en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Open in Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Show more
4 039
Subscribers
+6824 hours
+3957 days
+1 39230 days
Posts Archive
ከሱዳኑ የፈጥኖ ደራሽ ታሪክ የምንማረው የትኛውም የነፃ አውጭ ድርጅት በሂደት ድሮንን እንደ ክላሽ የሚታጠቅ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ በሁለት መልኩ እውን ሊሆን ይችላል፣ በአንድ በኩል ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ድሮን የሚያስታጥቁ አገሮች ይኖራሉ- ልክ ኤምሬትስ ብልፅግናን እና የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ እንደምታስታጥቀው ማለት ነው። በሌላ በኩል ድሮን አምራች አገሮች እየተበራከቱ ሲመጡ  የድሮንን ዋጋ በመቀነስ፣ የተለያዩ ቡድኖች በርካሽ ዋጋ እንዲይዟቸው ያመቻቻሉ። የዘመኑ ጦርነት በቀደመው መንገድ የሚሄድ አይደለም፤ ታንክና መድፍ እያንጋጉ፣ የሚፎከርበትም አይደለም። 100 የጦር አውሮፕላን አለኝ እያሉ የሚተረተሩበትም አይደለም። (በነገራችን ላይ የአንድን አገር ወታደራዊ ሚስጢር በአደባባይ መናገር በሌሎች አገሮች በአገር ክዳት የሚያስቀጣ ነው። የትኛውም ትክክለኛና የሚያመዛዝን አዕምሮ ያለው ሰው፣ አገሩ ስለታጠቀቻቸው የጦር መሳሪያዎች አይነትና ብዛት አይናገርም- ወታደራዊ ሚስጢር ነው።) ስመለስ:- የአብይ የፉከራው ምንጭ ሰራዊቱ ወይም ደጀኑ ህዝብ ሳይሆን ድሮን ነው። እንዳልኩት ድሮን በታጠቁ ኀይሎች እጅ ሲገባ፣ ከዚያ በኃላ የሚፎከርበት ነገር ይጠፋል። ከዚያ ይልቅ የተሻለው የሚያመዛዝኑና ነገን የሚያዩ ሰዎችን ምክር ሰምቶ እውነተኛ መፍትሄ መፈለግ ነበር። አብይ ልቡም አዕምሮውም ተደፍኗል። እርሱ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ እረፍት የምታገኝ አይመስለኝም። አንዳንድ መሪዎች የጦርነት ማግኔት ናቸው፣ ጦርነትን ሳይወዱም ሆነ ወደው ይስባሉ።

ከሱዳኑ የፈጥኖ ደራሽ ታሪክ የምንማረው የትኛውም የነፃ አውጭ ድርጅት በሂደት ድሮንን እንደ ክላሽ የሚታጠቅ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ በሁለት መልኩ እውን ሊሆን ይችላል፣ በአንድ በኩል ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ድሮን የሚያስታጥቁ አገሮች ይኖራሉ- ልክ ኤምሬትስ ብልፅግናን እና የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ እንደምታስታጥቀው ማለት ነው። በሌላ በኩል ድሮን አምራች አገሮች እየተበራከቱ ሲመጡ  የድሮንን ዋጋ በመቀነስ፣ የተለያዩ ቡድኖች በርካሽ ዋጋ እንዲይዟቸው ያመቻቻሉ። የዘመኑ ጦርነት በቀደመው መንገድ የሚሄድ አይደለም፤ ታንክና መድፍ እያንጋጉ፣ የሚፎከርበትም አይደለም። 100 የጦር አውሮፕላን አለኝ እያሉ የሚተረተሩበትም አይደለም። (በነገራችን ላይ የአንድን አገር ወታደራዊ ሚስጢር በአደባባይ መናገር በሌሎች አገሮች በአገር ክዳት የሚያስቀጣ ነው። የትኛውም ትክክለኛና የሚያመዛዝን አዕምሮ ያለው ሰው፣ አገሩ ስለታጠቀቻቸው የጦር መሳሪያዎች አይነትና ብዛት አይናገርም- ወታደራዊ ሚስጢር ነው።) ስመለስ:- የአብይ የፉከራው ምንጭ ሰራዊቱ ወይም ደጀኑ ህዝብ ሳይሆን ድሮን ነው። እንዳልኩት ድሮን በታጠቁ ኀይሎች እጅ ሲገባ፣ ከዚያ በኃላ የሚፎከርበት ነገር ይጠፋል። ከዚያ ይልቅ የተሻለው የሚያመዛዝኑና ነገን የሚያዩ ሰዎችን ምክር ሰምቶ እውነተኛ መፍትሄ መፈለግ ነበር። አብይ ልቡም አዕምሮውም ተደፍኗል። እርሱ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ኢትዮጵያ እረፍት የምታገኝ አይመስለኝም። አንዳንድ መሪዎች የጦርነት ማግኔት ናቸው፣ ጦርነትን ሳይወዱም ሆነ ወደው ይስባሉ።

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠለት ላይ የተሳካ ደፈጣ ሰራ! ==================================== 22ኛ ክፍለጦር ወጥ የሆነ የስራ ግምገማ ካደረገ ማግስት እጅን በአፍ እሚያስጭን ጥቃት በጠላት ላይ እየፈፀመ ይገኛል። በትናንትናው እለት የጠዋት ጀንበሩ ልትጠልቅበት አስራ አንደኛው ሰዓት ላይ በጣረሞት ፍርግጫ ላይ የሚገኘው ብልፅግና በሰቀለጥ ቀበሌ ገበያ ላይ ህገወጥ የጤና መድህን በግዴታ ትከፍላላችሁ እያለ ሲያንገላታ መዋሉን መዘገባችን ይታወቃል። እናም ትናንት ከማህበረሰቡ ኪስና መቀነት በአስገዳጅ ሁኔታ የሰበሰበውንና የዘረፈውን ገንዘብ ዛሬ በቀን 26,05,2018 ዓ.ም ወደ ባህርዳር ጭኖ ለመግባት ብዛት ባለው ሰራዊት ታጅቦ ከሰለቀጥ ቀበሌ ተንስቶ ተንቀሳቅሶ ወንጀጣ ቀበሌን አልፎ ትኋን ተራራ ላይ ሲደርስ ከቀኑከ6:30_ 7:00 ሰዓት ድረስ ለ30 ደቂቃ የቆየ ውጊያ በማድረግ አይበገሬ የ22ኛ ክፍለጦር የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ከያዙበት የደፈጣ ቦታ እየወጡ ጠላት ላይ በመከመር የቦንብና የክላሽ የጨበጣ ውጊያ በማድረግ ጠላትን እንደ ቆሎ ሲያመርቱት፤በሁኔታው ግራ የተጋባው እና መድረሻ የጠፋው የብርሀኑ ጁላ ጦር ድንብርብሩ እየወጣ እግሬ አውጭኝ እያለ በሚፈረጥጥበት ሰሀት ከኋላ ተቆርጦ የቀረ ኃይል ደርሶ ሽፋን በመስጠት ቁስለኛና አስከሬኑን ታቅፎ ፣ቅስሙ ተሰብሮ ወደ ባህርዳር ገብቷል። አሁንም ለጠላት ክንዳችን የማይዝልና በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለጦሩ ወታደራዊ ክንፍ ገልጿል። ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት። ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ ትውልድ! አዲስ ተስፋ!

ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር የተሰጠ መግለጫ❗ " በስማችን የሚነግዱ ግለሰቦችም ይሁን ቡድኖች ለአፍታም ቢሆን ከጉዟችን አያስቆሙንም ! " **** የአማራ ፋኖ ትግል ከተጀመረ አንስቶ በርካታ ፖለቲካዊ ወታደራዊና ሌሎች ድሎችን እያስመዘገበ እንሆ 3 አመታትን በማገባደድ ላይ ይገኛል። ከወታደራዊና ፖለቲካዊ ስራዎች ጎን ለጎን አንድ አማራዊ ቤት መገንባት ድሉን ከማፋጠኑም በላይ ለመላው ጭቁን የሰው ልጆች ሁሉ ዘላቂያዊ እልባት የሚሰጥ መሆኑን በመረዳት በአንድ መሪ የሚመራ አንድ ድርጅት ከ2 ሳምንታት በፊት መስርተን ለህዝባችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቃችን ይታወቃል። በመሆኑም ይህ አንድ አማራዊ ድርጅት መመስረት የእግር እሳት የሆነባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በጎንደር ከተማ የሚኖሩ ባለሃብቶችን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር የፋይናንስ አሰባሳቢ ነን በማለት የተለያዩ የእጅ ስልክ ቁጥሮችን በመቀያየር ገንዘብ እየጠየቁ እንደሆነ ኮራችን በመረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ስለሆነም መላው የጎንደር ከተማ ህዝብ እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዊያን እንዲያውቁልን የምንፈልገው ከዚህ በፊት በኮሩ እውቅና ገንዘብ ያልጠየቅን እና ለወደፊቱም ድጋፍ የምንጠይቅ ከሆነ በይፋ በኮሩ መግለጫ አሳውቀን እንጂ በዚህ መንገድ ህዝባችንን የሚበዘብዙ ኮራችን እውቅና እንደሌለን እናሳውቃለን።ከዚህ በፊት በ5ኛ ኮር ስም የተፈፀሙ ገንዘብ ማሰባሰብ ድርጊቶች በሙሉ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮርን ፈጽሞ የማይወክሉ መሆኑን እናሳውቃለን። በኮራችን ስም የከተማውን ባለሃብቶች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመጠየቅ የብልጽግናን መ*ሰሪ ተግባር በሚያስፈጽሙ አካላት ላይ የማያዳግም እር*ምጃ የምንወስድ መሆኑን እየገለጽግን ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸ*ሙት ግለሰቦችም ይሁን ቡድኖች እነማን ናቸው የሚለውን ዝርዝር መረጃ በጥልቀት በማጣራት ለህዝባችን በቀጣይ ይፋ የምናደርግ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን። አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ጎንደር --አማራ --ኢትዮጵያ ጥር 26/2018 ዓ.ም

አባ ገብረ መድኅን የት ናቸው? ለምንስ እንዲታፈኑ ተደረገ ? አባ ገብረ መድኅን በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም እና በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ነዳያንን በማብላት በማጠጣት ፤በእግርም በመኪናም  ገዳማት ለመሳለም  የመጣውን ትንሽ ትልቅ ሳይሉ እግር አጥበው  በቅዱሳን ስም እየዘከሩ የሚያበሉ ሩሕሩሕ አባት ናቸው። ታዲያ ሰኔ 13 /2017ዓ.ም  ለአገልግሎት አዲስ አበባ በመጡበት ሰዓት የመንግሥት ኃይሎች ነን ባሉ አካላት ታፍነው ከተወሰዱበት ቀን አንስቶ እስከ አሁን ያሉበት አልታወቀም ። ወንጀል ከተገኘባቸው በአግባቡ በሕግ ይጠየቁ ከሌለባቸው በነጻ ይሰናበቱ ። እስር ቤትም  ከሆኑ እንድንጎበኛቸው ያሉበት ይነገረን። መነኩሴ አፍኖ ወስዶ መሰወር ቁጣ ያመጣል፤ እንደከተማ  መነኩሴ እንዳይመስሉህ ጸሎተኛ፣ ትሁትና የነዳያን አባት ናቸው። የመነኩሴውን ታፍኖ መጥፋት ያሳሰበው አንድ ደግ ሰው እንድንጠይቃቸው የትነው ያሉት ብሎ በመጠየቁ ምክንያት ‘ ስለ እሳቸው ለምን ትጠይቃለህ ’ ተብሎ ለሁለት ወራት ታስሮ መፈታቱን ምንጮች ገልጸውልናል፡፡ እነዚሁ ምንጮች አክለውም አባ ገብረ መድኅን በአበመኔትነት ያገለገሉበት የሰሜን ሸዋው አርበሐራ መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳደርም ሆነ አሁን እያገለገሉ የሚገኙበት መሃል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴደራል ቤ/ን አስተዳደር የመነኩሴውን መጥፋት አስመልክቶ በየደረጃው ጥያቄ በማቅረብ ፈንታ ዝምታ መምረጣቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ በዋልድባ፣ በአርበሐራ መድኃኔዓለም ገዳም አባት ፣ በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፣ በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ  እና በመሃል ሜዳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴደራል ቤ/ን እና በሌሎችም ታላላቅ ገዳማት በሰሯቸው ምግባረ ሰናያት ለብዙ ሰው ልብ ቅርብ ናቸው። አባ ገብረ መድኅንን የሚወዷቸው በሳቸው ርህራሄና ደግነትን የተጎበኙ ሁሉ አሁንም በየደረጃው ለሚገኙ የቤተክህነትና  የመንግስት ባለስልጣናት ይጠይቃሉ። አባ ገብረ መድህን የት ናቸው? ለምንስ እንዲታፈኑ ተደረገ? ©ስምዐ ተዋሕዶ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ​ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር​ ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የትግሉን ቁመና በተመለከተ ውይይት አካሄደ !!   ጥር 25/2018 ዓ.ም አፋብን ደቡብ አመራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ክ/ጦር ወቅታዊ የትግሉን ቁመና አስመልክቶ የከሰም ፪ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበት አመርቂ ውይይት ተካሂዷል ። የአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት ተነፍጎ ከአረመኔው አብይ አህመድና ምስለኔዎቹ ለመላቀቅ ትግል ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በሸዋ ምድር በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኘውን የሥርዓቱን ጡት ቆራጭ  ኮማንዶና "ጥምር ጦር" ተብሎ የሚጠራውን ቅጥረኛ ኃይል በመደበኛና በደፈጣ ውጊያዎች በማድቀቅ፤ ፀረ-አማራ የሆነውን የብልፅግና ሥርዓት ለማፍረስ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ። ​በመሆኑም በሸዋ፡ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ስር በሚገኘው የቡልጋ ቀጣና ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ እንደመገኘቱ የማይቀርውን የአማራን ነፃነት ለማረጋገጥ ወጣቱን በማሰልጠንና በማደራጀት ሰፊ የትግል እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ ።​ ሆኖም ከአንድነቱ ማግስት ጀመሮ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ​ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ​ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አንዳንድ የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የአማራን ትግል በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆች ጥረት ወደ አንድ በመሰብሰብ ፥ አንድ ወጥ አታጋይ ድርጅት መመሥረቱን ተከትሎ፤ ክፍለ ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ወቅታዊ የትግል እንቅስቃሴንና የአንድነትን አስፈላጊነት በተመለከተ ሰፊ ውይይት አካሂዷል ። በውይይቱም የጋራ አቋም በመያዝ የቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቋል ። በውይይቱም ላይ የክፍለ ጦሩና የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል ። 1. ​አርበኛ ፻ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ዋና መሪ 2. ​አርበኛ ደጉ ተስፋዬ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ 3. አርበኛ እንዳልካቸው ግርማ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ 4. አርበኛ ፶ አለቃ ጎሽመው ኃይሌ ---  የከሰም ፪ኛ ኮር ዋና ወታደራዊ አዛዥ 5.​ አርበኛ ፲ አለቃ ሙሉጌታ ፍቅሬ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፡ እንዲሁም በተጨማሪም አንድነታችን ለአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት ዋስትናችን በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የክፍለ ጦሩ አመራሮች በውይይቱ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል ። ​ድል ለአማራ ፋኖ !! ድል ለአማራ ሕዝብ !!! ጥር 25/05/2018 ዓ.ም ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ሪፖርተር አርበኛ ኃቀኛው ይታፈር

በአገዛዙ በሀይል ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ ምልምል ሰልጣኝ ወታደሮች ፋኖን ተቀላቀሉ!! =========================== ፋሽስቱ አብይ አህመድና አገዛዙ ስልጣኑን በኢትዮጵያውያን ህጻናት ደምና ጉልበት ለማቆዬት ከተለያዬ የመዝናኛ ቦታ እንዲሁም ከትምህርት ቤት አፋኖ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ያስገባቸው ምልምል ወታደሮች ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም በመክዳት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ። አገዛዙ በሀይል አግቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ካስገባቸው በኃላ ከከዳችሁ ፋኖ ያርዳችኋል፣ይቆራርጣችኋል እያለ የማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳ እንደ እንደሚነገራቸው ሰልጣኞች አክለው አስረድተዋል። ዳሩ ግን የ109ኛ ኮር ከተለያዬ የሀገሪቱ ክፍሎች ታፍነው የሚመጡ ሰልጣኞችን ልዩ እንክብካቤ በማድረግ የትራንስፖርት ወጭያቸውን በመሸፈን ከ136(አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት) በላይ ምልምል ሰልጣኞችን ወደ ትውልድ ቀያቸው በክብር በመሸኘት እና ከወላጆቻቸው ጋር በማገናኘት የወገን አለኝታ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ➡️ወደ ማሰልጠኛ ታግተው የገቡት ኢትዮጵያውያን ዕድሜያቸው ከ15-17 የዕድሜ ክልል እንደሚገኙ ምልምል ሰልጣኞች ለፋኖ አስረድተዋል። 👉በኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህጻናት ጉልበትና ደም ጸንቶ የሚኖር ስልጣን(ዙፋን) የለም!!! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 26/2018 ዓ.ም

በመተማ መስመር ታይተዋል እያሉ፡ ጎንደር ፋሲለደስ ታይተዋል እያሉ፡ ምንነው ወደ ወሎ ባልመጡብን አሉ፡ የእነ አፄዎቹ ዘር የኛ የወርቅ አምባር ፡ ምን አለ አገራችን ምንስ አለ ጎንደር፡ አባይን አቋርጠህ በድል ስትሻገር፡ የእነ አፄወቹ ዘር ሄደ ገሰገሰ ፡ ያነን የሾህ አጥር እየደመሰሰ፡ በወሎ ምድር ላይ ደሙን አፈሰሰ፡ እየተባባልን በቀን 19 /4/2018 ዓ ም እኔ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ አኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ እና ወንድሜ ታማኙ የዘመናችን ጀግና እና የልጅ አዋቂው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ፣ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባት ኮር ዋና አዛዥ ፋኖ አመኑ አለማንተ አንድ ላይ ተገናኝተን ወንድም አማችነትን እና ወንድማዊ አንድነትን ጥብቅ ትስስር በሚል መሪ ቃል ላይ ውይይት እያደረግን ባለንበት ቦታ የአማራ ህዝብ ቋሚ ጠላት የሆነው ብልፅግና ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ከቡግና ወረዳ ወደ ብርኮ የሚባል ቦታ እንቅስቃሴ ያደርገ ቢሆንም በወሎ አናብስቶች እና በጎንደር ጀግኖች ተመክቶ ሊያፍን የመጣው ታፍኖ ብርኮ በተባለ ቦታ አብዛኛው ጠላት የያዘውን ተቀብለን ላይመለስ እስከዛኛው ሽኝተነዋል፡፡ ከጧት 4፡00-10:00 ሳዓት ድርስ በወሰደው አውደ ውጊያ ጠላት የሰው ሁይሉን በጣም ያጣበት፣ በርካታ ክላሽ ፣ ብሬን እና ተተኳሹን እንዲሁም የክፍለ ጦር የሰው ሀይል አመራር ተመቶ የማርክንበት እና ቅስሙን የሰበርንበት የተቀናጀ የሁለቱ ኮሮች የቅንጅት ውጊያ ያደረግንበት ነበር፡፡ እኛ የላስታ አናብስቶች እና የጎንደር አንበሶች በወሎ ምድር ላይ ያሳየነው ተጋድሎ በወሎ ሰማይ ስር ብዙ አሳምነው በጎንደር ብዙ ቴወድሮስ እንዳለ ያሳየንበት ድንቅ የውጊያ ጥበብ በየልምዳችን ተጠቅመን ጠላትን አንገት ያስደፋንበት ውጊያ ነበር፡፡ በዚህ ውጊያ ጠላትን ያከሰርንበት እኛ ያተርፍንበት እና የተማርንበት ወንድሜ አርበኛ አመኑ እና ያሉ የሰራዊት አባላትን ከኛ ከጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጋር በጥብቅ ያስተሳሰርንበት ነው፡፡ በነበርው አውደ ውጊያ የሁለቱ ኮሮች ቅንጅታዊ ውጊያ ስመለከት አማራ አሁንም በርካታ አሳምነው እና ቴዎድሮሶች እንዳሉ እና ትግላችን አጠናቀን የህዝብ ጠላት የሆነው ብልፅግና የምንቀብርበት ሰአዓት እሩቅ እንዳልሆነ ተርድቻለው፡፡ የተማርኩት እና የተርደውት አንድነት የሁሉም አሸናፊ እንደሆነ ነው፡፡ በነበርው ውጊያ ጠላትን አከርካሪውን የመታነው በአንድ አላማ በአንድ ልብ አንድን ቋሚ ጠላት ላይ ተናበን ሰለነበር ነው፡፡ ባጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን ልንመክተው የምንችለው ፣ ስራቱንም ማሸነፍ የሚቻለው አንድ ሁነን ስንቆም ብቻ እንደሆነ ተምረንበታል። አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ !!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ተናዳፊ ተረቮች

የፋኖ ደጋፊ ነህ በሚል ሰበብ የአንድ ግለሰብ ሰብል በአገዛዙ ብልፅግና አመራሮች ተወረሰ! በአገዛዙ ብልፅግና መንግስት ጥርስ ውስጥ የገባው የአማራ ህዝብ ይገደላል፣ ይፈናቀላል፣ ሐብት ንብረቱ ይዘረፋል፤ ጌቶቹ ህጋዊ ድሃ አድርገነዋል አሉ፤ የጌቶቹ ሎሌዎች የእኛዎቹ ጥቁር አማራዎች ሁነኛ ማስፈፀሚያ ከሆኑ ውለው አድረዋል። በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የቡግና ወረዳ 01 ቀበሌ አይና እየሱስ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን የ65 ዓመት አዛውንት አቶ ይመር ገበያው የተባሉትን ግለሰብ በ2017 ለ2018 ዓ/ም የምርት ዘመን አርሰው፣አርመው፣አጭደውና ከምረው ያስቀመጡትን ከዛሬ ነገ ወቅቼና አምርቼ ቤተሰቦቼን አስተዳድራለሁ ያለትን የስንዴ ክምር ጥር:-25/2018 ዓ/ም በሌሊት በመውቃትና በማምረት 13.5 ኩንታል ስንዴ የቡግና ወረዳ ብልፅግና ካቢኔዎች ለግላቸው እንደተከፋፈሉት ታውቋል። የአዛውንቱ እህል የተወረሰው የፋኖ ደጋፊ ነህ፣ፋኖ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ሚዛን እማይደፋ ምክኒያት ሲሆን በሌሊትና በግዴታ የግለሰቦችን ከብቶችና አህያወች በማስወጣት በወረዳው ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ባለሙያዎች አስተባባሪነት፣ በብልፅግና የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪ ጌታየ ካሳውን ጨምሮ፣ ውበት ገናኑ ድርጅት ኃላፊ፣ ሻምበል አስረሴ ሞላ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ፣ ውለታው ምስጌ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ፣ ኮሎኔል ዘውዱ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊና አንዳንድ ሚሊሻዎች እንዳስተባበሩት ታውቋል። በጠራራ ፀሐይ ሐብት ንብረታቸው የተዘረፉት አቶ ይመር ገበያው የአንድ ወንድና የአራት ሴቶች ልጆች አባት የሰባት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ እርሳቸው በሦስት እግር እየሄዱ አርሰው ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩበትን እህላቸውን በግልፅ ሲቀሙና ሲዘረፉ እያየን ብልፅግና ዛሬም ነገም በእያንዳንዳችን ቤት የአይናችሁ ቀለም አላማረንም እየተባልን መዘረፋችን አይቀርም ሲሉ አንዳንድ የአይን እማኞች አስተያየታቸውን ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ  ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 26/2018 ዓ/ም

አማራነትን የምንኖረው እንጅ የምናወራው አይደለም በማለት ለሌሎች ንፁሃን አማራዎች ነፃነት የተከፈለ መስዋዕትነት!! ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳመነዉ ፅጌ ኮር አካል የሆነው በመደራጀት ላይ ያለው ራስ አንቺም ክፍለ ጦር  ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የሆነው ጓዳችን አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ጥር 25/2018 ዓ.ም በሰ/ወሎ ፍላቂትና ገረገራ ከተማ በቅርብ ርቀት አግሪት ዙሪያ በነበረዉ እልህ አስጨራሽ ዉጊያ ብዙ ባንዳዎችን እስከ ወዲያኛዉ ሸኝቶ በጀግንነት የክብር መሰዋትነትን ተቀብሏል። ጀግናው አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ከአባቱ ከወታደር ሙላቴ አማረ እና ከእናቱ ወ/ሮ ደናዬ አበበ በ1985 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 026 ቀበሌ በጎጨረቃ ተወለደ። ከልጅነቱ ጀምሮ በሀገር ፍቅር ስሜት ተከትቦ ያደገው አርበኛ ማንዴ ሙላቴ በ2013 የሰሜኑ ጦረነት በወቅቱ በቀረበው ሀገራዊ ጥሪ የመከላከያ ተቋም ውሰጥ በመግባት ከ1 ዓመት በላይ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለህዝብ ክብር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ታግሏል አታግሏል። እጅግ ሲበዛ ቆራጡ አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በመከላከያ ተቋም በቆየበት ወቅት በብሬን ተኳሺነት እና በድሽቃ ተኳሽነት የሚታወቅ ሲሆን በጀግንነቱ ፣  በስነ-ምግባሩ እና በስራ አክባሪነቱ አርዓያ እንደነበር ጓድኞቹ እና ባልደረቦቹ በቁጭት ይናገራሉ።              " ማንደፍሮ መጣ ስናይፐር ታጥቆ"         " ጠላት ራደ ልቡ ተጨንቆ " ተብሎ የተገጠመለት ጀግናው አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ከ 2015 ዓ/ም ጀምሮ በመቄት ወረዳና ዙሪያው የአማራ ፋኖን ከጓድኞቹ ጋር ሆኖ የመሰረተና ያደራጀ ሲሆን  ትግሉን ከተራ አባልነት እሰከ ተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ጓዶቹ የጣሉበትን ሁለተናዊ ኃላፊነት በቅንነት ፣ በታማኝነት ፣ በፅናት እና በጀግንነት ተወጥቷል።  ይህ ብቻም ሳይሆን የትግሉ መሰረት ከሆነው የሺምቅ ውጊ እስከ ፊት ለፊት በርካታ አውደ ውጊያዎች ልቡን የተማመነው ጀግናው አርበኛ ታግሏል አታግሏል። የቅርብ ጓድኞቹ አርበኛውን ሲገልፁት ጦረኛ ብቻ አይደለም እግጅ ሲበዛ ደፋር ልቡን የተማመነ ባህር ሰንጣቂ ፣ ወንዝ አሻጋሪ እንደነበር የዥጣና ፣ ሾደብ እና ተከዜ ወንዞች ምስክሮች ናቸው ይላሉ ።                    "ዝናቡ ቢጥል ወንዙም ቢሞላ"            "ግንድ ቢያገላብጥ ቢመስል አተላ"            "ማንዴ ያሻግራል አዝሎ በገላ" ቆራጡ አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በመቄት ወረዳና ዙሪያው  በፋኖ አደረጃጀት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በቅንነት እና ትግሉ በሚፈልገው የስነ ምግባር ደረጃ ታግሎ ያታገለ ሲሆን በኃላፊነት ደረጃ ለአብነት ለማንሳት ያህል የአንድነት ሻለቃ ሻበል አዛዠ ፣ በውባንተ አባተ ክ/ጦር በመቄት ም/ዘመቻ መምሪያ እና የራስ አንቺም ክፍለጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ስኬታማ የአመራር ሰጭነት ሚናውን በብቃት ተወጥቷል። አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በተሰማራበት አውደ ውጊያ እና የአመራር ሰጭነቱ ውጤታማ ከመሆኑም በተጨማሪ በስነ- ምግባሩ እና በአላማ ፅናቱ የተመሰከረለት የመልካም ስብዕና ባለፀጋ የነበረ ቆራጥ ፣ታታሪ፣  ከመልካም ተክለ ቁመናው ጋር የወገን ኃይል የሚሳሳለት  የጠላት ጦር ግን   አርበኛ ማንዴ ሙላቴ መጣ ሲባል የሚደነብርበት ጀግና ታጋይና አታጋይ ነበር። ራስ አንቺም ክ/ጦር  ከሌሎች አሃዶች ጋር በጋራ  ከአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ጋር በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 018 ቀበሌ አግሪት ዙሪያ በተደረገው ትንቅንቅ በርካታ የግል ወንበር ዘበኞችን ደምስሶ ጀብድ በመፈፀም ጥር 25/2018 ዓ.ም በክብር ተሰውቷል። "የጀግና ታሪክ ሁሌም ከመቃብር በላይ ነው!!" መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለጦሩ ቃል አቀባይ 50/አ መንግስቱ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምናልክ ዕዝ ላስታ ጄ/ አሳምነው ፅጌ ኮር ራስ-አንችም ክፍለ-ጦር ጥር 26/ 2018 ዓ.ም