uk
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Відкрити в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Показати більше
3 011
Підписники
+2324 години
+367 днів
+41430 днів
Архів дописів
ሰበር ዜና! የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፉ ልጆች በመቄት ምድር  ታሪክ ሰርተዋል!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦር  ታላቅ ጀብድ በመቄት ምድር ተሰርቷል!!! ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም ረፋድ ላይ የተጀመረው አውደ ውጊያ  ከቁር አንበሳ እስከ ሲሲጊ አድማሱን የዘረጋው የውጊያ ውሎ የአገዛዙ ሰራዊቶች በገፍ ሲደመሰሱ የመከላከያው ኮሎኔል ፓትሮል በፋኖዎች እጅ በቦምብ ጋይታ ከጥቅም ውጭ ተደርጋለች። በስቦ መምታት ጥበብ የተቃኙት የቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ግስላዎች  የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት እንደ ተርብ በሚናደፉ የፋኖዎች ክንድ ቅንድቡን ሲፈለጥ ውሎ በመጨረሻም ከ17 በላይ ክላሽኮ መሳሪያ ፤ከ803 በላይ የብሬን ተተኳሽ፤ከ501 በላይ የክላሽ ተተኳሽ፤7 (ሰባት)የወገብ ትጥቅ እና 5(አምስት) ኤፍዋን ቦምብ ተማርኳል።ለአሞራ ሲሳይ የሆኑ ለቁጥር የሚያታክት የተደመሰሱ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊቶች በመቄት ምድር ተለሽልሸው አለቆቻቸው ጥለዋቸው ፈርጥጠዋል። በእብሪትና እብደት ቻርጅ የተሞላው የብልፅግና አገዛዝ በስተመጨረሻ የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲሳነው በየሸለቆውና ጫርቻው ተበታትኖ ነፍስ አውጭኝ ገደል ለገደል እየተፍረጨረጨ ይገኛል።በጥቅም ተገዝቶ አላማ ካለው ፋኖ ጋር የገጠመው የብልፅግና ስርዓት አስጠባቂ በባለ ራዕዮቹ ዶግ አመድ ተደርጓል።   መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!! ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም

ቀን፦ ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)፦ በላይ ዘለቀ እዝ ከዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር የተሰጠ የሃዘን መግለጫ የኅልውና ትግላችንን ለግለሰቦች ፖለቲካዊ ቁማር መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካሄዶች እንቁ አርበኞቻችንን ነጥቆናል። ትናንት ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦርና በጥቁር አንበሳ ክፍለ ጦር አመራሮች መካከል የተዛባ ትርክት ፈጥረው ለአንዱ ሌላ፣ ለአንዱ ደግሞ በተቃራኒ ሌላ የጥላቻና የፍረጃ ሀሳብ እያሰራጩ የጸና አቋም ያላቸውን አንገታም ወንድማማቾችን እርስ በርስ አታኩሶ ያጋደለ ክፉ አስተሳሰብን በጽኑ እናወግዛለን። እዚህ ምስቅልቅል ውስጥ እንድንዘፈቅ እንቅልፍ አልባ የሚደክሙ አካላት የተሳሳቱ እሳቤዎችን የሚናግሩ አንደበቶች እንደሆኑ በውል እንገነዘባለን። ሃሰተኛ አንደበት የተሳሳተ መረጃ፣ የተሳሳተ እሳቤን እየረጨ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን እየሰበከ ለጠላት መሳቂያና መሳለቂያ የሚሆኑ አሳፋሪ ጥቁር ታሪኮችን እንድንጽፍ አድርጎናል። በሁለቱ የኮራችን አሐዶች በኩል የተጎዱ ወንድሞቻችን የግለሰብና የቡድን ፍላጎት አጥብቀው የሚያወግዙ በአንጻሩ ለአማራ ሕዝብ ኅልውና መረጋገጥ ሲታትሩ የከረሙ መሆናቸውን መላው የኮራችን ሠራዊት ያውቃል። ይባስ ብሎ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር ስም ሚዛናዊነት የጎደለው መግለጫ የሚሰጡ አካላት ከኮሩ እውቅና ውጭ መሆናቸውንና ኮራችንንም የማይወክል መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን። ከምንም በላይ የሁለቱም አሐድ ወንድሞቻችን የእገሌና የእገሌ ሠራዊት ሳይሆኑ የአማራ ሠራዊት አመራሮች የነበሩ ሰፊ አዕምሮ የነበራቸው አርበኞች ናቸው። በመሆኑም የዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር አሐድ በጓዶቻችን ኅልፈተ ሕይወት የተሰማንን መራር ሃዘን እየገለጸ ቸሩ ፈጣሪያችን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን ዘንድ እንመኛለን።      ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!               ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!

ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ። ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ================================
+1
ቅዱስ ሲኖዶስ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመጥፋት እንዲታደጋት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ። ሚያዚያ 27/2018 ዓ.ም ======================================= የአብይ አህመድ ጀነራሎች በአደባባይ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የጦር መኮንኖች በቤተ ክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ ምሽግ በማድረግ ልዕልናዋን እንደገፈፏት የጎዛምን ወረዳ የሐይማኖት አባቶች ተናግረዋል። በአማራ ህዝብ ላይ በተፈፀመው ወረራ ቤተ ክርስቲያኗ በቀጥታ ጥቃት እየተፈፀመባት ነው ያሉት የሐይማኖት አባቶች በበኩላቸው ካህናት፣ ቀሳውስት ፣ የአብነት ተማሪዎችና ዲያቆናት እየተገደሉ ስርዓተ ቤተክርስቲያን እየተስተጓጎለ ይገኛል ብለዋል። ከዚህ በፊት በድምቀት የሚከበሩት አመታዊ ሐይማኖታዊ በዓላት የአገዛዙ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ በመመሸጉና የሐይማኖት አባቶችን በማሳደዱ በተለመደው መልኩ ማክበር አለመቻሉንም አስታውቀው፤ ቤተ ክርስቲያኗ ቅርሷ እየተዘረፈ፤ ስርዓቷ እየተገፈፈ፤ አገልጋዮቿ እየተገደሉ በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኗን ከመጥፋት እንዲታደጋት ጥሪ አቅርበዋል። በዚህም 206ኛ ኮር በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ጎዛምን ወረዳ ከኃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት

የዜጎች ክብር የዲፕሎማሲያችን ኹሉ ቊንጮ ይኹን! ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ለሰቆቃ ስለተጋለጡ ዜጎች የተሰጠ መግለጫ ኢትዮጵያዊያን በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን ያለ ቪዛ ወደ ውጪ አገር ለትምህርት በሚላኩበት ወቅት ፈተናቸውን አልፈው የምረቃ ሥነሥርዓት እንኳን ሳይጠብቁ ተሳፍረው ወደ አገራቸው ይመለሱ ነበር። ኢትዮጵያ ከምእራቡ ዓለም ጋር ሲነጻጸርም ደካማ የኢኮኖሚ ደረጃና የማኅበራዊ ግልጋሎትም አልነበራትም። የምእራቡ ዓለም ምቾት የአገር ፍቅርንና የእናት ቤት ሽሮን የሚያስንቅ አልነበረም። አንድ ሰው ከተማረ ተከብሮ አገሩ ያገለግላል። ማኅበረሰቡም ይኮራበት ነበር። ይኹንና በመጨረሻው ያለንን ኹሉ አፍርሰን እንደ ቻይናና ሦቪዬት ኅብረት ሦሻሊዝምን፣ የስታሊንን የብሔር ብሔረሰቦች ፓለቲካ ብንተክል የተሻለ እንኾናለን ተባለ። ያም ኢትዮጵያን ወደ ምድራዊ ሲዖል ቀየረ። ስደት እንደ ጌጥና ልዩ እድል ተቆጠረ። አዛውንቶችንና አርበኞችን በጅምላ መረሸን፣ ወጣቱን በቀይ ሽብር መጨረስ እድል ፈንታችን ኾነ። በዚያም ሳይበቃ ቀጥሎ የመጣው ደግሞ መጤ፣ ነፍጠኛ፣ ኦርቶዶክስ፣ ሴማቲክስ እያለ ምድሪቷን በደም አጠባት። ምንም የማያውቁ ሕጻናት ለሰቆቃ የሚዳረጉበት፣ እርጉዝ እናት በአሰቃቂ የምትገደልበት ዘመን መጣ፣ አለ፣ ደርሰን ካላስቆመነው ይቀጥላል። ይኽን ግፍና አድሏዊነት ፈርቶ የሚሸሸው ከመጥበሻው ወደ እሳቱ፣ ጅብ ፈርቸ ዛፍ ብወጣ ነብር ቆዬኝ እየኾነ መጣ። እስከአኹን በወጣ ይፋዊ መረጃ በዚኽ ሣምንት ብቻ ከ7 በላይ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን Xenophobia(መጤ ጥላቻ) በተሰኘ ዘመናዊ አፓርታይድ አስተሳሰብ ወንድሞቻችን በአሰቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል። ትናንት ለአፍሪካውያን ከባርነትና ና ነጻነት በተለይ ለደቡብ አፍሪካውያን የበዛ ግፍ አገዛዝ ለማላቀቅ እነኔልሰን ማንዴላን ዜግነት ሰጥታ፣ ወታደራዊ ስልጠና፣ ስንቅና ትጥቅ ቋጥራ ለነጻነት ጎሕ የቀደደች አገር ዜጎች ለውለታቸው መታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸው በድባብና ቀይ ምንጣፍ መሄድ ሲገባቸው በጉልበታቸው ጥረው ግረው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያን መሳደድና መገደል እጅጉን አስቆጥቶናል፤ ለፀፀት ዳርጎናል። ትብብራችን በግፍና በደቦ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ልባዊ ሐዘኑን ይገልጻል። በሌላ በኩል በሳውዲ አረቢያ ምድር በአገሬው ሕግ(ሸሪዓ) መሠረት ከ 60 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ እንዳለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ካወጡት ሪፖርት መረዳት ችለናል። ይኽም እንደዜጋና የሕዝብ ሕመም እንደሚሰማው ፓርቲ ልባችን ክፉኛ ተነክቷል። በእርግጥ ይሄ ስደተኞችን ምክንያት እየፈለጉ ማጥቃት በዓለም ላይ እየጨመረ የመጣ አባዜ አካል ነው ብለን እናስባለን። ኢትዮጵያና ሳውድ አረቢያ ከንግድና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዘለለ የቀደመ የሚባል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት በሃይማኖት፣ በምግባር አገሩን ያቀኑበት ትስስሩን ያጎለበቱበት ይልቁኑም ኢትዮጵያ የነቢዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ተከታዮች የኾኑ ካዕባዎችን በአገራቸው በዕምነታቸው ምክንያት ተሳደው ሲመጡ ለዘር አትርፎ ያቆዬ ሕዝብና አገር ነው። በዚኽም ኢትዮጵያ እስልምናን ከመጥፋት የታደገች ግምጃ ቤት ናት ቢባል ማጋነን አይኾንም። የዚኹ ውለታዋና ክብሯ እንደተጠበቀ ኾኖ የትኛውም ሰው በየትም ቦታ በወንጀል ከተገኘ በፍትሕ አደባባይ መቅረቡን በጽኑ የምናምነውና የምንከራከርለት መርሕ ቢኾንም እነዚኽ ኢትዮጵያውያን ላይ የመጨረሻው የጭካኔ ፍርድ መፈጸሙን በጽኑ እንቃወማለን። ነገሩ በቅርብ ጊዜያት ወዲኽ እያቆጠቀጠ የመጣውን ስደተኛ ጠልነት ጋር የተገናኘ እንጂ በወንጀል  እንዳልኾነ ጥርጣሬው አለን። ይኽም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንደምንቆጥረው የሳውዲ መንግሥትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቅልን እንሻለን። ስለኾነም፣ 1. የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በኢትዮጵያውያንና በመላው አፍሪካውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የግፍ ግድያና ማሳደድ እንዲያስቆም ለሞቱትም አግባብ ያለውን ማቋቋሚያና ካሳ እንዲሰጥ አፍሪካ ሕብረትና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። 2. የኢትዮጵያ መንግሥት በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደውን የግፍ ግድያ ማስቆም የድፕሎማሲ ሥራው ኹሉ ቊንጮ መኾኑን መረዳት አለበት ብለን እናምናለን። ውቂያኖስ አቋርጦ ስለሌሎች አገር ዜጎች መገደል ጥብቅና ሲቆም ያየነው የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ይሄንን በጉያው የሚፈጸም የግፍ ግድያ ማስቆም ካልቻለ በአፍሪካ ኅብረት ያለውን ተሳትፎ ጭምር እንዲጤን ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር በመኾን ግፊት እንዲደረግ ጥሪ እናቀርባለን። 3. ኢትዮጵያ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነትና የኢትዮጵያን ውለታ በማውሳት መንግሥት በመታረጃው ቄራ ቆመው የሞት አፋፍ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን እንዲታደግና ጣልቃ ገብቶ የሞት ፍርዱ ወደ እሥራት እንዲቀየር ብሎም በአገራቸው እንዲዳኙ አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ኹሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን። 4. መንግሥት የችግሩ መነሻ የኾነውን፣ በአገር ውስጥ መኖር የማያስችሉና ለስደት የሚዳርጉ አገራዊ ቀውሶችን እንዲያስቆም እናሳስባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

የምኒልክ ዕዝ አርበኞች አጥቢያ ለሊቱን በአልብኮ ወረዳ ነጋሽ ታዳጊ ከተማ ውስጥ በፈፀሙት መብረቃዊ ኦፕሬሽን 23 የጠላት ወታደሮችን በመደምሰስ ድል ተቀዳጁ! በአፋብን ወሎ ቤተ ዐምሓራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ104ኛ ኮር  አብሪ ቡድንና በኮሩ ስር 25ኛ ክ/ጦር ከ1ኛ ሬጅመንት የተውጣጡ የፋኖ አሃዶች በጋራ በመሆን ትናንት ሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም ለዛሬ ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም አጥቢ ለሊቱን በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ነጋሽ ታዳጊ ከተማ ውስጥ በወሰዱት የተጠና መብረቃዊ እርምጃ የጠላት አከርካሪን ሰብረው ድል አስመዝግበዋል። እርምጃው የተወሰደው ከጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝ ጋር በመወገን በገዛ ሕዝባቸው ላይ እልቂት ሲፈፅሙ የነበሩ የሚኒሻና ፖሊስ ኃይሎች ካምፕ ላይ ሲሆን፡ በዚህም ስምንቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ፡ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በፅኑ ቆስለው በሞትና በሕይወት መካከል እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል። በተጋድሎው ሦስት የሚኒሻ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው እጅ ከፈንጅ ሲማረኩ፡ አራት ክላሽንኮቭ መሣሪያና አንድ አብራራው ጠብመንጃ በወገን ኃይል ቁጥጥር ስር ውሏል። ፀረ አማራውና ሀገር አፍራሹ የብልፅግና አገዛዝ እድሜውን ለማራዘምና ተጨማሪ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ በምርጫ ስም ለማጭበርበር ያዘጋጀው የምርጫ ካርድና የምርጫ ማስፈፀሚያ ቁሣቁስ በአርበኞቹ እንዲወድም ተደርጓል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ ዐምሓራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 27/2018 ዓ/ም

ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን ፋሽስታዊ አገዛዝ ከአምስት ዓመታት ተጋድሎ በኋላ በተመሳሳይ ቀን ተሸንፎ የወጣበት ዕለት በመሆኑ በሀገራችን የነፃነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ዕለት ነው። ይህ እለት ፋሽዝም የተሸነፈበት ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ቀን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ ቀንም ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ ይላል። የብልፅግና አገዛዝ የሀገሩን የፖሊሲ ሉዓላዊነት ከማከራዬት አልፎ አዬር ኃይሉን እና መሰል ተቋማትን ለውጭ ኃይሎች መፈንጫ በማድረግ በአርበኞች መስዋዕትነት የተገኘውን የሀገር ነፃነት ለርካሽ ስልጣን ሲል አሳልፎ በመስጠቱ ሀገራችን ያልተነገረ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። የብልፅግና አረመኔ አገዛዝ በአምስቱ የአርበኝነት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈፀመው ግብ በብዙ እጥፍ የራቁ የዘር ማጥፋት እና ሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ነው። የአባቶቹን ታሪክ የወረሰው ሰራዊታችን የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ከዘመኑ ጥቁር ፋሽስቶች ጋር በመተናነቅ ላይ ይገኛል። ዘር አጥፊዉን አገዛዝ ታግለን በማሸነፍ የተነጠቅነዉን ሀገር ማስመለስ ግባችን እንደመሆኑ መጠን ንቅናቄው አሁን ላይ እያደረገ ያለው ትግል የቀድሞ አርበኞች ካደረጉት የነፃነት ተጋድሎ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። ፅናትን፣ አይበገሬነትን፣ ቁርጠኝነትን በሚጠይቀው ተጋድሎ ውስጥ በመስዋዕትነት ድል እያስመዘገበ ያለው ሰራዊታችን በአማራ ህዝብ ጠላቶች ላይ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን። የባርነት ቀንበር የተሰበረበት የአርበኞችን ቀን ስናከብር የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለማስወገድ የሚከፈለዉን ማንኛዉንም መስዋዕትነት በመክፈል ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ቃል በመግባትም ጭምር ነው።

የችሎት ውሎ በእነ ዶክተር ወንደሰን  አሰፋ መዝገብ የተከሰሱት የአማራ የፖለቲከኛ እና  የሕሊና እስረኞች በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎች መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት መጋቢት 2015 ዓ/ም በመንግስት ኃይሎች ከየቤታቸው ታፍነው ከቆዩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ቢመሰረትባቸውም በአቃቤ ሕግ የቀረቡት 66 ምስክሮች ተከሳሾችን አናውቃቸውም ብለው ቢመሰክሩም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ የፀረ-ሽብር ችሎት በፋኖ እና በመንግስት ሀይሎች መካከል በሚደረገው ጦርነት ላይ በቀጥታ ተሳትፋችኋል በማለት እና የፀረ ሽብር አዋጁን አንቀፅ 3 (2) በመጥቀስ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ከሚያዚያ 26 እስከ. ግንቦት 30 /2018 ዓ/ም ተከላከሉ በማለት መወሰኑ ይታወሳል። ተከሳሾች ዛሬ ሚያዚያ 26/2018 ዓ/ም የመከላከያ ማስረጃ ለማቅረብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ተከሳሾች በሁለት መሰረታዊ ምክንያት በዛሬው ቀጠሮ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል። 1ኛ) ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከቤታችን ታፍነን ተይዘን በጦርነት ተሳትፈዋል በማለት ተከላከሉ ተብሎ መበየኑ በአገዛዙ ጫና የተወሰነ የፖለቲካ ውሳኔ በመሆኑ እንዲሁም ተከሳሾችን ፊት ለፊት ላለማየት በሕግ የተደነገገውን ተከሳሾች በችሎት ቀርበው ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን በመንፈግ በአካል ሳትቀርቡ በፕላዝማ ተከላከሉ በመባላቸው። 2ኛ) ተከሳሾች ተከላከሉ የተባሉበትን ጭብጥ መመልከት እንዳይችሉ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጩን ለተከሳሾች አልሰጥም በማለት የሚከላከሉበትን ፍሬ ነገር ሳይመለከቱ ይከላከሉ በማለቱ ሲሆን። ተከሳሾች በአካል ፍርድ ቤት የማንቀርብ ከሆነ የአገዛዙ ሀይሎች መከላከያ ምስክሮቻችንን ያስፈራሩብናል ፣ ተገቢውንም ጥያቄ መጠየቅ አንችልም፣ እንዲሁም መከላከል ያለብንን ፍሬ ሀሳብ ሳናውቅ መካላከል አንችልም በማለት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

በአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦርን የማብቃት፣ የማንቃት፣ የማደራጀት ስራዎች በተገቢው መንገድ ተከናውነዋል‼️ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ምክትል ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ እና የ105ኛ ኮር ምክትል ወታደራዊ አዛዥ መቶ አለቃ ገረመው አጋዥ እንዲሁም የክፍለጦሩ ወታደራዊ አመራሮች በጥምረት የ44ኛ ክፍለ ጦር ቃኝና መሃንዲስ አባለት ጋር ሰፊ የሆነ ውይይት አካሂደዋል። በተካሄደው ፍሬያማ የምክክር መድረክ በወታደራዊ አመራሩ በኩል ጦሩ ለግዳጅ ዝግጁ እንዲሆን የስነልቦና ግምባታ ከመስጠት እስከ አሁናዊ የትግሉን ደረጃ በማስመረዳት ቀጣይ እንደ ሀገርም እንደ ድርጅትም ለሚከናወኑ ወታደራዊ ግዳጆች በሙሉ ሰራዊቱ ብቁና ንቁ ሁኖ እንዲጠባጠቅ ትዕዛዝ ሰጠዋል። የ44ኛ ክፍለ ጦር ቃኝና መሃንዲስ አባላትም በተሰጣቸው ግምባታ በመደሰት የነበረዉን ገናና ስም ለመመለስ እንዲሁም ከሰሞኑ የሰሩትን ጀብድ በላቀ ሁኔታ ለመፈፀም ፍፁም ዝግጁ ሁነዉ #ትዕዛዝን_ብቻ እንደሚጠብቁ ሀሳባቸውን ሰጠዋል። ከዚህ በተያያዘ የ44ኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች በየ ሻለቃዎች የስራ ስምሪት በመዉጣት ላቅ ያለ ስራ እየሰሩ የነበሩ ጉድለቶችን እየሞሉ፣ ጦሩን በተገቢው መንገድ በማነቃቃት ለመጭዉ ወታደራዊ ግዳጅ ብቁ እንዲሆኑ ከምንግዜውም በላይ ታላቅ ስራ ተሰርቷል። አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት 26/ዐ8/2018 ዓ.ም

ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎች ይድረስ!!! የወረዳ ምርጫ አስተባባሪዎች ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1/2018 ዓ/ም በባህር ዳር ከተማ የምርጫ ስልጠና በድብቅ የሚወስዱ ናቸው።  ከ26 ቀን ጀምሮ ጥብቅ ፍተሻ አርገን ተገቢ አቀባበል እንድናደርግላቸው በማለት መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡              ከደጀን 1)  አበባው ልንገረው 2)  ይበልጣል ባዩልኝ 3)  አሞኘሽ ደቤ               ከቢቸና 1 ማርቆስ(0921328563) የምታውቋቸው ጓደኞቹ            ከደብረ ማርቆስ 1 አንሙት ጌትነትና እናንተ ጋ የያዛችኋቸው ጓዶቹ               ከድጓ ጽዮን 1)  ጥላነህ ነበረ አዲስ 2)  ልንገር እንዳሌ ደስታ 3)  ቦሰና እውነቱ እንዳለ               ከደብረ ወርቅ 1)  ለወየሁ ተመስገን ሞሴ 2)  አዲሱ ይሁኔ በላይ 3)  የሽ ጫኔ ከቤ 4) አዝመራ ጠበቃው ዳኛው            ከአምበር 1) ማስተዋል ታረቀኝ ይርሴ 2) ሁልጊዜ ታደለ 3) ስነወርቅ ታደለ ሁለቱ አግለዋል ማስተዋል ግን 2 አዲስ አስገብታ ለብልግና የምታሽቃብጥ አምበር ስራዋ ሉማሜ ማደሪያዋ(0949961004)                   ከየእድ ውኃ 1) ዮሴፍ ንጉሴ ማፈሪያ የሌለው ሆዳም ምን እንደምታረግ እናውቃለን 2) ሙሉጌታ መንግስት 3) እየሩስ እራሷን ያገለለች         ከየጁቤ 1) ከዳርዳር አሳምረህ 2) አይመር ማናየ 3) ልጃለም ጤናው 4) ይደግ አንተነህ              ከዱርቤቴ 1) ሀብታሙ አቸንፍ 2) እሱባለው አምሳሉ 3) ላቀ አይገኝ 4) መጣአለም ጌታነህ              ከቡሬ 1) አንዷለም ታረቀኝ 2) መንግስት ጌታነህ 3) ንጹህ ሰለሞን 4) ማስተዋል በሪሁን 5) ኢዛና በላቸው አለባቸው 1) ዮናስ ሞገስ 2) ዘውዴ ብሻህ 3) ይልማ አበበ                ከቁይ 1) ጽላት አበረ ፈጠነ 2) አለምነህ ፈጠነ መርሴ 3) መሰረት አለማየሁ 4) ነብዩ ላመነው እምሬ              ከግንደወይን 1) መኮነን አወቀ 2) እሱባለው ጸጋ 3) መቅደስ አየሁ 4) ጥሩዓለንም መንግስት           ከመርጦለማርያም 1) ሰለሞን ወርቅየ አስጨንቅ 2) እንደግ አግድ በዛብህ 3) አወቀ አባተ ይላቅ 4) ደመቀ ሙሉዓለም ተዋበ            ከጎዛምን 1) ዳንኤል ማኔ 2) ማናየ አለኸኝ 3) ቴወድሮስ አያሌው              ከሉማሜ 1) አዲሱ ዘሩ 2) እንቻለው አያሌው 3) ሳንበል              ከዳንግላ 1) ቴወድሮስ መኮነን 2) ታደለ ዳኛው            ከፍኖተ ሰላም 1 መለሰ ጌታነህና እናንተ የምታቋቸው ጓዶቹ               ከአማኑኤል 1 ጽዮን ዳምጤና የምታውቋቸው ጓደኞቿ               ከሞጣ 1) ተመስገን ፈለቀ 2) ታደገ ወንዴ 3) ላመስግን               ከአዲስ ቅዳምን 1) ስሜነህ እንግዳ 2) መኳንንት በላይነህ              ከረቡ ገብያ 1) ቢንያም እንቻለው ወንዳለ 2) ዝጋለ መንግስት አበበ 3) ውዴ እናውጋው በላይ                  ከባ/ዳር ሞላልኝ ደሳለው                  ከወረባቦ 1) መሀመድ ሙሳ ይመር 2) እንዳለው አበበ አላምረው 3) ሰይድ ኢብራሒም መሃመድ               ከድል ይብዛ 1) አማረ ባየ 2) ዘመናይ መንግስቴ 3) ጀጃው ገ/ማርያም 4) ቢምረው በየነ                  ከደብረ ሲና 1 1) አበበ ዳምጠው 2) ሙሃመድ መንግስቱ 3) አሊ ምትኩ               ከጃማ ደጎሎ 1) አቡሽ ፍስሃ 2) አብራክ ዘውዱ 3) ሳቦም ደመቀ ኃይሉ            ከጎንደር ዙሪያ 1) ጌታቸው ሙጨየ አቡሃይ 2) መንበሩ ሙሉ 3) ሙሉቀን ከሳው                 ከድብረ ብርሃን 1 ስመኘው አታላይና እናንተ የያዛችኋቸው ጓደኞቹ             ከመተማ 1 መሰረት ዋሲሁን መንግስቴና የምታውቋቸው ጓደኞቿ              ከኩታበር 1 ይመር አህመድና የያዛችኋቸው ጓደኞቹ               ከላይ አርማጭሆ 1 ሃጎስ ደነቀውና እናንተ የምታውቋቸው ጓደኞቹ                  ከደላንታ 1) አብርሃም ዓለሙ 2) ጌጥየ አበባው መልካም 3) ጌትነት አዳነ አዱኛ 4) ብርሃን ታርቀኝ                ከጎንደር ዙርያ 1) ታድሎ ሹመት አየለና የምታውቋቸው ጓደኞቹ                  ከዓለም ከተማ 1) አግዘው ካሳና የያዛችኋቸው ጓደኞቹ                 ከደንቢያ 1) ናትናኤል ስመኘውና እናንተ የምታውቁቸው ጓደኞቹ                ከወግራ 1 1) ፋሲል ዓለሙና የምታውቋቸው ጓዶቹ                 ከቃሉ 1 1) ቃልኪዳን ሰለሞን 2) ስመኘው አያሌው 3) አመለወርቅ የውድ 4) ሰለሞን በፍቃድ                ከቃሉ 2 1) ሁሴን ሞሃመድ 2) ብርሃኑ አውራሪስ 3) ጀማል አብዱ 4) ሙስጦፋ ኢብራሒም                ከጎንደር 04 1) መንበሩ ሙሉዓለም 2) ጌታቸው ሙጨየ                 ከመቅደላ 1) ዑስማን ሹምየ 2) አማኑኤል ዓለሙ 3) ዳንኤል ብርሃኑ 4) ሙራድ ፈጠነ ይቀጥላል...................!

ተስፋ ሲደረግ መከራ፤ ይሻሻላል ሲባል መዓት! በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ህዝቡ የለውጥ ያለህ እያለ ቢጮህም፣ በምላሹ ያገኘው ግን የባሰበትን መከራ ነው። ዛሬ የነዳጅ ዋጋ በሊትር 25 ብር ሲጨምር፣ ይህ ዝምተኛ ህዝብ ላይ የተጫነ ሌላው የሞት ፍርድ ነው። ዝምታው እስከመቼ? ኑሮ በካስማው ላይ ቆሞ፣ የቤት ኪራይና የሸቀጥ ዋጋ ጣራ ነክቶ፣ አሁን ደግሞ ነዳጅ የህዝቡን ጉሮሮ እንደተለመደው ሊዘጋ መጥቷል። ይሄ ተኝቶ የሚገረፍ ህዝብ ካልነቃ፣ ከዚህ የከፋ መዓት ገና ይወርድበታል። ዛሬ ካልተቆጣህ፣ ነገ መቆጫው ጊዜ ያልፋል። ‘ብልፅግና’ የተባለው ተስፋ፣ ዛሬ የውድመትና የጭቆና ተምሳሌት ሆኗል። ህዝብን እያደኸዩ መክበር አብቅቷል። ይሄ የመጨረሻው የስርዓቱ መቃብር መቆፈሪያ እንጂ ሌላ አይደለም። ህዝባዊ ቁጣው ሲገነፍል፣ ብልፅግና እንደ ጉም መበተኑ የማይቀር ነው። መዓቱ ሳይጠናቀቅ፣ ህዝብ ሆይ ንቃ!

#ከሣሲት_ክላስተር_ወጣቶችና_የሀይማኖት_አባቶች_ጋር_የተደረጉ_ሁለት_ህዝባዊ_መድረኮች✅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የስራ መመሪያ መሰረት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች የህዝብ መድረኮች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረገ ይገኛል። ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም አፋብን ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠራቸው በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በአማራ የህልውና ጉዳይ ላይ ያተኮረ ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶችን ያሳተፈ ሁለት መድረክ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሞጃና ወደራ ወረዳ በሣሲት ክላስተር ተካሒዷል። ዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2018ዓ.ም በተካሔደው መድረክ የሣሲት ክላስተር ነዋሪ ከሆኑት ወጣቶችና የሀይማኖት አባቾች ጋር ውጤታማ መድረክ መካሔዱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር በግንባር መረጃው ገልጿል። የአፋበን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣የህግና ፍትህ አመራሮች፣ በዕዙ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር ያሉ የ3 ክፍለ ጦር አመራሮች፣የራንቦ ክፍለጦር ፣የ7ለ70 ክፍለጦር፣ የንጉስ ሳህስ ሥላሴ ክፍለጦር አመራሮች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል። ለውይይት በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ወቅታዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች መድረኩን በመሩት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የፖለቲካ መምሪያ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ስር ባሉ የተጉለት አውራጃ በግፍት ክላስተር ታላቅ ህዝባዊ መድረክ ተካሄደ። በተደራጀ የፖለቲካ ሥራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ህልዉናውም ይረጋገጣል።በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ህዝባዊ መድረክ ወቅታዊ የትግሉን ጉዳዮችን የአካተተ በሳል የመድረክ ዉይይት ተደርጓል። ከዕዝ አመራር ጀምሮ፣የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች በመገኘት ህዝባዊ መድረኩን በመምራት ተሣትፈዋል ከአፋብን የወረደውን የድርጅቱን ሰነድ በማብራራት እና ዉይይቱን በመምራት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እና ግዴታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል። የዉይይቱ ተሣታፊ አርሶ አደሮች በርካታ ሀሳቦችን በመድረኩ ላይ አንስተዋል።ከተነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል ጥቂቶቹ፦ 1. የብልፅግናን የምርጫ ቀልድ የአማራው አርሶ አደር በፍፁም የማይቀበሉት መሆኑን ከህዝቡ አንደበት የተረጋገጠበት የመድረክ ዉይይት መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለበት ሆኗል። 2. ጨፍጫፊው እና አረመኔው አገዛዝ ሆን ብሎ ህዝቡ በኑሮ ውድነት እና በትራንስፖርት ችግር ምክነያት መኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማድረግ እያሰቃየን ይገኛል።ስለዚህ ትግሉን ተባብረን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በድል ማጠናቀቅ የሁላችንም ግዴታችን መሆን አለበት። 3. የአማራ ፋኖ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ድርጅታዊ አንድነቱን እና እርስ በርሱ በመወያየትና በመተማመን የተያዘውን ትግል በአጭር ጊዜ መቋጨትና ማጠናቀቅ አለበት በማለትም አክለው ገልፀዋል። 4. እኛ የአማራ አርሶ አደሮችን ብልፅግና በተለያዩ የጥቅማጥቅም ወጥመዶች ሊያጠምደን እና ሊያታልለን አይችልም።ምክነያቱም የአማራን አርሶ አደር በከባድ መሣሪያ ሀብት ንብረቱን እያወደመ ምረጡኝ ማለት የአገዛዙን ሽንፈቱን ያመለክታል።በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነትን አውጆብን እየፈጀን የይስሙላ ምርጫን አንቀበልም ሲሉም ሀሳባቸውን በመድረኩ ላይ አንፀባርቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዚያ 25 ቀን 2018ዓ/ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተጉለት አውራጃ በግፍት ክላስተር በተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ መደረክ ላይ በሣል እና ዉጤታማ የመድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከመድረኩ ተሣታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ የተለያዩ ጥያቄዎች መድረኩን ከሚመሩት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ግልፅ የሆነ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት የመድረኩ ውይይት ተጠናቋል። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሚያዚያ26/2018 ዓ/ም