uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Kanalga Telegram’da o‘tish

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Ko'proq ko'rsatish
4 039
Obunachilar
+22224 soatlar
+3937 kun
+1 35930 kun
Postlar arxiv
መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ከእርሳቸው አስቀድሞ ግን የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የባህር በር፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታ፣ ህወሓት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነሱት ጥያቄ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በሀገሪቱ  ያለው የሰላም እና የፀጥታ  ችግር አለመቀረፍ ነው ብለዋል። ይህንን ለመቅረፍም የምክር ቤት አባላቱ ለ3 ዓመታት ውትወታ ሲያደርግ እንደነበር ቢከርምም ምንም ዓይነት ለውጥ አለመምጣቱ እንዲሁም  መንግስት ከተለያዩ የታጠቁ አካላት ጋር ድርድር እያደረግኩ ነው ቢልም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር ይልቅ በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው? ሲሉም አክለዋል፡፡ የባህር  በር ፣ የልማት፣ ሀገራዊ ምክክር እና ምርጫን በተመለከተ መንግስት ያለሠላም እንዴት ለማሳካት አሰበ የሙሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሠንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ምላሽ ጀምረዋል፡፡ ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት
መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ጋር ከሚደራደር በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው የሚል ጥያቄ በፓርላማ ተነሳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላቱ ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት የጀመሩ ሲሆን ከእርሳቸው አስቀድሞ ግን የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል፡፡ በዋናነት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፣ የባህር በር፣ ሰላምና ጸጥታ፣ የተፈናቃዮች ሁኔታ፣ ህወሓት፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የፓርላማ አባሉ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባነሱት ጥያቄ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ከሚያባብሱ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው በሀገሪቱ  ያለው የሰላም እና የፀጥታ  ችግር አለመቀረፍ ነው ብለዋል። ይህንን ለመቅረፍም የምክር ቤት አባላቱ ለ3 ዓመታት ውትወታ ሲያደርግ እንደነበር ቢከርምም ምንም ዓይነት ለውጥ አለመምጣቱ እንዲሁም  መንግስት ከተለያዩ የታጠቁ አካላት ጋር ድርድር እያደረግኩ ነው ቢልም ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ በተጨማሪ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር ይልቅ በርካታ የጦር ሠራዊት ካላቸው ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር የማያደርገው ለምንድነው? ሲሉም አክለዋል፡፡ የባህር  በር ፣ የልማት፣ ሀገራዊ ምክክር እና ምርጫን በተመለከተ መንግስት ያለሠላም እንዴት ለማሳካት አሰበ የሙሉ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሠንዝረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ በመስጠት ምላሽ ጀምረዋል፡፡

#የመንግስት_ሽንፈት እና #የመከላከያ_ሠራዊት_የምርኮ ሁኔታ_አሳሳቢ_ደረጃ_ላይ_መድረስ‼‼‼ The defeat of the government and the captivity situation of the def
#የመንግስት_ሽንፈት እና #የመከላከያ_ሠራዊት_የምርኮ ሁኔታ_አሳሳቢ_ደረጃ_ላይ_መድረስ‼‼‼ The defeat of the government and the captivity situation of the defense forces and worrying level. የመንግስት ሀይሎች የመዋጋት አቅም የሚፈጠረው የሞራል ብቃት እና ዝግጅት እንድሁም የሰለጠነ የሰው ሀይል እና የታጠቀው መሳሪያ ወሳኝነት አለው። የብልጽግና መንግስት መከላከያ ሀይል የመዋጋት አቅምም ሆነ ብቃት አለያም የሰለጠነ የሰው ሀይሉ ተሟጦ በማለቁ በአጭር ጊዜ በመክዳት ፋኖን በመቀላቀል እና በጦርነት እጅ በመስጠት ሊበተን ይችላል የሚል የውጭ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። ለዚህም እንደቅርብ ምሳሌ የሚቀርበው #የአፍጋኒስታን_መንግስት በነሐሴ 2021 በማስወገድ ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ከሀገር እንድሸሹ ያደረጋቸው የአፍጋኒስታን ብሔራዊ የመከላከያ እና የደህንነት ኃይሎች ለታሊባን በፍጥነት እጅ በመስጠታቸው ነው። #የብልጽግና_መንግስት በአጭር ጊዜ እንደዚህ አይነት እጣ ፈንታ ሊገጥመው ይችላል የሚል ግምገማ ተወስዷል።

ሰበር የድል ዜና‼️‼️ አርበኞች ክፍለ ጦር ድርጅቱ በተመሰረተ ማግስት በጠላት ላይ መብ*ረቃዊ ጥ*ቃት አደረሰ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ከብርጌዶ
+2
ሰበር የድል ዜና‼️‼️ አርበኞች ክፍለ ጦር ድርጅቱ በተመሰረተ ማግስት በጠላት ላይ መብ*ረቃዊ ጥ*ቃት አደረሰ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በላይ ዕዝ 4ኛ ደጃዝማች ኮር አርበኞች ክፍለ ጦር ከብርጌዶች የተዉጣጣ ሃይል በቀን 25/5/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ እንባጋላይ ቀበሌ ላይ ዘር መርጦ ገዳ*ይ የብልፅግና ሰራዊት በመሸገበት ፍኖ መብረ*ቃዊ ጥ*ቃት በማድረሱ እስካሁን ባለዉ:- ✅ የሞ*ተ =ከ25 በላይ ✅ የተማረ*ከ = 14 ✅የቆ*ሰለ =5 ሲሆን ✅ 1 ብሬን ✅ ከ20 በላይ ነፍስ ወከፍ ክላሽ ልዩ ለዬ ተተኳሾች ተማር*ኳል። በጠያይሞቹ አንገት በጣ*ሽ ተኳ*ሾቹ ዉ*ጊያ እንደቀጠ ሲሆን ሙሉ መረጃዉን በየሰዓቱ እንገልፃለን። አርበኛ ባንዴራዉ ግርማይ የ4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ

ሰበር ዜና‼️ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ !   የብልፅግና መራሹ መንግስት አራት የሰራዊት አባላት ከአርሲ ዞን ቦሰት ወረዳ ቦሌ ከሚባል አከባቢ በመነሳት ሶስት ቀን የፈጀ የጫካ ጉዞ በማድረግ፤ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወራዳ በመግባት አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር የነበልባል ክ/ጦር'ን ከነ'ሙሉ ትጥቃቸው መቀላቀላቸው ተገለፀ ። ዕድሚያቸው ለአቅመ-ውትድርና ያልደረሱ በብልፅግናው አገዛዝ በግዳጅ ታፍሰው መከላከያ ሰራዊት የነበሩ፤ በአሁኑ ሰዓት የአማራ ፋኖ ወደ አንድ መምጣቱን ተከትሎ እነሱም የነበሩበትን ስርዓት በመቃወም እና ለነፃነቱ የሚታገለው ፋኖ ጋር አብረው ለመታገል እና ይህን ጦርነት-ጠማቂ መንግስት ለማስወገድ በማሰብ ከኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ቦሰት ወረዳ  ቦሌ ከሚባል አከባቢ በመነሳት ለሶስት ቀን የእግር ጉዞ በማድረግ ነበልባል ክ/ጦር'ን እንደተቀላቀሉ ታውቋል ። የአገዛዙ ሰራዊት አባላት የነበልባል ክ/ጦርን ሲቀላቀሉ፤ የተሰማቸውን ደስታ እና ምድር ላይ ያለውን ሀቅ በተለይም አገዛዙ ያስተማራቸውን የሀሰት ትርክት ሲናገሩ፤ "እኛ ዕድሚያችን ለውትድርና ሳይደርስ ነው ታፍሰን ወደ መከላከያ የተቀላቀልንው፤ በአገዛዙ ቤት ቆይታችን ስለ ፋኖ የሚነገረንና አሁን ምድር ላይ መጥተን የተመለከትንው ፍፁም ልዩነት አለው ፥ ፋኖ ጀግና የአማራ ህዝብ አለኝታ መሆኑን በተለያዩ ነገሮች አስመስክሯል ። እናንተን ስለተቀላቀልን እጅግ ደስተኞች ነን ። መንግሥት ስለ እናንተ የነገረን ሀሳት መሆኑን መጥተን ከጎናችሁ ሆነን አረጋግጠናል ። እዚህ ከመጣን ብዛት ያላቸው የቡድን መሳሪዎች፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰራዊት አባላትን ተመልክተናል ። አሁን የቀሩትን ጓዶቻችን መጥተው ወንድሞቻቸውን (ፋኖን) እንዲቀላቀሉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል ። አክለውም፤ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለሀገራችን እኛም ከዛሬ ጀምሮ ፋኖ ወንድሞቻችንን ተቀላቅለን በቆራጥነት እንታገላለን" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ሪፖርተር አርበኛ ጋዜጠኛ አበባየሁ ሰይፈ

​በታሪክ ማህደር ውስጥ ስማቸው በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ጥቂት ጀግኖች አሉ። እነዚህ ጀግኖች ሞትን እንደ ሰርግ የሚቆጥሩ፣ ስለ ህዝባቸው ክብር ሲሉ ህይወታቸውን በቆራጥነት የሰጡ የጄነራል አሳምነው ጽጌ
​በታሪክ ማህደር ውስጥ ስማቸው በወርቅ ቀለም የሚጻፍ ጥቂት ጀግኖች አሉ። እነዚህ ጀግኖች ሞትን እንደ ሰርግ የሚቆጥሩ፣ ስለ ህዝባቸው ክብር ሲሉ ህይወታቸውን በቆራጥነት የሰጡ የጄነራል አሳምነው ጽጌ የርዕዮተ-ዓለም ልጆች ናቸው። "የአሳምነው ፋኖዎች" ሲባሉ ዝም ብሎ ስም አይደለም፤ የፅናት፣ የቁርጠኝነት እና የአልበገሬነት ትርጉም እንጂ። ሁሌም ስራ ላይ" ጀግኖች እንቅልፍ የላቸውም። ለጥቁር አስፓልቱ ባዕድ አይደሉም፤ ይልቁንም አስፓልቱ በነሱ የጀግንነት እርምጃ ይርገበገባል። "ሁሌም ስራ ላይ" መሆናቸው ​የማያቋርጥ ዝግጁነት፡ ጠላት ባልጠበቀበት ሰዓትና ቦታ ተገኝተው የህዝባቸውን ደህንነት የማስጠበቅ ብቃታቸውን። ​ለዓላማ መኖር፡ የግል ምቾታቸውን ትተው፣ ቀዝቃዛውን ሌሊትና ትኩሱን ፀሐይ ተቋቁመው ለታላቁ ዓላማ መሰለፋቸውን። በወሬ ሳይሆን በሚያሳዩት ተጨባጭ ድልና ስራ ማንነታቸውን መግለፃቸው ብቻ በቂ ነው።

የፋኖ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። የማጥቃት መስመሮቹም.... ወልደያ ..ደሴ..ደብረብርሀን..አዲስ አበባ ***" ባህር ዳር ወረታ ደብረማርቆስ ደጀን አዲስ አበባ ***" ወለጋ ለቀምቴ አምቦ ቡ
የፋኖ ሰራዊት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል። የማጥቃት መስመሮቹም.... ወልደያ ..ደሴ..ደብረብርሀን..አዲስ አበባ ***" ባህር ዳር ወረታ ደብረማርቆስ ደጀን አዲስ አበባ ***" ወለጋ ለቀምቴ አምቦ ቡራዩ አዲስ አበባ * መተማ ቋራ ጭልጋ ቆላድባ ጎንደር ወረታ ባህርዳር አዲስ አ. ** በለሳ ጎህላ እብናት ጋይት ደበረታቦር ባህርዳር አዲስ አበባ **

ሰላም እንደምን አላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰብ ይህን ለሶስት ቀን መረጃዎች የአላጋራናችሁ ለግዳጅ ወጣ ብለን ስለነበር  ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን ቀጣዩን 24 ስዓት እንደተለመደው እውነታውንና ትክክለኛውን የፋኖ መርጃዎች እዚሁ ከግንባር ሁነን የምናደርሳችሁ መሆኑን ከልብ እንገልፃለን ታዲያ ከእናንተ ጆይንና ሸር በማድረሰግ መወዳጀት ብቻ ነው ውድ አማራዊያን!!

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ!! በዚህ ወቅት ወልቃይትም ሆነ ራያ፣ መተከልም ሆነ ደራ፣ ደብረዘይትም ሆነ በረራ፣ ደብረብርሃንም ሆነ ባህርዳር፣ ደሴም ሆ
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ!! በዚህ ወቅት ወልቃይትም ሆነ ራያ፣ መተከልም ሆነ ደራ፣ ደብረዘይትም ሆነ በረራ፣ ደብረብርሃንም ሆነ ባህርዳር፣ ደሴም ሆነ ጎንደር... ጥያቄዎቻችን ናቸው። የሁሉም ጥያቄዎቻችን መልስ ያለው 'አራት ኪሎ' ነው። የትናንቱ ጥገኛ ብአዴን ወልቃይትና ራያን፣ መተከልና ደራን አሳልፍ እንደሰጠው ሁሉ የዛሬው ተረኛ ተለ*ጣፊ የአማራ ብልፅግና ደብረብርሃንና ባህርዳርን፣ ደሴ እና ጎንደርን ለኦህዴድ ወረራ አሳልፎ መስጠቱን ማንም ቢሆን መዘንጋት የለበትም። እየታገልን ያለነው ትናንትም ዛሬም አሳልፎ በመስጠት አማራን ለሁለንተናዊ ህልውና አደጋ የዳረገዉን 'ጥገኛ እና ተለጣፊ ቡድን' እስከነአስተሳሰቡ ለመቅበር ነው። በአጭሩ የአማራ ህልዉና በዘላቂነት የሚረጋገጠው የባህርዳሩ ተላላኪ የክልል መንግስት ከሥሩ ሲነቀል፣ የአዲስ አበባዉ ፀረ አማራ አገዛዝ ፈፅሞ ሲወገድ፣ የአማራ ህዝብ በአዲሱ አማራዊ ድርጅት 'የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ' ተመርቶ ለስልጣን ሲበቃ ብቻ ነው። የወቅቱ ትኩረታችን 2015 ዓ.ም የጀመርነውን ጦርነት ማሸነፍ ብቻ ነው። አማራነት ይለምልም!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,2018ዓ.ም መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ከፍተኛ የመከላከያ አመራርን በሰባት ፓትሮልና ተጨማሪ መኪናዎች አጅቦ ጭንባ ደርሶ በሚመለስበት ሰሀት 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ተናዳፊ ተርቦች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ባህርዳር አፍንጫ ስር ይጎዲ ቀበሌ አቅራቢያ እሪ በከንቱ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ጠላት አገር አማን ነው ብሎ በሚመለስበት ጊዜ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ግሪሳው የብርሀኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ድንብርብሮ እየወጣ ወደ ባህርዳር ከተማ ገብቷል። ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት:: ጥር 25,2018ዓ.ም ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተሰፋ!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፀመ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ➯ በቀን 25,05,2018ዓ.ም መነሻውን ባህርዳር አድርጎ ከፍተኛ የመከላከያ አመራርን በሰባት ፓትሮልና ተጨማሪ መኪናዎች አጅቦ ጭንባ ደርሶ በሚመለስበት ሰሀት 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ተናዳፊ ተርቦች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ባህርዳር አፍንጫ ስር ይጎዲ ቀበሌ አቅራቢያ እሪ በከንቱ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ጠላት አገር አማን ነው ብሎ በሚመለስበት ጊዜ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ድንገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በጠላት ላይ ሰባዊና ቁሳዊ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን፤ግሪሳው የብርሀኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ድንብርብሮ እየወጣ ወደ ባህርዳር ከተማ ገብቷል። ፋኖ አማረ ጌታቸው ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት::   ጥር 25,2018ዓ.ም ክፋት ለማንም!በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተሰፋ! ❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር ዜና! በአፋብን የተለያዩ አሃዶች ጥምረት መቄት ወረዳ ላይ ዲሽቃ እና ብሬን ተኳሾችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ተደመሰሱ:: አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር
ሰበር ዜና! በአፋብን የተለያዩ አሃዶች ጥምረት መቄት ወረዳ ላይ ዲሽቃ እና ብሬን ተኳሾችን ጨምሮ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ተደመሰሱ:: አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር፤ጎንደር ጠ/ግ/ዕዝ ጨጭሆ ብርጌድ እንዲሁም እራስ አንችም ክፍለጦር በጋራ በመሆን በጥላት ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል! ጥር 25/2018 ዓ/ም በተደረገ የተጠና ኦፕሬሽን የፋሽስቱ ድሽቃ ተኳሽና ብሬን ተኳሾች እድሁም 39 እግረኞች ጭምር ተደምስሰዋል። ዘጠኙ ሚሊሻ 13 አድማ ብተና እድሁም 17 የመከላከያ ሰራዊት ሲሆኑ የአድማ ብተና የድሽቃ ተኳሽና የመቄት ወረዳ ሚኒሻ ብሬን ተኳሽም የተደመሰሱ ሲሆን በርካታ የብሬንና የነፍሰኮፍ ተተኳሾች በሶስቱም የአፋብን አሃዶች ተማርኳል። የጥላት ሰራዊት በበኩሉ የተለመደ የዘወትር ተግባሩን ማለትም አስከሬንና ቁስለኛውን በመኪና ጭኖ ወደ ፍላቂት ከተማ የፈረጠጠ ቢሆንም በመቄት ከተማ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ፍርሃት በፋሽስቱ ሰራዊት ላይ ነግሷል። የብአዴን የመንፈስ ልጅ የሆኑት በሰባት ሽህ ብርና በሰባ ውሸት ተደልለው የአማራን ህዝብ የሚወጉ አድማ ብተናና ሚኒሻ ከብልፅግና ስብስብ የሚከፈላቸው ገንዘብም ሆነ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ከውሻ ሞት ሊታደጋቸው ፈፅሞ ባለመቻሉ ወደማይቀረው ተሸኝተዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የደጋው መብረቅ ኮር ህ/ግ ክፍል ጥር 25/2018 ዓ.ም

አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ስርዓት  ገበያ በወጣ ህዝብ ላይ ግፍ ፈፀመ። በሰሜን ወሎ አስተዳደር  ዞን መቄት ወረዳ ፍላቂት ትላልቅ ፎቆችን እንደ ቤተ መንግስት  አስቦ የሚኖረው  የአፓርታይዱ አብይ አህመድ ስርዓት ያለ የለለ ኃይሉን አንቀሳቅሶ መቄት ወረዳ አግሪት ገበያ በወጡ ንፁሃን ላይ የጥላቻ በትሩን  አሳርፎ  ወደ መደበኛ ጉሬው ፍላቂት ፎቅ ስር ተመልሶ ተወሽቋል። መቄት ወረዳ አግሪት ገበያ ላይ ከ100 በላይ ወጣቶችን አፍሶ የተመለሰው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣እንግልትና ወከባ በማድረስ  የበቀል በትሩን አሳርፏል። የገበያ ቀንን እና እለተ ሰንበትን ጠብቆ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ጠሉ አገዛዝ ሰራዊት  ፋኖን በአውደ ውጊያ ከመፋለም ይልቅ ህዝብን  ማሸበር እና ማንገላታትን ዋነኛ የውጊያ ስልት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ  ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በአደባባይ  ያረጋገጠ ነው ሲሉ  አስተያየት ሰጭዎች ገልፀዋል። የዛሬውን  አግሪት ገበያ ወጣቶችን አፈሳ እና ለገበያ የወጣውን ንፁሃን ህዝብ ድብደባና እንግልት ያስተባበረው ጥቁር አማራ የመቄት ተወላጁ ኢንስፔክተር አየሁ በላይ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ያመለክታሉ። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የመቄት ወረዳ ጊዜያዊ ወታደራዊ ሲቪል አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አርበኛ ፋኖ መምህር በሪሁን ደምሌ መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 25/2018 ዓ/ም

ውድ የፋኖ ቤተሰቦች ይህን ድንቅ መፃፍ እንድታነቡና ላይክ ሼር እንድርጉት➺➺➺👇👇👇 አርበኛ ፣ደራሲ ፣ጋዜጠኛ ጀግናው ወንድሜ በርታ🙏 አዲስ መፅሐፍ ከትግል ሜዳ ለትግሉ ተበረክቷል ከአርበኛና ጋዜጠኛ ቃልኪዳን ግርማው የደራሲው ማንነት :- አርበኛ እና ጋዜጠኛ ቃልኪዳን ግርማው 1.በአሚኮ በባለሙያነት እና በአስተባባሪነት 6 ዓመት በድምሩ ለ12 ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ አገልግሏል። 2. ከ2016ዓ.ም ጀምሮ በነበሩ አደረጃጀቶች ታቅፎ ሲታገል የቆየ ሲሆን አሁን በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የስትራቴጂክ ክፍል አባል በመሆን ይህን ስርዓት ለማስወገድ እያታገለ እና እያታገለ ይገኛል። 👇👇👇 የመግቢያ ቃል ከደራሲው እንደዋርካ ጥላ ለአስሩ ደብር ወንድየ ሕዝብ መሰባሰቢያ የነበረው የመቶ አለቃ ጥሩነህ አባተ ጊዜ እና ትውልድ የጣሉበትን የታሪክ ቋጠሮ ተሸክሞ ሰው በሚፈለግበት ጊዜ ሁሉ ከፊት ኖሮ ሄዷል። 'ታምነህ የተሰጠኸውን አደራ እንደዐይንህ ብሌን ጠብቀው' የሚለውን አባታዊ አደራ ቆሜ ተቀብየዋለሁ። ለአገር እና ለሕዝብ ዋስትና የሚበቃ ሰው 'ታምኖ የተሰጠውን አደራ እንደውሀ ገድቦ፣ እንደጉም ሰብስቦ፣ እንደወተት አርግቶ፣ እንደጤፍ ጥሬ ደብቆ እና እንደፍትሕ በአደባባይ አሰምቶ በሚፈለግ ጊዜ መልሶ የሚሰጥ ነው' ይላል። የታመንሁበትን አደራ የትኛውም አይነት ይሁን ከነሙሉ ክብሩ መጠበቅ በትንሹ የሞከርሁት ወደፊት በሙላት የምኖረው የእደርስበት የሕይወት መሻቴ ነው። እኔ 'ኢትኖግራፊክ ጸሐፊ ነኝ' ብየ አምናለሁ። ኢትኖግራፊ ከተገላጩ ማህበረሰብ ጋር አብሮ በመኖር በታዛቢነት እና በተሳታፊነት ሕይወቱን በመቅመስ የሚጣፍጠውንም ሆነ የሚመረውን እንደወረደ የመሰነድ ጉዳይ ነው። 'የእውቀት ምንጩ ማህበረሰቡ ነው' ማለት ነው። ማህበረሰቡ የኔ ብሎ የያዘውን የጋራ እምነት፣ እውቀት፣ እውነት፣ ባሕል፣ የኑሮ ፍልስፍና እና ማንነት በገላጭ ክዋኔያዊ ድርጊት፣ በሐተታ ተፈጥሮ፣ በትውፊት፣ በተረክ እና ታሪክ መልክ እያስተላለፈ ትውልድ ይመራበታል። የ'እንዲህ አድርግ እና እንዲህ አታድርግ' የልማድ ሕግ እያወጣ ስርአት ይጠብቅበታል። ማህበረሰብ ያጸናበታል። ስለሆነም እግሬ በደረሰበት ሁሉ ያገኘሁትን በኢትኖግራፈር አይን ሳነሳ ኖሬያለሁ። ይህ የ'አማራነት ጥቁር ሰው' መጽሐፍም በኑሮ ምልከታ፣ በስራ አጋጣሚ ተሳትፎ፣ በነገር አስረጂ ቃለመጠይቅ እና ውይይት እንዲሁም በማመሳከሪያ ንባብ ድምር እይታ ተጨምቆ የቀረበ ነው። 'አማራነት ጥቁር ሰው' ከ'ታሪክ እና ትውፊት' ቀጥሎ የአያቴን አደራ ለመወጣት የተሰጠኝን ለመስጠት የሞከርሁበት ሁለተኛ ስራየ ነው። በ'ታሪክ እና ትውፊት' መጽሐፍ ሁለተኛው ምእራፍ 'የአባቶቼ እርስት' በሚለው ንዑስ ርእስ ስር እንደተቀመጠው 'የሁላችንም የሕይወት መንገድ ዳዋ እንደመጣስ ያለ ነው፡፡ ሳናስተውል ከተጓዝንበት ጎዳና ቆም ብለን ካሰብነው ታሪካችን' ነው፡፡ ከዚህ አንጻር 'አማራነት ጥቁር ሰው' ሦሥት ትውፊታዊ የታሪክ እርከኖችን የሚዳስስ ነው። እነዚህ ትውፊታዊ የታሪክ እርከኖች የጥቁር ሰው ምሳሌ፣ ጥቁር ሰው እና አማራነት የሚሉ ናቸው። የጥቁር ሰው ምሳሌዎች ብሔራዊ አርበኞች ናቸው። ለሕዝብና ለአገራቸው የሚቆጠር፣ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ሞያ የሰሩ ናቸው። ጥቁር ሰው ዓለምአቀፍ አርበኛ ነው። ስሙ ለራሱ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የሚተርፍ ነው። አማራነት ደግሞ የጥቁር ሰው ምሳሌ ነው። ከዚህ አንጻር ከአያሌ የጥቁር ሰው ምሳሌዎች መካከል አርሶ ማደር የጋረዳቸው የመቶ አለቃ ጥሩነህ አባተን፣ ሐገር ጠባቂው ቀኝ አዝማች ባብል ደስታን፣ የወንዶች ቁና በላይ ዘለቀን እና ደንቢያ ላይ የልብ ሐውልት የቆመላቸውን የደጃዝማች ማሩ አካሉን ትውፊታዊ ታሪኮች ይዟል። የጥቁር ሰው ርዕይ መነሻ፣ መድረሻ ወይም ፍኖት እና መዳረሻ የሆኑትን እውነተኛውን ጥቁር ሰው ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ደግሞ ጥቁር ሰው ከሸዋ እስከ አድዋ በሚል ታሪካዊ ሐተታ አካቷል። የጥቁር ሰው ሕልምና ትልም ማሰሪያ የሆነውን አማራነት ከውጭና ከውስጥ በሚነሳ የእይታ መነጸር በመዳሰስ በስብስቡ የመጨረሻው ምእራፍ ተቀምጧል። ውጫዊ እይታው በስልጣኔ የሩቅ ህዝብ የሆነውን አማራን ያለ ስሙ ስም ሰጥተው፣ ያለ መልኩ መልክ አበጅተው ከገናና ማንነቱ አውርደውና አዋርደው የተጠላ፣ የሚጠቃና የሚጠፋ ወይም ጠቅላላ እጣፋንታው በሌሎች የሚወሰን ተቅበዝባዥ የሆነ ህዝብ ለመፍጠር የደከሙትንና የሚደክሙትን ስሁት ሐተታና የተፈጸመ የተግባር እቅድ የሚያመላክት ነው። በአንጻሩ ውስጣዊ እይታው ባለፈ የማህበረሰብ ስሪትና መንግስታዊ ልምምድ ስርአት የገባ የነበረው የአማራ ህዝብ በራሱ የውስጥ ጉድለት ያገኘውን የወል ማንነት መፍረስ እና የሌሎች መጠቀሚያ የመሆን ተጨባጭ አውድ ከእነመፍትሄው ለመጠቆም የተሞከረበት ነው። ከዚህ አይን በታሪክ አጋጣሚ የረገጥሁትን የሕይወት ዳና በተረዳሁት ልክ በመክተብ ለመጭው ትውልድ ምስክር እና ማመሳከሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑን እየገለጽሁ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ቃልኪዳን ግርማው ገበያው ( ጋዜጠኛ)

ሰበር ዜና 4ኛ ደጃዝማች ኮር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ።   በቀን 11/05/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12 ላይ ከማእከላዊ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ ጃንሱማ ቀበሌ ሽመል በር  በተባለ ቦታ ላይ የኮሩ ልዩ ዘመቻ እና የተከዜ ክፍለ ጦር  በጥምረት በወሰዱት  እርምጃ ከፍተኛ  በጠላት ላይ ኪሳራ ደርሶበታል። የፋሽሽቱ ወንበር አስጠባቂ የሆነዉ የ92ኛ እና 78ኛ ክፍለ ጦር 2ሬጅመንት እና አንድ የሻለቃ አድማ በተን ወደ 70 የሚሆን ሰላም አስከባሪ በጥምረት ያሰማራዉን ሃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአሳረኛዉ ፋኖ ተደምስሷል በዚህም መሰረት በሽመል በር (ጎጥ)  በጠላት በኩል ከ70 በላይ ሙት ሲሆን 40 ቁስለኛዉ ታቅፎ ይገኛ ። ለጊዜዉ ስማቸዉ ያለታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ተመተዋል። በፋኖ ምት የተበሳጨዉ አገልጋዩ ሰራዊት ነኝ ባዩ በአካቢዉ ባሉ አርሶ አደሮች ላይ የተለመደዉን የበቀል እርምጃ ወስዷል ። አርሶ አደሮች አገር ሰላም ብለዉ በተቀመጡበት ቤታቸዉ በመግባት 2 አርሶ አደሮችን የገደለ ሲሆን ቤት አቃጥሏለ  እህል አቃጥሏል እንሰሳት ገሏለኝ ። የዚህ ሁሉ የበቀል እርምጃ ዋናዉ አላማ አማራን በኢኮኖሚ ማሽመድመድ የስነ ልቦና ስብራት ለመፋጠር  መሆኑን የአማራዉ ፋኖ በመረዳቱ በአማራ ህዝብ እና በፋኖ የአርበኝነት ጀብድ እቅዱ ከሽፏል ። ሰራዊታችንም በሙሉ ጤንነትና ቅፅበታዊ እርምጃ ለመዉሰድ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል    በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ አንድነት መመስረቱን ተከትሎ ጠላት እሚይዘዉ ሚጨብጠዉ አቷል  ።    €  በመስዋትነታችን ድላችን እናረጋግጣለን ባንዴራዉ ግርማይ የ4ኛ ደጃዝማች ኮር ህዝብ ግንኙነት

ፋኖ ወደ ደምበጫ ከተማ በመግባት በወሰደው እርምጃ ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተገደሉ! ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል "ሁሉም አማራ ፋኖ ነው" በሚል አራት ንፁኋንን መግደሉ ተሰምቷል። በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ስር ከ99ኛ ክ/ጦር የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ዛሬ ጥር 25/2018 ዓ/ም ወደ ደምበጫ ከተማ በመግባት፡ አገዛዙ ጥምር ኃይል እያለ የሚጠራው የሚሊሻ፣ የአድማ በተናና የመከላከያ ሰራዊት ስብስብ ላይ በወሰዱት መብረቃዊ እርምጃ፡ የጠላትን አከርካሪ በመስበር ታላቅ ድል መጎናፀፋቸውን 109ኛ ኮር በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል በላከው መረጃ ገልጿል። በአውደ ውጊያው ከ15 በላይ የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን ቁጥሩ በውል ያልታወቀ በርካታ የጠላት ኃይል ደግሞ ቁስለኛ መደረጉን ኮሩ አክሎ ገልጿል። ጥቃቱ የተፈፀመው ከአጥቢያ ለሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ በከተማዋ ዋድ የጎመዲ፣ደምበጫ ጉላ ማዶ ዩኒየን እና ሀይስኩል በተባሉ አከባቢዎች ላይ ነው። በዚህ ተጋድሎ ስምንት ክላሸንኮቭን ጨምሮ ከ8 መቶ በላይ የክላሽ ተተኳሽና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶች በ99ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል በላከው መረጃ ገልጿል። በተያያዘ ዜና! የአገዛዙ ኃይሎች በዋድ ከተማ በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በወረወሩት ቦምብ አራት ንፁኋን ሲሞቱ ሌሎች ንፁኋኖች ደግሞ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የአገዛዙ ኃይል "ሁሉም አማራ ፋኖ ነው" በሚል ነው በንፁኋኑ ላይ የዘፈቀደ ተኩስ በመክፈትና ቦምብ በመወርወር ጥቃት የፈፀመው።