en
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
3 019
Subscribers
+4524 hours
+967 days
+45930 days
Posts Archive
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ማጀቴ ግንባር የጠላት ኃይል በአስደናቂ የፋኖ ጀግንነት እየተመከተ ይገኛል!! ​ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም | ​በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ ማጀቴ እና አካባቢው ከትናንት ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም ጎህ ሲቀድ ጀምሮ የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ውጊያ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በአስደናቂ የፋኖ ጀግንነት እየተመከተ ነው። ​በዚህም ከኮምቦልቻ፣ ከኬሚሴ፣ ከአጣዬ እና ከመሀል ሜዳ የተሰበሰበው የአብይ አህመድ አየር ወለድ ኮማንዶ ኃይል በአራት አቅጣጫዎች ወረራ ለመፈጸም ቢሞክርም፣ በቦታው በሚገኙት የፋኖ ክፍለጦሮች ብርቱ ጥቃት ተቀጥቅጦ ወደመጣበት እንዲመለስ ተደርጓል። ​በማጀቴ ቀጠና፣ መስኖ እና ጅጉቢ አካባቢ ሰባት ለሰባ (7 ለ 70) ክፍለጦር እና ዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የጠላትን ጥቃት በጽናት ሲመክቱ ውለዋል። በተለይም በካራለጎማ በተካሄደው ከባድ ፍልሚያ፣ ሰባት ለሰባ ክፍለጦር የጠላትን ኃይል ያለ ንቅንቅ በመግታት ከፍተኛ ጀግንነትን ተጎናጽፏል። በአርብ ገበያ ግንባር ደግሞ የሁለቱ ክፍለጦሮች ሻለቆች ለ46 ሰዓታት ያላሰለሰ ውጊያ በማድረግ፣ የጠላትን ኃይል አንገቱን አስደፍተው ወደኋላ መልሰውታል። በመንዝ ጌራ ወረዳም፣ ብሩኬ ደንሴ ክፍለጦር በቆረጣ በመግባት የጠላትን ኃይል በመደምሰስ የሟቾችን አስክሬን ወደ መሀል ሜዳ ከተማ መመለሱ ተረጋግጧል። ​ ሆኖም ​የፋኖን ብርቱ ክንድ መቋቋም ያቃተው የጠላት ኃይል፣ ቁጣውን በሰላማዊ አርሶ አደሮች ላይ በመወጣት ላይ ይገኛል። በማጀቴ ዙሪያ በሚገኙ የሰላማዊ ነዋሪዎች እርሻ ላይ በመድፍና በሞርተር ጥቃት በመሰንዘር የሕዝቡን ሰብል እያወደመ ይገኛል። ​በአንድ በኩል ህዝብን በመድፍ እየደበደቡ፣ በሌላ በኩል ለምርጫ ጥሪ ማቅረብ "የአገዛዙ የሞራል ዝቅጠት" ማሳያ ነው ያሉት የሽዋ ጠቅላይ ግዛት ነዋሪዎች፣ ይህ ድርጊት አገዛዙን ከታሪክ አምባገነኖች ጋር የሚያስተያየው "ሂትለራዊ" አካሄድ መሆኑን ይገልጻሉ። "በጥይት እያደኑ ምርጫ መጠየቅ የፖለቲካ ቅቡልነት ያጣ አገዛዝ የመጨረሻው የህልውና መፈራገጫ ነው" ሲሉ ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን አንጸባርቀዋል። ​ ​የአገዛዙ ኃይሎች በግንባር ከፋኖ ጋር ሲጋጠሙ፣ ከኋላ ደግሞ ከኬሚሴ ዞን ያመጣውን ቅልብ ሚሊሻዎችን በማሰማራት በንጹሃን ላይ ግፍ እየፈጸሙ መሆናቸው ተጋልጧል። በዚህ የክህደት ድርጊት፣ ማጀቴ የሚገኙ አርሶ አደር ሸጋው ይልማ በኬሚሴ ዞን ሚሊሻዎች በግፍ የተገደሉ ሲሆን በተጨማሪም፣ በማጀቴ አካባቢ በሚገኘው ማር ምድር በተባለ ጎጥ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የቁም እንስሳት በዚሁ ሚሊሻዎች ተዘርፋዋል። ​ የክፍለጦሩ አመራሮች ከግንባር በአደርሱን መረጃ የህዝብን ደህንነት ለማስከበር ያላቸው ቁርጠኝነት የጸና መሆኑን አረጋግጠዋል። የአፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦርና የ7ለ70 ክፍለጦር ፋኖዎች ዛሬ የሰጡት ተገቢ ምላሽ፣ ነገም ከዚህ በተሻለ ጥንካሬ እንደሚደገም በማረጋገጥ፣ ህዝቡን አገዛዙ በመድፍ ጭምር እየታገዘ እያዘረፈውና እያደህየው በመሆኑ በተባበረ ክንድ የህልውና ዋስትናውን እንድረጋገጥ መልእክት አስተላልፈዋል። ​'' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ​አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ የአሳምነው ዕዝ ስር የሚገኘው የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ ሰባት ለሰባ  ክፍለ ጦር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጠላት ላይ ታሪካዊ ድል ተቀዳጀ። በኤፍራታ ግድም ወርዳ ​በካራለጎማ ግንባር ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሰላም እና የነጻነት ጠላቶች በከፈቱት ያልተጠበቀ ጥቃት፣ ሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር በነበረው ከፍተኛ የመከላከል አቅም ጥቃቱን ወደ መልሶ ማጥቃት ቀይሮት አምሽቷል። የክፍለ ጦሩ ቃኚዎች እንደገለጹት ፋኖዎች በያዙት ስልታዊ ቦታ ላይ ባደረሱበት ከፍተኛ ምት የጠላት ኃይሎች በከፍተኛ ጥንቃቄና በታክቲካል ብልጫ ሰባብረዋቸው ውለዋል። ​​በዚህ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ፡ ​የጠላት ድል መመታት የስርዓቱን የሽብር አጀንዳ ለማስፈጸም የተሰማሩ ሁለት ወንበር ጠባቂዎች በቆራጥ የፋኖ አባላት እርምጃ ተወስዶባቸው ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል። የጠላት ኃይል አካል የነበሩ ሁለት ሚሊሻም በዚሁ ግንባር በተወሰደባቸው ፈጣን እርምጃ በአውደ ውጊያወስከወዲያኛው ተሰናብተዋል። በፋኖዎች ጥንካሬ የተደናገጠውና ተስፋ የቆረጠው የጠላት ኃይል፣ በርካታ ሙታኑንና ቁስለኞቹን ይዞ ወደ ኋላ ለመሸሽ ተገዷል። በጦር ሜዳው ላይ የነበሩ የሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር አባላት እንደገለጹት፣ የጠላት ኃይል ሽንፈቱን ተላብሶ በከፍተኛ መደናገጥ ወደ መጣበት መመለሱ ታይቷል። ​የሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር ቃኚዎች በስፍራው እንደታዘቡት የፋኖዎች ወኔ የጠላትን ሰራዊት ሞራል ክፉኛ እንደሰበረውና የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አባላት ለግዛታቸው ደህንነት ያላቸው ጽናት ለቀጣይ ትግል ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል። አካባቢው በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ በሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር ቅጥጥር ሰር ይገኛል። ​በግንባሩ የነበሩ የክፍለ ጦሩ አባላት "ይህ ድል የነጻነት ጉዟችን ማሳያ ነው" ሲሉ በኩራት ተናግረዋል። ​'' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መረጃው የአጼ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

#የአርበኞ_በዓል_በታሪካዊቷ_አንድት_ግራር_ተከብሮ_ዋለ። አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሚያዚያ 27/2018ዓ.ም አንድት ግራር-ተጉለት-ሸዋ የጀግኖች አባቶች 85ኛው የአርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል በሸዋ ክፍለ-ሀገር በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሳሲት ክላስተር በታሪካዊቷ አንድት ግራር ስፍራ ታስቦ ዋለ። በመርሐ-ግብሩ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች፣የአባት አርበኞች፣የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሸማግሌዎች፣የክላስተር አመራሮችና የአካባቢው የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። ይህ በዓል ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የድል በዓል መሆኑን ያወሱት በዬደረጃው የሚገኙ የመርሃ-ግብሩ ተሳታፊዎች ነጩን የጣሊያን ፋሽስታዊ አገዛዝ በተባበረ ክንድ በማሸነፍ ለድል አባቶቻችን እንደበቁት ሁሉ ይህ ትውልድም ውስጣዊ አንድነቱን ጠብቆ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመተባበር ጥቁሩን ፋሽስታዊ የብልፅግና አገዛዝ ከስር መሰረቱ በመመንገል የራሱን ዘመን ታሪክ ሰርቶ እንደ አባቶቻችን የድል በዓሉን ያከብራል በማለት ቃል ጭምር በመግባት ታሪካዊ ሁነቱን ዘክረውት ውለዋል። በበዓሉ ዝግጅት ላይ የተገኙት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆነው የንጉስ ሣህለ ሥላሴ ክፍለጦር ቃኝዎች ወታደራዊ ትርዒት ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የበዓሉን የፀጥታ ውሎ በማስከበር ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል። አገዛዙ ሀገርና ታሪክ ጠል ስለሆነ ትውልዱ ጀግኖች አባቶች በጦር በጎራደ ተዋድቀው ያጎናጸፉንን የድል በዓል እንዳይበርዘውና እንዳይከልሰው ትውልዳዊ ሀላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም በበዓሉ የተገኙት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፍተኛ አመራሮችና አባት አርበኞች እንዲሁም የመርሃ-ግብሩ ታዳሚዎች አሳስበዋል። ክብርና ሞገስ ለጀግኖች አባቶቻችን! ድል ለፋኖ፣ድል ለአማራ! ድል ለኢትዮጵያ! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም አንድት ግራር-ተጉለት-ሸዋ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ የአሳምነው ዕዝ ስር የሚገኘው የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ ሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጠላት ላይ ታሪካዊ ድል ተቀዳጀ። በኤፍራታ ግድም ወርዳ ​በካራለጎማ ግንባር ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሰላም እና የነጻነት ጠላቶች በከፈቱት ያልተጠበቀ ጥቃት፣ ሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር በነበረው ከፍተኛ የመከላከል አቅም ጥቃቱን ወደ መልሶ ማጥቃት ቀይሮት አምሽቷል። የክፍለ ጦሩ ቃኚዎች እንደገለጹት ፋኖዎች በያዙት ስልታዊ ቦታ ላይ ባደረሱበት ከፍተኛ ምት የጠላት ኃይሎች በከፍተኛ ጥንቃቄና በታክቲካል ብልጫ ሰባብረዋቸው ውለዋል። ​​በዚህ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ፡ ​የጠላት ድል መመታት የስርዓቱን የሽብር አጀንዳ ለማስፈጸም የተሰማሩ ሁለት ወንበር ጠባቂዎች በቆራጥ የፋኖ አባላት እርምጃ ተወስዶባቸው ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል። የጠላት ኃይል አካል የነበሩ ሁለት ሚሊሻም በዚሁ ግንባር በተወሰደባቸው ፈጣን እርምጃ በአውደ ውጊያወስከወዲያኛው ተሰናብተዋል። በፋኖዎች ጥንካሬ የተደናገጠውና ተስፋ የቆረጠው የጠላት ኃይል፣ በርካታ ሙታኑንና ቁስለኞቹን ይዞ ወደ ኋላ ለመሸሽ ተገዷል። በጦር ሜዳው ላይ የነበሩ የሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር አባላት እንደገለጹት፣ የጠላት ኃይል ሽንፈቱን ተላብሶ በከፍተኛ መደናገጥ ወደ መጣበት መመለሱ ታይቷል። ​የሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር ቃኚዎች በስፍራው እንደታዘቡት የፋኖዎች ወኔ የጠላትን ሰራዊት ሞራል ክፉኛ እንደሰበረውና የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አባላት ለግዛታቸው ደህንነት ያላቸው ጽናት ለቀጣይ ትግል ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል። አካባቢው በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ በሰባት ለሰባት ክፍለ ጦር ቅጥጥር ሰር ይገኛል። ​በግንባሩ የነበሩ የክፍለ ጦሩ አባላት "ይህ ድል የነጻነት ጉዟችን ማሳያ ነው" ሲሉ በኩራት ተናግረዋል። ​'' ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! መረጃው የአጼ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

#በራሳ_ክላስተር_ከተቋማት_ሰራተኞች_ጋር_የተደረገ_መድረክ✅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የስራ መመሪያ መሰረት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች ከተቋማት ሰራተኛ  ክፍሎች ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል።     ሚያዚያ 27/2018ዓ.ም አፋብን ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠራቸው በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በአማራ የህልውና ጉዳይ ላይ ያተኮረ ከሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከተውጣጡ ሰራተኞች ጋር መድረክ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በራሳ ክላስተር ተካሒዷል። ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2018ዓ.ም በተካሔደው መድረክ የራሳ ክላስተር የተቋማት ሰራተኞች ጋር  ውጤታማ መድረክ መካሔዱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ከፋተኛ አመራሮች እና የራሳ ክላስተር አመራሮች በተገኙበት ውምይት መደረጉ ታውቋል ። ለውይይት በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ወቅታዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች መድረኩን በመሩት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ  ከፋተኛ አመራሮ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።       ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ !!

ሰበር ዜና! የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፉ ልጆች በመቄት ምድር  ታሪክ ሰርተዋል!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር  ታላቅ ጀብድ በመቄት ምድር ተሰርቷል!!! ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም ረፋድ ላይ የተጀመረው አውደ ውጊያ  ከቁር አንበሳ እስከ ሲሲጊ አድማሱን የዘረጋው የውጊያ ውሎ የአገዛዙ ሰራዊቶች በገፍ ሲደመሰሱ የመከላከያው ኮሎኔል ፓትሮል በፋኖዎች እጅ በቦምብ ጋይታ ከጥቅም ውጭ ተደርጋለች። በስቦ መምታት ጥበብ የተቃኙት የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ግስላዎች  የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት እንደ ተርብ በሚናደፉ የፋኖዎች ክንድ ቅንድቡን ሲፈለጥ ውሎ በመጨረሻም ከ17 በላይ ክላሽኮ መሳሪያ ፤ከ803 በላይ የብሬን ተተኳሽ፤ከ501 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፤7 (ሰባት)የወገብ ትጥቅ እና 5(አምስት) ኤፍዋን ቦምብ ተማርኳል።ለአሞራ ሲሳይ የሆኑ ለቁጥር የሚያታክት የተደመሰሱ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊቶች በመቄት ምድር ተለሽልሸው አለቆቻቸው ጥለዋቸው ፈርጥጠዋል። በእብሪትና እብደት ቻርጅ የተሞላው የብልፅግና አገዛዝ በስተመጨረሻ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲሳነው በየሸለቆውና ጫርቻው ተበታትኖ ነፍስ አውጭኝ ገደል ለገደል እየተፍረጨረጨ ይገኛል።በጥቅም ተገዝቶ አላማ ካለው ፋኖ ጋር የገጠመው የብልፅግና ስርዓት አስጠባቂ በባለ ራዕዮቹ ዶግ አመድ ተደርጓል።   መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!! ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም

ቀን፦ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፦ በላይ ዘለቀ እዝ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር የተሰጠ የሃዘን መግለጫ የኅልውና ትግላችንን ለግለሰቦች ፖለቲካዊ ቁማር መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካሄዶች እንቁ አርበኞቻችንን ነጥቆናል። ትናንት ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርና በጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር አመራሮች መካከል የተዛባ ትርክት ፈጥረው ለአንዱ ሌላ፣ ለአንዱ ደግሞ በተቃራኒ ሌላ የጥላቻና የፍረጃ ሀሳብ እያሰራጩ የጸና አቋም ያላቸውን አንገታም ወንድማማቾችን እርስ በርስ አታኩሶ ያጋደለ ክፉ አስተሳሰብን በጽኑ እናወግዛለን። እዚህ ምስቅልቅል ውስጥ እንድንዘፈቅ እንቅልፍ አልባ የሚደክሙ አካላት የተሳሳቱ እሳቤዎችን የሚናግሩ አንደበቶች እንደሆኑ በውል እንገነዘባለን። ሃሰተኛ አንደበት የተሳሳተ መረጃ፣ የተሳሳተ እሳቤን እየረጨ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን እየሰበከ ለጠላት መሳቂያና መሳለቂያ የሚሆኑ አሳፋሪ ጥቁር ታሪኮችን እንድንጽፍ አድርጎናል። በሁለቱ የኮራችን አሐዶች በኩል የተጎዱ ወንድሞቻችን የግለሰብና የቡድን ፍላጎት አጥብቀው የሚያወግዙ በአንጻሩ ለአማራ ሕዝብ ኅልውና መረጋገጥ ሲታትሩ የከረሙ መሆናቸውን መላው የኮራችን ሠራዊት ያውቃል። ይባስ ብሎ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር ስም ሚዛናዊነት የጎደለው መግለጫ የሚሰጡ አካላት ከኮሩ እውቅና ውጭ መሆናቸውንና ኮራችንንም የማይወክል መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን። ከምንም በላይ የሁለቱም አሐድ ወንድሞቻችን የእገሌና የእገሌ ሠራዊት ሳይሆኑ የአማራ ሠራዊት አመራሮች የነበሩ ሰፊ አዕምሮ የነበራቸው አርበኞች ናቸው። በመሆኑም የዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር አሐድ በጓዶቻችን ኅልፈተ ሕይወት የተሰማንን መራር ሃዘን እየገለጸ ቸሩ ፈጣሪያችን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን ዘንድ እንመኛለን።      ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!               ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ። ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ================================
+1
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ። ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ======================================= የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የጦር መኮንኖች በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግ ልዕልናዋን እንደገፈፏት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግረዋል። በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት አመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም 206ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ጎዛምን ወረዳ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት

የዜጎች ክብር የዲፕሎማሲያችን ኹሉ ቊንጮ ይኹን! ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰቆቃ ስለተጋለጡ ዜጎች የተሰጠ መግለጫ ኢትዮጵያዊያን በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ያለ ቪዛ ወደ ውጪ አገር ለትምህርት በሚላኩበት ወቅት ፈተናቸውን አልፈው የምረቃ ሥነሥርዓት እንኳን ሳይጠብቁ ተሳፍረው ወደ አገራቸው ይመለሱ ነበር። ኢትዮጵያ ከምእራቡ ዓለም ጋር ሲነጻጸርም ደካማ የኢኮኖሚ ደረጃና የማኅበራዊ ግልጋሎትም አልነበራትም። የምእራቡ ዓለም ምቾት የአገር ፍቅርንና የእናት ቤት ሽሮን የሚያስንቅ አልነበረም። አንድ ሰው ከተማረ ተከብሮ አገሩ ያገለግላል። ማኅበረሰቡም ይኮራበት ነበር። ይኹንና በመጨረሻው ያለንን ኹሉ አፍርሰን እንደ ቻይናና ሦቪዬት ኅብረት ሦሻሊዝምን፣ የስታሊንን የብሔር ብሔረሰቦች ፓለቲካ ብንተክል የተሻለ እንኾናለን ተባለ። ያም ኢትዮጵያን ወደ ምድራዊ ሲዖል ቀየረ። ስደት እንደ ጌጥና ልዩ እድል ተቆጠረ። አዛውንቶችንና አርበኞችን በጅምላ መረሸን፣ ወጣቱን በቀይ ሽብር መጨረስ እድል ፈንታችን ኾነ። በዚያም ሳይበቃ ቀጥሎ የመጣው ደግሞ መጤ፣ ነፍጠኛ፣ ኦርቶዶክስ፣ ሴማቲክስ እያለ ምድሪቷን በደም አጠባት። ምንም የማያውቁ ሕጻናት ለሰቆቃ የሚዳረጉበት፣ እርጉዝ እናት በአሰቃቂ የምትገደልበት ዘመን መጣ፣ አለ፣ ደርሰን ካላስቆመነው ይቀጥላል። ይኽን ግፍና አድሏዊነት ፈርቶ የሚሸሸው ከመጥበሻው ወደ እሳቱ፣ ጅብ ፈርቸ ዛፍ ብወጣ ነብር ቆዬኝ እየኾነ መጣ። እስከአኹን በወጣ ይፋዊ መረጃ በዚኽ ሣምንት ብቻ ከ7 በላይ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን Xenophobia(መጤ ጥላቻ) በተሰኘ ዘመናዊ አፓርታይድ አስተሳሰብ ወንድሞቻችን በአሰቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል። ትናንት ለአፍሪካውያን ከባርነትና ና ነጻነት በተለይ ለደቡብ አፍሪካውያን የበዛ ግፍ አገዛዝ ለማላቀቅ እነኔልሰን ማንዴላን ዜግነት ሰጥታ፣ ወታደራዊ ስልጠና፣ ስንቅና ትጥቅ ቋጥራ ለነጻነት ጎሕ የቀደደች አገር ዜጎች ለውለታቸው መታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸው በድባብና ቀይ ምንጣፍ መሄድ ሲገባቸው በጉልበታቸው ጥረው ግረው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን መሳደድና መገደል እጅጉን አስቆጥቶናል፤ ለፀፀት ዳርጎናል። ትብብራችን በግፍና በደቦ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ሐዘኑን ይገልጻል። በሌላ በኩል በሳውዲ አረቢያ ምድር በአገሬው ሕግ(ሸሪዓ) መሠረት ከ 60 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ እንዳለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ካወጡት ሪፖርት መረዳት ችለናል። ይኽም እንደዜጋና የሕዝብ ሕመም እንደሚሰማው ፓርቲ ልባችን ክፉኛ ተነክቷል። በእርግጥ ይሄ ስደተኞችን ምክንያት እየፈለጉ ማጥቃት በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣ አባዜ አካል ነው ብለን እናስባለን። ኢትዮጵያና ሳውድ አረቢያ ከንግድና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዘለለ የቀደመ የሚባል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በሃይማኖት፣ በምግባር አገሩን ያቀኑበት ትስስሩን ያጎለበቱበት ይልቁኑም ኢትዮጵያ የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች የኾኑ ካዕባዎችን በአገራቸው በዕምነታቸው ምክንያት ተሳደው ሲመጡ ለዘር አትርፎ ያቆዬ ሕዝብና አገር ነው። በዚኽም ኢትዮጵያ እስልምናን ከመጥፋት የታደገች ግምጃ ቤት ናት ቢባል ማጋነን አይኾንም። የዚኹ ውለታዋና ክብሯ እንደተጠበቀ ኾኖ የትኛውም ሰው በየትም ቦታ በወንጀል ከተገኘ በፍትሕ አደባባይ መቅረቡን በጽኑ የምናምነውና የምንከራከርለት መርሕ ቢኾንም እነዚኽ ኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻው የጭካኔ ፍርድ መፈጸሙን በጽኑ እንቃወማለን። ነገሩ በቅርብ ጊዜያት ወዲኽ እያቆጠቀጠ የመጣውን ስደተኛ ጠልነት ጋር የተገናኘ እንጂ በወንጀል  እንዳልኾነ ጥርጣሬው አለን። ይኽም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንደምንቆጥረው የሳውዲ መንግሥትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቅልን እንሻለን። ስለኾነም፣ 1. የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በኢትዮጵያውያንና በመላው አፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ግድያና ማሳደድ እንዲያስቆም ለሞቱትም አግባብ ያለውን ማቋቋሚያና ካሳ እንዲሰጥ አፍሪካ ሕብረትና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። 2. የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን የግፍ ግድያ ማስቆም የድፕሎማሲ ሥራው ኹሉ ቊንጮ መኾኑን መረዳት አለበት ብለን እናምናለን። ውቂያኖስ አቋርጦ ስለሌሎች አገር ዜጎች መገደል ጥብቅና ሲቆም ያየነው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ይሄንን በጉያው የሚፈጸም የግፍ ግድያ ማስቆም ካልቻለ በአፍሪካ ኅብረት ያለውን ተሳትፎ ጭምር እንዲጤን ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር በመኾን ግፊት እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን። 3. ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና የኢትዮጵያን ውለታ በማውሳት መንግሥት በመታረጃው ቄራ ቆመው የሞት አፋፍ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲታደግና ጣልቃ ገብቶ የሞት ፍርዱ ወደ እሥራት እንዲቀየር ብሎም በአገራቸው እንዲዳኙ አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ኹሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን። 4. መንግሥት የችግሩ መነሻ የኾነውን፣ በአገር ውስጥ መኖር የማያስችሉና ለስደት የሚዳርጉ አገራዊ ቀውሶችን እንዲያስቆም እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የምኒልክ ዕዝ አርበኞች አጥቢያ ለሊቱን በአልብኮ ወረዳ ነጋሽ ታዳጊ ከተማ ውስጥ በፈፀሙት መብረቃዊ ኦፕሬሽን 23 የጠላት ወታደሮችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጁ! በአፋብን ወሎ ቤተ ዐምሓራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ104ኛ ኮር  አብሪ ቡድንና በኮሩ ስር 25ኛ ክ/ጦር ከ1ኛ ሬጅመንት የተውጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም ለዛሬ ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም አጥቢ ለሊቱን በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ነጋሽ ታዳጊ ከተማ ውስጥ በወሰዱት የተጠና መብረቃዊ እርምጃ የጠላት አከርካሪን ሰብረው ድል አስመዝግበዋል። እርምጃው የተወሰደው ከጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመወገን በገዛ ሕዝባቸው ላይ እልቂት ሲፈፅሙ የነበሩ የሚኒሻና ፖሊስ ኃይሎች ካምፕ ላይ ሲሆን፡ በዚህም ስምንቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ፡ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በፅኑ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል። በተጋድሎው ሦስት የሚኒሻ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው እጅ ከፈንጅ ሲማረኩ፡ አራት ክላሽንኮቭ መሣሪያና አንድ አብራራው ጠብመንጃ በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር ውሏል። ፀረ አማራውና ሀገር አፍራሹ የብልፅግና አገዛዝ እድሜውን ለማራዘምና ተጨማሪ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ በምርጫ ስም ለማጭበርበር ያዘጋጀው የምርጫ ካርድና የምርጫ ማስፈፀሚያ ቁሣቁስ በአርበኞቹ እንዲወድም ተደርጓል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ ዐምሓራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን ፋሽስታዊ አገዛዝ ከአምስት ዓመታት ተጋድሎ በኋላ በተመሳሳይ ቀን ተሸንፎ የወጣበት ዕለት በመሆኑ በሀገራችን የነፃነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ዕለት ነው። ይህ እለት ፋሽዝም የተሸነፈበት ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ቀን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ ቀንም ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ ይላል። የብልፅግና አገዛዝ የሀገሩን የፖሊሲ ሉዓላዊነት ከማከራዬት አልፎ አዬር ኃይሉን እና መሰል ተቋማትን ለውጭ ኃይሎች መፈንጫ በማድረግ በአርበኞች መስዋዕትነት የተገኘውን የሀገር ነፃነት ለርካሽ ስልጣን ሲል አሳልፎ በመስጠቱ ሀገራችን ያልተነገረ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። የብልፅግና አረመኔ አገዛዝ በአምስቱ የአርበኝነት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈፀመው ግብ በብዙ እጥፍ የራቁ የዘር ማጥፋት እና ሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ነው። የአባቶቹን ታሪክ የወረሰው ሰራዊታችን የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ከዘመኑ ጥቁር ፋሽስቶች ጋር በመተናነቅ ላይ ይገኛል። ዘር አጥፊዉን አገዛዝ ታግለን በማሸነፍ የተነጠቅነዉን ሀገር ማስመለስ ግባችን እንደመሆኑ መጠን ንቅናቄው አሁን ላይ እያደረገ ያለው ትግል የቀድሞ አርበኞች ካደረጉት የነፃነት ተጋድሎ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። ፅናትን፣ አይበገሬነትን፣ ቁርጠኝነትን በሚጠይቀው ተጋድሎ ውስጥ በመስዋዕትነት ድል እያስመዘገበ ያለው ሰራዊታችን በአማራ ህዝብ ጠላቶች ላይ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን። የባርነት ቀንበር የተሰበረበት የአርበኞችን ቀን ስናከብር የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለማስወገድ የሚከፈለዉን ማንኛዉንም መስዋዕትነት በመክፈል ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ቃል በመግባትም ጭምር ነው።