴ ጫኔ.
6.ም/ዘመቻ መምሪያ........ አርበኛ በላይ መንግስቱ
7.ወታደራዊ አሰተዳር.......አረበኛ ፈለቀ ደጉ
8.የሰው ሀይል አስተዳደር.....አርበኛ መ/ር ሞላ ዝናቤ
9.ጤና መምሪያ..............አርበኛ ተፋየ ታደሰ
10.ፋይናንስ ሃላፊ................አርበኛ አለሙ ፈንቴ
11.ም/ፋይናንስ ...................አርበኛ ምስጋን ታደሰ
12.የፖለቲካ መምሪያ..............አርበኛ ሻምበል አሌ
13.የህዝብ አስተዳደር.........አርበኛ ሳሙኤል ሞገስ
14.የህዝብ ግንኙነት.........አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
15.ሀብት አፈላላጊ...............አርበኛ ሀበቴ ዘውዱ
16.መረጃና ደህንነት.............########
17.ስልጠና መምሪያ......አርበኛ መ/አለቃ ሲሳይ መንግስቴ
18.አማካሪና ፀሀፊ...............አርበኛ ባየ ዝናቤ
19.የህግ መምሪያ................አርበኛ መስፍን አያሌው
20.ሎጅስቲክ መምሪያ..........አርበኛ ዝናቤ በሪሁን
21.ኦርድናንስ...................አርበኛ ፈንታቢል ደርሶ
22.ም/ኦርዲናስ................አርበኛ አንዱአለም አዲሴ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት አርበኛ መ/ር አታሎ ሙሉጌታ
የካቲት 2/2018 ዓ.ም
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር በእሥቴ መዳረሻ
[የካቲት 02/2018ዓ.ም]
🔑ጉና ክፍለ ጦር
✔እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
✔ሐገረ ቢዘን ብርጌድ
✔አንዳ ቤት ብርጌድ
🔑ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን በጥምረት እየገረፉት ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ወደፊት
ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው
